Daily Kal
Open in Telegram
Daily Kal is a group of Christian graphic designers who serve the lord by sharing the word of God in a daily basis. Contact us at @nate_suga, @MERCYaDv
Show more2 154
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-1430 days
Posts Archive
2 154
ሕያው ቃል
--------------------
1 ሳሙኤል 19:18 ዳዊትም ሸሽቶ አመለጠ፥ ወደ አርማቴምም ወደ ሳሙኤል መጣ፥ ሳኦልም ያደረገበትን ሁሉ ነገረው፤ እርሱና ሳሙኤልም ሄዱ በነዋትዘራማም ተቀመጡ።
1 ሳሙኤል 19:19 ሳኦልም፡— ዳዊት፥ እነሆ፥ በአርማቴም አገር በነዋትዘራማ ተቀምጦአል የሚል ወሬ ሰማ።
1 ሳሙኤል 19:20 ሳኦልም ዳዊትን ያመጡት ዘንድ መልእክተኞችን ሰደደ፤ የነቢያት ጉባኤ ትንቢት ሲናገሩ፥ ሳሙኤልም አለቃቸው ሆኖ ሲቆም ባዩ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በሳኦል መልእክተኞች ላይ ወረደ፥ እነርሱም ትንቢት ይናገሩ ጀምር።
1 ሳሙኤል 19:21 ሳኦልም ያንን በሰማ ጊዜ ሌሎች መልእክተኞችን ሰደደ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ። ሳኦልም እንደ ገና ሦስተኛ ጊዜ መልእክተኞችን ሰደደ፥ እነርሱም ደግሞ ትንቢት ተናገሩ።
1 ሳሙኤል 19:22 የሳኦልም ቍጣ ነደደ፥ እርሱም ደግሞ ወደ አርማቴም መጣ፥ በሤኩም ወዳለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድጓድ ደረሰ። ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው? ብሎ ጠየቀ፤ አንድ ሰውም፡— እነሆ፥ በአርማቴም አገር በነዋትዘራማ ናቸው፡ አለው።
--------------------
Solo Scriptura
WongelAdvocate.com
2 154
The Lord is with me; I will not be afraid. What can mere mortals do to me?
Psalm 118:6
