cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Ethiopiawinnet CDCR( ኢትዮጵያዊነት) 🇪🇹

ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ድርጅት በሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ተመስርቶ ከመስከረም 05 ቀን 2013 ዓ.ም ጀመሮ በኢ.ፌ.ድ.ሪ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ባለሥልጣን በሰርተፍኬት ቁጥር 5099 የተመዘገበ ሃገር በቀል ድርጅት ነው። መልእክት / አሰተያየትዋን በ @ethiopiawinnet1 ወይም 09 65858580 ይላኩልን።

Show more
Advertising posts
423
Subscribers
No data24 hours
-37 days
+1630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የድርጅታችን መስራችና በሰሜን አሜሪካ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር እርቁ ይመር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ይከታተሉ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=GH-AzIy--5s&t=1131s
Show all...
ኢትዮጵያዊነት ለጊዜው በብሔረተኞች ቢፈተንም ዳግም ተጠናክሮ ያንሰራራል--የኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ዶ/ር እርቁ

የኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባኤ ፕሬዚዳንት የሆኑት ዶ/ር እርቁ ይመር ኢትዮጵያዊነት ለጊዜው በብሄረተኞች ቢፈተንም ዳግም ተጠናክሮና ጎልብቶ መቀጠሉ አይቀሬ መሆኑን ያስረዳሉ #Ethiopia #Ethiopian #Amhara #Oromo #Tigray #Amharic #AmharicSongs #EVN

ዌቢናሩን ለመታደም በቀጣዩ ሊንክ በመክፈት እንዲመዘገቡ በአክብሮት እንብዛለን ይመዝገቡ፡: https://us06web.zoom.us/webinar/register/WN_TXdo1-akSJmMRGUEFykW5g Share to Others
Show all...
ኢትዮጵያዊነት የዜጎች መብት ማስከበሪያ ጉባዔ የአማራን ሕዝብ እንደ ጨቋኝ ያስፈረጀው ትርክቶች ያስከተሉት ፖለቲካዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ማህበረሠባዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳቶች” በሚል ርዕስ ሁለተኛው የዌቢናር ጉባዔ ቅዳሜ ኦክቶበር 21, 2023 10:00 AM EST ጀምሮ ይከናወናል። ይህ ባለፈው ሳምንት በዌቢናር 1 ተደርጎ የነበረው "የፀረ አማራ ትርክቶች መንስኤዎች ምን ምን ናቸው? በሚል የተደረገው ታሪካዊ ውይይት ተከታይ ነው። በመጭው ሳምንት ኦክቶበር 28፣ 2023 ዓ/ም ደግሞ፣ ከዚህ ምን እንማራለን ፣ ምንስ ማድረግ አለብን? በሚል በመፍትሔ ላይ ያተኮረ ውይይት፣ በምሁራንና ታዳሚዎች ይደረጋል። ይህ ይህ የመጨረሻው ክፍል ይሆናል። እርስዎም የእነዚህ ዌቢናሮችታዳሚ እንዲሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን። ይመዝገቡ።
Show all...
👍 1
ስለ ኢትዮጵያዊነት፣ ኢትዮጵያዊነት የዜጎች ምብት ማስከበሪያ ድርጅት (ኢትዮጵያዊነት) እ.ኤ.አ በ 2012 ዓ/ም የተቋቋመ፣ በውጭና በሀገር ቤት የሚንቀሳቀስ፣ ፆታ፣ብሔር፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ወዘተ የማይለይ፣  የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሕጋዊ የማህበረሰብ (ሲቪክ) ድርጅት ነው።  ድርጅታችን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ያየተደረጉትን ጥረቶች ፣ በከፊልም ቢሆን የሚገልፁ ፣ ሀገራዊ ይዘት ያሏቸውን ምስሎችና  ቪዲዮዎችን በ ዩትዩብ : Voice of Ethiopiawinnet ላይ ያገኛሉ። ዌብሳይት፡- https://www.ethiopiawin.net    ፌስ ቡክ: https://www.facebook.com/ETHIOPIAWINNET.AA ቴሌግራም፡ https://t.me/ethiopiawinnetaa ሊንክደን፡ https://www.linkedin.com/company/79367322/ ዩትዩብ : Voice of Ethiopiawinnet በቀጥታ ለማግኘት   [email protected]  / [email protected] ብለው ይፃፉልን።
Show all...

ቅዳሜ የተካሄደውን ዌቢናር መከተል ላልቻላችሁ በቀጣዩ ዩትዩብ ሊንክ መከታተል ትችላላችሁ https://youtu.be/ahCDr_7KSvU?si=M37tCpn_JPNnH8d-
Show all...
ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ ትርክቶች መቸና እንዴት ተጀመሩ?

ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ ትርክቶች መቸና እንዴት ተጀመሩ? ይህ በውጭ ሃይሎች የተቀነቀነው የተሳሳተ ትርክት በሀገር በቀል ሃይሎች ተግባራዊ ሊሆን እንዴት ቻለ Contents -- TIMESTAMPS -- 00:00 Dr. Tessema Guebre X, Master of Ceremony 00:04:42 Dr. Erku Yimer, Opening Remarks 00:14:25 Professor Haile Larebo, በውጭ ሰዎችና ተቋማቾቻቸው ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ የሃሰት ትርክት አቀንቃኞች የተጫወቱት ሚና 00:49:11 Dr. Abeba Fekade, የሃገር-በቀል  ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ የሃሰት ትርክት አቀንቃኞች የተጫወቱት ሚና 01:23:50 Ato Geletaw Zeleke, ፀረ-አማራና ፀረ-ኢትዮጵያ የሃሰት ትርክት በዛሬዋ ኢትዮጵያ እንዴትና ለምን ቀጣይነት አገኘ   01:49:40 Professor Minga Negash, Discussant 02:24:09 Question and Answer 04:08:17 Dr. Erku Yimer, Closing Remarks About Ethiopiawinnet: Ethiopiawinnet website:

https://ethiopiawin.net/

[email protected] Telegram:

https://t.me/ethiopiawinnetaa

Facebook :

https://www.facebook.com/ETHIOPIAWINNET.AA/

Twitter:

https://twitter.com/ethiopiawinnet

Support Ethiopiawinnet Bank account: Ethiopiawinnet CDCR Dashen Bank Account No. 0155219603011

የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በኢትዮጵያ [በትግራይ] ተሰማ...!! ባያድለን ነው እንጂ ይሄ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያን ሁሉ ኀዘን፤ የምድሪቱ ልቅሶ መሆን ነበረበት!! በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) "ኢትዮጵያ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚፈውስሽ ማን ነው. . . ?!"  እንደ መግቢያ፤ "የኢትዮጵያ ሀገሬ ታጠቂ በገመድ፤ የወንድ ልጅ እናት ታጠቂ በገመድ፤ ያም ልጅሽ ያም ልጅሽ፤ ያም ዘመድ ያም ዘመድ፤ ለማን ታድያለሽ ... ለማንስ ይፈረድ?! (የባህል ሙዚቃ ንግሥቷ ማሪቱ ለገሠ/እንደው ዘራፌዋ) የኢትዮጵያና የኢትዮጵያን የታሪክና የሥልጣኔ እምብርት፤ የክርስትና እና የኢስላም ሃይማኖቶች (የርዕሰ አድባራት አክሱም ጽዮን እና የአልነጃሺ) መሠረት/መነሻ ምድር ኢትዮጵያ/አክሱም/ትግራይ፤ ኢትዮጵያውያን ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ጫፍ ተጠራርተው ብሔርና ጎሳ፤ ሃይማኖትና ቋንቋ ሳይለያቸው በአጥንታቸው ብዕርነት በደማቸው ቀለምነት የነጻነትን ክቡር መንፈስ ከፍ ባደረጉበት፤ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ የነጻነት ሰንደቅ በተውለበለበባት፤ የኢትዮጵያዊነት የቃልኪዳን ውሉ በተቋጠረባት በዐድዋ/በትግራይ ምድር፤ በወንድማማች ጦርነት በአንድ ጀምበር ለወሬ ነጋሪ አንዱ እንኳን ሳይተርፉላት አምስቱም ልጆቿ/ሁሉም ማለቃቸውን ሰምታ ራስዋን ስላጠፋች፤ ኀዘን አቅሏን ስላሳታት የትግራይ/የኢትዮጵያ ምስኪን እናት ምን ምላሽ፤ ምንስ የማጽናኛ ቃል አለን...?! በአማራ፣ በአፋር፣ በቤሻንጉል ጉሙዝ፣ በወለጋ... በሁሉም ኢትዮጵያ ምድር በጦርነት ነዲድ እየተለበለቡ በገፍና በግፍ ስላለቁትና እያለቁ ስላሉት የኢትዮጵያ ልጆች ምን እያልን፤ ምን እያሰብን ይሆን...?! በቤተ መቅደሱ ደጃፍ ስለታረዱት ካህናት፣ ደማቸውን ውሻ ስለላሰው፣ በድናቸውን ለአውሬና ለአሞራ ሲሳይ ስለዳረግናቸው ወገኖቻችን፤ ስለተደፈሩ መነኮሳት፤ የሴትነታቸው ክብር በአደባባይ ስለተዋረደባቸው፣ ስለተጎሳቆለባቸው ምስኪን እናቶቻችና እህቶቻችን ምን ቃል፤ ምንስ አንደበት ይኖረን ይሆን...?! የጦርነት ነጋሪት ስንጎስም፣ በወንድማማች ሕዝብ፤ በኢትዮጵያውያን መካከል የጥላቻን፤ የመለያየትን ዘር ስንዘራ የነበርን ነፍሰ-ገዳዮች/ቃኤላውያን ሆይ አሁን ገና የደም ግብራችን አልረካ ይሆን...?! የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በኢትዮጵያ [በትግራይ] ተሰማ...!! እነዚህ ኃይለ-ቃላት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰዱ ጥቅሶች ሲሆኑ፤ በተለያዩ ጊዜያት የእግዚአብሔር ነቢያት ስለ እስራኤል፣ ስለ ኢየሩሳሌም/ስለጽዮን ውርደት፣ መከራና ሰቆቃ የተናገሯቸው ናቸው። ጥቅሶቹ የእናት ምድራችንን የኢትዮጵያን ኀዘን፤ የኢትዮጵያውያን እናቶችን ሰቆቃ/ታላቅ ስብራት የሚገልጽ መስሎ ስለተሰማኝ ነው- ኢትዮጵያ የሚለውን ስም በመተካት አካፍላችሁ ዘንድ የወደድኹት። "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ [በትግራይ] ተሰማ፤ ራሔል [ኢትዮጵያ] ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፤ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን ፈጽሞ እንቢ አለች።" (ትንቢተ ኤርምያስ ፴፩፤፲፭)። "ድምፅ በኢትዮጵያ ተሰማ፥ ልቅሶና ብዙ ዋይታ፤ የትግራይ እናት ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ መጽናናትንም አልወደደችም።" ኢትዮጵያ አለቀሰች፥ ደጆችዋም ባዶ ሆኑ በምድርም ላይ ጨለሙ፤ የእናቶች ጩኸት ከፍ ከፍ ብሎአልና፤ የኢትዮጵያ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፤ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፥ ማቅም ታጠቁ፤ ደናግላን ራሳቸውን ወደ ምድር አዘነበሉ። ወደ ዓመት በዓልም የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች [የአክሱም መንገዶች] አለቀሱ፤ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል ካህናቶችዋም እየጮኹ ያለቅሳሉ፤ ደናግሎችዋም ተጨነቁ፤ እርስዋም በታላቅ ምሬት ውስጥ አለች። በኢትዮጵያ ሴቶችን፥ በከተሞቿም ደናግልን አጐሰቈሉ፤ አለቆች በእጃቸው ተሰቀሉ፤ በመቅደሱ የካህናት፣ በአደባባይም የሽማግሌዎች ፊት አልታፈረም።  ጕልማሶች ወፍጮን ተሸከሙ፥ ልጆችም ከእንጨት በታች ተሰናከሉ። ሽማግሌዎች ከአደባባይ፥ ጕልማሶች ከበገናቸው ተሻሩ። አቤቱ፥ ተጨንቅናል፥ አንጀታችም ታውኮብናልና፤ ተመልከት፤ ልባችን በውስጣችን ተገላበጠብን፤ በሜዳ ሰይፍ ልጆቻችንን አጠፋ በቤታችንም ሞት አለ። ድንጋጤና ቍጣ፥ ጥፋትና ቅጥቃጤ ሆነብን። ስለ ወገናችን ሴት ልጆች ቅጥቃጤ ዓይናችን የውኃ ፈሳሽ አፈሰሰች። እግዚአብሔር ከሰማይ እስኪጐበኝና እስኪመለከት ድረስ ዓይናችን ሳያቋርጥ ዝም ሳይሉ እንባን ያፈሳሉ።  የልባችን ደስታ ቀርቶአል፤ ዘፈናችን ወደ ልቅሶ ተለውጦአል፤ ዓይናችን በእንባ ደከመች፥ አንጀታችንም ታወከ፤ ስለ ኢትዮጵያ ወገኖቼ ቅጥቃጤ ጉበታችን በምድር ላይ ተዘረገፈ።  ኢትዮጵያ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? አጽናናሽ ዘንድ በምን አስተካክልሻለሁ? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚፈውስሽ ማን ነው?  ነቢያቶችሽ ከንቱና ሐሰተኛ ራእይ አይተውልሻል፤ ምርኮሽንም ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፤ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል። እንደ መውጫ፤ አንጋፋው ፖለቲከኛ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁሩ፣ አዛውንቱ ዶክተር ኃይሉ አርዓያ- በዛን ጊዜው የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ/የአሁኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በነበሩበት በ1950 ዎቹ ስለኢትዮጵያ የቋጠሩት ስንኝ ለአሁኗ ኢትዮጵያም የሚስማማት ይመስለኛል። እንሆ ከዶ/ር ኃይሉ አርዓያ እንጉርጉሮ/ስንኞች፤ "... ይኸው ትታያለች ለሕዝብ በይፋ፣ ጥቁር ተከናንባ ጥቁር ተጎናጽፋ፡፡ እኔስ መስሎኝ ነበር ዘመድ የሞተባት፣ የእናት ሞት የአባት ሞት፣ የልጅ ሞት ያጠቃት፣ ለካ እሷስ ኖራለች ዘመን የሞተባት...!! (ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕ. ፭) ---------- ፲፯፤ አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፤ ተመልከት ስድባችንንም እይ። ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ።  ፲፰፤ ድሀ አደጎችና አባት የሌለን ሆነናል፤ እናቶቻችን እንደ መበለቶች ሆነዋል።  ፲፱፤ አቤቱ፥ አንተ ለዘላለም ትኖራለህ፤ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።  ፳፤ ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?  ፳፩፤ አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።  ፳፪፤ ነገር ግን ፈጽመህ ጥለኸናል፤ እጅግ ተቈጥተኸናል። ሰላም ለኢትዮጵያ፤ ሰላም ለምድራችን🕊🕊
Show all...
👍 1 1
Happening Now: Attending consultation meeting on CSOs and Academia on promoting and consolidating HR and Democracy
Show all...
መስቀልን:- ከሺሕ ዘመን ታሪካችን እና ከኢትዮጵያ ቤ/ክ አንጻር በጨረፍታ. . . የመስቀል የክርስትና ሃይማኖት ትልቅ ትእምርት/ሲምቦል ነው። መስቀል ከክርስትና ሃይማኖት ጋር ሺሕ ዘመናትን የዘለቀ፣ የጠበቀ ትስስር አለው። ወደ እኛው ታሪክ ስንመለስ ደግሞ ቅዱስ መስቀል በኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ትልቅ ክብር፤ ልዩ ስፍራ አለው። ወደኋላ ተጉዘን ታሪክ መዛግብትን ስንፈትሽ፤ ክርስትና ሃይማኖት የሀገራችን ብሔራዊ ሃይማኖት በሆነበት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የአክሱም/የኢትዮጵያ ነገሥታት የነበሩት ወንድማማቾቹ ኢዛና እና ሳይዛና በስመ ክርስትናቸው አብርሃ ወአጽብሃ በ፬ኛው መቶ ክ/ዘ የክርስትና ሃይማኖትን በይፋ ከተቀበሉና የመንግሥታቸው ሃይማኖት ባደረጉ ማግሥት በወርቅ ሳንቲሞቻቸው ላይ ቀድሞ ይጠቁሙበት የነበረውን የጨረቃ እና ሌሎች የግሪክ አማልክት ምስሎችን ወደ መስቀል ቀየራቸውን ያወሳሉ። (በነገራችን ላይ የግሪክ ሥልጣኔ በዘመኑ እጅግ ገናና ከመሆኑ የተነሳ ሃይማኖታቸው/አማልክቶቻቸው፣ ቋንቋቸውና ባህላቸው መላውን ከዓለም ተቆጣጥሮት ነበር። ልክ እንደዛሬው እንግሊዝኛ የግሪክ ቋንቋም Linguafranka/ዓለም አቀፍ ቋንቋ ነበር። ኢትዮጵያውያን የግሪክ ቋንቋን ለዓለም አቀፍ ግንኙነት በሀገር ውስጥ ደግሞ ግእዝን እና የሳባውያንን ቋንቋዎችን ይጠቀሙ እንደነበርም ጥንታውያን የታሪክ መዛግብት በስፋት ይጠቁማሉ።) በዘመኑ እጅግ ገናና የነበሩት ኢትዮጵያውያን/አክሱማውያን (በነገራችን ላይ በዘመኑ በዓለማችን ላይ ከነበሩ አራት የዓለማችን ታላላቅ ሥልጣኔዎች መካከል ከግሪክ፣ ከፐርሺያ/የአሁኗ ኢራንና ቻይና አገራት ጋር አክሱም/ኢትዮጵያ አንዷ የዓለማችን ታላቅ ሥልጣኔ እንደነበረች ልብ ይሏል፤) አክሱማውያን የአሁኗን የመንን ጭምር ሲገዙ የነበሩ ግዙፍ የባሕር ኃይል ባለቤቶች፣ ዓለም አቀፍ ንግድን ያሳልጡ የነበሩና በወርቅ ሳንቲም ይገበያዩ የነበሩ ታላቅና ሀብታም ሕዝቦች ነበሩ/ነበርን ልበል ይሆን... ከታሪካችን አንድ ሰበዝ እንምዘዝ እስቲ፤ ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበረችው ኢትዮጵያዊቷ/አክሱማዊቷ ንግሥተ ሳባ/አዜብ እስራኤላዊውን ንጉሥ ሰለሞንን ለመጎብኘት ወደ ኢየሩሳሌም በሄደችበት ጊዜ ብዙ አጀብ አስከትላና በርካታ ውድ ገጸ-በረከት/ስጦታን ይዛ ነበር። ከእነዚህ ገጸ-በረከቶች መካከልም፤ ወርቅ፣ ዕንቁ፣ የከበሩ ድንጋዮች፣ ሽቱ፣ ልዩ ልዩ መዓዛ ያላቸው ለሽታና ለግንባታ የሚሆኑ ውብና ጠንካራ እንጨቶች... ይገኙበታል። (መጽሐፈ-ነገሥት ፲፤፲)። መጽሐፍ ቅዱስ፤ ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሳባ ለንጉሥ ሰለሞን ይዛ ስለሄደችው ስጦታ መጠንና ዓይነት ሲናገር፤ ከዛም በፊት ሆነ ከእርሷ በኋላ ለንጉሥ ሰለሞን እንዲህ ዓይነት ስጦታ ተመጥቶለት እንደማያውቅ በአድናቆት ተጽፎአል። እንግሊዛዊው የታሪክና፣ የፖለቲካ ምሁር/ጸሐፊ ዊሊያም ባጅ ደግሞ ከዛሬ 50 ዓመት በፊት፤ "Queen Sheba and Her Only Son Menilik" በሚል ርእስ በጻፈው የዳጎሰ መጽሐፉ፤ "... ንግሥተ ሳባ ለንጉሥ ሰለሞን ይዛ የሄደችውን የስጦታ መጠን በዘመኑ የዋጋ ስሌት መጠን 25 ሚሊዮን ፓውንድ እንደሚገመት፤" ጽፏል። ይሄ ስሌት ከዛሬ 50 ዓመት በፊት መሆኑን ልብ ይሏል። በዛሬው የዋጋ ጣሪያና የፓውንድ ምንዛሬ ስናሰላው የአገራችንን የዓመት በጀት በእጥፍ የሚያስከነዳ ይሆናል። እንግዲህ በዘመኑ ኢትዮጵያውያን/አክሱማውያን ምን ያህል ሀብታምና ታላቅ እንደነበሩና ዛሬ ግን የት እንዳለን ቆም ብለን ማሰብ ነው። በሌላ በኩልም፤ እንደዛሬው ጠበን ጠበን በጎሳና በጎጥ ተከፋፍለን...የእናንተና የእኛ መሬት እያልን በመገዳደል የዓለም መሳለቂያ ከመሆናችን በፊት የቀደሙት ኢትዮጵያውያን/አክሱማውያን ሰውን በሰውነቱ ብቻ የሚያከብሩ ታላቅ ሕዝቦች ነበሩ። አሁንም ዳግመኛ ዓለም ካወቀው፤ ጸሐይ ከሞቀው ታሪካችን እንምዘዛ፤ በዘን ዘመን የነበሩትኢትዮጵያውያን/አክሱማውያን፤ የነቢዩ መሐመድን ተከታዮች/ሱሃባዎችን በምድራቸው በሰላም ተቀብለው ሲያስተናግዱ፤ ከግሪክና ከሮም ተሰደው የመጡ ተሰዓቱ/፱ኙን መነኮሳት/ቅዱሳንን በግዛታቸው በፍቅር ተቀብለው ሲያስጠልሉ፤ ግብፃውያኑን አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን የሃይማኖታቸው ሐዋርያ ሲያደርጓቸው፤ የኦሮሞ ሕዝብም እኚህን ቅዱስ አባት አቡዬ/አባታችን በማለት በፍቅር ቃል ሲጠሯቸውና ሲያከብሯቸው መለኪያቸው ዘር/ጎሳ/ብሔር ሳይሆን ፍቅር፤ ሰውነት/ሰው መሆን ብቻ ነበር። እንግዲህ መስቀሉ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የሰላም ምልክትም አይደል... ታዲያ ጥንታውያኑ ኢትዮጵያውያን ቅዱስ መስቀሉን በቃል ብቻ ሳይሆን በተግባር ጭምር የዘከረ እንዲህ ዓይነቱን አኩሪ ታሪክ ትተውልን አልፈዋል። ወደቀደመው የመስቀል ጥንተ ታሪክ ጉዳይ ስንመለስም፤ አክሱማውያን ክርስትናንን ከተቀበሉ በኋላ ከግሪክ አማልክት ወደ ክርስትና ፊታቸውን በመመለስ መስቀልን ምልክታቸው ኢየሱስ ክርስቶስን ደግሞ አምላካቸው አደረጉ። ነገሥታቱ በዘመቱበት የጦር ግንባር ድል ባደረጉበት ጊዜ ሁሉ፤ "በመስቀል ምልክት፤ በአምላካቸውና በጌታቸው በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ድል ማድረጋቸውን!!" የሚዘክር የድንጋይ ላይ ጽሑፍን አስቀርተውልናል። ከእነዚህም መካከል፤  ታዋቂዎቹን "የኢዛና ኢንስክሪፕሽን እና የአዶሊስ ኢንስክሪፕሽንን" የድል ዜናን የሚዘክሩት በግሪክ፣ በግዕዝና በሳባውያን ቋንቋዎች የተጻፉት የአክሱም ነገሥታት የድንጋይ ላይ ሐውልቶች ሺሕ ዘመናት የተሻገረውን ታሪካችንን ለዓለም እየተናገሩ ሕያው ምስክር ሆነው በታሪካዊቷና በጥንታዊቷ የአክሱም ከተማ ዛሬም ድረስ ቆመው ይታያሉ። በዚህ ታሪካችን ላይ ተጨማሪ ለማወቅ/ለማንበብ ለምትሹ ማስረጃ ላጣቅስ፤ ከ120 ዓመታት በፊት የጀርመንን የታሪክና የአርኪዮሎጂ የጥናት ቡድንን በመምራት በዳግማዊ ዐጤ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ የመጡትና የአክሱምን ታሪክ ለዓለም ያስተዋወቁት፤ የDeutsche Aksum Expidition የታሪክና የአርኪዮሎጂ ጥናት ቡድን ከሆኑት ውስጥ፤ the Leading Orientalist Eno Litmman, Architect Daniel Krencker, Photographer and Draughtsman Thedor von Lupke and Physician Erich Kaschke በአክሱም ከተማ ባደረጉት የአርኪዮሎጂ ጥናት በቁፋሮ የመስቀል ምልክት የተቀረጸባቸውን የወርቅ ሳንቲሞችን አግኝተዋል። እነዚህ የታሪካችን ሕያው ምስክሮች የሆኑ ሳንቲሞች በታላቅ ክብር- ልዩ ቅርስ ሆነው በብሔራዊ ሙዚየም እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ኢትኖግራፊክ ቤተመዘክር/ሙዚየም ይገኛሉ። ከአክሱማውያን በኋላ የመጡ ኢትዮጵያውያን ነገሥታት መስቀልን ይጠቀሙ እንደነበርም በርካታ የታሪክ ማስረጃዎች አሉን። የቀደምት ነገሥታት ማኅተም በመስቀል ቅርጽ ሆኖ በአራቱ ማዕዘን ‹‹ኢየሱስ›› የሚል ስም ይጻፍበት ነበረ፡፡ ከዘመነ መሣፍንት ታላላቅ መሪዎች መካከል ሣህለሥላሴ መስቀልን ምልክት ያደርጉ ነበር፤ በመዓዝናቱ ኢየሱስ፣ አንዳንዴም ኢየሱስ ክርስቶስ እያሉ ጽፈውበታል፡፡ ከአክሱም ዘመነ መንግሥት የአንደኛው ንጉሣችን ስም ገብረ መስቀል ነበረ፡፡ የላሊበላ ሚስት ስም መስቀል ክብራ ነው፡፡ የዐፄ ይስሐቅ ስመ መንግሥትም ገብረ መስቀል ነው፡፡
Show all...