cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

TlkVAH -ETH

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
1 450
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በአዲስ አበባ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው አንድ መቶ አስራ አምስት (115) ሰዎች ክፍለ ከተማ ፦ • አዲስ ከተማ - 18 ሰዎች • ጉለሌ - 10 ሰዎች • ቦሌ - 42 ሰዎች • ልደታ - 5 ሰዎች • ኮልፌ ቀራኒዮ - 13 ሰዎች • የካ - 5 ሰዎች • ቂርቆስ - 9 ሰዎች • ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 4 ሰዎች • አራዳ - 5 ሰዎች • አቃቂ ቃሊት - 2 ሰዎች * አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 2 ሰዎች አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ 1,625 ሰዎች ክፍለ ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል ፦ • አዲስ ከተማ - 428 ሰዎች • ጉለሌ - 211 ሰዎች • ቦሌ - 202 ሰዎች • ልደታ - 201 ሰዎች • ኮልፌ ቀራኒዮ - 154 ሰዎች • የካ - 90 ሰዎች • ቂርቆስ - 76 ሰዎች • ንፋስ ስልክ ላፍቶ - 72 ሰዎች • አራዳ - 69 ሰዎች • አቃቂ ቃሊት - 50 ሰዎች * አድራሻቸው በመጣራት ላይ ያለ - 72 ሰዎች #ሀረሪ በሐረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰኣት ውስጥ የተደረገው 48 የላቦራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 2 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በክልሉ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር አሰራ ሰባት (17) ደርሷል፡፡ የዕለቱ ታማሚዎች ተጋላጭነት ሁኔታ የታወቀ ንክኪ ያላቸው ሲሆን የ54 አመት ሴት የሀኪም ወራዳ ነዋሪ እና የ25 ወንድ ሲሆኑ የሽንኮር ወረዳ ነዋሪ ናቸው፡፡ #ደቡብ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ መንግሥት 476 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል አንድ (1) ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል። በኮሮና ቫይረስ መያዙ የተረጋገጠው የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሀዋሳ ነዋሪ ነው። ግለሰቡ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የሌለው ሲሆን በበሽታው መያዙ ከተረጋገጠው ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት (ንክኪ) እንዳለው የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጿል። #ትግራይ በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ሰባ ዘጠኝ (79) ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 207 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው ሰባት (7) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው። ከሰባቱ (7) መካከል ሁለቱ (2) የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ፣ ሶስቱ (3) ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት (ንክኪ) ያላቸው እንዲሁም የተቀሩት ሁለቱ (2) የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው። #Oromiyaa ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 519 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው ዘጠኝ (9) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው። የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦ ታማሚ 1 - የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሀረርጌ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው፤ በለይቶ ማቆያ የሚገኙ። ታማሚ 2 - የ10 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሀረርጌ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በለይቶ ማቆያ የምትገኝ። ታማሚ 3 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሀረርጌ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በለይቶ ማቆያ የምትገኝ። ታማሚ 4 - የ12 ዓመት ኢትዮጵያዊት የምስራቅ ሀረርጌ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በለይቶ ማቆያ የምትገኝ። ታማሚ 5 - የ42 ዓመት ኢትዮጵያዊ የሰንዳፋ ቤኬ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም ፤ በለይቶ ማቆያ የሚገኝ። ታማሚ 6 - የ3 ዓመት ህፃን ኢትዮጵያዊ የጉጂ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው። ታማሚ 7 - የ14 ዓመት ኢትዮጵያዊት የጉጂ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የላትም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላት። ታማሚ 8 - የ25 ዓመት ኢትዮጵያዊ የምዕራብ ወለጋ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የለውም፤ ከማህበረሰቡ የተገኘ። ታማሚ 9 - የ48 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው ድንበር ተሻጋሪ መኪና አሽከርካሪ (ምርመራው የተደረገው ነቀምቴ ላብራቶሪ ነው) የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉን መረጃ ቶሎ ይደርሶታል @covid_ethiopia @covid_ethiopia ለአስተያየት @covid_comment
Show all...
በ1999 (እ.ኤ.አ) ሚያንማር ውስጥ "ትያንትውና ኪን" የተባለ አንድ የፖለቲካ እስረኛ የአለምን ትኩረት ስቦ ነበር፡፡ ይህ እስረኛ ፓጉ ከተማ ውስጥ በሚያንማር መንግስት ላይ የተቃውሞ ሰልፉ ካደረጉ ሰዎች ውስጥ አንዱ የነበረ ሲሆን ፤ እስረኛውን ለየት ያደረገውና የአለም ክብረ ወሰንን ያጎናፀፈው ጉዳይ ግን ገና የ3 ዓመት ጨቅላ ህፃን መሆኑ ነው፡፡ በጣም ትንሹ የአለማችን የፖለቲከኛ እስረኛ ይኸው ትያንትውና ኪን የተባለው ጨቅላ ልጅ ነው፡፡ ይህም እድሜው በታሪክ ድርሳነ መዛግብት ውስጥ በሪከርድነት ተይዞለታል! ይሁንና የ3 ዓመት ጨቅላን እስር ቤት ውስጥ ማቆየት ግን ምን የሚሉት ህግ ነው ?? የሚል ጥያቄ በበርካቶች ዘንድ አስነስቶ ነበር።
Show all...
ከአዕዋፍ ሁሉ በጣም ሰነፍ የምትባለዋ (ካው በርድ) ናት፡፡ ይቺ የወፍ ዝርያ ስራ ከመጥላትዋ የተነሳ የጣለችውን እንቁላል እንኳን ታቅፋ ማስፈልፈል አትፈልግም፡፡ ካው በርዶች የራሳቸውን ጎጆ መስራት አይወዱም፡፡ ጫጩቶቻቸውንም አያሳድጉም ወይም አይንከባከቡም፡፡ ሴቷ ካው በርድ እንቁላል ከጣለች ቡሀላ አሳቻ ሰአት ጠብቃ የሌላ ዝርያ ያላት አዕዋፍ ጎጆ በመሄድ የራሷን እንቁላል ታስቀምጥና የዚያችኛዋን ወፍ እንቁላል ትሰርቃታለች፡፡ የተታለለችው ወፍ የአታላይዋን እንቁላል ታቅፋ ታስፈለፍልና መብረር እስኪችሉ ድረስ ይንከባከቧቸዋል፡፡ እስከ 144 የወፍ ዝርያዎች ባለማወቅ የካው በርድን እንቁላል በጉዲፈቻነት ታቅፈው ያስፈለፍላሉ፡፡ የሚገርመው ግን ጫጩቶቹ ከተፈለፈሉ በኋላ ወደ ቤተሰቦቻቸው ካው በርዶች መመለስ መቻላቸው ነው።
Show all...
የፌደሬሽን ምክር ቤት... ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በጠሩት የምክር ቤቱ መደበኛ ሰብሰባ ዋዜማ የመልቀቂያ ውሳኔ መስጠታቸው ተገቢነት የሌለውና የብሔር ብሔረሰቦችን ሃላፊነትን ከግምት ያላስገባ መሆኑን የፌዴሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ። አፈ-ጉባዔዋ ዛሬ በመገናኛ ብዙሃን ልዩነታቸውን ቢናገሩም ምክር ቤቱ ምንም አይነት የጽሁፍም ሆነ የሃሳብ ልዩነት እንዳልነበራቸው ገልጿል። ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ከሃላፊነት መልቀቃቸውን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤን ጨምሮ የምክር ቤቱ የስራ ሃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ከኢዜአ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ምክትል አፈ ጉባኤው አቶ መሃመድ ረሽድ ሀጂ እንዳሉት አንድ የምክር ቤት አባል መልቀቂያ ሲያስገባ የራሱ የሆነ ደንብና ስርዓት ቢኖረውም የአፈ-ጉባዔዋ ውሳኔ ግን ከዚህ ያፈነገጠ እንደሆነ ገልጸዋል። እስካለፈው ሐሙስ ድረስ የምክር ቤቱን መደበኛ ስብሰባ ተገኝተዋል፤ በመጪው ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓም ደግሞ ራሳቸው በደብዴቤ ስብሰባ መጥራታቸውንና በቀረቡ አጃንዳዎች ላይ ምንም ልዩነት እንዳልነበራቸው ገልጸዋል። አፈጉባኤዋ ጥያቄዎቸ ቢኖረቸው እንኳን ለምክር ቤቱ ማቅረብ እንደነበረባቸው ገልጸው፤ የምክር ቤቱን መደበኛ ስብሰባ ለማድረግ አስተባባሪ ኮሚቴው ሳያውቅ በሚዲያ መናገራቸው ትክክለኛ ውሳኔ አይደለም ብለዋል። በአፈጉባኤዋ መልቀቅም በቀጣይ በምክር ቤቱ አጀንዳዎችና መደበኛ ስራውን የሚያስተጓጉል ሂደት እንደሌለ ገልጸው ሁሉም ጉዳዮች በቂ ቅድመ ዝግጅት ስለተደረገባቸው ይካሄዳሉ ብለዋል። ወይዘሮ ኬሪያ ራሳቸው በጠሩት ስብሰባ ዋዜማ መልቀቃቸው፣ የፓርቲ ወገንተኝነታቸውን ከብሄር ብሄረሰብ ተወካይነታቸውን ያሳነሰ ተገቢነት የሌለው ውሳኔ ነው ሲሉም ተናግረዋል። #ኢዜአ @tikvahethmagazine
Show all...
አምባሳደሯ ወደ ሀገር ቤት ያልተመለሱት በምን ምክንያት ነው? በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለሙሉ ባለ ሥልጣ አምባሳደር ትርፉ ኪዳነማርያም የአገልግሎት ጊዜያቸው ቢያበቃም ወደ ሀገር ቤት አልተመለሱም። ይህን ተከትሎ አንዳንድ ግምታዊ ምክንያቶች ከሰሞኑ ሲንሸራሸሩ ነበር። ለመሆኑ ሚያዚያ 30 የአገልግሎት ዘመናቸው ያበቃውና ወደ ሀገር ቤት የተጠሩት አምባሳደር ትርፉ ኪዳነ ማርያም በምን ምክንያት ቀሩ ሲል SBS ራዲዮ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ባለሙሉ ሥልጣን ሚኒስትርና የዲያስቦራ ጉዳዮች ክፍል ኃላፊ አቶ በሪሁን ደጉን ጠይቋል። አቶ ደጉ እንደገለጹት አምባሳደሯ የሥራ ጊዜያቸውን መጨረሳቸውን ተከትሎ እጃቸው ላይ የሚገኘውን ቤት፣ መኪናና ሌሎች ንብረቶች በአግባቡ አስረክበዋል ለመመለስም በዝግጅት ላይ እንደነበሩ እንደሚያውቁ ገልጸዋል። ሆኖም በተከሰተው የኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት እንዲሁም አምባሳደሯ በአንዳንድ በግል ችግሮች ምክንያትና በቤተሰብ ጉዳይ እስክ መስከረም 30 ድረስ ያለደሞዘ እና ያለ ኢምባሴው ውክልና በጠየቁት ፍቃድ መሰረት በመንግሥት እውቅና አግኝቶ በእረፍት ላይ ናቸው ብለዋል። በቅርቡ በኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት የሚወክሉ 15 አዳዲሰ አምባሳደሮችን ሹመት ይፋ አድርገው ነበር። በዚሁ መሰረትም ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ብርሁኑ ፀጋዬ አውስትራሊያ ካንቤራ መመደባቸው ይታወሳል። @tikvahmagbot @tikvahethmagazine
Show all...
የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ አዲስ ፕሬዚዳንት ሹመት ፀደቀ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት በነበሩት አቶ አቤ ሳኖ ምትክ፣ በተጠባባቂ ፕሬዚዳንትነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ተፈሪ መኮንን ሹመት አፀደቀው፡፡ አቶ ተፈሪ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ማገልገል እንዲችሉ ከባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ለብሔራዊ ባንክ የቀረበው ጥያቄ ከታየ በኋላ ነው ሐሙስ፣ ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም. ብሔራዊ ባንክ ሹመታቸውን ያጸደቀው፡፡ ከምሥረታው ጀምሮ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክን ሲመሩ የቆዩት አቶ አቤ ሳኖ፣ በመንግሥት ሹመት ከሁለት ወራት በፊት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው የሚታወስ ነው፡፡ #Reporter @tikvahmagbot @tikvahethmagazine
Show all...
አጫጭር መረጃዎች ፦ - በዩናይትድ ኪንግደም ከመጋቢት 13/2012 ዓ/ም ዓ/ም በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዝቅተኛ የሟቾች ቁጥር ተመዘገበ። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ55 ሰዎች ህይወት ማለፉ ሪፖርት ተደርጓል። - በሳዑዲ አረቢያ በአንድ ቀን 3,369 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ እስካሁን ከተመዘገበው የአንድ ቀን ኬዝ ከፍተኛ ነው። - የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ትላንት ብቻ ከ136,000 በላይ አዲስ ኬዞች መመዝገባቸውን አሳውቋል። ይህ ቁጥር እስካሁን በአንድ ቀን ከተመዘገበው ከፍተኛው ነው። - በጣልያን ለዘጠነኛ ቀን የሟቾች ቁጥር ከ100 በታች ሆኖ ተመዝግቧል። በሀገሪቱ አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም በእጅጉ ቀንሷል። - በኩባ ለዘጠነኛ (9) ተከታታይ ቀን በኮሮና ቫይረስ የሰው ህይወት አላለፈም። ይህ ተከትሎ ሀገሪቱ መንግስት የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን መቆጣጠሩን ገልጿል። - በጋና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ሲባል ላለፉት 3 ወራት ክልከላ ተጥሎባቸው የነበሩት የእምነት ተቋማት ተከፍተዋል። - የታንዛኒያ ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ አገራቸው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ነጻ መሆኗን አውጀዋል። ፕሬዝዳንቱ ሀገራቸው ከወረርሽኙ ነጻ የወጣችው በሕዝቧ ጸሎት መሆኑን ነው እንደ ምክንያት የጠቀሱት - #BBC @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Show all...
ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም የሰጡት መግለጫ ፡- ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም ከፌደሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤነት መልቀቃቸውን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ላይ ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ ኬሪያ እንዳሉት ሥልጣንን ያለ ህዝብ ምርጫ ለማራዘም ሲባል ሕገ መንግሥቱን መጣስ ህሊናዬ አይፈቅድልኝም ሲሉ ነው የገለጹት፡፡ የሕገመንግሥት ትርጉም የሕገመንግስቱን መንፈስ ለመተርጎም እንጂ አዲስ ህግ ለማውጣት አይተረጎምም፣ መንግሥት ሥልጣኑን ለማራዘም አማራጭ የፈለገበት መንገድ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ የፌዴሬሽኑን ሥልጣንና መብት በተጋፋ መልኩ ውሳኔው ቀድሞ የተወሰነ ነው 'ከዚህ ውጪ ወየውላችሁ' የሚል መግለጫም ተሰጥቷል የሚሉት ወ/ሮ ኬሪያ ይህም ታሪካዊ ሥህተት ነው፡፡ ውሳኔውም የምክር ቤቱ እንጂ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም የምሑራን አይደለም ብለዋል፡፡ እኔ ሙስሊም ወጣት ሴት ሆኜ የወጣቶችን ነፍስ የታደገውን፣ የሃይማኖት እኩልነት ያረጋገጠውን ሕገመንግስት መጣስ ስለማልፈልግና ሕብረ ብሔራዊ ሥርዓትን አደጋ ላይ የሚጥል አንባገነናዊ ሥርዓት ለመቀበል አልፈልግም፣ አልተባበርም፣ አልፈጽምም ሲሉ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡ @tikvahmagbot @tikvahethmagazine
Show all...