cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ዛብሎን ዜማ

NEW MEZMUR EVERYDAY

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
293
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

🔹pm abiy ahemd 🔹Contact me @Davemik 🔹Phone 0936635903 🔹 #Quality Printing 🔹ይዘዙን!!! 🚚 FAST DELIVERY 🛵 🔎🔎🔎ለስጦታ የሚሆኑ ያልተገለፁ ብዙ ስራዎች አሉን ይጎብኙን።🔍🔍🔍 👇👇👇👇 @Davemik join by link https://t.me/+7QWMflZFK4FmNzI0
Show all...
IMG_1011.MOV5.41 MB
Are gud new are kahun behula begizi enwetalen
Show all...
. የማልደርስበት ላይ መስከረም ጌቱ | New Clip 🕑-5:31Min◦💾-10.8MB sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ▷ @yedestaye_elilta ◁ ▷ @yedestaye_elilta△Join Us△
Show all...
የማልደርስበት_ላይ_YEMALDERSBET_LAY_New_Ethiopian_Gospel_song_Hq2GVq_geb4.mp418.80 MB
. የማልደርስበት ላይ መስከረም ጌቱ | New Clip 🕑-5:31Min◦💾-6.6MB sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ▷ @yedestaye_elilta ◁ ▷ @yedestaye_elilta△Join Us△
Show all...
4_6017337881360599436.mp36.59 MB
. ኢየሱስ ሜሮን አለሙ | New Clip 🕑-8:10Min◦💾-25.5MB sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ▷ @yedestaye_elilta ◁ ▷ @yedestaye_elilta△Join Us△
Show all...
Meron_Alemu_Judi_ኢየሱስ_eyesus_ሜሮን_አለሙ_New_Amharic_gospel_ULBI5sfNMAI.mp425.48 MB
. ኢየሱስ ሜሮን አለሙ | New Clip 🕑-8:10Min◦💾-8.9MB sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ▷ @yedestaye_elilta ◁ ▷ @yedestaye_elilta△Join Us△
Show all...
4_6012709727681645050.m4a8.91 MB
╔═══❖• •❖═══╗ የጠፋው ሬሳ ╚═══❖• •❖═══╝ ክፍል ሶስት ...በጣም ደነገጥኩኝ ልቤ እጥፍ መምት ጀመረ በአንዱ ዛፍ ራሴን ከይታ ሸሽጌ ሚሆነውን ማየት ጀመርኩ...የመኪናው በር ተከፈተ ወዲያውኑ ፀጉሩ የተንጨባረረ አይኖቹ በቁጣ የፈጠጡ ፊቱ በፂም የተወረሰ አንድ ሰው ከመኪናው ወረደ የለበሰው ጃኬት ከማደፉ የተነሳ ምን አይነት ከለር እንዳለው ለመገመት ይከብዳል ሱሪው በደም የተጨመላለቀ ነው ከስክስ መሳይ ጫማ አድርጓል ቀስ እያለ ወደኛ መኪና ማዝገም ጀመረ አሁን ወደኔ እየተቃረበ እየመጣ ነው እጅግ በጣም ፈራሁኝ እየደጋገመ መኪናውን አትኩሮ ተመለከተው...በእኔና በሰዬው መሀል ያለው ርቀት የሶስት ሜትር ቢሆን ነው...ከመኪናዋ ጀርባ ሄዶ ዝም ብሎ ቆመ የሚያረገውን ነገር በነበርኩበት አቅጣጫ ሆኜ ለማየት ስለቸገረኝ አመቺ ቦታ ፍለጋ ወደሌላኛው ዛፍ ስሮጥ ተጋድሞ የነበረ ግንድላ ጠለፈኝ ልክ ስወድቅ ሰውዬው ወደኔ አቅጣጫ ከመቅፅበት ዞረ ፈጣሪ ሲረዳኝ ልክ ዛፉ ጋ ስወድቅ ስደርስ ነበር የወደኩት ወዲያውኑ ራሴን ከእይታው ሰወርኩ...ቀስ ብዬ ስመለከተው አሁንም ወደኔ አቅጣጫ እየተመለከተ ነው እንዳጋጣሚ ከጫካው ውስጥ በዛ ያሉ ወፎች እየበረሩ ወጡ አሁን አይኑን መለሰ እኔ ስወድቅ የተሰማው ድምፅ ከወፎቹ እንደሆነ አስቦ ይመስለኛል ከዛም ወደመኪናው ገብቶ እኛ ወደመጣንበት መስመር አመራ...ቀስ እያልኩ ከተደበኩበት ዛፍ ስር ወጣሁኝ ከጫካው ዳር ቆሜም ግራ ቀኙን ተመልክቼ በአካባቢው እሱ እንደሌለ ካረጋገጥኩ በሗላ ወደ መኪናችን አመራሁ ዙሪያዋን ቃኘሗት ምንም አልሆነችም ግን የሗላው የመኪናው መስታወት ላይ #እመለሳለሁ ተብሎ በደም ተፅፎበት እጅግ በጣም ደነገጥኩኝ እየሮጥኩ ወደ ጓደኞቼ አመራሁ..."ባርሳ ከዚ ቦታ መሄድ አለብን" ማለት ጀመርኩ አጠገባቸው ሳልደርስ "ምነው ሜርሲዬ ምን ሆነሽ ነው የተፈጠረ ነገር አለ" አለችኝ ባርሰናይት "በቃ እንሂድ አልኳቹ እኮ የቅድሙ ባለ መኪና ተመልሶ መጥቶ ነበር" አልኳቸው "ይሄ የውሻ ልጅ ከኛ ምንድነው ሚፈልገው ዋጋውን ነው ምሰጠው" ብሎ የቅድስት ጓደኛ ቦርሳውን ከፍቶ ሽጉጥ አወጣ..."ወደ ጫካው መውጫ ላይ ነበርኩ መኪናዋን ለማየት ሄጄ ነበር ከዛም ያ ሰውዬ መጣ ካላመናችሁኝ ከሗላ መስታወቱ ላይ በደም የፃፈውን መመልከት ትችላላችሁ" አልኳቸው "ምን በደም" እያለ የቅድስት ጓደኛ ወደ መኪናው ሄደ ሶስቱም አንድ በአንድ ተከተሉት ከደቂቃዎች በሗላ ጮክ ያለ ድምፅ "ሜርሲ" ሲል ሰማሁኝ አንዳች ሆነው እንደው ብዬ በሩጫ ወደነሱ ሄድኩ በድጋሜ "እረ ሜርሲ" አለ በጣም ደነገጥኩኝ ፍጥነቴን ጨምሬ ሮጥኩኝ ስደርስ ሁሉም ከመኪናው ጀርባ ቆመው ይስቃሉ "የታለ ምን አይተሽ ነው" አለኝ ባባ "ምን እየቀለዳችሁ ነው እሱ ላይ የተፃፈውን ነዋ ያየሁት" አልኳቸው ወደነሱ እያመራሁ ግን ስደርስ መኪናው ላይ ምንም አልነበረም ሁሉንም ክስተት በቅርብ ርቀት ሆኜ ተከታትዬዋለሁ ፅሁፉንም ጭምር አንብቤዋለሁ ግን አሁን የለም ይሄ ሰውዬ ከገመትኩት በላይ አሰፈሪና እንግዳ ሰው ነው..."እንዴ በምን አይነት ቅፅበት አጠፋው አሁን ነበር እኮ" አልኩኝ በግርምት እና በፍራቻ ውስጥ ሆኜ "ተረጋጊ ሜርሲዬ ጭንቀትሽ የፈጠረወሸ ነገር ነው ሰውዬው ለምን እኛ ጋር ይመጣል ምን ያገናኘናል "አለች ቅድስቴ "አዎ ሜርሲ ቅድስት ልክ ነች ራስሽን አረጋጊ ዕረፍት አርጊ ሁሉም ሰላም ነው" አለ ባባ "እኔ ያየሁትን አይቻለሁ ከመሬት ተነስቼም እንደዚ ልላችሁ እብድ አይደለሁም" አልኳቸው በንዴት ስሜት ውስጥ ሆኜ "እሺ ምን እናርግ" አለች ባርሳ "ከዚ ቦታ እንሂድ ከዚ በላይ እዚ አካባቢ ላይ መቆየት አልፈልግም" ብዬ መለስኩላት "አረ ሜርሲ...ብሎ የቅድስት ጓደኛ ወሬውን ሊጀምር ሲል ስልኬ ጠራ ከሗላ ኪሴ አወጣሁት "ምንም አይነት ድምፅ እንዳታሰሙ አባቢ ነው" አልኳቸው ትዕዛዜን መቀበላቸውን በአንገታቸው ንቅናቄ ገለፁልኝ "ሄሎ የኔ አባት" አልኩኝ "የኔ ሜርሲ እንዴት ነሽልኝ ልጄ እስካሁን ሳትደውዪ በሰላም ነው" አለኝ "አዎ የኔ አባት ተኝቼ ስለነበር" አልኩት "ደረሳችሁ እንዴ ነው ወይስ ሌላ ቦታ ላይ ቆይታችሁ ለመሄድ አስባችሁ ነው" ብሎ ጠየቀኝ "አንዳድ ቦታዎችን እያየን እንረፍ ተባብለን ነው የኔ አባት እናቴስ እንዴት ነች " አልኩት ከዚ በላይ ሌላ ውሸት ላለመጨመር "አጠገቤ ነች አዋሪያት" ብሎ ወደ ማሚ መራኝ "የኔ ውድ ልጅ እንዴት ነሽልኝ ምግብ በላሽ" አለችኝ የምትሳሳልኝ እናቴ "የኔ እናት እስካሁን አራበኝም ሰላም ዋልሽ " አልኳት "ደህና ነኝ የኔ ልጅ ራስሽን ጠብቂ ደሞ ቶሎ ቶሎ ደውዪ ጊዜሽን እንደልሻማብሽ ወደ ጓደኞችሽ ተመለሽ ሰላም ተመለሺልኝ የኔ ውድ ልጅ" አለች እናቴ "እሺ የኔ እናት አባቴን ቻው በዪልኝ እወዳችዋለሁ" ብዬ ዘጋሁት ለደቂቃም ቢሆን የነበርኩበት ስሜት እነ ማሚ አስረስተውኛል "ከዚ ቦታ አንሄድም" አልኳቸው አሁን ሰዓትም እየሄደ ነው ወደ ከተማው ሲመሽ ነው ምንደርሰው ሳናያት ከምንተኛ ነገ በጠዋት እንሂድ" አለ ባባ "እሺ ግን አንዳች ችግር ቢፈጠር እና የሆነ ሰው የሆነ ነገር ቢሆን እኔ እንሂድ ማለቴን እንዳትረሱት እኔ ለናንተ ስሜት ብዬ እንጂ መቆየት ፈልጊ አይደለም ምቆየው" አልኳቸው "እናመሰግናለን ሜርሲዬ" ብላ ባርሰናይት ጉንጬን ሳመችኝ ከዛ ሁሉም ወደ ጫካው ውስጥ ማምራት ጀመሩ እኔ እዛው ቆምኩኝ "ነይ እንጂ" አለኝ ባባ "እሺ ትንሽ ደቂቃ ብቻዬን ልሁን" አልኩት "እሺ ግን ብዙ አትቆዪ እንዳታሳስቢኝ" ብሎ ወደ ውስጥ አመራ ወደ አስፓልቱ ተጠጋሁኝና ግራ ቀኙን አየሁኝ ምንም አይነት መኪናም ሆነ ሰው የለም አስፓልቱ በግራና በቀኝ በዛፍ የተከበበ ነው ጫካው የያዘው ስፋት ደሞ እጅግ ሰፊ ነው ፀሃይ እያዘቀዘቀች ነበርና ብርሃኗ ለዘብ ብሎ ደስ የሚል ቀልብን የሚገዛ ነው ቀስ እያልኩ በመጣንበት አቅጣጫ ወክ ማረግ ጀመርኩኝ ኤርፎኔን ሰክቼ መዝሙር እያዳመጥኩ...ትንሽ እንደተራመድኩ እኔ ባለሁበት ተቀራኒ ከአስፓልቱ ማዶ የወደቀ ታፔላ ተመለከትኩ አስፓልቱን አቋርጬ ወደዛው አመራሁ አነሳሁት ግን ጭቃ እላዩ ላይ ደርቆበት ስለነበር ምን እንደሚል ለመለየት ይቸግራል ከዛም በእንጨት ማፅዳት ጀመርኩ በቀይ የተፃፈ ፅሑፍ ይታየኛል ግን መለየት አልቻልኩም አሁንም ደግሜ አፀዳሀት ግልፅ ሆኖ ታየኝ "#የሙት_ጫካ" የሚል ነበር እኔም አነበብኩት ወዲያውኑ ከፊት ለፊቴ ያለው ጫካ ውስጥ ሰቅጣጭ ቀጭን የሴት ድምፅ ጩኸት ሰማሁኝ ታፔላውን ጥዬ እየሮጥኩ አስፓልቱን ልሻገር ስል ከየት መጣ ሳልለው መኪና ሳተኝ ቀልቤን ነው የገፈፈው እጅግ ፍጥነት ነበር እሱን አሳልፌ ከተሻገርኩ በሗላ ወደ ጓደኞቼ መሮጥ ጀመርኩ ከበስተሗላዬ የመኪና ድምፅ ሰማሁ ሩጫዬን አቆምኩና ዞሬ አየሁት ሰውዬው ነበር በፈጣጣ አይኖቹ ገላምጦኝ እኔን ወደሳተኝ መኪና ፍጥነቱን ጨምሮ ተከተለው ይሄ ሰውዬ የሆነ ነፍሰ በላ መሆን አለበት ብዬ አሰብኩኝ ወዲያው ወደ ጓደኞቼ አመራሁ ብነግራቸው ስለማይረዱኝ ዝም አልኩኝ "ሜርሲዬ ቆየሽ እኮ" አለች ቅድስቴ"ትንሽ ልሩጥ ብዬ ነው" አልኩኝ ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ እያለ "ነይ አረፍ በይ" ብሎ ባባ ወደ ምንጣፉ ጋበዘኝ "ልብስ ልቀየር የኔ ድንኳን የቱ ነው" አልኳቸው "መሀል ላይ ያለው ሜርሲዬ ብቻሽን ከዳር ከምትሆኚ ብለን ነው"አለች ባርሰናይት የምወዳት ጓደኛዬ "እሺ የኔ ባርሳ" አልኩኝና ወደ ትንሿ ድንኳኔ አመራሁ ፀሃይ ባዘቀዘቀች ቁጥር ነፍሴን ይጨንቃታል ያ ሰውዬ ቀኔን አክብዶብኛል ደሞ ያነበብኩት ታፔላ የሰማሁት ድምፅ ብቻ ሁሉም ቀኔን የስጋት አርገውብኛል በተለይ የጓደኞቼ እኔ
Show all...
የጠፋው ሬሳ ╚═══❖• •❖═══╝ ክፍል አራት የኔታ ፍቄ(ግጥም እና ፍቅር) ፡ ...የእጅ ባትሪ እያበራ ወደኛ የሚመጣ ሰው ተመለከትኩ ከዛም ወደ ድንኳኔ መግባቴን ትቼ ዘፈኑን አጠፋሁትና ወደኛ አቅጣጫ ሰው እየመጣ መሆኑን ነገርኳቸው "ምን አባቱ ነው ሚመጣው" አለ ባባ "ዝም በል ቅድምም ያንንአንዳች ተናግራችሁት ነው የሚከታተለን አሁን ደግሞ ድጋሜ ትናገራላችሁ" ብዬ በተናደደ ስሜት ውስጥ ሆኜ ተቆጣሁ "ለማንኛውም መሳሪያዪን ልያዝ" ብሎ ባባ ወደ ድንኳኑ ገባ እነ ቅድስቴ በጣም ደንግጠዋል ፍራቻቸው ከፊታቸው ላይ ይነበባል መብራቱ እየቀረበን መጣ ለመሞቅ ብለን ያነደድነው እሳት አቅጣጫ ጠቋሚ እንደሆነ ተረዳሁ ከዛም በውሃ አጠፋሁት ሁላችንም አንድ ቦታ ላይ ቆመን ጫካው ፀጥ አለ አንዳች ድምፅ አይሰማማም ጭንቅ ውስጥ ሆነናል በድንገት ወደኛ ይመጣ የነበረው መብራት ደብዛው ጠፋ ምንም የተዋጠልኝ ነገር የለም ባለንበት እንድንቀመጥ ነገርኳቸው አሁን ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ ነው ከትንፋሻችን ውጪ የማንም ድምፅ አይሰማም ፀጥ እንዳልን ረዘም ያለ ደቂቃ ተቆጠረ ከግራ ከቀኝ እያማተርን..."ባክሽ ምንም የለም እኛ ብቻ ነን" ከማለቱ የቅድስት ጓደኛ የእጅ ባትሪው ወደኛ አቅጣጫ በረጅም ተለቀቀ አሁን የባሰ ጭንቅ ውስጥ ገባን ትንሽ ተረጋግተን ነበር...ምን ኩረት እንደጠላሁት ከበፊትም ቀልቤ አይወደውም "የሚነገርህን ብትሰማ ትሞታለህ" አልኩት "ይቅርታ ሜርሲዬ..."ብሎ ወሬውን ሊቀጥል ሲል "በቃ" ብዬ አቋረጥኩት...ባትሪው ድንኳኖቻችን ላይ እየበራ ነው ሰውዬውም እየተጠጋን ነው...ግን ድንኳኖቹ ጥቁርና የማያንፀባርቁ መሆናቸው ድንኳን አያስመስላቸውም ድንጋይ እንጂ ለዛም ይመስለኛል ባለ ባትሪው ሰው ትኩረት አልሰጣቸውም...ባትሪው አሁንም በድጋሜ ጠፋ ብቻ የሆነ ሰው በዙሪያችን እየተፈታተነን እንደሆነ ይሰማኛል...ያ ባለመኪና ሳስታወሰው ይከነክነኛል ከሱ ውጪ ማንም አይሆንም እዚ ቦታ ላይ ከሱ ውጪ ያየን የለም እኛም ከሱ ውጪ የተናገርነው የለም በገዛ አንደበታችን ራሳችን ላይ ገዳይ ገዛን..."ነግቶ የማለዳዋን የፀሀይ ወገግታ፣የማይሰለቸውን የአዕዋፍ ዝማሬ፣ የጠዋቱ የአየር ቅዝቃዜ ደግሜ ስለማላያቸው ናፈቁኝ የኔ ጊዜ የዛሬዋ ምሽት ነችነገ የኔ አይደለም"...እያልኩ ከራሴ ጋር ማውራት ጀመርኩ "ሜርሲዬ ካሁን በሗላ የሚመጣ አይመስለኝም ሄዷል" አለች ባርሰናይት ዝግ ባለ ሹኩሽኩታ "ሰውዬው ሊሄድ ይችላል ግን ምሽቱን እንደዚ እየተጠባበቅን ማሳለፍ አለብን" አልኩኝ ለሁላችንም ደህንነት አስቤ..."ግን ማን ሊሆን ይችላል" ብላ ጠየቀችኝ ቅድስቴ "ቀን ላይ የወደቀ መኪና የሚያነሳውን ሹፌር ተናግረነው ነበር ከሱ ውጪ ማንም አይሆንም" ብዬ መልኩላት "ሜርሲ ያን ያህል እኮ የሚያስከፋ ንግግር እኮ አይደለም ከተማ ውስጥ ከዚ የባሰ እላፊ እንነጋገራለን እኮ" አለ ባባ በተጨነቀ እና ራሱን በወቀሳ ስሜት ውስጥ አስገብቶ..."ይሄ ሰውዬ ንግግርን እንዴት እንደሚረዳ ባላውቅም በትንሽ ነገር የሚቆጣ አይነት ሰው ይመስለኛል" አለች የኔ ውድ ጓደኛ ባርሰናይት "ልክ ነሽ ባርሳ እኔም እንደዛ ነው ማስበው" ብዬ ሀሳቧን ደገፍኩላት...አንድ ነገር ገርሞኛል ያ ሰውዬ መጥፎና ገዳይ መሆኑን ጓደኞቼ ማመናቸው...አይ የጭንቅ ጊዜ...ምነው በሰላሙ ሰዓት ያልኳቸውን ሰምተው ከዚ ቦታ በሄድን ነበር አሁን ከረፈደ በሗላ ቢያውቁት ቢያውቁት ምን ጥቅም ይኖረዋል..."ጅብ ከሄደ ውሻ" አልኩኝ በሆዴ...እዛው እንደተቀመጥን ደቂቃዎች ሰዓትን ወለዱ የጫካው ቅዝቃዜ እጅግ እየጨመረ መጣ ጣቶቼ እስከማይታዘዙ ድረስ በብርድ ቆረፈዱ..."አረ ይበርዳል ወደ ውስጥ እንግባ" አለች ባርሰናይት "አይሆንም ከተነጣጠልን ለጥቃት እንመቻለን አብረን ብንሆን ለኛ መልካም ነው" ብዬ በሀሳቧ አለመስማማቴን ገልፅኩላት "በርዶኝ እኮ ነው ሜርሲዬ ግን እሺ በቃ እዚው እንሁን" አለች ባርሳ "እሽሽሽ ዝም በሉ ቆይ" አልኳቸው ረጋ ብሎ በቀስታ የሚራመድ የእግር ኮቴ ይሰማኛል ባባ ሽጉጡን አቀባበለ ይመስለኛል ሰውዬው ከድንኳናችን ጀርባ ነው...ነፍሴ ተጨነቀች ልቤ አካሌን ቀዶ እስኪወጣ መምታት ጀመረ ላቤ ልብሴን እስኪያረጥበው እንደ ጉድ ይወርዳል እጅና እግሬ አቅም አጥተው ይብረከረካሉ ብቻ መላ ሰውነቴ ተዳክሟል...የማን ስልክ እንደሆነ እኔንጃ ከተቀመጥበት ቦታ ጮኸ እንዲቀጥል አብሮነታችሁ አይለየን ይቀጥላል ብቻችሁን አታንብቡ ሼር አርጉ https://t.me/manuheta
Show all...
(ማኑሄ ስነ-ፅሁፍ)Manuhe Christian literature ✍️

በስነ-ፅሁፍ ፦ ወንጌል ይሰራል ፦ ክርስቶስ ይገናል ፦ መንፈስ ይታደሳል ፦ ጌታ ይከብራል ኑ አብረን ጌታን እናገልግል የስነ ፅሁፍ ስራዎቻችሁን እና አስተያየቶቻቹን ለመላክ @manuhecl ያግኙን።

Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.