ቀለም ሚዲያ/Kelem Media
Open in Telegram
ለሚዛናዊና ወቅታዊ መረጃዎች ቀለም ሚዲያን ይቀላቀሉ!
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
926
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
Update በክብር በተሸኙት አቶ ደመቀ መኮንን ቦታ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ ተመርጠዋል።
ሐብት ካስመዘገቡ 41 ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት ውስጥ አንዱ ብቻ ነው ትክክለኛ ተባለ‼️
ሐብት ካስመዘገቡ 41 ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች መካከል ትክክለኛ ሆኖ የተገኘው አንዱ ብቻ መሆኑን የፌደራል የሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ።
ባለፉት ስድስት ወራት 41 ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ያስመዘገቡትን ሐብት እውነተኝነት ለማረጋገጥ በተደረገው ማጣራት ትክክለኛ ሆኖ የተገኘው አንድ ብቻ መሆኑን በኮሚሽኑ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ገዛኽኝ ጋሻው መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ ዘግቧል።
አዲስ ማለዳ የተመለከተችው ዘገባ እንዳመላከተው ከ41ዱ 24ቱ ከፍተኛ ልዩነት እንዲሁም 16 የሚሆኑት መካከለኛ ልዩነት የተገኘባቸው ሲሆን ትክክለኛ ሆኖ የተገኘው አንድ ብቻ ነው።
ጉዳዩም ለፍትህ አካላት ደርሶ የማጣራት ስራ እየተከናወነ ይገኛል የተባለ ሲሆን በቀጣይ ስድስት ወራት የ55 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የተመዘገበ ሐብት የማረጋገጥ ስራ እንደሚከናወን ተገልጿል።
ቻርጅ ሳይደረግ ለ50 ዓመታት የሚያገለግለው ባትሪ
የቻይና ኩባንያ ቤታቮልት “ቢቪ100” የተሰኘ አቶሚክ ባትሪን ያስተዋቀ ሲሆን፤ ባትሪው ለ50 አመታት ያለምንም ሃይል መሞላት (ቻርጅ መደረግ) አገልግሎት ትሰጣለች ተብሏል።
በተደጋጋሚ ሃይል መሞላት (ቻርጅ መደረግ) የማትፈልገው አነስተኛ ባትሪ ለስማርት ስልኮችም ሆነ ለድሮኖች ሁነኛ የሃይል ምንጭ ትሆናለች ተብሏል “አቶሚክ” የሚለው ስያሜ አስፈሪ ቢመስልም “ቢቪ100” ጨረር የማይለቅና ዘመኑን የዋጀ ስለመሆኑ አምራቹ ይገልጻል። ባትሪው በተለይ ለአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሳሪያዎች፣ ለአነስተኛ ድሮኖች እና ሮቦቶች ሁነኛ የሃይል ምንጭ እንደሚሆንም ነው ያስታወቀው።
ዋጋው ምን ያህል እንዳልሆነ ያልተጠቀሰው የቤታቮልት አቶሚክ ባትሪ ስማርት ስልኮችን ሃይል መሙላትን ያስቀራልም ተብሏል።
ኩባንያው በድረገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ” “አቶሚክ ባትሪያችን ስማርት ስልኮችን ድጋሚ ሃይል ሳይሞሉ፤ ድሮኖችም ሃይል ለመሙላት ማረፍ ሳይጠበቅባቸው ለ50 አመታት አስተማማኝ ሃይል ያቀርብላቸዋል” ብሏል።
የቻይናው ኩባንያ እስከ 230 አመት ሊያገለግሉ የሚችሉ አቶሚክ ባትሪዎችን ለመስራት ምርምሩን መቀጠሉን መግለጹንም ኦዲቲ ሴንትራል አስነብቧል። ©️
የሰላም “አለመኖር እንቅልፍ እየነሳኝ ነው!” አባ ህፃን
ሰሞኑን “የኦሮሚያ ቅዱስ ሲኖዶስ” መቋቋሙን ይፋ ያደረጉ አባቶችን አስመልክቶ አባ ህፃን ባደረጉት ንግግር መሃል የሀይላኖት አባቶች፣ መንግስትና የሚመለከታቸው ሁሉ በፋኖና በመከላከያ መካከል ያለው ግጭት በሰላም እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡ ንግግራቸውን ከዚህ ቪዲዮው ይመልከቱ 👇👇👇
