cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ለውጥ

ዉድድርህ ከሰዎች ጋር አይደለም! ዉድድርህ:- ✓ ከገደልከዉ ሰአት ✓ ከፈጠርከዉ በሽታ ✓ መማር እያለብህ ችላ ካልከዉ እዉቀት ✓ መስዋእት ካረከዉ ጤናህ ✓ አዲስ ሃሳብን አልቀበልም ካልከዉ ማንነት ✓ ያንተን መጣር ከማይወዱ ሰዎች ✓ እድለ ቢስ እንደሆንክ ከሚነግርህ ሰይጣን ጋር ነዉ” creator @fuOzi

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
809
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

Show all...
🇱 🇾 🇷 🇮‌🇨 🇸

You can get any type of ★★Music ★★Lyrics ★★Celebreties pic ★★ " Biography Her send your suggestion ☞☞ ☞☞ @fuOzi

📚 📚 #ለውጥ 📚 📚 🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን 🙏 ህፃኑ ልጅ ወደ አንድ ፋርማሲ ይገባና አንድ ባዶ ካርቶን ፈልጎ ያመጣል፡፡ በመቀጠል ካርቶኑ ላይ ቆሞ የተሰቀለውን የግድግዳ ስልክ አንስቶ ደወለ፡፡ የፋርማሲው ባለቤት የህፃኑን እንቅስቃሴ እየተከታተለ ነበር፤ በስልክ የሚያወራውንም እያዳመጠ ነበር፡፡ ህፃኑ :- " እህት የግቢሽን ሳር የመከርከም ስራ ተሰጪኛለሽ?" ሴቲቱ ፡- (በስልኩ በሌላኛው ጫፍ ያለችው) "ሳሮቹን የሚከረክም ሰው አለኝ" ህፃኑ ፡- "ሳሮቹን አሁን የሚከረክምልሽ ሰው ከሚያስከፍልሽ በግማሽ ቀንሼ እኔ እከረክምልሻለሁ" ሴቲቱ ፡- "አሁን ሳሮቹን በሚከረክመው ሰው በጣም ደስተኛ ነኝ" ህፃኑ ፡- በበለጠ ትጋት " እህት በተጨማሪ የጎንዮሽ መንገዶችን እና መታጠፊያዎችን እጠርግልሻለሁ፡፡ በዚህም የተነሳ እሁድ እሁድ በግቢ ውስጥ ለመንቀሳቀስ በጣም የሚያምር የግቢ መስክ ይኖርሻል፡፡" ሴቲቱ ፡- "አይ አሁን ባለኝ ሰራተኛ ደስተኛ ነኝ፤ አመሰግናለሁ፡፡" ህፃኑ በፈገግታ ስልኩን ዘጋና ከቆመበት ካርቶን ላይ ወረደ፡፡ የህፃኑን ሙሉ ንግግር ሲያደምጥ የነበው የፋርማሲው ባለቤት ወደ ህፃኑ መጣ፡፡ ባለቤቱ ፡- "ልጄ ፀባይክን ወድጄዋለው፤ ያለክ መልካም ተነሳሽነት ደስ ስላለኝ ስራ ልሰጥክ እፈልጋለው፡፡" ህፃኑ ፡- " አይ አመሰግናለሁ፡፡" ባለቤቱ ፡- " ግን እኮ ስራ ለማግኘት እየለመንክ ነበር?" ህፃኑ ፡- "አይደለም ጌታዬ፤ የተቀጠርኩበት ስራ ላይ ያለኝን እንቅስቃሴ እየገመገምኩ ነበር፡፡ ሴትዮዋ ሳሮቹን የሚቆርጥልኝ ሰው አለ ያለችው እኔን ነው፡፡ በስራዬ ደስተኛ ናት ወይስ ደስተኛ አይደለችም የሚለውን ለማወቅ ነው ሌላ ሰው መስዬ የጠየኳት " #ጭብጥ ፡- ሁሌም ቢሆን ከሌሎች አንድ እርምጃ ቀድመን ካልተገኘን ለሚገጥመን ችግር ሌሎችን መውቀስ እንጀምራለን፡፡ ሁሌም ቢሆን እራሳችንን ነው መመልከትና ማወዳደር የሚጠበቅብን፡፡ ድክመታችንን በማወቅ ጠንክረን መስራትና ድክመታችንን አርቀን መጣል አለብን፡፡ ሁሌም ቢሆን ጠንክረን እንስራ፤ ተማኞች እንሁን፤ ለዓላማችን ሙሉ ተኩረታችንን እንስጥ፤ መልሶ ይከፈለናል እና፡፡ ✅share ማድረግ እንዳይረሳ! 👇👇 👇👇 📚 📚 #ለውጥ 📚 📚 #ከኛ_ብዙ_መልካም_ነገሮችን_ያገኛሉ !! ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👇👇👇 ✍ @fuOzi Join us 👉 @fuOzilewte @fuOzilewte @fuOzilewte
Show all...
👍 31
👎 4
📚 📚 #ለውጥ 📚 📚 🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን 🙏 የሚሞትለት አላማ የሌለው ሰው ለመኖር ብቁ አይደለም። ማርቲን ሉተርኪንግ እውነት ነው ሰው ለመኖር ብቁ የምንሆነው የሚሞትለት መክሊት ፤ትልቅ ራዕይ ፤ስኬት ሲኖር ነው። ምንድነው የምንሞትለት ህልማችን ምንድነው?? መክሊታችን ውስጣችን የተቀበረው ታምር ምንድን ነው። ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ቁም ነገር ሰርተህ አሻራህን ጥለህ የማይሞት ማንነትን ተክለህ እለፍ ማለት ነው እንጂ። ካነበብኩት የወደድኩት ድንቅ  የህይወት ታሪክ ለምጣዱ ሲባል...! አንዲት ሴትዮ ጓዳቸው ውስጥ እየተንጎዳጎዱ ድንገት አንዲት አይጥ ምጣዳቸው ላይ ትወጣለች ወንድ ልጃቸው እንጨት ያነሳና አይጧን ለመምታት ሊሰነዝር ሲል ሴትየዋ አስቆሙትና <ልጄ አይጧን ስትመታ እንጀራ ማብሰያችንን ምጣዶን ሰበርከው ማለት ነው ስለዚህ እስኪ ግድ የለም ለምጣዱ ሲባል አይጧን ዝም እንበላት> አሉት አሉ፡፡ #ጭብጥ ሁሌም ለምንፈልገው ነገር ስንል ብዙ ነገሮች መታገስ እንዳለብን፤ከድርጊት በፊት አስተውለን መወሰን እንዳለብን እንረዳለን። ✅share ማድረግ እንዳይረሳ! 👇👇 👇👇 📚 📚 #ለውጥ 📚 📚 #ከኛ_ብዙ_መልካም_ነገሮችን_ያገኛሉ !! ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👇👇👇 ✍ @fuOzi Join us 👉 @fuOzilewte @fuOzilewte @fuOzilewte
Show all...
👍 16
👎 2
📚 📚 #ለውጥ 📚 📚 🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን 🙏 መልካም ውጤት የሚገኛው ይቅርታ በማድረግ ብቻ ነው ። በተለይ የሰው ልጅ በድክመቱ ሳይሆን ሃይልና ብቃቱ እያለው መበቀል እየቻለ ለፈጣሪ ብሎ ማለፍ ከቻለ እውነተኛ አሸናፊ ይሆናል ። ምክንያቱም ለፈጣሪ ብሎ በይቅርታ ማለፍ የነብያትና የታላላቅ ሰዎች ባህሪ ነውና ። ✅share ማድረግ እንዳይረሳ! 👇👇 👇👇 📚 📚 #ለውጥ 📚 📚 #ከኛ_ብዙ_መልካም_ነገሮችን_ያገኛሉ !! ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👇👇👇 ✍ @fuOzi Join us 👉 @fuOzilewte @fuOzilewte @fuOzilewte
Show all...
👍 12
👎 1
📚 📚 #ለውጥ 📚 📚 🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን 🙏 ወጣቱ ልጅ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪውን በሆነ ሰርግ ላይ ያየዋል። ሮጦ ሄዶ በትህትናና በአድናቆት ሰላም ካለው በኃላ "አስታወስከኝ ወይ?" አለው። አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "ይቅርታ አላስታውስኩህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" በማለት መለሰለት፡፡ ወጣቱም ልጅ እንዲህ እያለ ተረከለት "3ኛ ክፍል እያለን ያንተ ተማሪ ነበርኩ። ታዲያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ሰዓቱን ሰርቄበት ነበር። እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀበት ላንተ ይናገራል፤ አንተም መጥተህ ልትፈትሸን ሁላችንም ክፍል ውስጥ ያለን ልጆች አይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አድርገን ፊታችንን ወደ ግድግዳ አዙረን እንድንቆም አዘዝከን። በዛን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት እያሰብኩ በጣም ተረበሽኩ፤ የሚገባበትን አጣሁ። አስበው ሰዓቱ በኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ስሰድበኝ፤ ግቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ስሆን፤ ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄን አሳፋሪ ድርጊቴን ሲሰሙ። በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ሲገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰመኝ፤ በቃ መጥፎ ዜናውን ልነገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ምንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ ጋር እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ። ፍተሻውም ሲያልቅ አይናችሁን ግለጡና ወደየቦታችሁ ተመለሱ አልከን። እኔ ግን መልሰህ ታስቆመኛለህ ብዬ መቀመጡን ፈራሁ። በጣም የሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት፤ ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኘህና ማን እንደሰረቀበት ምንም አልተናገርክም ነበር። በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠረ ማንም አላወቀብኝም ነበር፤ አንተም ምንም ብለኸኝ አታውቅም። እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳደንክና ስብዕናዬን እንደጠበክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውስሃለው። አንተም ይሄን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገምትም አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው። አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለው በማን ኪስ ውስጥ እንዳገኛሁ ግን አላስታውስም፤ ምክንያቱም እኔም ስፈትሻችሁ የነበረው አይኔን ጨፍኜ ነበር!!"አለው። #ጭብጥ በህይወታችን ለሚናከናውናቸው ነገሮች ሁሉ ጥበብ ያስፈልገናል። እንደ አስተማሪ እንደ ወላጅ እንደ መሪ...ወዘተ ለአንዳንድ ነገሮች አይናችንን መጨፈን አለብን ምክንያቱም ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙም!!! ✅share ማድረግ እንዳይረሳ! 👇👇 👇👇 📚 📚 #ለውጥ 📚 📚 #ከኛ_ብዙ_መልካም_ነገሮችን_ያገኛሉ !! ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👇👇👇 ✍ @fuOzi Join us 👉 @fuOzilewte @fuOzilewte @fuOzilewte
Show all...
👍 18
👎 4
📚 📚 #ለውጥ 📚 📚 🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን 🙏 #የወፏ__ምክር አንድ ሰው አንዲት በጣም ቆንጆ ወፍ በመዳፉ ውስጥ ይዞ ጨምቆ ሊገድላት ሲል ከመሞቷ በፊት አንድ ወይም ሁለት ቃላት ትናገር ዘንድ እንዲፈቅድላት ጠየቀችው፡፡ እንዲህም አለች “እባክህ አትግደለኝ፡፡ ሶስት ጠቃሚ ምክሮችን እሰጥሃለሁ፡፡ የመጀመሪያው ምክር፤ በእጅህ ያለውን ነገር አትልቀቅ፡፡ ሁለተኛው ምክር፤ ስለሆነው ነገር ሁሉ አትቆጭ፡፡” ካለችው በኋላ ዝም አለች፡፡ ሶስተኛውንም ምክር ትነግረው ዘንድ ሲጠይቃት “ሶስተኛው ምክር ለልጆችህና ለልጅ ልጆችህ በጣም ጠቃሚ ስለሆነ ካለቀከኝ አልነግርህም፡፡” አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ ሰውየው ሶስተኛውን ምክር ለመስማት በጣም ጓጉቶ ስለነበረ ወፏን ሲለቃት ከአንድ ዛፍ ላይ በርራ ወጥታ “ምንድን ነበር ያልኩህ? ታስታውሳለህ?” ብላ ጠየቀችው፡፡ እርሱም “በእጅህ ያለውን ነገር አትልቀቅ ነው ያልሺኝ፡፡” አላት፡፡ “ሁለተኛውስ?” “ስላለፈው ነገር ሁሉ አትቆጭ፡፡” “አዎ፡፡ ነገር ግን የነገርኩህን ነገር አልተቀበልክም፡፡ ባትለቀኝ ኖሮ ከሆዴ ውስጥ ለልጅ ልጆችህ የሚሆን ወርቅ ታገኝ ነበር፡፡ ይኸው ነው፡፡” አለችው፡፡ ሰውየው “ሶስተኛውስ ታዲያ?” አላት፡፡ እሷም “ሶስተኛው የሁለተኛው ምክር ድጋሚ ነው፡፡ ስላጣኸው ነገር አትቆጭ፡፡ ይኸው ነው፡፡ ደህና ሁን፡፡ ምክሬንም ባለመቀበልህ በድህነት ትኖራለህ፡፡” አለችው፡፡ ✅share ማድረግ እንዳይረሳ! 👇👇 👇👇 📚 📚 #ለውጥ 📚 📚 #ከኛ_ብዙ_መልካም_ነገሮችን_ያገኛሉ !! ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👇👇👇 ✍ @fuOzi Join us 👉 @fuOzilewte @fuOzilewte @fuOzilewte
Show all...
👍 12
👎 1
ተመልሻለሁ አላቹልኝ አ ውዶቼ በጣም ይቅርታ ስለጠፋሁ ከአሁን በሗላ የጠፋሁበትንም ጊዜ ክሳቹአለሁ እስኪ ለውጥ የናፈቃቹ ❤️❤️ ✍ 👉 @fuOzi
Show all...
❤ 24
📚 📚 #ለውጥ 📚 📚 🙏 ሰላም ለእናንተ ይሁን 🙏 ኔልሰን ማንዴላ ፕሬዝደንት ከሆኑ በኋላ አንድ እለት ከቅርብ ጠባቂዎቻቸው ጋር ለምን በእግራችን ወጣ ብለን አንንሸራሸርም በዛው ምሳ እንበላለን ብለዋቸው ተያይዘው ወጡ። አንድ ሞቅ ያለ ሰፈር ሲደርሱ ምግብ ቤት አግኝተው ከጠባቂዎቻቸው ጋር ገብተው እንዳዘዙ ከፊት ለፊታቸው ያዘዘው ምግብ የዘገየበት አንድ ሰው ስላዩ "ጥሩትና ከእኛ ጋር ይብላ"ብለው አንዱን ወታደር ላኩ። ሰውየው መጥቶ አብሯቸው ተመገበ። እየተመገበ ሳለ እጁ ይንቀጠቀጣል፤ ጨርሶ ሲሄድ ከጠባቂ ወታደሮቹ መሃል አንዱ "ማዲባ የቅድሙ ሰውዬ ህመምተኛ ነበርኮ እጁ ይንቀጠቀጥ ነበር" ይላቸዋል "አይደለም! ድሮ የታሰርኩበት እስር ቤት ጠባቂ ዘበኛ ነበር። ብዙ ግዜ ተደብድቤ ከቶርች ስመለስ ውሃ ስለሚጠማኝ ውሃ እንዲሰጡኝ በጩኽት ስጠይቅ ይሄ ሰው ይመጣና ፊቴ ላይ ሽንቱን ይሸናል። አሁን የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት ሆኜ ሲያየኝ የምበቀለው መስሎት ፈርቶ ነው" አሉት፡፡ ሀገር በመቻቻል እና በፍቅር እንጂ በቂም በቀል አትገነባም። ደካሞች ይቅርታን አያውቋትም፤ ይቅርታ የጠንካሮች መለያ ባህርይ ናትና!!! በተቻለን መጠን የበደሉንን ሁሉ እረስተን በሰላም የምንውልበት ቀን ይሁንልን፡፡ ምንጭ፡- የይቅርታና የምስጋና ገፅ ✅share ማድረግ እንዳይረሳ! 👇👇 👇👇 📚 📚 #ለውጥ 📚 📚 #ከኛ_ብዙ_መልካም_ነገሮችን_ያገኛሉ !! ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት 👇👇👇 ✍ @fuOzi Join us 👉 @fuOzilewte @fuOzilewte @fuOzilewte
Show all...
👍 29
👎 6
ጋሽ ስብሀት ገ/እግዚአብሔር ስለ እስልምና ምን አለ?! (አንብበው ለሌሎችም ያካፍሉ!) … ① "ኢስላም ሀይማኖት ከቆሻሻ መንፃት ነዉ…በቀን አምስት ግዜ የሚታጠብ ማንም የለም። እናንተ ሙስሊሞች ግን በዉሀ ትጥበት አምስት ግዜ ትነፃላችሁ…ከዛ ደግሞ በሰላት ልብና ህሊናችሁን በመንፈሰ ዉሀ ታጥባላችሁ…መስጊዳችሁ በሽቶና በጥሩ ማአዛ ይታወዳል… ነጭ ሽንኩርት የበላ፣ ካልሲዉ ሚገማ ሙስሊም መንፈሳዊዉን ኔቶርክ እንዳያዉክ ሲባል …አይደለም መስጂድ ዉስጥ ሊሰግድ ደጃፉ ላይም አይደርስም። ግሙን ራሱ ይጠጣት ተብሎ ተፈርዶበታል። እና የሱን ግም ማን እንዲጠጣለት ይፈልጋል?!" … ② "ሌላዉ አንድ ሰዉ እስላም ለመሆን ከፈለገ መጀመሪያ ሻሀዳ ማለት አለበት። በፍጡር ክዶ ለፈጣሪ እገዛለሁ ማለት አለበት። ሼኪ ፍጡር ነዉ፣ነብዩ መሀመድም ፍጡር ነዉ፣ ጅብሪል ፍጡር ነዉ፣ ፈጣሪ አላህ ብቻ ነዉ፣ እሱን ካወክ.. በመቀጠል ለሰላት ከመቆምክ በፊት ግምህን ሁሉ ትታጠባለህ …ከዛ ለሰላት ትቆማለህ። ፈስህን ካንዛረጥክ ድጋሚ ትታጠባታለህ .…በቃ እስላም ጋር ግም ነገር ጥዩፍ ነዉ። ጥርስ መፋቅ እንደስግደቱ ሁሉ ግዴታ ነዉ!" … ③ "እስላም ጋር ግብረስጋ ግንኙነት ነዉር አይደለም። ነዉሩ ዝሙት ነዉ እንዲያዉም ሚስትህን ስትገናኝ ላንተም ለሚስትህም የፅድቅ ምንዳ ይሰጥካል …ሰላት ስትሰግድ ምፅዋት፣ለነዳያን ስትመፀዉት እንደምትፀድቀዉ ሚስትህ ጋር ስትገናኝም ትፀድቃለህ …ለምን ካልክ ዝሙት ብትሰራ ወንጀል ይፃፍብካልም አይደል …'ለጨዋ ጉርሻ ለባለጌ አለንጋ' ይገባዋል ይላል ኢስላም…" … ④ "አንድ ሀብታም እስላም ለደሀ ቤት ሰርቶ ቢፀድቅ…ደሀዉ ደሞ ሙዝ ልጣጭ ከመሬት ላይ አንስቶ ሰዉ እንዳይጥል በማድረጉ ይፀድቃል …። በእስላም ደሀዉም ሀብታሙም ፅድቅ ስራ ለማፃፍ ሁለቱም እኩል እድል አላቸዉ። አንደኛዉ ከአንደኛዉ የተሻለ አድቫንቴጅ የለዉም ሀብታሙ ለሚስቱ ወርቅ ገዝቶ ቢያስደስታት ፃድቅ ተብሎ ይፃፍለታል። ደሀዉ ምን አናደደዉ ሚስቱን ግንባሯን ስሞ አንድ ጉርሻ ጠቅልሎ ቢያጎርሳት እሱም እንደሀብታሙ ፃድቅ ተብሎ ይፃፍለታል…" … ⑤ "የመፅሀፍ ቅዱስ የመጀመሪያው ምዕራፍ ዘፍጥረት ነዉ። የቁርዐን ደግሞ መጀመሪያ ለሰዉ ልጆች የቀረበዉ ጥሪ አንብብ! አንብብ ! አንብብ ! በፈጠረህ ጌታ ስም ይሁንብህ። የሚል ለሰዉ ልጆች የቀረበ ልመና ነዉ…የጌታህን የአንብብ ተማፅኖ ተቀብለህ ካነበብክ ባያንዳንዷ ቃል ሳይሆን ያነበብከዉ ፊደል ተቆጥሮልህ የፅድቅ ምንዳ ትንበሻበሻለህ።" … ⑥ "እስላም ለዕዉቀት ሲል ማይታመን ድርድር ዉስጥ ይገባል። በርካታ ሙስሊሞችን የገደሉ አይሁዶችን ማርኮ የቀጣዉ ቅጣት ምን ይመስልካል…?? መፃፍና ማንበብ ማይችሉ ሙስሊሞችን አስተምሮ ከምርኮ ነፃ መዉጣት። የጌታ ሰላምና ምህረት በረከት ከንፁህ ሙስሊሞች ጋር ይሁን አሜን!!" ጋሽ ስብሃት ገ/እግዚአብሔር
Show all...
👏 19
እስልምና ለኢትዮጵያ! «ዘውድአለም ታደሠ» ክርስቲያን ነኝ። ለክርስቶስ የተለየ ፍቅር አለኝ። ክርስቶስን እንዳመንሁ መኖር ብቻ ሳይሆን እንዳመንሁ መሞት ነው ፍላጎቴ። ነገር ግን የኢትዮጵያን ሙስሊም እወዳለሁ ብቻ ሳይሆን እጅግ እደነቅበታለሁ። ሁሌም እንደምለው የኢትዮጵያ ሙስሊም ለኢትዮጵያ ተስፋ ነው ብዬ አምናለሁ። ይሄን ምፅፈው ወዳጅ ለማብዛት አይደለም በዚህ ሃሳብ ከወዳጄ ይልቅ ብዙ ጠላት እንደማፈራ አይጠፋኝም። ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን ሐገር ነች። የክርስቲያንም ሆነች የሙስሊም አይደለችም። ኢትዮጵያ ከሶስት ሺ አመት በላይ ታሪክ አላት፣ ከእስልምና ቀድሞ ወደኢትዮጵያ የገባው ክርስትና ግን ከተመሰረተ እንኳ ሁለት ሺ አመቱ ነው። በዚህ አመክንዮ ብቻ ከሄድን ኢትዮጵያ ሁለቱም ሃይማኖቶች ወደሐገር ከመግባታቸው ቀድማ ስለነበረች ኢትዮጵያን ለአንድ እምነት በባለቤትነት መስጠት ስህተት ይሆናል። አንድ የማንክደው ሃቅ ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት እኩልነት ከመከበሩ አስቀድሞ ሙስሊሙ በእምነቱ የተነሳ ብቻ ያልደረሰበት በደልና እንግልት አልነበረም። ራሳቸውን በአንድ እምነት ካባ ውስጥ ከልለው የገዙት አፄዎች ዘመን ሙስሊሙ ኢትዮጵያዊ በፖቲካም ሆነ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ድርሻ እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም። ይህ ሁሉ ሆኖም ግን አሁን ያለው የሙስሊም ማህበረሰብ ታሪክን እየጠቀሰ ኢትዮጵያዊነቱ ላይ ሲደራደር አናይም። አሁን አሁን ደሞ ከምእራባውያን ሚዲያ የወረስናት ኢስላሚክ ፎቢያ ሐገራችን ገብታ በአንዳንድ ሰዎች አንደበት ስትለፈፍ ስሰማ ይገርመኛል። የሆኑ ዱርዬዎች ተሰብስበው በተስኪያን ሲያቃጥሉ እስልምናን ከዱርዬዎቹ ጋር የማያያዝ ፍረጃ ቢሰማም በአንዳንድ ቦታዎች መስኪድ ሲቃጠል ግን የእስልምና አመራሩ ከክርስቲያኑ ቀድሞ «ይሄ ተግባር ክርስትናን አይወክልም» የሚል መግለጫ በማውጣት የሞራል ከፍታውን አሳይቷል። ጃዋርን ከእስልምና ጋር የሚያያይዝ ብዙ አላዋቂ ቢኖርም ፀጋዬ አራርሳን ግን ከክርስትና ጋር የሚያይዝ ሙስሊም አላየሁም። እምነቱን ከፖለቲካና ዘር ጋር ቀይጦ የሚያራግብ ብዙ ሰው አይቻለሁ። ሙስሊሙ ግን አንድም ቀን «የሃይማኖት እኩልነት ይከበር» ከማለት በዘለለ ሃይማኖቱን ለፖለቲካ ፍጆታ ሲያውለው አላየሁም። እንደምናውቀው በሃገራችን ለተፈጠረ ፖለቲካዊ ለውጥም እንደቅርብ ፋናወጊ ሆኖ በአደባባይ አፈሙዝ ሳይፈራ የወጣ የተደራጀ ሙስሊም በሰላም ወጥቶ መብቱን ከመጠየቅ ባለፈ አንድም ኢሞራላዊ ተግባር ሳይፈፅም ለአመታት ድምፁን አሰምቷል። አብይ መጥቶ በአንፃራዊም ቢሆን የእምነት ጥያቄው መመለስ ሲጀምር ሰላማዊ ጥያቄውን ትቶ ከለውጥ ሃይሉ ጋር በሙሉ ልቡ ተሰልፏል። ይሄ እንግዴህ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ምን ያህል ምክኒያታዊና ጥያቄውን ጠንቅቆ የሚያውቅ እንደሆነ ያሳያል። አሁን እንኳ በአክሱም አካባቢ ያለው ጥያቄ ባይመለስለትም ባገኘው አጋጣሚ በእርጋታ ጥያቄውን ከመጠየቅ ባለፈ በሃይልና በግርግር ሃሳቡን ለማስፈፀም ሲሞክር አናየውም። ምንም እንኳ የአክሱም ሙስሊም ጥያቄ አንገብጋቢ እንደሆነ ቢያውቁም ሐገሪቱ ካለችበት ውጥንቅጥ አንፃር ሐገር እስክትረጋ ትእግስት ማድረግ የመረጡ ነው ሚመስለው። እንግዴህ ከዚህ በላይ ሐገር መውደድ፣ ከዚህ በላይ ለሐገር ማሰብ የለም! በግሌንኳ እንደታዘብኩት እዚህ ሶሻል ሚዲያ ላይ በአንፃራዊነት ዘረኝነትን አውግዘውና ተፀይፈው ስለአንድነት ሲሰብኩ የማያቸው በአብዛኛው ሙስሊሞችን ነው። ከግዜ አመጣሽ የዘር አምልኮና በፓስፖርት ከሚቀየር ቅፅል ማንነት ይልቅ የእምነታቸውን «ዘረኝነት ጥንብ ነች» የሚል መርህ እስከሞት ድረስ ለመጠበቅ ለራሳቸው ቃል የገቡ ነው ሚመስሉት። አክራሪ ሙስሊም የለም አላልኩም። ኢትዮጵያ የክርስቲያን ደሴት ነች ከሚለው አላዋቂ እኩል በእስልምና ካባ የሚንቀሳቀስ እስልምናን የማያውቅ ሙስሊም ይኖራል። እኔ ማወራህ ግን ስለብዙሃኑ ነው! ስለብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም! በተለያዩ አለማት ያሉ ሙስሊሞች ኢትዮጵያውያንን ሲያገኙ «ኢትዮጵያኮ የእስልምና ባለውለታ ነች» ይላሉ። አለም ሙስሊሞችን ሲያሳድድ ደጇን ከፍታ የተቀበለውችው ኢትዮጵያ መሆኗን እየጠቀሱ። እኔ ደሞ እንዲህ እላለሁ ... ኢትዮጵያ የሙስሊሞች ውለታ አለባት! ሙስሊም ኢትዮጵያውያንም ስጋት ሳይሆኑ ለአንድነታችንና ለኢትዮጵያዊነታችን ህያው ተስፋዎች ናቸው!! አዎ ሙስሊሞች ከሐገር ወዳድ ሌሎች ክርስቲያን፣ ፕሮቴስተሰንት፣ ካቶሊክ ፣ ጅሆቫ፣ ዋቄፋታ፣ እና ሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር ሆነው ኢትዮጵያን እንደሚታደጉ በፅኑ ተስፋ አደርጋለሁ። እስልምና ከዘርህም፣ ከማንነትህም ከሐገርህም በላይ ለእምነትህ ትዛዝ የምትገዛበት እምነት ነው። የትኛውም አማላይ የዘር ስብከት ከቁርአን ትእዛዝ ጋር ከተላተመ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ዘንድ ተቀባይነት የለውም። ይሄን ደግሞ ከአብዛኞቹ ሙስሊም ወዳጆቼ ያረጋገጥኩት ሃቅ ነው! ለዚህ ነው ቅዱስ ቁርአን «ጥንብ» ያለውን ዘረኝነት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች «ቅዱስ» ሲሉት የማናየው!!
Show all...
👏 10