cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

#Official je ❤

Well come To gate daily Love poems❤ music❤ Vine❤ broken heart 💔 tik tok❤ my photo oll my friend picture❤ Everything For any comment 👇 @jeeye Join& share @Jeriyeeeee

Show more
Advertising posts
203
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
-330 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ለወዳጅህ ሀዘንህን አሳየው ! ነገር ግን ለጠላትህ ስኬትህን እና ደስታህ አቋድሰው ። ምክንያቱም፦ወዳጅህ ማንነትህ ነው ጠላትህ ግን ስብራትህ ነው። እዮሪታ 👈🌹💝✍
Show all...
..........እዚህ ምድር ላይ አንዳንድ ሰዎች አሉ .......ለነፍሳችሁ ክሽን ያለች የቀይ ወጥ እንጀራ ፍትፍት የሆኑ........ ..........ትንሽ ደግሞ ጭልም ሲል እንደ ጠዋት ፀሀይ ፍክት የሚሉ....... የተሰበርንበት ቦታ ላይ ጥግን አድርገው ወጌሻ የሚሆኑ....... እንደዚህ አይነት ሰዎች እንዲኖሯችሁ ፈልጉ .............ካሏችሁ ደግሞ እንደ እንቁ ያዟቸው እንደዚህ አይነት ሰዎች........... እያወቃችሁ በገሃድ .......እናንተ ሳታውቁ ደግሞ በድብቅ ደጀን ናቸው!! ......... እነዚህ ሰዎች ናቸው በሌላችሁበት ስማችሁን የሚያስጠብቁ: ጋሻ ሆነው የሚከላከሉላችሁ........ ከወደዱት ቻናላችንን ይቀላቀሉ Join....✍️ t.me/Asresee         ....✍️ t.me/Asresee         ....✍️ t.me/Asresee
Show all...
ዝምታህ ሞኝነት፣ ትዕግሥትህም ቂልነት ሊመስላቸው ይችላል። 💠ፈቅደህ በተዋሃደህ ማንነት ቢዘባበቱብህ፣ በየዋህነትህ ምክንያት ጥለው ሊሻገሩህ ቢሞክሩ፣ በዝምታህ ምክንያት ሴራ ቢያሴሩብ እስኪያጠፉህ ግን አትጠብቅም፤ እስኪጫወቱብህ ግን ዝም አትልም። አዎ! ጀግናዬ..! አስመሳይነታቸውን ግታው፣ በደላቸውን አስቁም፤ እያየህ እንዳለየ፣ እያወክ እንዳለወክ ማለፉን ተው። እርምጃ መውሰድህ እራስህን ለመከላከል፣ እራስህን ለማዳን ብቻ አይደለም የእነርሱንም እውነተኛ ማንነት ለማጋለጥ ነው። መብትህን ሲጋፉ፣ ነፃነትህን ሲገፉ፣ አንተነትህን ሲያዋርዱ፣ ማንነትህን ሲያንቋሸሹ፣ ክብርህን ሲያረክሱ፣ ስብዕናህን ሲያሳንሱ ትዕግስትህ መፈተኑ፣ ስሜትህም መነካቱ አይቀርም። ነገር ግን እያንደንዱ ተግባር የእራሱ ገደብና ልኬት አለው። ከቀይ መስመርህ ባሻገር የሚመጣብህን ጫናና በደል የመጋፈጥ፣ የመመለስ የውዴታ ግዴታ አለብህ። ሚዛናዊ መሆንህ ቢያስከብርህ እንጂ አያዋርድህም፣ ቢያስሞግስህ እንጂ አያሳንስህም። እያወቁ አለማወቅም ገደብ አለው፣ በእራስ ማንነት ሲቀለድ ዝም ማለት አንድ ቀን ዋጋ ማስከፈሉ አይቀርም። አዎ! ማብቂያ አብጅለት፤ ለሚደርስብህ የትኛውም አይነት እንግልትና ነቀፋ፣ ለሚወረወርብህ ክብረ ነክ ተግባር ፍፃሜ ስጠው። እራስህን ባታስከብር የሚያከብርህ አይኖርም፣ ለእራሰህ ባታስብ የሚያስብልህ የለም። ዋጋ የምትከፍለው ለእራስህ ብለህ ነው፤ ከወዳጅ መሳይ ተጣቶችህ የምትርቀው ለክብርህ፣ ለደህንነትህ ብለህ ነው። ከአስመሳዮች ተነጠል፣ የሚጠቅሙህ መስለው ዋጋህን ከሚያሳንሱ፣ ጥቅምህን ፈልገው ከተቆራኙህ፣ በወዳጅነት ሰበብ ከሚጫወቱብህ፣ በበግ ለምድ ከተሸፈኑ አታላዮች እራስህን አድን። በየዋህነትህ መጎዳት፣ በቅንነትህ መሰበር ይብቃህ፤ በልበሙሉነት ቀና ብለህ እራስህን ማስከበር፣ ለእራስህም ተገን መሆን ጀምር።
Show all...
** 👉ከጎንህ ያለችው ሚስትህ.. የላጤዎች ሁሉ ምኞት ናት። 👉ደስተኛ ያልሆንክበት ልጅህ.. መውለድ የማይችሉ ሁሉ ምኞት ነው። 👉ትንሿ ቤትህ.. ቤት ላጡ ሁሉ ምኞት ናት። 👉አድካሚ ስራህ.. ስራ ላጡ ሁሉ ምኞት ነው። 👉ትንሿ ገንዘብህ.. ምንም ገንዘብ ለሌላቸው ሁሉ ምኞት ናት። 👉በገንዘብ የማይተመነው ጤናህ.. ጤንነት አተው ለሚሰቃዮ ምኞት ነው። 👉በነጻነት በእግርህ መጓዝህ.. እስር ቤት ሆነው ለሚሰቃዮ ምኞት ነው። 👉ፈጣሪ የደበቀልህ ነገር.. ተዋርደው ላፈሩ ሁሉ ምኞት ነው።     ፈ ጣ ሪ ተ መ ስ ገ ን 🙏 መልካም አዳር ይሁንላችሁ!! @Asresee @Asresee
Show all...