cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

Show more
Advertising posts
1 055
Subscribers
No data24 hours
+17 days
-930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

•••✿ ❒ ነብዩሏህ_የአቆብ_ና_ዩሱፍ_ዐለይሂ_ሰላም_ታርክ ❒✿••• #ክፍል 4 አሁን ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ፊለስጢንን ለቅቆ የሀራንን ምድር ከረገጠ 20 አመታትን አስቆጥሯል። ያዕቁብም አጎቱ ዘንድ በመሄድ፦"አጎቴ አሁን ፍቀድልኝ'ና ሚስት ልጆቼን ሰብስቤ ቤተሰቦቼ ጋር ልሂድ" ይለዋል። አጎቱ ላባንም፦"ያዕቁብ እኔ ባንተ ሰበብ ብዙ ንብረቴ በረካ ሆኖልኛል።ስለዚህ የፈለግከውን ያህል ንብረት ጠይቀኝ" አለው። ላባን በጣም ለቁጥር ሚያዳግት የእንስሳት መዐት ስለነበረው ያዕቁብም፦"በዚህ አመት የሚወለዱትን ሁሉ ባጎች ስጠኝ። ከተቀረው እንስሳቶችህ መልካቸው ጥቁር በነጭ የሚወልዱትንም ስጠኝ። ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችንም ስጠኝ" አለው። አጎቱ ላባንም፦"እሺ" አለው። ያዕቁብም ይህን ሀላፊነት ልጆቹ እንዲወጡ አዘዘ። በመጀመርያ ያዕቁብ እርጉዝ የሆኑ እንስሳቶችን ከሌሎቹ እንስሳት የሶስት ቀን መንገድ ያህል ርቀት አራራቃቸው። ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችን እንደዚያው አራራቃቸው።ይህን ካደረገ በኋላ እርጉዞቹም ወለዱ ያዕቁብም ድርሻውን ለይቶ በአላህ ትዕዛዝ ለጉዞ ተዘጋጀ። አሁን ያዕቁብ የብዙ ሺህ በጎች...እንስሳቶች...እና የብዙ አገልጋዮች ባለቤት ሆኗል። ወደ ፊለስጢን ጉዞ ሲዝጀምሩ ራሂል የተባለችዋ የያዕቁብ ሚስት የአባቷን ጣኦት ደብቃ ይዛ ወጣች። ያዕቁብ ልጆቹን፣ሚስቶቹን፣አገልጋዮቹን፣እንስሳቶቹን...ሁሉ ሰብስቦ በረሀውን እያቋረጠ ብዙ ተጎዞ የሀራንን ምድር ካጋመሰ በኋላ አጎቱ ላባን እና የሀራን ከተማ ነዋሪዎች ተከትለውት ደረሱበት። ልክ እንዳገኙት አጎቱ ላባን በወቀሳ መልኩ፦"ያዕቁብ ለምን ሳትነግረኝ ትተህ ትሄዳለህ!!! ምነው በደስታ ተሰነባብተን ከአከባቢው ህዝብ ጋር ጨፍረን ብንሸኛቹስ" በማለት አንድ ጣኦት ይዘው እንደመጡም አክሎ ጠየቀው። ያዕቁብ ዐ ሰ ምንም አይነት ከጣኦት ጋር ግንኙነት ባይኖረውም ለአጎቱ ሲል የሚስቶቹን እቃ ሀሉ ፈተሸለት ምንም አላገኘም። ራሂል ግን ጣኦቱን ይዛው ስለነበር ለፍተሻ ፍቃደኛ አልሆነችም ነበር አሞኛል አልነሳም አለች። ያን ግዜ ያ ጣኦት ምናልባት ጀልዓድ በተባለ ዳገት ላይ ይኖራል በሚል ግምት ላባን ልጆቹን እና የእህቱን ልጅ ያዕቁብን ተሰናብቷቸው ተመለሰ። ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ሊገባ ጥቂት ሲቀራው መላዕክት እየወረዱ እንኳን ደህና መጣህ እያሉት ያልፉ ነበር። አሁን ያዕቁብ ሳዒር የምትባል ቦታ ላይ ደርሷል ግን ሀገሩ ሊገባ የወንድሙን በቀል ፈርቷል። እዛው ሆኖ እንደማለማመጥ አይነት ነገር ፅፎ ደብዳቤ ለወንድሙ ላከለት። በነጋታው ሌላ የዛቻ ደብዳቤ የያዘች ወረቀት ዒስ(የያዕቁብ ወንድም) 400 እግረኛ ጦር አሰልፎ እየመጣ መሆኑን የሚያስረዳ መልዕክት ከወደ ፊለስጢን በኩል ለያዕቁብ መጣችለት። ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ። ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ። ከዚያም ወንድሙን ሊያስደስት በርከት ያለ ስጦታም አዘጋጀለት... 200 ሴት ፍየሎችን እና 20 ወንድ ፍየሎች 200 ሴት በጎችን እና 20 ወንድ በጎች 30 (ኮርማ)በሬዎችን እና 40 ላሞች 20 ሴት ግመሎችን እና 10 ወንድ ግመሎች እና አራቱንም የስጦታ አይነቶችን ለያይቶ ሊልክ በአራት ቡድን የተደራጀ አገልጋዮችን አዘጋጀ እና ቀድሞ አንዱን ቡድን ለከ። የመጀመርያው ቡድን ስጦታን ይዞ ሄዶ ትንሽ ራቅ ሲል ሁለተኛውን ይልካል ሁለተኛውም ትንሽ ራቅ ሲል ሶስተኛውን ይልካል.... እንዲ እንዲ እያለ አራቱንም የስጦታ አይነት ከነ አገልጋዮቻቸው ጨምሮ፦"ማንም የማን ነው ብሎ ከጠየቃችሁ ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው በሉ" ብሎ ላካቸው። ይህንንም ሊያደርግ የቻለው ወንድሙ ዒስ ስጦታዎች በተከታታይ ሲመጡለት ደስታው የላቀ ይሆናል በሚል ነው። ከዚያም የመጀመሪያውን ስጦታ የያዘው የአገልጋልይ ቡድን ዒስ እና ወታደሮቹ ያሉበትን ቦታ ሲደርሱ ዒስ፦"ይህ የማን ነው?" ብሎ ጠየቀ። አገልጋዮቹም፦" ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው" አሉት። እሱን ተቀበላቸውና ሁሉም የስጦታ ነጂ ቡድኖች ስጦታዎቻቸውን ተራ በተራ እየነዱ አስረከቡት። ያዕቁብም ሚስቶቹን ልጆቹን እና የተቀሩ አገልጋዮቹን አስከትሎ በሌሊት ወደ ወንድሙ ጉዞ ጀመረ። (በነገራችን ላይ በዚህች የሌሊት ጉዞ ነበር ክርስቲያን ወገኖች ያዕቁብ እና እግዚአብሄር ተደባድበው ያዕቁብ አሸነፈው የሚሉት።) ሌሊቱን ተጉዞ ፀሀይ ጀንበሯን አምልጣ መውጣት ስትጀምር ለ20 አመታት ያህል የተለያዩ ወንድማሞች አይን ለአይን ተገጣጠሙ። ዒስ 400 ጦረኛዎችን አሰልፏል።ያዕቁብም ወንድሙን ሲያየው 7 ግዜ አጎበደደለት(ይህ በዘመናቸው ሀራም አልነበረም የዘመናቸውም ሰላምታ ነበር። በቀጣይ ክፍላችን ለዩሱፍ ሲሰግዱ እንዳስሳለን" ዒስ ዱዓውን ከአባቱ የዘረፈውን ወንድሙን ሲያይ ሄዶ ተጠምጥሞበት ወንድሙን እየሳመ ያለቅስ ጀመር።በዚህ አጋጣሚ ከአጠገቡ ያሉትን ሴቶችን ልጆችን እና አገልጋዮችን ሲመለከት፦"ይሄም ሁሉ ኬት አምጥተህ ነው?" አለው። ያዕቁብም፦"እነዚህ አላህ የሰጠኝ ስጦታዎቼ ናቸው" አለው። ይህን ግዜ የያዕቁብ ልጆች እና ሚስቶች ተራ በተራ እየመጡ ዒስን ከዘየሩ በኋላ ያዕቁብ በአገልጋዮቹ አማካኝነት ለዒስ የላከውን ስጦታ ዒስ መቀበል እንቢ አለ። ያዕቁብም ለምኖት እንዲቀበል አደረገው'ና አብረው በረሀውን እያቆራረጡ አባታቸው ወደሚገኝበት የፊለስጢን ምድር መትመም ጀመሩ። በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ያኔ....ያዕቁብ አጎቱ ጋ ሲሄድ ተኝቶ ህልም ያየበትን ቦታ ደረሱና እዛ ቦታ ያዕቁብ በ200 በግ ያንን ቦታ ከአንድ ገበሬ ገዛው'ና አንድ ትልቅ የአምልኮ ቦታ ሰራ(ቁድስ) ከዚያ በኋላ ነው በሱለይማን ዘመን ሱለይማን ያደሰው። በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ነበር አንድ ደስታ እና ትልቅ ሀዘን በያዕቁብ ቤተሰብ የተከሰተው። ነፍሰ ጡር የነበረችው ትንሿ ራሂል ምጥ አስቸገራት...ብዙ ከተጨነቀች በኋላ ቢንያሚን የተባለ ልጅ ተገላግላ ለራሷም ዱንያን ተገላገለቻት። ያዕቁብም ባለቤቱን መንገድ ላይ ቀብሮ ሀዘኑን ታቅፎ ወደ አባቱ ጉዞ ቀጠለ። ከአባቱም ተገናኝቶ በከንዓን ምድር ሀብሩን በምትባል(ኢብራሂም ይኖር በነበረበት) አካባቢ መኖር ጀመረ። ኢስሀቅም እርጅና ተጫጭኖትም ስለነበር ጌታው የፃፈለትን 180 አመት ካጠናቀቀ በኋላ ነፍሱን ለጌታው አስረከበ። የነበቢዩሏህ የኢስሃቅ ዐለይሂሰላም ታረክ አዚህ ላይ ተፈፀመ። የነቢዩሏህ የአቆብ ዐለይሂሰላም ታሪክ የቀረውን የነቢዩሏህ ዩሱፉ ታረክ ውስጥ እናየወለንን!!       •••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿••• በቀጣይ #ነብዩሏህ_አዩብ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰 #share https://t.me/Umete_Resul
Show all...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

2

•••✿ ❒ ነብዩሏህ_የአቆብ_ና_ዩሱፍ_ዐለይሂ_ሰላም_ታርክ ❒✿••• #ክፍል 3 ይህችን ሌሊትም እሱ ጋር አሳልፈው በነጋታው እንደሚሄዱ ካሳመናቸው በኋላ በጥሩ መስተንግዶ እራት አብልቷቸው ያዕቁብ ስለተባለው ነቢይ መጠየቅ ጀመረ።በህይወት እንዳለ እና ዩሱፍ በተባለው ልጁ ሀዘን ምክንያት በጣሙን እንደተጎዳ ነገሩት። ዩሱፍ ይህን ሁሉ ሲሰማ ሆድ እየባሰው ከእንባው ጋር ትንቅንቅ ቢገጥምም ይህን ሀዘኑን ግን ለወንድሞቹ ግልፅ ሊያደርግ አልፈለገም።ያውቁኛል ብሎ ሰግቶ..... በነጋታው ዩሱፍ አገልጋዮቹን ጠርቶ፦"ለእህሉ የከፈሉትን ገንዘብ በየከረጢታቸው ውስጥ ደብቁትና ሳያውቁ ስጧቸው" ብሎ አዘዘ። ዩሱፍ ባዘዘውም መልኩ የከፈሉት ገንዘብ ተመልሶ በየከረጢታቸው ተጨመረላቸው። በመጨረሻም ሲሸኛቻው፦"በሚቀጥለው ዙር ስትመጡ ከንዓን ትታችሁት የመጣችሁትን ትንሹን ወንድማችሁን ይዛችሁ ኑ። እሱን ካላመጣችሁት ግን ምንም አይነት እህል አንሰፍርላችሁም" ብሎ ሸኛቸው። እነሱም እንደሚሞክሩ ቃል ገብተውለትጉዞ ወደ ከንዓን ጀመሩ። ረጅም ተጉዘው ከንዓንም ሲደርሱም በግብፅ ከተማ የገጠማቸውን ሁሉ ለአባታቸው ያዕቁብ ተረኩለት'ና በቀጣይ ዙር ግን ታናሽ ወንድማቸውን ቢንያሚንን ካላመጡ ምንም አይነት ስፍር እንደማይሰፈርላቸው ነገሩት። አባታቸው ያዕቁብ ግን ልጆቹ ከዚህ በፊት በልጁ ዩሱፍ የፈፀሙትን በማስታወስ ዳግም ልጁን ቢንያሚንን ለነሱ አምኖ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም ነበር። ይሁን እንጂ ያዕቁብ ምንም እንኳን ውድ ልጁን ቢንያሚንን ከአጠገቡ ማራቅ ቢከብደውም ከፊትለፊቱ የተደቀነው ድርቅ እና ቸነፈር ቢንያሚንን ወደ ግብፅ ለመላክ አስገድዶታል። ከመላኩ በፊትም ያዕቁብ ልጆቹን ሰብስቦ፦"ካልተከበባችሁ በስተቀር እርሱን(ቢንያሚንን) በእርግጥ የምታመጡልኝ ለመሆናችሁ ከአላህ የሆነን ቃል ኪዳን መተማመኛ እስከምትሰጡኝ ድረስ ከናንተ ጋር ፈፅሞ አልልከውም" አላቸው። መተማመኛቸውንም ቃል ኪዳን በሰጡት ጊዜ ፦"አላህ በምንለው ሁሉ ላይ ምስክር ነው" አላቸው። በገቡት ቃል ኪዳን መሰረትም ቢንያሚንን ከአባታቸው እቅፍ አውጥተው ከከንዓን ምድር ነዋሪዎች ጋር ጉዞ ወደ ግብፅ ከመጀመራቸው በፊትያዕቁብ ልጆቹን ነጥሎ፦" ልጆቼ ሆይ! ባንድ በር አትግቡ፤ ግን በተለያየ በሮች ግቡ፤ ከአላህም (ፍርድ) በምንም አልጠቅማችሁም፤ (አልመልስላችሁም)፤ ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም፤ በርሱ ላይ ተመካሁ፤ ተመኪዎችም ሁሉ በርሱ ብቻ ይመኩ" ብሎ መከራቸው። በከንዓን እና በግብፅ መሀከል ያሉትን በረሃማ እና አሸዋማ መንገዶችን ካቋረጡ በኋላ የዩሱፍን ታናሽ ወንድም ይዘው ቤተ መንግስት ገቡ። ዩሱፍም ከመጀመርያው በተሻለ መልኩ ካስተናገዳቸው በኋላ ታናሽ ወንድሙን ለግል አውጥቶ፦"እነሆ እኔ ወንድምህ ነኝ ይሠሩት በነበሩትም ሁሉ አትቆጭ" ብሎት ነገ እሱን ግብፅ ሊያስቀረው የንጉስ ዋንጫ በሱ ከረጡት እንደሚሸጉጥበትም ጨምሮ ነግሮት ለአዳር ወንድሞቹ ጋ አቀላቀለው። ጠዋትም ለጉዞ በተዘጋጁ ግዜ ዩሱፍ እቃዎቻቸውን አስጭኖላቸው ሸኛቸው።ብዙም ሳይርቁም ዩሱፍ እና ወታደሮቹ ከአንድ ኮረብታ ላይ ሆነው፦" እናንተ ባለ ግመሎች ሆይ! እናንተ በርግጥ ሌቦች ናችሁ" በማለት ተጣሯቸው። እነሱም ዞረው፦" ምንድነው የጠፋችሁ?" አሉ። ዩሱፍም፦" ፦ የንጉሡ መስፈሪያ ጠፍቶናል፤ እርሱንም ላመጣ ሰው የግመል ጭነት ሽልማት አለው፤ እኔም በርሱ ተያዥ ነኝ" አላቸው። እነሱም፦" በአላህ እንምላለን በምድር ላይ ለማጥፋት እንዳልመጣን በእርግጥ ዐውቃችኋል፤ ሌቦችም አልነበርንም" አሉት። ዩሱፍም፦" ውሸታሞች ብትሆኑ ቅጣቱ ምንድነው?" አላቸው። እነሱም፦"ቅጣቱ (በያዕቆብ ሕግ) ዕቃው በጓዙ ውስጥ የተገኘበት ሰው (ራሱን አገልጋይ አድርጎ መወሰድ) ነው፤ እርሱም ቅጣቱ ነው። እንደዚሁ በደለኞችን እንቀጣለን" ብለው መለሱለት። (ፍተሻውን) ከወንድሙም ዕቃ በፊት በዕቃዎቻቸው ጀመረ፤ ከዚያም (ዋንጫይቱን) ከወንድሙ ዕቃ ውስጥ አወጣት።ሁሉም ደነገጡ ሚሉት ጠፋባቸው በዚህ አጋጣሚ እራሳቸውን ለማዳን፦"እሱ ቢሰርቅ ምንም አይደንቅም አንድ ታላቅ ወንድሙም እንዲህ ይሰርቅ ነበር" አሉ። ዩሱፍም በውስጡ፦"እናንተ ሥራችሁ የከፋ ነው፤ አላህም የምትሉትን ሁሉ ዐዋቂ ነው" አለ። ከዚያም እነሱ ራሳቸው በተስማሙት መሰረት እቃውን የሰረቀውን ቢንያሚንን ዩሱፍ እና ወታደሮቹ ይዘውት ሊሄዱ ሲሉ፦"አንተ የተከበርከው ሆይ! ፦ ለርሱ(ለቢንያሚን) በእርግጥ ትልቅ ሽማግሌ አባት አለው፤ ስለዚህ በርሱ ፋንታ አንደኛችንን ያዝ፤( ይህን ከፈፀምክ) እኛ ከመልካም ሠሪዎች ሆነህ እናይሃለንና" አሉት። ዩሱፍም፦"ዕቃችንን እርሱ ዘንድ ካገኘነው ሰው ሌላን ሰው ከመያዝ በአላህ እንጠበቃለን፤ እኛ ያን ከፈፀምን በእርግጥ በዳዮች ነን" አለ። ዩሱፍንም ለምነው ለምነው ተስፋ ሲቆርጡ ወደ ጎን ነጠል ብለው መመካከር ጀመሩ። በመሀልም ታላቅ ወንድማቸው፦" አባታችሁ በናንተ ላይ ከአላህ የሆነን መታመኛ ቃል ኪዳን በእርግጥ የያዘባችሁ መሆኑን ከዚህም በፊት በዩሱፍ ላይ ግፍ የሠራችሁትን አታውቁምን? ስለዚህ አባቴ ለኔ እስከሚፈቅድልኝ ወይም አላህ ለኔ እስከሚፈርድልኝ ድረስ የግብፅን ምድር አልለይም፤ እርሱ ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው። ወደ አባታችሁ፣ ተመለሱ፤ እንዲህ በሉትም፦ አባታችን ሆይ! ልጅህ ሰረቀ ባወቅነውም ነገር እንጂ አልመሰከርንም፤ ሩቁንም ነገር (ምስጢሩን) ዐዋቂዎች አልነበርንም፤ ያችንም በውስጧ የነበርንባትን ከተማ ያችንም በውስጧ የመጣነውን ባለ ግመል ጓድ ጠይቅ፤ እኛም በእርግጥ እውነተኞች ነን በሉ"   ብሏቸው እነሱን ትቶ ወደ ከተማይቱ ገባ። እነሱም ምንም አማራጭ አልነበራቸውምና የጫኑትን እህል ጭነው ወደ ከንዓን ተጓዙ።ልክ ከንዓን ሲደርሱ አባታቸው መንገድ ላይ እየጠበቃቸው ነበር። ሁሉንም ሰላም ብሎ የልጁ ቢንያሚንን መምጣት በጉጉት ሲጠብቅ ቢንየሚን የውሀ ሽታ ሆነበት።ልጄስ ብሎ ሲጠይቃቸውም የሆነውን ሁሉ ነገሩት። ይህን ግዜ አባታቸው በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ፦"አይደለም ነፍሶቻችሁ አንዳች ነገርን ለናንተ ሸለሙላችሁ፤ (ሠራችሁትም) መልካምም ትዕግሥት (ማድረግ) አለብኝ፤ እነርሱን፣ (ሦስቱንም ልጆቼን) የተሰበሰቡ ሆነው አላህ ሊያመጣልኝ ይከጀላል፤ እነሆ እርሱ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና" አላቸው። ያዕቁብም ከአጠጋባቸው ዘወር ብሎ፦" በዩሱፍ ላይ ዋ ሐዘኔ!" እያለ የድሮውን ዩሱፍን በማስታወስ ይንሰቀሰቅ ጀመር። እነርሱም ፦ "በአላህ እንምላለን፤ ለጥፋት የቀረብክ እስከምትሆን ወይም ከጠ ፊዎቹ እስከምትሆን ድረስ፣ ዩሱፍን ከማውሳትአትወገድም" አሉ። ያዕቁብም፦"ጭንቀቴንና ሐዘኔን የማስማው፣ ወደ አላህ ብቻ ነው፤ ከአላህም በኩል የማታውቁትን ነገር ዐውቃለሁ" አላቸው። ቀን ቀንን እየተካ ቀስ በቀስ ልጆቹ ከግብፅ ይዘው የመጡት ቀለብ አለቀ።ቤተሰቡም አደጋ ላይ ወደቀ። ይህን ግዜ ያዕቁብ ልጆቹን ሰብስቦ፦ "ልጆቼ ሆይ! ሂዱ፤ ስለ ዩሱፍና ስለ ወንድሙም ፊንጭ ሰብስቡ፤ ከአላህም እዝነት ተስፋ አትቁረጡ፤ እነሆ ከአላህ እዝነት ከሐዲዎች ሕዝቦች እንጂ፣ ተስፋ አይቆርጥም" አላቸው። እነሱም አባታቸው ባላቸው መልኩ ዩሱፍን እና ወንድሞቹን ፍለጋ ወደ ግብፅ ምድር ለሶስተኛ ግዜ ብቅ አሉ። ዩሱፍ ዘንድም በመግባት፦ " አንተ የተከበርከው ሆይ! እኛንም ቤተ ሰቦቻችንንም ጉዳት ደረሰብን፤ ርካሽ ሸቀጥም ይዘን መጥተናል፤ ስፍርንም ለኛ ሙላልን፤ በኛም ላይ መጽውት አላህ መጽዋቾችን ይመነዳልና" እያሉ ሲማፀኑት... ክፍል 4 ይቀጥላል...

•••✿ ❒ ነብዩሏህ_የአቆብ_ና_ዩሱፍ_ዐለይሂ_ሰላም_ታርክ ❒✿••• #ክፍል 2 ተንኮላቸውንም ከእኔ ላይ ባትመልስልኝ ወደነሱ እዘነበላለሁ፡፡ ከስህተተኞቹም እሆናለሁ" ሲል አላህን ተማፀነው። የከተማይቱ አስተዳዳሪም በሚስቱ ሰበብ የጠፋውን ስሙን ለማደስ ሲል ዩሱፍን እስር ቤት ለመጣል ወሰነ። ዩሱፍም እስር ቤት በገባ ግዜ እሱን በፊትም የሚያውቁት ሁለት እስረኞች(አንዱ የንጉስ የምግብ ሰራተኛ ሲሆን አንዱ ደሞ የንጉስ ጠጅ ጠማቂ ነው።) ለዩሱፍም እንዲህ ሲል አንደኛው ጠየቀው፦" እኔ በህልሜ የወይን ጠጅን ስጠምቅ አየሁ" ሁለተኛውም፡-"እኔ በራሴ ላይ ዳቦ ተሸክሜ ከእሱ በራሪ (አሞራ) ስትበላ አየሁ፡፡ ፍቹን ንገረን፡፡ እኛ ከአሳማሪዎች ሆነህ እናይሃለን'ና" በማለት ጠየቀው። ዩሱፍም እችን አጋጣሚ በመጠቀም እስር ቤት ውስጥ ላሉ እስረኞች ዳዕዋ ለማድረግ አሰበ'ና፦"ማንኛውም የሚመጣላችሁ ምግብ ለናንተ ከመምጣቱ በፊት ፍቹን የምነግራችሁ ቢሆን እንጂ አይመጣላችሁም፡፡ ይኸ ጌታዬ ካሳወቀኝ ነገር ነው፤ እኔ በአላህ የማያምኑን እነርሱም መጨረሻይቱን ዓለም እነርሱ ከሓዲዎች የሆኑትን ሕዝቦች ሃይማኖት ትቻለሁ። የአባቶቼን የኢብራሂምንና፣ የኢስሐቅን፣ የያዕቆብንም ሃይማኖት ተከትያለሁ፤ ለኛ በአላህ ምንንም ማጋራት አይገባንም፤ ያ (አለማጋራት) በኛ ላይና በሰዎቹ ላይ የአላህ ችሮታ ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያመሰግኑም። የእስር ቤት ጓደኞቼ ሆይ! የተለያዩ አምላኮች ከብርና ከወርቅ ከእንጨት የተሠሩ...? ይሻላሉን ወይንስ አሸናፊው አንዱ አላህ? ከርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸውን ስሞች እንጅ አትግገዙም፤ አላህ በርሷ ምንም አስረጅ አላወረደም ፍርዱ የአላህ እንጅ የሌላ አይደለም እርሱን እንጅ ሌላን እንዳትግገዙ አዟል፤ ይህ ትክክለኛው ሃይማኖት ነው፤ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያውቁም" በማለት ወደ አላህ ከጠራቸው በኋላ የሁለቱንም ህልም እንዲህ ሲል ፈታላቸው፦"የእስር ቤት ጓደኞቼ አንደኛችሁ ለ ንጉሱ ጠጁን በመጥመቅ ወደ ቀድሞ ስራው ሲመለስ ሁለተኛችሁ ደግሞ ስቅላት ተፈርዶበት ከተሰቀለ በኋላም ጭንቅላቱን አዕዋፍ ይበሉታል። ይህ የህልማችሁ ፍቺ ጥርጥር የለውም ተፋፃሚ ነው።" ይህን ካላቸው በኋላ ዩሱፍ ዐ ሰ ህልማቸውን በፈታው መልኩ አንደኛው ተወስዶ ሲሰቀል አንደኛውም ወደ መጀመርያ ስራው ተመልሶ ለንጉሱ ጠጅ እንዲጠምቅለት ተወሰነ። ለንጉሱ ጠጅ እንዲጠምቅለት የተወሰነለት ሊወጣ ሲል ዩሱፍ አስቆመው'ና፦"ንጉሱ ዘንድ ስትሄድ አንድ ንፁህ ሰው ያለ ወንጀሉ በአስተዳዳሪው አማካኝነት ታስሯል ብለህ በደሌን ንገርልኝ" አለው። እሱም እሽ ብሎ ከወጣ በኋላ ንጉሱ ዘንድ ወደ ስራ ገበታው ሲቀላቀል ዩሱፍን ከነአካቴው ረሳው።በዚህ ሁኔታ ላይ ዩሱፍ ለረጅም አመታት ያለጥፋቱ እስር ቤት ከረመ። ከእለታት አንድ ቀን የሀገሪቱ ንጉሱ(በነገራችን ላይ ንጉስ እና አስተዳዳሪ ስል እንዳይመሳሰልባችሁ እሺ...! አስተዳዳሪው ዩሱፍን የገዛው ሲሆን ንጉሱ ደሞ ገና ዩሱፍን አያውቀውም። የአስተዳዳሪው የበላይ ነው) እናላችሁ ይህ ንጉስ በደረቅ ሌሊት ህልም አየው ብሎ ተነስቶ ቤተ መንግስቱ በአንድ እግር አቆመው። በአስቸኳይ የኮከብ አዋቂዎችን እና ካህናትን በዚያ ሌሊት እንዲሰበሰቡ አደረገ።ከዚያ ህልሙንም እንዲህ ሲል ተረከላቸው፦" እኔ ሰባትን የሰቡ ላሞች ሰባት ከሲታዎች ሲበሉዋቸው፣ ሰባትንም ለምለም ዘለላዎች ሌሎችንም ደረቆችን (ሲጠመጠሙባቸው በሕልሜ) አያለሁ፤ እናንተ ታላላቅ ሰዎች ሆይ! ሕልምን የምትፈቱ እንደሆናችሁ ሕልሜን ፍቱልኝ " ካህናቱ እና ጠንቋይዎቹ የንጉሱን ህልም ሊፈቱ እጅጉን ተቸገሩ። ቢያወጡ ቢያወርዱ በቃ ምንም ሊያውቁት አልቻሉም'ና፦"ንጉስ ሆይ! የዚህን ህልም ፍቺ ልናውቅ ስላልቻልን ይህ ህልም ቅዠት ነው" አሉት። ያን ግዜ ጠጅ ጠማቂው ያ የድሮ የእስር ቤቱን ህልም ፈቺ ጓደኛውን ዩሱፍን አስታወሰ። ከመሀከል ብድግ በማለትም፦"እኔ የህልሙን ፍቺ ይዤ እመጣለሁ ግን የእስር ቤት ፍቃድ አውጡልኝ" ሲል ለንጉሱ ተናገረ። ንጉስም አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግለት በማዘዝ ጠጅ ጠማቂውም ዩሱፍ ወደሚገኝበት እስር ቤት ብቅ አለ። ዩሱፍንም ስለረሳው ይቅርታ በመጠየቅ ንጉሱ ያየውን ህልም ተረከለት'ና ፍቺውን ጠየቀው።ዩሱፍም፦" ሰባትን የተከታተሉ ዓመታት ትዘራላችሁ፤ ያጨዳችሁትንም ሁሉ ከምትበሉት ጥቂት በስተቀር በዘለላው ውስጥ ተዉት። ከዚያም ከነዚያ በኋላ፣ ካከማቻችሁት ጥቂት ሲቀር፣ ለነሱ ያከማቻችሁትን ሁሉ የሚበሉ ሰባት የችግሮች ዓመታት ይመጣሉ። ከዚያም ከነዚያ በኋላ ሰዎቹ በርሱ የሚዘነቡበት፣ በርሱም (ወይንን) የሚጨምቁበት የጥጋብ ዓመት ይመጣል" በማለት ህልሙን ብቻ ሳይሆን መፍትሄውንም ጭምር ዘረዘረለት። ጠጅ ጠማቂውም የህልሙን ፍቺ ይዞ በደስታ ወደ ቤተ መንግስት ይገሰግስ ጀመር ልክ እንደደረሰም ለንጉሱ ፍቺውን ከነ መፍትሄው ሲተርክለት ንጉሱ ዩሱፍን አሁኑኑ አምጡልኝ አለ። ዩሱፍንም ከእስር ቤት አውጥቶ የሚያመጣ ሰው ተመድቦ እስር ቤት ሲደርስ ዩሱፍ፦" ወደ ንጉሱ ተመለስ፤ የነዚያንም እጆቻቸውን የቆረጡትን ሴቶች ሁኔታ ጠይቀው፤ ጌታዬ ተንኮላቸውን አዋቂ ነውና" በማለት ይህ ጉዳይ ሳይጣራ ለመውጣት ፍቃደኛ እንዳልሆነ ለንጉሱ ለከ። ይህን ግዜ ንጉሱም በዚያ ቀን ያን ዝግጅት ተካፍለው የነበሩ የመሳፍንት፣የከበርቴ እና የአስተዳዳሪውንም ሚስት አንድ ላይ እንዲ ቀርቡ ካደረገ በኋላ፦" ዩሱፍን ከነፍሱ ባባበላችሁት ጊዜ፣ነገራችሁ(ምክንያታችሁ) ምንድነው?" ብሎ ሲጠይቃቸው... ሴቶቹም በአንድ አፍ፦"ለአላህ ጥራትይገባው፤ በርሱ ላይ ምንም መጥፎን ነገርአላወቅንም" አሉት። ያን ግዜ ከመሀል የአስተዳዳሪው ሚስት ቀበል አድርጋ፦" አሁን እውነቱ ተገለጸ፤ እኔ ነኝ ከነፍሱ ያባበልኩት፤ እርሱም ከውነተኞቹ ነው" በማለት በህዝብ ፊት የዩሱፍን ንፁህነት መሰከረች። ንጉስ ይህን በሰማ ግዜ እውነተኛውን ዩሱፍን ለማየት እጅጉን ጉጉት አደረበት። ነፃነትህን አስመስክረሀል ና ብሎ ጠርቶት የግል አማካሪው ከማድረግም ባሻገር የሀገሪቱን ጉዳይ ሙሉ በሙሉ ፈላጭ ቆራጭ አደረገው። አሁን ዩሱፍ ህዝቡ ዘንድ ልዩ ቦታ አለው።አብዝሀኛውም የሀገሪቱ ነዋሪ የዩሱፍን ጥሪ ተቀብሏል...እንዲህ እንዲህ እያሉ 7 አመታት ካሳለፉ በኋላ የድርቁ ዘመን ከች አለ። ድርቁን ተከትሎ ከተለያዩ ሀገራት በድርቅ የተመቱ እህል ሸማቾች ወደ ግብፅ ምድርም ይተሙ ጀመር። በዚያ መሀል በከንዓን ይኖሩ የነበሩ የዩሱፍ ቤተሰቦችም የድርቁ ሰለባ ነበሩ'ና 10 ወንድሞቹ እህል ፍለጋ የግብፅን ምድር ረግጠው በማያውቁት የወንድማቸው መጋዘን ለእህል ተሰለፉ። በግዜው ከመንግስት መጋዘን ሁሉም እህል ሲሸምት ስሙን እና የመጣበትን ሀገር እያስመዘገበ ነበር የሚሸምተው። እነዚህም ወንድሞቹ ስማቸውን እስመዝግበው እህላቸውን ከመረከባቸው በፊት ዩሱፍ የከንዓን ሰዎች መጥተዋል የሚል ወሬ ሰምቶ ሊያጣራ ሲሄድ ወንድሞቹን ተመለከታቸው። ምንም እንኳን እሱ ቢያውቃቸውም እነሱ ግን በፍፁም ሊያውቁት አልቻሉም።ግን ዝም ብለው በግምት፦" ይህ ፊት አዲስ አልሆነብኝም ይባባላሉ" እርስ በርስ.... ዩሱፍም ከተለያዩ ሀገራት ከመጡ ቁጥር ስፍር ከሌለው ሰልፈኛ መሀል ለ40 አመት የተለያያቸውን ወንድሞቹን የሰሩበትን ተንኮል ወደ ጎን አድርጎ በናፍቆት ተሸንፎ ስለማንነቱ ምንም ሳይነግራቸው ወደሚኖርበት ቤተ መንግስት ይዟቸው ሄድ። ክፍል 3 ይቀጥላል... #share https://t.me/Umete_Resul
Show all...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

' •••✿ ❒ ነብዩሏህ_የአቆብ_ና_ዩሱፍ_ዐለይሂ_ሰላም_ታርክ ❒✿••• #ክፍል 1 ያዕቁብ ልጆቹን ሚስቶቹን እና አገልጋዮቹን ይዞ ከንዓን ምድር ላይ ኑሯቸውን ጀምረዋል። ያዕቁብ ልጆቹን ሁሉ እላፊ በመውደዱ የሚታወቅ አባት ቢሆንም ለየቲሞቹ ለዩሱፍ እና ለቢንያሚን ያለው ቦታ ልዩ ነበር። ከእለታት አንድ ቀን ዩሱፍ በሌሊት ተነስቶ ለአባባቱ ያየውን ድንቅ ህልም እንዲህ ሲል ይነግረዋል፦" አባቴ ሆይ! እኔ ዐስራ አንድ ከዋክብትን ፀሐይንና ጨረቃንም (በሕልሜ) አየሁ፡፡ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው" አባትየውም፦"ልጄ ሆይ! ሕልምህን ለወንድሞችህ አታውራ፡፡ ላንተ ተንኮልን ይሰሩብሃልና። ሰይጣን ለሰው ግልጽ ጠላት ነውና..... እንደዚሁም (እንዳየኸው) ጌታህ ይመርጥሃል፡፥ ከንግግሮችም ፍች ያስተምርሃል፡፡ ጸጋውንም ከአሁን በፊት በሁለቱ አባቶችህ በኢብራሂምና በኢስሐቅ ላይ እንዳሟላት በአንተ ላይና በያዕቆብ ዘሮችም ላይ ይሞላታል፡፡ ጌታህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና" ብሎ አብስሮት ህልሙንም ለማንም እንዳይናገር አስጠነቀቀው። አባትየው ያዕቁብ የዩሱፍን ህልም ከሰሙ በኋላ ለዩስፍ ያላቸው ፍቅር ወደ አክብሮት እና ለሱ ወደ መተናነስ ያደላም ጀመር። ይህ ግን ለዩሱፍ ለአባቱ ልጆች የእግር እሳት ሆኖባቸው ቅናት እረፍት ነስቷቸዋል። ከእለታት አንድ ቀን የዩሱፍ የአባት ልጆች በዩሱፍ እና በአባቱ መካከል ያለውን ፍቅር እንዴት በአጭሩ ማኮላሸት እንዳለባቸው ሊመካከሩ አንድ ቦታ ተሰበሰቡ። ብዙ ሀሳቦችን አንስተው በመጨረሻም ዩሱፍን በአንድ ውሀው ጨዋማ በሆነ ስምጥ ጉድጓድ ውስጥ ሊጨምሩት ወሰኑ። ማታ ላይ አባታቸው ዘንድ በመሄድም፦" አባታችን ሆይ! በዩሱፍ ላይ ለምን አታምነንም እኛም ለእርሱ በእርግጥ አዛኞች ነን። ነገ ከእኛ ጋር ላከውና ይደሰት፤ ይጫወትም፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎች ነን" በማለት ዩሱፍ ከነሱ ጋር እንዲሄድ አባታቸው ያዕቁብን ተማፀኑት። ያዕቁብም፦" እኔ እርሱን (ዩሱፍን) ይዛችሁ መሄዳችሁ በእርግጥ ያሳዝነኛል፡፡ እናንተም ከእርሱ ዘንጊዎች ስትሆኑ ተኩላ ይበላዋል ብዬ እፈራለሁ" በማለት መለሰላቸው። ከዚህም ከዚያም ብለው አባታቸውን ካሳመኑት በኋላ የልባቸውን ሊፈፅሙ ዩሱፍን ወዳጅ መስለው አቅፈው ወሰዱት። ያሰቡበትም ጉድጓድ ውስጥም እየለመናቸው እጅ እግሩን አሳስረው ቀሚሱን አውልቀው ወረወሩት። ማታ ሲሆንም የሁዳ ባመጣው ሀሳብ መሰረት ያወለቁትን የዩሱፍን ቀሚስ አንድ ፍየል አርደው ቀሚሱን በፍየሏ ደም ለወሱት። በመጨረሻም ምሽቱ ሲደምቅ እንስሳቶቹን እየነዱ መንደር ከደረሱ በኋላ የዩሱፍን በደም የተለወሰ ቀሚስ ይዘው እዬዬዬ....በማለት እያለቀሱ ሰፈሩን ቀወጡት። ይህን ሲያይ ያዕቁብ እግሩ ተብረከረከ ተንኮለኛ ልጆቹ በውዱ ልጁ ሴራቸውን ተግባር ላይ እንዳዋሉ ተረዳ። እሱም፦"ልጄ ምን ሆነ" ሲላቸው... እነሱም፦" አባታችን ሆይ! እኛ (ለሩጫና ለውርወራ) ልንሽቀዳደም ሄድን፡፡ ዩሱፍንም ዕቃችን ዘንድ ተውነው፡፡ ወዲያውም ተኩላ በላው፡፡ አንተም እውነተኞች ብንሆንም የምታምነን አይደለህም" አሉት (እነዚህ ቀልበ ደረቆች) አባታቸውም፦" አይደለም፤ ነፍሶቻችሁ (ውሸት) ነገርን ለእናንተ ሸለሙላችሁ፡፡ ስለዚህ መልካም ትዕግስት (ማድረግ አለብኝ) በምትሉትም ነገር ላይ መታገዣው አላህ ብቻ ነው" ብሎ ጉዳዩ ለአላህ የወው። ዩሱፍም እዚያ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ ወደ ግብፅ የሚሄድ ቅፍለት(ተጓዥ ነጋዴዎች) በዚያ ጉድጓድ ሲያልፉ ውሀ ለመቅዳት ባልዲያቸውን ወደ ውስጥ ወርውረው ውሀ ለማውጣት ወደ ላይ ሲጎትቱ ቆንጅዬ ልጅ ባልዲው ላይ ተንጠልጥሎ ወጣ። በዚህ ሁኔታ ላይ ውሀውን ሚቀዳው ሰውዬ ልጅ አገኘሁ እያለ ሲጮኽ የዩሱፍ ወንድሞች ሰምተው መጡ'ና፦ "ከኛ ያመለጠ ባሪያ ነው ከፈለጋችሁ ግዙን እንጂ በነፃ አትወስዱም" በማለት ወንድማቸውን በርካሽ ዋጋ ለነጋዴዎቹ ሸጡላቸው። ነጋዴዎቹ ደግሞ ሸቀጣቸውን ከሚገዙባት ግብፅ ከተማ ሲደርሱ ለግብፅ አስተዳዳሪ በርካሽ ዋጋ ሸጡለት። የሀገሪቱ አስተዳዳሪም ዩሱፍን ለሚስቱ በስጦታ ምልኩ አበርክቶላት ልጅ ስለሌላት እንድ ልጇ አድርጋ እንድታየውም ነገራት። ሚስቱም እጅጉን ተደሰተች የልጁ ውበትም ከልጅነቱ ጋር አጓጊነቱም ማረካት። ግዚያት ነጎዱ ቀን ሌሊትን ክረምት በጋን እየተተካኩ ብዙ አመታት ተቆጠሩ። ዩሱፍም ወጣትነቱ እና የአዕምሮ ብስለቱ ይልቅ ውበቱን ጨምሮበታል። የአስተዳዳሪው ሚስት ይህን ስታይ ሁኔታዋ እየተቀያየረ መምጣት ጀመረ። ከእለታት አንድ ቀንም ለዝሙት እራሷን አዘጋጅታ ክፍሏ አስጠራችው'ና በሩን ዘጋጋች።ከዚያም፦"ተዘጋጅቼልሀለሁ ናልኝ" ስትለው ዩሱፍም፦" በአላህ እጠበቃለሁ እርሱ (የገዛኝ) ጌታዬ ኑሮዬን ያሳመረልኝ ነውና፤ (አልከዳውም)፡፡ እነሆ! በደለኞች አይድኑም" አላት። በዚህ አጋጣሚ ዩሱፍ በሩን ከፍቶ ሲወጣ የሴትየዋ ባል፣የከተማይቷ አስተዳዳሪ፣የራሱ አለቃ....በር ላይ ተገጣጠሙ። ሚስቱ ዩሱፍን ተከትላም ስትወጣ ባሏን በር ላይ አገኘችው።ለትንሽ ሰዐት በሶስቱም መሀከል ዝምታ ሰፈነ።በመቀጠልም ምን እየተከሰተ እንደነበር አስተዳዳሪው ሲጠይቃቸው ሚስትየው ቀደም ብላ፦" በባለቤትህ መጥፎን ያሰበ ሰው ቅጣቱ መታሰር ወይም አሳማሚ ስቃይ እንጂ ሌላ አይደለም" አለች። ዩሱፍም ንግግሯ ውሸት እንደሆነ አስተባበለ በዚህ መሀልም አንድ በወራት ቤት ያለ የዙለይካ የዘመዷ ህፃን ልጅ ሊዳኛቸው አላህ በመሀል አስገባው። ህፀኑም፦" ቀሚሱ ከበስተፊት ተቀድዶ እንደሆነ (እሷ)እውነት ተናገረች፡፡ እርሱም ከውሸታሞቹ ነው ቀሚሱም ከበስተኋላ ተቀድዶ እንደሆነ እሷ ዋሸች፡፡እርሱም ከእውነተኞቹ ነው"በማለት ፍርዱን ሰጠ። አስተዳዳሪውም በመገረም ቀሚሱን ሲመለከት የተቀደደው ከኋላ ነው።ወደ ሚስቱ ዞር በማለት፦ "እርሱ (የተናገርሺው) ከተንኮላችሁ ነው (ሴቶች) ተንኮላችሁ በእርግጥ ብርቱ ነውና" ብሎ ወቀሳት። ለዩሱፍም ወሬውን እንዳያሰራጭ ነገረው። ነገር ግን በጥቂት ቀናት ውስጥ ወሬው በከተማይቱ እጅጉን ተሰራጨ።(ወይ dire tube የለ...ወይ ethiopian dj የለ...)ግን ብቻ ወሬው ከአጥናፍ እስካጥናፍ ተሰራጨ። ይንህ የወሬውን መሰራጨት ዙለይካ ስትሰማ አንድ ሴራ ጠነሰሰች'ና አንድ ትልቅ ዝግጅት በማዘጋጀት የከተማውን የመሳፍንት እና የከበርቴ ሚስቶችን ባጠቃላይ ጠራች። ከዚያም በዝግጅቱ ሁሉም ሴት መገኘቱን ስታረጋግጥ ፍራፍሬ እና ቢለዋ በመስጠት እሷ መብላት ጀምሩ ሳትል ማንም እንዳይበላ አዘዘቻቸው። በዚህ መሀል አሁን መብላት ትችላላችሁ ብላ ሴቶቹ የያዙትን ፍራፍሬ መቆራረጥ ሲጀምሩ፦"ዩሱፍ ና ግባ" በማለት ድምጿን ከፍ አድርጋ ጠራችው። ዩሱፍም ያማረ ልብስ አስለብሳው ነበር'ና ልክ የሌሊት ጨረቃ መስሎ ወደ ውስጥ ሲገባ ሴቱ ሁሉ አይናቸው በሱ ፈዘዘ'ና ፍራፍሬውን ረስተው እጆቻቸውን በያዙት ቢለዋ በመሸረካከት፦" አላህም ጥራት ይገባው፡፡ ይህ ሰው አይደለም፡፡ ይህ ያማረ መልአክ እንጅ ሌላ አይደለም" ማለት ጀመሩ። እሷም፦"ታዲያ ይህ ያ በርሱ (ፍቅር) የዘለፋችሁኝ ነው፡፡ በእርግጥም ከነፍሱ አባበልኩት፡፡ እምቢ አለም፡፡ የማዘውንም ነገር ባይሠራ በእርግጥ ይታሰራል፡፡ ከወራዶቹም ይሆናል" አለቻቸው። ዩሱፍም፦"ጌታዬ ሆይ! ወደርሱ ከሚጠሩኝ ነገር (ከዝሙት) ይልቅ መታሰር ለእኔ የተወደደ ነው፡፡ ክፍል 2 ይቀጥላል... #share https://t.me/Umete_Resul
Show all...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

•••✿ ❒ የነቢዩሏህ_እስሃቅ_ና_የአቆብ_ዐለይሂሰላም_ታረክ ❒ ✿••• #ክፍል 2 አሁን ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ፊለስጢንን ለቅቆ የሀራንን ምድር ከረገጠ 20 አመታትን አስቆጥሯል። ያዕቁብም አጎቱ ዘንድ በመሄድ፦"አጎቴ አሁን ፍቀድልኝ'ና ሚስት ልጆቼን ሰብስቤ ቤተሰቦቼ ጋር ልሂድ" ይለዋል። አጎቱ ላባንም፦"ያዕቁብ እኔ ባንተ ሰበብ ብዙ ንብረቴ በረካ ሆኖልኛል።ስለዚህ የፈለግከውን ያህል ንብረት ጠይቀኝ" አለው። ላባን በጣም ለቁጥር ሚያዳግት የእንስሳት መዐት ስለነበረው ያዕቁብም፦"በዚህ አመት የሚወለዱትን ሁሉ ባጎች ስጠኝ። ከተቀረው እንስሳቶችህ መልካቸው ጥቁር በነጭ የሚወልዱትንም ስጠኝ። ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችንም ስጠኝ" አለው። አጎቱ ላባንም፦"እሺ" አለው። ያዕቁብም ይህን ሀላፊነት ልጆቹ እንዲወጡ አዘዘ። በመጀመርያ ያዕቁብ እርጉዝ የሆኑ እንስሳቶችን ከሌሎቹ እንስሳት የሶስት ቀን መንገድ ያህል ርቀት አራራቃቸው። ነጭ ዳማዎችን እና ቀይ ዳማዎችን እንደዚያው አራራቃቸው።ይህን ካደረገ በኋላ እርጉዞቹም ወለዱ ያዕቁብም ድርሻውን ለይቶ በአላህ ትዕዛዝ ለጉዞ ተዘጋጀ። አሁን ያዕቁብ የብዙ ሺህ በጎች...እንስሳቶች...እና የብዙ አገልጋዮች ባለቤት ሆኗል። ወደ ፊለስጢን ጉዞ ሲዝጀምሩ ራሂል የተባለችዋ የያዕቁብ ሚስት የአባቷን ጣኦት ደብቃ ይዛ ወጣች። ያዕቁብ ልጆቹን፣ሚስቶቹን፣አገልጋዮቹን፣እንስሳቶቹን...ሁሉ ሰብስቦ በረሀውን እያቋረጠ ብዙ ተጎዞ የሀራንን ምድር ካጋመሰ በኋላ አጎቱ ላባን እና የሀራን ከተማ ነዋሪዎች ተከትለውት ደረሱበት። ልክ እንዳገኙት አጎቱ ላባን በወቀሳ መልኩ፦"ያዕቁብ ለምን ሳትነግረኝ ትተህ ትሄዳለህ!!! ምነው በደስታ ተሰነባብተን ከአከባቢው ህዝብ ጋር ጨፍረን ብንሸኛቹስ" በማለት አንድ ጣኦት ይዘው እንደመጡም አክሎ ጠየቀው። ያዕቁብ ዐ ሰ ምንም አይነት ከጣኦት ጋር ግንኙነት ባይኖረውም ለአጎቱ ሲል የሚስቶቹን እቃ ሀሉ ፈተሸለት ምንም አላገኘም። ራሂል ግን ጣኦቱን ይዛው ስለነበር ለፍተሻ ፍቃደኛ አልሆነችም ነበር አሞኛል አልነሳም አለች። ያን ግዜ ያ ጣኦት ምናልባት ጀልዓድ በተባለ ዳገት ላይ ይኖራል በሚል ግምት ላባን ልጆቹን እና የእህቱን ልጅ ያዕቁብን ተሰናብቷቸው ተመለሰ። ያዕቁብ የትውልድ ሀገሩን ሊገባ ጥቂት ሲቀራው መላዕክት እየወረዱ እንኳን ደህና መጣህ እያሉት ያልፉ ነበር። አሁን ያዕቁብ ሳዒር የምትባል ቦታ ላይ ደርሷል ግን ሀገሩ ሊገባ የወንድሙን በቀል ፈርቷል። እዛው ሆኖ እንደማለማመጥ አይነት ነገር ፅፎ ደብዳቤ ለወንድሙ ላከለት። በነጋታው ሌላ የዛቻ ደብዳቤ የያዘች ወረቀት ዒስ(የያዕቁብ ወንድም) 400 እግረኛ ጦር አሰልፎ እየመጣ መሆኑን የሚያስረዳ መልዕክት ከወደ ፊለስጢን በኩል ለያዕቁብ መጣችለት። ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ። ያዕቁብም ፈራ...አላህንም ከወንድሙ ተንኮል እንዲታደገው ተማፀነ...ለአላህም ስለት ገባ። ከዚያም ወንድሙን ሊያስደስት በርከት ያለ ስጦታም አዘጋጀለት... 200 ሴት ፍየሎችን እና 20 ወንድ ፍየሎች 200 ሴት በጎችን እና 20 ወንድ በጎች 30 (ኮርማ)በሬዎችን እና 40 ላሞች 20 ሴት ግመሎችን እና 10 ወንድ ግመሎች እና አራቱንም የስጦታ አይነቶችን ለያይቶ ሊልክ በአራት ቡድን የተደራጀ አገልጋዮችን አዘጋጀ እና ቀድሞ አንዱን ቡድን ለከ። የመጀመርያው ቡድን ስጦታን ይዞ ሄዶ ትንሽ ራቅ ሲል ሁለተኛውን ይልካል ሁለተኛውም ትንሽ ራቅ ሲል ሶስተኛውን ይልካል.... እንዲ እንዲ እያለ አራቱንም የስጦታ አይነት ከነ አገልጋዮቻቸው ጨምሮ፦"ማንም የማን ነው ብሎ ከጠየቃችሁ ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው በሉ" ብሎ ላካቸው። ይህንንም ሊያደርግ የቻለው ወንድሙ ዒስ ስጦታዎች በተከታታይ ሲመጡለት ደስታው የላቀ ይሆናል በሚል ነው። ከዚያም የመጀመሪያውን ስጦታ የያዘው የአገልጋልይ ቡድን ዒስ እና ወታደሮቹ ያሉበትን ቦታ ሲደርሱ ዒስ፦"ይህ የማን ነው?" ብሎ ጠየቀ። አገልጋዮቹም፦" ከያዕቁብ ለዒስ የተላከ ስጦታ ነው" አሉት። እሱን ተቀበላቸውና ሁሉም የስጦታ ነጂ ቡድኖች ስጦታዎቻቸውን ተራ በተራ እየነዱ አስረከቡት። ያዕቁብም ሚስቶቹን ልጆቹን እና የተቀሩ አገልጋዮቹን አስከትሎ በሌሊት ወደ ወንድሙ ጉዞ ጀመረ። (በነገራችን ላይ በዚህች የሌሊት ጉዞ ነበር ክርስቲያን ወገኖች ያዕቁብ እና እግዚአብሄር ተደባድበው ያዕቁብ አሸነፈው የሚሉት።) ሌሊቱን ተጉዞ ፀሀይ ጀንበሯን አምልጣ መውጣት ስትጀምር ለ20 አመታት ያህል የተለያዩ ወንድማሞች አይን ለአይን ተገጣጠሙ። ዒስ 400 ጦረኛዎችን አሰልፏል።ያዕቁብም ወንድሙን ሲያየው 7 ግዜ አጎበደደለት(ይህ በዘመናቸው ሀራም አልነበረም የዘመናቸውም ሰላምታ ነበር። በቀጣይ ክፍላችን ለዩሱፍ ሲሰግዱ እንዳስሳለን" ዒስ ዱዓውን ከአባቱ የዘረፈውን ወንድሙን ሲያይ ሄዶ ተጠምጥሞበት ወንድሙን እየሳመ ያለቅስ ጀመር።በዚህ አጋጣሚ ከአጠገቡ ያሉትን ሴቶችን ልጆችን እና አገልጋዮችን ሲመለከት፦"ይሄም ሁሉ ኬት አምጥተህ ነው?" አለው። ያዕቁብም፦"እነዚህ አላህ የሰጠኝ ስጦታዎቼ ናቸው" አለው። ይህን ግዜ የያዕቁብ ልጆች እና ሚስቶች ተራ በተራ እየመጡ ዒስን ከዘየሩ በኋላ ያዕቁብ በአገልጋዮቹ አማካኝነት ለዒስ የላከውን ስጦታ ዒስ መቀበል እንቢ አለ። ያዕቁብም ለምኖት እንዲቀበል አደረገው'ና አብረው በረሀውን እያቆራረጡ አባታቸው ወደሚገኝበት የፊለስጢን ምድር መትመም ጀመሩ። በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ያኔ....ያዕቁብ አጎቱ ጋ ሲሄድ ተኝቶ ህልም ያየበትን ቦታ ደረሱና እዛ ቦታ ያዕቁብ በ200 በግ ያንን ቦታ ከአንድ ገበሬ ገዛው'ና አንድ ትልቅ የአምልኮ ቦታ ሰራ(ቁድስ) ከዚያ በኋላ ነው በሱለይማን ዘመን ሱለይማን ያደሰው። በዚህ ጉዞ ላይም ሳሉ ነበር አንድ ደስታ እና ትልቅ ሀዘን በያዕቁብ ቤተሰብ የተከሰተው። ነፍሰ ጡር የነበረችው ትንሿ ራሂል ምጥ አስቸገራት...ብዙ ከተጨነቀች በኋላ ቢንያሚን የተባለ ልጅ ተገላግላ ለራሷም ዱንያን ተገላገለቻት። ያዕቁብም ባለቤቱን መንገድ ላይ ቀብሮ ሀዘኑን ታቅፎ ወደ አባቱ ጉዞ ቀጠለ። ከአባቱም ተገናኝቶ በከንዓን ምድር ሀብሩን በምትባል(ኢብራሂም ይኖር በነበረበት) አካባቢ መኖር ጀመረ። ኢስሀቅም እርጅና ተጫጭኖትም ስለነበር ጌታው የፃፈለትን 180 አመት ካጠናቀቀ በኋላ ነፍሱን ለጌታው አስረከበ። የነበቢዩሏህ የኢስሃቅ ዐለይሂሰላም ታረክ አዚህ ላይ ተፈፀመ። የነቢዩሏህ የአቆብ ዐለይሂሰላም ታሪክ የቀረውን የነቢዩሏህ ዩሱፍ ታረክ ውስጥ እናየወለንን!!       •••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿••• በቀጣይ #የነብዩሏህ_ዩሱፍ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰 #share https://t.me/Umete_Resul
Show all...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

👍 3
' •••✿ ❒ የነቢዩሏህ_እስሃቅ_ና_የአቆብ_ዐለይሂሰላም_ታረክ ❒ ✿••• #ክፍል 1 ለኢስሀቅ አባቱ ኢብራሂም (ዐሰ) በህይወት ሳለ በ40 አመቱ ነበር ረፍቃ ቢንት በትዋዪል ከተባለች እንስት ትዳር ያስያዘው። ምንም እንኳን ረፍቃ መውለድ የማትችል መሃን ብትሆንም በባለቤቷ ያላሰለሰ ዱዓ ሁለት መንታ ልጆችን ለመታደል በቅታለች። አንደኛው፦ዒስ ሲሆን ሁለተኛው፦ያዕቁብ (ዐሰ) ይባላል። ዒስ የሮም ህዝቦች ቅድመ አያት ሲሆን፤ ያዕቁብ ደሞ የእስራኢላውያን ቅድመ አያት ነው። የሁለቱም አባት ሁለቱንም ልጆቹን በጣም ቢወዳቸውም ከያዕቁብ ይልቅ ለዒሱ ግን ለየት ያለ ቦታ ነበረው። እናታቸው ረፍቃ ግን ያዕቁብ ታናሽ ስለሆነ ይበልጥ እሱን ነበር የምትወደው። ኢስሀቅ ከእርጅና የተነሳ አይናቸው ማየት ካቆመ ትንሽ ሰንበትበት ብሏል። ከእለታት አንድ ቀን ኢስሀቅ (ዐሰ) ስጋ ያምራቸውና የሚወዱትን ልጃቸውን ዒስን አደን አድኖ ስጋ እንዲያመጣለቸው እናም ከባድ ዱዓም እንደሚያደርጉለት ነግረውት እሱም ለአደን ሄደ። ይህን በድብቅ ስትሰማ የነበረችውም የልጆቹ እናት ረፍቃ ለያዕቁብ ነግራው ከፍየሎቹ ወፍራሙን ሙኩት እንዲያርድ ካደረገች በኋላ የወንድሙን ዒስን ልብስ አልብሳው እራሱን(ዒስን) አስመስላ የሰራውን ስጋ ለአባቱ እንዲያቀርብ አደረገች። ያዕቁብም ያዘጋጀውን ምግብ ይዞ አባቱ ዘንድ ሲያቀርብ አባቱ፦"ማን ነህ አንተ?" አሉት። ያዕቁብም፦"ልጅዎት ነኝ"አለ። አባቱም(ኢስሀቅ)፦"ድምፅህ የያዕቁብ ነው፤ልብስህ ግን የዒስ ነው" በማለት የቀረበላቸውን ምግብ በሉት። ምግቡን በልተው እንደጠገቡም ምግቡን ላቀረበው አላህ ክብሩን ከፍ እንዲያደግለት፣ የበላይ ዘርም እንዲያደርገው፣ልጆቹንም ሪዝቁንም አላህ እንዲያበረክትለት ዱዓ አደረጉ። ልክ ዱዓውን እንዳጠናቀቁ ያዕቁብ አሚን ብሎ የአባቱን ክፍል ለቆ ወጣ።ያዕቁብም ሲወጣ ዒስ በታዘዘው መልኩ ያደነውን ስጋ ጠባብሶ ለአባቶ አመጣ'ና አቀረበ። አባቱ ግን ቅድሙኑ ጠግበዋል። ዒስ ምግቡን ሲያቀርብላቸው፦"ልጄ ይህ ምንድነው?" አሉት። ዒስ'ም፦"አምጣልኝ ያሉት ስጋ ነዋ" አላቸው። አባትየውም፦"አሁን አምጥተህልኝ በልቼ ዱዓ አላደረግኩልም እንዴ!!!"ሲሉት ወንድሙ ያዕቁብ እንደቀደመው እና ዱዓውንም ሸውዶ እንደተቀበለ በመረዳት ሀይለኛ እልህ ያዘው። ዒስ አባታቸው ኢስሀቅ ከሞተ ያዕቁብን እንደሚገድለውም ይዝትበት ጀመር።ያን ግዜ አባት ለልጃቸው ዒስ ማስተዛዘኛ ይሆም ዘንድ፦"አላህ ዝርያዎችህን ጠንካሮች ያድርጋቸው፣ፍራፍሬዎችን እና ሪዝቆቹንም አላህ ሰፋ አድርጎ ይስጥህ" በማለት ዱዓ አደረጉለት። ነገር ግን እናት ልጇ ያዕቁብ ላይ ሚዛተው ዛቻ እረፍት ነስቷት ስለነበር የዒስ ቁጣ እስኪበርድለት ድረስ ያዕቁብን ሀራን በሚባል አካባቢ ወደሚገኘው ወንድሟ (ላባን) ላከችው። ያዕቁብም ስንቁን ይዞ ወደ አጎቱ ላባን እየተጓዘ ሳለ መንገድ ላይ መሸበት እና አንድ ድንጋይ ተንተርሶ ፏ ያለ እንቅልፍ ተኛ። እዛው በተኛበትም በህልሙ ወደ ሰማይ መወጣጫ ይመለከታል።በዚያ መወጣጫ መላዕክት ይወጣሉ...ይወርዳሉ።በዚያ መሀከል አላህም፦"እኔ አንተን እባርክሀለሁ።ዝሪያዎችህንም አበዛልሀለሁ...ምድርንም ላንተ እና ለዝርያዎችህ አደርጋታለሁ" አለው። በህልሙ ማለት ነው.... ልክ ይሄን እንዳየ ከእንቅልፉ ነቃ። ባየው ነገርም በጣሙን ተደሰተ'ና፦"ጌታዬ አሁን ከምሄድበት በሰላም ከመለስከኝ እዚህ ቦታ ላይ ላንተ አምልኮ እሚሆን ቤት እገነባለሁ።ከሚኖረኝም ሀብት አንድ አስረኛውን ባንተ መንገድ አውላለሁ" በማለት እዛ ቦታ ላይ የሆነ ምልክት አድርጎ ስለት ገብቶ ጎዞውን ቀጠለ። ብዙ ተጉዞ የሀራንን ምድር ደረሰ'ና ከአጎቱም ተገናኘ።ለአጎቱ ሁለት ሴት ልጆች ነበሩት አንዷ (ለያ) ስትባል ታናሿ ደሞ (ራሂል) ትባላለች። ምነው ለያ ራሂል...ስል የዩሱፍ ፊልም ትዝ አላችሁ ሀ....!!! ቆይ ዩሱፍንም ደርሰነዋል ትንሽ ነው የቀረን። ትንሸኛዋ ራሂል ቆንጅዬ ነገር ስትሆም ትልቋ ግን እስከዚህም ነገር ነበረ።ከዚያም ያዕቁብ ትንሸኛዋ ራሂል በልቡ መግባቷን ሲያውቅ አጎቱን ላባንን እንዲድረው ጠየቀው። አጎቱም፦"7 አመት በጎችን ካገድክልኝ እድርሀለሁ" በማለት ቃል ገባለት'ና ያዕቁብም ቆንጂዬዋን ራሂልን ለማግኘት ለ7 ተከታታይ አመታት እረኛ ሆኖ አሳለፈ። የማይደርስ የለም'ና ሰባቱ አመት ተጠናቅቆ የቀጠሮው ቀን ብቅ አለ።ላባንም ድል ያለ ድግስ ደግሶ ዘመድ አዝማድ ከጠራ በኋላ ኒክህ እስሮ ሙሽሪትንም ለያዕቁብ አስረከበው። በማግስቱ ጠዋት ላይ ጨለማው በብርሀን መገፈፍ ሲጀምር ያዕቁብ ሙሽሪትን ተመለከታት። ነገር ግን 7 አመት ለሷ ብሎ በግ የጠበቀላት ራሂል ሳትሆን ብዙም ማታምረዋ ለያ ሆና አገኛት። ያዕቁብ በጣም ተናደደ.... ያዕቁብ ሙሽሪትን ተመለከታት ነገር ግን 7 አመት ለሷ ብሎ በግ የጠበቀላት ራሂል ሳትሆን ብዙም ማታምረዋ ለያ ሆና አገኛት። ያዕቁብ በጣም ተናደደ በጠዋት አጎቱ ጋ በመሄድ፦"አንተ ቃል ኪዳንን አፍርሰሀል።እኔ የተዋዋልኩት ልጅህን ራሂልን ሀኖ ሳለ እንዴት ለያን ትሞሽርልኛለህ" በማለት ወቀሰው። የያዕቁብ አጎትም ላባን ብልጣ ብልጥ ነገር ነበር'ና፦"ይህማ በኛ ባህል ነውር ነው...እንዴት ታላቅ እያለች ታናሽ ትዳራለች!!! በል ራሂልን ምትፈልግ እንደሆን ለ7 አመት በጎችን አግድልኝ" አለው። ያዕቁብም ራሂልን በጣም ወዷት ስለነበር 7 አመታትን ለመጠበቅ ተገደደ።የማይደርስ የለም'ና ይህም ቀን ደረሰ።ያዕቁብም ለ14 አመት የጠበቃትን ራሂልን በእጁ አስገባት። (በነገራችን ላይ ሁለት እህትማማቾችን በአንድ ግዜ ማግባት በነሱ ህግ/ሸሪዓ ክልክል አልነበረም።ከዚያ በኋላ ነው ተውራት ሲወርድ ይህ ህግ የተሻረው።) ከዚያ ያዕቁብ ሁለት እህትማማቾችን አግብቶ ሳለ አጎቱ ላባን ለሁለት ለልጆቹ ሁለት አገልጋዮችን በስጦታ መልኩ ጀባ አላቸው። ለያ ለምትባለዋ፦ዘልፋ የምትባል አገልጋይ ሲሰጣት ራሂል ለምትባለዋም፦በልሃ የምትባል አገልጋይ ሰጣት። አላህም ለያ የምትባለዋን(ፉንጋዋን) 4 ወንድ ልጆችን በመስጠት ካሳት።ልጆቿም 1፦ረውቢል 2፦ሸምዑን 3፦ላዊ 4፦የሁዳ...ናቸው። ትንሿ ረሂል ምንም እንኳም ቆንጅዬ ብትሆንም ልጅ መውለድ ግን አትችልም። በታላቅ እህቷ መውለድ በጣም ቅናት ይይዛት'ና እራሷ ዘንድ የምትገኘውን በልሀ የተባለችውን አገልጋይ ለገዛ ባለቤቷ ዳረችው'ና አገልጋይዋም ከያዕቁብ 5፦ዳን 6፦ኒፍታሊ...የተባሉ ልጆችን ወለደች። ያን ግዜ ለያ ከእህቷ ረሂል እልህ ተያያዘች'ና እሷም ዘልፋ የምትባል አገልጋይዋን ለያዕቁብ ዳረችለት'ና ያዕቁብም ከዘልፋ 7፦ጃድ 8፦ዐሺር...የተባሉ ልጆችን ወለደችለት። ኧረ የሌላ ይደላል ያዕቁብ ዐ ሰ በመሀል ተመቻቸው እኮ...ሱብሀን አላህ የአላህ ተርቲብ ከዚያም ለያ(ታላቋ) አምስተኛ አረገዘች'ና 9፦ያሳካር...የተባለ ልጅ ወልዳ ብዙም ሳትቆይ 10፦ዛብሎን... የተባለ ልጅ ደገመች። አሁንም አላረፈችም 11፦ዲና... የምትባል ሴት ልጅ ለያዕቁብ አሳቀፈችው።ያ ማለት ለያ ከያዕቁብ 7 ልጆችን ወለደች ማለት ነው። ይህን ስታይ መቋቋም ያቃታት ራሂል አላህን ልጅ እንዲሰጣት መማፀን ጀመረች። አላህም በሩን ያንኳኳውን በከንቱ ማይመልስ ጌታ ነው'ና ዱዓዋን ተቀብሎ 12፦ዩሱፍ (ዐሰ) የሚባል ውብ እና ገራሚ የሆነ ልጅ ጀባ አላት። ይህ ሁሉ የሚሆነው በአጎቱ ሀገር በሀራን ምድር ላይ ነው። ክፍል 2 ይቀጥላል... #share https://t.me/Umete_Resul
Show all...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

👍 1
•••✿ ❒ የነብዩሏህ ኢብራሂም ዐ,ሰ ታሪክ ❒✿••• #ክፍል 5 አባቴ ሆይ ይህንን ድንጋይ ምን ነው ይዞልህ የመጣው ሲል ጠየቀው ፣ ያ መተረሰት የመይፈለገው እንዲሁም የማይደክመው አካል ጅብሪል ነው ያመጣልኝ አለው። እናም አል ሀጀሩል አስወድ ከጀነት ነው። ይህን ትልቅ ቤትም ገንብተው ካጠናቀቁ በኋላ አላህም ኢብራሂምን፦"ሰዎች ከየሀገሩ በመምጣት ቤቴን ይጎብኙ ዘንድ ተጣራ" አለው። ኢብራሂምም፦"ጌታዬ እኔ ደካማ ባሪያህ ነኝ ድምፄ እኮ አይደርስም"አለው። አላህም፦"አንተ ተጣራ ማድረስ የኔ ስራ ነው" አለው። ኢብራሂምም ትልቅ ተራራ ላይ በመውጣት ተጣራ።ያን ግዜ ከየሀገሩ ያሉ ህዝቦች ጥሪውን በመቀበል መካ መጥተው ሞሉ። ኢብራሂምም የሀጅን ስነስርዐት ለሁሉም አስተማራቸው። ከዚያ በኋላ የኢብራሂም ሚስት ሳራ በከንዐን ምድር ሀብሩን በምትባል ቦታ በ127 አመቷ ዱንያን ተሰናበተች። ከዚያ በኋላ ኢብራሂም ለሳራ ልጅ ኢስሀቅ ሪፍቃ ቢንት በቱኢል የተባለችን እንስት አጭቶለት አጋባው። ኢብራሂም እደሚያቸው 175 ሲሆን ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። እስማኢል ና እስሃቅቀበሯቸው። ኢብራሂም የተቀበሩት #በሀብሩንነው።የቺ አከባቢ በሁን ሰዐት ከሊል በመባል ትተወቃለች። አይሁዶች ና እንግሊዛዊያን ሄብሮን በማለት ይጠሯታል።እብራሂም ዐ ሰ የነቢያት አባት ነቸው። ከኢብራሂም ዐ ሰ ብሇላ ከሰቸው ዘር ካልሆነ በስተቀር አንደም ነቢይ አልተላከም።   •••✿ ❒ ተ_ፈ_ፀ_መ ❒✿••• በቀጣይ #የነብዩሏህ_ኢስሃቅ_ና_የያእቁብ(ዐ.ሰ) ታሪክ እንጀምራለን 🥰 #share https://t.me/Umete_Resul
Show all...
የረሱል ኡመቶች

የረሱል ኡመቶች ➻ጥበባዊ ንግግሮች ➻ኢስላማዊ ታሪኮች ➻ትክክለኛ ሀዲሶች ➻ የ ነብያቶች ታሪክ 😃 ☆የተለያዩ ውድድሮች♤ ➻Islamic Pic ➻ገጠመኞች ➻አስገራሚ እውነታዎች ወደ አሏህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ እኔ ከሙስሊሞች ነኝ ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው ሀሳብ አስተያየት ካሎት 群主👉 @IYIYasir.....লাভ

3
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.