cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Hule Addis Media ( ሁሌ አዲስ ሚዲያ)

ትክክለኛዉ የሁሌ አዲስ ሚዲያ ገፆች Facebook : bit.ly/42rUuKj WhatsApp : bit.ly/Huleadis_whatsapp YouTube : bit.ly/3p7kj3N Twitter : bit.ly/3NVMRrB Telegram: bit.ly/Huleadis_tele ለጥቆማ ና አስተያየት እንዲሁም ለማስታወቂያ ስራ ተከታዮን አድራሻ ይጠቀሙ bit.ly/3VMy7x7

Show more
Advertising posts
3 206Subscribers
No data24 hours
-57 days
-330 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViewsSharesViews dynamics
01
ኢራቃዊያን ተመሳሳይ ፆታን አውግዘዋል።ኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም ብለዋል። የኢራቅ ፓርላማ የግብረ ሰዶናዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ተግባርን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል። በአዲሱ ሕግ ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት እርስ ቤት ይወረወራሉ። እንዲሁም፦ ✔ግብረ ሰዶማዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤ ✔ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ ✔ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና ሚያደርጉ ዶክተሮች ✔ሆን ብለው ልክ #እንደ_ሴት_የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ። የኢራቅ ፓርላማ ተጠባባቂ አፈጉባኤ ሞህሰን አል-ማንዳላዊ " ይህ አዲስ ሕግ የህብረተሰቡን የሞራል / የግብረገብ / የስነምግባር መዋቅር ለመጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል። "በኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " ያሉት አል-ማንዳላዊ " ይህ የኢራቅ ምድር የነቢያት፣ የንፁህ ኢማሞች ፣ የጻድቃን እንዲሁም ቅዱሳን ምድር ነው " ነው ሲሉ ተናግረዋል።(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)
490Loading...
02
ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አሳፋሪ ልማዶች አንዱ የሆነውን የመንገድ ላይ መፀዳዳትን እስከመጨረሻው ለማስቀረት በሺዎች የሚቆጠሩ የህዝብ ዘመናዊ መፀዳጃ ቤት ቤቶችን ለመገንባት በጠ/ሚ አብይ አህመድ የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ይፋ አድርገዋል ። ጽዱ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚውለውን በጀት ለማሰባሰብ የጠ/ሚ ፅ/ቤት በዛሬው ዕለት ዲጂታል ቴሌቶን አስጀምሯል። ይህን ተከትሎ ብዙዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የድርሻቸውን በማበርከት ላይ ይገኛሉ።     
1730Loading...
03
የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53 በመቶ ድርሻ መያዙ ጥናት አመላከተ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር በተጠናቀቀው ዓመት አደረኩት ባለዉ ጥናት ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚዉሉ ልብሶች በሀገሪቱ ለሚገኙ የጨርቃጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ገበያውን ይበልጥ ፈታኝ" እንዲሆን እያደረገው እንደሚገኝ ገልጿል። ማህበሩ በዚሁ ጥናቱ በተለምዶ ቦንዳ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አልባሳት የሃገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያን 53 በመቶ ድርሻ መያዛቸዉን አስታዉቀዋል ። እነዚሁ ልብሶች ዋጋቸዉ ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ ዘንድ በጥራት የተሻለ ወይም ተቀባይነት ባላቸው አምራቾች የተመረቱ ናቸዉ በሚል አመለካከት ፍላጎቱ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል። እንደ ጥናቱ ከሆነ በአለም አቀፍ ደረዳ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት አልባሳት ገበያ 71.22 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ እንዳለው እና እኤአ በ2030 ደግሞ ወደ 282.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ የአልባሳት ገበያ በአሁኑ ወቅት ከአዉሮፓ እና አሜሪካ በመጡ ርካሽ ልብሶች መሞላታቸዉን በጥናቱ ተመላክቷል ። የቦንዳ ልብሶች ወደ ሀገር ዉስጥ በተለያዩ መንገዶች የሚገብ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው በሞያሌ ፣ በድሬዳዋና በሌሎች የድንበር ከተሞች ከሚባሉት በተጨማሪ በኢትዮጵያ አየር መንግድ በኩል በተለያዩ ሁኔታዎች ሲገቡ ይስተዋላል ። ሀገሪቱ በአማካኝ 54 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የጨርቃጨርቅ አልባሳት ያለ ክፍያ ( በዜሮ ወጪ) ድንበር አቋርጠው ይገባሉ፤ በዚህም ኢትዮጵያ በዓመት ከታክስ ገቢ 2.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደሚደርስባት ይገመታል ። እንደ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር ጥናት በህገወጥ መንገድ የሚገብ ልብሶች ኢንዱስትሪውን መፈታተናቸዉን መቀጠላቸውን እና ለኪሳራ እንዲዳረጉ እያደረገ በመሆኑ ማህበሩ በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ቅሬታዎችን ያቀረበ ቢሆንም ምላሽ ማግኘት እንዳልቻለ ጠቁሟል ሲል የዘገበው ካፒታል ጋዜጣ ነዉ።
1840Loading...
04
Media files
1600Loading...
05
ሳያት ደምሴ ከለዛ ሽልማት መውጣቷን አዘጋጁ ገለፀ ተዋናይት ሳያት ደምሴ ከማንኛውም የሀገር ውስጥ ውድድር ራሷን ማግለሏ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ማሳወቋን ይታወቃል:: ይህንን ተከትሎ የለዛ ሽልማት እስከ አሁን ድረስ እያወዳደራት የነበረ ቢሆንም የእሷን ሀሳብ በማክበር አዘጋጁ ብርሀኑ ድጋፌ በማህበራዊ ገፁ ላይ ይህንን አስፍሯል:: ምርጥ ተዋናይት ምድብ ዕጩዎች 4 ቀርተዋል:: ይህም የሆነው ከአክብሮት ጋር በሚል ተዋናይት ሳያት ደምሴ ከማንኛውም የአገር ውስጥ ውድድር ራሴን ማግለሌ ይታወቅልኝ ባለችው መሠረት ነው ይህ የሆነው :: ሃሣቧን እናከብራለን :: 13ኛው የለዛ ሽልማት የመጨረሻ ዙር እጩዎች ድምፅ መስጠት ሚያዚያ 23 ያበቃል! ብርሀኑ ድጋፌ የለዛ ሽልማት
2040Loading...
06
ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለግሰዋል 👏🙄 በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ የሆነውን የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን በመቀላቀል በርካቶች ድጋፍ ማድረጋቸውን እየሰጡ ነው። ከንቲባ አዳነች አቤቤም የተጣራ የአንድ ወር ደመወዛቸውን አስተዋጽኦ በማድረግ ንቅናቄውን መቀላቀላቸውን አስታውቀዋል፡፡
1650Loading...
07
🔴 የውጪ ባለሃብቶች በተከለሉ የወጪ፣ የገቢ፣  የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ኢንቨስትመንቶች የሚሳተፉባቸው ሁኔታዎች ምን ምን ናቸው? ከላይ የተያያዘውን መረጃ ይመልከቱ
2451Loading...
08
Media files
2190Loading...
09
ፈተናው በኦላይን ይሰጣል ተብሏል የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦን ላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተገልጿል። የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ምክክር መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተመረጡ ከተሞች በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል ። የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ለመስጠት ባይቻልም በሁሉም ክልሎች በተመረጡ ከተሞች ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በሁሉም ክልሎች ያሉ የተመረጡ ተማሪዎች በኦንላይን ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ በተለመደው አግባብ ፈተናቸውን ይወስዳሉም ብለዋል። የሀገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር (ዶ/ር) እሸቱ ከበደ በበኩላቸው ፈተናውን በኦንላይን ለመሥጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። ተማሪዎች የሙከራ ፈተና የሚለቀቅላቸው ሲሆን ደጋግመው እንዲሞክሩና እንዲለማመዱ ይደረጋልም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ለዚህም እንዲረዳ የአሰልጣኞች ስልጠና በመሥጠት ተማሪዎች ተደጋጋሚ ስልጠና እንደሚሠጣቸውም ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። ከቀጣይ ሳምንት ጀምሮ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት እንደሚጀምርም በመድረኩ ተገልጿል።
1960Loading...
10
Media files
2070Loading...
11
Media files
3171Loading...
12
Media files
560Loading...
13
ህወሓት በዝግ የተደረጉ ስብሰባዎች መረጃ ከየት ነው የምታገኙት በማለት ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶችን እያስፈራራ ነው ተባለ ህወሓት በቅርቡ ያካሄደውን 60 ቀን የፈጀ ዝግ ስብሰባን ጨምሮ በሌሎች ስብሰባዎች የተነሱ ጉዳዮችን የተመለከ መረጃ ለጋዜጠኞችና ለአክቲቪስቶች ማን ነው አሳልፎ እየሰጠ ያለው የሚለውን ለማወቅ ያለመ ኮሚቴ በማቋቋም ምርመራ መጀመሩን ተሰምቷል። በትናንትናው ዕለት አንድ የቀድሞ የድምፂ ወያነ ጋዜጠኛና የተለያዩ ህወሓትን የተመለከቱ ጉዳዮች በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በማጋራት የሚታወቅ ጋዜጠኛ በዚሁ መርማሪ ኮማቴ ጥሪ ቀርቦለት በመቀለ ከተማ በመገኘት ከኮሚቴው አባላት ጋር ቆይታ እንዳደረገ ተናግሯል። በቆይታውም በቅርቡ የተካሄደው 60 ቀናት የፈጀውን ስብሰባ ላይ የተነሱ ጉዳዮች የተመለከቱ መረጃዎች እንዴትና ከማን ነበር ስታገኝ የነበረው የሚሉ ጥያቄዎች እንደቀረቡለት የገለፀ ሲሆን ጥያቄዎቹም ከትብብር ይልቅ በማስፈራራትና ለማወጣጣት በመሞከር የተቃኙ እንደነበሩ ተናግሯል። ዳጉ ጆርናል የደረሰው መረጃ እንደሚያሳየው ከሆነም በጦርነቱ ወቅት የህወሓት ጦር ቃል አቀባይ የነበረው ገብረ ገብረፃዲቅና የቀድሞ የትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳዳሪ የነበረው ሃይለ አሰፋ የዚህ መርማሪ ኮሚቴ አባላት እንደሆኑ ነው።( Dagu Journal )
2750Loading...
14
Media files
40Loading...
15
አዲስ አበባ በርካታ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው ተብሏል። የአዲስ አበባ ፀጥታ ቢሮ እንዳስታወቀው ከሆነ ከሚሰጣቸው ሀላፊነት እና ስልጣን ውጪ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ የፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን እና ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። የከተማዋ አንዳንድ የፀጥታ አካላት በአማራ ክልል የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተገን በማደረግ ህገወጥ እስራት እና እንግልት እንደፈፀሙ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል። የአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በአማራ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአዲስ አበባ እንደማይገበር ገልፀው ከተማው ውስጥም ጉዳዮች ሲኖሩ በየትኛውም ሰዓት ኦፕሬሽን እንደሚሰራ ጠቁመዋል። በቅርቡ በተደረገው ፍተሻ ከ140ሚሊዮን ብር በላይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተጠቁሟል።በዚህም 1.5 ሚሊዮን ብር በቁማር የተሰበሰበ ብርን ጨምሮ ሌሎች ሀሰተኛ የብር ኖቶች ተይዘዋል ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ከ16,000 በላይ ተተኳሿችን ጨምሮ የስውር ትጥቅ እስከ ትልልቅ መሳሪያዎች መያዛቸው ተገልጿል። ለስራ ፍለጋ እና ለሌሎች ጉዳዮች ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ የሰዎች ብዛት በአጅጉ መጨመሩን ቢሮዉ አስታውቋል።
2881Loading...
16
Media files
451Loading...
17
Media files
2900Loading...
18
Media files
2601Loading...
19
Media files
2580Loading...
20
Media files
2780Loading...
21
ገጣሚና ደራሲ ዳዊት ጸጋዬ፤ የግጥም መድበልን ጨምሮ ሌሎች የፈጠራ ሥራዎችን ለንባብ ያበቃ ሲሆን፤በዘመነ ኢህአዴግ "የነጻነት ፈለግ" የተሰኘ  ፖለቲካዊ ቴአትሩ  ለአንድ ቀን ብቻ ታይቶ እንደታገደበት ያስታውሳል፡፡
2880Loading...
22
የፖለቲካ ሹመኞች የመንግሥት ሥራ  እንዲመሩ መፍቀድ ራስን በራስ ጠልፎ መጣል ነው   ገጣሚና ደራሲ ዳዊት ጸጋዬ  ከሚሰራበት  የመንግሥት መ/ቤት በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን ሰሞኑን  ለአዲስ አድማስ ተናገረ፡፡ ለመ/ቤቱ የመልቀቂያ ወረቀት አስገብቶ ሲመለስ ነበር ስልክ ደውሎ ያነጋገረኝ፡፡  የሚገርመው ደግሞ እኔ በገጣሚነቱና ደራሲነቱ እንጂ በመንግሥት ሥራ  ተቀጣሪነቱ ፈጽሞ አላውቀውም፡፡ በዚህም የተነሳ  ለእኔ የመንግሥት መ/ቤት ውስጥ መሥራቱም ሆነ መልቀቁ “ሰርፕራይዝ“ ነው የሆነብኝ፡፡  ለዚህ ዘገባ ዋና  መነሻ የሆነው ግን ከመንግሥት ሥራው የለቀቀበት ምክንያት ነው፡፡ ዳዊት ጸጋዬ እንደሚለው፤ በባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ጽ/ቤት፣ የኪነጥበብ ሃብት ልማት ባለሙያ በመሆን፣ የለውጡ መንግሥት ከመጣ ጀምሮ ላለፉት 6 ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ (በግጥሞቹ ፈጣሪን ራሱን ከመገዳደር ወደ ኋላ የማይለው ዳዊት ጸጋዬ፣ ይህን ሁሉ ዓመት በመንግሥት ተቋም ውስጥ መቆየቱ ብዙዎችን ሳያስገርም አይቀርም)፡፡ የኪነጥበብ ሃብት ልማት ባለሙያው፤ ሥራውን በገዛ ፈቃዱ የለቀቀው ሥራውን በአግባቡ ለማከናወን  የሚችልበት የሥራ ከባቢ በማጣቱ እንደሆነ ይናገራል፡፡  ”በተለያዩ ጊዜያት የመ/ቤቱ ሃላፊ ሆነው የሚመጡት ሰዎች የፖለቲካ ሹመኛ ወይም ካድሬ በመሆናቸው ለሥራው እንቅፋት ሆነዋል፤ ይህ አሰራር እንዲቀየርና መ/ቤቱ በባለሙያ እንዲመራ በስብሰባ ወቅት በተደጋጋሚ ባሳውቅም ሰሚ ጆሮ አላገኘሁም፡፡” ብሏል፤ ለአዲስ አድማስ፡፡ ዳዊት ጸጋዬ፤ የፖለቲከኛ ሹመኛ ወይም ካድሬ የሚላቸው የመ/ቤቱ ሃላፊዎች፣ ከሙያው ጋር ትውውቅ የሌላቸው በመሆኑ፣ ከባለሙያ ጋር መግባባት እንኳን እንደሚሳናቸው ነው የሚናገረው፡፡ በተለያዩ ጊዜያት ፕሮፖዛሎችን እያዘጋጀ ለሃላፊዎቹ ማቅረቡን የሚገልጸው ባለሙያው፤ ”ይሄ በዕቅዳችን ላይ የለም”፣ “በዚህ አትገመገምበት፣ ምን አስጨነቀህ” እያሉ የሥራ መነሳሳቱንና ሞራሉን እንደሚያላሽቁበት ይገልጻል፡፡  በዚህም የተነሳ በመ/ቤቱ ውስጥ ምንም ሥራ መሥራት አለመቻሉንና ደሞዝ ብቻ እየተከፈለው መቀመጡን ህሊናው ባለመቀበሉ ከሥራው በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን ጠቁሟል፡፡ “የመንግሥት ሥራ በፓርቲ ሹመኞች ቁጥጥር ሥር መዋሉ በህግ እንደሚያስጠይቅ ቢታወቅም፤ በእኛ መ/ቤት ግን አሁንም መደበኛ አሰራር ሆኖ ቀጥሏል” ያለው ደራሲና ገጣሚው፤ ”በተለያዩ መድረኮች ላይ በመንግሥት ሠራተኞች ላይ የተዘረጋው የፖለቲካ መዋቅር እንዲፈርስ ብጠይቅም ሰሚ አላገኘሁም፡፡“ ብሏል፡፡  ዳዊት እንደሚያስረዳው፤ የመንግሥት ሥራን በፓርቲ ሹመኞች ቁጥጥር ሥር ማዋል ከደርግ ዘመን አንስቶ የመጣ ችግር ሲሆን፤ በኢህአዴግ ዘመን ብሶበት ታይቷል፡፡ ይኸው አሁን በብልጽግና ደግሞ ያልተላቀቅነው አባዜ ሆኖ በመቀጠል ሥራ እያደናቀፈ ይገኛል ብሏል፡፡ እርሱ ባለፉት 6 ዓመታት በሰራበት በባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ጽ/ቤት ብቻ ሳይሆን፤ በአብዛኞቹ የመንግሥት ተቋማት ተመሳሳይ ችግር መኖሩንም ዳዊት  ያስረዳል፡፡  እርግጥ ነው የፖለቲካ  ሹመኞች ወይም ካድሬዎች ሃላፊ ሆነው በሚመሩበት የመንግሥት ተቋማት፤ ሥራ መደናቀፉ፣ መበላሸቱና መጓተቱ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የፖለቲካ ካድሬዎች ችግራቸው፣ በሃላፊነት የሚመሩትን ተቋም ወይም መ/ቤት የሥራ ሁኔታና ጠባይ አለማወቅ ብቻ አይደለም፤ቅንነትም ይጎድላቸዋል፡፡ ሌላው  ችግራቸው ደግሞ ራሳቸውን የህዝብ አገልጋይ አድርገው አለመቁጠራቸው ነው፡፡   እውነት ለመናገር የፖለቲካ ሹመኞች ወይም ካድሬዎች እንኳንስ ምን እንደሚሰራ የማያውቁትን የመንግሥት ተቋም በብቃትና በስኬት ለመምራት ቀርቶ በአብዛኛው ለፖለቲካውም ቢሆን የሚመጥኑ አለመሆናቸውን  በዓመታት ተሞክሯችን ደጋግመን አረጋግጠናል፡፡ እንኳንስ የአገር ዕድገትና ብልጽግናን እንዲያመጡልን ልናጫቸው ቀርቶ፣ በፈጠራ  ትርክታቸው አገራችንን  እንዳይበጠብጡብን ነው የዘወትር ፍርሃታችን፡፡ ለዚህ ነው ገጣሚ ዳዊት ጸጋዬ፤ የፖለቲካ ሹመኛ የሆኑ የጽ/ቤቱ ሃላፊዎች፣ “የሥራ እንቅፋት ሆነዋል” ሲል ብዙም ያልገረመኝ፡፡ (ታዲያ ያለቦታቸው ተቀምጠው ምን ይስሩ!?) አሁን ለምሳሌ የዚህች አገር ዋና ችግርና  እንቅፋት  ማነው? ብላችሁ መልሳችሁ ምን ይሆናል፡፡  እስቲ ያለፉትን  50 ዓመታት ወደ ኋላ ተጉዘን ታሪክን በቅጡ እንፈትሸው፡፡  የዚህች አገር ዋና ችግርና  እንቅፋት ፖለቲከኞች ሆነው ነው የምናገኛቸው፡፡ የየዘመኑ የጦቢያ ፖለቲከኞች! በአገራችን የሩቅም ሆነ የቅርብ ታሪክ ውስጥ በፖለቲከኛ ሹመኞች ወይም ከፍተኛ ካድሬዎች ተመርቶ ውጤት ወይም ስኬት ያስመዘገበ አሊያም ትርፋማ የሆነ የመንግሥት ተቋም ወይም ጽ/ቤት አሊያም ልማታዊ ድርጅት ሰምታችሁ ታውቃላችሁ፡፡ በኢህአዴግ ዘመን በ70 ቢሊዮን ብር እንደሚገነቡ የተነገሩን 10 የሚደርሱ የስኳር ፋብሪካዎች የት ገቡ? ምን በላቸው? መልሱን የሚያውቀው ”ኢህአዴግ ነፍሴ” ብቻ ነው፤ ለኛ ባይነግረንም፡፡ እኛ ግን አንድ ነገር በእርግጠኛነት እናውቃለን፡፡ ፕሮጀክቱ በባለሙያዎች ሳይሆን ተጠያቂነት አጠገባቸው ድርሽ በማይል  የፖለቲካ ሹመኞችና ካድሬዎች  በመመራቱ የማታ ማታ ተረት ሆኖ ቀረ፡፡ ገንዘቡም የት እንደገባ ፈጽሞ ሳናውቅ ሥልጣን ላይ በነበሩ ገዢዎቻችን ዓይናችን እያየ ተዘርፈን ቀረን፡፡ (ማንነታቸውን በስም ባናውቅም!) እስቲ አስቡት፤ ኢትዮ ቴሌኮም ብቃት ባላቸው ባለሙያዎችና አመራሮች ሳይሆን፤ በፖለቲካ ሹመኛ ወይም በከፍተኛ የካድሬዎች ስብስብ እንዲመራ ቢደረግ ምን ሊፈጠር እንደሚችል!? ፈረንጅ እንዲህ ያለውን ”ዲዛስተር” በሚል የሚገልጸው ይመስለኛል፡፡ ውጤቱ ያለጥርጥር ውድቀት፣ ኪሳራ፣ በዕዳ መዘፈቅ፣-- ወዘተ ነበር የሚሆነው፡፡ ኢትዮ ቴሌኮም አስደናቂ የዲጂታል ሽግግርና የፋይናንስ አካታችነትን እውን እያደረገ፣ በስኬትና ትርፋማነት የዘለቀውና  ተወዳዳሪነቱን በማስጠበቅ  መገስገስ የቻለው፣ በፖለቲከኛ ሹመኞች እጅ ላይ ባለመውደቁ መሆኑን መገመት አያዳግተንም፡፡ በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነውና እንደ አገራችን ሰንደቅ ዓላማ የሚቆጠረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ለአያሌ ዓመታት በስኬት ላይ ስኬት እየደራረበ፣ በላቀ ትርፋማነትና የልህቀት ደረጃ  መቀጠል የቻለው ብቃትና አቅማቸው በተረጋገጠ የየዘርፉ ባለሙያዎች በመመራቱ ነው፡፡  ብልጽግና መራሹ መንግሥት፣ እንደ ብሔራዊ መዝሙር ዘወትር የሚያዜመውና ሁላችንም በጉጉት የምንጠብቀውና የምንሻው የኢትዮጵያ  ብልጽግና፣ በቀላሉ እውን እንደማይሆን ይታወቃል፡፡ የግል ዘርፉንና የመንግሥት ተቋማትን እንዲሁም የሌሎቻችን የተጠናከረ ትጋትና ቁርጠኝነት በእጅጉ ይጠይቃል፡፡ በመንግሥት ተቋማት ወይም ቢሮዎችና ጽ/ቤቶች ሙያዊ ብቃትና አቅም  ያላቸው ሃላፊዎች ሳይሆኑ፤ የፖለቲካ ሹመኞችና ካድሬዎች እየተመደቡ መምራታቸውን ከቀጠሉበት ግን ገጣሚና ደራሲ ዳዊት ጸጋዬ እንዳለው፣ሥራንና ባለሙያን ማስተጓጎላቸው አይቀሬ ነው፡፡ አገርንና ልማትን ማደናቀፋቸው እሙን ነው፡፡ ይሄ ማለት ደግሞ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የአገራችንን የልማትና የዕድገት እንዲሁም የብልጽግና ጉዞ በእጅጉ እንደሚያዘገየው (ከእነአካቴውም ሊያደናቅፈው እንደሚችል!) ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር፣ የፖለቲካ ሹመኞችን ወይም ካድሬዎችን  በመንግሥት ተቋማት ውስጥ በሃላፊነት መመደብ ራስን በራስ ጠልፎ እንደመጣል እንደሚቆጠር ለብልጽግና መራሹ መንግሥት ልናስታውሰው እንወዳለን፡፡ (ሳያውቀው ቀርቶ ሳይሆን ምናልባት ዘንግቶት ከሆነ!)
3070Loading...
23
Media files
2910Loading...
24
ማርክ ዙከርበርግ የናጠጠ ቢሊየነር ነው። ሚስቱን ለማስደሰት ማንኛውንም በአለም ላይ ውድ የሆነ ቁስ ሊገዛላት ይችላል—ጌጣጌጦች፣ ቤት፣ መኪና፣ አውሮፕላን፣ የመዝናኛ መርከብ yacht ወዘተ። አንድ ደሴት ወይም ትንሽ ሀገር የሚገዛ ገንዘብ ያለው ሰው ነው። ገንዘብ ሊገዛው የሚችለውን ነገር ሁሉ በስጦታ ሊሰጣት ይችላል። ማርክ ግን ገንዘብ የሚገዛውን ትቶ ገንዘብ የማይገዛውን ሰጣት። ምን ይሆን ገንዘብ የማይገዛው?! የማርክ ሚስት ፕሪሲላ ቻን ትባላለች። በትውልዷ ቻይናዊ ናት። በላቧ ሰርታ የምታድር ሜዲካል ዶክተር ነች። ደግሞ በባህሪዋም ገንዘብ የሚያስደንቃት፣ ግድ የሚሰጣት ሴት አይደለችም። ታዲያ ለዚህች ሴት ማርክ ምን ይስጣት? ማርክ ለሚስቱ ሳይነግራት የቋንቋ ትምህርት ቤት ተመዘገበ። ለአመታት ማንዳሪን አጠና። በነገራችን ላይ ማንዳሪን ለመማር በጣም ከባድ ቋንቋ ነው። አይደለም በሁለተኛ እና ሶስተኛ ቋንቋነት አፈ ለፈቱበትም ዳገት ነው። በተለይ ጽሁፉ። አንዴ ስለ ማንዳሪን ሳነብ ከ48 ሺ በላይ ካራክተርስ አሉት ይላል። መሰረታዊ ጽሁፍ ለማወቅ ቢያንስ 3ሺ ካራክተር ማወቅ ይገባል። ምእራባውያን የለመዱት 26 የላቲን ፊደል ነው። ማንዳሪንን ተዉትና የኛ ቋንቋ 231 ፊደላት እንዳለው ሲያውቁ ልባቸው በድንጋጤ ቀጥ ነው የምትለው። አማርኛ ራሱ ለመማር ቀላል ቋንቋ አይደለም። ማንዳሪን የበለጠ ከባድ ነው። ብዙ ትጋት ይጠይቃል። ማርክ ራሱ ቋንቋውን በደንብ ለመካን ብዙ አመት ወስዶበታል። ያውም እሱ ከፍተኛ የአእምሮ ብቃት ስላለው ነው እንጂ ቋንቋው የሊማሊሞ ዳገት ነው። ታዲያ ማርክ በማንዳሪን ሲካን ለሚስቱ በመጀመሪያ እንዲህ ነበር ያላት፦ "我爱汝" ትርጉሙ "አፈቅርሻለሁ" ነው። ከዚህ የሚበልጥ ምን ስጦታ አለ?! በገንዘብ የማይተመን ዋጋ የማይወጣለት ውድ ስጦታ። ፍቅርና ቋንቋ። ቋንቋና ፍቅር። ፍቅር በቋንቋ ይገለጻል። እስኪ አንዳችን የሌሎቻችንን ቋንቋ በፍቅር እንማር። ፍቅራችንን እንገላለጽ። ቋንቋዎቻችን የፍቅር ድልድይ እንጂ የልዩነት ግድግዳ አይሁኑብን። ( Tewodros Shewangizaw )
3341Loading...
25
Media files
3050Loading...
26
Media files
3200Loading...
27
Media files
3310Loading...
28
ባይትዳንስ ' ቲክቶክ ' ን #ለአሜሪካ ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ ቢዘጋው እንደሚመርጥ ሮይተርስ ለኩባንያው ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ ዘገበ። ኩባንያው በ' ቲክቶክ ' ጉዳይ እስከመጨረሻው ያሉትን የህግ አማራጮችን ተጠቅሞ እንዳይታገድ ማድረግ ካልቻለ ፤ ለአሜሪካ ከመሸጥ ይልቅ እስከመጨረሻው #መዝጋት ይመርጣል ተብሏል። አሁን ' ቲክቶክ ' የሚሰራበት #አልጎሪዝም ለኩባንያው እንደ ዋናው ነገር እንደሚቆጠርና በዚህ አልጎሪዝም መተገበሪያውን የመሸጥ እድሉ እጅግ ሲበዛ አነስተኛ እንደሆነ የኩባንያው ምንጮች ገልጸዋል። በዚህም ፤ ለአሜሪካ ገዢ ከመሸጥ አሜሪካ ውስጥ እስከወዲያኛው ድረስ መዝጋትን እንደሚመርጥ ተጠቁሟል። አሜሪካ ' ቲክቶክ ' እንዲሸጥ ከ9 ወር እስከ 1 ዓመት ገደብ አስቀምጣለች ካልሆነ ግን እስከ ወዲያኛው እንዲታገድ ሕግ አጽድቃለች። በርካታ ጉዳዩን የሚከታተሉ የዘርፉ ሰዎች አሁን ባለው የአሜሪካ አቋም 170 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች ያሉት ' ቲክቶክ ' እስከ ወዲያኛው ድረስ የመወገዱ ነገር እውን መሆኑ አይቀርም ብለዋል።
3721Loading...
29
Media files
3590Loading...
30
በሰርቢያ የሶማሊያ ኤምባሲ ያወጣው ካርታ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ኤምባሲው ከኢትዮጵያ ኦጋዴንና አካባቢው ከጅቡቲና ከኬኒያን የተወሰነ ግዛት ያካተተ ካርታን አዘጋጅቶ "ታላቋ ሶማሊያ" ሲል ሰይሞታል። ከዚህ በተጨማሪም <<ሶማሊያ መደቡ ሰሚያዊ የሆነ ነጭ ኮከብ ያለው በግልፅ የሚታይ ባንዲራ አላት። ነጭ ኮከብ የሶማሌ ብሄራዊ ምልክት ነው። እያንዳንዱ አምስት ነጥቦቹ የሶማሌ አገርን ይወክላሉ።ታላቋ ሶማሊያ>> የሚል ፅሁፍ ጨምሮበታል። ጉዳዩን በሚመለከት ከሶስቱም የሶማሊያ ጎረቤት ሀገራት የተሰጠ መግለጫ የለም።
1050Loading...
ኢራቃዊያን ተመሳሳይ ፆታን አውግዘዋል።ኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም ብለዋል። የኢራቅ ፓርላማ የግብረ ሰዶናዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት ተግባርን ከ10 እስከ 15 ዓመት በሚደርስ እስር የሚቀጣ አዲስ ሕግ አርቅቋል። በአዲሱ ሕግ ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ከ1 እስከ 3 ዓመት እርስ ቤት ይወረወራሉ። እንዲሁም፦ ✔ግብረ ሰዶማዊነት / የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን የሚያበረታቱ፣ የሚያስተዋውቁ፤ ✔ሴተኛ አዳሪነትን የሚያራምዱ ✔ጾታ ለመቀየር ቀዶ ህክምና ሚያደርጉ ዶክተሮች ✔ሆን ብለው ልክ #እንደ_ሴት_የሚሆኑ ወንዶች እና " በሚስት መለዋወጥ " ላይ የተሠማሩ ሰዎች እስራት ይጠብቃቸዋል ፤ ዘብጥያም ይወርዳሉ። የኢራቅ ፓርላማ ተጠባባቂ አፈጉባኤ ሞህሰን አል-ማንዳላዊ " ይህ አዲስ ሕግ የህብረተሰቡን የሞራል / የግብረገብ / የስነምግባር መዋቅር ለመጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል። "በኢራቅ ውስጥ ለግብረ ሰዶማዊነት ቦታ የለም " ያሉት አል-ማንዳላዊ " ይህ የኢራቅ ምድር የነቢያት፣ የንፁህ ኢማሞች ፣ የጻድቃን እንዲሁም ቅዱሳን ምድር ነው " ነው ሲሉ ተናግረዋል።(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)
Show all...
ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ አሳፋሪ ልማዶች አንዱ የሆነውን የመንገድ ላይ መፀዳዳትን እስከመጨረሻው ለማስቀረት በሺዎች የሚቆጠሩ የህዝብ ዘመናዊ መፀዳጃ ቤት ቤቶችን ለመገንባት በጠ/ሚ አብይ አህመድ የ“ጽዱ ጎዳና - ኑሮ በጤና” ንቅናቄን ይፋ አድርገዋል ። ጽዱ ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚውለውን በጀት ለማሰባሰብ የጠ/ሚ ፅ/ቤት በዛሬው ዕለት ዲጂታል ቴሌቶን አስጀምሯል። ይህን ተከትሎ ብዙዎች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000623230248 የድርሻቸውን በማበርከት ላይ ይገኛሉ።     
Show all...
የቦንዳ አልባሳት የሀገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያ 53 በመቶ ድርሻ መያዙ ጥናት አመላከተ የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር በተጠናቀቀው ዓመት አደረኩት ባለዉ ጥናት ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የሚዉሉ ልብሶች በሀገሪቱ ለሚገኙ የጨርቃጨርቅ አምራች ኢንዱስትሪ ገበያውን ይበልጥ ፈታኝ" እንዲሆን እያደረገው እንደሚገኝ ገልጿል። ማህበሩ በዚሁ ጥናቱ በተለምዶ ቦንዳ በሚል መጠሪያ የሚታወቁት አልባሳት የሃገሪቱን የጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ገበያን 53 በመቶ ድርሻ መያዛቸዉን አስታዉቀዋል ። እነዚሁ ልብሶች ዋጋቸዉ ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በማህበረሰቡ ዘንድ በጥራት የተሻለ ወይም ተቀባይነት ባላቸው አምራቾች የተመረቱ ናቸዉ በሚል አመለካከት ፍላጎቱ ከፍተኛ እንዲሆን አድርጎታል። እንደ ጥናቱ ከሆነ በአለም አቀፍ ደረዳ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት አልባሳት ገበያ 71.22 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ እንዳለው እና እኤአ በ2030 ደግሞ ወደ 282.7 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። የኢትዮጵያ የአልባሳት ገበያ በአሁኑ ወቅት ከአዉሮፓ እና አሜሪካ በመጡ ርካሽ ልብሶች መሞላታቸዉን በጥናቱ ተመላክቷል ። የቦንዳ ልብሶች ወደ ሀገር ዉስጥ በተለያዩ መንገዶች የሚገብ ሲሆን ከእነዚህ ዉስጥ ዋነኛውን ድርሻ የሚይዘው በሞያሌ ፣ በድሬዳዋና በሌሎች የድንበር ከተሞች ከሚባሉት በተጨማሪ በኢትዮጵያ አየር መንግድ በኩል በተለያዩ ሁኔታዎች ሲገቡ ይስተዋላል ። ሀገሪቱ በአማካኝ 54 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የጨርቃጨርቅ አልባሳት ያለ ክፍያ ( በዜሮ ወጪ) ድንበር አቋርጠው ይገባሉ፤ በዚህም ኢትዮጵያ በዓመት ከታክስ ገቢ 2.5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደሚደርስባት ይገመታል ። እንደ ጨርቃጨርቅ አምራቾች ማህበር ጥናት በህገወጥ መንገድ የሚገብ ልብሶች ኢንዱስትሪውን መፈታተናቸዉን መቀጠላቸውን እና ለኪሳራ እንዲዳረጉ እያደረገ በመሆኑ ማህበሩ በተደጋጋሚ ለሚመለከተው አካል ቅሬታዎችን ያቀረበ ቢሆንም ምላሽ ማግኘት እንዳልቻለ ጠቁሟል ሲል የዘገበው ካፒታል ጋዜጣ ነዉ።
Show all...
👍 1

👍 2