cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ፍኖተ ቅዱሳን አበው

ሽፍታው መስቀል ላይ እያለ በአንድ ቃል ጸደቀ፤ ከሐዋርያት አንዱ ሆኖ የነበረው ይሁዳ ያን ሁሉ ድካሙን በአንዲት ምሽት አጥቶ ከመንግሥተ ሰማይ ወደ ሲኦል ወረደ፡፡ ስለዚህ ማንም ሰው ስለ ራሱ መልካም ስራ አይመካ፡፡ በራሳቸው የሚታመኑ ሁሉ ይወድቃሉና:: /አባ ዘንትያስ/.

Show more
Advertising posts
415
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ደብዳቤ.docx1.37 KB
ለሥልጣነ ክህነቱ የማይገባ' ካህን ብትመለከት፥ [በደፈናው] ክህነትን አትንቀፍ፡፡ ደገኛ የኾነውን የክህነት ሥልጣን ይዞ ያልተገባ ሥራን ሲሠራ በማየቱ ምክንያት፥ ከዚህ ተነሥቶ ሥልጣነ ክህነትን የሚነቅፍ አንድ ሰውስ እንኳን አይኑር፡፡ የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ይሁዳ እንዲህ በማድረጉ ግን ሐዋርያነት የሚነቀፍ ስለ ኾነ አይደለም፤ የይሁዳ የገዛ ነጻ ፈቃድ ችግር ነው እንጂ፡፡ የሚተቸውም ክህነቱ አይደለም፤ ጠማማው ነጻ ፈቃዱ ነው እንጂ፡፡ ስለዚህ አንተም ክህነትን አትንቀፍ፤ ክህነቱን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ካህኑን እንጂ፡፡ ... ሐኪም ሳይኾኑ ሐኪም ነን ያሉት ስንት ናቸው? በዚሁ ምክንያት በመድኃኒት ፈንታ መርዝ የሰጡትስ ስንት ናቸው? እየነቀፍኩ ያለሁት ሙያውን አይደለም፤ ሙያውን በአግባቡ የማይተገብሩትን ነው እንጂ፡፡ መርከቦች እንዲሰምጡ ያደረጉ መርከበኞችስ ስንት ናቸው? ነገር ግን ችግሩ የባሕር ላይ ጉዞ አይደለም፤ ሙያውን እንደሚገባ የማይተገብሩት ሰዎች ችግር ነው እንጂ፡፡ ስለዚህ አንተም አንድ ክፉ ክርስቲያን ብትመለከት በደፈናው የክርስትና ትምህርትን ወይም ሥልጣነ ክህነትን አትንቀፍ፤ ደገኛውን ሥልጣን ላልተገባ ሥራ የሚያውለውን ነው እንጂ፡፡" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ትንቢተ ኢሳይያስን በተረጎመበት ፬ኛ ድርሳን ላይ ከተናገረው የተወሰደ)
Show all...
ትሕትና በትክክል ትሑት የኾነ ሰው ማን እንደ ኾነ ማወቅ ትወድዳለህን? በእውነት ያለ ሐሰት ትሑት የነበረውን ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስን ተመልከት፡፡ መምህረ ዓለም፣ መንፈሳዊ አንደበተ ርቱዕ፣ ንዋይ ኅሩይ፣ ወጀብ የሌለበት ወደብ፣ የማይናወጽ ግንብ፣ በአካለ ሥጋ ትንሽ ሲኾን አክናፍ እንደ ተሰጡት ኾኖ ምድርን ኹሉ ያካለለውን ጳውሎስን ተመልከት፡፡ ያልተማረው ግን ደግሞ የተራቀቀውን፣ ድኻ ግን ደግሞ ባለጠጋ የኾነውን ይህን ቅዱስ ሰው ተመልከት፡፡ እልፍ ጊዜ መከራዎችን የተቀበለው፣ አእላፋት ጊዜ ዲያብሎስን ድል የነሣው፣ “ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋው ከንቱ አልነበረም፤ ከኹላቸው ይልቅ ግን ደከምሁ” ብሎ የተናገረው ተወዳጅ ጳውሎስን በእውነት ያለ ሐሰት ትሑት ነው ብዬ እጠራዋለሁ (1ኛ ቆሮ.15፡10)፡፡ ብዙ ጊዜ መታሰርን፣ ብዙ ጊዜ መገረፍን፣ ብዙ ጊዜ በድንጋይ መወገርን፣ [ከበረኻ አራዊት ጋር መጋደልን፣ በባሕር ውስጥ ለሦስት ቀናት ሲዋኝ ውሎ ሲዋኝ ማደርን፣ ቀንና ሌሊት ብዙ ጦምን፣ በብርድና በራቁትነት መኾንን] የታገሠ የተቀበለ፣ በመልእክታቱ ዓለምን በወንጌል መረብነት ያጠመደ፣ ከሰማያት በመጣ ሰማያዊ ቃል የተጠራው እርሱ ራሱን ዝቅ አድርጎ፡- “እኔ ከሐዋርያት ኹሉ የማንስ ነኝ” ያለውን ብፁዕ ጳውሎስ አማን በአማን ትሑት ነው ብዬ እጠራዋለሁ (2ኛ ቆሮ.11፡23-27)፡፡ እንግዲህ የቅዱስ ጳውሎስን የትሕትናው ታላቅነት ታያለህን? ራሱን ዝቅ አድርጎ ታናሽ ነኝ ሲል ትመለከታለህን? “እኔ” አለ ቅዱስ ጳውሎስ፥ “ከሐዋርያት ኹሉ የማንስ፤ ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ የማይገባኝ ነኝ፡፡” በትክክል ትሕትና ማለት ይህ ነው - በኹሉም ረገድ ራስን ዝቅ ማድረግ! ራስን እንደ ታናሽ መቊጠር! እነዚህን ኃይላተ ቃላት የተናገራቸው ማን እንደ ኾነ በነቂሐ ልቡና በሰቂለ ሕሊና ኾነህ አድምጥ! የሰማይ ሰው የምድር መልአክ የሚኾን ጳውሎስ፣ የአብያተ ክርስቲያናት ዓምድ የሚኾን ጳውሎስ ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስን እጅግ አብልጬ የምወደውም ለዚህ ነው፡፡ ምግባር ትሩፋት ሥጋ ለብሳ ሥግው ኾና ተውባ ተሞሻሽራ የማያት በእርሱ በብፁዕ ጳውሎስ ዘንድ ነውና፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ፊት በዓይነ ሕሊናዬ ተቀርፆ የሚሰጠኝን ተድላ ደስታ ያህል የብርሃን ጮራዋን የምትለግሰው ፀሐይ ለዓይኖቼ ደስታን አትሰጠኝም፡፡ ምክንያቱም ይህቺ ፀሐይ የሥጋ ዓይኖቼ በብርሃን እንዲያዩ ታደርጋቸዋለች፤ ንዑድ ክቡር የሚኾን ጳውሎስ ግን ዓይነ ልቡናዬ አክናፍ ኑሮት ወደ ሰማየ ሰማያት እንድወጣ ያደርግልኛል፡፡ ነፍስን ከፀሕይ ይልቅ ጽድልት፣ ከጨረቃም ይልቅ ልዕልት እንድትኾን ያደርጋል፡፡ የምግባር የትሩፋት ኃይሏ ሥልጣኗ ይህን ያህል ነውና - ሰውን መልአክ ታደርገዋለች ፡፡ ነፍስ አክናፍ አውጥታ ወደ ሰማየ ሰማያት እንድትበር ታደርጋለች፡፡ ተወዳጅ ጳውሎስም የሚያስተምረን ይህንን ነው - ምግባርን ! ስለዚህ ነቅተን ተግተን በምግባሩ አብነት እናደርገው፤ እርሱን እንምሰል፡፡ (ከገብረ እግዚአብሔር ኪደ "#ንስሓና_ምጽዋት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳስተማረው "
Show all...
ሕንጸተ ቤተ ክርስቲያን እንኳን አደረሰን! በኬልቄዶን አውራጃ በቂሣርያ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ያለ እንጨት፣ ያለ ጭቃና ያለ ውኃ በሰኔ ፳ ቀን ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሦስት ድንጋዮች ቤተ ክርስቲያን ያነጸበት ዕለት የከበረ በዓል ነው፡፡ ይህም የሆነው ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ገብተው በክርስቶስ ስም አሳምነው ብዙ አሕዛብን ካጠመቁ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩላቸው ፈልገው በተነሡበት ጊዜ ነበር፡፡ ቤተ ክርስቲያኗንም ለመሥራትም ለርእሰ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ላኩበት፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ በርናባስ ጋር በኢየሩሳሌም ተገናኙ፤ ቅዱስ ዮሐንስም ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር አብሮ መጥቶ ነበር፡፡ በዚያም በአንድነት ሱባዔ ይዘው በለመኑት ጊዜ ጌታችን የሞቱትን አስነሥቶ፣ ያሉትንም ጠርቶና ቅዱሳን ሐዋርያትን በፊልጵስዩስ ሀገር ሰብስቦ ‹‹በእናቴ በድንግል ማርያም ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚሠራውን የአብያተክርስቲያናት ሥራ ላሳያችሁ፤ ሥርዓቱንም ላስተምራችሁ ሰብስቢያችኋለሁ›› ብሎ ወደ ምሥራቅ ይዟቸው ወጣ፡፡ (መጽሐፈ ሥንክሳር ሰኔ ፳ ቀን) በዚያ ሥፍራ የነበሩትን ሦስት ድንጋዮችንም የተራራቁትን አቀራርቦ፣ ጥቃቅኑን ታላላቅ አድርጎ ቁመቱን በ፳፬፣ ወርዱን በ፲፪ ክንድ ለክቶ ለቅዱሳን ሐዋርያት ሰጣቸው፡፡ ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ድንጋዩ በእጃቸው ላይ እየተሳለ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ሠርተው ፈጽመውታል፡፡ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ የተሠራውም ጌታችን በዐረገ በ፲፱ኛው፣ እመቤታችን በዐረገች በ፬ኛው ዓመት ሰኔ ፳ ቀን ሲሆን በማግሥቱ በ፳፩ኛው ቀን ኅብስት ሰማያዊ፣ ጽዋዕ ሰማያዊ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ወረደ፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችን ጋር ከሰማየ ሰማያት መጥቶ እመቤታችንን ታቦት፣ ሐዋርያትን ልዑካን አድርጎ፣ እርሱ ሠራዒ ካህን ሆኖ ቀድሶ አቆረባቸው፡፡ ከዚያም በኋላ ‹‹እምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ፤ ከዛሬ ጀምሮ እናንተም እንደዚህ አድርጉ›› ብሎ አዟቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ቁመት የ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ አምሳል ነው፤ ወርዱ ደግሞ የ፲፪ቱ ሐዋርያት ምሳሌ ነው፡፡ አንድም ሦስቱ ድንጋዮች የሥላሴ አምሳል ምሳሌ ናቸው፤ ከታች አቀማመጣቸው ሦስት፣ ከላይ ሕንጻቸው አንድ መሆኑ የሥላሴን ሦስትነትና አንድነት ያስረዳል፡፡ የሠሩትም ሦስት ክፍልም የመጀመሪያው ክፍል የታቦተ አዳም፣ ሁለተኛው የታቦተ ሙሴ፣ ሦስተኛው የታቦተ ኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነው፡፡ አንድም የሦስቱ ዓለማት ማለትም የጽርሐ አርያም፣ የኢዮር፣ የጠፈር ምሳሌ ነው፡፡ አንድም አንደኛው የኤረር፣ ሁለተኛው የራማ፣ ሦስተኛው የኢዮር አምሳል ነው፡፡ በኤረር፡- መላእክት፣ መኳንንት፣ ሊቃናት፤ በራማ፡- ሥልጣናት፣ መናብርት፣ አርባብ፤ በኢዮር፡- ኃይላት፣ ኪሩቤል፣ ሱራፌል ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ዘጠኙ ነገደ መላእክት የዘጠኙ መዓርጋተ ቤተ ክርስቲያን (መዓርጋተ ክህነት) አምሳል ሲሆኑ ይኸውም መላእክት የመዘምራን፣ የመኳንንት የአናጕንስጢሳውያን፣ ሊቃናት የንፍቀ ዲያቆናት፣ ሥልጣናት የዲያቆናት፣ መናብርት የቀሳውስት፣ አርባብ፣ የቆሞሳት፣ ኃይላት፣ የኤጲስ ቆጶሳት፣ የሱራፌል፣ የጳጳሳት፣ የኪሩቤል እንዲሁም የሊቃነ ጳጳሳት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ይህም በምድር የሚኖሩ ደቂቀ አዳም ከቅዱሳን በቀር ወደ ሰማይ መውጣት እንደማይቻላቸውና ከመዘምራን እስከ ጳጳሳት ድረስ ያሉ ካህናትም ከእነርሱ በላይ ያሉትን መዓርግ መሥራት እንደማይቻላቸው ያስረዳል፡፡ እንደዚሁም መላእክት ወደ ምድር መውረድ እንደሚቻላቸውና ሊቃነ ጳጳሳትም ከእነርሱ በታች ያሉ ካህናትን ተልእኮ መፈጸም እንደሚቻላቸው ያስረዳል፡፡ በጽርሐ አርያም መንበረ ብርሃን፣ ታቦተ ብርሃን፣ መንጦላዕተ ብርሃን እንደዚሁም ፬ ፀወርተ መንበር፣ ፳፬ አጠንተ መንበር (መንበሩን የሚያጥኑ) መላእክት አሉ፡፡ ጽርሐ አርያም የመቅደስ፣ መንበረ ብርሃን የመንበር፣ መንጦላዕተ ብርሃን የቤተ መቅደሱ መጋረጃ፣ ፬ቱ ፀወርተ መንበር የ፬ቱ ሊቃነ ጳጳሳት ወይም የመንበሩ እግሮች፣ ፳፬ቱ አጠንተ መንበር የጳጳሳት (የኤጲስ ቆጶሳት) ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ምንጭ፡-መጽሐፈ ስንክሳር፣ ሰኔ ፳ ቀን እንዲሁም መጽሐፈ ታሪክ ወግስ፣ገጽ ፫፻፵፱-፫፻፶፩ ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
Show all...
Show all...
ሃይማኖት እና ባህል:- ክፍል አንድ

በደጅ መወለድሽ - በገዛ እጅሽ (Abayneh Kassie) አንቺን የሚሸከም ቤት በዚህ ዓለም አልተገኘምና ልደትሽ በውጭ ኾነ። ቅዱስ ያዕቆብ የሰማይ ደጅ እንዳለሽ ትዝ ይለናል። ድሮስ ሰማይን የሚችል ምን ቤት በዚህ ዓለም ይኖራል? ከምድር እስከ ሰማይ የተዘረጋሽ መሰላል ይልሻል። እናስ አንቺን ምን ዓይነት ቤት ያስተናግድሻል? ደግሞ ስትመጪ ብቻሽን አይደለም። የራቀንን እግዚአብሔርን ከአሽከሮቹ መላእክት ጋር ይዘሽ እንጅ። እኮ ለአንችም ቤት አላገኘን ስንኳን ለምሉዕ በኩለሄው። እስከዛሬ የሚመጥንሽን ቤት ልንሠራ አልተቻለንም። ያ ወንጌላዊ ስፍራ አልተገኘላቸውም ያለን ለዚህ ነበር ለካ። አንች ግን ቅዱስ ዳዊት እንደተናገረው ሰማይና ምድር ለማይችሉት ቤቱ ኾንሽ። ለወለዱሽ ለተራሮች መልሰሽ እናት ኾንሻቸው። ያ ዶኪማስ እንኳን ልጅሽ ተጨምሮ ለአንችም ቤቱ እንዳይበቃ ዐውቆ በአዳራሽ በድንኳን ቢያስቀምጥሽ ከመንበርሽ ሳለሽ ጓዳውን ዐየሽበት። ቤቱን ከባዶነት ወደ መትረፍረፍ ለወጥሽው። አክስትሽ ቅድስት ኤልሳቤጥም ቤቷ እንዳይበቃሽ ዐውቃ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይኾናል? ብላ ተርበተበተች። አንቺ ግን ገና በደጅ ሳለሽ በቤት በነበረችው በአክስትሽ ማኅፀን ላለው ጽንስ ታየሽ። በረድኤትሽ ቀርበሽዋልና ጠብ እርግፍ ብሎ ሰገደልሽ። የኾነው ሁሉ የተገለጠላት ቅድስት ኤልሳቤጥ እኛ ሁሉ እንሰማው ዘንድ በታላቅ ድምፅ ዐወጀችሽ። ከቤቷ በላይ ነሽና። ሰማይ ነሽ ብለን ስንደነቅ ምድር ኾነሽ ያለ ዘር ታበቅያለሽ። ምድር ነሽ ስንል ሰማይ ቤት ደርሰሽ ዙፋን ትዘረጊያለሽ። በሰማይ አንድ ልጅ ብቻ ቢኖር የእርሱም እናቱ ኾንሽ። አብ አንድ ዘር ቢኖረው ሙሽራው አደረገሽ። ያለ እናት ቢወልደው ያለአባት ወለድሺው። ታዲያ ምን ዓይነት ቤት ይችልሽ ኖሯል? እመቤታችን ሆይ በደጅ የተወለድሽው በገዛ እጅሽ ከአቅማችን ስለገዘፍሽ ነው። እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለአንቺ ማደሪያ የሚበቃ ቤትም ሰውነትም አሁንም ገና አልሠራንም። ግን የጎደለባት ጓዳችንን ባለሽበት ማየትሽ አይቀርምና ውኃ ውኃ የሚለውን ኑሯችንን መዓዛ ወይን አርከፍክፊበት።
Show all...
#እመቤቴ_ሆይ፤ ባትወለጂ እግዚአብሔርን በሥጋ ተገልጦ እናየው ነበርን? በፍጹም። አንቺ ባትወለጂ ፍቅር፣ ምሕረት እና ፍጹም መልካምነት በእውነት ሥጋን ነሥተው በክርስቶስ እናይ ነበርን? በፍጹም። አንቺ ባትወለጂ የእግዚአብሔርን ጸጋ እና ንጽሕና በሰውነት ተገልጦ እናይ ነበርን? በፍጹም። ይኸውም ያንቺ የቅድስና ሕይወት ነው። ከሊቃውንት አንዱ የአንቺ አንዲቷ ትንፋሽ ከቅዱሳን ሁሉ ገድል፣ ምስጋና እና ምልጃ ሁሉ የከበረች እንደሆነች ተናገረ። ይህ ሁሉ ከሰው ኅሊና ስለሆነው ንጽሕናሽ ነው። በዘወትር ቋንቋችን አንቺን "ንጽሕት" ብቻ ማለት ንጽሕናን ማጉደፍ ይሆናል እኮን። ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ያንቺ ንጽሕና እና ቅድስና በቃል ከመነገር ይልቅ፤ በዝምታ የልብ ለኆሳስ ቢመሰገን የተገባ ነው። አንቺ ባትወለጂ የእግዚአብሔር ትእዛዝ በምልዓት ሲፈጸም፤ ሕጉ ሲደረግ ምን እንደሚመስል በምን እናውቅ ነበር? አንቺ ባትወለጂ የክህነት ንጽሕና በምን ይጠበቅ ነበር? አንቺ ባትወለጂ የንስሐ መንገዱን ማን ያመለክተን ነበር? አንቺ ባትወለጂ ያንቺ መታዘዝ፡ የእኛን ዐመጸኛነት እንዴት ይገስፀዋል? አንቺ ባትወለጂ ያንቺ ትሕትና፡ የኔን ትዕቢት ይሰብረው ዘንድ እንዴት ይቻለዋል? ስለ አምላካዊው ኀይሉ፤ ጠላት ሰይጣን ለልጅሽ ይገዛል። የልጅሽ የክርስቶስን ስም ሲሰማ ይንቀጠቀጣል። አንቺ ግን በትሕትናሽ ሰይጣንን አራድሽው። እርሱ መንፈስ ሲሆን "ሥጋ ለባሽ" ብሎ በሚንቃት "በአንዲት ሴት" መሸነፉ ሁልጊዜም ግራ ይገባዋል። ስምሽን የሚጠሩ ሰዎች ፊትም መቆም አይቻለውም። ስምሽን ሲጠሩ ኀይላቸውን ትተው ኀይልሽን ይይዛሉና። ይኸውም እግዚአብሔር ነው። ስምሽን ሲጠሩ ትዕቢታቸውን ጥለው በትሕትናሽ ይጋረዳሉና። ስምሽን ሲጠሩ ጥርጣሬያቸውን በሃይማኖትሽ ያሸንፋሉና። በንጽሕና ቀሚስሽ ስለ እድፈታቸው ከሚከሳቸው ይጋረዳሉና። ሰይጣን ከእነርሱ ዘንድ አይቀርብም። እመቤቴ ሆይ አንቺ ባትወለጂ ከመልካሙ ሁሉ በአፍአ በቀረን ነበር እኮን። አሁንም "መጥተን" ሳለን የቀረን አታድርጊን። እኛ ራሳችንን ብንተው፤ አንቺ አትተዪን። እኛ ብንርቅ፡ አንቺ አትራቂን። እኛ ብንዘነጋ፡ አንቺ አትዘንጊን። መሐርነ፡ ወተሣሃልነ!
Show all...
#እመቤቴ_ሆይ፤ ባትወለጂ እግዚአብሔርን በሥጋ ተገልጦ እናየው ነበርን? በፍጹም። አንቺ ባትወለጂ ፍቅር፣ ምሕረት እና ፍጹም መልካምነት በእውነት ሥጋን ነሥተው በክርስቶስ እናይ ነበርን? በፍጹም። አንቺ ባትወለጂ የእግዚአብሔርን ጸጋ እና ንጽሕና በሰውነት ተገልጦ እናይ ነበርን? በፍጹም። ይኸውም ያንቺ የቅድስና ሕይወት ነው። ከሊቃውንት አንዱ የአንቺ አንዲቷ ትንፋሽ ከቅዱሳን ሁሉ ገድል፣ ምስጋና እና ምልጃ ሁሉ የከበረች እንደሆነች ተናገረ። ይህ ሁሉ ከሰው ኅሊና ስለሆነው ንጽሕናሽ ነው። በዘወትር ቋንቋችን አንቺን "ንጽሕት" ብቻ ማለት ንጽሕናን ማጉደፍ ይሆናል እኮን። ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ያንቺ ንጽሕና እና ቅድስና በቃል ከመነገር ይልቅ፤ በዝምታ የልብ ለኆሳስ ቢመሰገን የተገባ ነው። አንቺ ባትወለጂ የእግዚአብሔር ትእዛዝ በምልዓት ሲፈጸም፤ ሕጉ ሲደረግ ምን እንደሚመስል በምን እናውቅ ነበር? አንቺ ባትወለጂ የክህነት ንጽሕና በምን ይጠበቅ ነበር? አንቺ ባትወለጂ የንስሐ መንገዱን ማን ያመለክተን ነበር? አንቺ ባትወለጂ ያንቺ መታዘዝ፡ የእኛን ዐመጸኛነት እንዴት ይገስፀዋል? አንቺ ባትወለጂ ያንቺ ትሕትና፡ የኔን ትዕቢት ይሰብረው ዘንድ እንዴት ይቻለዋል? ስለ አምላካዊው ኀይሉ፤ ጠላት ሰይጣን ለልጅሽ ይገዛል። የልጅሽ የክርስቶስን ስም ሲሰማ ይንቀጠቀጣል። አንቺ ግን በትሕትናሽ ሰይጣንን አራድሽው። እርሱ መንፈስ ሲሆን "ሥጋ ለባሽ" ብሎ በሚንቃት "በአንዲት ሴት" መሸነፉ ሁልጊዜም ግራ ይገባዋል። ስምሽን የሚጠሩ ሰዎች ፊትም መቆም አይቻለውም። ስምሽን ሲጠሩ ኀይላቸውን ትተው ኀይልሽን ይይዛሉና። ይኸውም እግዚአብሔር ነው። ስምሽን ሲጠሩ ትዕቢታቸውን ጥለው በትሕትናሽ ይጋረዳሉና። ስምሽን ሲጠሩ ጥርጣሬያቸውን በሃይማኖትሽ ያሸንፋሉና። በንጽሕና ቀሚስሽ ስለ እድፈታቸው ከሚከሳቸው ይጋረዳሉና። ሰይጣን ከእነርሱ ዘንድ አይቀርብም። እመቤቴ ሆይ አንቺ ባትወለጂ ከመልካሙ ሁሉ በአፍአ በቀረን ነበር እኮን። አሁንም "መጥተን" ሳለን የቀረን አታድርጊን። እኛ ራሳችንን ብንተው፤ አንቺ አትተዪን። እኛ ብንርቅ፡ አንቺ አትራቂን። እኛ ብንዘነጋ፡ አንቺ አትዘንጊን። መሐርነ፡ ወተሣሃልነ!
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
“ይህ በዓል በሐዲስና በብሉይ ኪዳን መካከል መገኛ ሆነ፡፡ ምስሌዎቹ በእዉነታ፣ አሮጌው በአዲስ ቃል ኪዳን ተተኩ፡፡ ፍጥረት ሁሉ በደስታ ይዘምራል የዚህን ቀንም ደስታ ይካፈላል፡፡ ይህ መቅደሱን የሰራበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ዕለት ትልቅ ሕንፃ የታነጸበትና ፍጡር የፈጣሪ ማደሪያ ለመሆን የተዘጋጀበት ዕለት ነው፡፡” የቀርጤሱ ቅዱስ እንድርያስ እንኳን ለባሕርያችን መመኪያ ለንጽሕናችን መሠረት አምላካችን አማኑኤልን ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
"እንደ ተናገረ ተነሥቷል።" ማቴ. ፳፰፥፮ እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። "ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን አሰሮ ለሰይጣን አግዐዞ ለአዳም ሰላም እምይዕዜሰ ኮነ ፍሥሐ ወሠላም፤ ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ። ዲያብሎስን አሰረው፤ አዳምን ነጻ አወጣው። ሰላም! ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ኾነ።” መልካም በዓለ ትንሣኤ
Show all...
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.