en
Feedback
አ/ጎ/ት/ቤት ቁ.4

አ/ጎ/ት/ቤት ቁ.4

Open in Telegram

ይህ የቴሌግራም ቻናል አቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት አዳማ ቅርንጫፍ የተለያዩ መረጃዎችንና መልዕክቶችን ለወላጆች ተደራሽ የሚያደርጉበት ነው።

Show more
665
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ !!

ውድ የልጆቻችን ወላጆች !! እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ !!

በክልላችን የተለያዩ አካባቢዎች በድርቅና በጦርነት የተጎዱ ወገኖችን ለማገዝ ከNur. - 3ኛ 26 ብር ከ4ኛ - 8ኛ ክፍል 50 ብር በተማሪዎች እንዲዋጣ ት/ቢሮ መመሪያ አስተላል።በዚሁ መሰረት ከነገ ህዳር 12/2015 ዓ.ም ጀምሮ እንድትከፍሉ አናሳስባለን።

ለ6ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች በሙሉ !! በያዝነው የትምህርት ዘመን/2015 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና ይወስዳሉ የሚል መረጃ ከትም/ቢሮ በቅርቡ ደርሶናል::ስለሆነም የተሻለ ውጤት ይመዘገብ ዘንድ ወላጆች አስፈላጊውን ሁሉ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ከጎናችን ትሆኑ ዘንድ ከወዲሁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን !!!

የ2015 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ዛሬ መስከረም 16 ቀን 2015 ዓ.ም በአማረ መልኩ ተጀምሯል !!

እንኳን ለ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን !!

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ !!

ወድ የአቡነ ጎርጎርዮስ ወላጆች ሰላም ለእናንተ ይሁን እያልን ትምህርት ሰኞ በ21/03/2013 ዓ.ም ስለሚጀመር ተማሪዎችን በተመደቡበት ፈረቃ መሰረት እንድትልኩልን እያሳሰብን ለአንድ ሳምን(21-26/03/2013) ት/ት እስከ 6:30' ድረስ መሆኑን እናሳውቃለን። መረጃ ለሌሎች በማድረስ ይተባበሩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን !!

photo content

photo content

ቀን 21/12/2012ዓ.ም ለትምህርትቤታችን ወላጆችና አሳዳጊዎቹ በሙሉ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ በቅድሚያ የማክበር ሠላምታችንን እያቀረብን የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ በሁሉም የክፍል ደረጃዎች ( ከጀማሪ እስከ 8ኛ) ክፍል ከሰኞ ማለትም 25/12/2012 ዓ.ም እስከ 29/12/2012 ዓ.ም ድረስ ምዝገባ ስለሚካሄድ አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ተማሪዎችን ( ልጆቻችሁን) በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ብቻ እንድታስመዘግቡ በትህትና እናሳውቃለን። ማሳሰቢያ፨፨፨፨፨፨፨፨ _ከላይ በተጠቀሰው ቀናት ውስጥ ባልተመዘገቡ ተማሪዎች ቦታ አዲስ ተማሪ የምንቀበል መሆኑን ከወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለለን። _ለምዝገባ ሲመጡ የመመዝገቢያና የአንድ ወር ክፍያ ይዘው መምጣት ይጠበቃል። _የጀማሪ ( ነርሰሪ )ተማሪ 2 ጉርድ ፎቶና የወላጅ 1 ጉርድ ፎቶ የወሳኝ ኩነት ካርድ ( የክትባት ካርድ ) ይዘው መምጣት ይኖርባችኃል _የምዝገባ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00-6፡00 ከሰዓት ክ 8፡00-10፡30 ድረስ ብቻ ነው።

photo content

ሰላም ወላጆች ! ተማሪዎች ! እንዴት ናችሁ ? የሞዴል ፈተናው በወጣው በመርሃ ግብር መሰረት በመልካም ሁኔታ እየቀጠለ ስለመሆኑ ወላጆች በፎቶ የተደገፈ መረጃ አድርሳችሁናል ከልብ እናመሰግናለን።እኛም መልሰን ለወላጆች እና ለተማሪዎቻችን ከፊሉን እንሆ ብለናል።

photo content

photo content

ሰላም ወላጆች እንዴት ናችሁ ? የሞዴል ፈተናውን በአግባቡ እየፈተናችሁ ስለመሆኑ ሙሉ እምነት አለን፤ምስጋናችንም ከልብ ነው። ቀጥሎ የቀረበው ፎቶ የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ሞዴል ፈተና በየቤታቸው ሲፈተኑ የሚያሳይ ነው።ፎቶውን በመላክ የተባበራችሁን ወላጆች እናመሰግናለን።

photo content

Share 'English Lab Grade 3.pdf'

ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በሒሳብ የቪዲዎ ትምህርት በ36 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ ላይ sin 45 የሚለዉን tan 45 በማለት እናም በተሰጠዉ ወይም given ላይ ተመሥርታችሁ እንድታሰሉ የሒሳብ መምህራቹ ያሳስባል !! ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን !!

photo content