cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

❤️ዕፀ ፍህሶ ወዕፀ መአዛ❤️

የአባቶች ጥበብ ይተነተንበታል ። 🔰የቀደምት አባቶቻችንን እውቀት እና ጥበብ ሳይበረዝ እንደወረደ ይቀርባል። የአያቶቻችን የእጽዋት ጥበብ ፣ በህይወትዎ ላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮችና መፍትሔዎቻቸው ፣ ክፉ መናፍስትን እንዴት ማራቅ እንደምንችል🦅፣ የብራና መጽሐፍት እና ጥቅማቸው በዚ ይዳሰሳሉ። ➫የተለያዩ መድሀኒቶችን ➫ለተለያዩ በሽታ መፍትሄ ➫የተለያዩ የብራና መፅሀፍት @fihsoBot

Show more
Advertising posts
953
Subscribers
No data24 hours
-97 days
-4130 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሰላም ቤተሰብ እንደምን አመሻችሁ!!! ነጭ አብሹ የሚፈልግ በተመጣጣኝ ዋጋ እኔ ጋር ማግኘት ይችላል!! @fihsobot ላይ ታገኙኝ አላችሁ @etsemeaza
Show all...
ለጥንቃቄ !!! በፋብሪካ የተቀነባበሩና የታሸጉ፣ ጤናማ ያልሆኑ ምግቦች ወደ ሃገራችን በብዛት በመግባት ላይ ይገኛሉ ፣ እነዚህን ምግቦችና መጠጦች አዘውትሮ በመውሰድ  የሚከሰቱ ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች እየጨመሩ ነው። በፋብሪካ የተቀነባበሩ ከፍተኛ ጨው፣ ስኳር፣ የሚረጋ ዘይትና ቅባት  ይዘት ያላቸው ሃይል ሰጪ መጠጦችንና ምግቦችን አዘውትሮ  መመገብ  በጤና ላይ ከፍተኛ  ጉዳት ያስከትላል ።   ከልክ  በላይ ለሆነ ውፍረት፣   ካንሰር፣   ልብ ህመም፣   ስትሮክ፣   ዓይነት 2 የስኳር ህመም ያጋልጣሉ።  የእነዚህ ጤናማ ያልሆኑ ምግቦችና መጠጦች  ሰፊ አቅርቦት ወይም በገበያ ላይ እንደልብ መገኘት ፣ እና ልቅ ማስታወቂያ  በብዛት እንዲሸመቱ አድርጓቸዋል። #ከዳጉ ጆርናል የተወሰደ
Show all...
ለክረምት ፮ኛ እሑድ (ከሐምሌ ፲፮ - ፳፫) ❖ መዝሙር፦ «በቀዳሚ ገብረ እግዚአብሔር ሰማየ ወምድረ ወኵሎ ፈጺሞ አዕረፈ በሰንበት ወይቤሎ ለኖኅ አመ አይኅ ግበር ታበተ በዘትድኅን። አነ አቀውም ኪዳንየ ዘምስሌከ ለዓለም። ከመ ዳግመ ለምር ኢያማስና በአይኅ። ከመ አሀባ ለምድር ሣዕረ ሐመልማለ ክረምተ ወሐጋየ ዘርዓ ወማዕረረ። ዝኬ ውእቱ ጸጋሁ ለእግዚአብሔር። በአማን ኢይኄሱ ቃሎ ዘነበበ። ትርጉም፦ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረና ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሰባተኛው ቀን አረፈ። በማየ አይኅ ጊዜ ኖኅን የምትድንበትን መርከብ ሥራ አለው፡፡ ዳግምም ምድርን በንፍር ውኃ እንዳላጠፋት ለምድር ሣርንና ልምላሜን፣ ክረምትና በጋን፣ ዘርንና መከርን እስጣት ዘንድ ለዘለዓለም ኪዳኔን ከአንተ ጋር አጸናለሁ አለው፡፡ የተናገረውን ቃል አያስቀርምና በእውነት ለኖኅ የሰጠው የእግዚአብሔር ስጦታ ይህ ነው። ፨ በላይ ቤት (ዘቤተልሔም)፦ «አርውዮ ለትለሚሃ ወአሥምሮ ለማዕረራ ወትባርክ አውደ ዓመት አዝዞሙ ለደመናት ያውርዱ ዝናመ ዲበ ምድር......» ✔ የዕለቱ የቅዳሴ መልእክታት፣ ምስባክና ወንጌል [✞] ... ✞ መልእክታት:- ፩ኛ☞ ወደ ቲቶ ፫ : ፩ - ፍ:ምዕ /3 : 1- ፍ:ም ፪ኛ☞ ፩ኛ ጴጥሮስ ፬ : ፮ - ፲፪ /4 : 6 - 12 ፫ኛ☞ የሐዋ/ሥራ ፳፰ : ፩ - ፲፯ /28 : 1-17 ✞ ምስባክ ያዐርግ ደመናተ እምአጽናፈ ምድር። ወገብረ መብረቀ ለጊዜ ዝናም። ዘያወፅኦሙ ለነፋሳት እመዛግብቲሆሙ። ትርጉም:- ከምድር ዳር ደመናትን ያወጣል፤ በዝናብ ጊዜ መብረቅን አደረገ፤ ነፋሳትንም ከመዛግብቱ ያወጣል። [መዝሙር ፻፴፬ : ፯ /134 : 7] ❖ ወንጌል ማርቆስ ፮:፵፯ - ፍጻሜ /6:47 - ፍ:ምዕ ፵፯ በመሸም ጊዜ ታንኳይቱ በባሕር መካከል ሳለች እርሱ ብቻውን በምድር ላይ ነበረ። ፵፰ ነፋስ ወደ ፊታቸው ነበረና እየቀዘፉ ሲጨነቁ አይቶ፥ ከሌሊቱ በአራተኛው ክፍል በባሕር ላይ እየሔደ ወደ እነርሱ መጣ፤ ሊያልፋቸውም ይወድ ነበር። ፵፱ እነርሱ ግን በባሕር ላይ ሲሔድ ባዩት ጊዜ ምትሐት መሰላቸውና ጮኹ፥ ፶ ሁሉ ዐይተውታልና፥ ታወኩም። ወዲያውም ተናገራቸውና። አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፥ አትፍሩ አላቸው። ፶፩ ወደ እነርሱም ወደ ታንኳይቱ ገባ፥ ነፋሱም ተወ፤ በራሳቸውም ያለ መጠን እጅግ ተገረሙ፤ ፶፪ ስለ እንጀራው አላስተዋሉምና፤ ነገር ግን ልባቸው ደንዝዞ ነበር። ፶፫ ተሻግረውም ወደ ምድር ወደ ጌንሴሬጥ ደረሱ ታንኳይቱንም አስጠጉ። ፶፬ ከታንኳይቱም ሲወጡ ወዲያው አውቀውት ፶፭ በዚያች አገር ሁሉ ዙሪያ ሮጡና እርሱ እንዳለ ወደ ሰሙበት ስፍራ ሕመምተኞችን በአልጋ ላይ ያመጡ ጀመር። ፶፮ በገባበትም ስፍራ ሁሉ፥ መንደርም ከተማም ገጠርም ቢሆን፥ በገበያ ድውዮችን ያኖሩ ነበር፤ የልብሱንም ጫፍ እንኳ ሊዳስሱ ይለምኑት ነበር የዳሰሱትም ሁሉ ዳኑ። ✞ ቅዳሴ - ዘኤጲፋንዮስ (ዐቢይ) - በግዕዝ ዜማ _____ @etsemeaza
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
#ታር_ይገማ 'እስመ ስም ይመርሖ ኀበ ግብሩ' ይሉሀል ይኼ ነው። በባላገሮች ድርሹት በሊቃውንቱ ደግሞ #ታሪገም (ታሪገማ) እየተባለ ስለሚጠራው ዕፅ ምን ያኽል ታውቃላችሁ... #ታምረኛው_ዕፅ ይህ አስደናቂ ዕፅ በተጨማሪም #ግሜ_ሐረግ በመባል ይታወቃል። ጥቅሙም በዋነኛነት፦ *ላበደ ልቡን ለነሳው ሰው *የሴት ዛር ላለበት ለሚፈራ ለሚደነግጥና በሕልመ ሌሊት ለሚፈትነው *ለመሠውር *ለመካን ሴት *ለመንድግ *የአራዊትን ቋንቋ ለማወቅ እንዲሁም ዘርዝሬ ለማልጨርሳቸው አያሌ ነገሮች ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን ከሌሎች ዕፆች ጋር ኆኖም በሚቀባ #አይነ_ጥላ ያስለቅቃል። (ወደ ሴት ሲቀርብ ብልቱ ለሚሞትበትና ለሚፈራ ሰው) ዕፁ በወይና ደጋ የሚገኝ ሲሆን በዋነኛነት በሽታው ይታወቃል ቅጠሉን በነኩት ጊዜ ከመጠን በላይ ይሸታል፤ ሴቴና ወንድም አለው። ጠቃሚዋ ሴቴዋ ናት። እንዳለመታደል ሆኖ ቅጠሉ ስላልደረሰልኝ ቅጠሉን ማየት አልቻላችሁም። ዕፁ በቀላሉ መገኘት ስለማይችል አንድ ወዳጀ ነው ከሩቅ ቦታ የላከልኝ። *** #ከታሪገም አያሌ ገቢሮች አንዷን ላጋራችሁ ደግሞ #Like_share ለማድረግ አትሳሱ ላይክ ሸር የምታደርጉ ከሆነ እኔም ቶሎ ቶሎ ለመፖሰት እነሳሳለሁ። የማጋራችሁ ጥበብ የአንደርብ መመለሻ ሲሆን ሰዎች እኩያን መናፍስትን በመጠቀም ቤታችሁን በድንጋይ ሊደበድቡት ወይም ደግሞ በእሳት ሊያጋዩት ወይም ደግሞ ቤታችሁን #ዓይነ_ምድር ካልሆነም አውሬ ሊሞሉት ይችላሉ። #መፍትሔ #በዚህን ጊዜ ታሪገማን ቢቻል ማክሰኞ ቀን ካልተቻለ ግን በማንኛውም ቀን የተነቀለን ታሪገማ ቅጠሉንም ሥሩንም አንደርብ ከተላከበት ቤት ቢያጤሱት ማንኛውም በድግምት የተላከ አንደርብ ድራሹ ይጠፋል። @etsemeaza
Show all...
ጥቡዕ ልቡ ለሕጻን ፨ጥቡዕ ልቡ ለሕጻን ፨ እንዘ ሀሎ ውስተ ምኵናን ፨ ጥቡዕ ልቡ ለሕጻን ፨ ይቤላ ሕጻን ጥብዒኬ እም ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ጥብዒኬ ፨ እም ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ፨ ከመ ንርአይ ገጾ ለአምላክነ ፨ ይቤሎ ሕጻን ለእግዚኡ ዘመጠነዝ ገድለ ተጋዲልየ ፨  ምንተኑ ተዓሥየኒ ፨ ጥብዒኬ እም ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ፨  ይቤሎ እግዚኡ ለሕጻን አዓሥየከ ዘሀሎ ውስተ ልብከ፨ ጥብዒኬ እም ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ፨  ይቤሎ ሕጻን ለእግዚኡ ኢትቅብር ሥጋየ ዲበ ምድር ፨ ጥብዒኬ እም ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ይቤሎ እግዚኡ ለሕጻን አልቦ ዘየዓብየከ በመንግሥተ ሰማያት፨  ዘእንበለ ዮሐንስ መጥምቅ ፨ ወአነ ፈጣሪከ ወዓዲ ከመ ኢይማስን ዲበ ሠረገላ ኤልያስ ህየ አነብረከ። °༺༒༻°  ዓራራይ °༺༒༻° ጸርሐ ሕፃን ኀበ እግዚኡ እንዘ ይብል ፨  ዘመጠነዝ ገድለ ተጋዲልየ ምንተኑ ተዓሥየኒ ፨ አዓሥየከ ዘሀሎ ውስተ ልብከ ፨ ዘሐነፀ መርጡሉከ ወገብረ  ኢየኀጉል በኀቤከ ወበኀቤከ ፨ ወዓዲ ከመ ኢይማስን ሥጋከ ዲበ ሠረገላ ኤልያስ ህየ አነብረከ። °༺༒༻°  ሰላም  °༺༒༻° ሕፃን ንዑስ ዘኢፈርሃ ትእዛዘ ንጉሥ ፨ ወጸንዓ በመንፈስ ቅዱስ ፨ በሰላም ዓደወ ፨ መንግሥተ ክብር ወረሰ። °༺༒༻°  ተፈጸመ  °༺༒༻° በዕደ መልአኩ ይዕቀበነ ፤ ወበጸሎተ ሰማዕታት ይምሐረነ ለዘለዓለሙ፡፡ © 👉🏽 etsemeaza
Show all...
°༺༒  ሥርዓተ ማኅሌት  ዘሐምሌ  ፲፱  ༒༻° እንኳን ለሊቀ መልአኩ ለቅዱስ ገብርኤልና ለቅዱስ ቂርቆስ ወኢየሉጣ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!! ከሊቃውንቱ ጋራ ለማመስገን ይረዳን ዘንድ የሌሊቱ ሥርዓተ ማኅሌት እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል። ፩. ነግሥ / ለአቍያጺክሙ / ሰላም ለአቍያጺክሙ እለ ተኀብአ እምዐይን፤ አናምያኒሁ ሥላሴ ለሜላተ ሰማይ ብርሃን፤ ልብሰ ሰማዕትና ይኲነኒ ምሕረትክሙ ክዳን፤ ላዕሌየ እስመ ኢሀሎ ልብሰ እስጢፋኖስ ዕብን፤ ወሥርጋዌሁ እሳት ለቂርቆስ ሕጻን፡፡ ዚቅ፦ ሃሌ በ፫ ፨ አንቃዕዲዎ ሰማየ ፨ ጸለየ ወይቤ ቅዱስ ቂርቆስ እጼውዓከ እግዚእየ ፨  ዘኢትሠዓር ንጉሠ ነገሥት መዋዒ ፨ እጼውዓከ እግዚእየ ዘሰቀልኮ ለሰማይ ከመ ቀመር፨ እጼውዓከ ቅዱስ እግዚእየ ዘበሥላሴከ ዓመድካ ለምድር፨ እጼውዓከ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸግወኒ ስእለትየ። ፪. ነግሥ / ለልሳንከ / ሰላም ለልሳንከ መዝሙረ ቅዳሴ ዘነበልባል፤ ወለድምጸ ቃልከ ሐዋዝ ቀርነ መንግሥቱ ለቃል፤ ሞገሰ ክብሩ ሚካኤል ለተላፊኖስ ባዕል፤ አልቦ ዘይትማሰለከ በልማደ ምሕረት ወሣህል፤ እንበለ ባሕቲታ እኅትከ ማርያም ድንግል፡፡ ዚቅ፦ ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፨ ወብሥራት ለገብርኤል፨ ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል። ፫. ነግሥ / ዘመንክር ጣዕሙ / ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኰት ስሙ፡፡ ዚቅ፦ ምንተ እንከ እብል በእንተ ማርያም መሠረተ ጽድቅ ፨ ኀደረ ላዕሌሃ ወአዘዘ ደመና በላዕሉ። ፬.  ለዝክረ ስምከ / መልክአ ቂርቆስ / ሰላም ለዝክረ ስምከ ቂርቆስ ሕጻን፤ ዘፍካሬሁ ተብህለ ጽጌ ምዑዝ ዕፍራን፤ ለዝ ስምከ ነጋሢ ዘኢየዓርቆ ሥልጣን፤ ሶበ ይጼውዖ ልሳንየ ውስተ ገጸ ኲሉ መካን፤ ይደንገፅ ሞት ወይጒየይ ሰይጣን፡፡ ዚቅ፦ ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ፨  ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ፨  መላእክት ይትዋነይዋ፨ ኢየሉጣ ምስለ ወልዳ እሳተ ገብሩ ሐመዳ፨ ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ ለነ ጻድቃን፨ እስመ በጸሎተ ጻድቅ ትድኅን ወኢትማስን ሀገር። ወረብ፦ ኢየሉጣ ወለደት ኢየሉጣ ወለደት ነቅዓ ጽጌ ረዳ ወለደት፤ ፀሐየ ጽድቅ የዓውዳ ፀሐየ ጽድቅ። ፭. ለልሳንከ / መልክአ ቂርቆስ / ሰላም ለልሳንከ ለዐቃቤ ሥራይ በዕዱ፤ እንተ ተመትረ እምጒንዱ፤ ሕፃን ቂርቆስ ለጽሕርት ዘኢያፍርኀከ ነጐድጓዱ፤ ዮም ባርክ ማኅበረነ ለለ፩ዱ ፩ዱ፤ ከመ ባረኮ አብርሐም ለይስሐቅ ወልዱ። ዚቅ፦ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ፨ ድምፃ ለጽሕርት ከመ ነጐድጓደ ክረምት፨ ኢፈርህዎ ለሞት ቅዱሳን ሰማዕት። ወረብ፦ ሕፃን ወእሙ ክልኤሆሙ ፈጸሙ ገድሎሙ፤ ድምፃ ለጽሕርት ለጽሕርት ከመ ነግጐድጓደ ክረምት/፪/ ፮. ለእንግድዓከ / መልክአ ቂርቆስ / ሰላም ለእንግድዓከ ልቡና ዘከብዶ፤ ከመ እንግድዓሁ ለዕዝራ መጽሐፍ እንተ ይንዕዶ፤ ሕጻን ቂርቆስ ምስለ ወላዲትከ በተዋሕዶ፤ መኑ ከማከ ለእቶን አምሳለ አሣዕን ዘኬዶ፤ ወመኑ አምሳለ ማይ ዘአቊረረ ነዶ። ዚቅ፦ ሃሌ ሃሌ ሉያ ይቤላ ሕጻን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ፨ ነበልባለ እሳት፨ ኢትፍርሂ እም ፨ ንፈጽም ገድለነ። ወረብ፦ ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እም ነበልባለ እሳት፤ ንፈጽም ገድለነ ወስምዓነ ኢትፍርሂ እም። ፯. ለመልክእከ / መልክአ ቂርቆስ / ሰላም ለመልክዕከ በማየ ዮርዳኖስ ጥሙቅ፤ ወቅቡዕ በሜሮን ቅብዐ ሰላም ወእርቅ፤ በጸሎትከ ነጐድጓድ ወስእለትከ መብረቅ፤ አቊረርከ ቂርቆስ ነበልባሎ ለእቶነ እሳት ምውቅ፤ ከመ ነደ እሳት አቊረሩ ሠለስቱ ደቂቅ። ዚቅ፦ በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት፨ ወኮነ ጥምቀተ ለአግብርተ እግዚአብሔር ጽዋዓ ሕይወት፨ ወሀቦሙ መገቦሙ ወመርሆሙ፨ እስመ ክርስቶስ ሀሎ ምስሌሆሙ፡፡ ወረብ፦ በጸሎቱ ለቅዱስ ቂርቆስ እምውስተ ጽሕርት ወጽአ ማይ እምውስተ ጽሕርት፤ ለአግብርተ እግዚአብሔር ኮነ ወኮነ ጥምቀተ። ፰. ለህላዌከ / መልክአ ቂርቆስ / ሰላም ለህላዌከ ማዕከለ ሰብአቱ ነገድ፤ እለ ሥዑላን በነድ፤ አስተምሕር ቂርቆስ ቅድመ መንበረ አብ ወወልድ፤ ኀበ ተሐንፀ መርጡልከ ወዘዚአከ ዐጸድ፤ ኢይምጻእ ለዓለም ዘይቀትል ብድብድ፡፡ ዚቅ፦ በዛቲ መካን ኢይምጻእ ሞተ ላሕም፨ ወኢብድብድ በሰብእ ፨ ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን፨ በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ፨ ወኢዓባረ እክል ፨ ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን፨ ቂርቆስ ሕጻን አንጌቤናይ፨ ወልደ አንጌቤናይት፡፡ ወረብ፦ በዛቲ መካን ኢይኩን ሕፀተ ማይ፤ ባርካ #ቂርቆስ ለዛቲ መካን ባርካ ለዛቲ መካን። ፱. ለመልክአትኪ / መልክአ ኢየሉጣ / ሰላም ለመልክአትኪ አርብዓ ወሠለስቱ፤ ዓዲ ሰላም ለጠብአያትኪ አርባዕቱ፤ ኢየሉጣ ቅድስት ለቂርቆስ ወላዲቱ፤ ሰአሊዮ በእንቲአየ ከመ አይጥፋዕ በከንቱ፤ ለእግዚአብሔር አምላከ ጽድቅ ዘብዙኅ ምሕረቱ። ዚቅ፦ ሃሌ ፫ ፨ ሰላማዊት ሰላም ለኪ፨ ሰላመ ወልድኪ የሃሉ ላዕለ ኩልነ፨ ኢየሉጣ እምነ ፨ ወእሙ ለቂርቆስ እግዚእነ ሰአሊ ለነ፨  አስተምሕሪ ለነ፨ ከመ ኢንቁም አንቀጸ፡፡ ፲. ለልሳንከ / መልክአ ገብርኤል / ሰላም ለልሳንከ ወለቃልከ ማኅተሙ፤ ለእስትንፋስከ ጠል ለእሳተ ባቢሎን አቊራሬ ፍሕሙ፤ ገብርኤል ውኩል ለረድኤተ ጻድቃን ኲሎሙ፤ አንግፈኒ እምነበልባል ኢያንጥየኒ ሕማሙ፤ ከመ አንገፍኮሙ ቅድመ ለቂርቆስ ወእሙ። ዚቅ፦ ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት፨ ወበላሕኮሙ እምእሳት፨ አድኅነነ እግዚኦ ሃሌ ሉያ እምዕለት እኪት። ወረብ፦ ዘረዳእኮሙ ለሰማዕት ወባላሕኮሙ እምእሳት ሊቀ መላእክት፤ እግዚኦ አድኅነነ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ እም ዕለት እኪት። °༺༒༻° አንገርጋሪ °༺༒༻° ይቤላ ሕፃን ለእሙ ኢትፍርሂ እእም ነበልባለ እሳት ዘአድኃኖሙ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ። °༺༒༻°  አመላለስ °༺༒༻° ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል፤ ውእቱ ያድኅነነ ወሚሳኤል ውእቱ ያድኅነነ። °༺༒༻°  እስመ ለዓለም  °༺༒༻° ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ፨ አምላኮሙ ለቂርቆስ ወእሙ፨  በብዝኃ ኃይሉ ወበጽንዓ ትዕግሥቱ ፨  አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን፨  ሕፃን ዘኮና መርሐ ለእሙ ዘሠለስቱ ዓም፨  አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን፨  ኢፈርሐ ነበልባለ እሳት ዘይወጽእ እምአፈ እቶን፨ አኃዛ  ለእሙ ዕዳ ዘየማን ወሰሐበ ቅድመ መኰንን ፨  አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን ፨ ወይቤላ ሕፃን ለእሙ ጥብዒኬ እም ወኢትናፍቂ፨  እምዝ ዳግመ አልቦቱ ኲነኔ፨ አርአየ ጸጋሁ ላዕለ ሕፃን፨ አእኰትዎ ወሰብሕዎ ወባረክዎ ለአብ፡፡ °༺༒༻°  አመላለስ °༺༒༻° አእኰትዎ ወሰብሕዎ፤ አእኰትዎ ወሰብሕዎ። °༺༒༻°  አቡን °༺༒༻°
Show all...
ሰላም የዕፀ ፍህሶ ወዕፀ መአዛ ቻናል አባላት በአንዳንድ ምክንያቶች ከሚዲያ ርቄ ስለቆየሁ ይቅርታ @etsemeaza
Show all...
⬆️ #ምልከታ አንዳንድ በመንግስታት የሚለቀቁ የሞባይል መተግበርያዎች (Apps) የሚፈጥሩት ስጋት! ነዳጅ ለመቅዳት፣ ክፍያዎችን ለመፈፀም፣ አገልግሎት ለማግኘት... ወዘተ እየተባለ ህዝቡ በአስገዳጅነት አንዳንድ የሞባይል መተግበርያዎችን እና የዲጂታል መንገዶችን እንዲጠቀም የሚያስገድዱ አሰራሮችን በቅርቡ እያየን ነው። ነገር ግን ከሌሎች ሀገራት ልምድ እንደምንረዳው አንዳንድ መተግበርያዎች (የሞባይል አፖች) ዜጎችን ለመከታተል እና መረጃዎችን ለመመንተፍ በአንዳንድ መንግስታት ይውላሉ። በሶርያ፣ ሩስያ፣ ቤላሩስ፣ በአሜሪካ፣ በእስራኤል፣ በእንግሊዝ እና ቻይና በስፋት ጥቅም ላይ ውለዋል። ይህን ችግር እነ ኤድዋርድ ስኖውደን እና ጁሊየን አሳንጅ ቀድመው ያጋለጡ ነበር፣ በዚህም ምክንያት ብዙ ችግር ደርሶባቸዋል። ታድያ ይህን ፅሁፍ ለመፃፍ ምን አሳሰበኝ? ለምሳሌ በቅርቡ በስፋት ጥቅም ላይ የዋለው Tele Birr በምስሉ ላይ እንደሚታየው የተጠቃሚዎችን ስልክ ፎቶ እና ቪድዮ፣ አድራሻ፣ የግል መረጃ፣ የፋይናንስ መረጃ፣ ሴቭ የተደረጉ ስልኮች ቁጥር፣ የስልኩን መለያ እና ሌሎች መረጃዎች ማየት እንደሚችል ጉግል ፕሌይ ያሳያል (እቀባ/restriction ካልተደረገበት ማለት ነው)። ምን ያህሉ የመተግበርያው ተጠቃሚ እቀባ እንዳደረገ መገመት ይቻላል። አንድ የዘርፉ ባለሙያ እንዳስረዳኝ Tele Birr እነዚህን ሁሉ መረጃዎች የሚያገኝ ከሆነ የግል መረጃ አያያዝ ጥሰት ነው። "ይህ የ Tele Birr መተግበርያ እንደሚጠይቀው ሌሎች እንደ CBE Birr፣ Apollo ያሉ መተግበርያዎች አይጠይቁም። ጉግል ፕሌይ ይህ የ Tele Birr መተግበርያ እንደ ስልክ ማይክራፎን፣ ካሜራ፣ ወዘተ እንደሚያገኝ ይናገራል፣ ይህ አሳሳቢ ነው" ይላል ባለሙያው አብነት ተፈራ። አብነት አክሎም "እነዚህ የክፍያ ስርዓቶች እንደ ተጨማሪ የክፍያ አማራጭ ማለትም በጥሬ ገንዘብ፣ ኤቲም፣ POS ሳይሆን የግዴታ (mandatory) መደረጋቸው እና በዚህ መልኩ ብቻ ተጠቀሙ መባሉ የበለጠ የችግሩ ተጋላጭ እንድንሆን ሊያደርገን የሚችል ስጋት አለኝ" ብሏል። "መረጃዎችን ከግለሰብ ፈቃድ ውጭ ከመመንተፍ ጋር በተያያዘ ይህን ችግር ከማስፋትም በላይ የመንግስት የሚስጥር ደህንነት ተቋሟች ከግለሰብ ፈቃድ እና እውቅና ውጭ የግል ስልክ ላይ ያሉ ሙሉ መረጃዎችን እንዲያገኙ በር መክፈቱ ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል" ብሎ አስተያየቱን ሰጥቶኛል። የ Tele Birr መተግበርያ ይህን ድርጊት እየፈፀመ ነው ለማለት ማስረጃ እስካሁን የለም፣ መረጃውን ምን እንደሚያደርግበት ግን ራሱ ተቋሙ ያውቀዋል። ለማንኛው ቢያንስ ቢያንስ ስልኮቻችን ለተለያዩ መተግበርያዎች የ App Permission እንዳያገኙ በማድረግ ሊደርሱ የሚችሉ ችግሮችን በመጠኑም ቢሆን መከላከል ይቻላል ብዬ አስባለሁ። መጠንቀቁ አይከፋም። @EliasMeseret
Show all...
+++ እንኳን አደረሳችሁ! [ግንቦት ፳፩/21] +++ =>  በዓለ-እግዝእትነ ማርያም [ደብረ ምጥማቅ] #የዕለቱ_ግጻዌ (መልክታት፥ ምስባክ፥ ወንጌል፥ ቅዳሴ) ✝ ምስባክ ዘነግህ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ አሕዛብ ብዑላነ ምድር። ኩሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን። በዘአዝፋረ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት። ትርጉም:- የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ። ለሐሴቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ክብርዋ ነው። በወርቅ ዘቦ ልብስ የተጎናጸፈችና የተሸፋፈነች ናት። (መዝ ፵፬ ፥ ፲፪-፲፫ /44፥12-13) ✝ ወንጌል ዘነግህ ሉቃስ ፩ : ፴፱ - ፶፯  /1:39-57) ✝ መልእክታት፦ ➊.. ፩ኛ ቆሮንቶስ ፮ ፥ ፱-፳ /6፥9-20 ፱ ወይስ ዓመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንዳይወርሱ አታውቁምን? አትሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆን ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ቀላጮች ወይም ከወንድ ጋር ዝሙት የሚሠሩ ፲ ወይም ሌቦች ወይም ገንዘብን የሚመኙ ወይም ሰካሮች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም። ፲፩ ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፥ ተቀድሳችኋል፥ ጸድቃችኋል። ፲፪ ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም። ፲፫ መብል ለሆድ ነው፥ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሥጋ ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሥጋ ነው፤ ፲፬ እግዚአብሔርም ጌታንም አስነሣ እኛንም በኃይሉ ያስነሣናል። ፲፭ ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደ ሆነ አታውቁምን? እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን? አይገባም። ፲፮ ወይስ ከጋለሞታ ጋር የሚተባበር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን? ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ ተብሎአልና። ፲፯ ከጌታ ጋር የሚተባበር ግን አንድ መንፈስ ነው። ፲፰ ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል። ፲፱ ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደ ሆነ አታውቁምን? . ➋..የዮሐንስ ራእይ ፲፪÷፩ - ፭ /12፥1-5 ፩ ታላቅ ምልክትም በሰማይ ታየ ፀሐይን ተጐናጽፋ ጨረቃ ከእግሮችዋ በታች ያላት በራስዋም ላይ የአሥራ ሁለት ከዋክብት አክሊል የሆነላት አንዲት ሴት ነበረች። ፪ እርስዋም ፀንሳ ነበር፥ ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጭንቃ ጮኸች። ፫ ሌላም ምልክት በሰማይ ታየ፤ እነሆም ታላቅ ቀይ ዘንዶ፤ ሰባት ራሶችና አሥር ቀንዶችም ነበሩት በራሶቹም ላይ ሰባት ዘውዶች ነበሩ፥ ፬ ጅራቱም የሰማይን ከዋክብት ሲሶ እየሳበ ወደ ምድር ጣላቸው። ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕፃንዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት ሴት ፊት ቆመ። ፭ አሕዛብንም ሁሉ በብረት በትር ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ልጅዋም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ። . ➌..የሐዋር/ሥራ ፯ : ፵፬ - ፶፩ /7:44-51 ፵፬ እንዳየው ምስል አድርጎ ይሠራት ዘንድ ሙሴን ተናግሮ እንዳዘዘው፥ የምስክር ድንኳን ከአባቶቻችን ዘንድ በምድረ በዳ ነበረች፤ ፵፭ አባቶቻችንም ደግሞ በተራ ተቀብለው እግዚአብሔር በፊታቸው ያወጣቸውን የአሕዛብን አገር በያዙት ጊዜ ከኢያሱ ጋር አገቡአት፥ እስከ ዳዊት ዘመንም ድረስ ኖረች። ፵፮ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቶ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያን ያገኝ ዘንድ ለመነ። ፵፯ ነገር ግን ሰሎሞን ቤት ሠራለት። ፵፰-፶ ነገር ግን ነቢዩ። ሰማይ ዙፋኔ ነው ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ለእኔ ምን ዓይነት ቤት ትሠራላችሁ? ይላል ጌታ፥ ወይስ የማርፍበት ስፍራ ምንድር ነው? ይህንስ ሁሉ እጄ የሠራችው አይደለምን? እንዳለ፥ ልዑል የሰው እጅ በሠራችው አይኖርም። + ምስባክ ዘቅዳሴ ሰውረከኒ በዕለተ ቀትል መልዕለተ ርእስየ። ኢትመጥወኒ እግዚኦ እምፍትወትየ ለኃጥአን ተማከሩ ላዕሌየ ኢትኀድገኒ ከመ ኢየዘኀሩ። ትርጉም:- በሰልፍ ቀን ራሴን ሸፈንህ። አቤቱ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለኃጢአተኞች አትስጠኝ፤ በላዬ ተማከሩ፤ እንዳይጓደዱ አትተወኝ። (መዝሙር ፻፴፱:፯ /239:7) + ወይም የሚቀጥለውን ምስባክ በል። ኢትሚጦ ለልብየ ውስተ ነገር እኩይ ለአመክንዮ ምክንያት ለኃጢአት ምስለ ሰብእ ገበርተ ዐመፃ። ትርጉም:- ልቤን ወደ ክፉ ነገር አትመልሰው፥ ለኃጢአት ምክንያት እንዳልሰጥ፤ ዓመፃን ከሚያደርጉ ሰዎች ጋር÷ (መዝሙር ፻፵ : ፬ /140:4) ✞ ወንጌል ዘቅዳሴ ማቴዎስ ፲፰ : ፮ - ፲፱ (18:6:19) ፮ በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር። ፯ ወዮ ለዓለም ስለ ማሰናከያ፤ ማሰናከያ ሳይመጣ አይቀርምና፥ ነገር ግን በእርሱ ጠንቅ ማሰናከያ ለሚመጣበት ለዚያ ሰው ወዮለት። ፰ እጅህ ወይም እግርህ ብታሰናክልህ፥ ቈርጠህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት እጅ ወይም ሁለት እግር ኖሮህ ወደ ዘላለም እሳት ከምትጣል ይልቅ አንካሳ ወይም ጉንድሽ ሆነህ ወደ ህይወት መግባት ይሻልሀል። ፱ ዓይንህ ብታሰናክልህ አውጥተህ ከአንተ ጣላት፤ ሁለት ዓይን ኖሮህ ወደ ገሃነመ እሳት ከምትጣል ይልቅ አንዲት ዓይን ኖራህ ወደ ሕይወት መግባት ይሻልሃል። ፲ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና። ፲፩ የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአልና። ✝ ቅዳሴ - ዘእግዝእትነ ማርያም (ጎሥዐ)  - በዕዝል ዜማ ቀድስ __
Show all...
መጽሔተ ሰሎሞን ምስለ አውደ ከዋክብት @etsemeaza
Show all...
መጽሔተ_ሰሎሞን_ወአውደ_ከዋክብት_4_1.pdf3.64 MB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.