cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

🇨🇬በኣልጋድ /Baal-gad/

"በኣልጋድ" ማለት ባለ ዕድል፤አምላክ የረዳው ማለት ነው። @yezihalmgeziamlak --->group @yezihalmgeziamlak [---------------------------------------------] @etyotewahdo ---> channal @etyotewahdo ----®®®®®®®®®®®®-----

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
179
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

የውርስ ሀጢያት በመፅሀፍ ቅዱስ አይታወቅም።
Show all...
🚩 ክርስቶስ "አምላክ ነኝ" አላለምን? የክርስቶስን አምላክነት በማይቀበሉ ወገኖች በስፋት ከሚነሱት ጥያቄዎች መካከል ቀዳሚው "የቱ ጋር ነው ክርስቶስ በራሱ አንደበት "እኔ አምላክ ነኝ" ያለው?" የሚለው ነው። ይህን ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖች ክርስቶስ አንድም ጊዜ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም ሲሉ ይሰማሉ። ክርስቲያኑም ይህንን ጥያቄ በተለያየ መልኩ ሲመልሰው ኖሯል ነገር ግን እነዚህ ወገኖች ይህን አቋም ሲያራምዱ፥ አንድ የተሳሳተ ቅድመ ግንዛቤ ይዘው ነው። እርሱም ክርስቶስ አንድም ጊዜ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም የሚለው ነው። እነዚህ ወገኖች አንድም ጊዜ ክርስቶስ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ ብሎ እንደማያውቅ በምን አወቁ? ክርስቶስ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ አለማለቱን እንዴት እንዳወቁ ሲጠየቁ፥ መልሳቸው "በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ ያለበት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የለም" የሚል መልስ ይሰጣሉ። ማለትም፥ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አምላክ ነኝ ያለበት ቦታ ስላልተዘገበ፥ ብሎ አያውቅም የሚል ነው። ▶️ ይህ ግን እጅግ የተሳሳተ ቅድመ ግንዛቤ ነው። ምክንያቱም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ (በተለይ በወንጌላት) ያልተዘገቡ፥ ነገር ግን ክርስቶስ የተናገራቸው ብዙ ነገሮች አሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላልተዘገበ፥ የሆነ ነገር አልተባለም ወይንም አልተዘገበም ማለት አይደለም። ክርስቶስ በምድር ሳለ የተናገራቸው፥ ነገር ግን በወንጌላት ያልተዘገቡ ነገሮች አሉና። ለምሳሌ፦ "እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ። #ከሚቀበል ይልቅ #የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ የጌታን #የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።" (የሐዋርያት ሥራ 20:35) በዚህ ስፍራ ሐዋርያው ጴጥሮስ "ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው" የሚለውን የጌታ የኢየሱስ ቃል ሲያሳስባቸው እንመለከታለን። በዚህ ቦታ ላይ ሐዋርያው ክርስቶስ ተናግሮታል ያለው ቃል በወንጌላት ተዘግቦ አይገኝም። ነገር ግን የእርሱ ሐዋሪያ የሆነው ጴጥሮስ እንደ እርሱ ቃል ጠቅሶታል። ይህ ክርስቶስ በወንጌላት ያልተዘገቡ ብዙ ነገሮችን እንደተናገረ ያሳያል። ሌላ ምሳሌ፦ "ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት። #እግዚአብሔር #ብርሃን #ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት።" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 1:5) በዚህም ስፍራ፥ ሐዋርያው ዮሐንስ ከክርስቶስ የሰማውን መልእክት እንደሚያወራ ይናገራል። እርሱም፥ እግዚአብሔር ብርሃን እንደሆነና ጨለማ በእርሱ ዘንድ እንደሌለ ነው። በአራቱ ወንጌላት፥ ክርስቶስ ይህን ቃል ሲናገር አንመለከትም። ነገር ግን የእርሱ ሐዋርያ ከእርሱ የሰማው እውነተኛ መልእክት መሆኑን ተናገረ። ይህ ክርስቶስ በወንጌላት ላይ ያልተዘገቡ ብዙ ነገሮችን እንደተናገረ ያረጋግጣል። "ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ #ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት #አደረገ፤" (የዮሐንስ ወንጌል 20:30) በዚህም ቦታ ሐዋርያው ዮሐንስ ጌታ ኢየሱስ በዚህ መጽሐፍ (በዮሐንስ ወንጌል) ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት እንዳደረገ ዘግቦልናል። ይህ ክርስቶስ በወንጌላት ያልተጻፉ ብዙ ነገሮችን እንዳደረገና እንደተናገረ ያረጋግጣል። ሁሉም የክርስቶስ ስራዎችና ንግግሮች አልተዘገቡም "ኢየሱስም #ያደረገው ብዙ ሌላ ነገር ደግሞ አለ፤ ሁሉ በእያንዳንዱ #ቢጻፍ ለተጻፉት መጻሕፍት ዓለም ራሱ ባልበቃቸውም ይመስለኛል።" (የዮሐንስ ወንጌል 21:25) በዚሁ ስፍራም ሐዋርያው ዮሐንስ በምዕራፍ 20 ላይ የተጻፈውን ይደግመዋል። ክርስቶስ በወንጌል ላይ ያልተጻፉ ብዙ ነገሮችን አድርጓል። እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን እንድናምን የሚበቃን ተጽፏል (ዮሐ 20:31) በተረፈ ግን ሌሎች ብዙ ስራዎቹና ንግግሮቹ አልተጻፉም። ይህ ክርስቶስ በወንጌላት ያልተጻፉ ብዙ ነገሮችን እንደተናገረ ያረጋግጣል ✏️ ስለዚህ ክርስቲያን ያልሆኑ አካላት፥ ወንጌላት ላይ ክርስቶስ በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ ማለቱ ስላልተዘገበ ብቻ አላለም ማለት አይችሉም። ስላልተዘገበ ብቻ አላለም ማለት አይደለም። ክርስቶስ በወንጌላት ያልተዘገቡ ብዙ ነገሮችን ተናግሯልና ተቺዎቹ ክርስቶስ አምላክ ነኝ ማለቱን አናውቅም ማለት ይችላሉ እንጂ፥ በእርግጠኝነት አላለም ማለት አይችሉም። አለማለቱን የሚያረጋግጥ ምንም አይነት ማስረጃ የለም። አለማለቱን የሚያሳይ ማስረጃ እስከሌለ ድረስ፥ አፋቸውን ሞልተው አላለም ማለት አይችሉም። በወንጌላት አለመዘገቡ፥ ላለማለቱ ማስረጃ አይደለምና። መጽሐፍ ቅዱስ ወይ ቃል በቃል "ክርስቶስ አምላክ ነኝ አላለም" እስካላለ ድረስ ወይንም ደግሞ ብሎ እንደማያውቅ እስካላስተማረ ድረስ ወይንም ደግሞ ሊል እንደማይችል ከመጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጥ እስካልተቻለ ድረስ አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም ማለት አይቻልም። ይህ አይነቱ ማስረጃ እስካልቀረበ ድረስ፥ የሚቻለው አናውቅም ማለት ብቻ ነው። ♦️ ይህ የኢ-ክርስቲያናዊያንን ሙግት በይበልጥ ያደክመዋል። ምክንያቱም የክርስቶስ አይን እማኝ የሆኑት ሐዋርያት እግዚአብሔር መሆኑን መስክረዋል፥ ነቢያትም በትንቢታቸው የሚመጣው መሲህ አምላክ መሆኑን ተንብየዋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ክርስቶስ ራሱ፥ አምላክ ብቻ ያሉት ባህሪያት እንዳሉት ተናግሯል፥ መለኮት ብቻ ሊሰራቸው የሚችላቸውን ስራዎች ሰርቷል፥ እግዚአብሔር ብቻ ያሉት ስሞች እንዳሉት ተናግሯል። ይህ ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው ክርስቲያን ያልሆኑ ወገኖች ለተቃውሟቸው የሚያነሱት ሙግት በራሱ አንደበት አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም የሚል ነበር። ነገር ግን አሁን እንዳየነው፥ እንደዛ ማለቱን አናውቅም ማለት እንጂ አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም ማለት አይችሉም። ይህ የእነርሱን ተቃውሞ እጅግ ደካማ ያደርገዋል። ባለማወቅ ላይ የተመሰረተ ሙግት ነውና። ▶️ ስለዚህ የትኛውም የክርስቶስ ተቃዋሚ "ክርስቶስ አምላክ ነኝ ማለት አለማለቱን አናውቅም" እንጂ ማለት የሚችለው፥ አፉን ሞልቶ "አምላክ ነኝ ብሎ አያውቅም" ማለት አይችልም
Show all...
+ ከነፍስሽ ነስፍ ነሥቶ + ሁሌም ቢሆን በጸሎታችን ላይ "... መልአክ ወደእርሷ ገብቶ እንዲህ አላት ደስታ ይገባሻል እግዚአብሔር ከስጋሽ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ..."[ይዌድስዋ መላእክት አንቀጽ 2] እያልን እንማጸናለን ። ይህ ቃል "ክርስቶስ ከማርያም ስጋን አልወሰደም" ለሚሉ ሙሉ በሙሉ ፣ "ስጋን ቢወስድም ነብስ ግን አልወሰደም " ለሚሉት ደግሞ በከፊል ያሰናክላል ። ሰው ሲወለደ ነፍስ የተባለው የሕይወትን እስትንፋስ የሚቀበለው ከእናትና ከአባቱ ነው የሚለው ሀሳብ Traducianism ይባላል ። ልክ ጌታችን ኢየሱስ በሐዋርያት ላይ መንፈስን እፍ ብሎባቸው ስልጣንን እንደሰጠቸው[ዮሐ 20፡21-23] ከዛ በኋላ ግን ያንን ስልጣን ሌሎች ከተሾሙት ከሐዋርያት እንደተቀበሉና ጌታ ተመልሶ ሌላ ማንም ላይ እፍ እንዳላለ እንዲሁ ደግሞ የሕይወትን እስትፋስ በአዳም ላይ እፍ ተብሎ ሌሎች ከርሱ በቅብብሎሽ ያገኙታል እንጂ ጌታ ተመልሶ ማንም ላይ እፍ አይልም። ዶግማ ባይሆንም ይህ ትምህርት በእኛ ቤተክርስትያን ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ነው፤ ለዚህም ማሳያ የሚሆነን ቅዱስ አባ ጊዩጊስ ዘጋስጫ "የሁለታቸው (እናትና አባት) ሥጋና ደም አጥንትና ጅማቶች ነፍስና የሕይወት እስትንፋስ ተዋህዶ ወንድም ቢሆን ሴትም ብትሆን እግዚአብሔር ባደለው ገንዘብ አንድ ሕፃን ይሆናልና "ሲሉ የጻፉት ነው(መጽሀፈ ሚስጥር 23፡16) ። እንደውም አባ ጊዩርጊስ ከዚህ ሌላ ትምህርት ሲያስተምሩ የነበሩት እንደመናፍቅ ቆጥሯቸው ገስጿቸዋል በቅድሚያ በመጽሀፍ ቅዱስ ከአዳም ውጪ ሌላ የሕይወትን እስትንፋስ በእፍታ የተቀበለ ማንንም አናይም፡ ሔዋን እንኳን እግዚአብሔር ከአዳም ጎን አንዲት አጥንትን ወሰዶ ሴት አድርጎ ሠራት እንጂ የሕይወትን እስትንፋስ እፍ አላለባትም ፤ " የሕይወትን እስትንፋስ መቀብል በእናታችን በሔዋን ተቋርጧል... በእጅ መሠራትን ግን ተሠርታለች ትወለድ ዘንድ እናት የለቻትምና ። " የክርስቶስ ስብዕና ከኛ የተነሳ በመሆኑ ከኛ ጋር አንድ አይነት ባህሪ ነው እንላለን። ቫለንቲኖስ የክርስቶስ ስጋ ከሰማይ የመጣ እንጂ ከማርያም የተነሳ አይደለም በማለቱ የክርስቶስ ስብዕና ከእኛ ባህሪ ጋር አንድ የሆነ መሆኑን እንደመካድ ተቆጥሮበት ተወግዟል። ነብስም ብትሆን ከሰው ካልተነሳች የክርስቶስ ስብዕና ከእኛ ባህሪ ጋር አንድ መሆኑ ይቀራል ፤ ወይስ ስብዕናው ከእኛ ጋር አንድ የሆነው በስጋ ብቻ ነው? ሰው የሕይወት እስትንፋሱን(ነብሱ) ከእናትና ከአባቱ የማያገኝ ከሆነ፤ ነብስን እግዚአብሔር ልክ ስጋ በተጸነሰ ሰዐት ፈጥሮ ይሰጣል ማለት ሊኖርብን ነው። የሰው ልጅ ሰብዐዊ ባህሪ ከአዳም ውድቀት በኋላ ጉስቁልና ደርሶበታል የምንል ከሆነ ደግሞ እግዚአብሔር ለሰዎች ጉስቁልና የደረሰበትን ነብስ እየፈጠረ ይሰጣል ወደሚል ስህተት የሚያመራ ይሆንብናል። #traducianism #soul
Show all...
የገዳም ሕይወት ለምን አስፈለገ..?? የዮሐንስ ወንጌል 17 15፤ ከክፉ እንድትጠብቃቸው እንጂ ከዓለም እንድታወጣቸው አልለምንም። @Apostolic_Answers
Show all...
————— የሚያድነው ሥራ እንደምን ያለ ነው..?? @Apostolic_Answers
Show all...
Watch "_ክርስቲያናዊ መልሶች" on YouTube https://youtu.be/72SlrtMHsto
Show all...
_ክርስቲያናዊ መልሶች

በግ መሆን ይቀድማል ወይስ ማመን..?? በካልቪኒስቶች የሚጠቀስ ጥቅስ ዮሐ 10: 26
Show all...
ታቦት በሐዲስ ኪዳን @Apostolic_Answers
Show all...
የእግዚአብሔር መገለጥ οὐσία(ኡሲያ)፡ ባህሪ ἐνέργεια(ኤኔርጌያ)፡ መገለጥ
Show all...
በገነት መቶ ሚስት እንዳለ በመጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ተናግሯል? ማቴ 19፥29 ማር 10፥29 @orthodoxApologetics
Show all...