cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Äbđù-Řêžâk öffičiãĺ

አሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረከአቱሁ ይህ የኔ የማዲህ አብዱ-ረዛቅ የቴሌግራም ቻናሌ ነው ማንኛውንም የኔን የመንዙማ እና የ ከቨር ስራዎቼን እንዲሁም የሌሎች ማዲሆችን አዳዲስ እና ቆየት ያሉ መንዙማና ነሺዳዎችን ያገኛሉ:: ሀሳብ እና አስተያየት እንዲሁም ጥያቄ ካላቹህ http://t.me/Abdurezak_bot

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
247
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ኢሽተቅና ልዩ የመድረክ ፕሮግራም የፊታችን እሁድ ጥር 29 ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት በሰፊው ሙሉዓለም አዳራሽ ለእይታ ይበቃል። (ኢንሻአላህ) በፕሮግራሙ ላይ ⚡️ የመንዙማው ንጉስ ክቡር ዶ/ር ሸይኽ ሙሐመድ አወል ሐምዛ በመረዋ ድምፃቸው የዐለማትን እዝነት ያወዳድሳሉ ያሞጋግሳሉ። ⚡️ ሕፃናት በጣፋጭ አንደበታቸው ጥዑም ነሽዳዎችን ያቀርባሉ። ⚡️ ትንታግ ዑለማዎቻችን በርቱዕ አንደበታቸው ኮርኳሪ ዳዕዋዎች ያደርጋሉ። ⚡️ የተለያዩ ግጥሞች እና ጨዋታዎች በመድረኩ ፈርጥ ኡስታዝ ሷሊሕ አስታጥቄ መድረኩን ውብ ያደርጋሉ። ⚡️ አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ሰዎች አዝናኝ፣ አስተማሪ እና አስቂኝ ተውኔቶችን ያሳያሉ። ⚡️ራምሳ እና ዒሽቅ ለመድሕ በተካኑ ማዲሖች ይታሸቃል። ምን ይሄ ብቻ ልዩ ልዩ ሰርፕራይዝ ሽልማቶች መነባንቦች ወጎች ኧረ ብዙ ብዙ ታዳሚዎቻችን ሊያስደስቱ የሚችሉ ፕሮግራሞችን ደግሰን ፣ ቀምመንና መጥነን እንጠብቅዎታለን። ቲኬቶችን በሁሉም የሕብረት ባንክ ቅርንጫፎች እና በየሰፈሩ በወከልናቸው ወኪሎቻችን ያገኛሉ። ለበለጠ መረጃ 0918399260 ይደዉሉ። ያስታውሱ 6 ቀናት ብቻ ቀርተውታል። https://t.me/mehdi_multimedia
Show all...
Mehdi Multimedia Production

ኢስላማዊ ፊልሞች እና ድራማዎች የቪዲዮ ደርሶች እና ዳዕዋወች መጽሄቶች እና መፅሐፍት በራሪ ወረቀቶች እና ሌሎችም በመሕዲ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን t.me/mehdi_multimedia

ከነገ ጀምሮ በባህርዳር ከተማ በሕብረት ባንክ በሁሉም ቅርጫፎች ቲኬቶችን ማግኘት ትችላላችሁ 😊 https://t.me/mehdi_multimedia
Show all...
final.mp32.50 MB
Photo unavailableShow in Telegram
ልዩ የመድረክ ዝግጅት በቅርብ ቀን በባህር ዳር ከተማ ሙሉዓለም አዳራሽ እያሰናዳን ነው ይጠብቁን 😍 http://t.me/mehdi_multimedia
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ልዩ የመድረክ ዝግጅት በቅርብ ቀን በባህር ዳር ከተማ ሙሉዓለም አዳራሽ እያሰናዳን ነው ይጠብቁን 😍 http://t.me/mehdi_multimedia
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ልዩ የመድረክ ዝግጅት በቅርብ ቀን በባህር ዳር ከተማ ሙሉዓለም አዳራሽ እያሰናዳን ነው ይጠብቁን 😍 http://t.me/mehdi_multimedia
Show all...
Yehadra_gtmoch Yehadra_gtmoch
Show all...
ዋሪዳ_3_ባይመጡማ_አዲስ_ልዩ_የመድረክ_ነሺዳ_warida_3_baymetuma_New_neshida_stage.mp312.87 MB
እባካችሁ ይሄ የ እኔ ፔጅ አይደለም ሁላችሁም ሄት ስፒች የሚለውን ፌስቡክ ላይ ገብተን ሪፖርት በ ማድረግ እናዘጋው
Show all...
🔸 አሏሁመ ሶሊ ዓላ ሙሐመዴ ሐቢቢላሂል መሕቡቢ ረቢ አል-ሐሺምይል ዓረቢ ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ 🔹 ገለታ ይድረሰው ከውናቱን ላደሰው በትንሹዋ ንጋት ሰጦን ትልቁን ሰው ደሞ እኛን መረጠን መድ አስበጠበጠን መድሁንም መደዱን እንድንሆን ከታቢ እስኪ ላወድሰው ያንን የልቤን ሰው ገፍላየን ላብሰው ይመታልኝ ድቢ 🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁 🔹 እንኳን የኔ ብዕር ቀለሜ ትንሹ ለሱ አይደል መምጣቱ ሰማይ በለው ዓርሹ ግንስ ግድ የለውም ለዱንያ ለዓይሹ ሌጣ ሰሌን ነበር መተኛው ሐቢቢ ወርቅ ልሁን ብሎ ተራራው ቢማልደው እሱ መች ወደደው መለሰው ሲል እንቢ 🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁 ♥️እኔማ ወድጀው♥️ እረፍት አጧል ቀልቤ ታልዘየርኩት ሔጄ በልቤ ተስቤ አይሞቀኝ ለብሼ አልጠግብ ጎርሼ ሸውቅሆን ወርሼ ካልሆንኩኝ ቀራቢ ቀልቤ በሱ ሳስቷል ጀሰዴም ሟሙቷል አይኔም ሆኖለታል እንባውን አዝናቢ 🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁 🔹 ስሙ ቢያላብሰው የሐይባውን ካባ ሐብትና ሕይወቱን ሲዲቅ ያሉት ጀባ ዱዓው ተነጣጥሮ ዑመርን ቢያድነው ክፍቱን ደነደነው ሰይፉን ሆነ አንጋቢ ኡስማንን ቢለክፈው ሁቡ አርገፈገፈው አድርጎት አረፈው ፉርቃኑን አንባቢ 🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁 🔹 ዓልዩን አደሰው ፈትፍቶ አጎረሰው በሒዳያ ድር ማቅ ቀሚስ አለበሰው ከሌላው ነጥሎ ለልጁ ሰረገው ደግሞም አደረገው የአህለል በይት ዋቢ የከውናቱን መላው ያልታየው ምሰላው የእንስቶች ጥላ የወንዶች ሙረቢ 🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁 🔹 አባት አስጠልፎ ጫሌን የወሰደው በመደድ ጎተና ድልቡ የከበደው የመሐባው ሹኡን የማይለመደው ክረምቱን አንድዶ በጋውን አርጣቢ እኔስ ተክለፈለፍኩ ጧቱኑ ተለከፍኩ ላነሳሁ ተሰለፍኩ አብሽር በሉኝ ነቢ 🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁 🔹 ብላቴና ነብሴ ጮርቃዋ አካላቴ አንቱን ብናፍቁህ ነው አደቡን መሳቴ ዝው ብየ ሰተት ያለ አቅሜ መግባቴ ዝም አላስችል አለኝ ሲጠሩ ሐቢቢ ነዝር አለኝ ለጌታ አንቱን ያየሁ ለታ ከጫልዮች ይዤ ልል አዋየ ነቢ 👏🥁👏🥁👏🥁👏🥁👏🥁👏🥁👏 🔹 ባህሪው እንደ መልኩ ሁሉንም በለጠው የባህሪው ዝቃጭ ዱጁዱን ጨለጠው አንቢያ መላይካ አውሊያ አልገለጠው ሚሳል የለሽ አርጎ ከውኗቸው ረቢ ቢታሰስ ቢዳሰስ የላይ ታቹ ግድም ከቶ እናት አትወልድም እንደ አህመድ ነቢ 🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁 🔹 ባህሩ መድ ሆኖ ዛፉ ሁሉ ቀለም ከውኑ ሁሉን ቂርጧስ በመድህ እሚሸለም መድሁ ተከትቦበት ዘውትሮ ዘላለም ባህሩም ዛፉም አልቆ አልተነኩም ነቢ ባጭር እንተወው እንደነ በርዘንጅ አይችልም የኛ እጅ ሊሆነው ከታቢ 🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁🥁 ሀቢቢላሒል መህቡቢ ረቢ ×(4) 👏🥁🥁👏🥁🥁👏🥁🥁👏🥁🥁👏 🔸 የየቲም አባት ነው የመሳኪን ዋቢ 🔸 ለአለማቱ እዝነት አድርጓቸው ረቢ 🔸 መላ ስብእናው እንደ ማግኔት ሳቢ 🔸 ስጡኝ ሚለው ወገን ሲሆን ተሰብሳቢ 🔸 እንኩልኝ ሐላቸው ከቶ አያውቁም እንቢ 🔸 ለነገየ ብለው አይደሉም ቆጣቢ 🔸 ከቶ መች ተፈጥሮ ሚመስል የኛን ነቢ 🔸 ከኡማው አብልጠው ለኡማው አሳቢ 🔸 አውልቀው ሚያለብሱ የራስወን ጋቢ 🔸 ሆዳቸው ተርቦ ሌላውን ቀላቢ ሀቢቢላሂል መሕቡቢ ረቢ ×(2) 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 🔸 አዛኝነቱ ወደር የለውም 🔸 ቸር የተባለ አይቅጣጨውም 🔸 ቃላት ቢሰደር ከቶ አይገልፀውም 🔸 ከጀሊል በቀር ሌላ አያውቀውም 🔸 ባህር ነው እሱ የለም ማይቀዳው 🔸 አንዴ በመቅመስ የሚያፀዳው 🔸 ሐለትን ሁሉ የሚያሰናዳው 🔸 አንቱን ቀርቤ መቼ ተጎዳው ሀቢቢላሂል መህቡቢ ረቢ ×(2) 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 🔸 የአሪፎቹን መሽረብ ሆንኩኝ ተረካቢ 🔸 የወስፍዎ ማማር አርጎኝ ተቅለብላቢ 🔸 ከቶ ከየት ሊገኝ መሳይ የኔን ነቢ 🔸 ቀኑን በፃም ውለው ሌቱን ለአሏህ ሐምድ 🔸 በለዘብታ ቃላት ሐቁን አስገንዛቢ 🔸 በር እስካላንኳኩ አልነበሩም ገቢ 🔸 ፈገግታ ነው እንጂ ጮክ አያቁም ነቢ ሀቢቢላሂል መህቡቢ ረቢ ×(2) 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 🔸 ፈገግታ ነው እንጂ ጮክ አያቁም ነቢ 🔸 ልቡን ገለጥ አርጎ ለሆነው ቀራቢ 🔸 የግንባርሁ ግርማ ሸቃዋን ገላቢ 🔸 በኑር ተወሽሞ በመለክ ታጃቢ 🔸 የወር ምንገድ ያህል ሐይባቸው አባቢ 🔸 ጀቢናቸው ጀምበር አፉ ማር አዝናቢ 🔸 መርጋቱ ተሳነኝ አርጎኝ ተቅለብላቢ ×(2) 🔸 እስካልተሳለምኩት ያንቱን አካባቢ ሀቢቢላሂል መሕቡቢ ረቢ ×(3) 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 ሳረ ወኸረቀ ሁጅበን በዕደ ሁጅቢ ማ ዛለ የዝዳዱ ሁጅበን በዕደ ሁጅቢ ፈቀጥ ሁወ ዐላ ጀሚዑ ሩተቢ ወሳደ ሩሱላ ፊ ኩሊ መውኪቢ ወቀድ ተዐጀበ ሚንሁ ኩሉ ነቢ ቀድ ሀበት ኢለይሂም ነሳኢሙል ጀዝቢ ወሃየጀት ፊሂም ነሳኢሙል ሁቢ ፈሃኑ ኢሽቲያቀን ኢላ ዋዲል ቁርቢ ያ መን ላየህሷ ቢልዐዲ ፈድሉሁ ረቢዑል ኪራሚ ሰይዱል ዐረቢ ወያ መን ላዩጀድ ፊል ኸልቂ ሚስሉሁ ወሲለቱል ኩሊ ዐጀም ወዐረቢ 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 🔸 በሸጋ ስብዕናው ሙላውን አርጣቢ 🔸 ነብሴ ፊዳ አስባለው አጀም ከዓረቢ 🔸 እርሱ ነው ጎተናው የአርሳሉ ዘውድ 🔸 የሐምዱን ሱንዱቁን እርሱ ተረካቢ 🔸 የወር መንገድ ሐውዱ ሆኖለት ተንቧቢ 🔸 በል ጠጣ ይባላል የቂያም'ለት ሙሂቢ 🔸 የወር ምንገድ ሐውዱ ሆኖለት ተንቧቢ 🔸 በል ጠጣ ይባላል የቂያም'ለት ሙሂቢ ሀቢቢላሂል መሕቡቢ ረቢ ×(2) 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 🔸 ግንባርሁ ላይ ቢያዩ የኑሩን ጥማድ 🔸 ተማረኩ ባንቱ ሰልማንም ሱሃይቢ 🔸ቤዛ ሆኗል ስንቱ ብሎ ለአህመድ ነቢ ×(2) 🔸 በ'ሳት ተቀጥተዋል ዙበይርም ኸባቢ 🔸 ደሙ የፈሰሰው ላንቱ አደል ኹበይቢ (2) 🔸 ቤት አሰነዳዱ ደግሞ አቡ ዓዩቢ 🔸 ሲገቡ መዲና የዓለሙ ዋቢ ሀቢቢላሂል መሕቡቢ ረቢ ×(2) 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 🔸 ስንቱን ገደለው እየጠበሰው 🔸 መውደዱ ጠንቶ እያስለቀሰው 🔸 ከሀገር ወዳ'ገር እያፈለሰው 🔸 ሐያሉ መውደድ በኛም ደረሰ ሀቢቢላሂል መሕቡቢ ረቢ ×(2) 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 🔸 በልጅ'ግሬ ደርሶ የያዘኝ 🔸 ድንበሩን አልፎ ቢወዘውዘኝ 🔸 ይሔ መውደድ ነው ቀለም ያስያዘኝ 🔸 እንድከትብለት በጧት ያዘዘኝ 🔸 ይሔ መውደድ ነው ቀለም ያስያዘኝ 🔸 እንድከትብለት በጧት ያዘዘኝ ሀቢቢላሂል መሕቡቢ ረቢ ×(2) 👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏 🔸 ሰላም በረካ ረህመት ደህንነት 🔸 ከኮከብ ብዛት ከሰማይ ግዝፈት 🔸 ከፀሐይ ብርሐን ከ ቀመር ድምቀት 🔸 እጅጉን በዝቶ ልቆ በውበት 🔸 በከውኑ መላ አበል ፋጢመት 🔸 ይበርከትሎት አፍዶሉ ነቢ ሀቢቢላሂል መሕቡቢ ረቢ ×(3) 👏🥁👏🥁👏🥁👏🥁👏🥁 🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸 🔹 አሏሁመሶሊ ዓላ ሙሐመዴ 🔹 🔸 ሐቢቢላሂል መሕቡቢ ረቢ 🔸 🔹 አል ሐሺምይል ዓረቢ (2) 🔹 🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸🔹🔸 https://t.me/joinchat/SzuhpWWsHyqYUORC
Show all...
🧑‍🎤 የሀድራ ግጥሞች✍

ልትልኩልን የምትፈልጉ በዚህ @Yehadragtmoch_bot ያድርሱን::

አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏሂ ወበረካቱሁ መሕዲ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ከ ባህርዳር ሙስሊም ወጣት ጀመዓ ጋር በመሆን ከዛሬ ጀምሮ በባህርዳር ከተማ ይህችን መፅሐፍ ያቀርብላችኋል ።☺
Show all...
ከአዲስ አበባ ኑር መሥጅድ ወጣት ጀመዓ ጋር በቅርቡ በአዲስአበባ ከተማ
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.