cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት - ሐረር

ይህ በኢት/ኦ/ተ/ቤ/ክ የምሥ/ሐ/ሀ/ስ ጥንተ አድባራት ወገዳማት አቦከር ደብረ ፀሐይ ቅ/ጊዮርጊስ እና ሐኪም ጋራ ደብረ አድኅኖ ቅ/ገብርኤል አብያተ ክርስቲያናት ፍሬ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ገጽ ነው። ፨ ለመቀላቀል፡ 👉https://t.me/frehaymano ሀሳብ እንዲሁም አስተያየት ካሎት : 👉 @Frehaymanot1923 ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ "አገልግሎት ሕይወቴ ካልሆነ ፤ መኖር ለእኔ ሞቴ ነው"

Show more
Advertising posts
554Subscribers
+324 hours
+97 days
+1930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

❗#በግብረ_ሕማማት_ውስጥ❗ በተደጋጋሚ የምንሰማቸው_ቃላት ,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,, 🔴👉 በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ። የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ 🔵#ኪርያላይሶን 👉ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ «ኪርዬ ኤሌይሶን» ነው፡፡ «ኪርያ» ማለት «እግዝእትነ» ማለት ሲሆን «ኪርዬ» ማለት ደግሞ «እግዚኦ» ማለት ነው፡፡ ሲጠራም «ኪርዬ ኤሌይሶን» መባል አለበት፡፡ 🔴👉 ትርጉሙም «አቤቱ ማረን» ማለት ነው፡፡ «ኪርያላይሶን» የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው «ዬ» ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ «ኤ» በመሳሳባቸው በአማርኛ «ያ»ን ፈጥረው ነው፡፡ 🔵#ናይናን 👉 የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «መሐረነ፣ ማረን» ማለት ነው፡፡ 🔵#እብኖዲ 👉 የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «አምላክ» ማለት ነው፡፡ «እብኖዲ ናይናን» ሲልም «አምላክ ሆይ ማረን» ማለቱ ነው። 🔵#ታኦስ 👉 የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ «ጌታ፣ አምላክ» ማለት ነው፡፡ «ታኦስ ናይናን» ማለትም «ጌታ ሆይ ማረን» ማለት ነው፡፡ 🔵#ማስያስ 👉 የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ «መሲሕ» ማለት ነው፡፡ «ማስያስ ናይናን» ሲልም «መሲሕ ሆይ ማረን» ማለት ነው። 🔵#ትስቡጣ 👉 «ዴስፓታ» ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው። 👉 አምንስቲቲ = አስበን 👉 ሙኪርያ = አቤቱ ጌታ ሆይ 👉 አንቲ ፋሲልያሱ = በመንግሥትህ 👉 ሙአግያ = ቅዱስ 👉 ሙዳሱጣ = ቸር ጌታ 🔴👉 አምነስቲቲ ሙኪርያቱ አንቲ ፋሲልያሱ ። የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ» ማለት ነው፡፡ 🔵👉 አምንስቲቲ መዓግያ አንቲ ፋሲልያሱ። የቅብጥ ቃል ሲሆን «ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ - ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው። 👉 አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም «ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ- የሁሉ የበላይ የሆንክ ወይ በመንግሥትህ አስበን» ማለት ነው። ።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።። ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።። ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።። 🙏🙏🙏 አሜን 🙏🙏🙏
Show all...
👍 4
ዛሬ በሆሳዕና እለት በፍሬ/ሃ/ሰ/ትቤት በበጎ አድራጎት ክፍል ለምዕመናን   ነፃ የጤና ምርመራ ማድረግ ተችሏል ።  በዚህም ነፃ የጤና ምርመራ መርሀ ግብር ላይ ከሥልሳ  በላይ  እናቶች እና አባቶች ነፃ የጤና ምርመራ ማድረግ የተቻለ ሲሆን ።  በዚህም ለመርሀ ግብሩ መሳካት በአገልግሎቱ አብራችሁን ለነበራችሁ እህት ወንድሞቼ ። እግዚአብሔር አገልግሎታችሁን አይቶ የልባችሁን መሻት ይፈጽምላችሁ አሜን ! የፊታችን ባለው በዓል በበጎ አድራጎት ክፍል ደግሞ ላቅ ያለ የነዳያን ምገባ ስላዘጋጀን በዚህም መርሀ ግብር ላይ ደግሞ የምናገለግልበትን ቁሳ ቁስ በማምጣት   ። በጎ አድራጎት ክፍሉን መደገፍ ፣ ማገዝ ስላለብን    ። 👇👇 0953409521 0920892776 0923957184 እግዚአብሔር የልባችሁን ይስጣችሁ  ።
Show all...
👍 3
ውድ🤚 ሰላም ውድ የፍሬ ሃይማኖት ቤተሰብ ለፋሲካ በዓል   ለነዳያን ምገባ ስለምናደርግ እርስዎም በዚህ መርሀ ግብር ላይ የአቅምዎትን እንዲያደርጉ ፤ ተጋብዘዋል ። ለምገባው የሚያስፈልጉን ዝርዝር ። 1 ሽንኩርት ፥   ለብቻ ወይንም ለሁለት ወይም ለሦስት እየሆናችሁ ። 2 ዶሮ ፥ ለብቻ ወይንም ለሁለት ወይም ለሦስት እየሆናችሁ። 3 ዘይት ፥ ለብቻ ወይንም ለሁለት ወይም ለሦስት እየሆናችሁ 4 በርበሬ ፥ ለብቻ ወይንም ለሁለት ወይም ለሦስት እየሆናችሁ 5  ሥጋ ፥ ለብቻ ወይንም ለሁለት ወይም ለሦስት እየሆናችሁ ። ለበለጠ አገልግሎት ይጠቅም ዘንድ ፥                 0953409521                 0920892776 በፍሬ/ሃ/ሰ/ቤት ከበጎ አድራጎት ክፍል ። ምድር ላይ ቁጭ ብለህ ከእግዚአብሔር ጋር የምትታረቅበት በደልህም የሚፋቅበት መፋቂያ ፣ ጸሎትህም የሚሰምርበት መሣሪያ  ፣ ከወደቅክበትም የምትነሣበት መሣሪያ ፣ ስትደክምም ጥንካሬን የሚሰጥህ መሣሪያን ማግኘት ከፈለክ መስጠትን ገንዘብ አድርጋት ።
Show all...
👍 1
Go to the archive of posts