cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ABCD

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
935
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ስም መላኩ እድሜ 38 ቁመት 1.71 ስራ ጥሩ የንግድ ድርጅት አለኝ። የምፈልጋት ሴት እድሜ 20_29 ስራ ባይኖራትም ችግር የለዉም በጣም ስርአት ያላት አድራሻዬን የፍቅር ዓለም ከሚለው የቴሌግራም ቻናል ማግኜት ይቻላል። https://t.me/TRUELOVEADVISOR
Show all...
ስም ሰይድ👇 እድሜ 32 ገቢ ጥሩ ደመወዝ ያለኝ የምፈልጋት ሴት እድሜ 24_30 አላህን የምትፈራና ስራ ባይኖራትም ሰርቶ የመለወጥ ህልም ያላት። አድራሻዬን በሥለ ፍቅር ፔጅ በኩል ማግኘት ይቻላል። አድራሻዬን የፍቅር ዓለም ከሚለው የቴሌግራም ቻናል ማግኜት ይቻላል። https://t.me/TRUELOVEADVISOR
Show all...
ትዳር ፈላጊ👇 ስም ጺዮን እድሜ 32 ስራ ዶክተር መልክ ጠይም የምፈልገዉ ወንድ እድሜ 35_40 ስራ ያለዉ ፈጣሪን የሚፈራ አድራሻዬን የፍቅር ዓለም ከሚለው የቴሌግራም ቻናል ማግኜት ይቻላል።
Show all...
የዶክተር ያለህ ከፍቅረኛዬ ጋር የተዋወቅነው ዩኒቨርሲቲ አንድ ላይ ስንማር ነው፡፡ በተመረቅን በመጀመሪያው ዓመት ደግሞ አብረን መኖር ጀመርን፡፡ አሁን የትዳር ኑሯችን ሁለት ዓመት ሊሞላው ተቃርቧል፡፡ ደስ የሚል ፍቅር አለን፡፡ በቅርቡ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪ እያለን አብራኝ የተማረች ጓደኛዬ ለትምህርት ወደ ውጭ ከሄደችበት መጥታ ለሦስት ሳምንት አብረን ስንዝናና ቆይተናል፡፡ ታዲያ ያሳለፍነው ጊዜ የሚገርም ነው፡፡ እኔ ከትምህርት በኋላ ከትዳርና ሥራ ውጭ የመዝናናቱን ዓለም ብዙም ስለማላውቀው ከእሷ ጋር ያየሁት ነገር በጣም አስደንቆኛል፡፡ ይሄን ደስታ ሳላጣጥም ትዳር ውስጥ መግባቴ በጣም ቆጭቶኛል፡፡ አሁን እሷ ብትሄድም በዚሁ አጋጣሚ ከተዋወቅኳቸው ሴቶች ጋር መዝናናት ቀጥለናል፡፡ ባለቤቴ ፈፅሞ የእኔን መዝናናት የሚፈልግ አይደለም፡፡ እሱ ሁሌም ቤት የሚገባው በጣም በጊዜ ነው፡፡ በሳምንት አንድና ሁለት ቀን ብዝናና ምን ችግር አለው እያልኩ እየተከራከርኩት ነው፡፡ እሱ ግን አይፈልግም፡፡ ቤት ውስጥ ታፍኜ መኖርን አልፈልግም፡፡ ዕድሜዬ ገና 24 ነው፡፡ እንዴት አድርጌ ላሳምነው እንደምችል አላውቅም፡፡ መለያየት አልፈልግም፤ ነገር ግን ራሴን ነፃ ማውጣት እፈልጋለሁ፡፡ ምን ላድርግ? ቤቲ ነኝ #ethiopikaling
Show all...
ማሬ ነሽ እያለ ልብ እያማለለ ማሬ ነሽ ሲያበዛ በፍቅሩ ደንዝዛ በምላሱ ፈዝዛ በሰው አገር ሆና በሃሳብ መንምና አገሩ ቁጭ ብሎ ለሷ ያዘነ መስሎ መቼ! ትመጫለሽ? ምን! ትፈልጊያለሽ? ብሩን ልያዝልሽ መሬትም ልግዛልሽ እያለ ሲሞላት ሃቅ እየመሰላት ስትልክ ስትሰጠው መቅኔዋን ሲመጠው እሷ በሰው አገር በጣም ስትቸገር ያልፍልኛል ብላ ሃሳብ በሱ ጥላ ያላትን ሳትሳሳ ልካለት ጨርሳ ጨራርሳ ስትወጣ ወደአገር ስትመጣ ያመነችው ወጣት እሷን የጠበቃት ለለፋችው ልፋት ምንም ሳይገዛላት እቃም ባይገዛላት ገንዘቧን ባይሰጣት ታማኝ በሆነላት! እሱ ሌላ ይዞ በሱሱ ደንዝዞ ማሬ መሬት ቀርቶ እሱ የልቡን ሰርቶ አሷን አንከራቶ በባዶ አስቅርቶ፨ ምስኪኗ እህታችን! ይህን ሁሉ ለፍታ ወደ አገሯ ገብታ ድካሟን ሳትረሳ ያለውን አበሳ ወጣች ተመልሳ« -'"""""""""""""""""""---'' ማስታዎሻነቱ👇 በሰው አገር ላይ ለሚለፉና በየዋህነት ለሚታለሉ እህቶቼ ይሁንልኝ። ውድ አንባቢያን አስተማሪ ገጠመኝ ወይም ለመወሰን የተቸገራችሁበት ታሪክ ካላችሁ ቻናላችን እናንተን ለማስተናገድ ሁሌም ክፍት ነው።
Show all...
ፍቅረኛዬ ትዳሬን ፈትቼ እንዳገባት ትፈልጋለች 🙄 ትዳሬም የልጅነት ፍቅሬም አደጋ ላይ ናቸዉ እባካችሁ መላ ስጡኝ ነገሩ እንዲህ ነዉ ከዛሬ 1ዐ ዓመት በፊት የhigh school ተማሪ እያለሁ በድንገት የትምህርተ ቤት ጎደኛዬ አሚናት የሒሳብ መጸሃፍ ልትዋሰኝ እቤት ትመጣለች ከሷ ጋር አብራት የመጣችዉን ልጅ ከዛች እለት በፊት አይቻት አላዉቅም ስሟ ራህመት ይባላል፣ራህመትን ገና እንዳየኋት ልቤ ደነገጠ፣ የምሆነዉ ጠፋኝ፣ ተደናበርኩ፣ ጎደኛዋ መጸሃፌን፣ እሷ ደሞ ልቤን፣ ይዘዉ ተመለሱ፤ ከዛች እለት ጀምሮ ልቤን ድንገት ሰርቃዉ የሄደችዉን ራህመትን ለማግኘትና የራሴ ለማድረግ ሌሊትም በህልሜ ቀንም በእዉኔ ትምህርቴን ወደጎን ብዬ መሮጥ ጀመርኩ፤ በጎደኛዋ አማካኝነት ተገናኘንና በሂደት የፍቅር ጥያቄ አቀረብኩላት እሷም ተቀበለቺኝ፣ በወቅቱ እኔ ሰቃይ ከሚባሉ ተማሪዎች አንዱ ስለነበርኩ ከወላጅ እስከ ጓደኛ እንዲሁም በመምህራንም ጭምር የ12ኛ ክፍል ፈተናን ከፍተኛ ዉጤት እንደማመጣ በልበ ሙሉነት ይጠብቁኛል ይከታተሉኛል፤ ሆኖም ልቤ በራህት ስለተጠለፈ ትምህርቴ ላይ ማተኮሩን ትቼ በሷ ፍቅር ክንፍ ማለቱን ቀጠልኩበት። ይባስ ብሎ ትምህርት ቤት መቅረት፣ በእረፍት አቋርጦ መሄድ፣ አጥር ዘሎ መዉጣት ጀመርኩ፤ ጉዳዩን በቅርበት የሚያዉቁ ጎደኞቼ እነ ዳኒ ተዉ ይቅርብህ ትምህርትህን አርፈህ ተማር አሁን ግዜዉ አይደለም ለሁሉም ትደርስበታለህ እያሉ፣ ለስም ጠሪ መምህሬ ሳይቀር ተናግረዉ አስመከሩኝ ግን በፍጹም ልተዉ አልቻልኩም። ያኔ እኔ የ12ኛ ራህመት ደሞ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ነበርን፣ እንዲህ እንዳ እያልኩ ከትንሽ ወራት ብኋላ ራህመት ትምህርትን አቋርጣ ወደ አረብ ሀገር ልትሄድ እንደሆነ ነገረቺኝ፤ ሰማይ የተደፋብኝ ያክል ተሰማኝ፣ በጣም ደነገጥኩ የምይዘዉ የምጨብጠዉ አጣሁ፣ላስቀራት ሞከርኩ ግን አልቻልኩም ከትንሽ ግዜ ብኋላ ሄደች በእዛዉ ተለያየን። እኔም ሀዘኔን ዋጥ አድርጌ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ወሰድኩና በፈጣሪ እገዛ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ገባሁ። ከእራህመት ከተለየሁ ብኋላ የሴት ጎደኛ የለኝም እረ እንዳዉም የወንድም የለኝም በቃ ሰዉን መቅረብ እፈራለሁ። ሁሉም ሰዉ እንደሷ ጥሎኝ የሚሄድ ነዉ የሚመስለኝ። በዚህ ሁሉ ፈተና ዉስጥ ሆኜ የዩኒቨርስቲ ትምህርቴን ቀጠልኩ። በዛም ከባድ ግዜ አሳለፍኩ ብቸኛ ነኝ እንደእብድ ብቻዬን አወራለሁ ጓደኛ ብዬ የምቀርባቸዉም ስለእሷ ሳወራቸዉ ይሳለቁብኛል በዚህ የተነሳ ብዙም ሰዉ አልቀርብም ነበር። በዚህ ሁኔታ ዉስጥ ሆኜ ከዓመታት ብኋላ ሰኔ ወር ለይ ከዩኒቨርስቲ ስመለስ ራህመትም ከአረብ ሀገር ተመልሳ አገኘኋት፣ ሆኖም እኔ ፍቅራችንን ከቆመበት እንቀጥላለን ብዬ ሳስብ ያልጠበኩትን ነገር ሰማሁ፣ ራህመት አረብ ሀገር ስትቆይ ከሌላ ሰዉ ጋር ፍቅር ጀምራ አሁንም የመጣችዉ እሱን አግብታ ተመልሳ ልትሄድ እንደሆነ አረዳቺኝ፣ ያኔ መፈጠሬን ጠላሁ፣ ታመምኩ፣ አነባሁ፣ ከባለፈዉ የበለጠ ቁስል ገጠመኝ። ከወራት ብኋላ እሷም ያለቺዉን ሰዉ ድል ባለ ሰርግ አገባች እኔም የማይፋቀዉን ፍቅሯን ይዜ ዳግም ወደ ዩኒቨርሲቲ ተመለስኩና ትምህርቴን ጨረስኩ።በትምህርት ምኒስቴር ስፖንሰርነት ወደስራ ሳልገባ ወዳዉኑ የሁለተኛ ዲግሪዬን ቀጠልኩ። እሱንም ጨርሼ አንድ ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ ስራ ጀመርኩ። ቤተሰብና ጓደኛ ትዳር መያዝ እንዳለብኝ ይነግሩኛል እኔም ልቤ በራህመት ስለተጎዳ ጥያቂያቸዉን አልቀበልም ነበር።ድጋሚ ከአመታት ብኋላ ራህመትን ባጋጣሚ መንገድ ላይ አገኘኋት ። እሷም ያለችበት ትዳር እንደፈረሰና ኒካ ብቻ እንደቀራት እኔ ከተቀበልኳት ኒካዋን አዉርዳ ከኔ ጋር መሆን እንደምትፈልግ ባለፈዉ ነገር ሁሉ እንደተጸጸተች ትዳሯንም ጭምር የተወቺዉ እኔን ለማግኘት እንደሆ ነገረቺኝ ሆኖም እኔ በወቅቱ በቤተሰብ የተለመነቺልኝ ልጅ ነበረችና ቤተሰብን ላለማስከፋት የልጂቱንም ሞራል ለመጠበቅ ከብዙ ማመንታት ብኋላ የሷን ጥያቄ ሳልቀበላት ቀረሁ። ወዲያዉኑ በቤተሰብ የተለመነቺልኝን ልጅ አገባሁ ልጅም ወለድኩ። ሆኖም የድሮዋ ፍቅረኛዬ ራህመት ከአመታት በፊት ትዳሯን ከፈታች ብኋላ ዳግም ሌላ ሰዉ አላገባችም። አሁንም በስልክ እንገናኛለን ዛሬም እወዳታለሁ አግብቻት ብኖር ህይወቴ ሙሉ የሚሆን መስሎ ይሰማኛል ፣ እሷም ተመሳሳይ ፍላጎት እንዳላት ትነግረኛለች ሆኖም ያሁኗ ባለቤቴ የልጄ እናት ደግሞ ለኔ ብዙ ዋጋ ከፍላለች ከልቧ ትወደኛለች ከኔ መለየትን አታስበዉም ከራህመት ጋር ያለንን ከጅምሩ ታዉቀዋለች አልፎ አልፎም በዚህ የተነሳ ተጣልተን ተለያይተን በሽማግሌ ታርቀንም እናዉቃለን። በምሃል እኔ የማደርገዉ ጠፋኝ።ብዙ አማራጮችን አሰብኩ አልተሳካም በእርግጥ በእኛ እምነት ሁለት ማግባት ይቻላል እኔ ግን አሁን ባለሁበት እድሜ ያንን ማድረግ አልፈልግም። አኔ እስከዛሬ ያሳለፍኩትን ህመም ስለማዉቅ የልጄ እናት ባለቤቴ እንደኔ እንዲገጥማት አልፈልግም። የድሮዋ ፍቅረኛየ ራህመትንም ማጣት ከበደኝ። ሁሉንም ትቼ ወደሷ እንዳልሄድ ራስወዳድነት ሆኖ ተሰማኝ አሁን ያለሁበትን ህይወት እንዳልቀጥል የምወዳትን ልጅ በገዛ እጄ ማጣት መስሎ ታየኝ። መላ አጣሁ በጨዋነት እባካችሁ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ንገሩኝ እኔ አልቻልኩም ሁሉም ነገር ካቅሜ በላይ ሆኗል። ትዳሬም የልጅነት ፍቅሬም አደጋ ላይ ናቸዉ።
Show all...
የማስታወስ ችሎታዎን ለማሻሻል 11 ዘዴዎች አንዳንድ የማስታወሻ ዘዴዎችን መጠቀም እንደሚያግዝ ግልጽ ነው። አስታዋሾችን ወደ ስልክዎ የሚልክ የመስመር ላይ ካላንደር ማዋቀር እነዚያን ሁሉ ቀጠሮዎች እና ስብሰባዎች እንዲከታተሉ ያግዝዎታል። እለታዊ የተግባር ዝርዝሮችን መፍጠር መጠናቀቅ ያለባቸውን አስፈላጊ ስራዎችን እንዳትረሳ ያደርጋል። ግን በረጅም ጊዜ ማህደረ ትውስታዎ ውስጥ በትክክል እንዲሰሩ ስለሚያስፈልጉት ሁሉም ጠቃሚ መረጃዎችስ? የተወሰነ ጥረት የሚጠይቅ አልፎ ተርፎም ማስተካከል ወይም የእርስዎን መደበኛ የጥናት ልማዶች በሚያስደንቅ ሁኔታ መቀየርን ያካትታል ነገር ግን ከማስታወስዎ የበለጠ ለማግኘት ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸው በርካታ ስልቶች አሉ። ከሚቀጥለው ትልቅ ፈተናዎ በፊት፣ ከእነዚህ የተሞከሩ እና የተሞከሩ የማስታወስ ችሎታን ለማሻሻል ቴክኒኮችን መመልከቱን ያረጋግጡ። እነዚህ 11 በጥናት የተረጋገጡ ስልቶች የማስታወስ ችሎታን በብቃት ሊያሻሽሉ፣ ማስታወስን ሊያሳድጉ እና መረጃን ማቆየት ሊጨምሩ ይችላሉ። 1. ትኩረትዎን ይስጡ ትኩረት ከማስታወስ ዋና ዋና ክፍሎች አንዱ ነው. መረጃ ከአጭር ጊዜ ማህደረ ትውስታ ወደ የረጅም ጊዜ ማህደረ ትውስታዎ እንዲሸጋገር ፣ ይህንን መረጃ በንቃት መከታተል ያስፈልግዎታል። እንደ ቴሌቪዥን፣ ሙዚቃ እና ሌሎች ትኩረትን የሚከፋፍሉ ነገሮች በሌሉበት ቦታ ለማጥናት ይሞክሩ። በተለይ አብረውህ በሚኖሩ ሰዎች ወይም ጫጫታ በሚሰማቸው ልጆች ከተከበቡ ትኩረት የሚከፋፍሉ ነገሮችን ማስወገድ ፈታኝ ሊሆን ይችላል። ብቻዎን ለመሆን አጭር ጊዜ ይመድቡ። በስራዎ ላይ እንዲያተኩሩ አብረው የሚኖሩ ጓደኞችዎ የተወሰነ ቦታ እንዲሰጡዎት ወይም አጋርዎ ልጆቹን ለአንድ ሰዓት እንዲወስድ ይጠይቁ። 2. መጨናነቅን ያስወግዱ ቁሳቁሶችን በበርካታ ክፍለ ጊዜዎች ማጥናት መረጃን በበቂ ሁኔታ ለማስኬድ የሚያስፈልግዎትን ጊዜ ይሰጥዎታል። ጥናቶች በተከታታይ እንደሚያሳዩት በመደበኛነት የሚያጠኑ ተማሪዎች በአንድ የማራቶን ክፍለ ጊዜ ትምህርታቸውን ከሚከታተሉት በተሻለ ሁኔታ ትምህርቱን ያስታውሳሉ። 3. መዋቅር እና ማደራጀት ተመራማሪዎች መረጃ በማህደረ ትውስታ ውስጥ በተዛማጅ ስብስቦች ውስጥ የተደራጁ መሆናቸውን ደርሰውበታል።ይህንን የምታጠኑትን ቁሳቁሶች በማዋቀር እና በማደራጀት መጠቀም ትችላለህ። ተመሳሳይ ጽንሰ-ሀሳቦችን እና ቃላትን አንድ ላይ ለመቧደን ይሞክሩ፣ ወይም ከቡድን ጋር የተያያዙ ፅንሰ-ሀሳቦችን ለማገዝ የማስታወሻዎን እና የመማሪያ መጽሃፍ ንባቦችዎን ዝርዝር ያዘጋጁ። 4. ማኒሞኒክ መሳሪያዎችን ይጠቀሙ የማስታወሻ መሳሪያዎች ብዙውን ጊዜ ተማሪዎች ለማስታወስ የሚረዱ ዘዴዎች ናቸው። ሜሞኒክ በቀላሉ መረጃን ለማስታወስ መንገድ ነው። ለምሳሌ፣ ማስታወስ ያለብዎትን ቃል እርስዎ ከሚያውቁት የተለመደ ነገር ጋር ሊያያይዙት ይችላሉ። በጣም ጥሩው ሜሞኒክስ አዎንታዊ ምስሎችን፣ ቀልዶችን ወይም አዲስነትን የሚጠቀሙ ናቸው። የተወሰነውን የመረጃ ክፍል ለማስታወስ የሚረዳ ግጥም፣ ዘፈን ወይም ቀልድ ይዘው ይምጡ። 5. ይግለጹ እና ይለማመዱ መረጃን ለማስታወስ, የሚያጠኑትን ወደ የረጅም ጊዜ ማህደረ ትውስታ ኮድ ማስገባት ያስፈልግዎታል. በጣም ውጤታማ ከሆኑ የኢኮዲንግ ቴክኒኮች አንዱ ገላጭ ልምምድ በመባል ይታወቃል። የዚህ ዘዴ ምሳሌ የአንድ ቁልፍ ቃል ፍቺን ማንበብ, የቃሉን ፍቺ ማጥናት እና ከዚያም ይህ ቃል ምን ማለት እንደሆነ የበለጠ ዝርዝር መግለጫ ማንበብ ነው. ይህን ሂደት ጥቂት ጊዜ ከደጋገሙ በኋላ፣ መረጃውን ማስታወስ በጣም ቀላል እንደሆነ ያስተውሉ ይሆናል። 6. ጽንሰ-ሐሳቦችን በዓይነ ሕሊናህ ተመልከት ብዙ ሰዎች የሚያጠኑትን መረጃ በዓይነ ሕሊናቸው በማየት በእጅጉ ይጠቀማሉ። በመማሪያ መጽሐፍትዎ ውስጥ ላሉ ፎቶግራፎች፣ ገበታዎች እና ሌሎች ግራፊክሶች ትኩረት ይስጡ። ለማገዝ የእይታ ምልክቶች ከሌልዎት የእራስዎን ለመፍጠር ይሞክሩ። በማስታወሻዎችዎ ጠርዝ ላይ ገበታዎችን ወይም ምስሎችን ይሳሉ ወይም ተዛማጅ ሀሳቦችን በጽሑፍ የጥናት ማቴሪያሎችዎ ውስጥ ለመቧደን በተለያየ ቀለም ያጌጡ ወይም እስክሪብቶችን ይጠቀሙ። አንዳንድ ጊዜ ማስታወስ ያለብዎት የተለያዩ ቃላቶች ፍላሽ ካርዶችን መስራት እንኳን በአእምሮዎ ውስጥ መረጃን ለመጨመር ይረዳል። 7. አዲስ መረጃን አስቀድመው ከሚያውቋቸው ነገሮች ጋር ያገናኙ የማታውቀውን ነገር በምታጠናበት ጊዜ ይህ መረጃ ከምታውቀው ነገር ጋር እንዴት እንደሚዛመድ ለማሰብ ጊዜ ወስደህ አስብ። በአዳዲስ ሀሳቦች እና ቀደም ባሉት ትዝታዎች መካከል ግንኙነቶችን በመፍጠር በቅርብ ጊዜ የተማረውን መረጃ የማስታወስ እድልን በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደግ ይችላሉ። 8. ጮክ ብለህ አንብብ እ.ኤ.አ. በ 2017 የታተመ ጥናት እንደሚያመለክተው ቁሳቁሶችን ጮክ ብለው ማንበብ የቁሱን የማስታወስ ችሎታዎን በእጅጉ ያሻሽላል። አስተማሪዎች እና የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ተማሪዎች በእውነቱ አዲስ ጽንሰ-ሀሳቦችን ለሌሎች እንዲያስተምሩ ማድረጉ ግንዛቤን እና ትውስታን እንደሚያሳድግ ደርሰውበታል። አዲስ ጽንሰ-ሀሳቦችን እና መረጃዎችን ለጓደኛ ወይም የጥናት አጋር በማስተማር ይህንን አካሄድ በራስዎ ጥናት ይጠቀሙ። 9. ለአስቸጋሪ መረጃ ተጨማሪ ትኩረት ይስጡ በምዕራፍ መጀመሪያ ወይም መጨረሻ ላይ መረጃን ማስታወስ አንዳንድ ጊዜ እንዴት ቀላል እንደሚሆን አስተውለሃል? ተመራማሪዎች የመረጃ ቅደም ተከተል የማስታወስ ሚና ሊጫወት እንደሚችል ደርሰውበታል ይህም ተከታታይ አቀማመጥ ተጽእኖ በመባል ይታወቃል. መካከለኛ መረጃን ማስታወስ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ይህንን መረጃ በመለማመድ ተጨማሪ ጊዜ በማጥፋት ይህንን ችግር ማሸነፍ ይችላሉ። ሌላው ስልት የተማርከውን እንደገና ለማዋቀር መሞከር ነው ስለዚህ ለማስታወስ ቀላል ይሆናል። በተለይ አስቸጋሪ የሆነ ፅንሰ-ሀሳብ ሲያጋጥሙ፣ መረጃውን ለማስታወስ የተወሰነ ተጨማሪ ጊዜ ይውሰዱ። 10. የጥናት መደበኛ ስራዎን ይቀይሩ የማስታወስ ችሎታዎን ለመጨመር ሌላው ጥሩ መንገድ የጥናትዎን መደበኛነት መለወጥ ነው። በአንድ የተወሰነ ቦታ ማጥናት ከለመዱ በሚቀጥለው የጥናት ክፍለ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ ለመሄድ ይሞክሩ። ምሽት ላይ የምታጠኚ ከሆነ, ባለፈው ምሽት ያጠኑትን መረጃ በየቀኑ ጠዋት ጥቂት ደቂቃዎችን ለማሳለፍ ይሞክሩ. በጥናት ክፍለ ጊዜዎ ላይ አዲስ ነገር በማከል የጥረታችሁን ውጤታማነት ማሳደግ እና የረጅም ጊዜ የማስታወስ ችሎታዎን በከፍተኛ ሁኔታ ማሻሻል ይችላሉ። 11. አንዳንድ እንቅልፍ ያግኙ ተመራማሪዎች እንቅልፍ ለማስታወስ እና ለመማር ጠቃሚ እንደሆነ ከረጅም ጊዜ በፊት አውቀዋል. አዲስ ነገር ከተማሩ በኋላ ትንሽ መተኛት በፍጥነት እንዲማሩ እና በደንብ እንዲያስታውሱ እንደሚያግዝ ጥናቶች አረጋግጠዋል። እንዲያውም በ 2014 የታተመ አንድ ጥናት እንዳመለከተው አዲስ ነገር ከተማርን በኋላ መተኛት በአንጎል ውስጥ አካላዊ ለውጦችን ያመጣል. እንቅልፍ የተነፈጉ አይጦች በደንብ ካረፉ አይጦች ይልቅ የመማር ተግባርን ተከትሎ አነስተኛ የዴንዶቲክ እድገት አጋጥሟቸዋል። ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ አዲስ መረጃ ለመማር በሚታገሉበት ጊዜ፣ ካጠኑ በኋላ ጥሩ እንቅልፍ ለመተኛት ያስቡበት። #Share_for_others https://t.me/berhantutor
Show all...
ብርሃን የማስጠናት እና የማማከር አገልግሎት

ልኑነት እናመጣለን/We make a difference አስተማማኝ ብቃት እና ልምድ ባላቸው መምህራን የማማከር እና የማስጠናት አገልግሎት እንሰጣለን። We provide intensive Tutor for: 1. All Grade levels 2. College and University Students. 3. Project and Research works.

𝐈𝐟 𝐲𝐨𝐮 𝐰𝐚𝐧𝐭 𝐭𝐨 𝐜𝐨𝐧𝐭𝐚𝐜𝐭 𝐮𝐬, 𝐲𝐨𝐮 𝐜𝐚𝐧 𝐮𝐬𝐞 𝐭𝐡𝐞 𝐟𝐨𝐥𝐥𝐨𝐰𝐢𝐧𝐠 𝐥𝐢𝐧𝐤👇 @berhantutor4ALL
Show all...
Tutor ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ❗️ የማጠናከሪያ (Tutor) ፕሮግራሙ ሰኞ ሀምሌ 03/2014 ዓ/ም የሚጀምር በመሆኑ በሰዓቱ እንድትገኙ ከወዲሁ እናሳስባለን። https://t.me/berhantutor
Show all...
ብርሃን የማስጠናት እና የማማከር አገልግሎት

ልኑነት እናመጣለን/We make a difference አስተማማኝ ብቃት እና ልምድ ባላቸው መምህራን የማማከር እና የማስጠናት አገልግሎት እንሰጣለን። We provide intensive Tutor for: 1. All Grade levels 2. College and University Students. 3. Project and Research works.

👉ፈተና ከጀመርን በኋላ ማድረግ የሚገቡን ነገሮች (ፈተና ላይ እያለን)፤ 👉 ወደ ፈተና ከመሄዳችን ቀደም ብለን ለፈተና የሚረዱንን መሳሪያዎች እና የመፈተኛ ቁሶችን ማዘጋጀት። 👉አብዝተን ፈተናን እና የምናመጣውን ነጥብ ስሌት አለመገመት ። 👉ፈተና ስንጨርስ የተሳሳትነውን ጥያቄ አብዝቶ ማሰብ እና ሌላ ተማሪ መጠየቅ ጭንቀት ውስጥ ስለሚከተን ከዚህ ይልቅ ቤት ሄደን እረፍት ማድረግ እና ለቀጣይ ፈተና መዘጋጀት ። 👉 በፈተና ጊዜ ድንገተኛ ጭንቀት እና ድንጋጤ ከገጠመን ወዲያው የምንሰራውን ገታ አድርገን በጥልቀት አየር በአፍንጫችን ስበን ወደ ሳንባ እያስገባን መልሰን ማስወጣት ይህንንም እስክንረጋጋ መደጋገም ። ከዚህ በመቀጠል የማረጋጊያ ቃላትን ለራስዎ መንገር:: 👉 ፈተና በምንሰራ ጊዜ ግራ ያጋባንን እና እርግጠኛ ያልሆንበትን ጥያቄ በይለፍ ማቆየት እና ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ይህም ጊዜያችንን በአግባቡ እንድንጠቀም ይረዳናል። ነገር ግን ምልክት አድርገን ማለፍ፤ 👉በተመሳሳይ እርግጠኛ ያልሆልንበትን መልስ ላይ ተደናግጠን መሰረዝ እና መደለዝን መቀነስ ይህም ስንደነግጥ እና ስንጨነቅ የምናውቀውን መልስ ትተን ወደ ሌላ መልስ እንድሰጥ ስለሚያረግ መሰረዝና መደለዝን መቀነስ ። 👉ፈተናውን ወደ ማገባደድ ስንደርስ በይለፍ ያስቀመጥናቸውን ግራ ያጋቡንን ጥያቄዎች ጥቂት አስበንበት መልስ መስጠት ፤ ካልሆነም ደግሞ ብልሀት ተጠቅመን የግመታ መልስ ሰጥተን ወደ ቀጣዩ ጥያቄ መሄድ ። 👉በተደጋጋሚ ሰአትን አለመመልከት ወይም ሰአት በቃን አልበቃን እያልን አለመጨነቅ። https://t.me/berhantutor
Show all...
ብርሃን የማስጠናት እና የማማከር አገልግሎት

ልኑነት እናመጣለን/We make a difference አስተማማኝ ብቃት እና ልምድ ባላቸው መምህራን የማማከር እና የማስጠናት አገልግሎት እንሰጣለን። We provide intensive Tutor for: 1. All Grade levels 2. College and University Students. 3. Project and Research works.