The Gunners
Open in Telegram
የተረጋገጡ አርሰናልን የሚመለከቱ ዜናዎች የጨዋታ ውጤቶች እንዲሁም ትንታኔዎች የሚተላለፉበት ቻናል Join the channel to get only confirmed news, results and detailed statistical analysis about Arsenal
Show more1 505
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
1 505
Arsenal vs FC Barcelona, International: International Club Friendly live stream - Superabbit77 Football Live Stream For Free
https://devin3.live-streamfootball.company/livestream.html?y=MzczOTM5NV8x&icg=Tkc%3D
1 505
የአርሰናል ከዋክብት በስማቸው የተሰራ የ LA Rams ክለብ መለያ ተበርክቶላቸዋል
👉 LA Rams ማለት የአርሰናል ባለሀብት ክሮንኬ KSE(Kroenke Sports Entertainment) የሚተዳዳር በNFL (Natiinal football league) የሚወዳዳር ክለብ ነው
👉 አርሰናል ከ ባርሴሎና የሚጫወቱበት ሶፊ ስቴድየምም (70240 ተመልካች የመያዝ አቅም አለው) የነርሱ ነው
1 505
🗣 ዲላን ራይስ ቀሚኬል አርቴታ እጅግ ተደንቋል
"እግር ኳስን ፍጹም በተለየ መንገድ እያየሁት ነው። በእድሜህ እያደግህ ስትሄድና እንዲሁም በምትጫወትበት ጊዜ እግር ኳስን እንደምታውቅ ታስባለህ፣ ነገር ግን እንደ ማይክል ያሉ አሰልጣኞችን ስታገኝ ምንም እንደማታውቅ ትገነዘባለህ።"
🤔🤔 እኔ ደም እመለው ሞይስ እንዳይሰሙ ነው ሆሆሆ
1 505
በነገራችን ላይ አርሰናል ከባርሴሎና ጋር በጣም ዘግናኝ ሪከርድ ነው ያለው
👉 በነጥብ ጨዋታ (በሻምፒዮንስ ሊግ) 9 ጊዜ ተገናኝተው ማሸነፍ የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው ሁለት ጊዜ አቻ ሲወጣ 6 ጊዜ በካታሎኑ ስለብ ሽንፈትን ቀምሷል
1 505
ሚኬል አርቴታ የልጅነት ክለቡን ሲገጥም...
👉 ሚኬል አርቴታ እና ጓደኛው ዣቢ አሎንሶ በልጅነታቸው አንቲጉኦኮ ለሚባል አማተር ክለብ እየተጫዎቱ እያለ የሚያልሙት ለአካባቢያቸው ትልቅ ክለብ ሪያል ሶሲየዳድ (Royal Society) መጫዎት ነበር ሆኖም ሚኬል ከባርሴሎና የኮከቦች መፍለቂያ ከሆነው የእግር ኳስ አካዳሚ የሙከራ እድል አግኝቶ ፈተናውን አለፈና ላማሲያን ተቀላለቀለ - አርቴታ ላማስያ ከገባ ከ2 ዓመት በኋላ አሎንሶ ሪያል ሶሴዳድን ተቀላቀሎ ከመቶ በላይ ጨዋታዎችን ማድረግ ቻለ ከዛም ወደ ሊቨርፑል.....
👉 አርቴታ በአካዳሚው በነበረው እድገት በያኔው የክለቡ አሰልጣኝ ሉዊ ቫንሃል ስር ከዋናው ቡድን ጋር ልምምዶችን መስራት ቢችልም በሳምንቱ መጨረሻ ግን የሚጫወተው ለሁለኛው ቡድን (Barcelona B) ነበር ምክንያቱም ያኔ የቡድኑ አምበል የነበረው ፔፕ ጋርዲዮላ የአሁኑ የባርሳ አሰልጣኝ ዣቪ እና ኢንየስታ የመሳሰሉ ከዋክብት የታጨቁበትን የአማካይ ቦታ ፉክክር ሰብሮ መግባት አልቻለም
👉 ይባስ ብሎ ሉዊ ቫንሃል ተነስተው ሌላ አሰልጣኝ ሲተካ ትኩረቱን እንደነ አርቴታ ያሉ ወጣቶች እድል ከመስጠት ይልቅ እራሳቸውን በትልቅ ደረጃ ፈትነው ያለፉትን እነ ኢማኑኤል ፔቲትን (ከአርሰናል የተዘዋወረ) ስላደረገ የአሁኑ የአርሰናል አሰልጣኝ ለባርሴሎና የመጫዎት ዕድሉ ተመናመነ ከካታሎን መውጣቱም ግድ ሆነበት መውጫውም ፓሪስ ሆነች - PSG
👉 ይህ ብቻ ሳይሆን አርቴታ ጥሩ የሚባል የመሃል ሜዳ ተጫዋች የነበረ ቢሆንም ለሀገሩ ስፔን ብሔራዊ ቡድን አንድም ጨዋታ ማድረግ አልቻለም - የዚህ ሁሉ አንዱ ሰበብ የአሁኑ የባርሳ አሰልጣኝ ዣቪ ነው
👉 እንግዲህ ሚኬል አርቴታ ከ1 ቀን በኋላ የቀድሞ ክለቡን ሲገጥም ብዙ የልጅነት ትውስታዎችና ያልተሳኩ ህልሞችን ወደ ኋላ ማጠንጠኑ አይቀርም
1 505
አርሰናል 🆚 ባርሴሎና
👉 ሐሙስ ሲነጋጋ 11 : 30 (20/11/2015)
@ ሶፊ ስቴድየም (ሎስ አንጀለስ)
👉 መድፈኞቹ የአሜሪካ ጉዟቸው የመጨረሻ የሆነ ጨዋታቸውን ከሌላው የአውሮፓ ሃያል ክለብ ባርሴሎና ጋር ያደርጋሉ
👉 በማንቸስተሩ ጨዋታ ከነበራቸው ድክመት አሻሽለው እንደሚመጡ ተስፋ አደርጋለሁ በተለይ በአካል ብቃቱ ረገድ
1 505
'አሁን ሙሉ በሙሉ ጤነኛ ነኝ' ኤሚል ስሚዝ ሮው
👉 ''አሁን ጥሩ ስሜት ነው የሚሰማኝ ከቡድን አጋሮቸ ጋር ወደ ሜዳ መመለሴ በጣም ጥሩ ነው የኔ ፍላጎት በዚህ የውድድር ዓመት ተጨማሪ የጨዋታ ጊዜ ማግኘት ነው''
''ያለፈው ዓመት ለኔ በጣም ከባድ ነበር ስለዚህ አሁን በአዲስ መጀመር እና ለአርሰናል መጫዎት እንደምችል ማረጋገጥ እፈልጋለሁ''
''ሁለት ጊዜ ቀዶ ጥገና አድርጌያለሁ ስለሆነም ለኔ ሁኔታው በጣም ከባድ ነበር ነገር ግን ቤተሰቦቸ ጓደኞቸ እና ክለቡም አስቸጋሪውን ጊዜ እንዳልፍ ረድተውኛል አሁን ምንም የሚሰማኝ የህመም ስሜት ባለመኖሩ እና ወደ አቋሜ በመመለሴ በጣም ደስ ብሎኛል''
''ቀዶ ጥገና ሳደርግ ለመጀመሪያ ጊዜየ ነበር ለዛ ነው ውሳኔውንም ለመቀበል ከብዶኝ የነበረው ነገር ግን አደረግሁት አሁን ምንም አይነት የህመም ስሜት አይሰማኝም ሙሉ በሙሉ ጤነኛ በመሆኔም በጣም ደስ ብሎኛል''
በውነቱ ባለፈው ዓመት አርሰናል በጣም አጥቶት ነበር ይህ ዓመት ለስሚዝ ሮው እውነተኛ ብቃቱን የሚያሳይበት ድንቅ ዓመት ይሆናል ነገር ግን ከሃቬርትዝና ማርቲኔሊ ጋር ከባድ ፉክክር ይጠብቀዋል
