cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

Ethio Facts 🇪🇹 ኢትዮ ፋክት️

ኢትዮጵያ ትቅደም Walk a mile in my shoes, Then you will know how I feel.

Show more
Advertising posts
372Subscribers
+324 hours
+87 days
+4930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አንድን ግለሰብ ኢ-ሰብአዊ በሆነ መልኩ በመደብደብ አስነዋሪ ተግባር የፈጸሙ አባላቱን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ በማጣራት ላይ መሆኑን የድሬዳዋ ፖሊስ ገለጸ፡፡ ሰሞኑን ሶስት የድሬ ዳዋ ፖሊስ አባላት አንድን ግለሰብ ከበው ኢ-ሰብአዊ በሆነ ሁኔታ የመደብድበ አና የማንገላታት ተግባር ሲፈፅሙ የሚያሳይ ምስል በማህበራዊ ሚዲያ ሲንቀሳቀስ ተመልክተናል ሲል የድሬ ፖሊስ አመልክቷል። በዚህ አስነዋሪ ተግባር የድሬዳዋ ፖሊስ አመራር እና አባላት በእጅጉ ማዘኑንም መምሪያው ጠቁሟል።የተከሰተው አስነዋሪ ተግባር የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያን በፍጹም የማይወክል እና የማይገልጽ ተግባር በመሆኑ በጽኑ እናወግዛለን ብሏል። በመሆኑም ‹‹በጀግንነት መጠበቅ ፤በሰብዓዊነት ማገልገል›› የሚል መሪ ቃል አንግቦ ዜጎችን ከማንኛውም ጥቃት በጀግንነት ለመጠበቅ ሌት ተቀን የሚተጋው፤ ህይወቱን በጀግንነት ለመክፈል የቆረጠው ፤ የዜጎችን ሰብአዊ ክብር ጠብቆ ለማገለገል ቁርጠኛ አቋም ይዞ ወደ ስራ የገባው የድሬደዋ ፖሊስ ፤ የዜጎችን ሰብአዊ መብት አክብሮ በማስከበር ረገድ ለአፍታም ቸል እንደማይል ደግመን ደጋግመን ለማረጋገጥ እንወዳለን፡፡ ስለሆነም በአሁኑ ወቅት በምስሉ ላይ የሚታዩትንና በዚህ አስነዋሪ የወንጀል ተግባር ላይ የተሳተፉ ሶስት አባላትን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን እያጣራ መሆኑን የድሬዳዋ ፖሊስ አሳውቋል። አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4
Show all...
አየርላንድ ድንበር ተሻግረው የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ እመልሳለሁ አለች! የአየርላንድ መንግሥት ከዩናይትድ ኪንግደም የሚመጡ ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችለውን ሕጋዊ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ጀመረ።የአየርላንድ ጠቅላይ ሚንስትር ሲሞን ሃሪስ የአገሪቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ስደተኞችን ወደ ዩኬ መመለስ የሚያስችል ሕግ አርቅቆ ለአገሪቱ ካቢኔ እንዲያቀርብ አዘዋል። ዩናይትድ ኪንግደም በሕገ-ወጥ መልኩ ወደ አገሯ የሚገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ እልካለሁ ማለቷን ተከትሎ ዩኬ የሚገኙ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ ላለመመለስ ሲሉ እንደ አየርላንድ ያሉ አገራትን አማራጭ መዳረሻቸው እያደረጉ ነው።የአየርላንድ የፍትሕ ሚኒስትር ሄለን ማክኤንቲ በቅርቡ ወደ አየርላንድ ከተሻገሩ ስደተኞች መካከል 80 በመቶ የሚሆኑት መነሻቸው ዩኬ ነው ብለዋል። የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማይክል ማርቲን የዩኬ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ የመላክ እቅድ ገና ከአሁኑ በአየርላንድ ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው ብለዋል።ከቀጥቂት ቀናት በፊት ለበርካታ ወራት ብዙ ሲያወዛግብ የቆየው ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በሕገ-ወጥ መንገድ የገቡ ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ የሚያስችለውን ሕግ የአገሪቱ ፓርላማ ጸድቆ ሕግ ሆኗል። ይህ ሕግ ኢንግሊሽ ቻናል ተብሎ በሚጠራው የውሃ አካል በኩል በጀልባ በሕገ-ወጥ መንገድ ዩኬ የደረሱ ስደተኞችን በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ ሩዋንዳ የሚልክ ነው።ስደተኞቹ በዩኬ የሚያቀርቡት የጥገኝነት ጥያቄ የሚታየው ሩዋንዳ ተወስደው ሲሆን፣ የጥገኝነት ጥያቄያቸው አዎንታዊ መልስ የሚያገኝ ከሆነ ስደተኞቹ እዚያው እንዲቆዩ ይፈቀድላቸዋል። ነገር ግን የጥገኝነት ጥያቄያቸው ውድቅ ከሆነ ደግሞ ስደተኞቹ ሌላ ምክንያት በማቅረብ በሩዋንዳ አልያም በሌላ ሦስተኛ አገር የጥገኝነት ጥያቄ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ፈጽሞ ወደ ዩኬ መመለስ ግን አይችሉም።ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ ሕጉ ተግባራዊ ሆኖ ሐምሌ 2016 ዓ.ም. ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳ መላክ እንደሚጀር አስታውቀዋል።
Show all...
የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ"ችግሮችን በዘላቂ ሁኔታ ለመፍታት እንጂ ለጊዜው የሚደረግ ተግባር እንዳይሆን መጠንቀቅ ያስፈልጋል"---ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሀገራዊ የምክክር መድረክ አስፈላጊ ነቱ "ችግሮችን በዘላቂ ሁኔታ ለመፍታት እንጂ ለጊዜው የሚደረግ ተግባር እንዳይሆን መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ፕሬዚዳንቷ በሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ የሃሳብ ልዩነት እያደረስብን ያለው ኪሳራ ትልቅ በመሆኑ ይህ መድረክ የሚኖረው ጠቀሜታ ላቅ ያለ መሆኑንም አመላክተዋል። ፕሬዘዳንቷ ይህን የተናገሩት በዛሬው ዕለት በሀገራዊ የምክክር  ሂደቱ የሴቶች ተሳትፎና ድርሻ ምን መሆን አለበት በሚል በተካሄደ ውይይት ላይ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ሀገራዊና እጅግ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የሀሳብ ልዩነቶች ወይንም አለመግባባቶች መኖራቸውን አንስተው ፣እነዚህን የሀሳብ ልዩነቶች ወይም አለመግባባቶች እንደ ምክክር ባሉ ሰላማዊ አማራጮች ከመፍታት ይልቅ የሃይል  አማራጮች ጥቅም ላይ ሲውል ይስተዋላልም ነው ያሉት። በመሆኑ በሀገራችን ግማሽ ያህሉን የህዝብ ቁጥር የሚይዙት ሴቶች  ውሳኔ በሚሰጥባቸው ቦታዎች ላይ መኖር ለአገር ጥቅሙ ብዙነው ብለዋል፡፡ ፕሬዚዳንቷ ሴቶች በሀገር ጉዳይ ላይ በየትኛውም መስክ ከወንዶች እኩል ድምፃቸውን ማሰማት መብታቸው ነው፣ በመሆኑ እኩል ንቁ ተሳትፎ እንዲያ ደርጉ እንጂ  ለቁጥር ወይም ለኮታ ማሟያ መሆን የለበትም ብለዋል፡፡ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ በምክክሩ የሴቶች ድርሻ መኖሩ በከፍተኛ ሁኔታ የአገረ መንግስት ግንባታ ይፋጠናል፣ ዘላቂ ሰላምም እንዲሰፍን ጉልህ ሚና አለው፣ ለዚህም የሌሎች ሀገራት ተሞክሮን ማየት ተገቢ ነው  ብለዋል፡፡ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ በበኩላቸው፣ የምክክሩ ሂደት የሴቶች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በዚህ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች 30 በመቶው የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ብለዋል፡፡ በምክክሩ ሴቶች በንቃት  የሀሳብ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫና ድጋፍ እያደረግን፣ በምክክር መድረኩ ሴቶች ድምፃቸው ጎልቶ የሚሰማበት እንዲሆን እየሰራን ነው ብለዋል፡፡
Show all...
በርካታ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ የአዲስ አበባ ፀጥታ ቢሮ እንዳስታወቀው ከሆነ ከሚሰጣቸው ሀላፊነት እና ስልጣን ውጪ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ የፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉን እና ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ይፋ አድርገዋል። የከተማዋ አንዳንድ የፀጥታ አካላት በአማራ ክልል የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተገን በማደረግ ህገወጥ እስራት እና እንግልት እንደፈፀሙ ሪፖርተር ጋዜጣ በዘገባው መጥቀሱን አዩዘሀበሻ ተመልክቷል። የአዲስ አበባ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ በአማራ ክልል የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአዲስ አበባ እንደማይገበር ገልፀው ከተማው ውስጥም ጉዳዮች ሲኖሩ በየትኛውም ሰዓት ኦፕሬሽን እንደሚሰራ ጠቁመዋል። በቅርቡ በተደረገው ፍተሻ ከ140ሚሊዮን ብር በላይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተጠቁሟል። በዚህም 1.5 ሚሊዮን ብር በቁማር የተሰበሰበ ብርን ጨምሮ ሌሎች ሀሰተኛ የብር ኖቶች ተይዘዋል ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ከ16,000 በላይ ተተኳሿችን ጨምሮ የስውር ትጥቅ እስከ ትልልቅ መሳሪያዎች መያዛቸው ተገልጿል። ለስራ ፍለጋ እና ለሌሎች ጉዳዮች ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ የሰዎች ብዛት በአጅጉ መጨመሩን ቢሮዉ አስታውቋል።
Show all...
ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ ዛሬ ጠዋት ከቤተሰብ እና ጠበቃው ጋር መገናኘቱ ተዘገበ ተዋናይ አማኑኤል ሃብታሙ "እብደት በሕብረት" የተሰኘ የአንድ ሰው ቴአትሩን ለማሳየት ወደ እስራኤል አገር ሊጓዝ ሲል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት በፖሊሶች መያዙ ይታወሳል።በአዲስ አበባ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ ታስሮ የሚገኘው ተዋናዩ የቅርብ ወዳጅ የሆነው ያሬድ ሹመቴ እንደገለጸው አማኑኤል ሃብታሙ "እጁ ከተያዘበት ሰዓት አንስቶ የተከሳሽነት ቃል ሳይሰጥ እንዲሁ በእስር ላይ" እንደሚገኝ ቤተሰቦቹን ዋቢ አድርጎ ጽፏል። ይኹን እንጂ የቤተሰብ ጠበቃ የማግኘት መብቱ ተጠብቆለት ከቤተሰብ እና ከጠበቃ ጋር ዛሬ ጠዋት ሊገናኝ መቻሉን እና "በመልካም" ሁኔታ ላይ መኾኑ ተመልካቷል። በሕጉ መሰረት ወደ ቀጣይ ሕጋዊ ሂደቶች ለማምራት እስከ ነገ የሚሆነውን ለማየትም ቤተሰቦቹ እየተጠባበቁ ነው ተብሏል።  እያዩ ፈንገስ የአንድ ሰው ቴያትር 'ቧለቲካ' የተሰኘው ምዕራፉ ለዕይታ ከቀረበ ከእጭር ጊዜ በኋላ ማለትም ከጥር 2 ቀን 2016 ጀምሮ የመንግስት የፀጥታ አካላት ለዓለም ሲኒማ የስራ ሀላፊዎች ባስተላለፉት ትእዛዝ  ለህዝብ እንዳይታይ መከልከሉ አይዘነጋም።
Show all...
👍 2
አቶ ብርሃኑተፈተዋል‼ ኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ለገጣፎ አቅራቢያ 44 ማዞሪያ ጅዳ ኩራ በተባለ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደነበር የተገለፀው አቶ ብርሃኑ የሚባሉት እኝህ አባት ትናንት መፈታታቸው። እሳቸው ዛሬ ዛቻና ማስፈራሪያን የተሻገረ ተግባር ሲፈፅሙባቸው የነበሩት 7 ወጣቶች በፍ/ቤት ጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸው በእስር ላይ እንደሚገኙ የመረጃ ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል። @wasulife ቤተሰብ❤ በቅንነት ሰብስክራይብ በማድረግ ተባበሩ👇       https://www.youtube.com/channel/UCrdWHrcXNEhMfbp1ucgxd1g አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ Join አድርገው👇በዚህ ይከታተሉ https://t.me/+WNLm9dbzuIlp9DF4 ማስታወቂያና ጥቆማ 👇መቀበያ https://t.me/wasumohammed
Show all...
ቦትስዋና የዩናይትድ ኪንግደም ስደተኞችን እንድትቀበል የቀረበላትን ጥያቄ ውድቅ አደረገች የቦትስዋና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለደቡብ አፍሪካ የቴሌቭዥን ጣቢያ እንደተናገሩት የብሪታንያ መንግስት ከእንግሊዝ የተባረሩ ስደተኞችን ለመቀበል ሀገሪቱ ፈቃደኛ መሆን አለመሆኗን መጠየቃቸውን ተናግረዋል። ሚኒስትሩ ይህ ጥያቄ መቼ እንደቀረበላቸው ከመናገር ተቆጥበዋል።የዩናይትድ ኪንግደም መንግስት በቦትስዋና፣ አርሜኒያ፣ አይቮሪ ኮስት እና በኮስታ ሪካ ሩዋንዳ ስደተኞችን ለመቀበል የተስማማችበትን እቅዱን ለመድገም እንደሚፈልግ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በብሪቲሽ ፕሬስ ላይ ያልተረጋገጡ ዘገባዎች መውጣታቸው ይታወሳል። በኒውዝሮም አፍሪካ በተሰኘ ፕሮግራም ላይ በተደረገ የስልክ ቃለ ምልልስ ሚኒስትሩ ሌሞጋንግ ክዋፔ እንደተናገሩት ቦትስዋና የብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ጉዳይ ሚኒስትር በ‹‹ዲፕሎማቲክ ቻናል›› በኩል የቀረበላቸውን ጥያቄ ውድቅ አድርጋለች ብለዋል። ክዋፔ ቦትስዋና ከብሪታንያ የሚመጡ ስደተኞችን መቀበል አትችልም ምክንያቱም የራሷን የኢሚግሬሽን ጉዳዮች እያስተናገደች ነው ብለዋል። "የብሪታንያ መንግስት እነዚህን ሰዎች በአገራቸው እንዲኖሩ ስለማይፈልግ በሩቅ አገር እንዲቀብሩአቸው ይፈልጋል ሲሉ ተደምጠዋል። በራሳችን ቀጠና ያለውን ችግር እየፈታን በመሆኑ ያልተፈለጉ ስደተኞችን ከሌላ ሀገር መቀበል ለቦትስዋና ፍትሃዊ አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል። በሌላ በኩል የዩናይትድ ኪንግደም ፓርላማ ጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ የሚሰደዱበትን መንገድ የሚከፍተውን አወዛጋቢውን ህግ በማፅደቁ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ ባለስልጣናት ያለቸውን ስጋት አንስተዋል። ስደተኞች ወደ እንግሊዝ በህገ ወጥ መንገድ እንዳይገቡ ለማድረግ ያለመ የሩዋንዳ ሴፍቲ ወይን የጥገኝነት እና ኢሚግሬሽን ህግ ለወራት ከዘለቀው አለመግባባት በኃላ ሰኞ እለት ፀድቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ቮልከር ቱርክ በጋራ በሰጡት መግለጫ የእንግሊዝ መንግስት እቅዱን እንደገና እንዲያጤነው ጠይቀዋል። ይህ ህግ በሰብአዊ መብቶች ላይ "ጎጂ ተጽእኖ ይኖረዋል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። ህጉ "የስደተኞች ስምምነትን መጣስ" ነው ሲሉ አክለዋል ።
Show all...
በቀሲስ በላይ ሁለት መኖሪያ ቤቶች በብርበራ የተገኘ የጦር መሳሪያ ህጋዊነት የማረጋገጥ ስራ እየሰራ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ መርማሪ ፖሊስ በተሰጠው የ7 ቀን ጊዜ ውስጥ የምስክሮችን ቃል መቀበሉን፣ በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ኤሌክትሮኒክስ ምርመራ እንዲደረግ ለሚመለከተው ተቋም መጠየቁን፣ የቴክኒክ ምርመራ እንዲሰጠው በደብዳቤ መጠየቁን አስታውቋል። በተጨማሪም በቀሲስ በላይ ሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ብርበራ ማድረጉንና በብርበራ የተገኘ የጦር መሳሪያ ህጋዊነት የማረጋገጥ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል፤ ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ገልጾ መርማሪ ፖሊስ የ14 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ጠይቋል። ቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ ሌሎቹም ተጠርጣሪዎች በ6 ጠበቆች ተወክለው ችሎት የቀረቡ ሲሆን ደንበኞቻቸውን ተጨማሪ በእስር ለማቆየት የሚያስችል አይደለም በማለት ተከራክረዋል። የግራ ቀኝ ክርክሩን የተመለከተው ጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ ተጠርጣሪው ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ለጊዜው በማለፍ ለፖሊስ የ8 ቀን የምርመራ ማጣሪያ ጊዜ ፈቅዷል።
Show all...
👍 2
በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ ከብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣ ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን የሀገረ መንግሥትነት ታሪኳ፣ የፖለቲካ ልዩነቶችን፣ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ፣ በንግግር፣ በውይይት እና በሕጋዊ አግባብ የመፍታት ልምምድ የላትም። እንደ አለመታደል ሆኖ ፖለቲካችን የዜሮ ድምር ፖለቲካ ነው። በሀገራችን የተለመደው በጉልበት አሸንፎ ሥልጣን የያዘ ኃይል፣ በጉልበት ተሸንፎ ሥልጣን እስኪለቅ ድረስ ሁሉንም ጠቅልሎ የሚቆጣጠርበት እና የፈቀደውን የሚያደርግበት የፖለቲካ ባህል ነው። የለውጡ መንግሥት ወደ ሥልጣን የመጣው በጉልበት አይደለም። ይሄም አዲስ የፖለቲካ ባህል ነው። ይሄን አዲስ የፖለቲካ ምእራፍ የሚያጸና ሌላ ሰላማዊ የፖለቲካ ባህል ደግሞ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሕዝብ ይሁንታ አግኝቶ መንግሥት በመመሥረት አሳይቷል። ከዚህም በመሻገር ልዩ ልዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች አመራሮችና አባላትን በመንግሥት ኃላፊነት በመመደብ፣ ኢትዮጵያ የጋራ ቤት መሆንዋን አስመስክሯል። ሰላማዊ የፖለቲካ ሽግግር ብቻውን ግብ አይደለም። ሌሎች ግቦችን ለማሳካት መሣሪያ እንጂ። የኢትዮጵያ ችግር የአሁኑን አካሄድ በማስተካከል ብቻ አይፈታም። በታሪክ ውስጥ የወረስናቸውን ስብራቶች መጠገንም የግድ ይለናል። እነዚህን የታሪክ ስብራቶች ለመጠገን ሦስት ዓይነት መፍትሔዎች ተቀምጠዋል። ነባሩን ፖለቲካዊ ችግር በሀገራዊ ምክክር መፍታት፤ የቅርብ ዘመናችንን የፖለቲካ ችግር ደግሞ በሽግግር ፍትሕ እና በተሐድሶ ማረም።
Show all...
በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ ከብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

  የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣ ኢትዮጵያ በረጅም ዘመን የሀገረ መንግሥትነት ታሪኳ፣ የፖለቲካ ልዩነቶችን፣ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ፣ በንግግር፣ በውይይት እና በሕጋዊ አግባብ የመፍታት ልምምድ የላትም። እንደ አለመታደል ሆኖ ፖለቲካችን የዜሮ ድምር ፖለቲካ ነው። በሀገራችን የተለመደው በጉልበት አሸንፎ ሥልጣን የያዘ ኃይል፣ በጉልበት ተሸንፎ ሥልጣን እስኪለቅ ድረስ ሁሉንም ጠቅልሎ የሚቆጣጠርበት እና የፈቀደውን የሚያደርግበት የፖለቲካ ባህል ነው። የለውጡ […]

👍 1