💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
Open in Telegram
🌹 ለፍቅረኛዎ💕 ምን ማለት ይፈልጋሉ❓ ❤ ፍቅርዎን በመግለፅ surprise 😵 ማድረግ፤ ❤ HBD ለማለት፤ 🎂 ❤ ናፍቆትዎን ለመግለፅ፤ 🚶♀ ❤ ይቅርታ ለመጠየቅ፤🤦♂ & Cross ከፈለጉ በዚህ 👉 ,,📩 @Joon_Vision ይላኩልን ━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━ ⚠️ የሚልኩለት ሰው member ካልሆነ መጀመሪያ ሊንኩን @MENTA_LBOCH ይላኩለት።
Show more1 737
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
1 737
ከጨለመ አይደል...
ኩራዝ ትዝ ሚልህ
መሸት ሲል አይደል...
የብርሃን ጥቅሙ የሚገለጥልህ
ሲበርድህም አይደል...
ፀሀይ ምትናፍቀው
[እንግዲህ እሷንም]
ያጣሃት እለት ነው...
ፍቅሯን እምታውቀው
🥰🥰 😘😘 🌷🌷😍🙏🙏🥀🥀
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @joon_vision
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
😢 አስለቃሽ የቴሌግራም
ፕሮፋይል😔
እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመንታ ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ💛
🌹ክፍል አንድ (1)❤️
ሂክማ እባላለሁ ተወልጀ ያደኩት በመዲናችን አዲስ አበባ ገርጂ አካባቢ በሚባለዉ ሰፈር ሲሆን ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ሴት ልጃቸው ነኝ፡፡ ቤተሰቦቼ ለኔ ያላቸው ፍቅርና ስስት በቃል የሚገለፅ አይደለም! ፍላጎቴ ሳይዛነፍ አቀማጥለው ነው ያሳደጉኝ፡፡ በጥሩ ስነምግባር በኢስላም ተርብያ ዲኔን እያስተማሩ የአንድ ብቁ እና ንቁ እሆንላቸው ዘንድ ተንከባክበው አሳደጉኝ፡፡ የኔም የዋዛ አልነበርኩም በትምህርቴም ሆነ በቂርአቴ ስለጉብዝናየ ኡስታዞቼ እና መምህራኖቼ ምስክር ናቸው፡፡ ቦሌ መድሀኒያለም preparatory school የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ፡፡ ጓደኞቼ ስለኔ መልካምነት አውርተው አይጠግቡም፡፡
መምህራኖቼ ገና በዛ የአፍላነት እድሜ 1 ብሎ በሚጀምርበት fire age ተብሎ በሚጠራው እድሜ ክልል ውሰጥ ሆኜ የባህሪ ለውጥ ያለማሳየቴ ለመምህሮቸ ትንግርት ሆኖባቸውም ነበር፡፡ ከዛም በኃላ ለኔ ያላቸው ውዴታም ክብርም ከፍ ያለ ነው! እንደ ትልቅ ሰው ጓደኛቸው አርገው ያዩኛል፡፡
አባቴ የመንግስት ሰራተኛ ሲሆን ሸዋሮቢት በምትባለዉ ከተማ ነበር የሚሰራው ብዙ ጊዜ ፊልድ ስለሚበዛበት ከሸዋሮቤትም ወደ ሌላ ሀገር ይሄድ ነበር እቤትም እማ ብዙ ጊዜዋን ከኔ ጋር ታሳልፍለች፡፡ አሁን ላይ ሰወች ለሚወዱት ማንነቴ ግንባታ ኡሚ ከፍተኛውን ድርሻ ትወስዳለች! ወደ መልካም ነገር የምታመላክተኝ መንገድ መሪየ ኡሚ ናት፡፡ አባቢ ለእማ ልዩ ፍቅርና ክብር አለው መልካምነቷና ብልህነቷን ያደንቃል፡፡ በተለይ ደግሞ የአይኑ ማረፊያ የሆነችውን አንድ ልጅን ዲኗን እንድታውቅ መንገድ መሪ ሆናት ልጅም በሰወች ዘንድ ተወዳጅ እንድትሆንለት ከፍተኛውን ድርሻ ለወሰደቾው እናቴ አድናቆቱ ከልብ ነው፡፡
እኔም "አላህ ኸይርን ሽቶልኝ ዲኔን አስገንዝቦኛል! አንድ ስህተት እንዳለኝ አቀዋለሁ የሰዉ ልጅ ነኝ እና መሳሳቴ አይቀርም ጓደኞቼ ሁሉም profile pictur የራሳቸዉን ፎቶ ስለሚያረጉ በጓደኞቼ ግፊት እኔም profile የራሴን ማረግ ከጀመርኩ ሰነባበትኩ፡፡ ፎቶ መነሳቱ ሀራም መሆኑን እያወኩ ግን ጓደኞቼ ጋር ሰርግ በሚኖረን ሰአት ትምህርት ስንሄድ የማስታወሻ ፎቶ እየተባለ እየተነሳን profile ለማረግ እንቸኩል ነበር፡፡
በዛም ላይ የማላቀዉን ለማወቅ በተለያዩ social media ላይ የዳእዋ ጥሪ የሚያረጉ ግሩፓች ላይ ተሳታፊ ሆንኩኝ፡፡ whatsap እና telegram የኔ የዳእዋ ጥሪ መገልገያ ከሆኑ ሰነበቱ፡፡ ብዙ group ላይ እኔን add ያረጉኛልበትምህርት ቤት የሚከፈቱ የሰፈር ልጆች የሚከፍቱት group ላይ ብዙ group ገብቻለሁ አገለግላለሁ፡፡ በቦሌ priparatory scholl አንዱ ልጅ group ከፍቶ በጣም ብዙ ተከታታይ ያለዉ ኢስላሚክ group ሁኖ ነበር ከዛም ዉጭ ሌላ group ነበሩኝ፡፡ ፎቶየን እቀያይር ነበር የትዳረ ጥያቄ በቤተሰቦቼ እየመጣ ትምህርቴን ልጨርስ እያልኩኝ አሳልፊያለሁ፡፡
እናቴም ግን የዩኒቨርስቲ ዉጤት ቢመጣልሽ አትማርም ወደ ትዳር ነዉ የምገቢዉ ልጅ ወልደሽ ማየት እፈልጋለሁ እንጂ ዩኒቨርስቲ ገብተሽ ጊዜ እንድፈጂ አልፈልግም ብቻ ትምህርት እንደጨረሽ ከተቻለ አንቺ ያመጣሽዉን ባል እቀበላለሁ ግን ኢማን የሌለዉ ከሆነ እኔ የጠየቁኝ ያዘጋጀሁልሽ ትምህርቷን ትጨርስ ብየ የመለስኳቸዉ ስላለ እኔ የወደድኩትን እንደምወጂ እርግጠኛ ነኝ አለችኝ፡፡
...እናት ወልይ ናት አይደል የሚባለዉ እኔም እሺ ማሚ ነበር መልሴ፡፡እኔም ተፈትኜ ዉጤት ቢመጣም ዩኒቨርስቲ ላልገባ ወስኛለሁ፡፡
ብዙ የሚያወሩኝ የማላቃቸዉ ልጆች ቁጥሬን ከየት አገኛችሁ ብየ ስጠይቅ ከGroup አድራሻሽ ነዉ ቁጠርሽ የለንም ይሉኝ ነበር ከዛ በblock አሰናብት ነበር፡፡
ከእለታት አንድ ቀን ግን ከወትሮው ለየት ያለ ነገር አጋጠመኝ፡፡ ከማላውቀው ሰው በእኔ በtelegram ቁጥር የድምፅ መልእክት ተልኮልኝ አየሁ፡፡ መልእክቱን ስሰማ ቀጥታ ወደ ፕሮፍይሉ በመሄድ ስለሱ ማንነት ለማወቅ እንዲረዳኝ ማየት ጀመርኩኝ በጠቅላላ ኢስላማዊ ፎቶወች እና ዱአ ይበዛበታል፡፡፡ እኔም ለማጣራት ያህል ነበር ፕሮፍይሉን የፈተሽኩት፡ የድምፅ መልእክቱ ከአምስት ደቂቃ የበለጠ ሲሆን profile ባረኩት ፎቶ አላህን እንድፈራ ፎቶ ሀራም መሆኑን የካተተ record ነበር አነጋገሩ በጣም አስተማሪ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ እሱ ነበር ተይ ያለኝ የማላቀዉ ቁጥሮች profile እያዩ ቆንጂት ሀይ የማይለኝ የለም telegram ስገባ የማላቀዉ ቁጥር ይበዛብኝ ነበር እኔ ግን አጂ ነብይ ጋር አላወራም ብየ ማንንም አላወራም ግን ምን ዋጋ አለዉ profile ከgroup እያዩት መሆኑን የተረዳሁት ዘንግቼ ነበር፡፡
በፁሁፍም ከሀዲስ ከቁርአን ማስረጃ እያቀረበ ብዙ ትምህርቶችን ላከልኝ እኔም ጀዛ ከሏህ ብየ ፎቶየን profile ያረኩትን እንዳለ አጠፋሁ፡፡
ከዛም ግን ጎበዝ ዲነኛ እንደሆንሽ አቃለሁ profile ፎቶዉ የአንቺ መሆኑን ሳይ በጣም ነዉ የገረመኝ ሂክማ መቼ ጀምራ እንደዚህ ሁነች ብየ ግራ ገብቶኝ ነዉ አለኝ
....እኔም በመደንገጥ እንዴ ከአሁን በፊት ታቀኛለህ እንዴ ????? አልኩት
እሱም........
ይቀጥላል...
✎ ክፍል ሁለት (2) ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like & Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @joon_vision
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
😢 አስለቃሽ የቴሌግራም
ፕሮፋይል😔
እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ በመንታ ልቦች የ ቴሌግራም ገፅ ተዘጋጅቶ የቀረበ💛
🌹ክፍል አንድ (1)❤️
ሂክማ እባላለሁ ተወልጀ ያደኩት በመዲናችን አዲስ አበባ ገርጂ አካባቢ በሚባለዉ ሰፈር ሲሆን ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ሴት ልጃቸው ነኝ፡፡ ቤተሰቦቼ ለኔ ያላቸው ፍቅርና ስስት በቃል የሚገለፅ አይደለም! ፍላጎቴ ሳይዛነፍ አቀማጥለው ነው ያሳደጉኝ፡፡ በጥሩ ስነምግባር በኢስላም ተርብያ ዲኔን እያስተማሩ የአንድ ብቁ እና ንቁ እሆንላቸው ዘንድ ተንከባክበው አሳደጉኝ፡፡ የኔም የዋዛ አልነበርኩም በትምህርቴም ሆነ በቂርአቴ ስለጉብዝናየ ኡስታዞቼ እና መምህራኖቼ ምስክር ናቸው፡፡ ቦሌ መድሀኒያለም preparatory school የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ፡፡ ጓደኞቼ ስለኔ መልካምነት አውርተው አይጠግቡም፡፡
መምህራኖቼ ገና በዛ የአፍላነት እድሜ 1 ብሎ በሚጀምርበት fire age ተብሎ በሚጠራው እድሜ ክልል ውሰጥ ሆኜ የባህሪ ለውጥ ያለማሳየቴ ለመምህሮቸ ትንግርት ሆኖባቸውም ነበር፡፡ ከዛም በኃላ ለኔ ያላቸው ውዴታም ክብርም ከፍ ያለ ነው! እንደ ትልቅ ሰው ጓደኛቸው አርገው ያዩኛል፡፡
አባቴ የመንግስት ሰራተኛ ሲሆን ሸዋሮቢት በምትባለዉ ከተማ ነበር የሚሰራው ብዙ ጊዜ ፊልድ ስለሚበዛበት ከሸዋሮቤትም ወደ ሌላ ሀገር ይሄድ ነበር እቤትም እማ ብዙ ጊዜዋን ከኔ ጋር ታሳልፍለች፡፡ አሁን ላይ ሰወች ለሚወዱት ማንነቴ ግንባታ ኡሚ ከፍተኛውን ድርሻ ትወስዳለች! ወደ መልካም ነገር የምታመላክተኝ መንገድ መሪየ ኡሚ ናት፡፡ አባቢ ለእማ ልዩ ፍቅርና ክብር አለው መልካምነቷና ብልህነቷን ያደንቃል፡፡ በተለይ ደግሞ የአይኑ ማረፊያ የሆነችውን አንድ ልጅን ዲኗን እንድታውቅ መንገድ መሪ ሆናት ልጅም በሰወች ዘንድ ተወዳጅ እንድትሆንለት ከፍተኛውን ድርሻ ለወሰደቾው እናቴ አድናቆቱ ከልብ ነው፡፡
እኔም "አላህ ኸይርን ሽቶልኝ ዲኔን አስገንዝቦኛል! አንድ ስህተት እንዳለኝ አቀዋለሁ የሰዉ ልጅ ነኝ እና መሳሳቴ አይቀርም ጓደኞቼ ሁሉም profile pictur የራሳቸዉን ፎቶ ስለሚያረጉ በጓደኞቼ ግፊት እኔም profile የራሴን ማረግ ከጀመርኩ ሰነባበትኩ፡፡ ፎቶ መነሳቱ ሀራም መሆኑን እያወኩ ግን ጓደኞቼ ጋር ሰርግ በሚኖረን ሰአት ትምህርት ስንሄድ የማስታወሻ ፎቶ እየተባለ እየተነሳን profile ለማረግ እንቸኩል ነበር፡፡
በዛም ላይ የማላቀዉን ለማወቅ በተለያዩ social media ላይ የዳእዋ ጥሪ የሚያረጉ ግሩፓች ላይ ተሳታፊ ሆንኩኝ፡፡ whatsap እና telegram የኔ የዳእዋ ጥሪ መገልገያ ከሆኑ ሰነበቱ፡፡ ብዙ group ላይ እኔን add ያረጉኛልበትምህርት ቤት የሚከፈቱ የሰፈር ልጆች የሚከፍቱት group ላይ ብዙ group ገብቻለሁ አገለግላለሁ፡፡ በቦሌ priparatory scholl አንዱ ልጅ group ከፍቶ በጣም ብዙ ተከታታይ ያለዉ ኢስላሚክ group ሁኖ ነበር ከዛም ዉጭ ሌላ group ነበሩኝ፡፡ ፎቶየን እቀያይር ነበር የትዳረ ጥያቄ በቤተሰቦቼ እየመጣ ትምህርቴን ልጨርስ እያልኩኝ አሳልፊያለሁ፡፡
እናቴም ግን የዩኒቨርስቲ ዉጤት ቢመጣልሽ አትማርም ወደ ትዳር ነዉ የምገቢዉ ልጅ ወልደሽ ማየት እፈልጋለሁ እንጂ ዩኒቨርስቲ ገብተሽ ጊዜ እንድፈጂ አልፈልግም ብቻ ትምህርት እንደጨረሽ ከተቻለ አንቺ ያመጣሽዉን ባል እቀበላለሁ ግን ኢማን የሌለዉ ከሆነ እኔ የጠየቁኝ ያዘጋጀሁልሽ ትምህርቷን ትጨርስ ብየ የመለስኳቸዉ ስላለ እኔ የወደድኩትን እንደምወጂ እርግጠኛ ነኝ አለችኝ፡፡
...እናት ወልይ ናት አይደል የሚባለዉ እኔም እሺ ማሚ ነበር መልሴ፡፡እኔም ተፈትኜ ዉጤት ቢመጣም ዩኒቨርስቲ ላልገባ ወስኛለሁ፡፡
ብዙ የሚያወሩኝ የማላቃቸዉ ልጆች ቁጥሬን ከየት አገኛችሁ ብየ ስጠይቅ ከGroup አድራሻሽ ነዉ ቁጠርሽ የለንም ይሉኝ ነበር ከዛ በblock አሰናብት ነበር፡፡
ከእለታት አንድ ቀን ግን ከወትሮው ለየት ያለ ነገር አጋጠመኝ፡፡ ከማላውቀው ሰው በእኔ በtelegram ቁጥር የድምፅ መልእክት ተልኮልኝ አየሁ፡፡ መልእክቱን ስሰማ ቀጥታ ወደ ፕሮፍይሉ በመሄድ ስለሱ ማንነት ለማወቅ እንዲረዳኝ ማየት ጀመርኩኝ በጠቅላላ ኢስላማዊ ፎቶወች እና ዱአ ይበዛበታል፡፡፡ እኔም ለማጣራት ያህል ነበር ፕሮፍይሉን የፈተሽኩት፡ የድምፅ መልእክቱ ከአምስት ደቂቃ የበለጠ ሲሆን profile ባረኩት ፎቶ አላህን እንድፈራ ፎቶ ሀራም መሆኑን የካተተ record ነበር አነጋገሩ በጣም አስተማሪ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ እሱ ነበር ተይ ያለኝ የማላቀዉ ቁጥሮች profile እያዩ ቆንጂት ሀይ የማይለኝ የለም telegram ስገባ የማላቀዉ ቁጥር ይበዛብኝ ነበር እኔ ግን አጂ ነብይ ጋር አላወራም ብየ ማንንም አላወራም ግን ምን ዋጋ አለዉ profile ከgroup እያዩት መሆኑን የተረዳሁት ዘንግቼ ነበር፡፡
በፁሁፍም ከሀዲስ ከቁርአን ማስረጃ እያቀረበ ብዙ ትምህርቶችን ላከልኝ እኔም ጀዛ ከሏህ ብየ ፎቶየን profile ያረኩትን እንዳለ አጠፋሁ፡፡
ከዛም ግን ጎበዝ ዲነኛ እንደሆንሽ አቃለሁ profile ፎቶዉ የአንቺ መሆኑን ሳይ በጣም ነዉ የገረመኝ ሂክማ መቼ ጀምራ እንደዚህ ሁነች ብየ ግራ ገብቶኝ ነዉ አለኝ
....እኔም በመደንገጥ እንዴ ከአሁን በፊት ታቀኛለህ እንዴ ????? አልኩት
እሱም........
ይቀጥላል...
✎ ክፍል ሁለት (2) ይቀጥላል... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like & Share ♥️ ማድረግ አይርሱ።
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል ሼር ያድርጉ
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @joon_vision
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
ዘረኝነት፣ በሽታ፣ ጥላቻና ችግር ከምድራችን ጠፍቶ የምናይበት የፍቅር፣ የደስታና
የሰላም ዓመት ይሁንልን!🙏
🌼🌼🌼መልካም አዲስ ዓመት🌼🌼🌼
🌼
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @joon_vision
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
❣❣መልካሙ ዶክተር❣❣
┉┉✽»🌹✿🌹»✽┉┉
❣❣የመጨረሻ ክፍል❣❣
እራሴን ለማጥፋት እቅድ ሳወጣ በአጋጣሚ እዩኤል የሰጠኝ የአደራው ነገር እና የደብዳቤው ነገር ትዝ አለኝ... በፍጥነት ደብዳቤውን ካስቀመጥኩበት ቦታ አውጥቼ ስከፍት ሁለት ወረቀቶች በውስጡ አሉ... ቶሎ ብዬ አንዱን ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩኝ ደብዳቤው እንዲህ ይላል፦
ደብዳቤውን ከማንበባችሁ በፊት እስቲ ቻናሉን አጋሩ አቤት እናንተ የሚያስከፍል ይመስል ትትስታላችሁ ለማነኛውም ደብዳቤው እንዲህ ይላል👇
በጣም የምወድህ ምርጥ ጓደኛዬ እንዴት ነህ? እግዚአብሔር ይመስገን እኔ ደህና ነኝ፣ በእርግጥ ስለ አንተ ማንነት ብዙም አላውቅም ግን በዚህች አብረን በሆንበት ጥቂት ወራቶች ውስጥ ከአንተ ብዙ ነገሮችን ተምሬያለሁ ግን አሁን ማውራት የፈለኩት ስለ መልካምነትህ አይደለም፣ ከአንተ ልርቅ መሆኔን ልነግርክ ነው እንጂ! በርግጥ አንተ ምናልባት አንድም ቀን ከእኔ ይርቃል ብለህ ላታስብ ትችላለህ ግን እኔም ግድ ሆኖብኝ ነው ለመራቅ የወሰንኩት ምክንያቱም በአንተ እና በሀረግ ፍቅር መሃል መግባት አልፈልግም ዝም ብዬ እንዳልቀመጥ ደግሞ አቅም አጣሁ፣ ሀረግን በጣም እወዳታለሁ ለሷ ግን ተመንገር የለብህም አንተም እንድታውቅ የፈለኩት ልርቅህ ስለሆነ ምክንያቱን እንድታውቅ ብዬ ነው ይላል ምን? ዶክተር ከእኔ ፍቅር? ቀልድ መሆን አለበት ብዬ በፍጥነት ሁለተኛውን ወረቀት ስከፍት.. እንዲህ ይላል፦ ሁሌም የምወድሽ በልቤ ዙፋን ላይ ለዘላለም ተቀምጠሽ የምትኖሪ የመጀመርያዬም የመጨረሻዬም የልቤ ንግስት የምወድሽ የማከብርሽ ሀረግ ሰላም ላንቺ ይሁን... አንቺን ለመግለጽ ብዙ ቃላቶች አይበቁም እነዚህ ጥቂት ወራቶች አንቺ ከጎኔ ባትሆኝ እንዴት ሆነው ያልቁ ነበረ ብዬ ሁሌም አስብ ነበረ አንቺ ከቨጎኔ ስለነበርሽ ግን ይሄው የመጨረሻው ቀን ደረሰ የኔ ፍቅር በውስጤ ይዤ ለመሞት ያሰብኩ አንድ ምስጢር ነበረ አሁን ግን ላንቺ ጠቃሚ ስለሆነ ለመንገር ወሰንኩኝ እኔ የካንሰር በሽተኛ ብቻ አይደለሁም ትዝ ይልሻል? የዚያን ቀን በጣም ስሜት ውስጥ ከገባን በኋላ ምክንያት ፈጥሬ ጥዬሽ የሄድኩትን ቀን? የዚያን ቀን ጥዬሽ የሄድኩት ስሜት ስለሌለኝ ሳይሆን በደሜ ውስጥ ኤች አይ ሺ ኤድስ ስለነበረብኝ ነው። ደሜ ውስጥ እሱን ተሸክሜ እስከዛሬ አብሬሽ በመኖሬ ራስ ወዳድ ነኝ አይደል? የኔ ፍቅር እውነታውን ያወኩት ፍቅር ውስጥ ከገባን በኋላ ነበረ.. ከዛም ምክንያት ፈጥሬ ካንቺ ለመራቅ አሰብኩኝ በዚህ መሃል ግን ዶክተሩ ይሄን ደብዳቤ ሰጠኝ እኔም ዶክተሩ መልካም ሰው ስለሆነ የሱን መልካምነት በእኔ ምክንያት አንቺም እንድታውቂ ብዬ ዝም አልኩኝ እውነታው ይሄ ነው ፈጣሪ ሁሉንም ነገር ቀድሞውኑ ያውቃል እኔ የምሞተው ብኖርም ተስፋ ስለሌለኝ ነው እራስሽን ጠብቂ የእናቴን ነገር ደግሞ አደራ ሁሌም የምወድሽ የሁልጊዜ አፍቃሪሽ እዬኤል ይላል። ከአይኔ እምባ መውረድ ጀመረ... ለካ ሰውን አውቃለሁ ማለት ውሸት ነው የሰውን ልብ የሚያውቀው አንድ ፈጣሪ ብቻ ነው። ግን እሱንም መውቀስ አልችልም ምክንያቱም ለኔ ብሎ ያደረገው ነገር ነው የሚወዱትን አጥቶ መኖር በጣም ከባድ ቢሆንም ህይወት ግን ትቀጥላለች እሱ እንዳለውም ሁሉም ነገር ያለ ምክንያት አይሆንም!! እዩኤል ከሞተ ከሁለት ዓመት በኋላ ከዶክተሩ ጋር በፍቅር ማሳለፍ ጀመረን እኔም ቃሉን ጠብቄ ደስተኛ ሆኜ እናቱንም አቅሜ በቻለው መጠን ሁሉ እየረዳው እየኖርኩኝ ነው እናም የምትወዱትን ሰው በአጋጣሚ ብታጡ እንኩዋን ህልሙን ለመኖር ሞክሩ እንጂ ራሳችሁን ወደ መጥፎ ሱስ ወይንም እብደት አስገብታችሁ ነብሱን እረፍት አትንሱት እያልኩ ታሪኬን እዚሁ ልቋጭ።
ተ . ፈ . ፀ . መ
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @Joon_Vision
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
የመጨረሻው ክፍል ነገ ይለቀቃል ሀሳብ አስተያየታቹን ጣል ጣል አርጉባት
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @Joon_Vision
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
❣❣መልካሙ ዶክተር❣❣
┉┉✽»🌹✿🌹»✽┉┉
❣❣ክፍል አስር❣❣
አሁን ቀኑ አልደረሰም አለኝ እኮ ቀኑ መቼ ነው አልኩት ቀኑ....በአንድ አጋጣሚ በጣም ከፍቶሽ መፍትሄ ስታጪ ደብዳቤውን ከማንበብሽ በፊት የትኛውም ውሳኔ ላይ አትድረሽ ቀድመሽ ደብዳቤውን ማንበብ አለብሽ አለኝ እሺ ፍቅር አንተው እንዳልከው አደርጋለሁ ብዬ ደብዳቤውን ተቀብዬ ቤት ሄድኩኝ.. .. ደብዳቤው ውስጥ ያለውን ነገር የማወቅ ጉጉት እረፍት ቢነሳኝም ቃል ግን ቃል ነውና በአንድ ጥሩ ቦታ ላይ አስቀመጥኩት ዶክተር አንድ ቀን ስልክ ደውሎ እዩኤል እንዴት ነው አለኝ ምንም አዲስ ነገር የለም ግን በድጋሚ ሆስፒታል መሄድ አለበት እናቴ ብሩን ለመስጠት ቃል ገብታለች አልኩት የግድ መሄድ አለበት ካልሽ ችግር የለም እኔም በቻልኩ መጠን ለመርዳት እሞክራለሁ እንደውም ነገ ጠዋት መኪና ይዤ እመጣለሁ ከዛም አንቺ የፈለግሽበት ሆስፒታል ሁሉ ይዘን እንሄዳለን አለኝ ዶክተር በጣም አመሰግናለሁ ብዬ ስልኩን ዘጋውት በልቤ ተመስገን አምላኬ ብሩ አሁን ተገኝቶዋል... እዩኤል መቼም አይሞትም ብዬ ተመልሼ ወደ እዩኤል ሄድኩኝ ዛሬ ከእሱ ጋር ብዙም ቁጭ አላልኩም.. ቤት ውስጥ የቆሸሸ እቃ ምናምን ሞልቶ ነበር እቃዎችን አጥቤ ቤቱን አስተካክዬ ወደ ቤት ተመልሼ ልመጣ ስል ፍቅር የሚል ድምፅ ሰማሁ... አቤት ብዬ ስሄድ.. ለምን ጥለሽኝ ትሄጃለሽ አለኝ አይይይ ፍቅር እናቴ ቤት ውስጥ ይጠብቁኛል ብዬ እኮ ነው አልኩት አይዞሽ አሁን ጥቂት ጊዜ ነው የቀረኝ ግን እኮ ፍቅር በጣም ነው የምወድሽ አለኝ የኔ ውድ እኔም በጣም እወድሃለሁ አልኩት እስኪ በተግባር አሳዪ ቢሉሽ ምን ታደርጊልኝ ነበረ ብሎ ጠየቀኝ የመጨረሻ ምንያህል እንደምወድህ ለማሳየት ሞት እንኳን ቢሆን እሞትልህ ነበረ አልኩት በጣም ደንግጦ.... ፍቅር ሁለተኛ እንደዚህ እንዳትዪ አለኝ የምትወጅኝ ከሆነ እኔ በሌለውበት እኔ ለምወደው ነገር ጥንቃቄ ማድረግ ነው ሞትሽ ማለት እኮ እኔን አትወጅኝም ማለት አይደል አለኝ እኮ አንተ ምንድነው የምትወደው አልኩት እናቴን ነዋ! እኔ በሌለውበት እሷን መንከባከብ የሚችል ሰው የእውነት ይወደኛል ማለት ነው ጥሏት የሞተ ሰው ግን እኔንም አይወደኝም ማለት ነው አለኝ ስለ ምን ሞት የምታወራው አሁን ስለ ሌላ ነገር እናውራ አልኩት እናትህማ ለኔም እናቴ ናት ግን አደራ ስለ ሞት አታውራ አልኩት በጣም ደስ አለው ፍቅር ብሎ እጄን ያዘኝ.... እጁ በጣም ቀዝቅዞ ነበረ... ፍቅር ለምንድነው እጅህ እንደዚህ ቀዝቃዛ የሆነው አልኩት መልስ የለም.... ፍቅር ምነው ደከምክ እንዴ አልኩት... መልስ የለም... ፍቅር አውራ እንጂ እኔ እንደዚህ አይነት ቀልድ አልወድም አልኩት.... መልስ የለም... በድንጋጤ ጩኸቴን ለቀቅኩት
┉┉✽»🌹✿🌹»✽┉┉
ይቀጥላል.. አሳባችሁን ኮሜንት ላይ አስቀምጡልኝ።l
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @Joon_Vision
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
❣❣መልካሙ ዶክተር❣❣
┉┉✽»🌹✿🌹»✽┉┉
❣❣ክፍል ዘጠኝ❣❣
ዋውውውው በጣም ደስ አለኝ በልቤ ዶክተሩ ውሸታም ነው አልኩት ትንሽ አብረን ከተጫወታን በኋላ እዩኤል በአፉ ደም መትፈት ጀመረ... ፍቅር ፍቅር ደም እኮ ነው የተፈው አልኩት ታድያ ምነው አዲስ ሆነብሽ አለኝ ማለት እንዴት አይሆንብኝም አልኩት አይይይይ የተመመ ሰው ብዙም ጊዜ ደም ይታፍል አለኝ እዩኤል ከዚህ በፊትም ደም እየታፍ መሆኑን ነገር ግን ከእኔ ደብቆ እንደነበረ አሁን ገና ገባኝ የኔ ፍቅር ሃኪም ቤት እንሂድ አልኩት አይይይ አሁን እኮ ደህና ነኝ ደግሞ ምንም ለውጥ እንደሆነ የለም መሄዱስ ምን ያደርጋል ብለሽ ነው ባይሆን አንቺ ሁለም ደስተኛ ሁኝልኝ ደስ ስልሽ ደስ ይለኛል ብሎ እምባ ማፍሰስ ጀመረ ፍቅር እያለቀስክ እኮ ነው አልኩት የደስታ እምባ እኮ ነው አለኝ ስለ የትኛው ደስታ ነው የምታወራው አልኩት ፍቅር አንቺን አፍቅሮ ይሄን ሁሉ ወረቶችን በፍቅር አሰልፈን መሞት በራሱ ለኔ ትልቅ ደስታ ነው ብዙዎች እኮ ናቸው ይሄን እድል ማግኘት ያልቻሉት ብዙ ዘመናትን ኖረው ግን ፍቅር የሚባል ነገር በጭራሽ አያውቁም እኔ እድለኛ ነኝ፣ ፍቅር ግን ምንም ነገር ብመጣ ሀዘንተኛ እንድትሆኝ አልፈልግም ሁለም ደስተኛ ሁኝልኝ እሽ አለኝ ውዴ ስለ ምን ሞት ነው የምታወራው በእናትህ ሁለተኛ ስለ ሞት አታውራ አሁን እኮ ደህና ነህ ከዚህ በኋላ ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል አልኩት እኔ ግን አይመስለኝም ልቤን ፍርሃት ፍርሃት ይለኛል ከዚህ በፊት እንደዚህ አይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም ነበረ አሁን ግን መጨረሻው ምዕራፍ ላይ ያለውት ይመስለኛል፣ ግን ፍቅር ዶክተሩ በጣም መልካም ሰው ነው አለኝ ይሞታል የሚለውን ነገር ነግሮኝ ስለነበረ ባክህ እሱ አስጣልታ ነገር ነው እሱን ተው አልኩት ምነው ፍቅር በዚህ ዘመን እንደሱ ጊዜውን ገንዘቡን ሁሉንም ነገር አይቶ እንኩዋን ለማያውቅ ሰው አሰልፎ የሚሰጥ ሰው ማን ነው? እነዚህን ሁሉ ወረቶች የቆየውት ከፈጣሪ በታች በእሱ እርዳታ አይደል? እሱ ባይኖር ሌላ ቀርቶ ምግብ ራሱ አልነበርም እኮ አለኝ ለናገሩ እዩኤል ትክክል ነው ግን እኛ ሰዎች መቼም እውነት ተናግሮ ከሚጎዳ ሰው ይልቅ በውሸት የሚያጽናና ሰውን አብዝታን እንወዳለን የኔም ጥላቻ ከዚው የመጣ ነው። እሱማ ትክክል ነህ ግን ውሸታም ነው አልኩት ማን ዶክተር? ፍቅር እሱ በፍጹም ውሸታም አይደለም ባይሆን ይሄን ደብዳቤ ወስደሽ ቤትሽ አስቀምጪ አለኝ የምን ደብዳቤ ነው? ማነው የላከው? አልኩት ሁሉንም ነገር ደብዳቤ ላይ ታገኛለሽ ነገር ግን ደብዳቤውን አሁን መክፈት የለብሽም አለኝ እኔስ ድሮ በአንተ ፊት ምን ብዬ እከፍታለሁ ብለህ ነው አልኩት እንደዛ ማለቴ አይደለም.... ፍቅር ቤት ሄደሽም መክፈት የለብሽም አለኝ እኮ ለምን አልኩት መክፈት ያለብሽ ቀን ይመጣል አሁኑ ቀኑ አልደረሳም አለኝ እኮ ቀኑ መቼ ነው አልኩት ቀኑ
ይቀጥላል...
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @Menta_lbochh_bot
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
❣❣መልካሙ ዶክተር❣❣
┉┉✽»🌹✿🌹»✽┉┉
❣❣ክፍል ስምንት❣❣
ሀረግ የሆነ ያልናገርኩሽ ነገር አለ አለኝ እኮ ምንድነው ዶክተር ንገረኛ አልኩት ምን መሰለሽ ሀረግ አንቺ በጣም ጠንካራ እና ብልህ ልጅ ነሽ ስለዚህ የትኛውም ነገር ብመጣ ጽኑ መሆን አለብሽ ደግሞ ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ፍቃድ እንደሚሆን ታውቃለሽ አይደል ስለዚህ ጠንካራ መሆን አለብሽ አለኝ ዶክተር ስለ ምክሩ አመሰግናለሁ ያልናገርከኝ ነገር ግን ምንድነው ምንም ይሁን ምን ማወቅ እፈልጋለሁ ንገረኝ ብዬ መስጨናቅ ጀመርኩት ሀረግ ይሄን የምናግርሽ ብልህ ልጅ ነሽ ብዬ ስለሚያምን ነው እዩኤል የምርመራ ውጤት እንደሚያሳይ ከሆነ በህይወት መቆየት የምችለው ሁለት ወረቶችን ብቻ ነው ይህን የምናግርሽ ግን ቅድም እንደልኩሽ ብልህ እና ጠንካራ ሴት ስለሆንሽ ነው እነዚህን ጥቂት ቀናቶችን በሀዘን ሳይሆን በደስታ ለማሳለፍ ሞክሪ በርግጥ አውቃለሁ በጣም ከባድ ነው ቢሆንም ግን እዩኤል ሁለት ወር ራሱ መቆየት የምችለው ደስተኛ ከሆነ ብቻ ነው ይህ ከሊሆነ ሁለት ወር ራሱ መቆየት አይችልም እዩኤል እነዚህን ሁለት ወረቶችን እንዲቆይ የምትፈልጊ ከሆነ በሱ ፊት ደስተኛ መሆን መቻል አለብሽ ፍቅረኛሽን መትረፍ በለመቻሌ አዝናለሁ አንቺ ግን እራስሽን ጠብቂ አለኝ ዶክተር ምን እያልክ እንደሆነ ተውቆሃል? እዩኤል ይሞታል እያልከኝ እኮ ነው ቆይ ግን ምን አይነት ሞርተኛ ነህ? ዶክተር ብሩ እኮ ተገኝተዋል ዶክተር እዩኤል አይሞትም አልኩት ሀረግ ይሄ የብር ጉዳይ አይደለም ሰአቱ አልፏል It's too late ከእንግዲህ ወዲህ ተአምር ከልተፈጠረ በስተቀር እዩኤል የማዳን እድል የለውም አለኝ ዶክተር እዩኤል እይሞትም እያልኩ መንገድ ላይ ብቻዬን እዩኤል አይሞትም እያልኩ ወደ ቤት ተመለስኩኝ ቤት ውስጥ መጥቼ ከእግዚአብሔር ጋር ክርክር ጀመርኩኝ ቆይ ለምን ነብሴን እሾህ መሃል ፈጠርከት? አንዱን ሰጥታኝ አመስግኜ ሰልጨርስ ለምን ሌላውን ትወስድብኛለህ? ቆይ እኔ ደስተኛ እንዲኖር በ40ኛው ቀን ላይ አልተጻፈም? እያልኩ ያለውን የሌላውን ሁሉንም መጠየቅ ጀመርኩኝ አሁንም ግን መልስ የሚሰጠኝ አካል የለም ሰማይ ዝም አለ መንፈሴ ሰላም አጠች ነብሴ ተጨናቃች በዚህ ሰአት ከእኔ ከጤነኛ ሀረግ ህመምተኛው እሱ ይሻላል ለመሞት ከተዘጋጀው ከእሱ ይልቅ እኔ ተስፋ ቆረጥኩኝ ተመልሼ እና እዩኤል ቤት ሄድኩኝ በጣም ጤነኛ ሰው ይመስላል፣ ፍቅር መጣሽ አሁን እኮ በጣም ደህና ነኝ ደብሮኝ ነበረ እንኳን መጠሽ ብሎ መጫወት ጀመረ ዋውውውው በጣም ደስ አለኝ በልቤ ዶክተሩ ውሸታም ነው አልኩት ትንሽ አብረን ከተጫዋተን በኋላ እዩኤል ከአፉ ደም መትፈት ጀመረ
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @Menta_lbochh_bot
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
ለ ቅምሻ
አንዲት በተራራ ላይ ስትጓዝ የነበረች ጠንካራ ሴት
ከአንድ ፏፏቴ ዳርቻ ላይ ውድ ድንጋይ አገኘችና በቦርሳዋ
ውስጥ አኖረችው። በቀጣዩ ቀን ስትጓዝ ሌላ የተራበ ተጓዥ
በመንገዷ ላይ አገኘች። ብርቱዋ ሴትዮ ያላትን ለማካፈል
ቦርሳዋን ከፈተችው
የተራበው ሰው ውዱን ድንጋይ በቦርሳዋ ውስጥ እንዳለ
ሲመለከት እንድትሰጠው ይጠይቃታል ሴትየዋም ያለምንም
ማመንታት ሰጠችው። ተጓዡ ሰውዬ በገጠመው መልካም
አጋጣሚ በደስታ ሰክሮ ጉዞውን ቀጠለ። ድንጋዩ በህይወቱ
ሙሉ ሊያኖረው የሚችል በቂ ሀብት እንደሚሆነው አውቆ ነበር።
ከጥቂት ቀናት በኋላ ግን ሰውዬው ለዚያች ደግ ሴት
ድንጋዩን ሊመልስላት መጣ።
አንድ ነገር ሳስብ ነበር
የከረምኩት አለ ። ድንጋዩ ውድና ትልቅ ዋጋ ያለው መሆኑን
ባውቅም ከዚህ የበለጠ ውድ ነገር ትሰጭኛለሽ ብዬ በማመን
ልመልስልሽ መጥቻለሁ እንድትሰጪኝ ፈልጌ የመጣሁትም
ድንጋዩን እንድትሰጪኝ ያነሳሳሽን ውስጥሽ ያለውን
የመልካምነት ምስጢር ነው። አላት
.............
ሕልምህ እውን የሚሆነው ውስጥህ
የሚገኘውን ነገር መመልከት ስትችል ብቻ ነው
ውጪውን ከማያየውና ከማያልመው ሰው
ይልቅ ወደ ውስጡ የሚመለከት እሱ ይነቃል
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @menta_lboch
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
❣❣መልካሙ ዶክተር❣❣
❤️❤️ክፍል ሰባት❤️❤️
ዛሬ ከዶክተሩ ጋር ቀጠሮ አለን፣ የእዩኤልን የምርመራ ውጤት ለመንገር ሃኪም ቤት ቀጥሮኛል ምን ይፈጠር ይሆን?
ክፍል ገብቼ ሰላም ብዬ ቁጭ አልኩኝ ዶክተር እንዴት ነህ አልኩት እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ አለኝ ታድያ እንዴት ነው የእዩኤል የምርመራ ውጤት ብዬ አይን አይኑን ማየት ጀመርኩኝ ፊቱ ላይ ጥሩ ስሜት አይታይም የሆነ ለመንገር የፈለገው ነገር ያለ ይመስላል ግን መናገር አልቻለም ዶክተር ምነው ሰላም አይደለህም? አይይይ ደህና ነኝ ታድያ ምነው? ጥያቄውን እኮ አልመለስክም አልኩት ሀረግ ትንሽ ጭንቅ ብሎኛል ሌላ ጊዜ ማውራት እንችላለን ወይ ብሎ ጠየቀኝ ምነው ዶክተር የእዩኤል ነገር ነው አይደል እባክህን እውነቱን ንገረኝ እውነቱን ማወቅ እፈልጋለሁ አልኩት አንቺ ደግሞ ሁሉንም ነገር በቃ ከእዩኤል ጋር ማገናኘት ትወጃለሽ ባይሆን ሻይ ቡና ማለት እንችላለን? ብሎ ጠየቀኝ እሺ ግን በእናትህ እዩኤልን ማጣት አልፈልግም ብቻ የሆነ ነገር አድርግልኝ አልኩት በሰው ህይወት ላይ ሁሉንም የማድረግ አቅም ያለው ፈጣሪ ብቻ ነው እንጂ ሰው ምንም ማድረግ አይችልም፣ አይዞሽ ሊሆን ያለው ነገር ሁሉ ይሆናል ብሎ ወደ አንድ ካፌ ይዞኝ ሄደ የኔ ትግል ሁሉ ስለ እዩኤል የምርመራ ውጤት ማወቅ ቢሆንም ዶክተሩ ግን ጨዋታ እየቀየረ የምርመራውን ውጤት ለመንገር ፍቃደኛ አለመሆኑን በግልጽ እያሳየ ነው። እንቆቅልሽ የሆነብኝ ነገር ቢኖር የዶክተሩ አዲሱ ፀባይ ነው በልቤ ውስጥ ብዙ ጥያቄዎች ቢኖሩም ዶክተሩን ግን ከዚህ በላይ ማስገደድ አልቻልኩም ግን ልቤ አሁንም ፍርሃት ፍርሃት ይለኛል የሆነ ችግር እንዳለ ይገባኛል ግን ምንም የማድረግ አቅም የለኝም። ቤት መጥቼ ቤት ውስጥ ብቻዬን ማልቀስ ጀመርኩኝ
እዩኤል ጋር አጠገቡ ቁጭ ብዬ የእሱን ስቃይ ከማየት ሌላ ቦታ ለብቻ መኖር ሁሉ ሳይሻል አይቀርም በሩን ዘግቼ መኝታ ክፍል ውስጥ ብቻዬን ቁጭ ብዬ ሳለቅስ ህይወቴን ከጎዳና ላይ አንስታ አዲስ የህይወት ምዕራፍ እንድጀምር የረዳችኝ እናት በሩን ማንኳኳት ጀመረች እማማ ለጥቂት ጊዜ ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ አልኳቸው ተይ እንጂ ልጄ እንደዚህ አትሁኚ የሆንሽውን ነገር ንገሪኝ አሉኝ እማማ ምንም አልሆንኩም በቃ ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ አልኳቸው ልጄ መቼም በስጋ እናትሽ ባልሆንም እኔ ግን በዚህች በጥቂት ወራት ውስጥ በክፉ አጋጣሚ ያጣውትን ልጄን መልሼ ያገኘው ነበረ የመሰለኝ አንቺ ግን የሌላ ሰው ልጅ መሆንሽን ነው የነገርሽኝ ብለው ሊሄዱ ሲሉ... በፍጥነት በሩን ከፍቼ ወጥቼ እምባ ማፍሰስ ጀመርኩኝ... እማማ እኔ እኮ የእናቴን ማንነት አላውቅም ለእኔ ከእርሶ ሌላ እናት የለኝም እናት ማለት ለኔ መውለድ ማለት ብቻ አይደለም ትክክለኛ እናት ከሆዷ ለወጣ ልጅ ብቻ ሳይሆን ለየትኛውም ልጅ የሚያዝን ልብ ያላት እናት ናት ስለዚህ እኔ እናት የለኝም አልልም እናቴ እርሶ ኖት አልኳቸው ታድያ ለምን የሆንሽውን አትነግሪኝም ከእናት የሚደበቅ ነገር እኮ የለም አሉኝ በቃ እማማ ጓደኛዬ ሊሞት ነው አልኳቸው በጣም ድብቅ ነሽ ማለት ነው በቃ አሁን አንቺ አታልቅሽ የትም የትም ብለን ይድናል አሉኝ እማማ አመሰግናለሁ ብዬ ቶሎ ብዬ ወደ ዶክተሩ ሄድኩኝ ከዛም የሆነውን ነገር ሁሉ ነገርኩት እሱ ግን ምንም ደስ አላለውም ምነው ዶክተር ደስ አላለህም? እዩኤል እኮ ሊድንልኝ ነው አልኩት እግዚአብሔር ቢያደርግልሽ ደስ ይለኛል አለኝ ማለት? አልገባኝም ሀረግ ያልናገርኩሽ ነገር አለ አለኝ እኮ ምንድነው ዶክተር? ንገረኛ አልኩት ምን መሰለሽ ሀረግ...
ክፍል➑ ይቀጥላል
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @menta_lboch
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
😷መ ል ካ ሙ ዶ ክ ተ ር😷
❣❣ክፍል ስድስት❣❣
ለምንድነው ግን ህይወቴ እንደዚህ በመልካም ሰዎች ጥላ ስር የምትኖረው? እግዚአብሔር አንዱን ሲነጥቅ ሌላውን አዘጋጅቶ ነው ማለት ነው? የእዩኤል ህመም ከቀን ወደ ቀን እየባሰ እየመጣ ነው እናቱ ግን ከበፊቱ አሁን በትንሽም ቢሆን መንቀሳቀስ ጀምረዋሉ ዶክተሩም ክትትል ማድረጉን አላቆመም እንደውም በራሱ ብር ከሌላ ሃኪም ቤቶችም ጭምር መድሃኒት ገዝቶ እየመጣ ነው፣ ግን ምን አይነት መልካም ሰው ነው? ብዙም ጊዜ ሰዎች መልካም ነገሮችን የሚያደርጉት ለዘመድ አልያም ጥሩ ግኑኝነት ላላቸው ሰው ብቻ ነው እንጂ እንደ ዶክተሩ ምንም ለማያውቁት ሰው መልካምነትን የሚያደርጉት ከመቶ ምናልባትም ቢኖሩ ሁለት ወይንም ሦስት ሰዎች ብቻ ናቸው። እዩኤል አንድ ሰሞን ጤነኛ ይሆናል ግን ወዲያውኑ ተመልሶ የባሰ ለሞት ሁሉ የቀረበ በሽተኛ ይሆናል የምትወደው ሰው ችግር ውስጥ ነው ማለት ደግሞ ከሰውነትህ አንዱ አካል ላይ ትልቅ ቁስል እንደመኖር ማለት ነው ሰውነትህ ላይ ትልቅ ቁስል ሲኖር ለአንድ ቦታ ብቻ ህመም አይሰማህም ለሁሉም የሰውነትህ ክፍል እንጂ! የምትወደው ሰው ችግር ውስጥ ነው ማለትም ልክ እንዲሁ ነው ቁስሉ የአንድ ሰው ብቻ ሳይሆን ቁስሉ ሁለቱንም የመጉዳት አቅም አለው በህመም ምክንያት ይበልጥ እየተጎዳ ያለው እዩኤል ቢሆንም ህመሙ ግን ከእሱም አልፎ የኔንንም ደስታ መንጠቅ አልተወም፣ በቃ ደስተኛ መሆን አልቻልኩም ሁሌም ሀዘን ሁሌም እምባ ብቻ እዩኤል እንደዚህ ሆኖ ማየት በራሱ ራሱን የቻለ ትልቅ ህመም ነው አይዞሽ ሀረግ በእኔ ምክንያት አንቺም ተጨናነቅሽ አይደል አይዞሽ ፍቅር ለሁሉም ቀን አለ ቀን የማይለውጠው ነገር የለም እኛም አንድ ቀን ሙሉ ሰው እንሆናለን ግን ምንጊዜም ተስፋ አትቁረጪ ብሎ እኔን ለማጽናናት የማይናገረው ነገር የለም የኔ ጥያቄ ግን መቼ? የሚለው ነው ህይወቴን በሙሉ አንድ ቀን አንድ ቀን እያልኩ ለመኖር ለአንዲት ምስኪን ልጅ ተስፋ የሚባል ቀልድ ምን ያደርጋል? የተስፋ ትርጉም ያልገባቸው እንደ እኔ አይነቱ ስንት ሰዎች ይኖሩ ይሆን? ተስፋ ማለት ጭላንጭል አይተው የሚጠብቁት ነገር የሚመስላቸው ተስፋ ማለት ደመና አይተው ይዘንባል ብሎ መጠበቅ የሚመስላቸው ምስኪኖች ተስፋ ማለት ግን ምንም ጭላንጭል የሌለበትን ነገር በእምነት መጠበቅ ማለት ነው ምንም ጭላንጭል የሌላውን ነገር መጠበቅ ደግሞ በጣም ከባድ ነው ለዚህም ነው ሰዎች አንድን ነገር ተስፋ አድርገው እስከመጨረሻው በእምነት ጸንተው መጠበቅ የማይችሉት ለትንሽ ጊዜ ጠብቀው ጭላንጭል ሲያጡ ተስፋ ቆርጠው ወደኋላ ተመልሰው የሚወድቁት እኔ እንደሆንኩ መጀመርያውኑ ብሩህ ተስፋ የለኝም ገና ከአሁኑ ሽንፈት ሽንፈት እያለኝ ነው ቀድሞ የሽንፈት ጽዋ መቅመስ ደግሞ ሞት ነው! ዛሬ ከዶክተሩ ጋር ቀጠሮ አለን ዛሬ የእዩኤልን ሙሉ የምርመራ ውጤት ለመንገር ሃኪም ቤት ቀጥሮኛል ምን ይፈጠር ይሆን? . . . . .
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @menta_lboch
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
ስወድሽ ውደጂኝ😍
ውዴ.....
እኔ አንቺን መውደዴ
መጥፎ እድል አይደለም ችግር የሚያመጣ
ወንጀልም አይደለም በህግ የሚያስቀጣ
ሀጢያትም አይደለም አንገት የሚያስደፋ
ሰማይ ቤት አትቆምም ነብሴ ተጠይቃ-ትዕዛዝ ተላልፋ
ታድያ አንቺን መውደዴ ምን ላይ ነው ጥፋቱ?
ወደድኩሽ ማለቴስ ምንድነዉ ክፋቱ?
ጠልተሺኝ እንዳይሆን ቁርጡን እንዳላውቀው
እንደምትወጂኝ ነው ውስጥሽ 'ሚያሳብቀው።
ታድያ እየተዋደድን አንድ ሆኖ ውስጣችን
ለምን እንራራቅ እንሁን ለብቻችን
ስለዚህ ውድዬ.......
ባንቺ ጨርቅ ሳልጥል ወይ ሳታሳብጂኝ
በፍፁም ተማምነን ሳልከዳሽ ሳትከጂኝ
-- ሳልጎዳሽ ሳትጎጂኝ
መራራቁን ትተሽ ስወድሽ ውደጂኝ
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @menta_lboch
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
😷መ ል ካ ሙ ዶ ክ ተ ር😷
👑ክፍል አ ም ስ ት👑
┄┄┉┉✽»🌹✿🌹»✽┉┉┄┄
ቆይ ለምን እንደዚህ አናደርግም አለኝ እንዴት አልኩት እእእእ በብር ምክንያት ማንም ሰው መሞት የለበትም ስለዚህ በቻልኩ መጠን ቤት እየመጣሁ እኔ ክትትል አደርጋለሁ ምናልባት አንድ ቀን ጤናማ ህይወት መኖር ሲጀምር ሰርቶ መክፈል ይችላል፣ ክሊኒኩ የራሴ ስለሆነ ልጁን ለመርዳት እፈልጋለሁ አለኝ ዋውውውው በጊዜው የተሰማኝን ደስታ ልነገራችሁ አልችልም ዶክተር ከልብ አመሰግናለሁ በጣም ጨንቆኝ ነበረ እግዚአብሔር አብዝቶ ይስጥህ በእውነት መልካም ሰው ነህ ብዬ አመስግኜ እዩኤልን ወደ ቤት ይዤው መጣሁ። እናቱ ቤት ውስጥ በጭንቅ ተውጠው ቁጭ ብለው ነበር... ይህች አለም እንደዚህ ናት ምንም ፍትሕ የሚባል ነገር አታውቅም! ዛሬ የአንተ ጭንቅ ምናልባት ብር ማጣት ሊሆን ይችላል ዛሬ የአንተ ጭንቅ ጣፋጭ ምግብ ማጣት ሊሆን ይችላል ዛሬ የአንተ ጭንቅ ምናልባት ጥሩ ልብስ አለመኖር ሊሆን ይችላል ዛሬ የአንተ ጭንቅ ምናልባት ጥሩ አልጋ ላይ አለመተኛት ሊሆን ይችላል ዛሬ የአንተ ጭንቅ ምናልባት ከጓደኞችህ የበታች ሆኖ መታየት ሊሆን ይችላል ግን አንድ ቀን ፈጣሪ ለአንተ የሰጠህን ነጻ ስጦታዎች ዞር ብለህ ለማየት አይንህን ብከፈት እርግጠኛ ነኝ በህይወትህ ደስተኛ መሆን ትጀምራለህ። እንግዲህ አስቡ በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ ሁለቱም ሰዎች የአልጋ ቁረኛ መሆን ምንያህል ከባድ ነገር እንደሆነ እግዚአብሔር ከእንደዚህ አይነት የህይወት ፈተና ይሰውራችሁ እንደዚህ አይነት አጋጣሚ በጣም ከባድ ፈተና ነው ዛሬ አንተ በሰላም እየኖርክ ትርፍ ስለሆነ ነገር ትጨናቀለህ እባክህ የኔ ወንድም/እህት ጓደኛቼ እኔ እንዲሁ እያለሁ መኪና ያዙ ከማለትህ በፊት ጓደኞቼ እኔ እንዲሁ እያለሁ ሀብታም ሆኑ ከማለትህ በፊት ጓደኞቼ እኔ እንዲሁ እያለሁ ትልቅ ቦታ ደረሱ ከማለትህ በፊት . . . እኔ በሰላም እየኖርኩ ጓደኞቼ ግን ሰላም የላቸውም ለእኔ ቤተሰብ አለኝ ለጓደኞቼ ግን ቤተሰብ የላቸውም እኔ በህይወት አለው ጓደኞቼ ግን በህይወት የሉም የሚለውን ነገር ማሰቡን አትርሳ በዚህ አለም ላይ የህይወት ደረጃ የሚባል ነገር አለ አንድን ሰው መብለጥ የምትችለው በጥቂት ጎኖች ብቻ ነው እሱ ደግሞ በሌላ መንገድ ይበልጥሃል ወደድክም ጠላህም አንድን ሰው በሁሉ መብለጥ አትችልም አንተ አዋቂ ሀብታም ብትሆን ምናልባት እሱ ቆንጆ ደስተኛ ሊሆን ይችላል አንተ ውብ ቆንጆ ተወዳጅ ብትሆን ምናልባት እሱ ከአንተ የተሻለ ትዳር መስርቶ የሚኖር ሊሆን ይችላል አንተ ዲግሪ ላይ ዲግሪ ቢኖርክ እሱ በተፈጥሮ ከአንተ ይልቅ አስተዋይ ህይወቱን በትክክል መምራት የሚችል ሊሆን ይችላል በቃ ህይወት እንደዚህ ናት ይሄን ሁሉ መንገድ የመጣውት ደስተኛ ለመሆን ከእናንተ የበላይ የሆኑትን ብቻ ሳይሆን የበታች የሆኑትንም ተመልተኩ ለማለት ያህል ነው። እኔ ከብዙ ሰዎች የተሻልኩ እንደሆንኩ ያወኩት እዩኤል እና እናቱ ምንም አይነት የገቢ ምንጭ ሳይኖራቸው ሁለቱም በህመም ተገደው ቤት ውስጥ ሞትን እየጠበቁ በማየቴ ነው ፈጣሪ አብዝቶ ይስጠው መልካሙ ዶክተር ክትትል ብቻ ሳይሆን ምግብ ሳይቀር እርዳታ እያደረገ ነው ለምንድነው ግን ህይወቴ እንደዚህ በመልካም ሰዎች ጥላ ስር ገብታ የምትኖረው? ፈጣሪ አንዱን ሲነጥቅ ሌላውን አዘጋጅቶ ነው ማለት ነው? . . . . . .
ይቀጥላል ክፍል ❻
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @menta_lboch
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
❤️መልካሙ ዶክተር❤️
🌹🌹ክፍል አ ራ ት🌹🌹
ማነው ብዬ ሄጄ በሩን ስከፍት.. እዩኤል? እንዴት መጣህ አልኩት እእእእእእ ታምራት የለም አለኝ ታምራት ታምራት? ማነው ደግሞ ታምራት አልኩት ኦኦኦኦኦ ለካ ቤት ተሳስቼ ነው የመጣሁት ብሎ በተረፈ እንዴት ነሽ አለኝ ደህና ነኝ አልኩት እንዲህ እንዲህ እያለን ከእዩኤል ጋር ጥሩ ጓደኛሞች ሆንን.. ቤት ተሳስቼ ነው የመጣውት ያለኝ ቀን ለካ ውሸቱን ነው ሱቅ የተገናኘን ቀን ተከትሎኝ መጥቶ ነው ቤቱን አይቶ ተመልሶ የሄደው እዩኤል በጣም የዋሀ መልካም ልጅ ነው በጓደኝነት ብዙ መቆየት አልቻልንም ጓደኝታችን ቶሎ ወደ ፍቅር ተቀየረ... የእዩኤል እናት በህመም መሰቃየት ከጀመሩ ብዙ አመታትን አስቆጥረዋሉ የእናቱን ሙሉ ኃላፊነት ከልጅነቱ ጀምሮ በእጁ ላይ ይዞ ያደገ ምስኪን ልጅ ነው ህይወቱ ከእኔ ህይወት ጋር ብዙ ተመሳሳይ ነገሮች ያሉት እዩኤል ከራሱ እድገት አንጻር ለኔ ያለው ክብር እጅግ በጣም ደስ ይለኛል አንድአንድ ጊዜ የልቤን ሃሳብ ሁሉ የሚያውቅ ይመስለኛል እኔም ህይወቴን ከመንገድ ላይ አንስተው ዛሬ እንደዚህ በደስታ እንድኖር ካደረጉኝ እናቴ ጋር አብሬ በደስታ እየኖርኩኝ ነው ለዚህች ምስኪን እናት ልጅ ይሁን ዘመድ የሚባል ነገር የላቸውም አሁን ግን እሳቸውም ልጅ እኔም እናት አግኝተን በደስታ እየኖርን ነው። እዩኤል አልፎ አልፎ ልክ እንደ እናቱ ሁሉ በህመም እየተሰቃየ ነው ጥሩ ሃኪም ቤት ሄደው ጥሩ ህክምና የማግኘት እድል ግን አልነበረውም፣ አንድ ቀን ቤት ውስጥ ቁጭ ብዬ ቴሌቭዥን በማየት ላይ እያለሁ ስልክ ተደወለልኝ የእዩኤል ስልክ ነው እኔም በደስታ ሀይ ፍቅር አልኩት እዩኤል አይደለም እናቱ ነኝ ቶሎ ብለሽ ድረሽ ታውቂያለሽ እኔ እንደሆንኩ አቅም የለኝም አሉኝ እማማ እዩኤል ምን ሆነ ስላቸው አሁን ጥያቄው ምንም አያደርግም ቶሎ ብለሽ ቤት ነይ አሉኝ እኔም በፍጥነት ቤታቸው ሄድኩኝ፣ እዩኤል እራሱን ስቶ ወድቆ ነበረ.... ቶሎ ብዬ ታክሲ ጠርቼ ወደ ሃኪም ቤት ወሰድኩት ከብዙ የፀጥታ ሰአታት በኋላ እዩኤል በድጋሚ ማውራት ጀመረ... እዚህ አለም ላይ አለኝ የምለው እዩኤል እንደዚህ ሆኖ ከማየት በላይ ተስፋ የሚያስቆርጥ ነገር ምን አለ? ሀረግ አሁን እኮ ደህና ነኝ ይላል የሆዱን በሆዱ ይዞት ሁሉም ሰው የፍቅረኛውን ደስታ ይፈልጋል አይደል እሱም ለኔ ደስታ ብሎ ህመሙን ቀላል ለማድረግ እየሞከረ ነው ህመሙ በጣም ከባድ እንደሆነ ግን ሃኪሙ ነግሮኛል ዛሬ መልካሙን ዶክተር የተገናኘውበት ቀን ናት ለህክምናው የጠየቀኝ ብር በጣም ብዙ ብር ነው በኪሴ ውስጥ የነበረኝ ብር ደግሞ በጣም ጥቂት ብር ነው ይቅርታ አድርግልኝ ለጊዜው ሙሉ ብር የለኝም ልጁ እዚሁ ይቀመጥ እኔ ብሩን ይዤ እመጣለሁ አልኩት አይይይይ ችግር የለም ባይሆን ልጁ ክትትል ይፈልጋል ክትትል የሚያደርግለት ዶክተር ያስፈልጋል አለኝ አይይይ ዶክተር ክትትል ነው ያልከኝ? አይደለም ክትትል ለሚያደርግ ዶክተር እንደዚህ እራሱን ስቶ ወድቆ ህክምና ለማግኘት ብር እንኩዋን አጥተን እንዴት እንደሆንኩ እያየህ እንደዚህ ትላለህ አልኩት ቆይ ለምን እንደዚህ አናደርግም አለኝ እንዴት አልኩት እእእእ....
ይቀጥላል ..........
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @menta_lboch
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
😍በፍቅር ተጀምሮ በሀዘን
የሚያልቅ ሳይሆን በፍቅር ተጀምሮ
በፍቅር የሚያልቅ ፍቅር ይስጠን🙏
አሜን ሳይል ማንም እንያልፍ😉😜
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @Menta_lbochh_bot
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
💉መልካሙ ዶክተር💉
🎈ክፍል ሶስት🎈
ምግቡን ጨርሼ እማማ አመሰግናለሁ ብዬ ልሄድ ስል.. ልጄ የበሉበትን እቃ ማጠብ የጨዋ ሰው ተግባር ነው እቃውን ብታጥቢ ደስ ይለኛል አሉ እማማ ኧረ ችግር የለም እርስዎ ምግብ ሰጥተውኝ እኔ እቃ ማጠብ እንዴት ያቅተኛል እንደውም ቤት ውስጥ ያሉትን በሙሉ አምጡ አልኳቸው ተባረኪ ልጄ ብለው ትንሽ እቃ አምጥተው ሰጡኝ እኔም እቃውን ማጠብ ጀመርኩኝ...
እቃውን ጨርሼ ልሄድ ስል ልጄ አሁን ፀሐዩ በጣም ከባድ ነው ፀሐይ ትንሽ በረድ እስኪል ቁጭ ብለሽ ቴሌቭዥን መመልከት ትችያለሽ አሉኝ የዚህች መልካም እናት ሁኔታ ትንሽ ቢገርመኝም ቁጭ ብዬ ቴሌቭዥን ማየት ጀመርኩኝ በዚህ መሃል ከተቀመጡበት ተነስተው ቡና ማፍላት ጀመሩ...
ይህ ሁሉ ክብር ለኔ? ምን የሚሉት ነገር ነው? ቡናው ተፈልቶ ደረሰ በዚህ ሁሉ ሰዓታት ተጫወቺ ከማለት ውጭ ምንም ጥያቄ እየጠየቁኝ አይደለም እኔ ደግሞ ጥያቄ የማይጠይቅ ሰው ስወድ! በቃ ቤተሰብ ቤት ምናምን ስለሌለኝ ስለ ኑሮ ስለ ቤተሰብ ታሪክ ምናምን የሚጠይቁኝ ሰዎች ያስጠሉኛል፣ ነገር ግን እሳቸውን ለመጠየቅ ምክንያት የሆነኝ ነገር ቡናው ነበረ... እማማ ለምን ቤተሰብ እስኪመጣ ትንሽ አንጠብቅም አልኳቸው ትንሽ ከሳቁ በኋላ ቤተሰብ ነው ያልሽው? ብለው ጠየቁኝ እኔም አዎ ቤተሰብ ባይኖረኝም ቡና ከቤተሰብ ጋር ሲሆን ደስ ይላል ብዬ ነው አልኳቸው አይይይይ ልጄ የሉም አሉኝ አይመጡም ለማለት መስሎኝ ዝም አልኩኝ አብረን ቡናውን ጠጥተን በድጋሚ ለመሄድ ተነሳሁ ትልቅ ቀጠሮ ያለኝ ሰው አልመስልም? ልጄ ገበያ ለመሄድ አስቤ ነበረ ግን አቅም አጣሁ ብለው ዝም አሉ ታዲያ የሚልኩት ሰው የለም? በዚህ ጊዜ ሰው ከየት ይመጣል ብለሽ ነው የምትሄጅበት ከሌለ ለምን አንቺ ሮጥ ብለሽ አትመጪም አሉኝ ማን? እኔ ገበያ? እኔ እቃውን እንዴት ገዝቼ እንደሚመጣ እንኩዋን አላውቅም አልኳቸው በልቤ ደግሞ ለኔ ብር ሰጥቶ መላክ ውሻ ላይ አጥንት እንደመላክ ነው እስከአሁን ዝም ያልኩት ራሱ ምስኪን ስለሆንሽ ነው እንጂ ሌላ ሰው ቤት ገብቼ ቢሆን ኖሮ መቼ ምን ይዤ እንደወጣሁ ማወቅ አትችይም እያልኩ ሴትዮዋን በአግርሞት ማየቱን ቀጠልኩኝ... ቀላል እኮ ነው ልጄ ሮጥ ብለሽ ደርሰሽ ነይ ብለው 300ብር ሰጡኝ እኔም ብሩን ይዤ ከቤት ወጣሁኝ.... ልክ ከቤት እንደወጣሁ አእምሮዬ ላይ ብዙ ሃሳቦች መምጣት ጀምሩ፣ አንዴ ብሩን ይዤ ዛሬ ዘና ማለት አለብኝ የሚል ሃሳብ ነው ሌላኛው ልቤ ደግሞ ከዚህች ምስኪን እናት ብር ይዞ መጥፋት ከክህደት ሁሉ ትልቁ ክህደት ነው እያለ መውቀስ ጀመረ ቆይ እሺ በዚህ 300ብር እቃ ገዝቼ ስሄድ ትንሽ ብር ብቻ ብሰጠኝስ ብዬም ሐሳብ ውስጥ ገባሁ ልቤ ግን አሁንም ምንም ባይሰጡሽ እንኩዋን እቃውን ገዝተሽ መሄድ አለብሽ ብሎ ትእዛዝ ሰጠኝ እኔም የልቤን ትእዛዝ ተቀብዬ እቃውን ገዝቼ ወደ ቤታቸው ተመለስኩኝ ተመልሼ በመምጣቴ ደስታ ብቻ ሳይሆን ግራ የተጋቡ የሚመስሉት እናት እንዴት መጣሽ? እእእእ ማለቴ ቶሎ መጣሽ ቤት ገብተሽ ቁጭ በይ አሉኝ አይይይ አሁን እሄዳለሁ አልኳቸው ለምን? የት? ብለው ተጣድፈው ከተናገሩ በኋላ ግን አንድ ሁለት ቀን እዚህ ብትቀመጪ ደስ ይለኛል ብለው በትህትና ተናገሩ ኧረ ማዙካ አግኝቼ ነው ሲጀመር እኔ ምን መሄጃ አለኝ በደስታ ነው ቁጭ የምለው ብዬ ቁጭ አልኩኝ ለምሳ ብዬ የገባሁት ቤት የአራት ወር መኖርያ ቤት ሆኖ አገኘሁት። ከአራት ወር በኃላ ሱቅ ተልኬ ስሄድ በአጋጣሚ የሆነ ልጅ መጥቶ ሀይ ሀረግ ብሎ ሰላም አለኝ ሀረግ? እዚህ ሰፈር የኔን ስም ማንም አያውቅም እሱ እንዴት አወቀ እያልኩ ትንሽ በዝምታ ተዋጥኩኝ ምነው ሀረግ አላስታወሽኝም እንዴ? እዩኤል እኮ ነኝ ከጥቂት ወራት በፊት ከመንገድ ላይ አንስተሽ ሃኪም ቤት የወሰድሺኝ ልጅ ብሎ በድጋሚ ሰላም አለኝ ይቅርታ ወንድም ልቤ ሌላ ቦታ ስለነበረ ነው ታዲያ አሁን እንዴት ነህ አልኩት እግዚአብሔር ይመስገን አሁን ደህና ነኝ፣ ሻይ ቡና ማለት እንችላለን ብሎ ጠየቀኝ አሁን አልችልም ተልኬ ነው የመጣውት አልኩት እና እዚህ ሰፈር ነሽ ማለት ነዋ አለኝ አዎ እዚህ ሰፈር ነኝ አልኩት እኔም እኮ እዚሁ ሰፈር ነኝ አለኝ በቃ ቻው ብዬ ወደ ቤት መጣሁኝ ገበያ ተልኬ ታማኝ በመሆኔ አራት ወር በሙሉ ቁርስ ምሳ እራት ጠግቤ መብላት ጀመርኩኝ ጥሩ አልጋ ላይ ተኝቼ ማደር ጀመርኩኝ ጥሩ ልብስ መልበስ ጀመርኩኝ እነዚህ አሁን ያልኩት ነገሮች ታማኝ በመሆኔ ካገኘውት ነገሮች ጥቂቶቹ ናቸው። ከቀኑ ስድስት ሰአት አካባቢ የግቢው በር ተንኳኳ... እኔ እዚህ ቤት ከገባሁበት ቀን እስከዛሬ እዚህ ቤት ሰው መጥቶ አያውቅም ምስኪኗ እናት ደግሞ ቤት ውስጥ ናት ማነው ብዬ በር ለመክፈት ሄድኩኝ በሩን ስከፍት..
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @Menta_lbochh_bot
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
😍😍መልካሙ ዶክተር😍😍
🌺🌺ክፍል ሁለት🌺🌺
ሃኪም ቤት የካርድ ብር አጥቼ ወዲህ ወዲያ ስል አንዲት
መልካም እናት ልጄ ሰው ጠፍቶብሽ ነው ወይ ብለው ጠየቁኝ እኔም የሆነውን ነገር ሁሉ በትህትና ነገርኳቸው፣ እርሳቸውም አይዞሽ ልጄ አንቺ መልካም ልጅ ነሽ የካርዱን ብር እኔ እሰጣችኋለሁ ግን የህክምና ብር አለሽ ወይ ብለው ጠየቁኝ
ማዘር እኔጋ ምንም ብር የለም ምናልባትም ልጁ ቀድሞ
እራሱን ቢያውቅ ስልክ ቁጥር ተቀብለን ለቤተሰቦቹ መደወል
እንችል ነበረ አልኳቸው
መልካም ብለው እርሳቸውም ከእኔ ጋር አብረው የልጁን ሁኔታ
ለማየት ቁጭ አሉ
ዶክተሩ የመጀመሪያ እርዳታ ከሰጠ በኋላ ለጊዜው ብዙ
አሳሳቢ ችግር እንደሌለበት ነገር ግን እራሱን ከጭንቀት ነጻ
ማድረግ እንዳለበት ነግሮት አንድአንድ መድሃኒቶችን ሰጥቶ
ትንሽ ብር ሲጠይቅ እኔ ቶሎ ብዬ ቤተሰብ ጋር ልደውል ስልክ
ቁጥር ስጠኝ አልኩት
ከዝምታ ሌላ ምንም መልስ መስጠት አልቻለም
በዚህን ጊዜ ከልጁ ዝምታ የሆነ ነገር መረዳት የቻሉት እናት
ከቦርሳ ውስጥ አውጥተው ሃኪሙ የጠየቀውን ብር ሰጡ
በጣም ደስ አለኝ ግን ምን አይነት መልካም እናት ናቸው?
ከዛም ልጄ እኔ አሁን ወደ ቤት ልሄድ ነው እናንተም ወደ
ቤታችሁ ተመለሱ ይሄ የታክሲ ብር ነው ብለው ብዙ ብር ሊሰጡ
ሲሉ እማማ እኔ ምን ቤት አለኝ ብለው ነው ለኔ የሄድኩበት ሁሉ
ቤቴ ነው የትም ሰፈር ብሄድ መኖር እችላለሁ ብሩን ለሱ
ስጡት አልኳቸው ልጄ ምን እያልሽ ነው ቤት የለኝም ማለት ምን ማለት ነው?
ቤተሰብ አለሽ አይደል ብሎ ጠየቁኝ እማማ ለካ እርስዎም ቀልደኛ ኖት ቤተሰብ ቢኖረኝ ይሄን
እመስላለሁ ብዬ ጥዬ ልሄድ ሲል ታዲያ ወዴት ነሽ ብለው ጠየቁኝ
ወዴት ነኝ? እኔን ከየት ነሽ ብሎ እንጂ ወዴት ነሽ ብሎ ሰው
ጠይቆ አያውቅም ምክንያቱም እኔ እግሬ ወደ መራኝ መሄድ
እንጂ እዛ እሄዳለሁ ብዬ መንገድ አልጀምርም አልኳቸው
ታዲያ ለምን ዛሬ ከእኔ ጋር አትሄጅም አሉኝ ቡሌ ይስጡኝ እንጂ የትም እሄዳለሁ አልኳቸው
ቡሌ ደግሞ ምንድነው ሲሉኝ
እማማ ምሳ አልበላሁም አልኳቸው
ልጁን አንተስ አትሄድም አሉት
እማማ እርሶ በጣም መልካም እናት ኖት ስለ ሁሉም ነገር
በጣም አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ያክብሮት እኔ አሁን ቤት መሄድ እፈልጋለሁ እናቴ ትጠብቀኛለች ብሎ ልሄድ ሲል
ታዲያ ምስጋናው እኮ ከእኔ በላይ አጠገብህ ለቆመች ልጅቷ
ነው መሆን ያለበት እሷ እኮ ናት ከመንገድ ላይ አንስታ ሃኪም
ቤት የወሰደችህ አሉት
እሱም ወደ እኔ መጥቶ በመጀመሪያ ይቅርታ አድርግልኝ
ሃኪም ቤት የወሰድሽኝ አንቺ እንደሆንሽ አላወኩም ነበረ
በመቀጠል ደግሞ በጣም አመሰግናለሁ ስሜ እዩኤል ነው
ብሎ እጄን ጨበጠ
እኔም ሀረግ አልኩትና ለትንሽ ሴኬንዶች ሁለታችንም ፍዝዝ
ብለን ቀረን
በዚህ መሃል በይ አሁን እንሂድ እሱም ወደቤት ይሂድ ብሎ
እኔን ወደቤታቸው ይዘውኝ ሄዱ
ቤታቸው ደረስን፣ ቤት ውስጥ ለጊዜው ሌላ ሰው አልነበረም
ልክ ቤት እንደገባን የእጅ ውሃ ሰጥተውኝ ተሰርቶ ከተቀመጠው ምግብ አምጥተው ሰጡኝ
እኔም ተገኘ ብዬ ልጀምር ስል ቆይ ልጄ ምግብ ከመብላትሽ በፊት የሰጠሽን አምላክ ማመስገን አለብሽ ብለው አመስግነው
ሰጡኝ ምግቡን ግማሽ ካደረኩ በኋላ የእሳቸው ነገር ትዝ አለኝ
እማማ እርስዎ አይበሉም አልኳቸው እሺ መጣሁ አሉና ሌላ ምግብ አምጥተው ጨምረው ከእኔጋ አብሮ መብላት ጀመሩ
ይህች ቀን በህይወቴ ዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰዎች ክብር
የሰጡኝ ቀን ነበራች
ምግቡን ጨርሼ እማማ አመሰግናለሁ ብዬ ልሄድ ስል...... ይቀጥላል!
ይህን ታሪክ ስፖንሰር ያደረገው ኢትዮጵያን ኦንላይን ሾፒንግ ነው። በ ኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ኦንላይን ሾፒንግ የሚሰራ ነው። እሱም ብቻ ሳይሆን በብዞቹ ዘንድ ተቀባይነትን ያተረፈው ዋጋቸው በጣም ቅናሽ እና ኦርጂናል በመሆኑ ነው። ያላችሁበት ቦታ ድረስ መሙጣቱ ተመራጭነቱ እንዲያድግ አድርጎታል
አሜን ሳይል ማንም እንያል🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @Menta_lbochh_bot
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
1 737
😍በፍቅር ተጀምሮ በሀዘን
የሚያልቅ ሳይሆን በፍቅር ተጀምሮ
በፍቅር የሚያልቅ ፍቅር ይስጠን🙏
አሜን ሳይል ማንም እንያልፍ😉😜
🌹✨𝐉𝐎𝐈𝐍 𝐔𝐒💌𝐒𝐇𝐄𝐑✨🌹
💔መንታ💯 ❣️ልቦች💕💞
,,,,,,,,,,,🌹❣🌹❣🌹❣,,,,,,,,,,
•═•••♥️🍃🌺🍃♥️•••═•
@menta_lboch ,,📩 @Menta_lbochh_bot
━━━━━✦🌹✿🌹✦━━━━━
