cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ብራና ቲዮሎጅካል አገልግሎት

Pray+Study+Apply “ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።” — ራእይ 1፥3 “Blessed is he that readeth, and they that hear the words of this prophecy, and keep those things which are written therein: for the time is at hand.”

Show more
Advertising posts
341
Subscribers
No data24 hours
-17 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ሁላችንም ሰይጣን ፈታኝ መሆኑን እናውቃለን። እርሱና ረዳቶቹ የሆኑት ኣጋንንት የእግዚአብሔር ሕዝብ ኃጢኣትን እንዲፈጽም ባለማቋረጥ ይፈትናሉ። ከፈተኑን በኋላ ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት ይከሱናል። (ሰዕብራይስጡ «ሰይጣን» እና በግሪኩ «ዲያብሎስ› ማለት ከሳሽ ማለት ነው። ይህም ሰይጣን አማኞች ኃጢአት በሚሠሩበት ጊዜ እንደሚከሳቸው ያሳያል።) አንድ የተሳሳተ ተግባር ለመፈጸም በምንነሣበት ጊዜ እንፈተናለን። ነገሩ መልካም ወይም አስደሳች ይመስላል። የምንፈልገውን ነገር የምናገኝበት አቋራጭ መንገድ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን ይህ ሁልጊዜም እግዚአብሔር ለእኛ ከሚፈልገው መንገድ ውጭ ነው። ሔዋን እንደ እግዚአብሔር ለመሆን ስለ ፈለገች፥ መልካሙንና ክፉውን የምታስታውቀውን ፍሬ በላች። ወሲባዊ እርካታን ስለምንፈልግ፥ የጋብቻችን ጊዜ ሳይደርስ አሁኑኑ በአቋራጭ መንገድ ለመፈጸም እንሻለን። ወይም ቁሳዊ ሀብቶችን እንፈልግና እግዚአብሔር በጊዜው እንዲባርከን ከመጠበቅ ይልቅ አንድን ነገር ለማግኘት እንዋሻለን፤ ስለዚህ ጉቦ እንሰጣለን። ስለ ክርስቶስ ከሚያስደንቁን ነገሮች አንዱ፥ እግዚአብሔር ልጁም እንደኛ እንዲፈተን መፍቀዱ ነው። በዕብ 2፡17-18፤ 4፡15 ላይ ከኃጢአት በስተቀር በሁሉም ነገር እንደኛ የተፈተነ ሊቀ ካህናት እንዳለን ተገልጾአል። ፈተና ሲያጋጥመን እንድናሸንፍ የሚረዳን ስለዚህ ነው። ልጁ ለአገልግሎት በሚዘጋጅበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ሆን ብሎ ልጁ እንዲፈተን አድርጓል። እንዲያውም በምድረ በዳ በዲያብሎስ እንዲፈተን ያደረገው መንፈስ ቅዱስ ነበር። ክርስቶስ ለ40 ቀናት ያለምግብ በቆየባቸው ጊዜያት በተለያዩ መንገዶች ተፈትኗል። ዋንኛው ፈተና የተከሰተው ግን፥ ያለ ምግብ በቆየባቸው 40 ቀናት መጨረሻ ላይ ነበር። መሢሑ አካላዊ ድካም በተጫጫነው ሰዓት፥ ሰይጣን እርሱን ለማጥመድ የሚችልበት አጋጣሚ እንደደረሰ አሰበ። ሰይጣን ሁልጊዜ የሚፈትነን ደካማ በምንሆንበት ነገር ነው። በክርስቶስም ላይ ያደረገው ይህንኑ ነበር ። ፈተናዎቹ ክርስቶስ እንደ መሢሕ ከሚያጋጥሙት ነገሮች ጋር የሚዛመዱ ነበሩ። ማቴዎስ ይህንን ታሪክ የሚገልጸው ሰይጣን እያንዳንዳችንን እንዴት እንደሚፈትነንና ፈተናውን እንዴት እንደምንቋቋም ለማሳየት ነው። ክርስቶስ የተፈተነው በሦስት የሕይወት ፈርጆች ሲሆን፥ እነዚህም የሥጋ ምኞት፥ የሕይወት ትምክሕትና የዐይን አምሮት ናቸው (1ኛ ዮሐ. 2፡16)። አንዳንድ ምሑራን የዚህ ፈተና ውጤት የኣዳምና ሔዋን ፈተና ውጤት ተቃራኒ መሆኑን ይናገራሉ። የመጀመሪያዎቹ የሰው ልጅ ወላጆች በፈተናው ወድቀው ሞትን ሲያመጡ፥ «ሁለተኛው አዳም» ፈተናውን ተቋቁሞ የሰውን ልጅ ሊታደግ ችሏል (ሮሜ 5፡12-19)። ሌሎች ምሑራን የክርስቶስን ፈተና ከአይሁዶች በምድረ በዳ መቅበዝበዝ ጋር ያመሳስላሉ። ኣይሁዶች ለ40 ዓመት በምድረ በዳ እንደ ተቅበዘበዙ ሁሉ፥ ክርስቶስም ለ40 ቀናት በምድረ በዳ ውስጥ ቆይቷል። በምድረ እስራኤል ውስጥ በመቅበዝበዟ እንደ አገር የምትደራጅበትን ሁኔታ እንዳዘጋጀ ሁሉ (ዘዳግ. 8፡2-3)፥ የክርስቶስም ፈተና የእስራኤል መሢሕ እንዲሆን አዘጋጅቶታል። ኢየሱስ፥ እግዚአብሔር ከዚህ በፊት ከእስራኤል የፈለገውን ታዛዥነትና በመከራ ውስጥ በእርሱ የመታመን ምሳሌ ሆነ። ምንጭ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ማብራሪያ SIM Published https://t.me/+UK-E6QjEaWz2OCgp
Show all...
ብራና ቲዮሎጅካል አገልግሎት

Pray+Study+Apply “ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።” — ራእይ 1፥3 “Blessed is he that readeth, and they that hear the words of this prophecy, and keep those things which are written therein: for the time is at hand.”

ብራና ቲዮሎጂካል አገልግሎት የማቴዎስ ወንጌል ተከታታይ ጥናት ክፍል 15 ምዕራፍ 3፥13-17 ማቴዎስ 3 ¹³ ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ¹⁴ ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር። ¹⁵ ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት። ¹⁶ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ ¹⁷ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ። የኢየሱስ መጠመቅ ❖ቁ 13-17 የሚናገረው በኢየሱስና በመጥምቁ ዮሐንስ መሀከል ስላለው ግኑኝነት ነው። ስለ ኢየሱስ መጠመቅ አራቱም ወንጌላት ዘግበዋል።ማር 1፥9-11 ሉቃ 3፥21-22 ዮሐ 1፥31-34። የማቴዎስ ግን ትንሽ ለየት ባለ አቀራረብ ይዟል።የዮሐንስና የኢየሱስ የእርስ በርስ ንግግር የተጻፈው በዝህ ወንጌል ውስጥ ብቻ ነው። የጥምቀት ዓላማ ➤ለንስሐ ➤እግዚአብሔርን ለማክበርና ለመታዘዝ ➤የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ለማሳወቅም ነው።የዮሐንስ ጥምቀት የንስሀ ጥምቀት ነው። እኛ የምንጠመቀው ለዝህ ከሆን ኢየሱስ ንስሀ የምገባበት ሀጢያት የለበትምና ለምን ተጠመቀ የምል የብዙዎች ጥያቄ ነው። ዮሐንስ እንብ ያለው ለኢየሱስ ሀጢያት ስለለበት ነው። መፅሐፍ ቅዱስ ደግሞ ይመልሳል። ➡ኢየሱስ በዮሐንስ እጅ ለምን ተጠመቀ? ከዝህ ቀጥለን 5 ምክንያቶችን እንዘርዝር፦ 1. ኢየሱስ የእግዚአብሔር በግ መሆኑን ለማሳወቅ ዮሐ 1፥29 2.በነቢያት የተነገሩ ትንቢት እንድፈጸም(በመንፈስ ቅዱስ እንደምቀባ የተተነበየው) ሀዋ 10፥38 3. እንደምሞትና እንደምነሳ ለማሳወቅ ሉቃ 12፥50 4.ለመተባበር(ከዮሐንስ አገልግሎት ጋር) 5.ለክርስቲያኖች ምሳሌን ለማዘጋጀትም ነው። ❖በኢየሱስ ጥምቀት ጊዜ የተለያዩ የስላሴ አካላት እንደተሳተፉ ተጽፏል።ይህም፦ አብ-----------ስናገር (የምወደው ልጄ በማለት በማረጋገጥ) ወልድ---------በመጠቀም፤ስጸልይ መንፈስ ቅዱስ----በኢየሱስ ላይ በመውረድ ተሳትፈዋል። ❖ስጠመቅ መንፈስ ቅዱስ በኢየሱስ ላይ ወረደ ቀባውም። የተቀባውም፦ 1. ለነብይነት ማቴ 3፥17 2. ለክህነት ማቴ 17፥5 3. ለንግሥና መዝ 2፥7 ኢየሱስ ገና አግልግሎት ሳይጀምር በመንፈስ ቅዱስ ሀይል መቀባቱ አገልግሎት ያለ መንፈስ ቅዱስ ሀይል የማይቻል መሆኑንም ለማረጋገጥ ነው። ሀዋ 1፥8 ሉቃ 24 ''ሰማይ ተከፍቶ'' የምል ሀረግ አለ። በብሉይና በአዲሱ ኪዳን የተለያዩ ቦታዎች የሰማይን መከፈት የምያሳይ ቃል ተጽፏል። ኢሳ 64፥1 ህዝ 1፥1 ሀዋ 7፥56 ራዕ 4፥1 19፥11 ዘፍ 28፥12 ❖ሌላው'' በእርሱ ደስ የምለኝ '' የምል ሀረግ አለ። በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ “ጌታን ደስ ያሰኙ” የተባሉ ብዙ ነገሮች አሉ። 1. እግዚአብሔር እስራኤልን ይባርክ ዘንድ ደስ አለው (ዘኁ. 24፡1)። 2. እስራኤልን ሕዝቡ ያደርግ ዘንድ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው (1ሳሙ. 12፡22)። 3. የሰሎሞን ልመና እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው (1 ነገ. 3፡10)። 4. እግዝአብሔር በሕጉ በሚፈልገው ጽድቅ በጣም ይደሰታል (ኢሳ. 42፡21)። 5. እግዝአብሔር በልጁ ተደስቶ ነበር (ማቴ. 3፡17)። 6. በስብከት ሞኝነት ወንጌሉን ለማቅረብ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው (1ቆሮ. 1፡21)። 7. እግዚአብሔር ጳውሎስን ወንጌልን እንዲሰብክ መጥራቱ ደስ አለው (ገላ. 1፡15)። 8. ሙላት ሁሉ በክርስቶስ ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር ወደደ (ቆላ. 1፡19)። 9. ሄኖክ እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኘው መስክሮለታል (ዕብ. 11፡5)። 10. እግዚአብሔር በምስጋና መስዋዕት ደስ ይለዋል (ዕብ. 13፡16)። “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” — 2ኛ ቆሮ 13፥14 ተጻፈ በመብራቱ መንግሥቱ ብራና ቲዮሎጂካል አግልግሎት https://t.me/+UK-E6QjEaWz2OCgp
Show all...
ብራና ቲዮሎጅካል አገልግሎት

Pray+Study+Apply “ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።” — ራእይ 1፥3 “Blessed is he that readeth, and they that hear the words of this prophecy, and keep those things which are written therein: for the time is at hand.”

ዛሬ የማቴዎስ ወንጌል ጥናታችንን እንቀጥላለን። ስለቆየን ይቅርታ እንጠይቃለን 3፡00-4:00
Show all...
#ነቢያት የመፅሐፍ ቅዱሱ ነቢያት እንዲህ ሊከፈሉ ይችላሉ:- 👉 ቀደምት/ የዃላ (በዕብራውያን መፅ.ቅ) 👉 የጻፉ/ ያልጻፉ 👉 ታላላቅ/ ታናናሽ 👉 ቅድመ ምርኮ/ የምርኮ/ድህረ ምርኮ 👉 የእስራኤል/ የይሁዳ (ሰሜን/ ደቡብ) 👉 የእስራኤል/ የአሕዛብ https://t.me/+UK-E6QjEaWz2OCgp
Show all...
ብራና ቲዮሎጅካል አገልግሎት

Pray+Study+Apply “ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።” — ራእይ 1፥3 “Blessed is he that readeth, and they that hear the words of this prophecy, and keep those things which are written therein: for the time is at hand.”

💠የእግዚአብሔርን ፀጋ የምንጥልባቸው አራቱ መንገዶች እኛን ያቆመን የእግዚአብሔር ፀጋ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ፀጋ ውጭ እኛ ምንም ማድረግ አንችልም፡፡ "ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁ እኔ ነኝ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም ከሁላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ፥ ዳሩ ግን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም።" (1ኛ ቆሮ.15፡10) የእግዚአብሔርን ፀጋ ስንጥል ማደግ እናቆማለን፡፡ የእግዚአብሔርን ፀጋ ከጣልን መውደቃችን አይቀሬ ነው፡፡ የእግዚአብሄርን ፀጋ የምናጣበት ሃይል አልባ የሚያደርጉን አራቱ መንገዶች 1. ትህትናን መጣል   ሰው ትህትናን ከጣለ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ እንደሚወድቅ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ሰው እግዚአብሔር ከሰጠው ደረጃ በላይ ራሱን ከፍ አድርጎ ሲያይ ከእግዚአብሔር ጋር ይተላለፋል፡፡ እግዚአብሔር ፀጋን መስጠትና ማንሳት ከፍ ማድረግ እየፈለገ በራሱ ነገሮችን ማድረግ እንደሚችል የሚያስበውን ትእቢተኛን ሰው ግን ከመቃወም ውጭ ምንም ሊያደርገው አይችልም፡፡   "ነገር ግን ጸጋን አብልጦ ይሰጣል፤ ስለዚህ፦ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣልይላል።" (ያዕ. 4፡6) 2. እውቀትን መጣል ሰው ከመሬት ተነስቶ አውቆ የጨረሰ ከመሰለው በህይወቱ ማደግና መለወጥ አቁሟል ማለት ነው፡፡ ይህ ሰው ለአዲስ ተግዳሮት በእውቀት ራሱን ካላስታጠቀ መውደቁ አይቀሬ ነው፡፡ ይህ ሰው ያወቀና የጨረሰ ከመሰለው እጅግ አሰቃቂ ነው፡፡ "ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋም፥ ሁላችን እውቀት እንዳለን እናውቃለን። እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል። ማንም አንዳች የሚያውቅ ቢመስለው ሊያውቅ እንደሚገባው ገና አላወቀም፤" (1ኛ ቆሮ. 8፡1-2) "ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ አንተም እውቀትን ጠልተሃልና እኔ ካህን እንዳትሆነኝ እጠላሃለሁ፤" (ሆሴ. 4፡6) "በእግዚአብሔርና በጌታችን በኢየሱስ እውቀት ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።"( 2ኛ ጴጥ. 1፡2) 3. እምነትን መጣል ሰው በእግዚአብሔር ላይ መደገፍን ትቶ በራሱ ስራ ላይ ሲደገፍ ከእግዚአብሔር ፀጋ ይጎድላል፡፡ ሰው ለመዳንም ሆነ ከዳነ በኋላ ለመቀደስ ፣ ለእግዚአብሔር መንግስት ለመስራትና እግዚአብሔርን ለማስደሰት በራሱ ጉልበትና ቅልጥፍና ላይ ሲደገፍ ከእግዚአብሔር ፀጋ ይጎድላል፡፡ "በሕግ ልትጸድቁ የምትፈልጉ ከክርስቶስ ተለይታችሁ ከጸጋው ወድቃችኋል።" (ገላ. 5፡4) "ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ ተብሎ እንደተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።" (1ኛ ቆሮ.1፡30-31) 4. ምስጋናን መጣል ሰው ምንም ከማይወጣለት መልካም አምላክ ጋር እየኖረ ካጉረመረመና ማመስገን ካቃተው ከእግዚአብሔር ፀጋ ይጎድላል፡፡ ሰው በእግዚአብሔር አሰራር ላይ አቃቂር ማውጣት ከቻለ የሆነ የሳተው ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ሰው ከእግዚአብሔር በላይ የሚያውቅ ከመሰለው የሆነ የተዛባ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ሰው በእግዚአብሔር አሰራር ካልታመነ ከእግዚአብሔር ጋር በየዋህነት መኖር ፣ ራሱን መስጠት ፣ ለእግዚአብሔር በየዋህነት መስራትና ፍሬያማ መሆን ያቅተዋል፡፡    "አንድ መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ፦ ጌታ ሆይ፥ካልዘራህባት የምታጭድ ካልበተንህባትም የምትሰበስብ ጨካኝ ሰው መሆንህን አውቃለሁ፤ ፈራሁም ሄጄም መክሊትህን በምድር ቀበርሁት፤ እነሆ፥ መክሊትህ አለህ አለ።"(ማቴ. 25፡24-25) "ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንዳንጎራጎሩ በሚያጠፋውም እንደጠፉ አታንጐርጕሩ።" (1ኛ ቆሮ. 10፡10) አብይ ዋቁማ https://t.me/+UK-E6QjEaWz2OCgp
Show all...
ነገረ-ፍፃሜ(Eschatology)

Your word is true ቃልህ እውነት ነው ይህ ቻናል ነገረ ፍፃሜያዊ የሆኑ ሃሳቦች የሚዳሰሱበት እንድሁም መንፈሳዊ መጽሐፍቶች÷መዝሙሮች÷ወቅታዊ ፅሁፎች የምለቀቁበት ቻናል ነው። “መንፈሱና ሙሽራይቱም፦ ና ይላሉ። የሚሰማም፦ ና ይበል። የተጠማም ይምጣ፥ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው ይውሰድ።” — ራእይ 22፥17

“እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፥” — ዕብራውያን 10፥19-20
Show all...
HAPPY REFORMATION DAY! 506 years ago in 1517 Martin Luther a German Augustinian Monk nailed the 95 Theses or protests to the Church door of Wittenberg and then it began but ultimately it didn't begin with Luther, before him Jan Hus the Czech reformer who was burnt at the stake in 1415 and prior was John Wycliffe lived during the 1100's who saw problems with Rome's teachings. The Reformation happened because the Roman Church was corrupting the Church with false doctrines, the Pope was NOT the head of the Church Christ was (Eph 1:22). Tradition was NOT on the same authority as Holy Scripture, Purgatory which connected to indulgences some could pay money to the church and get 100's of years off Purgatory which is after the person dies the person would go through the fires of purgatory and be cleansed (or purged even through Christ cleanses you of ALL sin). But most important doctrine that was corrupted was salvation or the Gospel salvation is by grace through faith in Christ. The 5 solas of the Reformation are we are saved by Grace alone, through Faith alone, in Christ alone, according to Scripture alone and to the glory of God alone. Luther emphasised grace in his theology as did St. Augustine to show that we cannot earn our salvation but it's by unmerited favour (Romans 11:6). The motto of the Reformation were .. Post Tenebrus Lux - after darkness light. Which means after the darkness of the middle ages which Rome brought about the light of the Gospel shown through. Ecclesia semper reformanda which means "Church always reforming" meaning the Church (the believers) can fall into error and needs to always submit to the authority to God's Word alone, the Church is reformable but the Holy Scriptures cannot, God speaks through the Word, we obey God when we submit to His Word. Sola Fide https://lutheranreformation.org/theology/sola-fide/ Sola Scriptura https://lutheranreformation.org/theology/sola-scriptura/ History of the Reformation. http://www.ligonier.org/blog/reformation-and-men-behind-it/ https://t.me/+UK-E6QjEaWz2OCgp
Show all...
Sola Fide - Lutheran Reformation

by Rev. Christopher Maronde Faith is only as good as its object.  This is the danger of misunderstanding Sola Fide: that we would focus on faith in and of itself, and forget about the object of faith.  We would then spend all our time talking about our faith, bragging about our faith, and worrying about the... Read More >

የጳውሎስ ሕይወት እና አገልግሎት 33* በደማስቆ መንገድ ተለወጠ፣ ተጠርቷ ተሾመ (ሐዋ. 9:1–19፤ 22:6–11፤ 26:12–18፤ ገላ. 1:15–16) 33-35 በደማስቆ ለጥቂት ጊዜ ቆየ (ሐዋ. 9፡19ለ)፤ ወደ አረብ አገር ሄደ (2ቆሮ. 11:32; ገላ. 1:17); ወደ ደማስቆ ተመለሰ (ገላ. 1:17፤ የሐዋርያት ሥራ 9:20–22?)፤ እንዳይታሰር በከተማው ቅጥር አመለጡ (ሐዋ. 9፡23–24፤ 2 ቆሮ. 11፡32–33) በኢየሩሳሌም ከጴጥሮስ ጋር ተገናኘና ያዕቆብን አየው (ሥራ 9:26–30፤ ገላ. 1:18) የግሪክ እምነት ተከታዮች ሊገድሉት ፈለጉ። ወደ ጠርሴስ ሸሸ (ሐዋ. 9:28–30፤ ገላ. 1:21) 35–45 በሶርያ/ኪልቅያ ያሉ አገለገለ (2ቆሮ. 11፡22–27?) 45–47* ከበርናባስ ጋር በአንጾኪያ ያገለግሉ ነበር (ሐዋ. 11፡25–26) የኢየሩሳሌም ሁለተኛ ጉብኝት፤ የረሃብ ጊዜ (ሐዋ. 11፡27–30፤ ገላ. 2፡1–10) 47-48 የመጀመሪያ ሚስዮናዊ ጉዞ (ሐዋ. 13፡4–14፡26)፡ 1.5 ዓመታት? 48* ከበርናባስ ጋር፣ በአንጾኪያ “ጥቂት ጊዜ” አሳልፏል (ሐዋ. 14፡28፤ ገላ. 2፡11–14)፤ የገላቲያ መልዕክት መጻፍ 48/9። 49* ለሐዋርያዊ ጉባኤ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሰ (ሐዋ. 15) ጳውሎስና በርናባስ ወደ አንጾኪያ ተመለሱ (ሐዋ. 15፡30–33)፣ ነገር ግን በዮሐንስ ማርቆስ ላይ አለመግባባት እንዲለያዩ አደረጋቸው (ሐዋ. 15፡36–41) 49–52* ሁለተኛ ሚሲዮናዊ ጉዞ (ሐዋ. 15፡36–18፡22)፡ 3-4 ዓመታት? 49 ጳውሎስና ሲላስ በትንሿ እስያ በኩል ወደ ደቡብ ገላትያ፣ ወደ መቄዶንያ ተጓዙ (ፊልጵስዩስ [1 ተሰ. 2:2]); ተሰሎንቄ [1 ተሰ. 2:2; ፊል. 4:15-16]; እና ቤርያ (የሐዋርያት ሥራ 17፡10–15)፣ ከዚያም ወደ አካይያ (አቴንስ [1 ተሰ. 3፡1] እና ቆሮንቶስ [2 ቆሮ. 11፡7–9]) 51.5–52* በቆሮንቶስ 1.5 ዓመታት አሳልፏል (ሐዋ. 18፡11)። በጋልዮስ ፊት ታየ (የሐዋርያት ሥራ 18፡12–17)። 1 እና 2 ተሰሎንቄን ጽፏል 52 ወደ ኢየሩሳሌም ይመለሳል? ( የሐዋርያት ሥራ 18:22 ) 52–57* ሦስተኛው የሚስዮናውያን ጉዞ (ሐዋ. 18፡23–21፡17)፡ 5 ዓመት? 52 ወደ አንጾኪያ ተጉዟል፣ “የተወሰነ ጊዜ” አሳልፏል። በገላትያና በፍርግያ በኩል ይጓዛል (የሐዋርያት ሥራ 18:23) 52–55 ወደ ኤፌሶን ደረሰ (ሐዋ. 19፡1፤ 1 ቆሮ. 16፡8)፤ ለሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ (የሐዋርያት ሥራ 20:31) እና 1 ቆሮንቶስ ጽፏል; ወደ ቆሮንቶስ አጭር፣ “የተጎዳበትን ጉብኝት” አደረገ (2 ቆሮ. 2:1)፣ ከዚያም ወደ ኤፌሶን ተመልሶ “የሐዘን ደብዳቤ ” (አሁን የጠፋው) ለቆሮንቶስ ጻፈ (2 ቆሮ. 2:3–4፤ 7:8–16) 55–56* ወደ ሰሜን ወደ መቄዶንያ ተጓዘ፣ ቲቶ አገኘው (ሐዋ. 20:1፤ 2 ቆሮ. 2:12–13)፤ ይላል 2ኛ ቆሮንቶስ 7:5። ምናልባት የኤፌሶንን ቤተክርስቲያን ለጢሞቴዎስ አደራ የሰጠው በዚህ ጊዜ ይሆናል። 57* ክረምቱ በቆሮንቶስ (የሐዋርያት ሥራ 20:2-3፤ 2ቆሮ. 9:4)፣ ከቆሮንቶስ ለሮሜ ሰዎች ጻፈ። ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዘል። በዚያም ተያዘ (የሐዋርያት ሥራ 21:27-36) 58-59 የመጀመሪያው የቂሳርያ እስር (ሐዋ 24-26)። አንዳንዶች ፊሊጲሲዮስ ኤፌሶን እና ቆላስያስን ከዚህ እንደጻፈ ይገምታሉ። 60-61 የሮም ጉዞ እና የሁለት አመት እስር (ሐዋ 27-28)። ለሎች የእስር ደብዳቤዎች የተጻፋት በዚህ ጊዜ እንደሆነ ይገምታሉ። https://t.me/+dbCG8lRvV2VlNWM0
Show all...
Brana Youth Theological Ministry

Pray+Study+Apply “ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።” — ራእይ 1፥3 “Blessed is he that readeth, and they that hear the words of this prophecy, and keep those things which are written therein: for the time is at hand.”