en
Feedback
ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ

Open in Telegram
776
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
+4430 days
Posts Archive
ምስሉ ይናገራል
ምስሉ ይናገራል

🌿ካልቻልክ ግን ሲሳቅብህ ትኖራለህ፡» ✨ «መጀመሪያ ፍርሀትህን ግደለው፡፡ ፍርሀትህ ወደ መቃብር ሲወርድ የተሙአላ ማንነት ብቅ ማለት ይጀምራል፡፡ አትፍራ! ከህሊናህ በቀር ማንንም ምንንም አትፍራ! ከፈራህ አትማርም፡፡ እመነኝ ከፈራህ ምንም ነገር ሳታውቅ ይህችን አለም ተሰናብተህ ወደ መጣህበት ትመለሳለህ፡፡» ———————————————————————————————————————————— ✨«እሱ ከ ግድግዳው የተንፀባረቀው የአንጎል ምስል ላንተም ለሌላውም እኩል የተሰጠ ትልቅ አካል ነው፡፡ እንደ ህዋ ልታሰፋው እንደ ነጥብ ልታጠበው የምትችል አንተ ብቻ ነህ፡፡ አይምሮህን ከፉርሃት ነፃ አውጣው ፡፡ ከዛም በማይክሮ ሴኮንድ ተአምር መስራት የጀምራል፡፡ እውነቱን ልንገርህ አድያም ፡፡ የሳቁብህን ሁሉ አፍ ምታሲዝበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ይህን ማድረግ ካልቻልክ ግን ሲሳቅብህ ትኖራለህ፡፡» 🖊 ይስማዕከ ወርቁ 📚 ራማቶሃራ 🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾 💫 💫 🎖🌿ካልቻልክ ግን ሲሳቅብህ ትኖራለህ፡»» ———————————————————————————————————————————— @ethioterkaa @ethioterkaa @ethioterkaa

ሀሳባችሁን @janoooooom ላይ አካፍሉን🙏 💚💛❤️
ሀሳባችሁን @janoooooom ላይ አካፍሉን🙏 💚💛❤️

➮ ዘር ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ ➮በ ስብአት ገ/እግዚአብሔር ➮ ከ ሸገር ሼልፍ ➮ ከ 5 6 7 እና ሌሎችም ከሚለው መጽሐፍ ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲ አዘጋጅ፦⇨ @ethioterkaa@ethioterkaa ━━━━━━✦✗✦━━━━━━

➮ ዘር ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ ➮በ ስብአት ገ/እግዚአብሔር ➮ ከ ሸገር ሼልፍ ➮ ከ 5 6 7 እና ሌሎችም ከሚለው መጽሐፍ ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲ አዘጋጅ፦⇨ @Ethio_Tereka@Ethio_Tereka ━━━━━━✦✗✦━━━━━━

➮ ዘር ━━━━━━✦✗✦━━━━━━━ ➮በ ስብአት ገ/እግዚአብሔር ➮ ከ ሸገር ሼልፍ ➮ ከ 5 6 7 እና ሌሎችም ከሚለው መጽሐፍ ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲ አዘጋጅ፦⇨ @ethioterkaa@ethioterkaa ━━━━━━✦✗✦━━━━━━

ጦር አውርድ ➮ አጭር ግን በጣም አሰተማሪ ክታብ! ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ ✍🏽ድርሰት እና 🎙ትረካ: በዕውቀቱ ስዩም ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲ አዘጋጅ፦⇨@ethioterkaa @ethioterkaa @ethioterkaa ━━━━━━✦✗✦━━━━━━

ጦር አውርድ ➮ አጭር ግን በጣም አሰተማሪ ክታብ! ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ ✍🏽ድርሰት እና 🎙ትረካ: በዕውቀቱ ስዩም ━━━━━━✦✗✦━━━━━━ ⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲ አዘጋጅ፦⇨@ethioterkaa @ethioterkaa @ethioterkaa ━━━━━━✦✗✦━━━━━━

*የሰርግ ማታ ባል ለሚስቱ የሰጠው ምክር* የኔ ፍቅር ከእንግዲህ አንቺ ማለት ለኔ የመኖር ትርጉሜ ነሽ ❤#በእኔ እና ባንቺ መሀል ከእንግዲህ ምንም አይነት ድብብቆሽ ሊኖር አይገባም። ❤#የኔ ውድ በፊ
*የሰርግ ማታ ባል ለሚስቱ የሰጠው ምክር* የኔ ፍቅር ከእንግዲህ አንቺ ማለት ለኔ የመኖር ትርጉሜ ነሽ ❤#በእኔ እና ባንቺ መሀል ከእንግዲህ ምንም አይነት ድብብቆሽ ሊኖር አይገባም። ❤#የኔ ውድ በፊት እኔ ትልቅ ልጅ ነበርኩ አሁን ግን በድጋሚ ህፃን እሆናለሁ ትዝ ይለኛል ህፃን እያለሁ ምግብ በልቼ እንደሆነ ወይንም እርቦኝ እንደሆነ የምታውቃኝ እናቴ ነበረች ጥዋት ከእንቅልፍ የምትቀሰቅሰኝ እናቴ ነበረች ከቤት ከመውጣቴ በፊት መስተካከል ያለበትን ነገሮች አስተከክለ የምትሸናኝ እናቴ ነበረች ከእንግዲህ ግን እናቴ አንቺ ነሽ ከእንግዲህ የኔን ደካማ ጎን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም ከእንግዲህ ጥማቴን የምታውቅ ሌላ እናት የለችም አየሽ ፍቅር ልጅ እያለሁ የሆንኩትን ነገር ሁሉ ለእናቴ ነበር መጥቼ የምናግራት እሷም ምስጢሬን ለማንም ነግራ አታውቅም አሁን ግን እናቴ አንቺ ነሽ ምስጢሬን የምነግርሽ ላንቺ ብቻ ነው ለማንም ምስጢሬን አሳልፈሽ አትስጨ ልጅ እያለሁ ብዙ ጥፋቶችን አጠፋ ነበር እናቴም ለጊዜው በጣም ትቆጠኝ ነበር ግን ቁጣዋ ብዙም አይቆይም ወዳውኑ ተመልሶ መሳቅ ትጀምራለች የኔ ፍቅር ምናልባት አንቺንም ሊያስከፈሽ እችላለሁ እባክሽን ግን ቂም አትያዥብኝ ጥፍቴን ግን አይተሽ ዝም አትበይ ምክር ስጪኝ እቀበላለሁ የኔ ማር ወደ ጣፋጭ የአልጋ ጨዋታ ከመሄዳችን በፊት ደግሜ የምነግርሽ ነገር ለሰዎች ወሬ በፍጹም ጆሮ አትስጪ ከእንግዲህ ወዲህ ላንቺ ከእኔ የሚቀርብ ማንም ሊኖረ አይችልም መኖር የለበትም። የኔ ፍቅር የብዙ ሰዎች ትዳር መፍረስ ምክንያት ጎሮቤት አልያም የጓደኛ ብዛት ነው ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ከልክ በላይ አታቅርቢ በፈጣሪ ፊት ቃል እገባለሁ እኔም ምርጡ አባትሽ ሁሌም ከጎንሽ መቆም የምችል ከማንም አስቀድሜ ለልጄ ለሚስቴ የሚል መልካም ባል እሆንልሻለሁ! @ethioterkaa

ሚስጥራዊ ሚስት አዲስ የፍቅር ታሪክ ሙሉ ክፍል

የባከነ ሌሊት!!!! (በእውቀቱ ስዩም) ወይ ሮንድ አላደርኩ ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ ወይ ሰአታት ቁሜ ቤተክስያን ስሜ
የባከነ ሌሊት!!!! (በእውቀቱ ስዩም) ወይ ሮንድ አላደርኩ ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ ወይ ሰአታት ቁሜ ቤተክስያን ስሜ ሰይጣን አላሳፈርሁ:: ሌቦች ደብድበውት አንዱን ምስኪን ላሥር ባምቢስ ድልድዩ ሥር ቆስሎ የወደቀ ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ "በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ ምስኪን አባወራ ብብት ሥር ገብቼ አፋፍሼ አንስቼ ተሸክሜ አድኜ ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ ወይ ምግባር አልሠራሁ ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ:: አንድ በትረ-ሙሴ ሁለት ስስ አሎሎ ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ ሲባክን ዝምብሎ " እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ" የምትል መለሎ ልቤን ሳትሰውረው አልጋየን ሳትሰብረው:: ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ " እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ:: አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት ሲገፉ ሲስቧት " እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን ልመናዋ ስቦኝ እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ ከሁዋላ ደርሼ ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን በማረግ ቃኝቼ ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ:: ድል ሳላስመዘግብ ውጥረት ሳለረግብ ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ:: ሼር 💚💛❤️ ➡️@ethioterkaa ➡️@ethioterkaa

ፍቅርና ፊዚክስ-1 ፍቅርና የቦታ-ጊዜ አውታር (Love & Space - Time Dimension) እጅግ አስደናቂ፣ እጅግም መሳጭና ረቂቅ ወደ ሆነ ሳይንሳዊ ፍልሰፍና ልወስዳችሁ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ፈጽሞ አስባችሁት አታውቁም፤ ሆኖም ግን በውስጡ ኖራችኋል፡፡ ሕግጋቱን አክብራችሁ ተመላልሳችኋል፡፡ ክስተቱ አንዳንዶቻችሁን ገጣሚ፣ ሰዓሊና የውበት አድናቂ አድርጓችኋል፤ አንዳንዶቻችሁን ደግሞ የስቃያችሁ መነሻም ሆና አሳልፋችሁታል፤ ለብዙዎቻችሁ ግን የትዳራችሁ መሠረት ሆኗል፤ ይዘቱን ስትቀይሩለት ደግሞ መንፈሳዊ አድርጓችኋል - ፍቅር፡፡ ፍቅር ስለ ዓለም ያለንን ሸውራራ አመላካከት የምንቀይርበት መነጽር ነው፡፡ ስለፍቅር ምን አዲስ ነገር አለ ብላችሁ እንዳትጠይቁኝ፡፡ እኔ ፍቅርን የማሳያችሁ እናንተ አስቀድማችሁ በምታውቁት መንገድ አይደለም፤ ወይም ደግሞ አርቲስቶችና ደራሲያን ባሳዩዋችሁ መንገድም አይደለም የማሳያችሁ፡፡ ፍቅር ያልተዳሰሰ ሚስጢራዊ ገጽታ አለው፤ እጅግ አስገራሚ ፤ እጅግ አስደናቂ፡፡ ፍቅርን ከፊዚክስ ጋር አነፃጽሮ ማን አየው? ፍቅርን ከኬሚስትሪ ጋር አዋህዶ ማን ተመለከተው? ሌላው ይቅርና ፍቅርን ከመለኮት ጋር አጣምሮ ማየት የተለመደ ቢሆንም እንኳ ክስተቱ ግን በደንብ አልተፈተሸም፡፡ ፍፁማዊ ፍቅር እንደ ሶፍትዌር ፕሮግራም አእምሯችሁ ላይ ቢጫን ዕጣ ፋንታችሁ ምን ሊሆን እንደሚችል አስባችሁት ታውቃላችሁ? ፍፁማዊ ፍቅር እላያችሁ ላይ ቢጫን አልቅሳችሁ እንደምታልቁስ ምን ያህል ታውቃላችሁ? በቅንጫቢ ፍቅር የምንወደው ሰው ሲሞትብን ያንን ያህል ካለቀስን፤ ፍቅራችን ፍፁማዊ ቢሆን እንዴት እንሆን ይሆን? በረዶ ቀስ በቀስ እየቀለጠ ወደ ፈሳሽ ውሃነት እንደሚለወጠው ሁሉ፤ ፍፁማዊ ፍቅርም እላያችሁ ላይ ቢጫን ቀስ በቀስ ሁለመናችሁ እየቀለጠ ወደ እንባነት ትቀየራላችሁ፡፡ በፍፁማዊ ፍቅር የምትሰቃዩ ከሆነ ብዙም ሳትቆዩ ሙሉ በሙሉ እንባ ትሆናላችሁ፡፡ ሙቀት በረዶን እንደሚያፈርሰው ሁሉ፣ በቅዝቃዜ ያገኘውን ትምክህትም እንደሚያስጥለው ሁሉ፣ ፍቅርም የራስ ኩራትን ያስጥላል፣ ሰውነትንም አፈራርሶ ወደ እንባነት ይለውጣል፡፡ በፍፁማዊ ፍቅር የምትሰቃዩ ከሆነ የሚጠብቃችሁ እድል ይሄው ነው፤ እንቅጩን ልንገራችሁ፡፡ ፍፁማዊ ፍቅር ላይ ሰውን ለመወደድ በስጋ እስክትዛመዱ፣ በጓደኝነትም እስክትተዋወቁ አትጠብቁም። ያለ ሰብሳቢና ያለፍትህ ምድር ላይ በድህነትና በጦርነት ለሚማቅቀው የሰው ልጅ ሁሉ ደረታችሁን ትደቃላችሁ፤ ፍቅርህን መጠለያ አድርጋ ከቤተሰቦቿ ለተሰደደችው ፍቅረኛህ ታነባለህ፤ ከእናንተ ሌላ ሰብሳቢ ለሌላቸው፣ የእናንተን ፍቅርና መግቦት ተስፋ አድርገው ከእናንተ ለተወለዱ የአብራካችሁ ክፋዮች፣ ህያው አለመሆናችሁን ስታስቡት ሰቀቀኑ ያንገላታችኋል፤ ፍቅር ያሰቃያችኋል፡፡ ፍቅርን ከአልበርት አንስታይን አንፃራዊነት ንድፈ ሃሳብ ጋር፣ ከእሾ የፍቅር ምልከታ ጋር እና ከፕሌቶ ሁለንተናዊነት (universals) ጋር ለንቁጣችሁ ብትመለከቱት እጅግ ትደነቃላችሁ፤ በርግጥም ፍቅር ገና ያልተዳሰሰ ብዙ ሚስጢራዊ ገጽታ እንዳለው ትደርሱበታላችሁ፡፡ እናም አሁን እኔ ይሄንን የፍቅር ህብረትና ሚስጥር ላሳያችሁ ተጣድፌያለሁ፡፡ ሆኖም ግን ይሄንን ጽሑፍ ለመረዳት የአንስታይንን "አንፃራዊነት" እና የፕሌቶን "ሁለንተናዊነት" በትንሹም ቢሆን ግንዛቤ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡ ፍቅርና ፊዚክስ ምን ያገናኛቸዋል? እንዳትሉኝ። እንደዚህ አይነት ጥያቄ የፀሐይ ብርሃን ከሕይወት ጋር ምን ግንኙነት አለው ብሎ እንደመጠየቅ ነው፡፡ ሕይወት ከቁስ ስለመሰራቱ ሳይንሳዊም ሆነ ሀይማኖታዊ ድጋፍ ኣለው፡፡ አዳም ከአፈር፣ ሄዋንም ከአዳም መሰራታቸውን ማወቃች፣ ስለፍቅር ጾታዊና ግልብ የሆነ አመለካከት ይዘን እንድንቆይ አድርጎናል። ፍቅርን ከፊዚክስና ከሁለንተናዊነት ጋር ያለውን ግንኙነት እንዳንገናዘብ አዘናግቶናል፡፡ አስገራሚ የሚያደርገው አዳም ከአፈር ተፈልቅቆ መሰራቱ ሳይሆን ቁስ ወደ ሕይወት ሲሸጋገር መርሆዎችም አብረው መሸጋገራቸው ነው፡፡ ቁስ ወደ ህይወት ሲሸጋገር ቁስን ሲገዛ የነበረው መርህና ሕግ ሕይወትን መግዛት ጀመረ፡፡ ግራቪቲን፣ ኤሌክትሮ ማግኔቲዝምንና የቅራኔ ህግን እንደምሳሌ መውሰድ እንችላለን፡፡ የእነዚህ ቁሳዊ ሕጎች ተጽእኖ ሕይወት ድረስ ዘልቆ የገባ ነው፡፡ ተቃራኒ የኤሌከትሪክ ሙሌቶች (Charges) እንደሚሳሳቡት ሁሉ ተቃራኒ ዋልታዎችም እርስበርስ እንደሚፈላለጉት ሁሉ፣ ከቁስ የተሰራሁ ሕይወትም ይህንን ሕግና ባሕሪ ወርሷል፤ "አጥንትሽ ከአጥንቴ፣ ደምሽም ከደሜ ነውና የኔ ነሽ!" የሚለውን ሕይወታዊ (የፍቅር) ህግ ቋንቋና ስሜት ዘራንበት እንጂ መርሁን የወሰድነው ከተቃራኒ መግነጢሳዊ ዋልታዎችና የኤሌክትሪክ ሙሌቶች ባህሪ ነው፡፡ ወንዶች የስፐርም ህዋሶቻቸውን ባህሪ እንደወረሱት ሀሉ፣ ሴቶችም የእንቁላላቸውን ባህሪ እንደሚያንፀባርቁት ሁሉ፣ ሕይወትም የተሰራበትን ቁሳዊ ህግና መርህ ያንፀባርቃል፡፡ ቁሳዊ ሕግጋት ፊዚክስን ሲወልድ፣ የህይወት ህግጋት ደግሞ ባዮሎጂን ፈጥሯል፡፡ ባዮሎጂም ወደ ሌሎች ማህበራዊ ሳይንስ ዘርፎች ተመንዝሯል፡፡ የኬሚስትሪ ሕጎች ከፊዚክስ ህጎች እንደሚመነጩ ሁሉ፣ እንዲሁም የባዮሎጂ ህግጋት ከኬሚስትሪ ሕግጋት ይመነጫሉ። ሰነልቦናዊና ማህበረሰባዊ (sociological) መርሆዎችም ከባዮሎጂካዊ ሕግጋት እንደሚመነጩ እርግጥ ነው፡፡ እናም ሕይወት ላይ ፊዚክሱ፣ ኬሚስትሪው፣ ሳይኮሎጂውና ሶሲዮሎጂው ሚስጢራዊ ህብረት አላቸው፡፡ እስኪ ከዚህ እንጀምር፤ ያፈቀረ ሰው ክብደቱ ስንት ነው? ሚዛን ላይ ብታስቀምጡት ስንት ኪሎ ግራም ይመዝናል? ስታፈቅርና ሳታፈቅር ክብደትህ የተለያየ ይሆን!? በሌላ አነጋገር ፍቅር ክብደቱ ስንት ነው? ነው ወይስ ፍቅር ክብደት የለውም! ምንድነው ታዲያ 400 ፍቅር 300 ትዝታ? ግን እኮ የማይጨበጠውና የማይዳሰሰው ኢነርጂ ክብደት እንዳለው ብንደነግጥም አንስታይን ነግሮናል (energy has mass) ስለዚህ ፍቅርም ክብደት ይኖረው ይሆናል! ማን ያውቃል፤ እንዲያውም እንቅልፍ ራሱ ክብደት ሳይኖው አይቀርም! እና ምን አላችሁ? ያፈቀረ ሰው ክብደቱ ስንት ነው? የራሱና የፍቅረኛው ክብደት ድምር ነው እንዳትሉ፣ ፍቅረኛው ግዝፈቷን አጥታ ትዝታ ብቻ ሆናለች፡፡ ክብደቱ የሰውየው የራሱ ብቻ ነው እንዳትሉ ደግሞ ፍቅረኛው በልቡ ውስጥ ሆና ከቦታ ቦታ ትዘዋወራለች፡፡ "እስከ አሁን..." ይላል ኦሾ፣ "እሰከ አሁን መንገደኛን የሚያጓጉዙ ሁሉ፤ ሰዎች በሌላው ልብ ውስጥ ተደብቀው እንደሚጓዙ አልደረሱበትም።" እናም ፍቅር ያለ አንዳች ቲኬት በሰው ልብ ውስጥ ሆናችሁ ከቦታ ቦታ እንድትጓዙ አስችሏችኋል፡፡ ቁስ ግዝፈቱን ሲያጣ ኢነርጂ እንደሚሆነው ሁሉ፣ ፍቅርም የሰውን ግዝፈት ዋጋ ያሳጣዋል፣ የራስ ኩራትንም ያስጥላል፡፤ ቁስ ግዝፈቱን ሲያጣ ወደ ብዙ ኃይልነት እንደሚለቀቀው ሁሉ፣ ሰውም ግዝፈቱን ጥሎ ወደ ፍቅር ሲሰየም የበረታ ኃይል ይሆናል፡፡ እናም በዚህ ሀይል መላው አካል ይንቀሳቀሳል፤ ውስብስቡ ባዮኮምፒውተር (አእምሮ) ይታዘዛል። ምንጭ ፦ ፍልስፍና ፩ ፀሀፊ ፦ ብሩህ አለምነህ @ethioterkaa @ethioterkaa @ethioterkaa ✍ይቀጥላል✍

ታላቅ ምክር ለአዲሱ ትውልድ.pdf1.26 MB

🌿#ወረት ...ወረት ማለት ይሄ ነው... ወረት ማለት በማመን ውስጥ ያለ የመርሳትን ነገር የሚያመቻች ነገር ነው #ወረት... ለምሳሌ አንተ ይህን የምታነብ ሆይ በእውነት telegram,facebook ወ.ዘ.ተ ካለነዚህ መዋል የማትችል የሚመስልህ ወይም ለህዋ አውታር ፍቅር አለኝ የምትለው እንደዚህ ሲዘጋ ምን ሆንክ? ምንም ምክንያቱም ፍቅርህ #የወረት ነበራ... እሺ አንዳንዶች የስሜት ተገዢ የኳስ አፍቃሪዎች ኳስ ሲቀር ምን ሆኑ?? ምንም ስለዚህ ይህም #ለወረት ነበር... ዳሩ ግን ትልቁ ምሳሌ በእናት ይመሰላል፡፡ ምጥ የያዛት ሴት ስቃዪዋ የሚታመን በመሆኑ ምናልባት ልጁ እስኪወለድ ድረስ ነው ለዚህም ነው 'ምጡን እርሺው ልጁን አንሺው' የሚሉት አበው... እናም ሁሉም የሚታመኑ ነገሮች #ለወረት ናቸው... ነገር ግን ማመን ያቃቱን ስቃዮች እድሜ ልክ ናቸው ምናልባት ከዛም በላይ ሁሌም የሚኖሩ በወረት የማይረሱ ፡ የማይሽሩ...." •• ◉ Join us share◉●•• ═════❥━━━❥═════ 🌾ነገ መልካም ይሆናል ! 🌾 🇪🇹ኢትዮ መፅሀፍት እና ትረካ 🇪🇹 🎖 @ethioterkaa 🎖 🎖 @ethioterkaa 🎖 🎖 @ethioterkaa 🎖

💚💛❤️ዉበቷ ለሐገሬ ንብረቷ!💚💛❤️ 💛 ይኸዉልህ ወዳጄ ___እንደዚህ ነዉ ዉበት ምላጭ በቅንድቧ___ ክርክም ሳያርፍባት። 💛 ፊት ገፆን___ሳይነካዉ ቀለመ ቀለማት። ፀጉሯን ሳተኩስ___በኤሌ
💚💛❤️ዉበቷ ለሐገሬ ንብረቷ!💚💛❤️ 💛 ይኸዉልህ ወዳጄ ___እንደዚህ ነዉ ዉበት ምላጭ በቅንድቧ___ ክርክም ሳያርፍባት። 💛 ፊት ገፆን___ሳይነካዉ ቀለመ ቀለማት። ፀጉሯን ሳተኩስ___በኤሌክትሪክ ብረት።💛 የአንገቷ ዙሪያ___ወርቅ እና አልማዝ ንቆ ፣ የብሩ ሐብሏ___ደረቷ ላይ ወድቆ፣ የነሐሱ ብረት___በጆሮዋ ጠልቆ። ❤️ ዞማዋን ሳትለቀዉ___በሻሿ ጠፋፍራ፣ ደም የተነከረ___ ሳይመስል ከንፈሯ፣ ሳይዶለዘበት ምርግ___ከጥፍሯ። ሳይርከፈከፍባት__የናርዶሱ ሽቶ፣❤️ የተፈጥሮን ጠረን__ ፈጣሪ ቀብቶ። ❤️ በሰዎቹ መሐል__አብርታ የታየች፣ ብላቹ አጠይቁ___ይህች ልጅ የማን ነች? ❤️ የዉሸት ፈገግታ___ የማታዉቀዉ ልጅት፣ የአገዋ እመቤት___የሐገሬ ወርቅ ናት። ብዙ ብዙ ሰዎች__ሚስጥር ሲጠይቁ፣ ከእርሷ ጋር ለመኖር__ለወግ እንዲበቁ።❤️ የጥሎሹን ነገር__ስለማወቅ ሽተዉ፣ ተመልሰዉ ሄዱ__መዋቢያዋን አጥተዉ።❤️ ሐገር እንደዚህ ናት__ በራሷ ያማረች፣ በፈረሠኛዉ እጅ__በተሠራ ኩታ የተንቆጠቆጠች፣ ከዉድ አልማዝ ይልቅ__የሚያጎመሯት ያንጥረኛ ጣቶች።🥰 እንደዚህ ናት ህይወት__ የግዜር ድንቅ ስራ፣ በጨለማ መሐል__ሁሌም ምታበራ። አንገትህ ሲደፉ ሐገርህ ስትከሳ __ መከራ በዝቶበት፣ ነገህን የሚያሳይድንቅ ሚስጥር አለዉ ያንዳንድ ሰዉ ዉበት። ❤️❤️❤️❤️❤️💛💛💛💛💛💚💚💚💚 ❤️❤️❤️❤️❤️💛💛💛💛💛💛💚💚💚 🥰 ቻናሉን ከወደዳችሁት like እና share በማድረግ ለጓደኞቻችሁ እንድታጋሩ በአክብሮት እንጠይቃለን🙏🙏🙏🙏🙏 ሼር@ethioterkaa @ethioterkaa @ethioterkaa

🔓🔓🔓ኢትዮ መፅሃፍት እና ትረካ🔓🔓🔓🔓🔓 ዘነበ በአንድ አካባቢ ችፍግ ብለው ተቀራርበው ከሚገኙት ቤቶች በአንዱ አፓርትመንት ውስጥ ከስድስት ጓደኞቹ ጋር ደባል ሆኖ መኖር ከጀመረ ድፍን ሦስት ዓመታትን አሳልፏል። እነ ዘነበ (ዘነበ የሚለው ለዚህ ጽሁፍ የተሰጠው ስም ነው) ተከባብረው ተዋደው በፍቅር ሲኖሩ ነበር። ያች ቀን ግን ለዘነበ መጥፎ አጋጣሚ ነበረች። ቀኑ ሰኞ ነበር። ለወትሮው ከደባሎቹም ቀድሞ የሚነሳው ዘነበ ፣ ከስራ ባልደረቦቹ ቀድሞ ቢሮ የሚገባው ዘነበ ዛሬ ግን ቅዠት ከበዛበት ህልሙ የባነነ ከረፋዱ 3:00 ላይ ነበረ ። ተቻኩሎ ወደስራ ሊሄድ እየተዘጋጀ ባለበት አንድ መጥፎ ነገር ከመንገዱ ገታው .. አደገኛ ሽታ አፍንጫን የሚነቅል መጥፎ ሽታ። ዘነበ አለመናገር አልቻለም "ምንድነው የሚሸተኝ " አላቸው ጓደኞቹን ። ጓደኞቹ ራሳቸውን ፈተሹ ያገኙት ነገር የለም ግን ይሸታቸዋል። "የእኛም ጥያቄ ነው " አሉት ። ዘነበ ቤቷን በአንድ እግሯ አቆማት .. የሚሸተውን ነገር ለማግኘት እቃውን እያነሳሳ ፍራሹን ሳይቀር በረበረ ምንም ሊያገኝ አልቻለም ሽታው ግን አለቀቀውም።በሁሉም ቦታ ሲበረብር ሽታው ይሸተዋል የሸተተውን ነገር ሊያገኝ ግን አልቻለም ተናደደ። ምንም እንኳን ለዘመናት በፍቅር አብረውት የኖሩ ጓደኞቹ ቢሆኑም አላመናቸውም ተናደደ ..ብሎም ሰደባቸው "ግማታሞች" አላቸው ። እነሱ ግን ፈትሸን አሉትና ዘነበ ሁሉንም ፈተሻቸው ። ነገርዮውን ቢያጣውም ሽታው አለቀቀውምና እያጉተመተመ ተራግሞ ወጣ "ምኑ ግማታም ቤት ነው በፈጣሪ .." ዘነበ ከቤት ወጥቶ ጉዞ ቢጀምርም ሽታው አሁንም አፍንጫውን እየሰነፈጠው ነው ። ፊትለፊት ያገኘውን የእትዬ በለጡን ቤት ሊያረጋግጥ ወደ በሩ ሲጠጋ ባለፈው ከእግሩ ጅማት የቦተረፈለት ውሻ ምላሱን ሁለት ሜትር ጎልጉሎ ሲያፈጥበት ዘነበ ሆዬ ውሻውን በዐይኑ ገረመመውና ረግሞት አለፈ.."አንተ ትሆናለህ ይሄኔ ታጥበህ የማታቅ ግማታም ውሻ ..ደግሞ በላኸኝ አይደል!" ዘነበ ወደቢሮ እየሄደ ታክሲ ውስጥ ሆኖ እንኳን ሽታው አለቀቀውም "ወራጅ "አለ መውረጃው ሳይደርስ ሽታው ትዕግስቱን አሳጥቶታል። ወርዶ ሲጓዝ ሽታው አሁንም አለቀው ሲል አንድ ነገር ደመደመ "በቃ ይህቺ ዓለም ገምታለች!" አለ። ወዲያው ከኋላው አንድ ህጻን ልጅ መጥቶ "ጋሼ የዳቦ ቦጭቅልኝ እስኪ" አለው። "የግማታም ልጅ በአንዱ ኮብል እንዳልቦጭቅህ" ዘነበ በንዴት ጡፎ ኮብልስቶን ሊያነሳ ቢፈቅድ በማጣቱ "ሰሞኑንስ ምነው አስፓልቱን አልቆፈሩትም እንዴ ለምርጫው ቆጥበውታል ማለትነው" ብሎ ቀና ሲል ህጻኑ እየሮጠ "ጋሼ ጋሼ ጫማህ ላይ ሌላ ኮብል አለ ካጣህ እሱን አንሳው " እያለ ቁልቁል ሮጠ። ዘነበ ጫማውን ሲመለከት የህጻን ልጅ የምታክል ዐይነ ምድር በጫማው ስር አገኘ። ዘኔ ደነገጠ #መልእክቱ ፦ ችግራችንን በሌሎች ላይ ከማላከካችን በፊት ወደራሳችን እንመልከት ........💐💐ሰላም በምድራችን ላይ ይስፈን 💐💐........፤ ቻናሉን ከወደዳችሁት like እና share በማድረግ ለጓደኞቻችሁ እንድታጋሩ በአክብሮት እንጠይቃለን🙏🙏🙏🙏🙏 ሼር@ethioterkaa @ethioterkaa @ethioterkaa ሃሳብ፣ጥያቄና አስተያየቶቻችሁን ፦ @janoooooom አድርሱን።

በሚመለከተን ነገር ላይ ብቻ እናተኩር ብሪታኒያ ውስጥ ነው፤ አንዲት ሴት አውራ-ጎዳና ላይ እርቃኗን ስትንጎራደድ ትቆይና መንገድ ዳር ቆመው ተሳፋሪ ከሚጠብቁ ታክሲዎች ወደ አንዱ ዘው ብላ ትገባለች። የገባችበት ታክሲ ቻይናዊ ሹፌርም ግራ በመጋባትና በመገረም ከራስ ፀጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ በጥያቄ ስሜት መላልሶ ማየት ይጀምራል። አጅሪት ግን ምንም ያልተፈጠረ በማሥመሰል መሄድ የምትፈልግበትን ተናግራ እንዲንቀሳቀስ በዓይኗ ምልክት ትሰጠዋለች። ቻይናዊው ታክሲ ሹፌር ግን ያልተመለሠለት ጥያቄ ነበርና አሁንም ከእግር እስከራሷ መላልሶ ማየቱን ይቀጥላል። ይኼኔ ቆንጂት በሷ ብሶ በስጨት እንደማለት እያደራረጋት "ልብስ ያልለበሰች ሴት አይተህ አታውቅም? ብላ ታፈጥበታለች። ቻይናዊው ባለታክሲ ግን እንዲህ በማለት በትህትና መለሠ "የኔ እህት እኔ ግራ ተጋብቼ የማይሽ እርቃንሽን መሆንሽ ገርሞኝ ሳይሆን ለአገልግሎቴ ልትከፍይኝ የሚገባኝ ገንዘብ የቱጋ እንዳለሽ ጥያቄ ስለሆነብኝ ነው።" ✍️ አየህ ወንድሜ በዚህች ዓለም ስትኖር ልክ እንደቻይናዊው ታክሲ-ሹፌር ማተኮር ያለብህ ስለሚመለከትህ ጉዳይ ብቻ ነው። ስለማያገባህ ጉዳይ ስትፈተፍት በመዋልና በማደር በራስህ ህይወት ላይ የምትጨምረው ምንም ዓይነት ጠቃሚ ነገር የለም። አቅምህ እስከቻለው ለሌሎች መልካምን አድርግ የሌሎችን ግላዊ ህይወት ግን ለባለቤቶቹ ተውላቸው። 💚💛❤️ 💚 💚 💛 💛 ❤️ 💚💛❤️ ❤️ ........💐💐መልካም ምሽት 💐💐........ ቻናሉን ከወደዳችሁት like እና share በማድረግ ለጓደኞቻችሁ እንድታጋሩ በአክብሮት እንጠይቃለን🙏🙏🙏🙏🙏 ሼር@ethioterkaa @ethioterkaa @ethioterkaa ሃሳብ፣ጥያቄና አስተያየቶቻችሁን @janoooooom አድርሱን። @ethioterkaa @ethioterkaa