cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

🇪🇹🇪🇹ስለ እኛ እንወቅ 🇪🇹🇪🇹

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
141
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ዛፍ አንዲት ዛፍ ነበረች አምላክ የፈጠራት ውብ አድርጎ ነበር ከሆሉም የሰራት ገናም ልጅ እያለች ችግኝ ሁና በቅላ ማደጓን ቀጠለች አረሙንም ችላ ፀሀዩን ወጀቡን ሁሉን ተቋቁማ ሊቆርጧት ያሏትን አቅፋ አስታምማ ቂምን ሳትቋጥር ክፋን ይቅር ብላ በቅርጫፎቿ ሁሉን አስጠልላ ይቅርባይም ሁና ይቅርታን ሰበከች የተጣላን ሁሉ ይቅር ባይ አረገች እናማ ያኔ ለጋ እያለች የፈጠረት ጌታ በችግር በስቃይ ያሳደጋት ለታ ይህንን ያውቅ ነበር ለዛሬ መድረሷን የትናንቱን ቸግር የዛሬን ደስታዋን አቡሽ ጥሩየ 29/01/14
Show all...
ናፈቀኝ የሞት ጥላ ከቦኝ መሄጃ ሲሳነኝ ብርሃን የማላይ መሆኔ ሲሰማኝ የመኖሬ ተስፋ መንገዱ ሲጠፋኝ ሁሉንም ለበጎ ነው ማለቱን ተውኩኝ ምን ልሁን አምላኬ እየኖሮኩ ነው ብየ ተስፋ እንዳልሰጥ ለኔ መኖር ትርጓሜው ስላልገባኝ እኔ ብቻ እማ አምላኬ ሁሉም ናፍቆኛል ከአንተ መራቄም ይበልጥ ያሳመኛል ከደጅህ መጥቸ በቅዳሴ ዜማ እጣኑ ሽታ የወፎቹ ዜማ በተመስጦየ እራሴን ስሰማ ስምህን ጠርቸ ስዘምር ለራሴ በፍቅርህ ዝማሬ ሲታደስ መንፈሴ በዲቆናት ወረብ በካህናት ፆሎት በዘማሪያን መዝሙር በአረጋውያን ስግደት በአባቶች ምርቃት በመምህራን ስብከት ጭቀቴን እረስቸ እፎይ የምልበት ሁሉም ይፍቆኛል ካንተ መራቄም ይበልጥ ያሳመኛል አቡሽ ጥሩየ መስከረም 26
Show all...
ህይወት ህይወት ማለት እንቆቅልሽ የምድር ላይ ምን አውቅልሽ አንዱ በገንዘብ ተሞልቶ በመጠጥ በሽሻ እራሱ ስቶ የሀገሩን ባህል እርግፍ አርጎ እረስቶ ከጣራ ላይ ጣራ እየደረደረ በአርቴፊሻል ፍቅር እራሱን ያሰረ ለሰው መኖር ይልቅ ለራሱ የኖረ አንዳንዱ ደግሞ የልት ጉርስ አጥቶ ያገኛትንም ለሌሎች ሰጥቶ በመስጠት ብቻ እራሱን ያኖረ ትልቁን ትንሹን ሁሉን ያከበረ በፍቅር የኖረ አምላኩን አመስጋኝ ከተሰጠው ሌላ ምንም የማይመኝ እና ህይወት ፍትኋ ተዛብቶ ማግኘት የነበረው ጭራሹን አጥቶ ማጣት ያለበት ሰው በምድር ፈንጭቶ እኔም ስላልገባኝ ትርጉምሽ ከሰራ ይልቅ ለሰረቀ ማድላትሽ ከሌለው ይልቅ ላለው መጨመረሽ አልኩሽ ነሽ እንደ እንቆቅልሽ አቡሽ ጥሩዬ 04/02/14
Show all...
ሀገሬን አንዳንዶቹ ለሆዳቸው ብለው ታሪክና ቅርስን እየሸጡ በልተው ሀገርን ሲዘርፉ ሀገር ወዳድ መስለው እራስን እንደ እስሰት እየቀያየሩ ከነብስ ይልቅ ለስጋ እየኖሩ ማንነታቸውን በገንዘብም ሲያስሩ ለሀገር እድገት ብለው ዳገት እየሰሩ ፍቅርን ሰጠን ብለው ጥላቻን ሚሰብኩ በለያዩን ቁጥር እነሱ እየረኩ አሉ ደግሞ አንዳንዶች ለሀገር ሚኖሩ ከልዩነት ይልቅ ለአንድነት የሰሩ ጥላቻን አጥፍተው ፍቅር ያስተማሩ የአንድነትን ሚስጥር ለአለም ያበሰሩ እናማ ወገኔ ገንዘብ ጠፊ እንደሆን አውቀህ የማይጠፋ ታሪክ ለመስራትም ቁመህ ከራስ አልፈህ ለሀገርህ ሰርተህ እንድትኖር እላለሁ በአንድነት በጋራ ስርቆቱንም ትተን ለእድገት እንድስራ አቡሽ ጥሩየ 05/02/14
Show all...
እንዲህ ይታየኛል እንዲህ ያታየኛል ሀገሬ ሳስባት ከሀገራት ልቃ በእደገት ስንትንስፈፍ በቱሪስት መስህቧ ሁሉንም ስታጎርፍ ዘረኝነት ጠፍቶ ልጆቿ በአንድነት አንድ መሆንንም ለአለም ሚያሳዩበት ክፋን ይቅር ብለው አረሙንም ነቅለው ትርፍ የሆነው ከራሳቸው ቆርጠው መዋደድን ይዘው ጥላቻን አጥፍተው እርቅን ባህል አርገው በፍቅር መስርተው እንዲህ ይታየኛል ሀገሬን ሳስባት ዛሬ የኮሩባት ነገ ሲለምኗት የናቋትም ሁሉ እግራ ሲወድቁላት ቀደምት ታሪኳም አሁን ላይ አብቦ በልጆቿ ብርታት ይኖራል ተውቦ አቡሽ ጥሩዬ መስከረም 27
Show all...
አዳም ሄዋንን ሲያስፈጠራት አምላኩም ፈቅዶ ከጎኑ ሲሰራት ያውቅ ነበር አለማወቁን ያለ እሷ ባዶነቱን ግን እኔ አምላክ እሷን ሲፈጥር ካጥንቱ ወስዶ እሱን ሲያበስር ይመስለኝ ነበር ወስዶ የሰራት ከጭቅላቱ አለማሰቡን አውቆ እሷን መስጠቱ Tila abu
Show all...
ሰውን ላዩን አይተህ ከፈረጅክ የውስጡን ቀርበህ ካላወክ አታውቅም ማንነቱን እኔ ሚለውን እሱነቱን አንዳንዱ ጥርስ አሳይቶ መርዝ ይተፋል ፍቅር ዘርቶም ክፋት ያጭዳል እናማ በላይ ውበት ቢኮን ጥሩ የአዳም ዘሮች ገነት ላይ በነበሩ @Enate07
Show all...
ጥሩ ባሰብክ ቁጥር ጥሩ ይሰጥሃል ክፉ ያሰብክ ለት መጥፎ ያደርግሀል ሁሌም በልቡ ውስጥ ፍቅርን የያዘ በኖረበት ገዜም ለእግዜር ከታዘዘ ችግር ቢገጥመውም መከራው ቢከብደው እራስን አስጥሎ ሁሉንም ቢያስረሳው ሁሌም አምላክ አለ ከጎኑ ማይጠፋ ለቸገረው ሁሉ ልብን የሚያሰፋ እናማ የትም ሲሄድ አምላኩን የያዘ መንገድ አይጠፋውም እሱን ስለያዘ Tila abu @Enate07
Show all...
አንች የሰውነት ልኩ ማዕዛሽ ያማረ የመኖርሽ ሚስጥር በአምላክ የታሰረ አንች የተራበን አጎራሽ የወደቀውን አንሽ ከራስ አልፎ ለሌሎች ደራሽ አንች የመስጠት ስጦታ የክፋት ይቅርታ አንች ያየሽ የሚወድሽ ውበት ደምግባትሽን በፍቅር ሚመኙሽ ሁሉም አንችነትሽን በሁለቱም በኩል አሟልቶ የሰራሽ በውስጥም በውጭም የተጨነቀበሽ አንች ጨለማን ገፋፊ ብርሀን ፈንጣቂ የተከፋን ሁሉ በሳቅሽ አድማቂ አንች ሀዘንን ችግርን በ ደስታ ቀያሪ ለተከፋ ሁሉ ሁልግዜ ምትራሪ እኔም ስላወኩሽ አምስገኘ አምላኬን አይለውጠው እላለሁ ሁሌም ስብናሽን አቡሽ ጥሩየ 30/02/14
Show all...
መቸ ነው መቸ ነው ሚፈታ የአንድነት ሚጥሩ ሰላምስ ሚሰፍን መቸ ነው ባገሩ በሁሉም ነገር ላይ እርቀትን ፈጥረው እንዳንድርስበትም ከፍ አድርገው ሰቅለው ለማዕረግ ተብሎ ሕዝቡ አየታመሰ ከተዘራውም ላይ ዙሮ እየታረሰ ቡቃያው ሳይበቅል አራሹም ደክሞበት በገዛ መሬቱ ሌላ እያዘዘበት ማረምም ሲፈልግ ይከለክሉታል ማዳበሪያም ብለው መርዙን ይሰጡታል እምቦሳ አሳይተው ላሟን ይሰርቁታል ያላመረተውን ተናገር ይሉታል መቸ ያልቅ ይሆን የስግብግብ ነሮ ለራስ ጥቅም ተብሎ መዝጋት የሰውን ጉሮሮ እናማ ደሀውን ቀምተህ ሆድክን ብትሞላ ለራስ ጥቅም ብለህ ህዝብን ብታባላ ይዘገያል እንጅ መውደቅህ አይቀርም ስልጣን ጊዚያዊ ነው ሁሌም አይገኝም አቡሽ ጥሩየ 07/02/14 @Enate07
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.