cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ጋሜል Media

✍️ "ጋሜል" ማለት "እግዚአብሔር ሊመረመር የማይቻል ግሩም ድንቅ ነው።" ማለት ነው። ✍️ ✍️ "ጋሜል ብሂል ግሩም እግዚአብሔር።" ✍️ ✍️ "Gamel" means "God is wonderful beyond measure." ✍️ መዝሙረ ዳዊት (Psalm) 118÷7 Youtube - https://www.youtube.com/channel/UCHxwszkxLPFCFKAOf1WtaDw

Show more
Advertising posts
6 778Subscribers
-424 hours
-207 days
-9230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ቃሊቲዎች ስረዓት ያዙ ለሚመለከተው አድርሱልኝ ሼር ሼር ሼር "ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዷልና" (፩ኛ ቆሮ. ፭፣፯)። ፋሲካ ማለት ደስታ ማለት ነው። ደስታችን ክርስቶስ ታርዷል ማለት በመስቀል ላይ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ሰጠን ማለት ነው። ስለዚህ ንስሓ ገብተን፣ ምግባር ትሩፋት ሠርተን መቀበል ይገባናል። ፋሲካ ማለት ሌላ ትርጉሙ መሻገሪያ ማለት ነው። "ፋሲካ ብሂል ማዕዶት ብሂል" እንዲል ቅዱስ ያሬድ (መጽሐፈ ድጓ)። በኢየሱስ ክርስቶስ ከባርነት ወደ ነጻነት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከምግባረ ኃጢአት ወደ ምግባረ ጽድቅ አሸጋግሮናልና ፋሲካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ብሏል። በኦሪት ዘመን እስራኤላውያን በጉን አርደው ከግብፅ ባርነት ተላቀው ባሕረ ኤርትራን ተሻግረው ወደ ከነአን ገብተዋል። ያ በግ የክርስቶስ ምሳሌ ሆኖ ይነገራል።
Show all...
👍 9
እግዚአብሔር ወደ ሕይወታችን መጥቶ ፍሬ ሲያጣብን ነገ ያፈራሉ እመለሳለው ብሎ ምን ያክል ጊዜ ታግሶን ይሆን? ኢየሱስ በማለዳም ወደ ከተማ ሲመለስ ተራበ። በመንገድም አጠገብ በለስ አይቶ ወደ እርስዋ መጣ፤ ከቅጠልም ብቻ በቀር ምንም አላገኘባትምና፦ ለዘላለሙ ፍሬ አይገኝብሽ አላት። በለሲቱም ያንጊዜውን ደረቀች። ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው፦ በለሲቱ ያንጊዜውን እንዴት ደረቀች? ብለው ተደነቁ። ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ እምነት ቢኖራችሁ ባትጠራጠሩም፥ በበለሲቱ እንደ ሆነባት ብቻ አታደርጉም፤ ነገር ግን ይህን ተራራ እንኳ፦ ተነቅለህ ወደ ባሕር ተወርወር ብትሉት ይሆናል፤ አምናችሁም በጸሎት የምትለምኑትን ሁሉ ትቀበላላችሁ አላቸው። ማቴዎስ 21÷18 አሁንስ ምሳር (መቁረጫ) በዛፎች ሥር ተቀምጦአል እንግዲህ መልካም ፍሬ የማያደርግ (የማያፈራ) ዛፍ ሁሉ ይቈረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። ማቴዎስ 3፥10 እግዚአብሔር መልካም ፍሬን አፍርተን ከመቆረጥ ይጠብቀን! @Gamel_Media
Show all...
​​​​​​በሰሞነ ሕማማት የሚጸለዩት እና የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው? ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አድርሱ አሳውቁ! ከነገ ጀምሮ የጌታችንን ሕማም የምናስብበት ሰሞን ነው። እንደ ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን ሥርዓት በዚህ በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸው እና ለጊዜው የምንታቀባቸው ጸሎቶች አሉ። 👉 በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸው ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው? በሰሞነ ሕማማት አጥብቀን የምንጸልያቸው ጸሎቶች ውዳሴ ማርያም መዝሙረ ዳዊት ሰይፈ ሥላሴ ሰይፈ መለኮት ድርሳነ ማሕየዊ ውዳሴ አምላክ ናቸው። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ በሰሞነ ሕማማት በልጅዋ ምክንያት ብዙ እንግልት ስለደረሰባት የእሷን ምስጋና የሆነውን ውዳሴ ማርያም አናስታጉልም። ውዳሴ ማርያም ማመስገኛ መማጸኛ ስለሆነ እንጸልያለን። ምክንያቱም በዚህ በሰሞነ ሕማማት መከራ ተቀብሎ ሞቶ ሕይወቱን የሰጠንን ጌታ በሥጋ ወልዳልናለችና በውዳሴዋ እናስባታለን። የቅዱስ ዳዊት ድርሰት የሆነው ታላቁ መዝሙረ ዳዊት በትንቢት ክፍሉ ስለ ጌታችን ሕማም ፣ ስቃይ እና ሞት የሚናገርና በዳዊት ምስጋና በምድር የሰው ልጆች በሰማይ ቅዱሳን መላእክት ስለሚያመሰግኑ እንጸልየዋለን። ሰይፈ ሥላሴ ከሦስቱ አካላት እግዚአብሔር ወልድን የሚያመሰግን አምላክነቱን የሚመሰክር እና የሚያመሰጥር በመሆኑ እንጸልየዋለን። ሰይፈ መለኮት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ስለ ምስጢረ መለኮት እና ስለ ጌታችን አምላክነት ስለሚናገር እንጸልየዋለን። ድርሳነ ማሕየዊ በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ-ነጎድጓድ የዓይን እማኝነት እና የቃል ምስክርነት የተጻፈና የጌታችንን መከራ ስቃይ እንግልት እና ሞት በልዩ ሁኔታ የሚናገር በመሆኑ ልክ እንደ ውዳሴ ማርያም የየእለት/የየቀን ስላለው ብንጸልየው በዓይነ ሕሊና ቀራንዮ ወሰዶ በነፍሳችን የጌታችንን ሰማያዊ ውለታ ያስቃኘናል። በመጸለያችንም ልዩ ጸጋና ክብር የሚያሰጥ የቃል-ኪዳን ጸሎት በመሆኑ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ብንጸልየው እጅጉን እንጠቀምበታለን። ውዳሴ አምላክም የጌታችን ምስጋና በመሆኑ መጸለይ እንችላለን። 👉 በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው? በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩትን ጸሎቶች ጠቅለል አድርገን ስናያቸው ድርሳናት ገድላት እና መልክዓ መልኮች ናቸው። ይህም የሆነው በሰሞነ ሕማማት ጌታችን ለእኛ ለሰው ልጆች ብሎ የተቀበላቸውን ስቃይ እና መከራ ሞት የምናስብበት እና የምናለቅስበት እንጂ ሌሎቹን በድርሳናቸው ፣ በገድላቸው በመልካቸው የምናመሰግንበት ጊዜ ስላልሆነ ነው። በተረፈ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ለራሳችሁ እና ለሀገራችሁ ብቻ አትጸልዩ ይልቁንም ለዓለም ሕዝብ እና ለአሕዛብ በሙሉ ጸልዩ። @Gamel_Media
Show all...

3🙏 1
ወደ ፈጣሪያችን በቃል ሳይሆን በተግባር የምንመለስበት ሳምንት ይሁንልን! @Gamel_Media
Show all...
3🥰 1
“ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ።” መዝ 8፡2 ሆሳዕና በአርያም! እንኳን አደረሳችሁ! @Gamel_Media
Show all...
8👍 4
በሕማማት በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚከናወነውን ሥነ-ሥርዓት እየተከታተላችሁ ታከናውኑ ዘንድ አስቀድመን በማዘጋጀት እነሆ ብለናል። @Gamel_Media
Show all...
4👍 3
እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም። ማቴዎስ 10÷40 @Gamel_Media
Show all...
👍 7
በጣም ብዙ መንፈሳዊ ቻናሎች ውስጥ አባል ነኝ እናም መሬት ላይ ካለችው ቤተ ክርስቲያን ሌላ አንድ የክርስቲያን ማኅበር አለ። የኢንተርኔት ክርስትና ይባላል አንዱ ስለ አንዱ ውሸት እና ስህተት Video የሚሰራበት እና የሚከራከርበት እውቀት ተኮር የሆነ ክርስትና ግን ወንድሜ ስለ ሌላው ውሸት Video ስለመስራት ስለምን ታስባለክ? መጀመርያ ስለራስክ ውሸት ለምን  Video አትሰራም? እስቲ አስተውል እነዚህን የራስክ ሕይወት ላይ ሰርተካል? ካልሰራካቸው አንተም ውሸታም ነክና መጀመርያ Video ራስክ ላይ ስራ። 🥰🥰🥰 ንስሃ ገብተካል? [ይህንን ካላደረግክ ውሸታም በመሆንህ መጀመርያ Video መስራት ያለብህ ራስህ ላይ ነው።] ቤተ ክርስቲያን ያወጀችውን ሰባቱንም የአዋጅ ጾሞች ሳትዘል ትጾማለክ? [ይህንን ካላደረግክ ውሸታም በመሆንህ መጀመርያ Video መስራት ያለብህ ራስህ ላይ ነው።] ቅዱስ ጳውሎስ ሳታቋርጡ ጸልዩ ይላል ግን ቤተክርስቲያን በስራ ምክንያት ላይመቻቸው ይችላል ብላ ሰባት የጸሎት ጊዜያት ሰጥታናለች አንተ ያንን ሳትረሳ እያደረግክ (እየጸለይክ) ነው? [ይህንን ካላደረግክ ውሸታም በመሆንህ መጀመርያ Video መስራት ያለብህ ራስህ ላይ ነው።] መጽሐፍ ቅዱስ ለደሃ ቸርነችን (ምጽዋትን) የሚያደርግ ለእግዚአብሔር ያበድራል። ይላል እናስ በቀን ምን ያክል ሰው ትረዳለህ? [ይህንን ካላደረግክ ውሸታም በመሆንህ መጀመርያ Video መስራት ያለብህ ራስህ ላይ ነው።] የክርስቶስን ሥጋ ካልበላን ደሙን ካልጠጣን ከክርስቶስ ጋር እድል ፈንታ እንደማይኖረን ቤተ ክርስቲያን ታስተምረናለች እናስ አንተ የክርስቶስን ሥጋ እና ደም እየተቀበልክ ነው? ወይስ ካቋረጥ ዘመናት ተቆጥረዋል? [ይህንን ካላደረግክ ውሸታም በመሆንህ መጀመርያ Video መስራት ያለብህ ራስህ ላይ ነው።] ይህንን ማድረግ ስትጀምር ክርስትና በሌላው ስህተት ላይ Video መስራት ሳይሆን ምን እንደሆነች ትገባካለች። የክርስቶስን ሥጋ እየበላክ ደሙን እየጠጣክ የምትኖር ከሆነ መድኃኒትክን እየተጠቀምክ ነውና ለንግግሬ ይቅርታ አድርግልኝ። 🥰🥰🥰 ጨዋታው Replay እያደረጉ መሸናነፍ ሳይሆን የተግባራዊ ክርስትና ነው። አንዳንድ ግሩፕ ውስጥ ተግባራዊ ክርስትና ሳይሆን እውቀት ተኮር ክርስትና እየበዛ ነውና እናስተውል። ክርስቶስ ሲመጣ "ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ የዘለዓለም ሕይወት አለው።" የሚለው ጥቅስ ምን ላይ ነው የሚገኘው? ብሎ ጥቅስ አይጠይቀንም። ጉዳዩ ቃሉን በተግባር መፈጸም ላይ ነው። መጀመርያ Video የራሳችን አለመታዘዝ እና ውሽርት ላይ እንስራ ብዬ ነው እንጂ ስህተትን ማጋለጥን እየተቃወምኩ እንዳልሆነ ልብ በሉ። መልካም ዕለተ ሰንበት! 🙏🙏🙏 @Gamel_Media
Show all...
👍 4
ከፈሪሳውያንም ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ፦ መምህር ሆይ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ከሆነ በቀር አንተ የምታደርጋቸውን እነዚህን ምልክቶች ሊያደርግ የሚችል የለምና መምህር ሆነህ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ መጣህ እናውቃለን አለው። ኢየሱስም መልሶ፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው። ኒቆዲሞስም፦ ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ሊወለድ ይችላል? ሁለተኛ ወደ እናቱ ማኅፀን ገብቶ ይወለድ ዘንድ ይችላልን? አለው። ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልሃለሁ፥ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፥ ከመንፈስም የተወለደ መንፈስ ነው። ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ። ነፋስ ወደሚወደው ይነፍሳል፥ ድምፁንም ትሰማለህ፥ ነገር ግን ከወዴት እንደ መጣ ወዴትም እንዲሄድ አታውቅም፤ ከመንፈስ የተወለደ ሁሉ እንዲሁ ነው። ኒቆዲሞስ መልሶ፦ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? አለው። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ አንተ የእስራኤል መምህር ስትሆን ይህን አታውቅምን? እውነት እውነት እልሃለሁ፥ የምናውቀውን እንናገራለን ያየነውንም እንመሰክራለን፥ ምስክራችንንም አትቀበሉትም። ስለ ምድራዊ ነገር በነገርኋችሁ ጊዜ ካላመናችሁ፥ ስለ ሰማያዊ ነገር ብነግራችሁ እንዴት ታምናላችሁ? ዮሐንስ 3÷1-12 @Gamel_Media
Show all...
👍 10 2
ሊቅ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን መጠኑ ከፍተኛ የኾነ ገንዘብ ወደ ግል ሒሳባቸው ሊያስገቡ ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ ተባለ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ የኾኑት ሊቅ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በጸጥታ አካላት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዋዜማ ከታማኝ ምንጮች ሰምታለች። ምክትል ሥራ አስኪያጁ ትላንት ማክሰኞ ሚያዚያ 9 ቀን በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ አፍሪካ ኅብረት ዋና መስሪያ ቤት አካባቢ በሚገኝ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መጠኑ ከፍተኛ የኾነ ገንዘብ ወደ ግል ሒሳባቸው ሊያስገቡ ሲሉ መሆኑን ምንጮች ለዋዜማ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ከዘገባዉ ተመልክቷል። ሊቀ አዕላፍ በላይ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ልደታ ወደሚገኘው አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች። ሊቀ አዕላፍ በላይ ከዓመታት በፊት ከቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ልዩነት ከፈጠሩ በኋላ፣ በእርቅ ወደ ቤተክህነት ተመልሰው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኾነው እንደተሾሙ ይታወሳል። Via ዋዜማ #ዳጉ_ጆርናል
Show all...
👍 6😁 1