SCHOOL OF MARVEL- ASELLA
Open in Telegram
KG => @marvel_KG Grade 1 @marvelG1 Grade 2 @marvelG2 Grade 3 @marvelG3 Grade 4 @marvelG4 Grade 5 @marvelG5 Grade 6 @marvelG6 Grade 7 @marvelG7 Grade 8 @marvelG8 Grade 9 @marvelG9 Grade 10 @marvelG10 Grade 11 @marvelG11 Grade 12 @marvelG12
Show more5 726
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-1030 days
Posts Archive
#Waamicha barattoota haaraa bara 2019 ramadmtanii fi bara 2018 sagantaa fooyyeffannaa hordofaa turtanii qabxii darbinsaa galmeessiftaniif
#ጥሪ ለ2019 ዓ.ም. የተመደባችሁ ተማሪዎችና በ2018 የአቅም ማሻሽያ ትምህርት ስትከታተሉ ለነበራችሁና የማለፊያ ውጤት ላስመዘገባችሁ።
#Call for Freshman of 2019 E.C and Remedial of 2018 E.C who have scored sufficient results to continue their education
Like Our Star Athletes, Excelling Professionals!
#MaddaWalabuUniversity
በ2019 ዓ.ም በመደበኛ መርሐግብር መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፦
በዩኒቨርሲቲው ዋና ካምፓስ
ትምህርት ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ፋይዳ መታወቂያ (National ID)፣
● ከ8-12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
● ጉርድ ፎቶግራፍ፣
● ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
በ2019 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#WerabeUniversity
1ኛ) ከትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የ1ኛ አመት ተማሪዎች በሙሉ
2) በ2018 ትምህርት ዘመን የሪሜዲያል ፕሮግራም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ አጠናቃችሁ የማለፊያ ነጥብ ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
✔️ ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 16 እና 17/2019 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በተራ ቁጥር 1 የተገለጻችሁ ተማሪዎች
🟢የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ክልላዊና በሔራዊ ፈተና ሰርተፍኬት እና ከ9ኛ -12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ኦርጂናልና አንድ የማይመለስ ኮፒ መያዝ ይኖርባችኋል
🟢 በተለያየ ምክንያት በ1ኛ አመት 1ኛ መንፈቅ የመልሶ ቅበላ ሞልተው የወጡ የመጀመሪያ ዲግሪ የመደበኛ መርሐ ግብር ተማሪዎች ጥቅምት 19/2019 ሪፖርት ማድረግ ይኖርባቸዋል።
🟢 ጥቅምት 18/2019 የቅጣት ምዝገባና መማር ማስተማር የሚጀምር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
#AssosaUniversity
በ2019 ዓ.ም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 16 እና 17/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
#BuleHoraUniversity
በ2019 ዓ.ም ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 16 እና 17/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#WolkiteUniversity
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የፍሬሽማን ተማሪዎች እና በ2018 ሪሜድያል ተምራችሁ ያለፉችሁ ተማሪዎች
የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 9 እና 10 2019 ዓ.ም መሆኑን እሳውቋል።
#DebreBerhanUniversity
በ2019 ዓ.ም ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 11 እና 12/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ከጥቅምት 13-15/2019 ዓ.ም ልዩ ስልጠናና ኦሬንቴሽን የሚሰጥ ሲሆን፣ ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም ትምህርት ይጀመራል ተብሏል፡፡
የ2018 ሪሚዲያል ትምህርት በዩኒቨርሲቲው ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ትምህርቱን ስትከታተሉ በነበረበት ካምፓስ እንደሆነ ተገልጿል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ የለሊት ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
#InjibaraUniversity
በ2019 ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 12 እና 13/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ፣
● አንሶላ፣ የለሊት ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
በ2019 ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ትምህርት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ወደፊት በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡
#WallagaUniversity
በ2019 ዓ.ም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
በ2019 ትምህርት ዘመን ለሪሚዲያል ትምህርት ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደ ፊት በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡
የምዝገባ ቦታ፡-
● በ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በዋናው ግቢ ነቀምት ካምፓስ፣
● በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ማለፊያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ስትማሩበት በነበረው ካምፓስ
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ የለሊት ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
#DireDawaUniversity
በ2019 ዓ.ም ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 07 እና 08/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
● አንሶላ፣ የለሊት ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
በተለያዩ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ጥቅምት 10 እና 11/2019 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
#DambiDolloUniversity
በ2019 ዓ.ም ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ትምህርት ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ስድስት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የአልጋ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
በ2019 ዓ.ም ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።
#JigjiggaUniversity
በ2019 ዓ.ም ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እና የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 9-11/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
● አራት የቅርብ ጊዜ ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የአልጋ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
https://portal.jju.et/biography ላይ በመግባት ከላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች እና አንድ የመታወቂያ ፎቶ የአድሚሽን ቁጥራችሁን በመጠቀም ማስገባት ይጠበቅባችኋል።
@
#WoldiaUniversity
በ 2018 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እና በ 2019 ዓ.ም አዲስ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች
✔️ የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#wolaitasodouniversity
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን የፍሬሽማን ተማሪዎች እና በ2018 ሪሜድያል ተምራችሁ ያለፉችሁ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት 9 እና 10 መሆኑን እሳውቋል።
ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማያስተናግድ መሆኑን ገልፆል።
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#MattuUniversity
በ2019 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ መቱ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች (Freshman) እና በ2018 ዓ.ም በመቱ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች፤
✔️ ምዝገባ የሚካሄደው ጥቅምት 9 እና 10/2019 ዓ.ም
ማሳሰቢያ
በ2018 ዓ.ም. በበደሌ ካምፓስ በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁና በ2019 ዓ.ም. በትምህርት ሚኒስቴር ተመድባችሁ ስማችሁ በፊደል A-B የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስና የማኅበራዊ ሳይንስ ስትሪም ተማሪዎች፣ ምዝገባችሁ የሚካሄደው በበደሌ ካምፓስ መሆኑን እናሳስባለን።
የሌሎች ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው በዋናው ግቢ ይሆናል።
ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ
• ብርድ ልብስ፣ አንሶላና የትራስ ልብስ፣
• የስፖርት ልብስ፣
• ከ8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ኦሪጅናልና ኮፒ፣
• ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda National ID)፣
• መጠኑ 3x4 የሆነ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ ይዛችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን።
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#Arbaminchuniversity
በ2019 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ እና በ2018 ዓ.ም የማካካሻ (Remedial) ትምህርት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች የቅበላ ቀን ረቡዕ ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም፣ የምዝገባ ቀናት ሐሙስ እና ዓርብ ጥቅምት 5 እና 6/2019 ዓ.ም፣ ትምህርት የምጀመረው ቀን ሰኞ ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በዚህ መሠረት በ2018 ዓ.ም የማካካሻ (Remedial) ትምህርት በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በመከታተል የማለፊያ ውጤት 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በ2018 ዓ.ም የማካካሻ (Remedial) ትምህርት በተማራችሁበት ካምፓስ እንድሁም በ2019 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ቀጥሎ የተመለከተውን ሊንክ በመጫን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መለያ ቁጥር በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ በምደባው መሠረት ኩልፎ (Kulfo Campus)፣ አባያ (Abaya Campus)፣ ጫሞ (Chamo Campus)፣ እና ዋናው ግቢ (Main Campus) የተመደባችሁ ተማሪዎች በአርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙ ኩልፎ፣ አባያ፣ ጫሞ፣ እና ዋናው ግቢ ካምፓሶች፣ ሳውላ ካምፓስ (Sawula Campus) የተመደባችሁ ተማሪዎች ደግሞ በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ ሬጂስትራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በአካል እየቀረባችሁ ሪፖርት እንዲታደርጉና ምዝገባ እንዲትፈጽሙ እናሳውቃለን፡፡
ሊንክ፡- https://smis.amu.edu.et/pages/check_campus_placement
ማሳሰቢያ፡-
1ኛ) ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርቴፍከት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ እንድሁም የፋይዳ መታወቂያ ካርድ፣ አንሶላ፣ ትራስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡
2ኛ) ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም
#WachemoUniversity
በ2019 ዓ.ም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ቦታ፦
በ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ (Freshman) ተማሪዎች
● ስማችሁ ከ A-M ዋናው ግቢ - ሆሳዕና
● ስማችሁ ከ N-Z ዱራሜ ግቢ - ዱራሜ
በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የሪሚዲያል ትምህርት በተከታተላችሁበት ካምፓስ
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● ስድስት 3X4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● የፋይዳ መታወቂያ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፡፡
በ2019 ዓ.ም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት በሌላ ማስታወቂያ ይገለጻል ተብሏል፡፡
