cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፈለገ ካፄ የኪነ-ጥበብ ቡድን

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
153
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ግለ- ንግግር (ሞኖሎግ)ክፍል፩ ሞኖሎግ (ግለ-ንግግ)በአንድ ተዉኔት ውስጥ ለአንድ ተዋናይ ንግግ ተደርጎ ታሪክ /ድርጊት ነው ይህም አጭር ወይም ረጅም ሊሆን ይችላል ።ለትወና መለማመጃ ነትየሚውል ግለ-ንግግ በአንድ በአንድ ተውኔት ውስጥ በንረት ትዕይንቶች ውስጥ የሚመጣና የአንድን ገፀ-ባህሪ ህይወት ከጅምር እስከ ፍፃሜ ድረስ ያለ ህይወቱን የሚዳስስበት ስፍራ ላይ የሚገኝ ግለ-ንግግር ተገቢ ነውግለ-ንግግ እና ረጅም ግጥም የተለያዩ ናቸው። ግለ -ንግር እንደ ህብራዊ ንግግር/ቃለ- ተውኔት ሁሉ በግጥምወይም በዝርው/ ብትን ፁሑፍ ተፅፎ ሊገኝ ይችላል ይቀጥላል……
Show all...
☞ዛሬ ተዋናይ ምን ማሟላት እንዳለበት ከማውራታችን በፊት. አንድ የቤት ስራ እንስጦዎና ወደ ጉዳያችን እንግባ... ( በመጀመሪያ ደረጃ .ልብ ሊሉ ሚገባዎትና በተመስጦ እራሶዎን ሊጠይቁ ሚገባው ነገር....☞ ተዋንያን ተምን መሆን ፈለጉ.??? ታዋቂ ስለሚያደርግ ? ብር በደንብ ስለሚገኝበት ? ወይስ ተሰጦዎ ስለሆነ...? ) ሁለቱን አስበው ከሆነ ወንድማዊ ምክር ልምከሮዎ አይልፉ  ሌላ ነገር ይሞክሩ . ተሰጦዬ ነው ብለው ካመኑ ግን .አንድ ተዋናይ ምርጥ ለመሆን የሚያስፈልጉትን ሶስት መሰረታዊ ነገር ላውራዎ..... 1= ድምፅ 2= አካሉ 3= አዕምሮው ( ምናቡ ) ( እነዚህ 3 ነገሮች ለተዋናይ የሚያስፈልጉት መሰረታዊ ነገሮች ናቸው ) 1☞ ድምፁ...! ንግግር ወይም ድምፅ የሚፈጠረው .ከሰው ልጅ አካላት ውስጥ . በአፍ ፡ በምላስ ፡ በትናጋ ፡ በጥርስ ፡ በላንቃና ጉሮሮ ህብረት ነው. የተስተካከለ ድምፅ ለማምጣት አዕምሮ እንዚህን አካላት ማጣመር ወይም ማቀናጀት አለበት... እንደ ተዋናይ እነዚህ የሰውነት ክፍሎች ባህሪ. የድምፅን ልክና የሚነገረውን ነገር ፡ ሊያመጣ የተፈለገውን ስሜት .አቀናጅቶ መረዳትና በተገቢው ማስተላለፍ ካልቻለ. ትወና ይከብደዋል... እስቲ ምን ፊደል በምን በኩል እንደሚያልፍ እንይ... ለምሳሌ.... * በምላስ የሚነገሩ ፊደላት..( ደ፡ ሃ፡ ለ፡ ጠ፡ ተ ) * በትናጋ    የሚነገሩ ፊደላት ( ቀ፡ ከ ፡የ፡ኸ፡ገ ) * በአፍንጫ.....................( ቸ ፡ዠ፡ኘ፡ሸ፡ጀ ) * በከንፈር........................( ሀ፡መ፡ፐ፡ጰ፡ፈ፡ወ ) * በጉሮሮ.........................( ሀ፡ሐ፡አ፡ኀ፡ ) * በጥርስ..........................( ሠ፡ዘ፡ሰ፡ፀ፡ረ፡ዐ፡) እነዚህን ቃላቶች በሚገባ በመናገር ድምፅ ማውጣት ላይ የተሻለ መሆን ይቻላል.. ከዛ በተጨማሪ... የመተንፈሻ አካላትንም ሆነ ትንፋሽን ሊያሳጥሩ ከሚችሉ ነገሮች መቆጠብ. ሲጋራ ፡ አልኮል መጠጦች.... በተቻለ መጠን የትንፍሽ እስፖርት መስራት.... እረጋ ባሉ ዘፈኖች ቮካል መለማመድ....መዝፈን ማንጎራጎር. ( በተለይ ጠዋት ቢሆን ይመረጣል ) እነዚህን መንገዶች በተከታታይ ያለ ሟቋረጥ በመስራት ፡ ድምፆትንና ትንፍሾትን ያስተካክሉ..... 2☞ አካል.....                  ( ይቀጥላል..... )
Show all...
 ☞ጓዶች...ትላንት ቃል በገባነው መሰረት . እናወራባቸዋለን ብለን ባነሳናቸው ሀሳቦች እንወያያለን . ከጥበብ ምንነት ጀምረን እስከ ትወና ምንነት እናወራ... ኪነ ጥበብ ምንድነው ?? አዲስ ተስፋ a guide to future film writng በሚል መፀሐፉ ላይ ☞ የኪነ ጥበብ ዘርፎች ማለትም .ስነ ስዕል ፡ ስነ ፁሁፍ ፡ ሙዚቃ ፡ ቴያትር ፡ የአንዳንድ ሀገር ርዕዮተ አለም እንዲወክሉ ሆነው በምናባዊ የፈጠራ ክሂሎች ተቀምረው ይቀርባሉ፡፡ ከስነ ፁሁፍ ውስጥ የማገኘው የፊልም ፁሁፍ . ከፈጠራ ድርሰቶች .ለምሳሌ ከረጅምና አጭር ልቦለድ ፡ ተውኔት ፡ ድራማ ፡ ግጥም ፡ ወጎችና ፡ ተዛማች የፈጠራ ስራዎች አንድ የሚያደርገው በሀሪ አለው .. ይኸውም የአንድን ሀገር ወይም ዘመን ፍልስፍናዊ ፡ ኢኮኖሚያዊ ፡ ፖለቲካዊ ፡ አመለካከቶችና አስተሳሰቦች ጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ ፡ ከዘመን ዘመን ያሸጋግራል..... ☞ ይህ ማለት ከስነ ፁሁፍ ዘርፎች ውስጥ ፊልም የአንድን ሀገር ሁለንተና ገፅቃዋን ፍልስፍናዋን ይናገራል ማለት ነው.. የፊልም ፁሁፍ ከመነሻ ታሪክ ጀምሮ እስከ እስክሪን እስኪቀርብ ድረስ ብዙ ፕሮሰሶች አሉት ( እሱን በሰፊው እመለስበታለሁ ) ፊልም ታሪክ ከሚኖራቸው አለባውያን...መቼት ፡ ጭብጥ ፡ ቃለ ተውኔት...ወዘተ. ቢኖሩትም . ከድርጊቱ ባሻገር ቃለ ተውኔት በዋናነት ይዘን. ቃለ ተውኔቱን የሚገልፁት አካላት ወይም ገፀ ባህሪያት ላይ እናወራለን...ከሚገለፁባቸው መንገዶች ውስጥ . ገፀ ባህሪው የመጀመሪያው ነው. (ለፊልም እስክሪፕት ሀሳብን ለመግለፅ. ድርጊትና ቃለ ተውኔት ማንቀሳቀሻ ሞተሩ ናቸው.ያ ማለት ሌሎች ነገሮች ሀሳቡን አይገልፁም ማለት አይደለም ) ገፀ ባህሪ እንሰሳም ፡ አሻንጉሊትም ፡ ሰውም መሆን ይችላል... እንደ ፊልሙ ሀሳብ ነው ሚወሰነው. እኛም ገፀ ባህሪን የሚወክላቸው  ሌሎቹን ነገሮች ትተን. ሰው ስለ ሚወኩላቸው ገፀ ባህሪያት እናወራለን.... ☞ ገፀ ባህሪ ምንድን ነው ከማለት ብንነሳ..... ገፀ ባህሪ ማለት የደራሲው ፍጡራን ናቸው. የፊልሙን ሀሳብ የሚያንቀሳቅሱ . የደራሲው የፈጠራ ውጤት ናቸው. ገፀ ባህሪውን ሚያንቀሳቅሱት ነገሮች ውስጥ .አክተር ወይም ተዋናይ የመጀመሪያው ነው. ያ ማለት . ተዋናይ ከራሱ ስብዕና ወጥቶ ገፀ ባህሪውን የሚወክል እና የሚጫወት ነው ማለት ነው.ሲጫወት ተወነ ይባላል...! ☞ ስለ ጥበብና የፊልም ፁሁፍ በስሱ ካወራን. በቀጣይ ተዋናይ ምን ሟሟላት አለበት በሚለው እንገናኛለን...                 
Show all...
ግለ-ንግግር (ሞኖሎግ) ክፍል ፪ ረጅም ዘመን ጠቃሽ ወይም ተራኪ ግጥሞች ና ወጎችን እንደ ግለንግር መቁጠር ስህተት ነው።ከዚበተጨማሪ ተዋንያን ትወና ሲጀምሩ በዝርው ግለ-ንግግር ቢለማድ መልካም ነው። ይህም በግጥም የተፃፉ ግለ-ንግግርን በግጥም አነባበብ እየተወኑ ዜመኛ ታዋቂ ተዋንያን ጭምር ምሳሌ በማድረግጀማሪ ዎችን በተሳሳተ መንገድ የሚመሩ መኖራቸው ይታወቃል በመሆኑም ጀማሪዎች በዝርው ገለ-ንግግር ይለማመድ።ግጥማዊ ግለ-ንግግር ከግጥማዊ ንበት አላቆ ተውኔትዊ ለዛ ና ስሜት በመፍጠር እንዴት መተወን አንመሚቻል እራሱን የቻለ አንድ ትምህርትልክ /ነው
Show all...
#ከታሪክ_ማሕደር 3 የውጫሌ ውልን #አንቀፅ-17ን የጣሊያንኛ ትርጉም ችግር ያለበት መሆኑን ያወቁ በኋላም ለእነራስ መኮንንና ጃንሆይ ያሳወቁ የመጀመሪያዉ ሰው ናቸው። ነጋድራስ ፕሮፌሰር #አፍወርቅ ገ/ኢየሱስ በሀገራችንም የመጀመሪያው የልብወለድ ታሪክ [#ጦቢያ]” (1900)እ.ኤ.አ አሳትመዋል ይህ መፅሐፍም 90 ገጾች አሉት። አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ በ1860 ዓ.ም ዘጌ(ጣና ሀይቅ) በተሰኘችው ስፍራ ተወለዱ አፈወርቅ የ20 ዓመት ብላቴና ሳሉ በ1880 ዓ.ም ወደ ስዊዘርላንድ ለትምህርት ተላኩ። ከዛም ወደ ጣሊያን ቱሪን ሄደው በኮሌጅ ኢንተርናሲዮናል ደ.ቤሊ አርቲ ከፍተኛ የሥነ ጽሑፍ ትምህርት ተከታተሉ። ከአድዋ ጦርነት በፊት ወደ ኢትዮዽያ ተመልሰው በ1882 በቤተመንግስት ባለሟልነትና በሠዓሊነት ሙያ አገለገሉ፡፡ በ1908 ዓ.ም. እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በሮም ባሳተሟት ልቦለድ ታሪክ የፈጠራ ሥራቸው-በኢትዮጵያ የአማርኛ ዘመናዊ ሥነጽሑፍ መሥራች ካሰኛቸው ማእረግ ባሻገር በአፍሪካ ቋንቋዎችም ታሪክ- በሀገርኛ ቋንቋ በመጻፍ የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ የሚል ምስክርነት አግኝተዋል። ነጋድራስ አፈወርቅ ገ/ኢየሱስ በተወለዱ በ79 ዓመታቸው መስከረም 15 ቀን 1939 ዓ.ም አረፉ።
Show all...
የትወና ጥበብ : ቴአትር በመድረክ ;ስናቀርብ በራዲዮ ሞገድ በድምፅ ስናስራጭ;በቴሌቪዥን መስኮት ድራማ ስናቀርብ;በፊልም ስክሪን ተዉኔታዊ ክዋኔ ስናይ በሁሉም ዉስጥ የተለያዩ ተግባራት በመፈፀም በአካላቸውና በድምፃቸው አንድ ታሪክ የሚነግሩ ሙያተኞች ተዋንያን ይባላሉ። ተዋናይ ሰው ወይም እንስሳ ሊሆን ይችላል። ዋናው ነገር በአንድ ድርሰቱ ዉስጥ የተፃፋትን ገፀ-ባህሪያት ወክሎ እንደነሱ የሚናገር የሚንቀሳቀስ ፍጡር (ሙያተኛ)ነው።ለምሳሌ ሪን ቲን ቲን ዉሻ ሲሆን በአሜሪካን ሆሊውድ የታወቀ ተዋናይ ነበር ከላይ በገለፅኩት መገኛ ማለት በመድረክ .በሬዲዮን .በቴሌቪዥን እና በፊልም የሚርቡ ተዉኔቶች በሙሉ በመጀመሪያ ደራሲው ድርሰት ይፅፋል።የሚፅፈው የመድረክ ተዉኔትድርሰት፡የሬድዮ ተውኔት ድርሰት፡ የቴሌቪዥን ድርሰት እና የፊልም ተውኔት ድርሰት ሊሆን ይችላል ሁሉም ተውኔት ቢሆንም ከመገናኛቸው ወይም ማቅረቢያቸው አንፃር ግን ይለያያሉ። እናም ፀሐፊው ድርሰቱን ፅፎካመጣበኋላ በአዘጋጅ ወሳኝነትበድርሰቱ ውስጥ የተፈጠሩትን ገፀ-ባህሪያት ተዋንያን ተመልምለው አጥንተው ይተውናሉ።
Show all...
ግለ-ንግግር (ሞኖሎግ) ክፍል ፪ ረጅም ዘመን ጠቃሽ ወይም ተራኪ ግጥሞች ና ወጎችን እንደ ግለንግር መቁጠር ስህተት ነው።ከዚበተጨማሪ ተዋንያን ትወና ሲጀምሩ በዝርው ግለ-ንግግር ቢለማድ መልካም ነው። ይህም በግጥም የተፃፉ ግለ-ንግግርን በግጥም አነባበብ እየተወኑ ዜመኛ ታዋቂ ተዋንያን ጭምር ምሳሌ በማድረግጀማሪ ዎችን በተሳሳተ መንገድ የሚመሩ መኖራቸው ይታወቃል በመሆኑም ጀማሪዎች በዝርው ገለ-ንግግር ይለማመድ።ግጥማዊ ግለ-ንግግር ከግጥማዊ ንበት አላቆ ተውኔትዊ ለዛ ና ስሜት በመፍጠር እንዴት መተወን አንመሚቻል እራሱን የቻለ አንድ ትምህርትልክ /ነው
Show all...
ግለ- ንግግር (ሞኖሎግ)ክፍል፩ ሞኖሎግ (ግለ-ንግግ)በአንድ ተዉኔት ውስጥ ለአንድ ተዋናይ ንግግ ተደርጎ ታሪክ /ድርጊት ነው ይህም አጭር ወይም ረጅም ሊሆን ይችላል ።ለትወና መለማመጃ ነትየሚውል ግለ-ንግግ በአንድ በአንድ ተውኔት ውስጥ በንረት ትዕይንቶች ውስጥ የሚመጣና የአንድን ገፀ-ባህሪ ህይወት ከጅምር እስከ ፍፃሜ ድረስ ያለ ህይወቱን የሚዳስስበት ስፍራ ላይ የሚገኝ ግለ-ንግግር ተገቢ ነውግለ-ንግግ እና ረጅም ግጥም የተለያዩ ናቸው። ግለ -ንግር እንደ ህብራዊ ንግግር/ቃለ- ተውኔት ሁሉ በግጥምወይም በዝርው/ ብትን ፁሑፍ ተፅፎ ሊገኝ ይችላል ይቀጥላል……
Show all...
የገፀ ባህሪ አሳሳል.... አንድ ፊልም ሲፃፍ... . ፀሐፊው ወይም ደራሲው የሚያካትታቸው ገፀ ባህሪያትን . አራቱን የገፀ ባህሪ አሳሳልን በመከተል ቢፅፍ የተሻለ ይሆናል. ይህ የገፀ ባህሪ አሳሳል ዘዴ .እንደ ደራሲውም ለተዋናዩ ዘርፈ ብዙ ጥቅም አለው . አንድ ተዋናይ የፊልም እስክሪፕት መጥቶለት . የሚሰራውን ካራክተር ከመረጠና ከተስማማ በዋላ. የተሰጠውን እስክሪፕት ደጋግሞ በማንበብ . የተሰጠውን ገፀ ባህሪ በ 4 አሳሳል መንገዶች ተጠቅሞ የተሰጠውን ካራክተር በመዋሀድ ሆኖ የመተወኑን ጥበብ ይካነዋል.. እነዚህ የገፀ ባህሪ አሳሳል ደረጃ ውስጥ የመጀመሪያው... 1 . አካላዊ አሳሳል ደረጄ ይባላል.. ይህም የተዋናዩ ውጫዊ ማንነቱን ምናውቅበት ወይም ምናበለፅግበት ነው. 2. ማህበራዊው አሳሳል ደረጃ ይባላል. ይህም ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ግንኙነትን ያሳያል 3. ስነ ልቦናዊ የአሳሳል ደረጃ ይባላል . .ይህም ውስጣዊ ማንነቱን ምናቅበት ነው 4. ሞራላዊ የአሳሳል ደረጃ. ነው... ከዚህም በተጨማሪ ተዋናዩ የገፀ ባህሪውን ፍላጎትና ግቡን ቢያቅ ተመራጭ ያረገዋል. እነዚህን 4 የገፀ ባህሪ አሳሳሎችን በቀጣይ ተንትነን እንመለከታቸዋለን.........
Show all...
☞ ምናብ ..... ምናብ ለአንድ ተዋንያን እንደ አካል ፡ እንደ ድምፅ ፡ መሰረታዊና ጠቃሚ ነው...! ምናብ ነገሮችን በአይምሮ የመሳል ጥበብ ነው . አንድ ተዋናይ የተሰጠውን ገፀ ባህሪ ከ እስክሪፕቱ ላይ በማንበብ . ገፀ ባህሪው ምን አይነት ፊዚካል ፡ ምን አይነት አስተሳሰብ ፡ አረማመዱን ፡ አነጋገሩን ፡ በአይምሮው ቀድሞ የመሳል ጥበብ ነው. አንድ ተዋናይ የምናብ ብቃቱ አሪፍ እና የተሻለ ለማረግ . የመፀሐፍ ንባብ ፡ ኢንፕሮቫይዜሽን በማድረግ ፡ የምናብ ልምድ ሊያዳብር ይገባዋል...! በተለይ የተለያዩ እስክሪፕቶችን በማንበብ ካራክተሩ ( ገፀ ባህሪው ) ምን ሊመስል እንደሚችል በምናቡ ወይም በህሊናው በመሳል መለማመድ ይኖርበታል. ለምሳሌ አንድ ኢንፕሮቫይዜሽን ስራ እንሞክር. እስክሪፕቱ ላይ እንዲ የሚል ድርጊት ተፅፋል...! ☞ አንድ ጥቅጥቅ ያለ ጫካ ውስጥ . በጣም ረጅምና በጠባቡ በሆነ መንገድ ላይ በባዶ እግርህ ብቻህን እየተጓዝክ ነው .ፀሐይዋ ወደ ቤቷ እየጠለቀች ነው. እንዳይጨልምብህ ቶሎ ቶሎ እየተራመድክ ነው.በጣም በተራመድክ ቁጥር በአካባቢው የአውሬዎች ድምፅ ጎልቶ ይሰማል. እና በምትሰማው ድምፅ በጣም እየፈራህ ነው. በፍርሀት እየተጓዝክ በመሀል የሚለሰልስ ነገር ረገጥክ .. ዝቅ ብለህ ስታየው የተጠቀለለ ጥቁር እባብ ነው.......... እያለ የሚቀጥል ድምፅ ድርጊት ቢኖር. አንተ ደሞ የዚን ገፀ ባህሪ ወክለህ ምትጫወት ቢሆን. የካራክተሩ የአካሄድ ሁኔታ ፡ ፍራቻው ፡ አካዋወኑን .... በህሊናህ ወይም በምናብህ ልትስለው ይገባል. ☞ የተዋናይ 3 መሰረታውያንን አይተናል. በቀጣይ አንድ ተዋናይ . ገፀ ባህሪ ሲሰጠው . ገፀ ባህሪውን እንዴት አርጎ በ 4 መንገድ እንደሚስላቸው እንመለከታለን.....
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.