cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቴቴሌስታይ GOSPEL MEDIA

#በእርሱ/በእየሱስ/ የሚያምን ሁሉ #የዘላለም_ሕይወት እንዲኖረው እንጂ #እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፤ ዮሐንስ 3:16

Show more
Advertising posts
429
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
* ብቸኛው የተቀመጠ ሊቀካህናት! * > ወደ ዕብራውያን መልዕክት ምዕራፍ ስምንት ከቁ፡1 እስከ 6 የሚያጠና ክርስቲያን፣ የዕብራውያንን መልእክት ጠቅለል አድርገው የሚገልጡ ሶስት አሳቦችን ያገኛል 1ኛ፡ ሊቀ ካህናቱ ማነው? > ይህን በተመለከተ "በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ" (ቁ፡1) ተብሎ ተገልፆልናል። ይህ ከአሮን ጀምሮ ያሉትን የብሉይ ሊቀ ካህናት ለሚያውቅ አይሁድ አስደንጋጭም አስደናቂም አገላለፅ ነው። ምክንያቱም በብሉይ የተቀመጠ አንድም ሊቀ ካህናት አናይም። የራሳቸውና የህዝቡ ኃጢአት ዋጋ ፈፅሞ ሊያስቀምጣቸው አይችልም። > እንኳን ሊቀመጡ አይደለም ቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ እንኳ የሚገቡት በዓመት አንዴ(ዕብ፡9÷7)፣ ለዚያው ከብዙ ፍርሃትና ጭንቀት ጋር እንደሆነ አስባለው። ሐዋርያው በዚህ ስፍራ የሚናገርለት ሊቀ ካህናት ግን በምድር ሳይሆን በሰማያት፣ በማደሪያው ድንኳን ቅድስተ ቅዱሳን ሳይሆን በግርማው ዙፋን ቀኝ፣ በዓመት አንዴ ሳይሆን ለዘለዓለም ተቀምጧል ይለናል። > ተቀምጧል የሚለውን ስናነብ፣ እግዚአብሔር ውድ ልጁን ኢየሱስን እንዲህ እንዳለው አናስብምንህ፣ "ልጄ የከፈለከው ዋጋ በቂና ከበቂ በላይ ነው፤ ከእንግዲህ ወዲያ ስለኃጢአት መሥዋዕት ማቅረብ የለም፤ ስራው ተፈፅሟል፤ ስለዚህ በግርማው ዙፋን ቀኝ ተቀመጥ"! 2ኛ፡ ሊቀ ካህናቱ የሚያገለግለው በየት ነው? > እግዚአብሔር ይመስገን! ሊቀካህናችን ስራውን ፈፅሞ መቀመጡ ቢነገረንም፣ "የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነውም" (ቁ፡ 2) ተብለናል። > አዎን፣ ቃሉ የሚለን በአላፊ ግስ "ነ*በ*ረ" ሳይሆን በአሁን ጊዜ አመልካች ግስ "ነ*ው" ነው። እርሱ ምድረበዳውን ካላሻገረን ማን ሰማይ ሊያደርሰን(ዕብ፡2፣4፣5)? ኢየሱስ ምስጋናችንን ካላሳረገ ማን አምልኮውን ሊመራ(ዕብ፡10፣13)? > የአገልግሎቱም ስፍራ በምድር ሳይሆን በሰማይ፣ በሰው እጅ ሳይሆን በጌታ በተተከለ፣ በጥላው ሳይሆን በእውነተኛው ድንኳን ነው(ቁ፡2-5)። 3ኛ፡ የሊቀ ካህናቱ አገልግሎት እንዴት ተገለፀ? > ቁ፡6 "እጅግ የሚሻል አገልግሎት" ይለዋል። በነ አሮን ሊቀካህነትነት ስር የነበሩት ምን አገኙ? ከእርግማን ከመቅሰፍት ዳኑን? ኢየሱስ መካከለኛ የሆነለት ግን "የሚሻል ተስፋ" (ቁ፡6) ባለቤት ሆኗል። በኢየሱስ ሊቀ ካህናትነት ስር ሆኖ በምድረ በዳ የሚቀር፣ ተስፋውን የማይወርስ እስቲ ማነው? ፈፅሞ ማንም አይኖርም። # አዎን "እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን" (ዕብ፡8÷2) https://t.me/tetelestaye
Show all...
* የዳዊት መንግስት ከቤ/ን ጋር ሲነፃፀር! * #የሁለቱ ልዩነት ምንድን ነው? 1ኛ፡ የዳዊት መንግስት በብሉይ የሚታወቅ መንግስት ሲሆን፣ ቤ/ን ግን በብሉይ አትታወቅም። 2ኛ፡ የዳዊት መንግስት ምድራዊ(ኤር፡23፥5-6) ሲሆን ቤ/ን ግን ሰማያዊ ነች(ፊል፡3÷20-21)። 3ኛ፡ የዳዊት መንግስት በአይሁዶቹ የሚመራ ሲሆን (ጌታም በዳዊት ዙፋን የሚቀመጠው ከይሁዳ ነገድ የሆነ አንበሳ፣ የዳዊት ዘር ስለሆነ ነው) (ዘፍጥ፡49÷10)፣ ቤ/ን ግን አይሁድም አህዛብም ያልሆነች፣ ከሁለቱም ወጥተው ዳግም በተወለዱ አዲስ ሰዎች የተዋቀረች ናት(ኤፌ፡2፥14-16)። 4ኛ፡ የዳዊት መንግስት በረከት ምድራዊ ሲሆን(ኢሳ፡11÷1-12)፣ የቤ/ን ግን መንፈሳዊ ነው(ኤፌ፡1÷3)። 5ኛ፡ የዳዊት መንግስት ዓለም ከተፈጠረ በኋላ የተዘጋጀ ሲሆን(ማቴ፡25፥31)፣ ቤ/ን ግን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የታሰበች ናት(ኤፌ፡1÷4)። 6ኛ፡ የዳዊት መንግስት መቀመጫ ምድራዊቷ ኢየሩሳሌም ስትሆን(መዝ፡2÷6)፣ ቤ/ን ግን ራስዋ ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም የተባለች ናት(ራዕ፡21፥10-11)። 7ኛ፡ የዳዊት መንግስት ተስፋ የመሢሑ መምጣትና በሺው ዓመት ጊዜ በምድር ወደ ቀደመው፣ ከቀደመውም ወደ በለጠ ክብር መለስ ሲሆን(ሆሴ፡3÷4-5)፣ የቤ/ን ግን በአብ ቤት መኖር ነው(ዮሐ፡14÷3)። 8ኛ፡ በዳዊት መንግስት ኢየሱስ ንጉስ ሲሆን(ህዝ፡37÷23-45)፣ በቤ/ን ግን የቤ/ን ሙሽራ ነው(ዮሐ፡3÷29)። 9ኛ፡ የዳዊት መንግስት በሺው ዓመት እንኳ ሳይቀር ምድራዊ መቅደሱን የሚሰራ ሲሆን(ሕዝ፡40 እስከ 45)፣ ቤ/ን ግን ራስዋ የእ/ር መቅደስ ነች(ራዕ፡21)። 10ኛ፡ የዳዊት መንግስት መንግስት ሲሆን፣ ቤ/ን ግን የክርስቶስ አካል ናት(ኤፌ፡1÷23)። https://t.me/tetelestaye
Show all...
* የሰው ሁለንተና መንፈስ፣ ነፍስ እና ሥጋ! * 1ኛ፡ ሰው ከኃጢአት በፊት > ኃጢአት ዘፍጥ፡3 ላይ ወደ ዓለም ከመግባቱ በፊት (ሮሜ፡5÷12) እግዚአብሔር ሰው ብሎ የፈጠረው ፍጡር ሶስት ክፍሎች አሉት። መላዕክትን መንፈስ ናቸው፣ እንስሳት ደግሞ ሥጋ እና መንፈስ አላቸው፣ በምንለው ልክ፣ ሰው ከመላእክትም ሆነ ከእንስሳ የተለየ መንፈስ፣ ነፍስ እና ሥጋ ያለው ፍጡር ነው፤ ሥጋው ከአፈር (ዘፍጥ.2፡7)፣ መንፈስና ነፍሱን ደግሞ ከእግዚአብሔር እስትንፋስ ተግኝተዋል (ዘፍጥ.2፡7፣ ኢዮ.32፡8)። > እግዚአብሔር በዔደን ገነት ያኖረው ሰው፣ ከመንፈስ አኳያ ክፉ እውቀት የሌለው (እውቀት/ማስተዋል ከመንፈስ ጋር ይገናኛል 1ቆሮ.2፡11)፣ ከነፍስ አኳያ ኃጢአትን ፈፅሞ የማያስብና የማይመኝ (ነፍስ በዋናነት ከስሜት ምኞት ከመሳሰሉት ጋር ትገናኛለች መዝ.107፡5፣9፣18፣ 84፡2)፣ ከሥጋ አንፃር ደግሞ መልካም የሆነውን የመንፈስ አሳብ እና የነፍስ ምኞትን የሚተገብርና የማይበሰብስ (እስከታዘዘ ድረስ የማይሞት) ነበር። > ከሄደን ሕይወት አንድ ምሳሌ እናንሳ፦ እግዚአብሔር ሰው በምድር ተባዝቶ እንዲኖሮ ያቀደው ከውድቀት በፊት ነው። ጋብቻ የኃጢአት ውጤት አይደለም። ታዲያ ያለ ስጋ ጋብቻ ሊኖር አይችልም። ነፍስ ደግሞ በጋብቻ ውስጥ የምትመኘውንና የሚያስደስታትን ታገኛለት። የመንፈስ እውቀት ደግሞ ሕይወትን ይመራዋል። > ነፍስ ከሌለ ስሜት የሚባል ነገር የለህም፣ መንፈስ ከሌለህ እውቀት ወይም ማስተዋልህን ታጣለህ፣ ሥጋ ከሌለ ደግሞ መንፈስና ነፍስ የፈለጉትን ያስቡ ይመኙ፣ በተግባር የማይውል “ላም አለኝ በሰማይ ወተትዋን የማላይ” ይሆናል፡፡ ሶስቱም ወሳኝ ናቸው። 2ኛ፡ ሰው ከኃጢአት በኃላ > ሰው ባለመታዘዙ ኃጢአት ወደ ዓለም ሲገባ፣ ነገሮች ተገለባበጡ። እንዴት ወደቀ ካልን(ዘፍጥ፡3÷7) ሀ፡ በመንፈሱ ያለውን እውቀት ላለመታዘዝ ተጠቀመው ለ፡ ነፍሱ እንደ እግዚአብሔር መሆንን ተመኘች፣ ፍሬው አስጐመጃት ሐ፡ ሥጋውን በመንፈሱና በነፍሱ ያሰበውን በተግባር ፈፀመበት። #ውጤት፦ (ዘፍጥ፡3÷1-21) ሀ፡ መንፈሱ ከእግዚአብሔር ጋር ተቆራረጠ ለ፡ ነፍሱ ተቅበዝባዥ ሆነች፣ የዘላለምም ሞት ተፈረደባት ሐ፡ ሥጋው በስባሽ ሆነ > ስለዚህ የሆነ መንፈስ ወይም ነፍስ ወይም ሥጋ የሚባል ነገር ሳይሆን “ሰው” የሚባል ፍጡር በሁለተናው ኃጢአት ሰራ፣ በሁለንተናው ተበላሸ። 3ኛ. ሰው በክርስቶስ ሲሆን ሀ፡ መንፈሱ ሕያው ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር ተገናኘ (ሮሜ፡8÷16) ለ፡ ነፍሱ ከዘላለም ሞት ዳነች (1ጴጥ.1፡9) ሐ፡ ሥጋው ወደፊት በክብር ሥጋ ይለወጣል (ፊል.3፡21-22)። > የመንፈስ ሕያውነትና የነፍስ መዳንን በቅፅበት ብናገኝም ሥጋችን ግን የሚለወጠው ወደፊት ጌታ ሲመጣ ነው። 4ኛ፡ ሰው በክርስቶስ ከሆነ በኋላ > በ1ተሰ፡5÷23 መሰረት ሀ፡ መንፈስ ይቀደስ። በውስጥ የምናስበው ነገር ሁሉ እንደቃሉ ይሁን (ፊል፡4÷8-9) ለ፡ ነፍስ ትቀደስ። ምኞትና ፍላጐታችን በቃሉ ይገራ (1ጴጥ፡2÷11)። ሐ፡ ሥጋ ይቀደስ። የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ነውና ከማይገባ ቦታ ማራቅ ይገባል (1ቆሮ፡6÷19-20)። 5ኛ፡ ዘላለም ውስጥ የምንኖረው እንዴት ነው? > የሕያው መንፈስ፣ በዳነች ነፍስ፣ በክብር ሥጋ ማንነታችን ተመስርቶ ከጌታ ጋር እንሆናለን (1ቆሮ፡15÷51-54)። # ስለዚህ ሰው እንዲህ ነው ብሎ አንዱን በመውሰድ መደምደም አንችልም። ስንናገር ሰው መንፈስ፣ ነፍስና ስጋ አለው ብቻ እንላለን፣ ከፍጥረት እስከዘላለም ሁለንተናው ይህ ነው። ቃሉ ውስጥም የምናየው፣ ሰው "መንፈሴ፣ ነፍሴ፣ ስጋዬ" እያለ ሲጠራ እንጂ "መንፈስ ነኝ" ሲል አላየንም። https://t.me/tetelestaye
Show all...
*በትክክል ለጋብቻ የተዘጋጀ ሰው መፈተኛዎች!* #አምስት ትክክሎች ከዘፍጥረት 24 1ኛ፡ ትክክለኛ እድሜ (ዘፍጥ፡24÷1-3) > አብርሃም ባለጠጋ ነው። ነገር ግን ብዙ ሀብት ስላለው ብቻ ልጁን ገና አስራዎቹ ላይ ሳለ አልዳረውም። ጊዜን ጠብቋል። ይሄ ነው ብለን የተቆረጠ እድሜ ባናስቀምጥም፣ ጋብቻን ሲታሰብ እድሜያችንን መፅሐፉ መስፈርቱ ውስጥ ከቶታል። ሐዋርያው እንዲህ ይለናል " ዳሩ ግን ማግባት ወደሚገባው ዕድሜ በደረሰ ጊዜ … ኃጢአት የለበትም፤ ይጋቡ።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:36) 2ኛ፡ ትክክለኛ የውስጥ አሳብ/ሞቲቭ(ዘፍጥ፡24÷3-4 > ተቀባይነት ያለው እድሜ ላይ መድረስ ብቻ ግን ለጋብቻ ብቁ አያደርግም። የውስጥ አሳብ መፈተሽ አለበት። አብርሃም ለይስሐቅ የፈለገው "ሚስት" እንጂ "የሴት ጓደኛ/ገርል ፍሬንድ" አልነበረም። " … ለልጄ ለይስሐቅም ሚስትን ትወስድለታለህ።" (ኦሪት ዘፍጥረት 24:4) 3ኛ፡ ትክክለኛ ቦታ (ዘፍጥ፡24÷4) > ትክክለኛ እድሜና የውስጥ አሳብ ኖረው፣ ይኽኛው ከጎደለ ትልቅ አደጋ ይፈጠራል። ሚስት ማሰቡ መልካም ሆኖ፣ የምታገኛት ከየት ነው የሚለው ቁልፍ ጥያቄ ነው። አብርሃም ሎሌውን፣ በፍፁም ከከነዓን ሴቶች ለልጁ ሚስት እንዳይወስድለት ያማለው በእግዚአብሔር ነው። ትክክለኛዋ ሚስት የምትገኝበት ቦታ " ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ተወላጆቼ ትሄዳለህ፥ " (ኦሪት ዘፍጥረት 24:4) ሲል አብርሃም እንደተናገረው ነው። > ይህ ለክርስቲያን ሲተረጎም የምናገባት ሴት አገሯ ሰማይ፣ ተወላጅነቷ ከእግዚአብሔር መሆን አለባት። በፍፁም ያማያምን ማግባት አይቻልም(2ቆሮ፡6÷14)! 4ኛ፡ ትክክለኛ መንፈሳዊ ሁኔታ (ዘፍጥ፡24÷11-14) > ከእነዚህ ቀጥሎ ደግሞ ለማግባት ያሰብነው ራሳችን ትክክለኛ መንፈሳዊ ሕይወት ሊኖረን ይገባል። የአብርሃም ሎሌ ያረፈበት ሥፍራ የውኃ ጉድጋድ አጠገብ ነው (ቁ፡11)። ውሃ ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል ምሳሌ ነው። "በቃሉ ያረፈች ሚስት የምናገኘው፣ እኛ አስቀድመን በቃሉ ስር ስናርፍ ነው፤ ያኔ እዛው እንገናኛለን!" > በቃሉ ያረፈ ደግሞ ስለ ሚስት እንደ ሎሌው ይፀልያል፤ እግዚአብሔርት ምረጥልኝ ይለዋል "…አምላክ እግዚአብሔር ሆይ … ያዘጋጀሃት ትሁን" ዘፍጥ፡24÷12-14 5ኛ፡ ትክክለኛ ሰዓት (ዘፍጥ፡24÷16-22) > የአብርሃም ሎሌ ርብቃ መጥታ ነገሮች የተቃኑለት ቢመስልም፣ በስሜታዊነት ተቻኩሎ አልፈጠነም። ቃሉ " ሰውዮውም ትክ ብሎ ይመለከታት ነበር፤ እግዚአብሔር መንገዱን አቅንቶለት እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ ለማወቅም ዝም አለ። " (ኦሪት ዘፍጥረት 24:21) ይላል። > ስለዚህ ከመጣደፍና በሥጋ ወጥመድ ውስጥ ከመግባት፣ ነገሮች ከእግዚአብሔር እንደሆኑ በስክነት ማየት መልካም ነው! እርግጠኞች ስንሆን ልክ እንደሎሌው ጌታን አመስግነን እንቀበላለን! እንዲህ ብለን " … ቸርነቱንና እውነቱን … ያላራቀ …እግዚአብሔር ይመስገን" (ኦሪት ዘፍጥረት 24:27) #እነዚህ አምስት "ትክክሎች" ማግባት ለምናስብ መልካም መፈተኛዎች እንደሆኑ አስባለሁ! https://t.me/tetelestaye
Show all...
* "ጌታ ሆይ በቶሎ ና" ያስባለን ምን ይሆን? * > ማራናታ ስንል እንናገራለን ደግሞም እንዘምራለን። እንደዚያ ያስባለን ምን ይሆን? በዚህ ለሞት በተሰጠ ሰውነት መኖሮ አማሮን፣ የምንኖርባት ምድር አስጠልታን እና ሰልችታን፣ ነገሮች በምድር አልሳኩ ብለውን፣ ገነት ምን እንደሚመስል ለማየት ናፍቀን ይሆንን? > ብዙ አስደናቂ መፅሐፎችን የፃፈው ወንድም ቤሌት ወደ ጌታ የሚሄድበት ጊዜ በተቃረበ ወቅት፣ በአልጋ ላይ ሳለ ሌሎች ወንድሞች ወደ እርሱ መጥተው በቅርቡ ስለሚቀበለው አክሊል ይናገሩ ነበር። በኋላ ላይ ግን አንድ ወንድም ቤሌትን እንዲህ ሲፅልይ ሰማ "ኦ ጌታ ሆይ፣ ወንድሞች መጥተው ስለአክሊል ይናገራሉ፣ እኔ ግን አክሊል አልፈልግም፤ የምፈልገው አንተን ማየት ነው! በሲካር ውኋ ጉድጓድ አጠገብ የተቀመጠውን ሰው ማየት እፈልጋለሁ። ልቤ እየናፈቀ ያለው ይህንን ነው። ማየት የምፈልገው እርሱንና እርሱን ብቻ ነው። አክሊሉ እኔን አይማርከኝም።" > እንዴት ያለ ፀሎት እንዴትስ ያለ ቅናት ነው! አዎን፣ በዚህ ሙት ሰውነትና በተረገመችዋ ምድር መኖር አሰልቺ፣ ደስ የማይል ነው። መቼ በተገላገልኩት ያሰኛል፣ ያስብለናልም። ከእነዚያ ነገሮች መገላገያ ቀንን መናፈቅ ምንም ጥፋት የለውም። ነገር ግን ኢየሱስን ለማየት መናፈቅ እንዴት የላቀ፣ የማይወዳደር ነገር ነው! > የምትወዱትና ለማየት የምትናፍቁት ሰው፣ ዛሬ እንደምታገኙት ስታስቡ አእምሯችሁ ያ ሰው ሊረዳችሁ፣ ሊያግዛችሁ በሚችላቸው ነገሮች፣ ስለምታጫውቱት ችግራችሁ ማሰላሰል ይጀምራል ወይስ የዛን ሰው ፊት ማየት፣ ሰውየውን ማቀፍ እና መሳም ልባችሁን ይሞላዋል? > እንዲህ የሚመልሱ ቅዱሳን እንዴት የታደሉ ናቸው! " ኢየሱስን ልናይ እንወዳለን" (የዮሐንስ ወንጌል 12:21) > አዎን፣ በጌታ ደረት ላይ ያርፍ የነበረው ሐዋርያ እንዲህ አለ " ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለን" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3:2) > ምን ማለት ይቻላል! እንዲህ ያለውን ጥማት ያብዛል። እንዲህም እንዘምረው "መቼ ነው የምንተያየሁ አይንህን በአይኔ የማየው ቶሎ ና ዓለቴ ባሰብኝ ናፍቆቴ ቶሎ ቶሎ ቶሎ ና" https://t.me/tetelestaye
Show all...
* ኢየሱስ ለምን አያማልድም?! * 1ኛ፡ አምላክ ስለሆነ > ኢየሱስ ለጴጥሮስ ሉቃ፡22÷32፣ ለሁሉም ደቀመዛሙርቱ ደግሞ ዮሐ፡17÷6-26 ላይ ሲያማልድ አምላክ አልነበረም እንዴ? 2: ሰውነቱ አብቅትዋል > ጌታ ያረገው በሥጋ ሰውነት አይደለም እንዴ (ሉቃ፡24÷50፣ የሐዋ፡1÷9)? በእግዚአብሔር ቀኝ የተቀመጠው የሰው ልጅ አይደለምን (ሉቃ፡22÷68)? እስጢፋኖስስ ሰማይ ተከፍቶ የተመለከተው "የሰው ልጅ" (የሐዋ፡7÷56) አልተባለምን? ራሱ ጌታም ስለወደፊቱ መምጣቱ ሲናገር የሰው ልጅ ከሰማይ ሲመጣ ታዩታላችሁ አላለምን (27÷64)? 3: ክብሩን መንካት > ጌታ ለጴጥርስ ሆነ ለደቀመዛሙርቱ ሁሉ ሲያማልድ ክብሩ ቀንሷልን? ከሰማይ ውጫዊ ክብሩን ትቶ፣ እስከ መስቀል ድረስ ወርዶ ለሞተላቸው፣ ነፍሱን እንኳ አሳልፎ ለሰጠላቸው መማለዱን ማን ነው ውርደት ያደረገው? 4ኛ: መፅሐፍ ቅዱስ ስለማይል > መፅሐፍ ኢየሱስ በሰማይ ለቅዱሳኑ እንደሚማልድ (ሮሜ፡8÷34፣ ዕብ፡7÷25) እንጂ እንደማይማልድ አይናገርም አይደል እንዴ? 5ኛ፡ እንዴት ኢየሱስ ቁጭ ብድግ እያለ በመለመን ይማልዳል? > ቁጭ ብድግ እያለ ይማልዳል ያለው ማን ነው? መፅሐፍ ቅዱስ የኢየሱስ ምልጃ የክርስቲያን ዋስትና (ዕብ፡7÷25፣ ሉቃ፡22÷32) እንደሆነ እንጂ በሰማይ እንዲህና እንዲህ እያደረገ ይማልዳል ብሏልን? 6ኛ፡ መንፈስ ቅዱስም ይማልዳል ተብሏልና ሁለት አማላጅ እንዴት ይሆናል > መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ሆኖ በምድር (ሮሜ፡8÷26)፣ ኢየሱስ በሰማይ መማለድ (ሮሜ፡8÷34) ግራ ከማጋባት ወይም የኢየሱስን ማላጅነት ከመካድ ይልቅ የክርስቲያኖች ዋስትና ፍፁም መሆኑን አያሳይምን? በምድርም በሰማይም አማላጅ አለኝ ማለት መተማመን አይሰጥምን? > ይህም ብቻ እኮ አይደለም! በምድር በእኛ ውስጥ የሚያፅናና ወይም እኛን የሚወክል (ጰራቅሊጦስ) መንፈስ ቅዱስ (ዮሐ፡14÷16)፣ በሰማይ እኛን ወክሎ ያለ ጠበቃ (ጰራቅሊጦስ) ኢየሱስ እንዳለን (1ዮሐ፡2÷1) አልተፃፈልንምን? https://t.me/tetelestaye
Show all...
* የኢየሱስ ሊቀ ካህናትነት በየት ነው? * > ወደ ዕብራውያን መልዕክት ምዕራፍ ስምንት ከቁ፡1 እስከ 6 የሚያጠና ክርስቲያን፣ ቁ፡1 እንደሚናገረው፣ ከዚያ በፊት የነበሩት አሳቦች ሁሉ መጠቀለያ የሆኑ ሶስት ጥያቄዎች ሲመለሱ ማስተዋል ይችላል። 1ኛ፡ ሊቀ ካህናቱ ማነው? > ይህን በተመለከተ "በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ" (ቁ፡1) ተብሎ ተገልፆልናል። ይህ ከአሮን ጀምሮ ያሉትን የብሉይ ሊቀ ካህናት ለሚያውቅ አይሁድ አስደንጋጭም አስደናቂም አገላለፅ ነው። ምክንያቱም በብሉይ የተቀመጠ አንድም ሊቀ ካህናት አናይም። የራሳቸውና የህዝቡ ኃጢአት ዋጋ ፈፅሞ ሊያስቀምጣቸው አይችልም። > እንኳን ሊቀመጡ አይደለም ቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ እንኳ የሚገቡት በዓመት አንዴ(ዕብ፡9÷7)፣ ለዚያው ከብዙ ፍርሃትና ጭንቀት ጋር እንደሆነ አስባለው። ሐዋርያው በዚህ ስፍራ የሚናገርለት ሊቀ ካህናት ግን በምድር ሳይሆን በሰማያት፣ በማደሪያው ድንኳን ቅድስተ ቅዱሳን ሳይሆን በግርማው ዙፋን ቀኝ፣ በዓመት አንዴ ሳይሆን ለዘለዓለም ተቀምጧል ይለናል። > ተቀምጧል የሚለውን ስናነብ፣ እግዚአብሔር ውድ ልጁን ኢየሱስን እንዲህ እንዳለው አናስብምንህ፣ "ልጄ የከፈለከው ዋጋ በቂና ከበቂ በላይ ነው፤ ከእንግዲህ ወዲያ ስለኃጢአት መሥዋዕት ማቅረብ የለም፤ ስራው ተፈፅሟል፤ ስለዚህ በግርማው ዙፋን ቀኝ ተቀመጥ"! 2ኛ፡ ሊቀ ካህናቱ የሚያገለግለው በየት ነው? > እግዚአብሔር ይመስገን! ሊቀካህናችን ስራውን ፈፅሞ መቀመጡ ቢነገረንም፣ "የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነውም" (ቁ፡ 2) ተብለናል። > አዎን፣ ቃሉ የሚለን በአላፊ ግስ "ነ*በ*ረ" ሳይሆን በአሁን ጊዜ አመልካች ግስ "ነ*ው" ነው። እርሱ ምድረበዳውን ካላሻገረን ማን ሰማይ ሊያደርሰን(ዕብ፡2፣4፣5)? ኢየሱስ ምስጋናችንን ካላሳረገ ማን አምልኮውን ሊመራ(ዕብ፡10፣13)? > የአገልግሎቱም ስፍራ በምድር ሳይሆን በሰማይ፣ በሰው እጅ ሳይሆን በጌታ በተተከለ፣ በጥላው ሳይሆን በእውነተኛው ድንኳን ነው(ቁ፡2-5)። 3ኛ፡ የሊቀ ካህናቱ አገልግሎት እንዴት ተገለፀ? > ቁ፡6 "እጅግ የሚሻል አገልግሎት" ይለዋል። በነ አሮን ሊቀካህነትነት ስር የነበሩት ምን አገኙ? ከእርግማን ከመቅሰፍት ዳኑን? ኢየሱስ መካከለኛ የሆነለት ግን "የሚሻል ተስፋ" (ቁ፡6) ባለቤት ሆኗል። በኢየሱስ ሊቀ ካህናትነት ስር ሆኖ በምድረ በዳ የሚቀር፣ ተስፋውን የማይወርስ እስቲ ማነው? ፈፅሞ ማንም አይኖርም። # አዎን "እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን" (ዕብ፡8÷2) https://t.me/tetelestaye
Show all...
*የጌታ ሊቀ ክህነትና ጥበቅና!* ኢየሱስ ስለ እኛ ይማልዳልን? > ምልጃ ማለት አንድን አካል ወክሎ በሌላ አካል ፊት መገኘት ማለት ነው፡፡ ይህ በአዎንታዊ ወይም በአሉታዊ መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡ ለምሳሌ በአዎንታዊ ሮሜ.8፡26 መንፈስ ቅዱስ ስለ-ቅዱሳን፣ በአሉታዊ ደግሞ የሐዋ.25፡24 አይሁድ-በጳውሎስ ላይ ሲማልዱ እናያለን፡፡ > እናም “ኢየሱስ ስለ እኛ ይማዳልን?” ብሎ መጠየቅ “ኢየሱስ በሰማይ እኛን ወክሎ የሚታይበት ሁኔታ አለን?” ብሎ እንደመጠየቅ ነው፡፡ #መጽሐፍ ቅዱስ ጌታ በሁለት መልኩ ዛሬ እኛን በምድር ሳይሆን በሰማይ እንደሚወክል ይናገራል > አንደኛው፦ ጌታ እኛን ዛሬ “በሰማይ” የሚወክለው በሊቀክህነት ነው፡፡ ይህ “የዕብራውያን መልእክት” ነው፡፡ > ሁለተኛው፦ ጌታን “በሰማይ” እኛን ዛሬ የሚወክለው በጥብቅና ነው፡፡ ይህ ደግሞ “የአንደኛ ዮሐንስ መልእክት” ነው፡፡ > ሊቀካህን  ከእግዚአብሔር ጋር ባለው ነገር ስለ ሰው የሚሾም አገልጋይ ነው (ዕብ.5፡1)፡፡ ሊቀካህን ለመሆን ሰው መሆን ፣ መሾም እና መሥዋዕት የግድ ነው፡፡ ጌታ ሰው ሆኑዋል፣ እንደመልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ሆኑዋል፤ መሥዋዕቱም እርሱ ራሱ ነው፡፡ ስለዚህ የዕብራውያን መልእክት ኢየሱስን በሰማይ ያለ ሊቀካህን አድርጎ ያቅርብልናል(ዕብ፡5÷1-10፣ ዕብ፡8÷1-6)፡፡ > ጠበቃ ማለት የሌላ ሰውን ጉዳይ የሚይዝ አካል ማለት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ተከሳሽን የመወከል ወይም ሰው መሆንና ከሳሽን የማሸነፍ ብቃት የግድ ይላል፡፡ #ጌታ በሊቀካህንነቱ በዋናነት 1ኛ፡ በድካማችን (በኃጢአታችን አላልኩም) ይራራልናል፣ ይረዳናል፣ (ዕብ.2፡17-18፣ 4፡14-16)፡፡ 2ኛ፡ ኃጢአት ውስጥ እንዳንገባ ያድነናል (ዕብ.7፡25፣ ሮሜ.5፡10)፡፡ #ጌታ በጠበቃነቱ በዋናነት 1ኛ፡ እኛ ከሳሽ አለብን፤ በተለይም ደግም ኃጢአት በሰራን ጊዜ ክሱ አደገኛ ነው (ራዕ.12፡10)፤ ስለዚህ ጌታ ወዲያውኑ ጉዳዩን በመስቀሉ ለመፍታት ጥብቅና ይቆምልና (1ዮሐ.2፡1-2፣ ሉቃ.22፡31-32)፡፡ 2ኛ፡ ኃጢአት ሰርተን ወድቀን መቅረት የለብንም፤ ከዚያ ልንወጣ ይገባል፤ ወደ ስፍራችን መመለስ አለብን፤ ለዚህም ጠበቃው አስፈላጊውን ስራ ያከናውናል (ሉቃ.22፡60-62 መዝ.23፡3)፡፡
Show all...
በመንፈስ ቅዱስ መመራት ለአማኞች ሁሉ የተሰጠ ነው!. ❝በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።❞ —ሮሜ 8፥14። ሰው በአምስቱ የስሜት ህዋሳት ከሚደርሱት መረጃዎች ተነስቶ ይኖራል፤ መንፈሳዊ ሰው ግን ከተወለደበት የእውነት መንፈስ እና የእውነት ቃል የተነሣ ይመላለሳል!! ፍጥረታዊ/ሥጋዊ ሰው በምክንያታዊነት ሕይወቱን ይመራል፤ መንፈሳዊ ሰው ግን በእግዚአብሔር መንፈስ ይመራል!! የእግዚአብሔር ልጆች የሕይወት መለኪያ ወይም #የተፈለገው #የኑሮ ደረጃ (standard) የመንፈስ ቅዱስ #ምሪት (Guidance) ነው!! መንፈስ ቅዱስ በእግዚአብሔር ልጆች ሁሉ ውስጥ አለ!! የሁላችንም አኗኗር ግን በእርሱ ጌትነት ስር እየተዳደረ ላይሆን ይችላል!! መንገድ የምናሳየው ለሚጠይቁ እንደሆነ ሁሉ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት የሚጠይቁ ልጆች ምልልሳቸው የበለጠ እንደፈቃዱ ይቃኛል!! እርሱ ሁልጊዜ ለመምራት ዝግጁ ነው!! እኛ በእርሱ ለመመራት ፈቃደኞች መሆን እንችላለን?! መንፈስ ቅዱስ በጥበብ ከሸመገሉ አማካሪዎች ይበልጣል!! መንፈስ ቅዱስ ልምድ ካላቸው አገልጋዮች በላይ ነው!! #አይነጻጸርም!! በውስጣችን ያለውን የማይነቅፍ አስተማሪ፣ የማይሰለች አማካሪ እና የማይደክም አጽናኝ እንስማው!! እኛ አልሰማንም እንጂ እርሱ ያልተናገረበት ጊዜ የለም!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
መንፈስ ቅዱስ ቤት አለው፤ እርሱም፦ እኛው ነን! “የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?” — 1ኛ ቆሮንቶስ 3፥16 አሁን የእግዚአብሔር መንፈስ መኖሪያ እኛ ነን!. የእውነትን ቃል በቅንነት ተቀብለን፥ በአዳኛችን በክርስቶስ ኢየሱስ አምነን፥ በመንፈስ ቅዱስ ታትመናል!. “እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤” — ኤፌሶን 1፥13 ለዚያ ነው "የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?" ያለው! በክርስቶስ ካመንን በኋላ የመንፈስ ቅዱስ መኖሪያ ሆነናል!. አሁን መጠየቅ ያለበት "የእግዚአብሔር መንፈስ በእኛ እየኖረ እንዳለ እናውቃለን?" የሚለው ነው። ከዚያ ባለቤት እንደሌለው ቤት አንሆንም!. ሌላው ጥያቄ ለእርሱ ምን አይነት ቤት ነን? የሚል ይሆናል!. ቤቱ እንደመሆናችን እንደፈለገ እየኖረብን ነው? እኛ በቤታችን ስንሆን እንደምንሆነው እርሱ በእኛ ሲኖር ተመችቶት እንዲኖር ራሳችንን ለቀናል? ለአሠራሩ ምቹ ነን? https://t.me/tetelestaye
Show all...
*የመንፈስ ቅዱስና የኢየሱስ ምልጃ ልዩነቶች!* > መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ምዕራፍ ላይ ሁለቱም የመለኮት አካላት ስለ እኛ እንደሚማልዱ ይናገራል፡፡ ሮሜ ምዕራፍ ስምንት ላይ ከቁ.26-27 መንፈስ ቅዱስ፣ ቁ.34 ደግሞ ኢየሱስ ይማልዳል ይላል፡፡ #የሁለቱ ምልጃዎች ልዩነት ምንድን ነው? ጥቂቶቹን እንመልከት 1ኛ. ከቦታ አንፃር መንፈስ ቅዱስ የሚማልደው በምድር በአማኞች ውስጥ ሆኖ ሲሆን (ሮሜ.8፡27)፣ ኢየሱስ ግን በሰማይ በእጅ ባልተሰራ መቅደስ ውስጥ ሆኖ ነው (ሮሜ.8፡34፣ ዕብ.8፡1-2)፡፡ 2ኛ. መንፈስ ቅዱስ የሚማልድበት ምክንያት ከአማኞች ድካም ማለትም በተፈጥሮ ውስንነት ከተፈጠረ ችግር ጋር ተያይዞ ሲሆን (ሮሜ.26)፣ ኢየሱስ ግን የሚማልደው የግድ አስፈላጊ ስለሆነና ያለዚያ ሰው መዳኑ ፍፁም መሆን ስለማይችል ነው (ሮሜ.5፡10፣ ዕብ.7፡25)፡፡ 3ኛ. የመንፈስ ቅዱስ ምልጃ ጸሎትን “እንዴት እንድምንጸልይ” እና “ስንጸልይም እንደ እግዚአብሔርን ፈቃድ  ካለመጸለያችን” ጋር ተገናኝቶ እገዛን ከመስጠት ጋር ሲገናኝ (ሮሜ.8፡26-27)፣ የኢየሱስ ምልጃ ግን የሚያረዳንን፣ የሚያስፈልግን ጸጋ ከሰማይ እንድናገኝ (ዕብ.2፡17-18፣ 4፡14-16) እና በኃጢአት ስንወድቅ ደግሞ ከሳሻችንን ድል ከመንሳት (1ዮሐ.2፡1-2) ጋር የተያያዘ ነው፡፡ 4ኛ. የመንፈስ ቅዱስ ምልጃ አፈጻጸም በአማኝ ልብ ውስጥ ሆኖ “በማይነገር መቃተት” ወይም የሚነገር ቃል በማይወጣበት ሁኔታ የተባለ ሲሆን (ሮሜ.8፡26-27)፣ የኢየሱስ ምልጃ ግን ቀጥታ በአብ ፊት እንደሚቆም ተነግሮናል (ዕብ.9፡24. 8፡2)፡፡ 5ኛ. መንፈስ ቅዱስ ሊቀካህን እና በአብ ፊት የሚቆም ጠበቃ  ያልተባለ ሲሆን፣ ኢየሱስ ግን ሊቀካህንና በአብ ፊት የሚቆም ጠበቃ ተብሎዋል (ዕብ.4፡14፣ 1ዮሐ.2፡1-2)፡፡ 6ኛ. የመንፈስ ቅዱስ ምልጃ በጠባዩ አማኝ በምድር እስካለ ብቻ የሚደረግለት ሲሆን (ሮሜ.8፡26-27)፣ ከኢየሱስ የምልጃ ሥራዎች መካከል ግን ዘላለማዊ የሆኑ አሉ፡፡ ለምሳሌ በሊቀካህንነቱ አምልኳችንን ማሳረግ የዘላለም አገልግሎቱ ነው (ዕብ.13፡15)፡፡ ቃሉ “ለዘላለም ካህን ነህ” (ዕብ.5፡6) እንዳለው ማስታወስ ይገባል፡፡ 7ኛ፡… በጠቅላላው ** > ክርስቲያን ስለመንፈስ ቅዱስና ኢየሱስ ምልጃ ሲሰማ፣ በምድርም ሆነ በሰማይ ስለ እርሱ የሚቆሙ የመለኮት አካላት እንዳሉ በማወቅ ሐሴት ያደርጋል፤ በሕይወቱ ፍፁም መተማመኛ እንዳለው ይመለከታል። እግዚአብሔርንም "አመሰግንሃለሁ" ይላል። https://t.me/tetelestaye
Show all...
ስታይል ቀይሮ ፀባይ አሳምሮ የተጠራ የለም!   ፀባዩን አስተካክሎ እግዚአብሔር የጠራው አለ? #የአለባበስ ስታይል ቀይሮ የተጠራ አለ? #የፀጉር ስታይሉ ተስተካክሎ የተጠራ አለ? ኢየሱስ በተሰቀለ ሰዓት #ዘራፊ ሆኖ የኖረው ወንበዴ ገነት ገባ! የተሻሉ ሰዎች እያሉ ለምን ወንበዴ ገነት ያስገባል? ምን ይደረግ ፀባይ በማሳመር የእግዚአብሔር መንግስት አይገባ፤ ልጁን ኢየሱስን በመቀበል እንጂ! አብ የወንበዴውን የዕዳ ክፍያ የተቀበለው ከኢየሱስ ነበር! #ያልተከፈለልህ፥ #ያልተከፈለልኝ ሒሳብ የለም! የኢየሱስ የደም ዋጋ በቂ ክፍያ እንደሆነ የማይሰማችሁ ወገኖች በሰላም ነው? የኢየሱስ ክፍያ=100% በቂ ነው! አሳዳጁ እና አንገላቹ ጳውሎስ በጸጋ ተጠራ! ❝አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ........." (1ጢሞ.1:13) አማኞችም የተጠራነው በጸጋ ነው! ❝በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ.....ገላ.1:6" እግዚአብሔር ጳውሎስን በመጥራቱ ጸጸት የለበትም! እግዚአብሔር እኛን በመጥራቱ ጸጸት የለበትም!  ❝እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትም።❞ —ሮሜ 11: 29 https://t.me/tetelestaye
Show all...
የዳነ ሰው ችግር ምንድን ነው? በጸጋ የዳነ ሰው ዋና ችግር አለመብሰል ነው። በጥንትም ዘመን የብዙ አማኞች ችግር ይህ ነበረ። ለምሳሌ፦ የቆሮንቶስ ቤተክርስቲያን ችግር ይሄው ህፃንነት ነበረ። የገላትያ አማኞች ችግር ደግሞ ወደ ህፃንነት መመለስ ነበረ። የቆሮንቶስ አማኞች ችግር የምልልስ ነበር። የገላትያ አማኞች ችግር የትምህርት ነበረ። የሁለቱም መዳረሻ ሕፃንነት ነበረ። ሐዋርያው ጳውሎስ ይህን ችግር ከመሰረቱ ለመንቀል ደብዳቤዎች ጽፏል። የደብዳቤዎቹ አላማ በጸጋ እውነት መጽናት እና በጸጋ አቅም መመላለስ ነው። ጳውሎስ ይህን ችግር ለመቅረፍ ከጸጋ ውጭ ሌላ ቢውልዲንግ ማቴሪያል አልተጠቀመም። የእግዚአብሔር ጸጋ ለሁሉም ችግሮች መልስ ነው። አማኝ አለመብሰልን መምረጥ የለበትም። መንፈሳዊ ህፃንነትን ማስወገድ የሚቻለው በማደግ ብቻ ነው። ለማደግ ወይም ለመብሰል የእግዚአብሔርን ቃል መማር ያስፈልጋል። https://t.me/tetelestaye
Show all...
የመስቀሉ ቃል የመስቀሉ ቃል የተሰቀለው ክርስቶስ ነው!. “የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥18 የመስቀሉ ቃል ክርስቶስ ነው!. ቃል የሚለውን የእንግሊዝኛ ትርጉሞች መልእክት ብለውታል!. የመስቀሉ መልእክት የተሰቀለው ክርስቶስ ነው!. “መቼም አይሁድ ምልክትን ይለምናሉ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ፥” — 1ኛ ቆሮንቶስ 1፥22 የአይሁድ ትኩረት ምልክቶች ላይ ነው!. አይሁድ በሃይማኖት የተሠራ ነፍስ ነው ያላቸው!. ዛሬም የሃይማኖቶች ትኩረት ምልክቶች እንጂ ክርስቶስ አይደለም!. የኛ ስብከት ክርስቶስ ነው!. የኛ ትኩረት ክርስቶስ ነው!. የግሪክ ሰዎች ፍላጎት ወደ ጥበብ ነው፤ ይህ ጥበብ የዓለም ጥበብ ነው!. ዛሬም የፍልስፍናው ዓለም የመስቀሉ ቃል ቀልቡን እንዲወስደው አይፈልግም!. የኛን ቀልብ ግን ራቁቱን የተሰቀለው ኢየሱስ ወስዶታል!. የመስቀሉ ቃል ክርስቶስ መሆኑን እንዴት ተረዳሁ? ሐዋርያዬ ጳውሎስ ቀጥሎ ... "እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥ ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።" 1ኛ ቆሮንቶስ 1:23_24 እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን!. ለአይሁድም ለአሕዛብም ያለን መልእክት ክርስቶስ ነው!. ከላይ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ነው ብሎ ነበረ? ቁጥር 24 ላይ ደግሞ ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው ብሎ በወቅቱ የመስቀሉን ቃል የገፉትን ግልጽ አደረገ። "አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።"  በማለት ያጠቃልላል። የግሪክ ሰው አሕዛብን አመልካች ነው። ለአይሁድም ለአሕዛብም የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው። ስለሆነም የመስቀሉ ቃል የተሰቀለው ክርስቶስ ነው!. እርሱ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ ነው!. የመስቀሉ ቃል 'በመጀመሪያው ቃል ነበረ' የተባለለት ክርስቶስ ነው!.  ይህ ቃል በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ እግዚአብሔር ነበረ። (ዮሐ 1፥1) የመስቀሉ ቃል ሥጋ የሆነ ቃል ነው። ይህ ቃል ከሥጋ በፊት የነበረ ቃል ነው፤ ያለ ሥጋ የነበረ፤ ሥጋ የሆነ ቃል!. (ዮሐ 1፥14) https://t.me/tetelestaye
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ግንኙነት በክርስቶስ በተደረገልን ላይ፥ ከሰዎች ጋር ባለ ግንኙነት እኛ ማድረግ ባለብን ጉዳይ ላይ ትኩረት እናድርግ!. *** እግዚአብሔር ከእኛ ምላሽ ይልቅ የክርስቶስ የመስቀል ሥራ የመለሰው ላይ ትኩረት ያደርጋል!.  የእኛ ጥረት ሳይሆን የራሱን ብቃት ያያል!. ከእርሱ ጋር ያለን ኅብረት ከእኛ በእኛ የጀመረ አይደለም!. ከእኛ ጋር ላለው ግንኙነት የሚቆጥረው ራሱን ነው። *** ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት በሁለታችንም ፈቃድ እና አቅም ላይ የተመሰረተ ቢሆንም መለወጥ የምንችለው ግን የእኛን ሁኔታ ነው!. የሰዎችን ባሕርይ መቆጣጠር አንችልም!. እኛ ማድረግ ያለብንን እንጂ የእነርሱን ድርጊት አንወስንም!. ስለዚህ ከሰዎች የምንጠብቀውን ራሳችንን መወጣት ይኖርብናል!. ቡሩካን ናችሁ!. https://t.me/tetelestaye
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
አሁን እኛም እንወደዋለን! "እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።” — 1ኛ ዮሐ 4፥19 እግዚአብሔር አስቀድሞ መውደዱ የሚደንቀን እኛ ያለንበትን የቀድሞ ሁኔታ ስንረዳ ነው። “በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ..።"   — ኤፌ2፥1 ለመወደዳችን ምክንያት እንዳይኖረን መልካምና በጎውን ማድረግ በማንችልበት በኃጢአታችን ሙታን በነበርንበት ዘመን የወደደን። ...ይህ የእግዚአብሔር ፍቅር በክርስቶስ ሕይወትን ወደ መገለጥ አመጣ!! “በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ #ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል #በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።” — 1ኛ ዮሐ 4፥9  አስቀድሞ የተወደድንበትን የእግዚአብሔርን ፍቅር በክርስቶስ አገኘነው። አሁን እርሱን አለመውደድ አንችልም!!!  የተቀበልነው ሕይወት ፍቅር ነውና!!!
Show all...
እኛ የምንሰማዉን እንወስናለን፤ የሰማነው ነገር ደግም የምናምነውን ይወስናል!! ❝እንግዲያስ እምነት #ከመስማት ነው፤ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።❞ —ሮሜ 10፥17። እምነት ከመስማት ነው። የምናምነው የሚወሰነው ደግሞ በሰማነው ነገር ነው!! እኛ የምንሰማዉን እንወስናለን፤ የሰማነው ነገር ደግም የምናምነውን ይወስናል!! ከእግዚአብሔር አፍ የወጣውን ቃል ከሰማን እውነተኛ እምነት በውስጣችን ይፈጥራል!! ሰዎች እግዚአብሔርን በሚስሉበት መንገድ ሳይሆን #ኢየሱስ አባቱን በተረከበት መንገድ እግዚአብሔርን መስማት ያስፈልጋል!! እግዚአብሔር የሚገባህ በልጁ በኢየሱስ ካየኸዉ ብቻ ነው!! ስለ እግዚአብሔር የምንሰማው ነገር እጅግ በጣም ወሳኝ ነው! ስለ እግዚአብሔር የምትሰማው ነገር ከእግዚአብሔር ያርቅሀል፤ ወይም ወደ እርሱ ያስጠጋሀል!! በትክክል መስማትህ በትክክል ወደ ማመን ያመጣሃል!! እምነት የሚመጣው ከመስማት ነው፤ ፍርሃትም የሚመጣው ከመስማት ነው። ፍርሃት ልባችንን እንዳይቆጣጠር ከፈለግን የምንሰማውን መምረጥ አለብን። በትክክል ለማመን በትክክል የእግዚአብሔርን ቃል መስማት አለብን። ለእግዚአብሔር ቃል በቂ ጊዜ እንስጥ። በተፈጸመው የክርስቶስ ሥራ መገለጦች ነፍሳችንን እንቅረጻት!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
* ክርስቲያን እና ሰማይ! * > የክርስቶስ ተከታይ የሆንክ ክርስቲያን ሆይ 1ኛ: ጥሪ ምን አይነት ነው? > " ሰማያዊው" (ወደ ዕብራውያን 3:1) 2ኛ:በረከትህስ? > "በሰማያዊ ስፍራ" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1:3) 3ኛ: መዝገብን በየት ማከማቸት ነው ትላለህ? >" በሰማይ" (የማቴዎስ ወንጌል 6:20) 4ኛ: ሊቀ ካህንህ የት ነው ያለው? > " በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ" (ወደ ዕብራውያን 8:1) 5ኛ:የተዘጋጀልህ ተስፋና ርስት የሚገኝበትን ስፍራ የት ነው? > " በሰማይ" (ወደ ቆላስይስ ሰዎች 1:3-5) > " በሰማይ" (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:3-5) 6ኛ፡አገርህ በየት ነው? > " በሰማይ" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:20) 7ኛ: ወደፊት የምትለብሰው መኖርያ (አካል) ምን ይመስላል? > " ከሰማይም የሚሆነውን" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:3) 8ኛ:የምትጠብቀው ምንድነው? > " እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤" (ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:20) 9ኛ:የዚህን ምድር ህይወትህን እንዴት ትገልጠዋለህ? > " እንግዶችና መጻተኞች" (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:11) 10ኛ:አገርህ እስክትሄድ ምን ትሰራለህ? > " እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።" (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:20) #እግዚአብሔር ይህን እንድንረዳው ይርዳን። ደግሞም ምድር ምድርን ከመሽተትና አሁን የክርስትናውን ዓለም ካጥለቀለቀው ምድራዊ ስብከት ይጠብቀን። አሜን https://t.me/tetelestaye
Show all...
👇👇👇👇👇👇👇👇👇 There's no place like your presence my Lord There's no body like your presence my daddy 😍 የእግዚአብሔርን የተገለጠ ሕልውና ያህል የሚሆንልን ምንም፣ማንም የለም። የእግዚአብሔርን የለመድነው ሽታ፣የአባትነት ጠረን ያህል የሚሆንልን ማንም፣ምንም የለም ። የእግዚአብሔር የተገለጠ ሕልውና የሚያህል በምድር ብሆን በሰማይ ምንም የለም። እግዚአብሔር አምላካችን ብቻ ሳይሆን አባታችን ነው።እግዚአብሔር ብዙ ልጆች ብኖሩትም፣ለማንኛው ልጅ ከአንዱ የተለየ አቅራቦት፣ወይም የተለየ ነገር አያደርግም ለሁሉም ልጆቹ በተመሳሳይ ነው የሚያደርገው ግን ልጆቹ በቀረበታቸው መጠን ለአባታቸው ልዩነት በልጆቹ መኃል ይታያል።እግዚአብሔር የመሰለ ድንቅ አባት እንደ አለህ ማወቅ ትልቅ ነገር ነው እርሱ መጠጋት ደሞም መጠጋጋት የሚልቅ ነው ። አስታውሳለሁ ታች የት/ት ደረጃ እያለው 5ኛ 6ኛ እና 7ኛ ክፍል ከአባቴ ጋር ጥሩ የሆነ የተለየ ቀረበታ ነበረን ።አብረው ብዙ ጊዜ አድር ነበር ፣ጠረኑ ደስ ይለኝ ነበር ።ያኔ ጥም/ጽም/ አልነበረኝም የፊት እርሱ ግን ነበረው እኔ ጽም/ጥም/ ባለሌው ፊቴ እነካካ ነበር ማለት ጽም ያለውን የእርሱን ፊት ይህ እጅጉን ደስ ያሰኘኝ ነበር። እኔ ይሄው ለዚህ ወግ ማዕረግ በቃ ይመስግነው ማለት ለጽም መብቀሉ ማለቴ ነው ።እና ይህ የምድሩ አባቴ እንዲህ ቀረበው ትዝታው ከአምዕሮዬ አልጠፋም አሁን እንደ ወትሮ አብረን እንዲህ የማደር እድል ባላገኝም፣የመጫወት የመሳሳቅ፣እድል ብቻ ብኖረኝም።ያኔ ከእርሱ ጋር የነበረኝ ህብረት በዚያ መልክ የተገለጠው ድንቅና የሁል ጊዜ ትዝታ ነው ።አሁን ልሆን አይችል ይሆናል ከአባቴ ጋር የነበረን ነገር በተለይ ከላይ ያወራሁት ።ግን የሰማዩ አባቴ እግዚአብሔር ጋር ደሞ ትዝታ አይደለም ዛሬም እንዲያው/ሕያዊ/ ነው።እንደውም አመቱ በጨመረ ቁጥር ቀረቤታዬ፣ከእጅ ይልቅ ፊቱን ማለቴ እየጨመረ ይሄድብኛል እንጅ አይቀንስም፣ዛሬም በሰማዩ በአባቴ ፊት ልጅ ነኝ፣ሽታው የሚሰማኝ፣የተገለጠው ሕልውናው የሚባርከኝ፣ትልልቅ ቁም ነገር በመንፈሱ በኩል ለመስማት ቃሉን የሚከፍት፣በእርሱ ፊት መብት ሳይሆን ህብረት የሚጠቀም ሕያዊ አባት ፣ሕያው ህብረት፣ያለኝ ሕያዊ ልጁ ነኝ። እግዚአብሔር አምላችሁ ብቻ ሳይሆን አባታችሁ እንደ ሆነ ማወቅ የሚልቅ መረዳት ነው።ከአባትም ድንቅ አባት እንዳላችሁ ማወቅ የሚበልጥ ድንቅ መረዳት ነው ።በዚያው እና ከዚያው በላይ በሆነ መረዳት አባታችሁ ፊት በህብረት መንፈስ መገኘት ይህ ደሞ የሚልቅ፣የሚበልጥ፣ከመብራራት ደሞ ያለፌ ነው። " የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም #ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።" (2 ቆሮ 13: 14)
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
ፍቅር #በክብር ይገለጣል!! ❝በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤❞ —ሮሜ 12፥10። ፍቅር በክብር ይገለጣል፤ ሰው ፍቅሩን ለመግለጽ ክብሩን ሊለቅ ይችላል!! ክብር የፍቅር መኖሪያ ዓለም ነው!! ሳናውቀዉ ወደሚያከብሩን እና ትኩረት ወደሚሰጡን እንሳባለን!! ክብር የፍቅር አንዱ መገለጫ መንገድ ነው!! ክብር ምን ያጠቃልላል? ትኩረት ሰጥቶ መስማት፣ ቃላት መርጦ መናገር፣ ቃልን ማክበር፣ ለነገሮች (ግብዣዎች እና ስጦታዎች) ዋጋ መስጠትን፣ ...ሊያጠቃልል ይችላል!! የፍቅር እድሜ ያለው በመከባበር ውስጥ ነው!!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
እንዲህ ተደርገን ስለተወደድን እንዲሁ ልንወድ ይገባል!! ❝ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።❞ —1ኛ ዮሐንስ 4፥11። እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን ... እንዴት አድርጎ? ቁጥር 9-10 ላይ ፍቅር በትክክለኛው መሰረት ላይ ቆሞ ተተርጉሟል፤ "እግዚአብሔር ልጁን ኢየሱስን ለኃጢአታችን ማስተስሪያ አድርጎ መላኩ ለእኛ ያለውን ፍቅር ያስረዳል"ተብሎ!! ኢየሱስ ለእኛ መሞቱ የፍቅር ልክ ነው!! ሐዋርያው የሰጠውን ማጠቃለያ አስተውሉ፦ "እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ ከወደደን እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል" እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍቅር በተግባር ተገልጿል፤ ፍቅሩ ጥያቄ ሊሆን ወይም ሊጠረጠር አይችልም!! የእኛም ፍቅር በድርጊት ሊገለጥ ይገባል!! እንዲህ ተደርገን ስለተወደድን እንዲሁ ልንወድ ይገባል!! አዲስ ኪዳን ፍቅርን የሰበከበት መንገድ በራሱ አስደናቂ ነው!! አስቀድሞ በማስረጃ የነገረን #መወደዳችንን ነው!! ከዚያ የተወደደ መውደድ እንደሚችል ግልጽ አደረገልን!! ማስታወስ ያለብን እንዲህ ተደርገን መወደዳችንን ነው!! ከዚያ ለመውደድ የሚያስችለን ተፈጥሯችን ይንቀሳቀሳል!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
#እርሱ #ለእኛ ያለው #ፍቅር እኛ ለራሳችን የለንም!! ❝ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።❞ —ሮሜ 5፥8። እግዚአብሔር ... እኛን እንዲወድ ያስገደደው የለም፤ ወይም ውደደኝ ብሎ የፍቅር ጥያቄ ያቀረበለት ሰው አልነበረም። ፍቅር የጀመረው ከእርሱ በኩል ነው፤ እኛን መውደድ ምርጫው ነው!! እኛን የወደደበት ፍቅር 'እንዲህ ነው' ተብሎ በቃላት ከመብራራት ያልፋል!! ፍቅሩን ለመተረክ ብቁ የሆነው የኢየሱስ ስርየታዊ ሞት ብቻ ነው!! "ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ መሞቱ" የሚያስረዳው "እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር" ነው!! ለእኛ ያለው የራሱ ፍቅር ... እርሱ ብቻ ለእኛ ያለው ፍቅር ነው!! ይህ ፍቅር ማንም ጋር የለም!! እርሱ #ለእኛ ያለው #ፍቅር ... እኛ እንኳን ለራሳችን የለንም!! "እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር" ያስረዳው ያለውን አንድያ ልጁን በመስጠት ነው!! ኢየሱስ የእግዚአብሔር ፍቅር መገለጥ ነው!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
#ተብሎ እንደ #ተጻፈው ሆነ!! ❝ነገር ግን፦ የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ #ተብሎ እንደ #ተጻፈው ይሆን ዘንድ፥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።❞  —1ኛ ቆሮንቶስ 1፥30-31። ሐዋርያው ... እግዚአብሔር "የዓለምን ምናምንቴ ነገር" እንደመረጠ በመናገር የክፍሉን አሳብ ጀምሯል!! ለዚህም ❝ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት እንዳይመካ።❞ የሚል ማጠቃለያ ሰጠው!! ታዲያ የእግዚአብሔር እቅድ ምንድን ነው? ስንል ... "የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ #ተብሎ እንደ #ተጻፈው ይሆን ዘንድ" የሚል አሳብ አነሳ። ታዲያ እንደተጻፈው እንዲሆን ምን አደረገ? ሁሉንም በአንድ አካል (Person) አደረገው!! እርሱም፦ ክርስቶስ ኢየሱስን #ጥበባችን፣ #ጽድቃችን፣ #ቅድስናችን እና #ቤዛችን አደረገው!! ስለዚህ ማንም በእግዚአብሔር ፊት አፉን አይከፍትም! ማንም በራሱ አይኮራም! ማንም ሌላ መመኪያ የለውም!! የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ #ተብሎ እንደ #ተጻፈው ሆነ!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ሁሉን ሊያስተምረን መጥቶ አንዳንዱን እንኳን እንዲያስተምረን እድል ሳንሰጠው ዘመናችን እንዳያልቅ! አንድ ወዳጄ ጋር በአገልግሎት ዙሪያ እያወራን "ብዙ አገልጋዮች ብዙ ጠቅመውኛል፤ የመንፈስ ቅዱስን ያህል ግን የጠቀመኝ የለም" አልኩት!! እርሱም "ዋናው አስተማሪ እኮ እርሱ ነው፤ ብዙዎች ያልተጠቀሙበት አገልግሎቱ #አስተማሪነቱ ነው" አለኝ!! እኔም ከመደነቅ ጋር ተስማማሁ!! ጌታ ኢየሱስም ስለመንፈስ ቅዱስ የተናገረው ይኸው ነው!! ❝አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ #ሁሉን #ያስተምራችኋል፤ እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።❞ —ዮሐንስ 14፥26። ስንቶቻችን ከመንፈስ ቅዱስ እንማራለን? ሁሉን ሊያስተምረን መጥቶ አንዳንዱን እንኳን እንዲያስተምረን እድል ሳንሰጠው ዘመናችን እንዳያልቅ! ብዙዎቻችን የጌታን መንፈስ በትንቢት፣ በፈውስ እና በልሳን ወስነነዋል!! ሕይወታችንን እንዲመራው አንፈልግም፤ እንዲያስተምረን አንገኝም!! ነፍሳችን ለእርሱ መመለስ ይኖርባታል!! የመንፈስ ቅዱስን አስተማሪነት እንጠቀምበት!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
እግዚአብሔር አላቸው ብሎ የቆጠረልን ኢየሱስን ነው፤ እኛም አለን ብለን መቁጠር ያለብን እርሱን ነው!! ኢየሱስ አለልን!! ❝ጴጥሮስ ግን፦ ብርና ወርቅ የለኝም፤ ይህን #ያለኝን ግን እሰጥሃለሁ፤ በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ አለው።❞ —ሐዋርያት 3፥6። ጴጥሮስ እና ዮሐንስ ለጸሎት ወደ መቅደስ ሲሄዱ ምጽዋት የሚለምን አንድ ሰው አገኙ። ይህ ሰው አንካሳ ሆኖ የተወለደ ነበረ። ሲያያቸው እንደ ለመደው ገንዘብ ለማናቸው። ጴጥሮስ ግን "ብር እና ወርቅ የለኝም" አለው። እርሱ የሚፈልገው ገንዘብ የላቸውም፤ ነገር ግን ገንዘብ ሊገዛው የማይችለው አላቸው። ታዲያ ለምንድነው ወደ እነርሱ የምመለከተው? ሳይል አይቀርም። ጴጥሮስ ቀጠለ፤ ይህን #ያለኝን እሰጥሃለሁ። ያላቸው ምንድን ነው? ኢየሱስ። "በናዝሬቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሣና ተመላለስ" አለው። ወዲያው ተፈወሰ፤ ተራምዶ ስለማያውቅ እንዴት እንደሚቆም አልመጣለትም። ጴጥሮስ በቀኝ እጁ ይዞ አስነሣው፤ በዚያን ጊዜም እግሩና ቍርጭምጭምቱ ጸና። ወደ ላይ ዘሎም ቆመ፥ ይመላለስም ጀመር፤ እየተመላለሰም እየዘለለም እግዚአብሔርንም እያመሰገነ ከእነርሱ ጋር ወደ መቅደስ ገባ። (ሐዋ. 3፥1-8)። ይህ ሰው ያለ ፕሮግራሙ ነው የተፈወሰው። ሕይወቱን በዚህ መንገድ አስቦት የሚያውቅ አይመስለኝም፤ አንካሰነቱን ተቀብሎ መለመኛ አድርጎት ኑሮ ቀጥሏል። አሁን ከመራመድ አልፎ መዝለል እና መሮጥ ችሏል።  ይህ መለኮታዊ ጉብኝት በኢየሱስ ስም ነው የመጣለት። 👇 አይለወጥም ብላችሁ በተቀበላችሁት ነገር የእግዚአብሔር ጉብኝት በኢየሱስ ስም ያግኛችሁ!! ጴጥሮስ "አለኝ" ያለው እኛም አለን። እግዚአብሔርም አላቸው ብሎ የቆጠረልን ኢየሱስን ነው፤ እኛም አለን ብለን መቁጠር ያለብን እርሱን ነው። ኢየሱስ አለልን፤አለኝ ማለት የሚያኮራው እርሱን ብቻ ነው። ሌላው ሲሄድ ሲመጣ ነው። አሉኝ ያልናቸው ቋሚ ሆነው አይኖሩም፤ እርሱ ግን የማይኖርበት ጊዜ አይኖርም። እግዚአብሔር እንዲኖረን የፈለገው ልጁን ኢየሱስን ነው። ደስ እያለው ሰጥቶናል። ኢየሱሳችን በጎ ስጦታ፤ ፍጹም በረከት ነው። እግዚአብሔር የሰጠንን ''አለኝ'' ብለን እንቁጠር። ልጁ ያለው ሕይወት አለው። ኢየሱስ ያለው ሙሉ ሰው ነው!! አለኝ ያልነው ጌታ እንኳን ለእኛ ላመነው ለሌሎችም ይተርፋል!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ራእይ በምጥ እንጂ በሰርጀሪ አይወለድም!! ራእይ እንደ ጽንስ ነው፤ የተለየ እንክብካቤ ይፈልጋል!! እስኪወለድ ሕመም እና ተግዳሮቶች አሉት!! ራእይ ሊወለድ ሲል አስጨናቂ ምጥ አለ!! ራእይ በምጥ እንጂ በሰርጀሪ አይወለድም!! ራእይ በጭንቅ ተወልዶ በጭንቅ ያድጋል!! ሌሎችን ግን በዕረፍት ያኖራል!! እኛ ከብዶን ለሌሎች የምናቀለው ሸክም አለ!!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
የያዘህ ስላለ ራስህን ልቀቅ!? አንድ በእግዚአብሔር የማያምን ሰው ... ገደል ገባ አሉ፤ የገደሉ መሀል ላይ አንዲት ሐረግ ይዞ በሞት ፍርሃት ተይዞ "አለህ የሚሉህ ካለህ አድነኝና ልመንህ" አለ። እግዚአብሔር ተገለጠለትና "እንዳድንህ ሐረጉን ልቀቅ" አለው። ሰውዬው "ሐረጉንም አለቅም፤ በአንተም አምናለሁ" አለ። ሐረግን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል ማመን አይቻልም!! የያዝነውንም የያዘንንም ማመን አይቻልም!! የያዘን ስላለ የያዝነውን መልቀቅ ይኖርብናል!! በእርሱ መደገፍ እና ማረፍ ይሻለናል!! የዋና አስተማሪዎች "ሰውነትህን ዘና፥ ለቀቀ አድርገው" ይላሉ። በእግዚአብሔር ላይ ራስን መጣል ወይም ራስን ለእግዚአብሔር መልቀቅ እንማር!! አንጨምደድ!! በእግዚአብሔር ላይ እንተማመናለን!!
Show all...
''ኑሮ ተወደደ'' አትበል፤ የአንተ ኑሮ በወደደህ ጌታ ላይ ባለ እምነት ነው!! 👇 ❝ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤ አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።❞ —ገላትያ 2፥20። https://t.me/tetelestaye
Show all...
እምነት በፍቅር ይሠራል!!! ❝በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነት እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና።❞ —ገላትያ 5፥6። ይህን ቃል ደጋግማችሁ አሰላስሉት፦ "በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ #በፍቅር የሚሠራ #እምነት ...." በክርስቶስ ኢየሱስ ... ከሙታን በተነሳው ጌታ ላይ የሆነ እምነት የሚሠራው በፍቅር ነው!! ክፍሉ የሚያወራው በክርስቶስ ስለሆነ እምነት እና ይህ እምነት እንዲሠራ ስለሚያደርገው ሕያው ፍቅር ነው!! በዚህ ክፍል የተጠቀሰው የፍቅር አይነት፦ የእግዚአብሔር ፍቅር (Agape) ነው፤ እርሱ ለእኛ ያለውን በሁኔታዎች የማይወሰን (unconditional + Sacrificial) ፍቅር በተረዳን ቁጥር እምነታችን ይንቀሳቀሳል!! ምን ያህል እንደ ተወደድን በገባን መጠን በእግዚአብሔር ላይ ያለን እምነት (መደገፍ) ይጨምራል!! አለማመን (በእርሱ አለማረፍ) የሚመነጨው የእግዚአብሔርን ፍቅር ካለመረዳት ነው!! አምፕሊፋይድ ባይብል ይህን ክፍል፦ "Faith activated and energized and expressed and working through love" ብሎ ተርጉመውታል!!  ስለዚህ እምነት እንዲሰራ ፍቅር ላይ እንስራ፤ ማለት የተወደድንበትን ፍቅር ዕለት ዕለት እንማር!! በአዲሱ ኪዳን መገረዝ ወይም አለመገረዝ አይጠቅምም!! የሚጠቅመው በክርስቶስ መሆን ነው!! በጊዜው መገረዝ አይሁድን፤ አለመገረዝ አሕዛብን ይወክላል!! አይሁዳዊ በመሆን ብዙ ጥቅሞች ነበሩ!! ከክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ በኋላ ግን ጥቅም ያለው በክርስቶስ በመሆን ብቻ ነው!! እግዚአብሔር አይሁድንም አሕዛብንም በክርስቶስ በማድረግ አዲስ ሰው ፈጥሯል!! በእርሱ በመሆን ያገኘነውን በማሰብ በዕረፍት እንመላለስ!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
#መንፈስ #ቅዱስ የማያስፈልገን ጊዜ የለም፡፡ ለብቻችን ከሆንን የምናበላሸው ይበዛል፡፡ ከእርሱ እንክብካቤ ውጭ ያለ ሕይወት በምሬት እና በጉስቁልና የተሞላ ነው፡፡ ሰው እንኳን ያለ መንፈስ ቅዱስ ያለ ልብስ ራቁቱን ያስፍራል፤ ያሳፍራልም!! * መንፈስ ቅዱስ ሩህሩህ እና ቅን ነው፤ የእኛ ነገር በቀላሉ ይገባዋል። ማንም መሄድ ወደማይችልበት ወደ ነፍሳችን እና መንፈሳችን ጥልቀት መሄድ ይችላል። ሙሉ በሙሉ ልባችንን ልንጥልበት እና ልንደገፍበት ከፈቀድን የምድር ስበት ወደ ማይዘው አኗኗር ይስበናል!! * መንፈስ ቅዱስ የእኛን ልብ መመርመር እና ማወቅ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርንም የልብ ምክር እና ፍላጎቱን ያውቃል። በእርሱ ውስጥ የተሻለውን ማየት እንድንችል ያግዘናል!! መንፈስ ቅዱስ በእርሱ የታየላችሁን ኑሮ ያሳያችኋል!! ** የመንፈስ ቅዱስ #አብሮነት በማንኛውም የሕይወት ገጽታ ሕይወት ሰጪ ነው!! ገደብ እና ወሰን ለሌለው የእርሱ ጥበብ ራሳችንን እንስጥ!! የልህቀት መንገዱ ያ ነው!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
#መንፈስ #ቅዱስ፦ አንድ ነው፤ ብዙ ይሠራል!! "ከበዓሉም በታላቁ በኋለኛው ቀን ኢየሱስ ቆሞ፦ ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ። በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። ይህን ግን በእርሱ የሚያምኑ ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ፤ ኢየሱስ ገና ስላልከበረ መንፈስ ገና አልወረደም ነበርና።" ዮሐንስ 7፥37-39። ❝He that believeth on me, as the scripture hath said, out of his belly shall flow #rivers of living water.❞ —John 7:38 (KJV) ኢየሱስ ይህን ሲናገር ይህ የሕይወት ውኃ ወንዞች በእርሱ ውስጥ ብቻ ነበረ!! አሁን ግን ኢየሱስ ከብሯል!! #መንፈስ #ቅዱስ #ወርዷል!! በኢየሱስ የምናምን ሁላችንም ይህን የሕይወት መንፈስ ተቀብለነዋል!! እንደ ወንዞች ከሆዳችን ይፈልቃል!! "የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል" የሚለውን "የሕይወት ውኃ #ወንዞች ከሆዱ ይፈልቃል" ብላችሁ አንብቡት!! (የእንግሊዝኛውን ቨርዥን ተመልከት) በእርግጥ ወንዝም ወንዞችም የመንፈስ ቅዱስን አቅም መግለጥ አይችሉም!! መንፈስ ቅዱስ አንድ ነው፤ ብዙ ይሠራል!! አንድ ነው፤ ልዩ ልዩ የጸጋ ስጦታዎችን እንደ ወደደ ይሠጣል!! ❝የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን #አንድ ነው፤❞ —1ኛ ቆሮንቶስ 12፥4። ለምሳሌ፦ የዮሐንስ ራእይ ላይ ሰባቱ መናፍስት የሚል አገላለጽ እናገኛለን። ❝... በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ...❞ —ራእይ 1፥4-5። ሰባት መንፈስ አለ ማለት አይደለም!! አንዱን የእግዚአብሔር መንፈስ በሥራው እና በአሠራሩ መግለጽ ነው!! የኢሳይያስ ትንቢት ይህን ይፈታል። ❝የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።❞ —ኢሳይያስ 11፥2። በኢየሱስ ላይ ያረፈው የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። ይህ መንፈስ ደግሞ አንድ ነው። ይኸው አንዱ መንፈስ ከላይ የተዘረዘሩትን ሁሉ ይሰጣል። ያኔ #በማንነቱ ሳይሆን #በሥራው ሊጠራ ይችላል። ለምሳሌ፦ ጥበብ ሲሰጥ የጥበብ መንፈስ ይባላል። ስለዚህ ሁለት ነገሮች መረዳት አለብን። የመጀመሪያው ወንዞች የሚለው ብዛትን ሳይሆን ሥራውን እና አሠራሩን የሚገልጽ ነው። ከሥራው የተነሳ አገላለጽ ነው። ሌላው የሕይወት ውኃ ወንዞች ሲል መንፈስ ቅዱስ ወንዝ ነው ማለት አይደለም። ኃይል ሲገልጥ የኃይል መንፈስ ተባለ እንጂ መንፈስ ቅዱስ ኃይል አይደለም። እውቀት ሲሰጥ የእውቀት መንፈስ ተባለ እንጂ መንፈስ ቅዱስ እውቀት አይደለም። የሕይወት ውኃ ወንዞች_ #ከሆዱ ይፈልቃል ነው ያለው! ይህ ኃያል መንፈስ በውስጣችን አለ፤ የእርሱ ኃይል ሕይወታችንን ያንቀሳቅሳል። የጥበብ መንፈስ በውስጣችን አለ፤ ነገሮችን በጥበብ እናስተዳድራለን። የምክር መንፈስ በውስጣችን አለ፤ የሌሎችን ሕይወት የሚያቀና ምክር ከእኛ ይገኛል። የመገለጥ መንፈስ በውስጣችን አለ፤ ቃሉ ይበራልናል። ይህ የሕይወት ውሃ ወንዞች - ከመቅደሱ (ከመንፈሳችን) ወደ ውጭ ይፈሳል። ነፍስና ሥጋችንን እየፈወሰ አልፎ ሌሎችንም ያረካል። በዙሪያችን ለውጥ ያመጣል!! ቀጣዩን የመጽሐፍ ክፍል አጥኑ፦ ❝ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ፤ እነሆም፥ ውኃ #ከቤቱ #መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፥ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና፤ ውኃውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመሠዊያው በደቡብ በኩል ይወርድ ነበር።❞ —ሕዝቅኤል 47፥1። ❝በወንዙም አጠገብ በዳሩ ላይ በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል፥ ቅጠሉም አይረግፍም ፍሬውም አይጐድልም፤ #ውኃውም #ከመቅደስ ይወጣልና በየወሩ ሁሉ #የፍሬ #በኵር ያገኛል፤ ፍሬውም ለመብል ቅጠሉም ለመድኃኒት ይሆናል።❞ —ሕዝቅኤል 47፥12። ❝ሕያው ነፍስ ያለው ተንቀሳቃሽ ሁሉ ወንዙ በመጣበት ስፍራ ሁሉ በሕይወት ይኖራል፤ ይህም ውኃ በዚያ ስለ ደረሰ ዓሣዎች እጅግ ይበዛሉ፤ የባሕሩም ውኃ ይፈወሳል፥ #ወንዙም በሚመጣበት ያለው ሁሉ #በሕይወት #ይኖራል።❞ —ሕዝቅኤል 47፥9። ❝አጥማጆችም በዚያ ይቆማሉ፤ ከዓይንጋዲ ጀምሮ እስከ ዓይንኤግላይም ድረስ መረብ መዘርጊያ ይሆናል፤ ዓሣዎችም እንደ ታላቁ ባሕር ዓሣዎች በየወገናቸው እጅግ ይበዛሉ።❞ —ሕዝቅኤል 47፥10። ከሆድህ የሚፈልቀው ይህ የሕይወት ውኃ ወንዞች በቃላት ማይብራራ ውጤት ያመጣል!! ሁሉ ያለው መንፈስ ነው። እርሱ እንዲሠራህና በአንተ እንዲሠራ ከፈቀድህ በተሠማራህበት መንገድ ሁሉ ፍሬያማ ትሆናለህ!! ሙሽሪት ከሙሽራሽ መንፈስ ጋር ተግባቢ፥ ስሚው፥ ለሠሪውም ለሥራውም እውቅና ስጭ!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
የመንፈስ ቅዱስን ያህል ኢየሱስን የሚያውቅ አገልጋይ የለም!! ❝እርሱ #የእውነት #መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል።❞ —ዮሐንስ 16፥13። የመንፈስ ቅዱስ የማንነቱ ፍቺ ከሆኑት ስሞች አንዱ #የእውነት #መንፈስ የሚለው ነው!! ለእውነት ማለትም ለኢየሱስ ያለው አንድ የምንተማመንበት ምስክር #መንፈስ #ቅዱስ ነው!! ወደ ኢየሱስ ያመጣህ ምርምርህ አይደለም!! ኢየሱስን በፍለጋህ አላገኘኸውም፤ በመንፈሱ ፈልጎ ያገኘህ እርሱ ነው!! ኢየሱስን ያለ መንፈስ ቅዱስ አላገኘኸውም፤ ያለ እርሱ አታጣጥመውም!! ወደ እውነት ሁሉ የመራን እርሱ ነው፤ ያወቅነውን ሁሉ ያወቅነው በመንፈስ ቅዱስ ምክንያት ነው!! የመንፈስ ቅዱስን ያህል ኢየሱስን የሚያውቅ አገልጋይ የለም!! ኢየሱስን ካወቅኸው በላይ ማወቅ ከፈለግህ መንፈስ ቅዱስን ተወዳጅ!! ጠይቅ፦ ኢየሱስን በማወቅ ብርሃን ነፍስህን ይሞላል!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
#ተቀብሎናል!! በክርስቶስ ኢየሱስ ያላችሁ ሁላችሁ ... እግዚአብሔር ተቀብሏችኋል!! የምስራች ...በፊቱ ሞገስ አግኝተናል!! በልጅነት ማዕረግ ተቀብሎናል!! ከክብር ጋር ተቀብሎናል!! ቅዱሳን ልጆቹ ሆይ ደስ እያላችሁ በፍቅሩ ተራመዱ!! በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት አሁን የምንሠራው ሥራ የለም!! በክርስቶስ የመስቀል ሥራ ተቀባይነት አግኝተናል!! ተቀብሎን ... በእርሱ ውስጥ እየኖርን ነው፤ ከክርስቶስ ውጭ አይደለንም!! ተቀብለነው ... በእኛ ውስጥ እየኖረ ነው!! በአሮጌው ኪዳን ...ሊቀ ካህናቱ ስለሕዝቡ ስለራሱም ኃጢአት መስዋዕት ያቀርባል። እርሱና መስዋዕቱ በእግዚአብሔር ተቀባይነት ካገኘ ሕዝቡም ተቀባይነት ያገኛሉ!! እርሱን ባይቀበለው ወይም በሞት ቢቀጣ ለሕዝቡ የመከራ ዓመት ይሆናል። የሕዝቡ ተቀባይነት የተወሰነው በእነርሱ ሥራ ሳይሆን በሊቀካህናቱ ሁኔታ ነው!! (ዕብራውያን 5፥3፤ 9፥25)። ይህ ተቀባይነት እስከ ቀጣዩ የስርየት ቀን ለአንድ ዓመት ብቻ የሚቆይ ነው!! የኛ ሊቀካህናት ኢየሱስ ድካም የለበትም፤ መስዋዕቱም (ራሱ) ነውር የለበትም። እርሱም መስዋዕቱም ለዘላለም ተቀባይነት አግኝቷል!! በእርሱ እኛም ተቀባይነት አግኝተናል!! በኢየሱስ ሥራ ስለመጣን አብ ያለ ፀፀት ተቀብሎናል!! የተቀበለን ልጁን አይቶ ነው!! ራሳችንን መጠየቅ ያለብን፦ እግዚአብሔር የልጁን የኢየሱስን ሥራ ተቀብሎታል? ኢየሱስ ላንተ እንደሠራ ተቀብለሃል? ኢየሱስ ላንቺ እንደሠራ ተቀብለሻል? መልሳችን አዎን እና አሜን ከሆነ ኢየሱስን ስንቀበል እግዚአብሔር ተቀብሎናል!! በፊቱ ለመቆም ድፍረት የሚሰጠንን ሥራ በክርስቶስ ሠርቷል!! በዚህ ሥራ ያለ ነቀፋ ያለ ኩነኔ በፊት መኖር ተሰጥቶናል!! የኛ ሥራ በፊቱ ሕያው መሆን አልቻለም ነበር። ለዚያ ነው እንዲቀበለን የሚያደርገውን ሥራ በልጁ የሠራው!! የተወደዳችሁ ልጆቹ ሆይ #የሠራችሁትን ሳይሆን #የተሠራላችሁን ተመልከቱ!! ❝እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።❞ —1ኛ ጴጥሮስ 2፥10። ከመቀበል አልፎ የእግዚአብሔር ወገን ሆነናል!! ምሕረት አግኝተናል!! ኢየሱስ መስቀል ላይ እያለ ..ለምን ተውከኝ? ማለቱ ትዝ አላችሁ? እርሱን ሲተወዉ እኛ ተቀባይነት አገኘን፤ ከእርሱ ፊቱን ሲያዞር ...ዞሮ ያዬው እኛን ነው!! የያሕዌ ዓይኖች በእኛ ላይ ናቸው!! ኢየሱስ የተተወዉ በእኛ ስፍራ ሆኖ ነው፤ እኛም የተገኘነው በእርሱ ሆነን ነው!! ኢየሱስ ትኩረት የሚሰጠው አጥቶ ነበረ፥ ትውልድ ፊቱን አዙሮበታል፥ እግዚአብሔር ትቶታል!! ሰማይ ምድሩ ለእኛ ትኩረት የሰጠዉ፥ ተቀባይነት ያገኘነው በዚህ ምክንያት ነው!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
አብን አውቃችኋል!! ❝ልጆች ሆይ፥ አብን አውቃችኋልና እጽፍላችኋለሁ።❞ —1ኛ ዮሐንስ 2፥13። አብን በምንጫችንንጭን ማወቅ ነው!! አብ ቡሩክ ምንጫችን ነው!! እግዚአብሔር "አባታችን ነው" የሚለውን እውነት በትክክል ከተረዳነው ሕይወታችን በሀሴት እና በዕረፍት ይሞላል!! ከስጋት፣ ከፍርሃት፣ ከሽንፈት እና ከዝቅተኝነት አስተሳሰብ ሙሉ በሙሉ ነፃ እንወጣለን!! አብን በመረጃ (Information) ስለማወቅ እያወራን አይደለም። ስለ አብ ማወቅ እና አብን ማወቅ ይለያያል። የተጻፈላቸው አብ ምንጭ፣ መገኛ እና የነገር ሁሉ ጀማሪ እንደሆነ የተረዱ ልጆች ናቸው። ጌታ ኢየሱስን አዳኝ እና ጌታ አድርገን የተቀበልን፥ በስሙም ያመንን ሁላችን ከራሱ ከእግዚአብሔር ተወልደናል!! እግዚአብሔር አባታችን ነው!! ኢየሱስን የማያውቅ አብን አያውቀውም!! በኢየሱስ የማያምን ከእግዚአብሔር አልተወለደም!! ያልተወለደ ደግሞ ወላጁን አያውቅም!! ❝እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም።❞ —ዮሐንስ 1: 13 ልጆቹ ሆይ ስለተገኛችሁበት ሕይወት እያወራዋችሁ ነው!! ስለተቀዳችሁበት ቡሩክ ምንጭ እያካፈልኳችሁ ነው!! እናንተ የታላቁ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁ!! #ከደህና ተወልዳችኋል!! እንኳን ተወለዳችሁ!! ከእግዚአብሔር በመወለዳችን ብቻ አሸናፊዎች ነን!! ከአሸናፊው የተወለደ ተሸናፊ መሆን አይመጥነውም!! እናንተ የአሸናፊው ልጆች አሸናፊነት ተሰጥቷችኋል!! ❝ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።❞ —1ኛ ዮሐንስ 5፥4 • አባት አብ የኢየሱስ አባት ነው!! ❝በአንድ ልብ ሆናችሁ በአንድ አፍ እግዚአብሔርን፥ እርሱም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት፥ ታከብሩ ዘንድ ...❞ —ሮሜ 15፥5-6። • ኢየሱስ ልጁ እንደሆነ አስታውቋል!! ❝እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።❞ —ማቴዎስ 3፥17። • ልጁን እንድንሰማው አዟል!! ❝ከደመናው፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።❞ —ማቴዎስ 17፥5። • ኢየሱስም አባቴ ብሎ ጠርቶታል፤ በፍቅር ተርኮታል፤ ፈቃዱን ፈጽሞለታል!! ❝ኢየሱስ ግን፦ አባቴ እስከ ዛሬ ይሠራል እኔም ደግሞ እሠራለሁ ብሎ መለሰላቸው።❞ —ዮሐንስ 5፥17። ❝መቼም ቢሆን እግዚአብሔርን ያየው አንድ ስንኳ የለም፤ በአባቱ እቅፍ ያለ አንድ ልጁ እርሱ ተረከው።❞ —ዮሐንስ 1፥18። ❝እነሆ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል።❞ —ዕብራውያን 10፥9። • የኢየሱስ አባት የእኛም አባት ሆኗል!! የኢየሱስ የመስቀል ሥራ ወደ ምንጫችን መልሶናል!! ❝በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፤❞ —ገላትያ 3፥26። • ልጆቹ ተብለን እንድንጠራ ፈቅዷል!! ❝የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን።❞ —1ኛ ዮሐንስ 3፥1። • አባ አባት ብለን እንድንጠራው የልጁን መንፈስ በውስጣችን ልኳል!! ❝ልጆችም ስለ ሆናችሁ እግዚአብሔር አባ አባት ብሎ የሚጮኽ የልጁን መንፈስ በልባችሁ ውስጥ ላከ።❞ —ገላትያ 4፥6። ልጆች ነን!! ልጅ የሚጣራው ... በምክንያትም ያለ ምክንያትም ነው!! የወንድሜ ልጅ ጧት ሲነጋ "ባባ" ይላል። አባቱ "አቤት" ይላል። ልጁ ቀጥሎ "ባባ" ይላል.... ልጁ ቀኑን ሙሉ እንዲሁ ሲል ይውላል። አባትም ደስ እያለው ሲጠጋጋው ይውላል!! አባታችንን እንዲሁ እንጥራው ... አባ!! አባት!! Abba, Papa, Daddy .... አባቴ፣ ምንጨ፣ መገኛዬ፣ ሕይወቴ፣ ዓለሜ፣ ማዕረጌ፣ .... አይቋረጥም እንዲሁ እንቀጥላለን!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ገደብ እና ወሰን ለሌለው የመንፈስ ጥበብ ራሳችንን እንስጥ!! ❝ዳንኤልም መልካም መንፈስ ስላለው ከአለቆችና ከመሳፍንት በለጠ፤ ንጉሡም በመንግሥቱ ሁሉ ላይ ይሾመው ዘንድ አሰበ።❞ —ዳንኤል 6፥3። ❝Then this Daniel was preferred above the presidents and princes, because an excellent spirit was in him; and the king thought to set him over the whole realm.❞ —Daniel 6:3 (KJV) ተራ ኑሮ ኖረን ማለፍ የለብንም። በእግዚአብሔር የታየልንን የላቀ ኑሮ መኖር፣ መልካም ተፅዕኖ መፍጠር፣ ለሌሎች ጥቅም መሆን እና አሳቡን አገልግለን ማለፍ እንችላለን። እንዴት? ለንጉሡ ህልምን፥ ለዳንኤል ፍቺውን የሰጠው #የልህቀት መንፈስ በእኛ ውስጥ እየኖረ ነው። ዝም ብሎ ለመኖር እንዳልመጣ ግልጽ ነው። በእኛ የእርሱን ሕይወት መግለጥ ይፈልጋል። ወደ ኢየሱስ ሲያመጣን ሥራ የጨረሰ ይመስላችኋል?አልጨረሰም!! የእኛን ተራ ኑሮ እያስቆመ፥ የኢየሱስን የከበረ ኑሮ ማስቀጠል ይፈልጋል!! (ገላ. 2፥20)። የሞተልን በእኛ ሕያው ሆኖ ይኖራል። ይህ ኑሮ መንፈሱ እኛን የሚያደርስበት ከፍታ ነው!! መንፈስ ቅዱስ ርህሩህ እና ቅን ነው፤ የእኛ ነገር በቀላሉ ይገባዋል። ማንም መሄድ ወደማይችልበት ወደ ነፍሳችን እና መንፈሳችን ጥልቀት መሄድ ይችላል። ሙሉ በሙሉ ልባችንን ልንጥልበት እና ልንደገፍበት ከፈቀድን የምድር ስበት ወደ ማይዘው አኗኗር ይስበናል!! መንፈስ ቅዱስ የእኛን ልብ መመርመር እና ማወቅ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርንም የልብ ምክር እና ፍላጎቱን ያውቃል። በእርሱ ውስጥ የተሻለውን ማየት እንድንችል ያግዘናል!! መንፈስ ቅዱስ በእርሱ የታየላችሁን ኑሮ ያሳያችኋል!! ከባለፉት ሦስት ዓመታት ይልቅ አሁን መገኘቱን የተራብኩት ጊዜ ነው!! እርሱ ወደ #እውነት #ሁሉ የመራኝ የኔታዬ፤ ያለፍኩትን ሁሉ ያለፍኩበት አለኝታዬ፤ ዓለሙ ሁሉ ትቶኝ ሲሄድ አጠገቤ ቆሞ ያበረታታኝ የበረሃ ጓዴ እንደሆነ መናገሬ ያኮራኛል!! የእርሱ #መገኘት በማንኛውም የሕይወት ገጽታ ሕይወት ሰጪ እንደሆነ አይቻለሁ፡፡ እርሱ ከምንፈልገው በላይ ያስፈልገናል!! #ከስጦታዎቹ በላይ መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገናል!! ለሰጭው ጊዜ እንስጥ!! ምን እንደሚፈልግ እንዲያወራን እንፍቀድ!!ገደብ እና ወሰን ለሌለው የእርሱ ጥበብ ራሳችንን እንስጥ!! በመንፈሱ የተሞላ፥ የሙላት ሕይወት...!? በየዕለቱ ጸጋና እውነትን [ክርስቶስን] ለመማር የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
የእግዚአብሔርን ቃል ደግመን እናስበው!! ❝እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፤ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፥❞ —መዝሙር 62: 11 ❝God hath spoken once; #twice have I heard this; that power belongeth unto God.❞ —Psalms 62: 11 (KJV) እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ነው የሚናገረው፤ እኛ ግን ሁለት ጊዜ መስማት አለብን። የመጀመሪያው እርሱ ሲናገር፥ ሁለተኛው የነገረንን ደግመን ስናስበው። እግዚአብሔር የነገረንን ደግመን እናስበው፣ እናሰላስለው፣ እናመንዥከው፣ የራሳችን አቋም አድርገን እናውራው!! እግዚአብሔር የነገረንን ስለምንረሳ ደግመን ለራሳችን እናስታውስ!! እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ሲናገር እኛ ሁለት ጊዜ እንስማው!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ከምንኖረው #ኑሮ ይልቅ የምንኖርለት #አላማ (Purpose) ይበልጣል!! እግዚአብሔር በእያንዳንዳችን ላይ ያለውን አላማ በመረዳት እንደግ!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
የፍቅር ትርጉም የሚገባን ከእኛ አስቀድሞ እኛን የወደደው ጌታ ሲገባን ነው!! እኛ እኛን ከመውደዳችን በፊት እርሱ እኛን መውደድ ጀምሯል!! አብ ለእኛ ያለው ፍቅር ማስረጃ አለው፤ እርሱም፦ የኢየሱስ ሞት!! ❝ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስሪያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም።❞ —1ኛ ዮሐንስ 4፥10 https://t.me/tetelestaye
Show all...
እግዚአብሔር #ለፈለገን ነገር መገኘት እርሱ ነው መኖር ማለት!! ለምን እንዳሰበን ማግኘት እርሱ ነው አላማ ማለት!! ስለ እኛ ያወቀውን ማወቅ እርሱ ነው እውቀት ማለት!! https://t.me/tetelestaye
Show all...
ሰው እንኳን ያለ መንፈስ ቅዱስ ያለ ልብስ ያስፈራል!! ሰው ከእግዚአብሔር መንፈስ ጋር መዋል እና ማደር ሲጀምር የሆነ እውቀት አይደለም የሚያውቀው፤ ከመታወቅ የሚያልፈውን ራሱን እግዚአብሔር ነው የሚያውቀው፡፡ ከመንፈሱ ጋር ስንጠጋጋ የሆነ መገለጥ ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ይገለጥልናል፡፡ ከራሱ ከእግዚአብሔር ጋር መነካካት ይሆንልናል፡፡ የበራልን እውቀት አይደለም፤ የእውቀት ምንጭ ነው፡፡ የሆነ ጥበብ ገብቶን አይደለም፤ ራሱ ጥበብ ውስጥ ገብተን ነው፡፡ "እግዚአብሔር አምላክ ነው፥ ለእኛም በራልን" (መዝ 118:27) በያንዳንዱ ማይክሮ ሰከንድ የመንፈስ ቅዱስ አብሮነት (Presence) ያስፈልገናል፡፡ በእያንዳንዱ ውሳኔያችን የመንፈስ ቅዱስ ምክር (Counseling) ያስፈልገናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የማያስፈልገን ጊዜ የለም፡፡ ለብቻችን ከሆንን የምናበላሸው ይበዛል፡፡ ከእርሱ እንክብካቤ ውጭ ያለ ሕይወት በምሬት እና በጉስቁልና የተሞላ ነው፡፡ ሰው እንኳን ያለ መንፈስ ቅዱስ ያለ ልብስ ራቁቱን ያስፍራል፤ ያሳፍራል፡፡ "በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።" (ዘካርያስ 4:6) ሐዋርያት ከኢየሱስ እንኳን ተምረው ያለ መንፈስ ቅዱስ አልተሠማሩም፤ እስኪ ወርድ መጠበቅ ነበረባቸው፡፡ (ሐዋ. 1፥8) ከሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 በፊት እና በኃላ ያላቸውን የሕይወት ልዩነት ስናይ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል አስፈላጊነት ይገባናል፡፡ በገረድ ፊት <አላውቀውም> ብሎ ያፈረበት ጴጥሮስ (ማቴ. 26፥74) በሺዎች ፊት በስልጣን ቃል ደፍሮ የመመስከሩ ምስጢር መንፈስ ቅዱስ ነው፡፡ (ሐዋ. 2፥1)። የእግዚአብሔር መንግሥት ሥራ ያለ መንፈስ ቅዱስ አይታሰብም፡፡ ስለዚህ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንሥራ፤ ሙሽራዋ (ቤተ ክርስቲያን) ያለ መንፈሱ ምንም ልትሠራ አትችልም፡፡ " ና " ያሉት ሙሽራ ኢየሱስ እስኪመጣ እየሠራት ይሠራባታል፡፡ (ራእይ 22፥17)፡፡ https://t.me/tetelestaye
Show all...