cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አፈምዑዝ🗣

በዚህ ቻናል ትምህርታዊ፣ ሐገራዊ ፣ ፍልስፍናዊ ሃሳቦችን እናነሳለን። ለአስተያየታችሁ T.me/Medlotetsedk

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
189
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

~ መጀመሪያ ዐሥራቴን አወጣለታለኹ ~ August 15, 2022 by ዲ/ን : ዳዊት : ሰሎሞን ፡፡ ብዙዎቻችን “ይኽን ያኽል ገንዘብ ብታገኝ ምን ታደርገዋለኽ?” ተብለን ብንጠየቅ የምንሰጠውን መልስ አስተውለነው እናውቅ ይኾን? “እንዲኽ እንዲኽ ዐይነት ቢዝነስ እጀምርበታለኹ ፣ እንዲኽ እንዲኽ እገዛበታለኹ ፣ እንዲኽ አደርግበታለኹ” እና መሰል መልሶች ናቸው ከአንደበታችን የሚወጡት።  አንድ ወዳጄ ግን የዋዛ አልነበረም። ይኽ ወንድሜ “ይኽን ያኽል ገንዘብ ብታገኝ ምን ታደርገዋለኽ?” ተብሎ ሲጠየቅ ዘወትር የሚመልሰው ነበር - "መጀመሪያ ዐሥራት አወጣለታለኹ!"  አንዳንዴ ይኽቺን መልሱን አሽሞንሙኖ ሲጠራት ‘Investment before Investment' ይላታል። “አፉ ላይ ነው። ይኼኔ ተግባር ላይ ባዶ ይኾናል” ብሎ የሚያጉረመርም ሰው ካለ ተግባሩም ላይ እንደ አፉ እንደኾነ ልነግራችኹ እወዳለኹ። ከቅርበታችን የተነሣ ጥቃቅኗን ነገር ኹሉ ስለምንጋራ ይኽን እውነታ ተረድቻለኹ። ይኼው እስከዛሬ ርሱን ይኽቺን ብሂሉን አልተወም። ተግባሩንም አልተወም። እግዚአብሔርም በረከት መስጠቱን አልተወም። እርሱም በዐሥራቱ ይታመናል። እግዚአብሔርም በበረከቱ ይታመናል! አንድ አባት “እኔ ኪሶቼን በምጽዋት ባዶ አደርጋለኹ። እግዚአብሔርም ይሞላቸዋል። እኔም ቃሌን በልቼ አላውቅም። እርሱም ቃሉን ተላልፎ አያውቅም” እንዳሉት ማለት ነው። በርግጥ እጅግ ዳጎስ ያለ ገንዘብ አግኝቶ በርግጥ ጭካኔውን አላየኹም። የሚሳሳ ግን አይመስለኝም። ምክንያቱም ዐሥራት ከማውጣት የሚገኘውን በረከት ዐሥራት ከመቅጣት የሚገኘውን ርግማን በደንብ ቀምሶታልና ነው። በዛ ላይ “በጥቂቱ የታመነ..” የሚለው ፎርሙላ የት ኼዶ?     እኩል ገንዘብ ኹለታችንም አግኝተን እኔ ሳስቼ በኾነ ምክንያት አሳብቤ ዐሥራቴን በልቼ ስ‘በላ እርሱ እጁ ላይ የቀረው ዘጠኝ ዐሥረኛው ብቻ ነው። አንድ ዐሥረኛው ለኾነ የቤተ - ክርስቲያን አገልግሎት ውሏል። ስስት ያሸፈተው ውስጤ “ከምኔው ጨከነ?” ይላል። ዐሥራት የማውጣቱን ፍሬ የማየው ከቀናት በኋላ ነው። አንድ ዐሥረኛው ዐሥራት ራሱን ሙሉ አድርጎ ዐሥር ዐሥረኛ ኾኖ ራሱን አባዝቶ እጽፍ ድርብ ኾኖ  ይመጣል። “ወይ ግሩም!” ማለት ብቻ! አኹን አኹን ተመስገን ነው። ትንሽ እየተሰበኩ ነው። ይኽን ኹሉ ምሥጢር በማውጣቴ መቼም ወዳጄ መቀየሙ አይቀርም። ግን ምን ላድርግ? ነገርዬውን ገሃድ ማውጣቱ ለብዙዎች ጥሩ ምሳሌ ይኾናል ብዬ ስላመንኹ ይኽን አደረግኹ።   ይኽ ወዳጄ ሌላም የሚላት ብሂል አለችው። “ዐሥራት ማለት ምን ማለት ነው?” ብላችኹ ብትጠይቁት “ከገንዘባችኹ ወይም ከእህላችኹ ላይ አንድ ዐሥረኛ ለእግዚአብሔር መስጠት ማለት ነው” ብሎ አይመልስላችኹም። እህሳ? “አንዳች ነገር 'የበቁ አባት ፊት' ወስደን ‘ይባርኩልኝ አባ!’ ብለን እንደምናስባርከው ዐሥራት ማውጣት ማለትም ገንዘብን ወሰዶ ‘ባርክልኝ እግዚአብሔር!’ ብሎ በእጁ አስባርኮ ‘መልሶ መውሰድ’ ማለት ነው” ብሎ ‘define' ያደርገዋል እንጂ። ግሩም ድንቅ! አባ ገብረ ኪዳን (ርእሰ ሊቃውንት) በአንድ ስብከታቸው እንዲኽ ብለው ነበር፦             “ዐሥራት ማውጣት ማለት መንፈሳዊ ንግድ መነገድ ማለት ነው።. . . እግዚአብሔር ‘ከ ዐሥር ብር አንድ ብር ስጡኝ’ ሲል ምን ማለቱ ነው? ‘ዘጠኙን ልባርክላችኹ’ ማለቱ ነው። ‘ለዘጠኙ ዘበኛ ልኹንላችኹ’ ማለቱ ነው። ንግድ ማለት ይኼ ነው - ‘እኔ ለአንተ አንድ እሰጥኻለኹ። አንተ ለኔ ዘጠኙን ባርከኽ ስጠኝ’ ማለት ነው። ‘የለም የለም! አንዷንም አናቀምስኽም!’ ማለት ደግሞ ‘ዐሥሩንም አባክንልን!’ ማለት ነው። “መጀመሪያ ዐሥራቴን አወጣለታለኹ!”  ይቆየን!
Show all...
~ እኔ እናት እኾናለኹ! ~ August 13, 2022 by ዲ/ን : ዳዊት : ሰሎሞን ፡፡ ውልደቱ በአውስትራሊያ ሀገር ነበር። የምንኲስና ኑሮው ደግሞ የቅዱስ እንጦንስ ገዳምን ጨምሮ በሌሎች ገደማት። “አባ አልዓዛር” ይባላል። በ‘እግዚአብሔር የለም’ እምነት ውስጥ ለአርባ ዓመታት የሚኖር አባት ነበር። የእናቱን ሞት ተከትሎ ለዓመት ያኽል ውስጡ ሠላምን አጥቶ አለመረጋጋትን ተመልቶ ከባድ ጊዜያትን አሳልፏል። ወደ ምንኲስና ሕይወት ከመግባቱ በፊት በአንድ ወቅት ‘ቅዱስ ሳቫ’ ተብሎ በሚታወቅ አውስትራልያ ሀገር ውስጥ በሚገኝ አንድ የሰርቪያ ኦርቶዶክስ ገዳም ውስጥ የገጠመውን እንዲኽ ይተርክልናል፦ ‘ወደ ቤተ - ክርስቲያኑ ስገባ እኔ የመጨረሻው ነበርኹ። ቀድመው የገቡ ኹሉ ፊት ለፊታችን በምትገኝ ለየት ባለ ትልቅ ፍሬም የተቀመጠች ግድግዳው ላይ ተስቅላ ፊት ለፊቷም ላይ መቅረዝ ይበራባት በነበረች በአንዲት የእመቤታችን ስዕለ አድኅኖ ፊት እየተሳለሙ ሦስቴ እየሰገዱ ሲያልፉ እመለከታለኹ። የሚያደርጉትን ተግባር ምን እያሰቡ ይሰግዱም እንደነበር አልተረዳኹትም ነበርና ተግባራቸውን በአትኩሮት እመለከት ጀመር። ኹሉም ተሳልመው ከጨረሱ በኋላ ተራዬ ደረሰና ወደ ስዕሏ ተጠጋኹ። “እኔ በዚኽ ቦታ ጎብኚ ነኝና ሌሎች እንዳደረጉት ማድረግ ይገባኛል” ስል አሰብኹ።   ምንም ለኔ ዐዲስና እንግዳ ነገር ቢኾንብኝም በጉልበቴ ተንበረከክኹ። ወደ ቤተ - ክርስቲያኑ ስገባ ስዕሏ የ “ወላዲተ - አምላክ” ወይም “የእመ - አምላክ” ስዕል እንደኾነች ሰዎች ነግረውኝ ነበር። በጉልበቴ እንደተንበረከክኹ “እመ - አምላክ - የአምላክ እናት” ስለሚለው ስም ማሰብ ጀመርኹ። “እኔ በዚኽ ሰዓት እናት የለኝም። እግዚአብሔር ደግሞ አ‘ለው። እግዚአብሔር ስለምን እናት ኖረው? እኔስ ስለምን አልኖረኝም?” የሚል ሓሳብ ውስጥ ገባኹ። ያለ እናቴ ምን ያኽል ብቸኝነት እንደወረሰኝ እያሰብኹ ዕንባዬ በጉንጮቼ ላይ ይፈስስ ጀመር። በዝግታ ተነሥኹና ኹለተኛውን ስግደቴን ለመስገድ ተዘጋጀኹ። እንደ ቀድሞው ተንበረከክኹና ግንባሬን መሬት አስነክቼ ተመሳሳይ ቃላትን ደጋግሜ እናገር ጀመር። ከዚያም ፥ ለስለስ ያለ ፣ ጥርት ያለ እና እጅግ መሳጭ ድምጽ “እኔ እናት እኾንኻለኹ” ብሎ ሲናገኝ ተሰማኝ። ምናልባት ከሰርቪያውያን ሴቶች አንዷ ከኋላዬ ደርሳ ልታጽናናኝ የተናገረችው መስሎኝ ቀኝና ግራዬን ዘወር ዘወር ብዬ ቃኘኹ።  ነገር ግን ማንም አልነበረም። ሦስተኛውን ስግደቴን ለመስገድ ቀጥ ብዬ ቆምኹ። በዚኽ ጊዜ ደጋግሜ ስጠራቸው የነበሩትን ቃላት ሙቀት ልምላሜ በተዋሕደው ጸሎት እጠራቸው ጀመር። እኔ ግን አልታወቀኝም ነበር። ታዲያ በዚኽም ጊዜ ቀድሞ የሰማኹትን ድምጽ “እኔ እናት እኾንኻለኹ” ሲል ደግሜ ሰማኹት። ማን እንደሚናገረኝ ለማወቅ ጓጓቼ ጣሪያ ጣሪያውን አስስ ጀመር። ምንም የለም። ነገር ግን በድንገት ስዕሏ ወደ እኔ አዘነበለች። ስዕለ አድኅኖው በቦታው እንዳለ ቅድስት ድንግል ማርያምም ከስዕሏ ወጥታ በፊቴ ቆመች። ፍቅርን በተመሉ ዓይኖቿም ፈገግ ብላ ትመለከተኝ ጀመር። ከዚያም ቃሏን ደገመችው ፦ 'እኔ እናት እኾንኻለኹ!' ውስጤ ታላቅ የኾነን መጽናናትን አገኘ። ሕመሜና ሐዘኔ ጓዘቸውን ጠቅልለው ውልቅ አሉ። ውስጤ ቀምሼው በማላውቅ አንዳች ደስታ ተጥለቀለቀ። ሌላ እናት እንዳገኹ አወቅኹ። እመቤቴ አኹንም ዘንበል ብላ እየተመለከተችኝ ነው።  እኔም ልጇን እጅግ በጥንቃቄ እንደምትንከባከብ እናት ኾና በብሩህ ገጽ እያየኋት ነው። ጭንቀቴ ኹሉ ጥሎኝ ጠፋ። ከእርሷ የሚወጣው የብርሃኑን ነጸብራቅ መቋቋም ስላቃተኝ ፥ ራሴን ዘንበል አደረግኹ። እርሷም ወደ ስዕሉ ተመልሳ ገባች። ቆም ብዬ አካባቢውን ቃኘኹ። ቤተ - ክርስቲያኑ እንደ ቀድሞው ጸጥታ እንደሰፈነበት ነበር። ማንም ኾነ ማን ምንም ምን አላየም ነበር። (አባ አልዓዛር ከዚኽ በኋላ እመቤታችን ባደረግችላቸው ነገር ልባቸው ተነክቶ በብሐትውና ኑሮ በሕይወት እየኖሩ የሚገኙ አባት ናቸው።)
Show all...
❝የሚጾም ሰው ሲያይ ሰይጣን ይፈራል!❞ April 9, 2021 by ዲ/ን : ዳዊት : ሰሎሞን ፡፡ በዚኽ አንቀጽ ስለ ጾም ማንሣት ተፈልጎ የተጠቀሰው ርእስ ተመረጠ እንጂ ሰይጣንስ የሚጾም ሲያይ ብቻ አይደለም የሚፈራው፡፡ የሚጸልይም ፣ የሚሰግድም ፣ የሚመጸውትም እንዲያው በአጠቃለይ በጽድቅ ሥራ የተጠመደ ሰው ሲያይ ሰይጣን ይፈራል፡፡ በነገራችን ላይ ፥ እንዲህ የሚልኽ ግን ማር ይስሐቅ ነው እንጂ እኔ አይደለኹም፡፡ ለጊዜው አነቀጹንና ገጹን ግን አላስታውሰውም። ይቅርታ ይደረግልኝ! ሰይጣን ግን ለምን የሚጾም ሰው ሲያይ ይፈራል? እርሱን እስኪ አብረን እንከታተል ፦ ፍትሐ ነገሥት ከጾም ስለምታስገኘው ረብህ ጥቅም ሲናገር ፥ " ... በደሉን ለማስተሥረይ ፣ ዋጋውን ለማብዛት ፣... የፈቲውን ኃይል ያደክም ዘንድ. . . " ነው ይለናል።¹ ስለዚኽ ኹሉ ነገር ጾም ትረብኻለች ትጠቅምኻለች። እስኪ አንድ በአንድ በስሱ እንዳስሳቸው ፦                         +++ በደሉን ለማስተሥርይ +++ "በጾም ወበጸሎት ይሠረይ ኩሉ ኃጢአት" እንዳለ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ፣ ዳግመኛም በሕዝበ - ነነዌ እንዳየነው አባቶችም እንዳስተማሩን ጾም ጸሎት ኃጢአት የሚሠረይባቸው ዕቃ ጦር ናቸው። በደልኽ ተሠረይልኽ ማለት ደግሞ ሰይጣን ለዓመታት ሲገነባው የነበረው የኃጢአት ግንብ ፈረሰበት ማለት እኮን ነው። ድካሙ ኹሉ ከንቱ ቀረ ማለት እኮን ነው። ለዓመታት የደከመበት ሕንፃው ቢፈርስበት የማያዝን ማን ነው?!  ይኽ ከኾነ ዘንድ ፥ የሚጾም የሚጸልይ ሰው ሲያይ ሰይጣን እንዴት አይፈራ?!                                        +++ ዋጋውን ለማብዛት +++                  የሰው ልጅ በሕግ የታዘዘውን ያኽል ቢጾም ፣ የተዘጋጀለትን ዋጋ ይቀበላል። የፈጣሪን ትዕዛዝ አክብሮ የተደረገ ነውና። ከሕግ ከታዘዘው በላይ ቢጾም ደግሞ በዛው ልክ ዋጋውን ያበዛል።  ፍትሐ ነገሥት ከዐቢይ ጾም ውጭ ስላሉት አጽዋማት ሲናገር ፥ “በእለዚኽ አጽውማት እስከ ፱ ሰዓት ድረስ ይጹሙ። ከዚኽ አብልጦ የጾመ ግን ዋጋው ይበዛለታል” እንዳለ።² ልበ - ሙሉ የኾኑት በሰዓት ጠንቅቀው ይጾማሉ። ልባቸው የተከፈለባቸው ደግሞ "ዋናው መጾም ነው እንጂ ፣ ከፍ አድርገው ጾሙት ዝቅ አድረገው ጾሙት ያው ነው!" ይላሉ። ከእነአካቴው ልብ የሌላቸው ደግሞ "ጾም አያስፈልግም" ይላሉ!                    +++ የፈቲውን ኃይል ያደክም ዘንድ +++ በአንድ ወቅት አንዲት ሴት በፍትወት ስሜት ተነሣሥታ የፍቅር ጓደኛዋን የሥጋ ፍትወቷን ይፈጽምላት ዘንድ ግድ ትለዋለች። እርሱም መለሰ ፦ “እሺ! ነገር ግን ለተወሰኑ ቀናት ዳጎስ አድርገን እንጹምና ፈቃድሽን እፈጽምልሻለኹ”አላት። በዚኽም ተስማምተው ጾሙ ተጀመረ። ቀናት ነጎዱ። የተስማሙት የጾም ቀናት በተጠናቀቁ ጊዜ ወንዱ በተራው ሓሳቡን ያነሣል ፦ “አኹን ፈቃድሽን ልፈጽምልሽ እችላለኹ”። እርሷ ግን ፦ “ይቅርታ ሓሳቤን ቀይሬአለኹ። አመሰግናለኹ” ስትል መለሰች። የሰይጣንም ተንኮል በዚኽ ፈረሰበት። ፍትወቱ በጾሙ ዐለፈ! ጾም እንዲኽ ናት! ታዲያ ሰይጣን ይኼን እያወቀ የሚጾም ሰው ሲያይ እንዴት አይፈራ?! ወዳጄ! “የጾም ረብህ ጥቅሟ ምንድር ነው?” ብለኽ ብትጠይቀኝ ፥ “የሥጋ ፈቃድ እንደ ፈረስ ሲጋልብኽ ፣ እንደ ጅራፍ ሲገርፍኽ ፣ እንደ አራዊት ሲያደርግኽ ፥ ያኔ የጾም ምንነት ይገባኻል!” ብዬ እመልስልኻለኹ። ለጊዜው ጨርሻለኹ። ይቆየን! ¹ ፍት ነገ.፲፭ ፥ ፭፻፷፬ ² ፍት ነገ.፲፭ ፥ ፭፻፸፪
Show all...
✝ ሰላም ለሁላችሁም ይሁን እያልኩ ሰላምታየን አቀርባለሁ። እንደምን አላችሁልኝ እኅት ወንድሞቼ እኔ ደኅና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን። ✍እግዚአብሔር ቢፈቅድና ቢዎድ ከነሐሴ ወር ጀምረን ብርቅየ የሆነውንና ለኢትዮጵያችን ብቻ የሆነውን ባሕረ ሀሳብን እንቀምራለን፣የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የምትጠቀምበትን ነበዓላትና የአጽዋማት የሚውሉበትን መአልትና ሌሊት እንቀምራለን። ✍ አባቶቻችን ሊቃውንት በሚቀምሩበት የቀመር ስልትና ኦንዲሁም ቀለል ባለመልኩ ቶሎ በምንችልበትና ትንሽ ቀናትን በሚወስድ መንገድ እንቀምራለን ፣እናሰላለን ማለት ነው። ✍ በብሉይ ኪዳን ነቢያቱ ፣ እግዚአብሔር ለአዳም ቃል ኪዳን በገባለት መሰረት 👉 እንዲህ ሲል "በኀሙስ እለት ወበመንፈቃ ለእለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድህከ እምወለተ ውስተ መርህብከ ወእትቤዘወከ በመስቀልየ ወበሞትየ " ይህንን የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን አዳም ለልጆቹ ነግሯቸው ስለነበር ነቢያቱም ይህን ይዘው የእግዚአብሔር ወልድን መምጣት በፀሐይና በጨረቃ እየቆጠሩ ያሰሉ ይቀምሩ ነበርና። ይህንንም መነሻ በማድረግ እኛም በብሉይ ኪዳን ቢአንስ የ3ቱን አበይት ነቢያት አቆጣጠር እናያለን። ✍ በዋናነት ደግሞ በሐዲስ ኪዳን የቅዱስ ድሜጥሮስን አቆጣጠር መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠርን (calendar) በሚገባ እናያለን። ✍ እንዲሁም በዓላትን፣አጽዋማትን በማንኛውም አመተምሕረት ወደፊት ርቀን በመሔድ ወደኋላም መለስ እያልን እንቀምራለን ማለት ነው። ✍ ከእኛ የሚጠበቀው አጀንዳችንን አዘጋጅተን እየጻፍን መከታተል እና እኛም ለሚቀጥሉት ጀኔሬሽን ይህን ውድና ብርቅየ የሆነውን የኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ማስተላለፍ ነው። ✍ በአብዛኛው ባሕረ ሀሳብ ሲቀመር ሒሳባዊ ባህሪ ስላለው እንደምራለን(+) ፣እንቀንሳለን(-)፣እናባዛለን( *) እናካፍላለን(፥) ማለትነው so ማወቅ የምትፈልጉ ካላችሁ ለመዘጋጀት ሞክሩ አብረን እየተረዳዳን እንማማራለን ማለት ነው። ይቅርታ አበዛሁባችሁ። ስለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ይርዳን አስጀምሮም ያስፈጽመን። ✝ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
Show all...
የሐዋርያው የቅዱስ እንድርያስ ታሪክና የቅኔ ማስነገሪያ
Show all...
የሐዋርያው የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ታሪክና የቅኔ ማስነገሪያ
Show all...
🌿🌿የዘአምላኪየ ዜማ ልክ🌿🌿 ✍ የዘአምላኪየ መደብ መጀመሪያ እንደ ግዕዝም እንደ ዕዝልም ልክ እንደ ጉባኤ ቃና ነው። ✍ተቀባዩም፦ ከማሁ ✍የቤት መምቻውም መደቡም እስከቤት መምቻው ድረስ ከማሁ። እንደጉባኤ ቃና ማለቴ ነው ✍ ሁለተኛው ቤት👇👇👇 መደብ መጀመሪያው ተነሽ/ተጣይ = ከ2 -- 4 ሰያፍ = ከ3--5 ወዳቂ = የዘአምላኪየ የሁለተኛው ቤት መደብ ማስጀመሪያ አይሆንም። ✍ ማንደርደሪያው = በተናባቢ 6 6 ሰያፍ ግን በምንም ሁናቴ ማንደርደሪያ አይሆንም። ✍ የቤት መምቻው መደብ መጀመሪያ ተነሽ = ከ3--4 ሰያፍ = ከ 4 -- 5 ተጣይ = ከ 4 4 ወዳቂ = 3 3 ሲሆን ✍ ቤት መምቻው ደግሞ 👉የ3ቱ ተነሽ የ4ቱ = መደብ ተቀባይ(ቤት መምቻ) ተነሽ፣ተጣይ ወዳቂ እንበለ ሰያፍ 3 3 👉 የ4ቱ ተነሽ የ5ቱ ሰያፍ = መደብ ተቀባይ(ቤት መምቻ) ተነሽ ፣ ተጣይ፣ ወዳቂ እንበለ ሰያፍ 2 2 👉 የ4ቱ ተጣይ መደብ ተቀባይ (ቤት መምቻ) ተነሽ፣ተጣይ፣ወዳቂ እንበለ ሰያፍ (ያለ ሰያፍ)= 2ም 3ም 👉 የ3ቱ ወዳቂ = መደብ ተቀባይ 3ቱ ንባባት(ተነሽ ፣ተጣይ፣ወዳቂ እንበለ ሰያፍ)= 3 3 🙏 በቀጣይ ወደ ሚበዝኁ ቅኔ ዜማ ልክ እንሄዳለን። 👉ወስብሐት ለእግዚአብሔር 👉ወለወላዲቱ ድንግል 👉 ወለመስቀሉ ክቡር ✝✝✝ይቆየን✝✝✝
Show all...
🌿🌿🌿 የ "ለ" ግስ🌿🌿🌿 ሐለለ (ቀተ) = አረረ፣በራ፣ተቃጠለ፣ሰፋ ደረተ ሐመለ (ቀተ) =ለቀመ፣ቀነጠሰ፣ጫነ ተሸከመ ሐሰለ (ቀተ)= ለበበ ፣ከተተ፣ሰበሰበ፣ሳበ ፣ጎተተ ሐቀለ (ቀደ)= ቀማ፣ባላገር ኾነ፣ ኃበለ (ቀደ) = ተደፋፈሩ፣ ሐበለ (ቀተ) = ታታ፣ (ሐብል=ገመድ) ሐብለ (ቀተ) = ዋሸ፣ ሐንበለ (ተን) = ጫነ የኮረቻ ሖለ/ሐወለ/(ቀደ,ቀተ)= ቀላቀለ፣አደባለቀ ሐዘለ (ቀተ) = አዘለ ኀየለ (ቀደ) = በረታ ፣አሸነፈ፣ ደፈረ፣በዛ፣ ።።።።።።።።። በረከተ፣ ቀማ፣ አደነቀ ኄለ/ኀይለ/ኀየለ (ቀተ,ቀደ) = መነጨ፣ሰበሰበ ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።እልል እልል አለ ።።።።።።።።። (ኄላ= ምንጭ) ሀጉለ (ቀተ)= ጠፋ ፣ አጣ፣( ሀጉል=ጥፋት) ሐፈለ (ቀተ) = ቁንጥረ ቁንጥር አለ የስካር መሐለ /ምሕለ (ቀተ) = ማለ፣ጠራ መለለ (ቀተ) = ላገ ጠረበ አለሰለሰ የእንጨት መምኤለ /መምዐለ (ተን) = ወነጀለ፣ መሰለ (ቀተ) = መሰለ መሰለ (ቀደ) = ጣዖት ሸራ ፣ተናገረ ፣አወጋ፣ ።።።።።።።።። ተረተ፣ ( ምስል=ጣዖት) መበለ (ቀደ) = ብልጭ አለ ፣በረታ፣ ታጀረ፣ ።።።።።።።።።።ሰለጠነ፣ደፈረ፣ገዛ መዐለ (ቀተ) = ወነጀለ መከለ (ቀደ) = ቆረጠ የእንጨት( አሜከላ =እሾህ) ሞጽበለ (ጦመ) =ሞረደ፣(ሞጽበል=ሞረድ) ሰሐለ (ቀተ) = ሳለ የብረት ሳሕለለ (ማህ) = ደረቀ ሰመለ(ቀደ) = አለዘበ (የእንጨት የጠባይ) ሰሰለ (ቀደ)= ወገደ ሰቀለ (ቀተ) = ሰቀለ (ሰቅል=የወርቅ ሚዛን) ሰብለ(ቀተ) = ዘረዘረ (ሰብል =እህል) ሰንሰለ (ተን) = አያያዘ፣ አቆራኘ ሰአለ (ቀተ) = ለመነ ፣ ፈጠረ፣አቆመ፣በገረ፣ ።።።።።።።።። መረጠ፣ ሰከለ (ቀተ) = አፈራ፣(ሰክል= ፍሬ) ሶለ,ሰወለ,(ቀተ,ቀደ) = ሸተ፣(ሰወል=እሸት) ሰደለ (ቀተ)= መዘነ (ሰድሉ= ሚዛን) ሰገለ(ቀተ) = ጠነቆለ ፣ አሟረተ፣አወቀ፣ ።።።።።።።።(መሰግል/ሰገል = ጠንቋይ) ሰፈለ (ቀተ)= መታ፣ ቀጠቀጠ፣የዱቄት የብረት ረመለ (ቀተ) = ጠነቆለ (ረምል/መርመሌ= አሸዋ) ሮለ/ረወለ(ቀተ/ቀደ)=በሳ፣ቀደደ(ረወል=ቀዳዳ ረገለ (ቀተ) = ቀዘፈ ቀለ/ቀለለ(ቀተ) = ቀለለ ፣ ተሻለ፣አረፈ፣ ።።።።። ።።።።።። አፋጠነ፣ ቈልቈሉ (ተን) = ዘቀዘቀ ፣ ደፋ፣ወረወረ፣ፈሰሰ፣ ቈስለ (ቀተ) = ቆሰለ ፣ አሳዘነ ቀበለ (ቀደ) = ሸኘ ቀብለ ( ቀተ) = ጎደለ፣አነሰ፣ከፈለ ቀተለ (በራሱ) = ገደለ፣ቆረጠ፣ወጋ፣አደከመ፣ ።።።።።።።።። አፈረሰ፣ረከሰ፣አደረቀ ፣አጠፋ ።።።።።።።።።። ከበበ፣ በተነ ቀፈለ(ቀተ/ቀደ) = ለቀጠ፣ሸለመ፣ ብህለ ( ክህ) = አለ በልበለ (ተን) = አረጀ አለቀ የልብስ ብቻ፣ በሰለ (ቀተ) = በሰለ በቈለ (ቀተ) = በቀለ ብዕለ ( ክህ) = ባለ ጸጋ ኾነ ከበረ፣አሰረ፣ፈጨ ።።።።።።።።። በለጠ፣አገባ፣በዛ፣ሰፋ ቤዐለ/ ቤዖለ(ሴሰ) = ወደደ፣ከበረ በአለ(ቀተ)/ቤአለ( ሴሰ) = እንቢ አለ ቤወለ ( ሴሰ) = ወደደ (ቤወል=ወዳጅ) በጠለ (ቀተ) = ጠፋ፣አስታጎለ በጸለ(ቀተ,ቀደ) = ቦጨቀ፣በላ፣ጋጠ፣መሸለቀ ትሕለ (ክህ) = ቀላወጠ ( ተሐሊ =ቀላዋጭ) ተለዐለ /ተልዕለ(ክህ/ተላዐለ = ከፍ ከፍ አለ ።።።።።።።።( መልዕል = መውጫ) ተማሕለለ (ማህ) = ምሕላ ያዘ ተመዝጎለ (ተን) = ተከራከረ ተሥህለ(ክህ)/ተሠሀለ(ቀተ) = ይቅር አለ፣ ።።።።።።።።።።።።።።( ሣህል = ይቅርታ,ምሥሃል=የታቦት ልብስ) ተሰአለ (ቀተ) ተስእለ(ክህ) = ተጠያየቀ፣ጠየቀ ።።።።።።።።።።።።።።። (ተስእሎት = ጥያቄ) ተሰነአለ /ተሰንአለ ( ተን) = ተስማማ ተቀበለ (ቀደ) = ተቀበለ፣ሰማ፣አመነ፣ይቅር አለ ተቀጸለ (ቀደ) = ተቀዳጀ።( ቀፈላ = ሻሽ) ተበቀለ (ቀደ) = ቂም ያዘ ፣ገደለ፣ፈረደ ።።።።።።።።። በቅል = ቂም ተንበለ (ርእስ) = ለመነ ተአንተለ(ተን) = ቸል ቸል አለ ተዐገለ (ቀደ) = ቀማ ተከለ (ቀተ) = ተከለ ፣ወሰነ፣ደነገገ ፣ፈንታ ሰጠ ።።።።።። አጣደፈ፣ አዳፋ ፣ፈጠረ፣ ተከወለ(ቀደ)/ተኬወለ(ሴሰ) = ወደኋላ አለ፣ ተወከለ (ቀደ) =ታመነ ተድሕለ (ክህ) = ኰበለለ ተደንገለ (ተን) = ተጠበቀ ድንግል ሆነ የድንግልና ብቻ ተዳወለ (ቀተ) = ተዳካ ፣ተዋሰነ፣(ደወል= ወሰን ድንበር ተጋደለ (ቀተ) = ተጋደለ ተፋወለ (ቀተ) = አሟረተ ንኅለ (ክህ) = ፈረሰ ነቀለ (ቀተ) = ነቀለ ነዐለ (ቀተ) = ተጫማ ነደለ (ቀተ) = በሳ ፣ነደለ ነጸለ (ቀተ) = ለየ ፣ነጠለ፣ወለቀ ከፊሉ ይቀጥላል👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram