en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

ቅዱሳት ሥዕላት ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ

Open in Telegram

በዚህ ቻናል ነባር እና አዳዲስ የጥበብ ሥራዎቼን የማቀርብበት ሲሆን እናንተም ሥራዎቼን በመመልከት ውስጣችሁን ታረኩበት ዘንድ እንሆ እላለሁ ። አስተያየትዎን ገንቢ ሃሳብዎን እንዲሁም ማሣል ሲፈልጉ ከታች ባለው መረጃ ይጠቀሙ። @zersh8 0929018509

Show more
1 407
Subscribers
No data24 hours
-17 days
-130 days
Posts Archive
።።።።።። + + + አቡነ ሰላማ + + + ።።።።።።።።። ከማስታውሰው ስለ አቡነ ሰላማ ከ አቡነ ዘካርያስ አንደበት እንደሰማሁት አቡነ ሰላማ ወደ ጵጵስናው ከመምጣታቸው በፊት ቆሞስ አባ ሐረገ ወይን ይባሉ ነበር ።በጎጃም ጉባዔ ቤት ዘርግተው ደቀ መዛሙርት ሰብስበው ቅኔ በሚያስተምሩበት ወቅት ከጉባዔቸው መሐል ልብሱ የነተበ መንፈሱ በተስፋ ማጣት የተጨነቀ ገበሬ ምዕመን ወደ ብፁእነታቸው ይጠጋል። አርሳቸውም መንፈሱን ተረድተው ምን ገጠመህ ለምንስ መጣህ ይሉታል። እሩሱም የበኩር ልጁ በደዌ ትይዞ የአልጋ ቁራኛ እንደሆነ ብዙ ቦታ ድህነት ይገኛል የተባለ ቦታ ይዞት እንደደከመ እና መፍትሔ በማጣት ተስፋው እንደተሟጠጠ በመንገር እግዚአብሔር ምሕረትን ለልጁ ይሰጥ ዘንድ እርሶ(አቡነ ሰላማን )ማለቱ ነው በቤቱ ተገኝተው ይጸልዩለት ዘንድ እንደመጣ ችግሩን ነገራቸው። አባታችን እኛ ምን አቅም አለን ደካሞች ነን ቢሉት እርሱ ግን ግድ ይላቸዋል ። እሳቸውም ብድግ ብለው ደቀ መዛሙርታቸውን ተነሱ ስለዚህ ገበሬ እምነት እግዚአብሔር የሚሰራውን አናውቅምና አብረነው ቤቱ ሔደን እንጸልይ በማለት ገበሬውን ተከትለው ታማሚው ልጅ ከተኛበት ጎጆ ገቡ ። ገበሬውንም ውህ በንጹሕ ዕቃ ከፊት ከጠረጴዛው እንዲያኖር አዘው ሲቀርብ እርሳቸው እየመሩ ከደቀ መዛሙርቶቻቸው ጋር ጸሎታቱን እያደረሱ ደሳለኝን በመሐል ሁሉን ያስገረመ የእግዚአብሔር ስራ መገለጥ ጀመረ በጠረጴዛው ላይ የተቀመጠው ውሃ ምድጃ እሳት ላይ እንደተቀመጠ ይንተከተክ ጀመር ። አባታችንም ይሔን ባዩ ጊዜ በፈላው ውሃ ታማሚውን ልጅ ያጠምቁታል። ታማሚውም እንደ መጻጉ አፈፍ ብሎ በመነሳት የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ መሰከረ ። በሐዘን ተውጦ የነበረው የገበሬው ቤት በደስታ ደመቀ አባታችን በአጸደ ሥጋ እያሉ እግዚአብሔር ብዙ ገቢረ ታዕምራትን አሳይቷል። ካላይ የተጻፈው ከብዙ ጥቂቱን ነው። ሰው መንፈሳዊ ሲሆን ሕይወት አነዋወሩ ምን ዓይነት ይመስላል ለሚለው ጥያቄዬ በተግባር ያየሁት እርስሳቸው ላይ ነው ብል ማጋነን አይሆንብኝ። የማይቋረጥ ጸሎት አፍቅሮተ ሰብ እና ትህትና እዩኝ እወቁልኝ የሌለበት ሃብተ ፈውስ ። የአባታችን በረከት አይለየን

ታሪክን_የኋሊት ፋሽስት ኢጣሊያ ፣ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የሚገኙ 300 መነኮሳትና ዲያቆናት በመደዳ በጥይት ያስደበደባቸው፣ በ1929 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ መነኮሳቱና ዲያቆናቱ እንዲገደሉ ትዕዛዝ የሰጠው ጀኔራል ሮዶልፎ ግራዚያኒ ነበር፡፡ ጀኔራል ግራዚያኒ የኢጣሊያ የምስራቅ ዕዝ አዛዥና በኋላም የኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ገዥ በነበረበት ጊዜ ሁሉ፣ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና መነኮሳት ላይ የተለየ ጥላቻ ነበረው፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት፣ ኢትዮጵያ እንዳትገዛልን የሚያወግዙ፣ ስለነፃነት የሚሰብኩ፣ አርበኞችን የሚደግፉ ናቸው ፤ የሚል እምነት ስለነበረው ቤተ ክርስቲያኗን ለመበተን ይመኝ ነበር፡፡ የካቲት 12፣ አብርሃም ደቦጭ በቦምብ ካቆሰለው በኋላ ፣ሚስቱን ደብረ ሊባኖስ ገዳም መደበቁን ሰማ፡፡ ይኽም በካህናት መነኮሳት ላይ ያለውን ጥላቻ አጠናከረለት፡፡ ለሸዋ ጦር አዛዠ ፣ለጀኔራል ማልቲ፣ አደጋ የጣሉብኝ ሰዎች በግዛትህ ሲዘዋወሩ ባለመያዝህ ሀላፊነት ትወስዳለህ ብሎ ተቆጣው፡፡ በቴሌግራም ቁጥር 26320 በደብረ ሊባኖስ መነኮሳት ላይ የግድያ ርምጃ እንዲወሰድ ከገዳሙ አለቃ ጀምሮ ያለምንም ምርጫ መነኮሳቱ ዲያቆናት እንዲረሸኑ ትዕዛዝ አስተላለፈለት፡፡ ጀኔራል ማልቲ፣ በርካታ ቁጥር ባላቸው ወታደሮች ታጅቦ ግንቦት 12 ደብረ ሊባኖስ ደረሰ፡፡ እለቱ የአቡነ ተክለሃይማኖት በዓል የሚከበርበት ቀን በመሆኑ በርካታ ሰው ተሰብስቧል፡፡ የተራራውን ዙሪያ በወታደር አስከበበው፡፡ ወደ ገዳሙ ሲደርስ ፣ ሊቀበሉት የተሰለፉትን የካህናት “እናንተ ቁጥራችሁ ትንሽ ነው፡፡ ሌሎቹ ለምን አልተቀበሉኝም” ብሎ ተቆጣ፡፡ የተቀበሉትን በቅጥር ግቢው እንዲቆዩ አዞ ፣ሌሎቹን መምህራንና መነኮሳት ታድነው እንዲያዙ አዘዘ፡፡ 300 የሚሆኑ ሞታቸውን የሚጠብቁ አዛውንትና መነኮሳት፣ ዲያቆናትና የንግስ በዓል ለማክበር የሄደውን ሕዝብ እያስገደደ በመኪና ጫናቸው፡፡ ከገዳሙ ወጣ ብሎ በሚገኘው ሽንኩርት ከተባለው ቀበሌ ሲደርሱ፣ ከመኪና አስወርዶ 300 የሚሆኑትን በጥይት አስደበደባቸው፡፡ ሌሎቹ በዓል ለማክበር ደብረ ሊባኖስ የተገኙትንና ዲያቆናትን ወደ ደብረ ብርሃን ትሄዳላችሁ ብሎ አሳፈራቸው፡፡ በመንገድም ላይ ሲደርሱ 129 የሚሆኑትን ዲያቆናት ገደላቸው፡፡ ጀኔራል ማልቲ ይኽንም ለአለቃው ለግራዚያኒ እለቱን ሪፖርት አደረገ፡፡ ከአሰቃቂው ግድያ በኋላ ወታደሮች ገዳሙን ዘረፉት፡፡ የደብረ ሊባኖስ ገዳም ፣ መኳንንትና ዝና ያላቸው ኢትዮጵያዊውያን የተቀበሩበት ገዳም ስለሆነ አብሩዋቸው ወርቅ ተቀብሮ ይሆናል እያሉ ቀብራቸውን እየከፈቱ አዩ፡፡ ከሁሉም ብልጫ ያለው ንብረትና መፃህፍት የሚገኙበትን የደብረሊባኖስ ገዳም ጣሊያኖች ያገኙትን ሁሉ መዝብረው ወናውን አስቀሩት፡፡ ገዳሙ ለአገልግሎት ዝግ ሆኖ፣ ቁልፉ ለአካባቢው የኢጣሊያ ሹም መሰጠቱን ግራዚያኒ በቴግራም ለሮም አሳውቋል፡፡ በግራዚያኒ ትዕዛዝ 429 የደብረ ሊባኖስ ገዳም መነኮሳት ፣ ካህናት መምህራንና ሲቪሎች ከተገደሉ ዛሬ 88 ዓመት ሆነ፡፡ እሸቴ አሰፋ ግንቦት 12/2018 የሸገርን ወሬዎች፣

ዜና_ዕረፍት ለበርካታ ዓመታት ከገጠር እስከ ከተማ ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገራት ቅዱሱን ሕያው ወንጌል በታማኝነትና በትጋት ያለዕረፍት ያገለገሉት መምህር_ዘለዓለም_ወንድሙ በዛሬው ዕለት ከድካመ ሥጋ ዐረፉ። ኦ እግዚኦ አዕርፍ ነፍሰ ገብርከ ወልደ_ሰማዕት ሀገረ ሕይወት መንግስተ ሰማያት ያውርስልን፤ በአብርሃም በይስሐቅ በያዕቆብ ዕቅፍ ያኑርልን፤ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ለኦርቶዶክሳውያን በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልግሎት/Addis Ababa Diocese Media Service

ማስታወቂያ ለኦርቶዶክሳዊያን ሠዓሊያን፣ ቀራጺያን፣ አርክቴክቶች፣ ግራፊክስ ዲዛይነሮች በዚህ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ፈተና እና ችግር ላይ ናት።  ይህንንም ፈተና በዘላቂነት ለመቅረፍና ጥበቧን ለቀጣይ ተውልድ ለማስተላለፍ ኅበረት አስፈላጊ እና ወሳኝ ነው። ስለዚህም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  የሠዓሊያን ኅብረት ለመመስረት እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ውድ የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን የሆናችሁ የጥበብ ሰዎች በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ እንድትሳተፉ በቅዱስ ሉቃስና በቅዱስ መብዓጽዮን ስም ጥሪ እናቀርባለን። ቦታ፥ ገርጂ ማርያም የሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ ቀን፥ የካቲት 22፣ 2018 ዓ.ም. (እሑድ) 🕰 ከ 8:00 - 11:00 (ከሰዓት) በእለቱ መሳተፍ የምትፈልጉ እስከ የካቲት 20 2018 ዓ.ም. ከታች👇👇👇👇 ባለው መመዝገብ ትችላላችሁ። ፎርም https://forms.gle/G7bFf5D4bj7m9RBa7

በምሥራቅ አርሲ የኦርቶዶክሳውያን ግድያ እና የወጣቶች አፈና አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ የአካባቢው ምእመናን ገለጹ። EOTCMK TV ኅዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ዛሬ ኅዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ልዩ ቦታው ጠለታ ቅዱስ ገብርኤል በተባለ አካባቢ ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ገደማ ሦስት ኦርቶዶክሳውያን በአውድማ ላይ እህል እየወቁ ባሉበት በጥይት ተደብድበው በግፍ መገደላቸው ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ያመላክታል ። ከተገደሉት ምእመናን መካከል ዲ/ን ኢዮብ እጅጉ፣ ጥላሁን ቦጌ እና ሕፃን ጻድቃኔ ሠራዊቱ የተባሉ ኦርቶዶክሳውያን ይገኙበታል ። ሥርአተ ቀብራቸው በጠለታ ቅዱስ ገብረኤል ቤተክርስቲያን ዛሬ ኅዳር 01 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ ተፈጽሟል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በነበሩ የኦርቶዶክሳውያኑ አፈናና ግድያን በተመለከተ መረጃ አቀብላችኋ በሚል ምክንያት የአካባቢው ወጣት ምእመናን ወዳልታወቀ ሥፍራ ታስረው እየተወሰዱ እንደሚገኝ ምእመናኑ ለማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በሥፍራው ላይ የጸጥታ ሓይል ቢኖርም ኢ-ሰብአዊ ድርጊቱ ፣ አፈናና ግድያውም ተባብሶ መቀጠሉን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ። ስለጉዳዩ ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን መዋቅር ወደ ሆነው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ እና የዞኑ የጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ የእጅ ስልክ ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአሁኑ ሰዓት ሴቶች እና ሕጻናት አካባቢውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታም እየሸሹ እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመላክታል።

"አታልቅሽ ተመልሰው መጥተው ይገሉሻል..."የእናት ማሳሰቢያ *** እንደ ህልም በእዛች በተረገመች ምሽት የተደረገውን አሰቃቂ ግድያ ታስታውሰዋለች። 3 ወንድም እህቶቿን ፣እናቷን እና ሌሎች ቤተሰቦችን ጭምር ይዘው ከእነከብታቸው ስም አልባ የሞት አበጋዝ የሆኑ ታጣቂዎች ነድቷቸው ከአንድ ጫካ ላይ ወስደው አሳረፏቸው። ከመኖርያ ቤታቸው አርቀው ጫካ ላይ ከወሰዱ በኃላ ሁሉም እንዲንበረከኩ አደረጉ። በያዙት መሣርያ ያለርህራሄ አርከፈኩባቸው ።ከተስማው የመሣርያ ጥይት ድምጽ በኃላ ሁሉም ጸጥ አሉ። ከጸጥታው ውስጥ ግን የሚጣጣር እና የሚያቃስት ሰው ድምጽ በትንሽ በትንሹ ይሰማል። እንደ ቤተሰቧ ይህቺ የ8 ዓመት ህጻን በትከሻዋ አከባቢ እና በጎድኗ በኩል ሁለት ጥይት በስቷት አለፈ። በአፈሙዝ ያልሞቱትን በገጀራ ለመጨረስ ሁሉንም መከታተፍ ጀመሩ። ይህችንም ህጻን ልጅ መሃል አናቷን ሰነጠቁ። በጎድኗ እና ትከሻዋ በኩል ዘልቆ ከገባው የመሣርያ ቀለሀ በተጨማሪ ሰይፍ ለእዚህች ህጻን በአናቷ ታዘዘላት። ይህን ድርጊት ከፈጸሙ በኃላ ታጣቂዎች ከስፍራው ሄዱ።ይህች ህጻን ግን ከትንሽ ደቂቃ በኃላ ገላዋ በደም ረስርሶ ነቃች። ባልጠነከረ የስምንት ዓመት ገላዋ ላይ የገባው ቀለሃ እና ሰይፍ ድምጽ አውጥታ አስለቀሳት። በመሣርያ ተመተው በቆንጨራ ተጨፍጭፈው ከወደቁ አስክሬኖች መሃል የእዚህች እናት የልጇን ድምጽ ሰማች። በተኛችበት ወደ እርሷ ስባ "አታልቅሺ ድምጽሽን ከሰሙ መጥተው ይገሉሻል ዝም በይ " አለቻት። በእዛ ድቅድቅ ጨለማ እና ጫካ ውስጥ ልጅ የእናቷን ትዕዛዝ አክብራ ከህመሟ ጋር ዝም አለች። ከትንሽ ደቂቃ በኃላ ግን ህጻኗ እናቷ ዳግም እንድታናግራት ለመሞከር ስትጥር ምንም መልስ አትሰጥም። ሞት አጅሬ ወስዳቷል። ጥዋት ላይ ከእስክሬን መሃል ተነስታ ወደ ህክምና ተወሰደች። እናቷን እና 3 እህት ወንድሞችን በእዛችን ቀን በሞት ተነጠቀች። ይህን መርዶ የሰማው አባቷ ጻዲቁ ኢዮብ አይደለም እና " እርሱ ሰጠ እርሱ ነሣ" ብሎ አምላኩን ማመስገን አቃተው። አማረረ። ማማረር ብቻ ሳይሆን ጨርቁን ጥሎ አበደ። የልጆቹ እና የሚስቱን አስክሬን እንኳን በክብር ሳይቀርብ ጨርቁን ጥሎ አበደ። እጆቹን ለሰንሰለት ዳረገ። የቀሩት የሟች ቤተሰቦች ተከፋፍለው የቤተሰቦቻቸውን አስክሬን ወደ ቀብር ህሊናውን የሳተውን የሟች ልጆች አባት እና የእናታቸው ባል የሆነው አባወራውን ወደ ጸበል ይዘው ሄዱ። ይህ በእኛ ትውልድ መሃል የተፈጠረ ነፍስ ድረስ ዘልቆ የሚሰማ አሰቃቂ ታሪክ ይህ ነው ። ከጭፍጨፋው በኃላ ሁሉም የአከባቢው ኦርቶለታሪክና ለትውልድ ይቀመጥ። Kune Demelash kassaye -Arba Minch

የብፁዕ አቡነ ሰላማ የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት የበላይ ጠባቂ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር እሁድ መስከረም ፳ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል። ******** ዛሬ መስከረም ፲፰ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉት የብፁዕ አቡነ ሰላማን የቀብር ሥነሥርዓት በማስመልከት ቋሚ ሲኖዶስ ከቀትር በፊት አስቸኳይ ስብሰባ በማድረግ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት እሁድ መስከረም ፳ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ከቅዳሴ በኋላ የብፁዕነታቸው ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲፈጸም ውሳኔ አስተላልፏል። በዚህም መሠረት ነገ ቅዳሜ መስከረም ፲፱ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ዓ.ም ከቀኑ ፱ ሰዓት ላይየብፁዕነታቸው ክቡር አስከሬን ከሃሌ ሉያ ሆስፒታል በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአበው ቆሞሳትና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ጸሎት ከተደረገበት በኋላ ወደ መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ጉዞ በማድረግ ሥርዓተ ጸሎት ተደርሶ ሌሊቱን ሙሉ ጸሎተ ፍትሐትና ሥርዓተ ማኅሌት ሲደረግበት ያድራል። በማግስቱ እሑድ መስከረም ፳ ቀን ፳፻ ፲ወ፮ ዓ.ም ጠዋት ሥርዓተ ቅዳሴው በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ከተካሔደ በኋላ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ አበው መነኮሳት፣ የጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች ፣የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው ታጅበው ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ገዳም በእግር ጉዞ ይደረጋል። በካቴድራሉም ለብፁዕነታቸው የሚመጥን ሥርዓተ ጸሎት ተደርጎ የሕይወት ታሪካቸው ተነቦ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የማጽናኛ ቃለ ምዕዳን ተላልፎ ሲያበቃ ሥርዓተ ቀብሩ የሚፈጸም ይሆናል። በሥርዓተ ጸሎቱ ላይ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒዮወርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ይገኛሉ። የብፁዕነታቸው በረከት ይደርብን ። መረጃው. የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

።።።።።።። +" በዓለ ሥዕለ አድኅኖ "+ ።።።።።።።።።። ።።።።።። መስከረም 10 ።።።።።።።። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። +ይህች ቀን በቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሳት ሥዕላት የሚነገርባት ክብርት ቀን ናት:: 'ሥዕለ አድኅኖ' ማለት 'እግዚአብሔር በረድኤት የሚገለጥበት: አንድም በቅዱሳኑ አማካኝነት ጸጋ የሚገኝበት: የሚያድን ሥዕል' ማለት ነው:: +ስለዚህ ነገር አንዳንዶቹ ሊነቅፉን ይፈልጋሉ:: እኛ ግን ከማን እንደ ተማርነው እናውቃለን:: ከመነሻው እኛ ሥዕልን አናመልክም:: ይልቁኑ አምልኮን እንፈጽምበታለን እንጂ:: ሥዕልን ለሰው ልጆች የሰጠ ራሱ ባለቤቱ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይመሠክራል:: +እንዲያውም የመጀመሪያው ሠዐሊ ራሱ አምላካችን ነው:: አዳምን እንደ መልኩ: በምሳሌው ሲፈጥረው መላእክት የእግዚአብሔርን ምሥል አዳም ላይ አይተዋልና:: (ዘፍ. 1:26) ለሙሴም ሥዕለ ኪሩብን እንዲሥል ያዘዘ ራሱ ነው:: (ዘጸ. 25:22) በዚያም ላይ ሆኖ ሙሴና አሮንን ሲነጋገራቸው ኑሯል:: +በመቅደሰ ሰሎሞንም ተመሳሳይ ነገርን እናገኛለን:: (2ዜና. 7:12, 1ነገ. 9:1) በሐዲስ ኪዳንም ጌታ ሥዕለ ኪሩብ ያለበትን መቅደስ ቤቴ (ማቴ. 21:13): የአባቴ ቤት (ዮሐ. 2:16) ሲለው: በቅዱስ ሰውነቱ ሲመስለውም (ዮሐ. 2:21) እንመለከታለን:: ቅዱስ ዻውሎስ ለገላትያ ሰዎች ስለ ሥዕለ ስቅለት ሲያስታውሳቸው (ገላ. 3:1): ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ በደም የተረጨች ልብስ ብሎ ያላትን መተርጉማን ያትታሉ:: (ራዕይ. 19:13) +በትውፊት ትምህርት ደግሞ የመጀመሪያው ሥዕል በቅዱስ ሚካኤል ክንፍ ላይ የተሳለ ሲሆን ሥዕሉም የእመቤታችን ነው:: "ሚካኤል በክነፊሁ ጾራ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ" እንዳለ ቅዱስ ያሬድ:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቃርዮስና ለቬሮኒካ (12 ዓመት ደም ይፈሳት ለነበረችው ሴት) መልክአ ገጹን ሠጥቷቸዋል:: ('ቬሮኒካ' በላቲን 'ቬሮን-ኢኮን' 'እውነተኛ መልክ' እንደ ማለት ነው) +ቀጥሎም ዮሐንስ ወንጌላዊ ለጢባርዮስ ቄሣር ሥዕለ ስቅለቱን ሲሥልለት ቅዱስ ሉቃስ ደግም የእመቤታችን 'ምሥለ ፍቁር ወልዳን' ሥሏል:: ከዚያም ሲያያዝ ይሔው ከእኛ ደርሷል:: +ነገር ግን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ በከተሞች አካባቢ ቅርጾች በዝተዋልና ይሔ አላስፈላጊ መዋስ (ያውም ከመናፍቃን) ቢቀር መልካም ነው ባይ ነኝ:: ኋላ ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቁሞ ማውረድ ከባድ ነውና:: +" ጼዴንያ "+ +በዚህች ቀን ቅዱስ ሉቃስ የሣላትና ሥጋን የለበሰችው: ከፊቷም ወዝ የሚወጣትና ድውያንን የምታድነው የድንግል ማርያም ሥዕለ አድኅኖ ወደ ጼዴንያ ከወዳጇ ከብጽዕት ማርታ ዘንድ ገብታለች:: ቅድስት ማርታ ሀብት ንብረቷን በአብርሃማዊ ተግባር (በምጽዋትና እንግዳን በመቀበል) ላይ ያዋለች ክብርት ሴት ናት:: +ለእመ ብርሃን ካላት ፍቅር የተነሳ እንቅልፍ አልነበራትም:: ተግታ ታገለግላትም ነበር:: ሥዕሏን እንዲያመጣላት የላከችው ኢትዮዽያዊው መነኩሴ አባ ቴዎድሮስ የሥዕሏን ተአምራት ባየ ጊዜ ለራሱ ለመውሰድ ሞክሮ ነበር:: +ነገር ግን ከሁሉም በተሻለ የምትወዳት ቅድስት ማርታ ነበረችና በድንቅ ተአምር: በዚህች ቀን ወደ ጼዴንያ ገብታለች:: ቅድስት ማርታም ያለ ዕረፍት ስታገለግላት ኑራ ዐርፋለች:: +እመ ብርሃን ድንግል ማርያም ጣዕሟን ፍቅሯን: ጸጋ በረከቷን: ከሥዕሏም ረድኤት ትክፈለን:: የቅዱሳኑም ክብር አይለየን:: ጽሑፍ ከ ወርቁ ፈንታው የተቀነጨበ ቅድመ ሥዕልኪ እሰግድ ወለሥዕለ ወልድኪ እገኒ ማርያም ድንግል ማርያም እመ አዶኒ ማዕበለ ጌጋይ ጽኑዕ ሶበ ለአስጥሞ በጽሐኒ ሐመርየኒ ማዕዶትየኒ ሃይማኖትየኒ ማርያም ዘእንበሌኪ አልብየ ምንትኒ በጽሒፍ ኢይፌጽሞ ለስብሐትኪ እንግዳ ሼር በማድረግ ለሌሎች ያጋሩ ‹‹‹‹ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ››››

።።።+++ ጥቂት ስለ አቡነ ሰላማ ከዓይን ምስክር+++።።። ክፍል አንድ ብፁእ አቡነ ሰላማ ጵጵስና ከመቀበላቸው ከዛሬ 18 ዓመት በፊት የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ አለቃ በነበሩበት ጊዜ የርሳቸው ሹፌር ለኔ ቤተሰብ ነበር አሁን ውጭ ነው። እርሱ በስራ በነበረበት ጊዜ ገጠመኙን ያጫወተኝን ሁሌም ትዝ ይለኛል ላካፍላችሁ ። በአንድ ወቅት ብፁእነታቸው ታመው ሆስፒታል አልጋ ይይዛሉ እናም እርሱ ስለሚወዳቸው እየሄደ እያደረ የሳስታምም ይላላክ ነበር ። እና በአዳሩ ጊዜ ያለ እረፍት ለሌቱን ሙሉ ጸሎታቸው እንደማይቋረጥ በማየቱ ተገርሞ ሳይጨርስ በህክምና ቦታ ያሉ የታካሚ ቤተሰቦች የብፁእነታቸው ፀጋን ከሕይወታቸው ተረድተው በሃይላንድ ዕቃ ውሃ ከረፉበት አልጋ ስር በማስቀመጥ በቀጣዩ ቀን ሃይላንዱን በመውሰድ ለታማሚው በማጠጣት በመዳበስ ብዙ ታማሚዎች ተፈውሰው ወደ ቤታቸው ሲገቡ በዓይኑ በማየቱ አጫውቶኛል ። ።።።።።።+++።።።። ሃብተ ፈውስ ከሃብተ ጸሎት እና ሁሉን ወዳድ የሁኑ አባቴ ብፁእ አቡነ ሰላማ እንኳን ለ 18ኛ ዓመት በዓለ ሲመትዎ እንኳን አደረስዎ ! በእድሜ በጤና ያቆይልን ጸሎትዎ አትለየን! ይቆየን