ALFARUK MULTIMEDIA®
Open in Telegram
✨ ቀደምቱ አል-ፋሩቅ ኦዲዮ ቪዥዋል ፕሮዳክሽን በአዲስ አቀራረብ ተመለሰ! ✨ ጥራት ያላቸውን ፊልሞች፣ ሙሃደራዎችን፣ ነሺዳዎችን እና መንዙማዎችን ይዞላችሁ ቀርቧል። 📌 የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ 👉 [Join Channel] (https://t.me/ethioalfa) ▶️ የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ፡ 👇👇👇 https://www.youtube.com/channel/UCDIi
Show more3 819
Subscribers
+1024 hours
+347 days
+26130 days
Posts Archive
3 824
በፍቅር የታመመ ልብ… ከሀበሻ ምድር እስከ ጦይባ! ✨
አንድ ወረቀት፣ ጥቂት የሠርዶ ቀለም እና በጥልቅ ናፍቆት የታሰረ ልብ…
ይህ በቃላት ለመግለፅ የሚያቅት፣ በስሜት እንጂ በጽሁፍ ተተርጉሞ የማያልቅ የፍቅር ጥግ ነው!
"ጌታዬ እንዴት ነሁ… ምነው ባየንሁ?"
የኡስታዝ ሰኢድ አህመድ ድንቅና ስሜት ቀስቃሽ ግጥም በማዲህ መሀመድ አሚን በሚገርም ዜማ በጣፋጭ ድምፅ ሲታጀብ—ሩህ ቀድማ ወደ መዲና ትበራለች! እግር ሀበሻ ምድር ቢሆንም፣ ቀልብ ግን የጦይባን አየር መተንፈስ ይጀምራል።
✨ ያንን ውበት ማን በነገረው?
ከሰማይ ጨረቃ ይልቅ የሚያበራውን ያንን ሙሉ ጀማል…
ጠላትን እንኳ ሳይቀር በምህረት እና በእዝነት የሚያረክሰውን ያንን መልካም ጧይባ…
ግንድ እና ድንጋይ ሳይቀር ነቢይነትዎን የመሰከሩለትን ያንን ድንቅ ሀይባ…
እስኪ እንዴት ብሎ ዝም ይበል? ናፍቆቱ እኮ አቅም አሳጥቶ ልብን ይዘርፋል!
መሬቱ፣ ዳመናው፣ ዛፉ፣ እንስሳቱ ሁሉ ላንቱ ሰገዱ፤ ጨረቃ እንኳን ለሁለት ተከፈለች… ታዲያ የሰው ልጅ ልብ እንዴት አይንሰቀሰቅ?
እነዚያ አሺቆች፣ እነዚያ ሶሃባዎች እኮ በፍቅርዎ ሰክረው ነው «እየሞቱ የኖሩት፣ እየኖሩም የሞቱት»!
የሲዲቅ ፍቅር፣ የኡመር ጀግንነት፣ የኡስማን ልግስና፣ የዐሊይ ወኔ፣ የሀምዛ አንበሳነት፣ የቢላል ናፍቆት… ሁሉ የዚያ ታላቅ ኑር ነፀብራቅ ነበር።
"ያዙት ወዳጅሁን ዘርግተሁ እጅሁን…
ራህመት መሙላቱን አውቃሁ ልብሁን፤
ያስክኑልኝ አሁን ሳይገለኝ ሁብሁ!"
በኡስታዝ ሰኢድ አህመድ ግጥም ተፅፎ፣ በማዲህ መሀመድ አሚን ድንቅ አዜብ የቀረበው ይህ ልብ የሚነካ መንዙማ በአልፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን (Al-Faruk Multimedia Production) ይፋ ሆኖ ተለቋል!
👇 አሁኑኑ ገብታችሁ በመመልከት የረሱልን (ﷺ) የፍቅር ማዕበል አብራችሁን ተካፈሉ፦
[https://youtu.be/DiuZ0XciVNI?si=MWQ1lljFOdIneud5]
#አልፋሩቅ_መልቲሚዲያ #ኡስታዝ_ሰኢድ #መሀመድ_አሚን #መንዙማ #ናፍቆት #ጦይባ #መዲና #የፍቅር_መንገድ #ሶለዋት
3 824
ቁረተል ዓይኔ የሐበሾች የፍቅር ልሳን!
ከጥንት ከጠዋቱ የተዘረጋ የፍቅር መረብ ሐበሾች ዘንድ አለ። ይሄ ፍቅር ብዙዎችን በዝምታ አርምሞ ውስጥ ዱሏል። የርካቶችን የልብ አታሞ እየደለቀ በትዝታ ሲያከንፍ ሰንብቷል። ናፋቂና አፍቃሪዎችን በቃላትና በስንኝ ሲያናግር ኖሯል።
ሐበሻ ለፍቅር ርቀት ያልገደባት፣ ከጥንት እስከ ዛሬ ናፍቆት የወለዳቸው ቅኔዎች የሚከረርባት አንባ ነች። ይሄ ኑባሬ ቀደምቶቻችን ያሰመሩትን ቀኖና ይዞ እስካሁ እየተጓዘ ነው።
ቀደምቶቻችን ተወዳጁን ሰይዳችንንﷺ ቁረተል ዓይኔ ሲሉ አወድሰዋል። ያይኔ ማረፊያ ሲሉ ዘክረዋል። ይሄ ትውልድም ይህንኑ የውዳሴ መንገድ አጥብቆ ይዞታል። የአበው ውርስ አድርጎ ተቀብሎ ከዘመኑ ጋር እያራመደ ይገኛል።
አሁንም ሐበሾች በየ ጊዜው ቁረተል ዓይኔ እንላለን። የዘመኑ ጥበባዊ አንድምታን ተከትሎ በተለያዩ ገጣሚያን ቀለም እየተቀዳ በማዲሆቻችን ልሳን ውዱ ነቢ ሲወደሱ ይኖራሉ።
ታላቁ የውልደታቸው ወር ወርሃ ረቢዕም ድባቡን ማሸብረቅ ጀምሯል። እኛም በተለያዪ ቀለማት፣ በተለያዪ ማዲሆቻችን ልሳን…አሽረፈል ኸልቅንﷺ ቁረተል ዓይኔ እንላለን!!
በቅርቡ ከሚለቀቁ ቁረተል ዓይኔዎች ውስጥ አንዱ በገጣሚያችን ዛሒድ ኢቅባል ተፅፎ በድምፀ መረዋው ማዲህ አንዋር አል ቡርዳ የተዘከረው ቁረተል ዓይኔ ነው።
በቅርብ ቀን ለታዳሚያን ይደርሳል!
3 824
የአልፋሩቅ ሱፐርአፕ
(Al Faruk SuperApp) ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ላይ አጠቃሎ የያዘ በመሆኑ አጠቃቀሙ በጣም ቀላል እና ምቹ ነው። መተግበሪያውን በአግባቡ ለመጠቀም የሚከተሉትን ጥቂት ደረጃዎች መከተል በቂ ነው።
#muslimtiktok #foryoupage #alfaruk_multimedia_production #alfaruk #viralvideo @Alif Videography
3 824
ይህ ፊልም الخوافي والقوادم በሚል ርዕስ የተሰራ የግልፅና የህቡዕ ወይም የውጪና የውስጥ ድጋፍ የሚል ትርጉም ያለው በሁለቱ የነብዩ ክቡራን አጎቶች ሰይዱና አል ዓባስ እና ሰይዱና ሐምዛ የህይወት ገድል ዙርያ የሚያጠነጥን ድንቅ ፊልም ነው። ፊልሙ ሐምዛ ቀድመው ሰልመው ለነብዩ ይሰጡ የነበረውን ድጋፍ፤ አል ዓባስ ዘግይተው ቢሰልሙም ከእስልምና በፊት እንኳን ሁለንተናዊ ድጋፋቸው ለነብዩ እንደነበርና በቀዳሚው የእስልምና ዘመን ያበረከቱትን አስተዋፅዖ ያስቃኛል።
አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽንም ይህንን ታሪካዊ ፊልም ለአማርኛ ተናጋሪው ማህበረሰብ በማድረስ ላይ ያለውን ሃላፊነት በመረዳት፣ ለታሪኩ እውነትነት እና ለኢስላማዊ እሴቶች ቅድሚያ በመስጠት በጥንቃቄ አስተርጉሞ አቅርቧል። ፊልሙን በምናዘጋጅበት ጊዜ፣ የፊልሙን ስሜት እና ጥልቀት ለመጠበቅ የተለየ ትኩረት ተሰጥቷል። ዓላማችንም ይህንን ውድ የታሪክ ቅርስ ተደራሽ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ተመልካቾቻችን የታሪኩን መልክ በትክክል ተረድተው እንዲማሩበት ጭምር ነው። በመሆኑም የምንግዜም አገልጋያችሁ አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ይህንን ታሪካዊ ፊልም በአማርኛ አስተርጉሞ በአቻ የትወና ትርጉምና በላቀ ጥራት ወደናንተ ሲያቀርብ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል። ዕሮብ ምሽት 12:00 ላይ ይጠብቁን።
መልካም ጊዜ!
3 824
የአልፋሩቅ ሱፐርአፕ (Al Faruk SuperApp) ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ላይ አጠቃሎ የያዘ በመሆኑ አጠቃቀሙ በጣም ቀላል እና ምቹ ነው። መተግበሪያውን በአግባቡ ለመጠቀም የሚከተሉትን ጥቂት ደረጃዎች መከተል በቂ ነው፦
3 824
ጽህና፣ እምነትና ተአምር፡
የዓለም ሴቶች ሁሉ አርአያ፣ የጽናትና የትሕትና ተምሳሌት! በቅዱሳን ቁርኣን የተመሰከረላት ሴት ማናት ? ወዳያው በአእምራቹ ማን ከሰተች? ። ከዚህ ቀጥሎ አንድ ጥቆማ ብነግራቹ ወዲያው ታውቃታላቹ በሰሙ የቁርኣን ሱራ የተሰየመላት ።
አዎ አሁን እንደምታውቋት ተሰፋ አድርጋለሁ ?
ቅድስት መርየምን ያላቹ ራሳቹን ሸልሙ
እና ምን ልላቹ ነው የመርየም ታሪክ ከልጅነት እስከ ተአምረኛው የልደት ጉዞ ድረስ በታላቅ ጥበብ የተሰነደው ድንቅ ፊልም አሁን በአልፋሩቅ ቀርቧላቹሃል ።
አል ፋሩቅ መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን ይህን በአለማቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኘ ተከታታይ ፊልም በአማርኝ ሲያቀርብ በታላቅ ደስታ ነው።
እና የቅድስቷን መርየምን ታሪክ ማውቅ የወዴታ ግዴታ ነው ብያለሁ ።
3 824
ይህ ፊልም الخوافي والقوادم በሚል ርዕስ የተሰራ የግልፅና የህቡዕ ወይም የውጪና የውስጥ ድጋፍ የሚል ትርጉም ያለው በሁለቱ የነብዩ ክቡራን አጎቶች ሰይዱና አል ዓባስ እና ሰይዱና ሐምዛ የህይወት ገድል ዙርያ የሚያጠነጥን ድንቅ ፊልም ነው። ፊልሙ ሐምዛ ቀድመው ሰልመው ለነብዩ ይሰጡ የነበረውን ድጋፍ፤ አል ዓባስ ዘግይተው ቢሰልሙም ከእስልምና በፊት እንኳን ሁለንተናዊ ድጋፋቸው ለነብዩ እንደነበርና በቀዳሚው የእስልምና ዘመን ያበረከቱትን አስተዋፅዖ ያስቃኛል።
አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽንም ይህንን ታሪካዊ ፊልም ለአማርኛ ተናጋሪው ማህበረሰብ በማድረስ ላይ ያለውን ሃላፊነት በመረዳት፣ ለታሪኩ እውነትነት እና ለኢስላማዊ እሴቶች ቅድሚያ በመስጠት በጥንቃቄ አስተርጉሞ አቅርቧል። ፊልሙን በምናዘጋጅበት ጊዜ፣ የፊልሙን ስሜት እና ጥልቀት ለመጠበቅ የተለየ ትኩረት ተሰጥቷል። ዓላማችንም ይህንን ውድ የታሪክ ቅርስ ተደራሽ ማድረግ ብቻ ሳይሆን፣ ተመልካቾቻችን የታሪኩን መልክ በትክክል ተረድተው እንዲማሩበት ጭምር ነው። በመሆኑም የምንግዜም አገልጋያችሁ አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን ይህንን ታሪካዊ ፊልም በአማርኛ አስተርጉሞ በአቻ የትወና ትርጉምና በላቀ ጥራት ወደናንተ ሲያቀርብ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል። መልካም ጊዜ!
Al Faruk App
👇👇👇👇👇
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.alfaruk.app
3 824
ወጣትነት አንዳንድ ጊዜ በትናንሽ ስህተቶችና በትላልቅ ፀፀቶች ውስጥ ማለፍን ያካትታል። "አልቻልኩም፣ ጠፋሁ" ብለህ/ሽ ተስፋ በቆረጥክበት ሰዓት፣ የአሹራ ፆም መላእክታዊ መልዕክት ይዞ ይመጣል፦ "አሁንም ዕድል አለህ!" የፈጣሪ እዝነት ከአንተ/አንቺ ስህተት እጅግ እንደሚሰፋና በአንድ ቀን ፆም የዓመት ቆሻሻን ማጽዳት እንደሚቻል ማሳያ ነው።
3 824
ዐሹራ በእስልምና ታሪክ ውስጥ፣ በማስታወሻዎች የታጀበ ከፍተኛ ቦታ ያለው ቀን ነው። ይህ ቀን በሒጅራዊ አቆጣጠር የመጀመሪያው ወር በሆነው ሙሐረም ወር 10ኛው ቀን ነው። በዚህ ቀን የተፈጸሙ ብዙ ታላላቅ ክስተቶች በሙስሊሞች ዘንድ በክብር ይታወሳሉ።
ነብዩ ﷺ ወደ መዲና በተሰደዱ ጊዜ አይሁዶች በሙሐረም 10 ጾም ሲጾሙ አገኟቸው። ቀርበው ምክንያቱንም ጠየቁ በዚህ ጊዜ። “ይህ አላህ ነቢዩ ሙሳን (ዐ.ሰ) እና ሕዝቦቹን ከፈርዓውን ጭቆናው ያዳነበት ቀን ነው” ብለው መለሱላቸው።
የነገሩን ጥልቀት እና እውነተኛ መሰረቱን የተረደቱት ነቢዩ ﷺ …“እኛ ሙሳን ከእናንተ የበለጠ እንከተላለን።”አሉ።
ከዚያም እርሳቸው የአሹራን ፆም ጾሙት፣ ሰሓቦቻቸውንም እንዲጾሙ አዘዙ።
በ ሶሒሕ ሙስሊም በሰፈረው ሐዲስ መሰረት…ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
«የዐሹራን ጾም የፆመን ሰው አላህ ያለፈውን አንድ ዓመት ኃጢአት ያብስለታል»
እዚህ ላይ እንደተጠቀሰው ትንንሽ ኃጢአቶችን እንጂ ትልልቅ ኃጢአቶችን አይጨምርም። ይሁንና ትልቅ ምንዳን የሚያጎናፅፍ የተባረከ የነብዩ ሱና ነው።
የአሹራን 9ኛውን እና 10ኛውን ቀን መጾም ተወዳጅ መሆኑን ዓሊሞቻችን ይመሰክራሉ። 10ኛውን እና 11ኛውን ቀን መጾምም እንዱሁ።
የዐሹራ ዋናው የሃይማኖት ተግባር ከመጾም ባሻገር፣ አላህን ማስታወስ፣ ዱዓ ማድረግ፣ ቁርኣንን መቅራት እና ሌሎች መልካም ሥራዎችን ማብዛት ነው።
ዐሹራ የተራ ቀን አይደለም።አላህ አማኞችን እንደሚረዳ እውነት በመጨረሻ እንደሚያሸንፍ በችግር ጊዜ ትዕግስት ምን ያህል አስፈላጊ መሆኑ፣ ውጤቱም ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ምልክት ነው።
ለእምነትና ለመርህ መቆም እንዳለብን
የአላህን በረከት አስተንትነን ማመስገን እንደሚገባን ያስታውሰናል።
3 824
ነብዩላሂ ሱለይማን ታሪክ ልጋብዛቹ
ንግስናቸውንና ነብይነታቸውን ከአባታቸው ዳውድ ከተረከቡ በኋላ በእየሩሳሌም ላይ አጥልሎ የነበረውን የጂኖች ተፅዕኖ ለመጋፈጥ የሚያደርጉትን ተዓምራዊ ተጋድሎ በዘመነኛ ጥራትና ትወና ተውቦ ቀርቦላቹሃል ።
ይሄን ድንቅ ፊልምም እንደተለመደው
አል ፋሩቅ መልቲሚዲያ ፕሮዳክሽን በአማርኛ አስተርጉሞ በከፍተኛ ጥራት ቀርቦላቹሃል ።
