መዝሙር ግጥሞች ቤት
ይህ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ሥርዓትን የምንማማርበት Channel ነው ! ወደ ቻናላችን በመቀላቀል 👇 ➲ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መፅሐፍትን በPDF ➲ስንክሳር ትምህርቶች ➲ መዝሙራትን በግጥሞች ➲ ኪነ-ጥበብ ➲ ጥያቄዎችን በሐይማኖት ብትኖሩ እራሳችሁን መርምሩ" ( 2ኛቆሮ -13 ፥ 5)👇 Group ገጽ👇👇 https://t.me/Orthodoxs_Tewahdo_menfeswi_group
Show more16 336
Subscribers
+14124 hours
+8387 days
+2 51130 days
- Subscribers
- Post coverage
- ER - engagement ratio
Data loading in progress...
Subscriber growth rate
Data loading in progress...
Photo unavailableShow in Telegram
ንብ ዲኮር
ለየት ያሉና ሳቢ ዲኮር * ለሠርግ
*ለመልስ
*ለልደት
*ለምርቃት
*ለሽምግልና
*ለአጥር ወፍ አትስማሽ
*ለክርስትና
እንዲሁም ለሚፈልጉት ፕሮግራም ማዘዝ ከፈለጉ እንግድያውስ አሃዱ ብለው በ 0927334801 ላይ ይደውሉ በተጨማሪ በቴሌግራም @kingo8 በለው ይዘዙን በጥራት እና በውበት ፕሮግራሞን እናሳምራለን ንብ ዲኮር::
የተለያዩ የዲኮር ስራዎችን ለማየት JOIN ይበሉ::
ንብ ዲኮር
🕊
[ † እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ሕንጸተ ቤታ [ ሕንጸታ ] በሰላም አደረሳችሁ ፣ አደረሰን። † ]
† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †
🕊 † በዓለ ሕንጸታ † 🕊
† በዚሕች ቀን : በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን በአምላክ እናት ስም ታንጻለች::
ጥንተ ነገሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን "ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ" [አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ] [ማቴ.፳፰፥፲፱] (28:19) ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል::
የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና [ዮሐ.፮፥፶፮] (6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር::
በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን: ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲሕ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ::
በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚሕ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን "ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?" ቢሏቸው "እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደሆን የለን" ሲሉ መለሱላቸው::
ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት ጳውሎስና በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች "ለምን አናንጽም" ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን "ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም" አለ:: [ለዚሕ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተ ክርስቲያን የማይታነጸው::]
ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን ለቅዱስ ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱም "የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ" ብሎ አዋጅ ነገረ::
በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔአቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ::
ሁሉንም ሐዋርያት በደመና ጭኖ ፊልጵስዩስ አደረሳቸው:: ከከተማ ወጣ ብሎ ባለ መሬት ላይም "ቤተ ክርስቲያንን በእናቴ ስም አንጹ" ብሎ አዘዛቸው:: ለቅዱስ ጴጥሮስም ሦስት ዓለቶችን ሰጠው::
እነዚያን መሬት ላይ ተክሎ : ጌታችን ቆሞለት : ሐዋርያቱ እየተራዱት : ግርምት የምትሆን ሦስት ክፍል ያላትን የመጀመሪያዋን ቤተ ክርስቲያን በ52 ዓ/ም በዚህች ቀን አንጿል::
ቤተ ክርስቲያኗን ነገ ጌታችን ቀደሳት የምንል ነንና ይቆየን::
† አምላካችን የድንግል እናቱን ፍቅር : የተቀደሰች ቤቱን ጸጋ : የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን::
🕊
[ † ሰኔ ፳ [ 20 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]
፩. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
፪. ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
፫. ቅዱሳን ሐዋርያት
፬. ቅዱስ ኤልሳዕ ነቢይ [ ዕረፍቱ ]
[ † ወርኀዊ በዓላት ]
፩. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሊቀ ሠራዊት [ሰማዕት]
፪. ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
፫. ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
፬. ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ [ ንጉሠ ኢትዮጵያ ]
፭. አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
፮. ቅድስት ሳድዥ የዋሒት
† " በድካም : አብዝቼ በመገረፍ : አብዝቼ በመታሠር : አትርፌ በመሞት ብዙ ጊዜ ሆንሁ:: በድካምና በጥረት : ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት : በራብና በጥም : ብዙ ጊዜም በመጦም : በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው:: " † [፪ቆሮ. ፲፩፥፳፫-፳፰]
† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
† † †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖 🕊 💖
በጉባኤ ኬልቄዶት የተነሳው ምንፍቅና ምን ነበረ?
አንድ አካል አንድ ባህሪ
ሁለት አካል ሁለት በህሪ
አንድ አካል ሁለት ባህሪ
አንድ ባህሪ ሁለት አካል
Choose a Different Plan
Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.