en
Feedback
Chess in Ethiopia(ሰንጠረዥ)

Chess in Ethiopia(ሰንጠረዥ)

Open in Telegram
847
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-130 days
Posts Archive
👆Try all the puzzles with out using engines 👏👏👏

White turn Mate in 3
White turn Mate in 3

White to move In how many moves can you capture the black rook?
White to move In how many moves can you capture the black rook?

White to move and draw
White to move and draw

White to move and mate in 4
White to move and mate in 4

White to play mate in 4
White to play mate in 4

White to play mate in 2
White to play mate in 2

እስከ አሁን ባለው የምዝገባ ሂደት የሴቶች ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑ ያሳያል ያልተመዘገቡ እንዲመዘገቡ ላልሰሙ እንዲሰሙ ወይም እንዲያውቁ በማድረግ እንተባበር 👇👇👇 https://chess-results.com/Tnr700038.aspx?lan=1

መልእክት የ2015 የ3ኛው ራፒድና ብሊቲዝ ቼዝ ሻምፒዮናን ይመለከታል የኢትዮጵያ ቼዝ ፌዴሬሽን የ3ኛው ራፒድና ብሊቲዝ ሻምፒዮና ከህዳር 8 እስከ 12/2015 ዓ.ም ለማዘጋጀት የተወዳዳሪዎች ምዝገባ እያከናወነ መሆኑ ይታወቃል ይሁን እንጂ ህዳር 11/2015 (እሁድ) የታላቁ ሩጫ ፕሮግራም በመኖሩ የትራንስፖርት ችግር ሊያጋጥም ስለሚችል ውድድሩን በአንድ ሳምንት ማራዘም አስፈልጓል፡፡ በዚህም መሰረት የ3ኛው ራፒድና ብሊቲዝ ቼዝ ሻምፒዮና ከህዳር 16 እስከ ህዳር 19/2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ልደታ አከባቢ በሚገኘው በፍሊንትስቶን ሆምስ (መርካቶ ህንፃ 7ኛ ፎቅ) ላይ የሚካሄድ መሆኑን እየገለፅን ያልተመዘገባቹ በመመዝገብ ተሳታፊ እንድትሆኑ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ የኢትዮጵያ ቼዝ ፌዴሬሽን

የሀሳብ ድጋፍ የራፒድና ብሊትዝ ውድድር በዚህ ሳምንት ከአርብ ጀምሮ እስከ እሁድ እንደሚካሄድ ይታወቃል። ይህም ማለት አርብና ቅዳሜ ራፒድ ውድድር ሲካሄድ እሁድ ብሊትዝ ውድድር ይካሄዳል ። ይህ በእንዲህ እያለ እሁድ ታላቁ ሩጫ ይካሄዳል። በዚህም ምክንያት የተወሰኑ መንገዶች ይዘጋሉ። የብሊትዝ ውድድር ደግሞ እሁድ ጥዋት ይጀመራል። በመሆኑም በመንገድ መዘጋት ምክንያት ምን ያህል ተጫዋች ይቸገር ይሆን? የውድድር ቦታ፡ ልደታ ነው እናመሰግናለን

White to move and win
White to move and win

ለውድ ቼዝ ቤተሰቦች ከዛሬ ጀምሮ እስከ እሁድ 2022 great Ethiopian sport expo ላይ በኤግዝብሽን ማእከል ላይ በመምጣት ቼዝ ይጫወቱ ያስተምሩ ይማሩ ሁላችሁም ተጋብዛቹሀል ከጥዋቱ 3
ለውድ ቼዝ ቤተሰቦች ከዛሬ ጀምሮ እስከ እሁድ 2022 great Ethiopian sport expo ላይ በኤግዝብሽን ማእከል ላይ በመምጣት ቼዝ ይጫወቱ ያስተምሩ ይማሩ ሁላችሁም ተጋብዛቹሀል ከጥዋቱ 3 ሰአት እስከ ምሽት 12 ፡30 ሰአት

ለራፒድና ብሊትዝ ውድድር የተመዘገቡ ተወዳዳሪዎች 👇👇👇 https://chess-results.com/Tnr691083.aspx?lan=1

ሀገር አቀፍ የራፒድና ብሊትዝ ሻምፒዮና ውድድር ምዝገባ እየተካሄደ ነው። የውድድር ቀን፡ ከህዳር 8-11/2015 ዓ.ም መመዝገብያ፡ በነፃ የምዝገባ ሂደት፡ በኦንላየን የውድድር ቦታ፡ አዲስ አበባ ሆኖ በሂደት የሚገለፅ ለመመዝገብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ። ሁለት ሊንኮች ስላሉ የተኛው ሊንክ ለእርስዎ እንደሚሆን መመርያው በትክክል ተረድተው ይመዝገቡ። የፊደ አይዲ(FIDE ID) ላላቸው ተጫዋቶች ፊደ አይዲ ያላቹ ተጫዋቶች ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ በመጠቀም መመዝገብ ትችላላችሁ 👇👇👇 https://forms.gle/9wyenkBbk8Na6omo7 ፊደ አይዲ (FIDE ID) የሌላቹ ተጫዋቶች ፊደ አይዲ የሌላቹ ተጫዋቶች የመመዝገብያ ፎርሙ በእንግሊዝኛ መሞላት አለበት። የትውልድ ቀን በፈረንጅ መሞላት አለበት። እያንዳንዱ መረጃ ከፓስፖርት ወይም መታወቂያ ጋር አንድ አይነት መሆን አለበት ። ለመመዝገብ ከዚህ በታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ 👇👇👇 https://forms.gle/2RmJfSetL5sTW6QL6 ማሳሰብያ 👉የማይወዳደር ሰው መመዝገብ የለበትም 👉ከዚህ በፊት በአንድ የሬቲንግ ውድድር ተወዳድራቹ ከሆነ ፊደ አይዲ በእርግጠኝነት ስላላቹ የማታውቁት ከሆነ Google በማድረግ ወይም በመጠየቅ ፊደ አይዳቹን ማወቅና መያዝ አለባቹ። 👉 የተመዘገቡት በቅርብ ማሳወቅ እንጀምራለን በዚህ ውድድር ለመሳተፍ የእድሜም ሆነ የፆታ ገደብ የለውም። መጫወት የሚፈልግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ መመዝገብ እና መወዳደር ይችላል። በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑት የሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ይሰጣል። በራፒድና ብሊትዝ ድምር ውጤት መሰረት ሽልማቱ የሚከተለው ይመስላል በወንዶች 1ኛ ብር 5000 2ኛ ብር 4000 3ኛ ብር 3000 4ኛ ብር 2500 5ኛ ብር 1500 በሴቶች 1ኛ ብር 3000 2ኛ ብር 2500 3ኛ ብር 2000 4ኛ ብር 1500 5ኛ ብር 1000 ተጨማሪ መመርያዎች ከውድድሩ በፊት ግልፅ ይደረጋሉ። ሁላችሁም ተጋብዛቹሀል እናመሰግናለን

ሀገር አቀፍ የራፒድና ብሊትዝ ሻምፒዮና ውድድር ቦታ፡ አዲስ አበባ ቀን፡ ከህዳር 8-11/2015 ዓ.ም ይህ ለሁሉም ክፍት የሆነ በየአመቱ የሚካሄድ ተወዳጅ ሀገር አቀፍ የራፒድና የብሊትዝ ሻምፒዮና ውድድር ሲሆን ከ1ኛ እስከ 5ኛ ለወጡ የብር ሽልማት ይሰጣቸዋል። ሁላቹሁም ተጋብዛቹሀል ይመዝገቡ ይወዳደሩ የምዝገባው ሂደት በቅርብ እናሳውቃለን አንድ ቤተሰብ ነን የኢትዮጵያ ቼዝ ፌዴሬሽን

እንኳን ደስ አለን ኢትዮጵያ የቼዝ አለምአቀፍ የውድድር አዘጋጅ(International Organiser) ለመጀመርያ ግዜ አግኝታለች። አቶ ሰይፉ በላይነህ ሀገርአቀፍ እና አለምአቀፍ ውድድር በማዘጋጀት
እንኳን ደስ አለን ኢትዮጵያ የቼዝ አለምአቀፍ የውድድር አዘጋጅ(International Organiser) ለመጀመርያ ግዜ አግኝታለች። አቶ ሰይፉ በላይነህ ሀገርአቀፍ እና አለምአቀፍ ውድድር በማዘጋጀት የኢትዮጵያ ስም ከፍ ብሎ እንዲነሳ እያደረጉ የሚገኙ የቼዝ ባለሙያ ናቸው። በአለምአቀፍ ቼዝ ፌዴሬሽን የተዘጋጀውን ስልጠና እና ፈተና በብቃት በማለፍ እንዲሁም አለምአቀፍ ውድድሮችን እና ሀገርአቀፍ ውድድሮችን ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ በማዘጋጀት የአለምአቀፍ ውድድር አዘጋጅ(IO) መአርግ ከአለአቀፍ ቼዝ ፌዴሬሽን ማግኘት ችለዋል። ይህ እንደሀገር እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በጣም የሚያኮራ ውጤት ነው ። 👉ማንኛውም አለምአቀፍ ውድድሮችን ኢትዮጵያ ውስጥ ማዘጋጀት ይቻላል 👉ደረጃቸውን የጠበቁ አለአቀፍ ውድድሮችን ኢትዮጵያ ውስጥ በማዘጋጀት የቱሪዝም ፍሰትን መጨመር ይቻላል 👉ውድድሮችን ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲዘጋጁ ያግዛል 👉ተጫዋቶቻችን ደረጃቸውን በጠበቁ ውድድሮችን እንዲወዳደሩ ይረዳል 👉የውድድር ብዛት ይጨምራል 👉የቼዝ ተደራሽነት ይጨምራል 👉 ኢትዮጵያ ውስጥ የሚዘጋጁ ውድድሮች አለአቀፍ ሽፋን ያገኛሉ። እንዲሁም ሌሎች ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን ከሁሉም በላይ ደግሞ በሀገር ደረጃ በሁሉም ዘርፍ ባለሙያዎች እንዲበዙ ይህ ትልቅ ምሳሌ በማድረግ እንዲከተሉ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ። አቶ ሰይፉ በላይነህ ለቼዝ ስፖርት እያደረጉት ያለው ከፍተኛ አስተዋፅኦ በሁሉም የቼዝ ቤተሰብ አድናቆት እና ክብር የተቸራቸው ሲሆን አሁን ባገኙት ከፍተኛ መአርግ ደግሞ ሀገራቸውን እና የቼዝ ማህበረሰቡን በላቀ ሁኔታ እንደሚያገለግሉ ይጠበቃል። IO Seifu Belayneh Congratulations!!! እንኳን ደስ አለዎት