cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

የክርስትና እውነቶች

📖መጽሐፍ ቅዱሳዊ📖 የሆኑ መንፈሳዊ ጽሑፎችን የሚያገኙበት ቻናል ነው❗ 📲Join/Subscribe📲 ብለው ይቀላቀሉና ቤተሰብ ይሁኑ!👥 ↪Share↩ በማድረግም "የክርስትና እውነቶችን" ለወዳጅዎ ያጋሩ!👇 https://t.me/Cchristiantruth

Show more
Advertising posts
1 001
Subscribers
+124 hours
+67 days
+930 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ክፍል ስምንት #መላዕክትም_እኛም_ብንሆን ገላ 1፡8-12 ዘማሪ ሀና ተክሌ ከወዳጆቿ ጋር በመሆን እንዲህ ታዜማለች። ካንተ በፊት የቆሰሉ ብዙ አሉ ለወንጌሉ እንደኔ እና እንዳተ በነፃነት ዘመን ያልተፈጠሩ ... ወንጌል ከአሁኑ በባሰ ዋጋ የሚያስከፍልበት ዘመን ነበር ።አሁንም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ ወንጌል ከፍተኛ ዋጋ ይከፈልለታል ይገባዋል !! ይህ የሚመጣው ለወንጌል ካለ እውነተኛ አቋምና ለወንጌል ካለ ትክክለኛ መረዳት ብሎም እርግጠኝነት ነው ። ደፋሩ ጰውሎስ ለእዚህ እውነት እንዴት በልበ ሙሉነት እንደሚናገር ተመልከቱ ‹‹ነገር ግን #እኛ_ብንሆን ወይም #ከሰማይ_መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን #ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።ወንድሞች ሆይ፥ በእኔ የተሰበከ ወንጌል እንደ ሰው እንዳይደለ አስታውቃችኋለሁ፤ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም።›› ጳውሎስ የማይደራደርበት እውነት በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኘውን የዘላለም ድነትን ነው ፡፡ ይሄን ለማስረዳት ከሰማይ ከምድርም የተለያዩ አካላትን ይጠቅሳል ፡፡ 🔸1ኛ የሰማይ መላዕክትና 🔸2ኛ የወንጌል አገላጋዮች ራሱንም ጨምሮ 🔸3ኛ ማንም ይህ ማለት ምን ማለት ነው ? 1ኛ የሰማይ መላዕክት ጳውሎስ የሰበከው ወንጌል እንደ ሰው ያለሆነ ወንጌል ነው፡፡ ‹‹ወንድሞች ሆይ፥ በእኔ የተሰበከ ወንጌል እንደ ሰው እንዳይደለ አስታውቃችኋለሁ›› 7ላ 1፡11 ይህ ማለት ሰማያዊና ክርስቶስ የገለጠለት ነው ፡፡ ስለዚህ ይህ በማንም አካለት ሊሻር የማይችል የከበረ እውነት ነው ማለት ነው ፡፡ ከሰማይ ቅዱሳን መላዕክት ወርደው ይሄ ወንጌል ስህተት ነው ቢሉ የተረገሙ ሊሆኑ ይችላሉ እንጂ ለእውነተኞች ሊሆኑ አይችሉም ፡፡ የእግዚአብሄር መላዕክት የሚሰሩትን የሚያውቁ ጥንቁቆች ናቸው ፡፡ በቅዱሳት መፅሀፍት በብሉያትም በአዲሳትም ይህ ተብረርቶ እናገኘዋለን ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን መለዕክት ከሰማይ ኦርደር የሚቀበሉ ታማኞች ናቸው ፡፡ ነገር ግን ይህንን የተከበረ ስራቸውን ትተው ጳውሎስ ከሰበከው ውጪ ሌላ ወንጌል ቢያመጡ በፍፁም እውነተኞች ሊሆኑ አይችሉም ፡፡ የትላንት እውነተኛነታቸው ለዛሬ ልዩ መልዕክት ለማምጣታቸው ዋስትና ሊሆን አይችልም ፡፡ ይልቅ የተረገሙ ሊሆኑ እንደሚችሉ ጳውሎስ ይጠቁማል ወይም የእርግማን ቃል ይናገራል ፡፡ ይህ የሚነግረን ነገር የጳውሎስን ለወንጌል ያለው ቆራጥ አቋምና እርግጠኝነት ነው ፡፡ እርግጠኛ ያደረገው ነገር በክርስቶስ የተሰጠው ከክርስቶስ የተቀበለው መሆኑ ነው ፡፡ ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም።›› ገላ 1፡12 በእዚህ ውስጥ የምንማራቸው ቁም ነገሮች ብዙ ናቸው ፡፡ ጳውሎስ ለሰማው እውነተኛ ወንጌል ምን ያህል ታማኝ እንደሆነ እና አስገራሚ ድፍረቱን ነው ፡፡ በክርስቶስ ለተገለጠለት ወንጌል በምንም የማይደረደር መሆኑን ነው የምናየው ፡፡ 🔸 እኛስ እንዴት አይነት ሰዎች እንሆን? ለእዚህ እውነተኛ 🔸ወንጌል ምን ያህል ዋጋ ለመክፈል ዝግጁ ነን? 🔸 የሰማይ መላዕክትን ሳይሆን አንድ ግለሰብን በወንጌል እውነት ለመሞገት ምን ያህል ታማኞች ነን ?ደፈሮች ነን? ብርቱዎች ነን ?የአቋም ሰዎች ነን?፡፡ ጳውሎስ ግን አስገራሚ ድፍረቱን ለሰማው ለክርስቶስ ወንጌል ታማኘረነቱን እናያለን ፡፡ አይ ጳውሎስ!! 2. እኛም ብንሆን ‹‹ ነገር ግን #እኛም ብንሆን ›› ገላ 1፡8 አ.መ.ት ጳውሎስ እኛም ብንሆን እያለ ነው ።ይህ አስገራሚው ነገር ነው ፡፡ እኛ ሲል ማንን እያለ ነው ካልን እርሱንና ከእርሱ ጋር ወንጌል የሚያገለግሉ ታማኝ አገልጋዮችን ነዋ !! የወንጌል እውነትነት የሰውን ማንነት መሰረት አያደርግም ሁሉ ለእዚህ እውነት ዝቅ ይላሉ እንጂ ወንጌል ለሰዎች ማንነት ዝቅ አይልም ፡፡ ጳውሎስ ራሱን ጨምሮ ነው የሚናገረው። ዛሬ ወንጌል ይህ ነው ብዬ ተናግሬ ነገ አቋም ብቀይር ዛሬ የተናገርኩት አይደለም ስህተት እኔ ነኝ አሁን ስህተት እያለ ነው ፡፡ ለምን ይህንን ወንጌል ጳውሎስ ከራሱ አፍልቆ የተናገረው ሳይሆን ከላይ ከክርስቶስ ከሰማይ ከመለኮት የሰማው ነው ፡፡ ክርስቶስ ደግሞ ሊሳሳት አይችልም ፡፡ ክርስቶስ ተሳስቼ ነው የመዳን መንገድን በጳውሎስ በኩል ያስታወኳችሁ አይልም ፡፡ የዛሬ የጳውሎስ እውነቱ ልክ ሲሆን ምናልባት የጳውሎስ የነገ ስህተቱ የዛሬውን እውነት ሳይነካ ስህተት ሆኖ ይቀጥላል እንጂ ጳውሎስ መጀመሪያ የሰበከው እውነት ነው ፡፡ ጳውሎስ እያለ ያለው ይህንን ነው ፡፡ ከእዚህ እውነት በኋላ የሐዋሪያት ሌላ አስተምህሮ ከመጀመሪያው የተለየ ቢያመጡ ስህተት ሊሆን ይችላል እንጂ የቀደመ ትምህርታቸው ስህተት ሊሆን አይችልም ፡፡ ክርስትና በተጋገጠ እውነት የመዳን ጉዳዩን የመሰረተ እንጂ ወደፊት የሚያረጋግጠው ያለቀ እውነት ማለትም ሌላ የመዳን መንገድ የለውም ፡፡ በእዚህ እውነት ወስጥ የምንረዳው ሌላ እውነት ደሞ ይህ ነው ፡፡ወንጌል በአገልጋዮች ማንነት ላይ አይመረኮዝም፡፡ ትላንት ዝነኛ የነበሩ አእማድ ሰዎች ዛሬ ሊስቱ ይችላሉ ፡፡ የትላንት ጉምቱነታቸው ትልቅ አገልጋይነታቸው የዛሬውን ስህተታቸውን አያፀድቅላቸውም ፡፡ ወንጌል ከዝነኛ ሰዎች በላይ እውነት ነው? ፡፡ በሃገራችን ትላንት እጅግ መልካም የነበሩ አገልጋዮች ዛሬ ስህተት ሆነዋል ፡፡ በቆሙበት አልጸኑምና ወድቀዋል ፡፡ ዛሬ እውነት የሆኑ ለነገ ያሰጋሉ ፡፡ በጳውሎስ የተሰበከው ወንጌል ግን በማንኛውም ጊዜ እውነት ነው ፡፡ 3. ማንም ቢሆን ‹‹ከተቀበላችሁት የተለየውን #ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።›› ገላ 1፡9 ጳወሎስ ምንም ክፍተት አይተውም ፡፡ ማንም የሚለው ቃል ከላይ የጠቀሳቸውን ጨምሮ የሚያካትትና መጠቅለያ መደምደሚያ ክፍተት መዝጊያ የሚሆን ቃል ነው ፡፡ ማንም ማለት በየትኛውም አቅጣጫ የሚመጣውን የስህተት ትምህርት ከወንጌል ተፃራሪ ሀሳብ የሚመክት ቃል ነው ፡፡ በእዚህ ውስጥ ጳውሎስ ለወንጌል ያለውን ቁርጠኝነት እና ከምንም ጋር ለፉክክር የማያቀርበው የከበረው እውነታው እንደሆነ ነው ምንረዳው ፡፡ ጳውሎስ ለምን እንዲህ አለ? ጳውሎስ በቀጣይ ባሉ ሶስት ቁጥሮች ውስጥ ማለትም በቁጥር 10-12 ባለው ክፍል ውስጥ ሊል የቻለበትም ምክንያት በአጭሩ ይናገራል ፡፡ ‹‹ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።ወንድሞች ሆይ፥ በእኔ የተሰበከ ወንጌል እንደ ሰው እንዳይደለ አስታውቃችኋለሁ፤ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም።›› 🔸1ኛ የክርስቶስ ባሪያ ስለሆንኩ ለሰው ደስታ አልሰብክም በሚል ነው 🔸2ኛ እንደ ሰው የሆነ ወንጌል አይደለም በእኔ የተሰበከው 🔸3ኛ ክስርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ ከሰው አልተማርኩትምና ነው ፡፡
Show all...
ጳውሎስ በእዚህ ወንጌል እርግጠኛ ሆኖ እንዲሰብክ ያደረው እውነታ ይህ ነው ፡፡ እኛስ ለእዚህ ወንጌል እርግጠኞች ሆነን በድፍረት መመስከር እንችላለን ? ከሁሉ ርዕሶች በላይ ርዕስ እናደርገዋለን? ልመርቃችሁ እውነተኛው ወንጌል አጥብቃችሁ የምትይዙበት ፀጋ ይጨመርላችሁ ። አሜን ይቀጥላል ... ✍️ Girum Difek
Show all...
ክፍል ሰባት ( በእርጋታ በደንብ አንብቡልኝ) #ከልዩ_ወንጌል_መለየት የምንውልበት ሰፈር ጠረናችንን ይወስናል ። በመልካም መአዛ ሰፈር የዋለ ሽታውም እንደዚያውም ነው። የገላትያ ሰዎች ከጳውሎስ ጋር በሚውሉ ሰአት ጠረናቸው የሚስብ የሚያውድ መአዛ ነበረው ። ሰው ያከብራሉ ። ለችግሩ ሰአት ለመቆም ቀኝ እጃቸውን ይሰጣሉ እጅግ የሚያሳሱ ምዕመናት ነበሩ ። ልዩ ነገር መቶ ልዩ ሳያረጋቸው በፊት !! ጳውሎስ ስ እንዲህ ሲል መስክሮላቸዋል ። "ሕመሜ ለእናንተ ፈተና ሆኖባችሁም እንኳ፣ አልሰለቻችሁኝም፤ ወይም አልተጸየፋችሁኝም፤ ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ፣ እንዲያውም እንደ ራሱ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ አድርጋችሁ ተቀበላችሁኝ። " ገላትያ 4:14 አሁን ግን እንደዛ አይደሉም ልዩ ወንጌል መጥቶ ብዙ ነገራቸውን ቀየረው የልዩ ወንጌል ችግሩ ይህ ነው መልካም የነበሩትን ሰዎች ድንገት ትቢተኛ ከእኛ በላይ ላሳር የሚሉ ያስብላቸዋል ትህትናቸውን ወስዶ ደረታቸውን በክፉ ያስነፋቸዋል ።ከክርስቶስ ለይቶ ከፀጋ ይጥላቸዋል። ጳውሎስ መልሶ እንዲህ ይላል "ለመሆኑ ያ ሁሉ ደስታችሁ የት ደረሰ? ቢቻላችሁ ዐይናችሁን ቢሆን እንኳ አውጥታችሁ የምትሰጡኝ እንደ ነበራችሁ እመሰክራለሁ። እውነቱን ስለ ነገርኋችሁ ጠላት ሆንሁባችሁን?" ገላትያ 4:15-16 ነበራችሁ መባል እንዴት ደስ የማይል ነገር ነው ። አገልጋይ ነበራችሁ ጥሩ ነበራችሁ ......ነበራችሁ ። ጳውሎስ ነበራችሁ እያላቸው ነው ።ከእዚህ እግዚአብሔር ይጠብቀን አሜን ። ልዩ ወንጌል መጀመሪያ ከአምላክ ጋር ያለውን ግንኙነት ያሻክራል ቀጥሎ የእለት ተእለት ህይወታችን ላይ ተፅዕኖ ያመጣል ። ጳውሎስ ልዩ ወንጌል የሚለው ምኑን ነው ? ይህን ከመመለሳችን በፊት #ወንጌል ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንመልስ ፡፡ ወንጌል የሚለው ቃል ከላቲን evangelium / ኢቫንጄሊየም, ይህም ራሱ ከጥንት የግሪክ ቃል εὐαγγέλιον / ኧውጄሊዮን = አስደሳች መልዕክት ከሚለው የተገኘ ቃል ነው። ወንጌል ለሰው ልጆች ሁሉ የሆነ መልካም የምሥራች ነው፡፡ የንስሐ፣ የመፍትሄ፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የተስፋ፣ የደኅንነት፣ የእርቅ፣ ከፍርድ የመዳን፣ የዘላለም ሕይወት፣ ትምህርት የሚገኝበት የምስራች ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር መንግስት አዋጅ የሆነውን ወንጌል ለመጀመሪያ ጊዜ እሱ ራሱ እንደሰበከ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል (ማ 4፡23 ማርቆ 1፡14-15 )፡፡ከእርሱ እግር የተተኩ ሐዋሪያት ስለ እርሱ እየሰበኩ እድሜቸውን አንጠፍጥፈው ተጠቅመው በክብር ለእርሱ ተሰውተው አልፈዋል ። ከእርሱ ለእርሱ ሆነዋል ። ወንጌል በአዲስ ኪዳን መፅሐፍ ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ሰራው ስራ እና ስለ ራሱ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ፡፡ ‹‹ሐዋርያ ሊሆን የተጠራ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ጳውሎስ በነቢያቱ አፍ በቅዱሳን መጻሕፍት አስቀድሞ ተስፋ ለሰጠው ለእግዚአብሔር ወንጌል ተለየ።ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።›› ሮሜ 1:1-4 የወንጌል ዋነኛው መልዕክት በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኝ የኃጢአት ሥርየት ነው። ወንጌል ሰዎች ከእግዚአብሔር ቁጣ እንዲተርፉ፤ኃጢአት የሚያስከፍለውን ዋጋ ለመክፈል ማለት ከሁሉ የከፋውን ሞትን ለመሻር ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ተወልዶ እንደ ሰው ሆኖ መሞቱን፣ መቀበሩን፣ ከሞት መነሣቱን ይህም በሞት ውስጥ የነበረውን በኃጢያት ምክንያት የተበላሸውን አለም እና የአለም ስርዐት ለማደስ እና የዘላለም ህይወት ለመስጠት በክርስቶስ የተሰራ ስራን የሚያሳይ ነው ገላ 1፡4 ፣ ሮሜ 3፡23-27 (ሐዋ13 ፡28 -30፣38 ። 1ቆሮ.15፡3-4። በተለይ ወንጌል የዘላለማዊ ሕይወት ዕጣዬ ምን ዓይነት ነው ለሚለው ጥያቄ ወንጌል ግልፅ የሆነ መልስ ይሰጣል። የወንጌል ዋና መልእክት 🔸የወንጌል አንኳር መልዕክት በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን የሚገኝ የኃጢአት ሥርየት ነው። የድኅነት ሥራ በክርስቶስ ተፈፅሟል የአዋጁ ዋና መልዕክት ነው (ሐዋ2፡38፣ 5፡31፣ 10፡43፣ 13፡38፣27 ፡18) 🔸የድኅነት ስራ በክርስቶስ ኢየሱስ ስለተከናወነ፣ ሰዎች በእርሱ እንዲያምኑ እና የዘላለምን ህይወት እንዲያገኙ የሚነገር የምስራች ነው። 🔸ሐዋርያው ጳውሎስ እንደተናገረው ወንጌል በመስቀል ላይ የተከናወነውን አስደናቂ የድኅነት ስራ የማወጅ ተግባር ነው ‹‹ወንድሞች ሆይ፥ የሰበክሁላችሁን ደግሞም የተቀበላችሁትን በእርሱም ደግሞ የቆማችሁበትን በእርሱም ደግሞ የምትድኑበትን ወንጌል አሳስባችኋለሁ፤በከንቱ ካላመናችሁ በቀር፥ ብታስቡት፥ በምን ቃል እንደ ሰበክሁላችሁ አሳስባችኋለሁ።እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ ››(1ኛቆሮ.15፡1-4) 🔸የክርስቶስ ሞት እና ትንሳዔ የወንጌል ማዕከል ነው። ወንጌል ለፍጥረት ሁሉ የሚታወጅ የመስቀሉ የማዳን ሥራ ነው፣ “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው…” (፩ኛ.ጢሞ1፡15)። 🔸 ወንጌል ሰዎች ከኃጢአታቸው ንስሃ በመግባት የበደላቸውን ስርየት እንዲቀበሉ ይናገራል፣ “..በስሙም ንስሐና የኃጢአት ስርየት ከኢየሩሳሌም ጀምሮ በአሕዛብ ሁሉ ይሰበካል ተብሎ እንዲሁ ተጽፎአል” (ሉቃ24፡47) በወንጌል የተገኘው ድነት የሰው ልጅ በመስቀል ላይ በተሰራው የድነት ሥራ በማመን 🔸የኃጢአት ሥርየትን ያገኛል ሮሜ 3፡25 🔸ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ይታረቃል ሮሜ 5፡8-10 🔸በክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ ይሆናል ዮሃ 1፡12 🔸የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ መንግስት ይወርሳል 1ኛ ጴጥ 1፡3-5 🔸ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ቀደመው የፍቅር ህብረት ይመለሳል ፡፡ ዮሃ 17 ፡20-26 🔸በዚህ ዓለም ሲኖር የዘላለማዊ ተስፋ ያገኛል ኤፌ 2፡12-13 🔸የምሥራቹን ወንጌል የማወጅ መብትና ብቃትን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል ማቲ 28፡19 🔸በኃጢአት ምንክንያት ከሚመጣ የእግዚአብሔር ፍርድ ይድናል ገላ 3፡13 ዮሃ 3፡18 ወንጌል መጽሐፍ እንደሚል ከፍርድ ነፃ መውጣት እና የዘላለም ሕይወት ጉዳይን የሚይይዝ ነው። • “በልጁ የሚያምን የዘላለም ህይወት አለው” (ዮሐ.3፡38)። • በኃጢአት ምክንያት ከሚመጣ የዘላለምም ፍርድ ያመልጣል፣ “በእርሱ የሚያምን አይፈረድበትም..”(ዮሐ.3፡18)። ታዲያ ልዪ ወንጌል ምንድነው? ከላይ ከጠቀስነው መፅሐፍ ቅዱሳዊው ወንጌል በቀር ሌላው ወንጌል ልዩ ወንጌል ነው ልዩ ወንጌሎች ብዙ ናቸው ከእነዚህ ውስጥ በገላቲያ አንዱ አይነት ተከቶ ነበር …. ይሄ ልዩ ወንጌል እንዲህ አይነት ነው ‹‹አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና። እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር።›› ልዩ ወንጌል ይህ ነው ፡- ካልተገረዛችሁ አትድኑም የሚለው ነው ።
Show all...
በአዲስ ኪዳን መዳን ከምንም ነገር ጋር ሳይሆን የተገናኘው ክርስቶስን ከማመን ጋር ነው ፡፡ መዳን ክርስቶስን በማመን ነው ፡፡ ጳውሎስ ለእዚህ ነው ይህንን ትምህርት ልዩ ወንጌል የሚለው ለምን ? መዳን ለእስራኤልም ሆነ ለአህዛብ በክርስቶስ ማመን ብቻ ሆኖ መንገዱ ስለተመረቀ ነው ፡፡ ጳውሎስ በእዚሁ መፅሀፍ እንዲህ የሚለው ለዛ ነው፡፡ ‹‹ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ፥ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል።›› ገላ 2፡16 ይህ ክፍል እንደሚነግረን ሰው ክርስቶስን በማመን ይፀድቃል ፡፡ ይህ ብቻ ሳይሆን እነ ጳውሎስ ያወቁት ሌላ እውቀትም አለ እርሱም ሰው በሕግ ስራ እንደማይፀድቅ ነው ፡፡ ‹‹ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን፥ ›› ጳውሎስ በገላቲያ ቤተ ክርስቲያን የተነሳውን የልዩ ወንጌል ትምህርት ስህተት እና የሚያስረግም መሆኑን ለመናገር አያቅማማም ደግሞም እንኳን አህዛብ የሙሴ ህግ ያልተሰጣቸው ቀርቶ በትውልድ እስራኤላዊ የሆኑት ሐዋሪያትና ራሱ ጳውሎስ እኛ ራሳችን በሕግ ስራ ሳይሆን በክርስቶስ ኡየሱስ አምናነል ይላል ፡፡ ስለዚህ ልዩ ወንጌል ተብሎ የተጠቀሰው እንደ ሙሴ ህግ መገረዝ ለመዳን የማይሆን የስህተት ትምህርት ነው ፡፡ ይህ ልዩ ወንጌል ከመገረዝ ጋር ብቻ የተገናኘ ሳይሆን የሙሴ ህግን ለድነት ከመጠበቅ ጋር የተገናኘም ነው ፡፡ ‹‹ከፈሪሳውያን ወገን ግን ያመኑት አንዳንዶቹ ተነሥተው። ትገርዙአቸው ዘንድና የሙሴን ሕግ እንዲጠብቁ ታዙአቸው ዘንድ ይገባል አሉ።›› የሐዋ 15 ፡5 ወዳጆች ኢየሱስ ብቻውን ካልነገሰበት የወንጌል ስብከት ራሳቹን ጠብቁ ኢየሱስ ላይ ሌላ አትደርቡ በቂ ከበቂ በላይ ነው ።እንደ ክርስቲያን ለመኖር ተጋደሉ ፀጋ ለምኑ ። እግዚአብሔር ለወዳጆቼ ፀጋ ጨምርላቸው 🙏 አሜን!! ይቀጥላል ....
Show all...
👍 1
00:31
Video unavailableShow in Telegram
10.60 MB
ክፍል ስድስት አንድ ብቻ እውነተኛ ወንጌል አለ!! በሞባይል ምርቶች ውስጥ የትክክለኛውን ብራንድ የሚመስሉ ሀይ ኮፒ ተብለው የሚጠሩ ምርቶች አሉ ፡፡ እነዚህ ምርቶች በመመሳሰል ደረጃ የሚጠጋጉ ቢመስሉም ነገር ግን የዋናውን ብራድ አይነት ሊሆኑ አይችሉም ፡፡ የክርስትና ወንጌል አንድ ነው አይነቱም እጅግ ከሌሎቹ የተለየ ነው ፡፡ ኢየሱስ ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር። ‹‹ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።›› ዮሃ 14፡27 ሁለት ሰላሞች ቀርበዋል ነገር ግን ተመሳሳይነት በስም ደረጃ ቢኖራቸውም በአይነትና በምንጭ ይለያያሉ ። 🔸አንደኛው አለም የሚሰጠው ሰላም ሲሆን 🔸 ሁለተኛው ደግሞ ኢየሱስ የሚሰጠው ነው ፡፡ 🔸 አንደኛው እውነተኛው ኢየሱስ የሚሰጠው ሲሆን 🔸ሁለተኛው አለም የምትሰጠው ሰላም መሳይ ሰላም ነው ፡፡ መመሳሰል እንጂ አንድ አይነትነት የለበትም ፡፡ በወንጌልም እንዲሁ ነው እውነተኛ አንድ ወንጌል አለ ውሸተኛ ልዩ ወንጌል ደግሞ በገላቲያ እንደተገኘው አለ ፡፡ ( ስለ ወንጌል ምንነት በቀጣይ በሰፊው መጣበታለሁ ) ወንጌል በአጭሱ ስለ ማን እንደሆነ መፅሀፍ እንዲህ ብሎ ይነግረናል ‹‹ይህም ወንጌል በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለ ተወለደ እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ በኃይል የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ #ስለ_ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።›› እውነተኛው ወንጌል ይሄ ሆኖ ሳለ ሰዎች አማራጭ መንገድ በመፈለግ ሊባዝኑ ይችላሉ ፡፡ እንደ ገላቲያ ሰዎች !! በገላቲያ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጠውን ጉደይ አስመልክቶ ጳውሎስ እንዲህ ይፅፋል ፡፡ ‹‹በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመይሁን።አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።›› #የጳውሎስ_መደነቅ ጳውሎስ የገላቲያ ሰዎችን እንደሚደነቅባቸው ይነግራቸዋል ፡፡ይህ መደነቅ ስለ ሰሩት መልካም ነገር ስላሳዩት ትጋት ሳይሆን ስላቃዊ ወይም አሉታዊ በሆነ መንገድ የተደነቀበትን መናገሩ ነው ፡፡ እንዴት ከክርስቶስ ውጪ ሌላ ፈለጋችሁ ? በክርስቶስ የጠራችሁን ትታችሁ ወደ ሌላ ወንጌል ለመሄድ እንዴት አሰባችሁ? በሚል ነው የሚደነቅባቸው ፡፡ እውነት ነው ከሱ ከእግዚአብሔር ውጪ እንመኝ ብንል እንኳ ምን የሚያስመኝ ነገር አለ ፡፡ እንኳን ወደ ውጭ ወደ ራስ ማይት ራሱ ከባድ ነው ፡፡ ሁሉ ተስፋ የሚያስቆርጥ ጭጋግ ነው ፡፡ ተስፋ የሚያለመልም እውነተኛ እርሱ እግዚአብሄር ነው ፡፡ ይህ አምላክ በክርስቶስ ጠርቶናል ሌላ ምን ያሻናል? ይህ ወንጌል እውነተኛ ወንጌል አንድ ብቻ ነው ፡፡ ተከታይም ቀዳሚም የለውም …… ‹‹በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ›› ሁለት አይነት ነገሮች በእዚህ ክፍል እናስተውላለን አንዱን እንመልከት 🔸1ኛ በክርስቶስ ፀጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ( በክርስቶስ ፀጋ የጠራችሁ እርሱን ትታችሁ አ.መ.ት ) አማኞች የተጠሩ ናቸው ፡፡ የተጠሩት በክርስቶስ ፀጋ ነው ፡፡ ሳይጠራ የመጣ አማኝ የለም ፡፡ይህ በተለያዩ የቅዱሳት መፅሐፍት ምስክርነት የፀና እውነት ነው ፡፡ ይህ ጥሪ በተላያየ መንገድ ተገልጧል ፡፡ የዕብራውያን መፅሐፍ ፀሐፊ እንዲህ ይላል ፡፡ ‹‹ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤›› ዕብ 3፡1 ስለዚህ ቅዱሳን አማኞች ሁሉ እንደተጠሩት እንደዚሁ የገላቲያ ሰዎችም ተጠርተዋል ፡፡ምናልባት እዚህ ጋር ማንሳት ያለብን አንድ ነጥብ የዳኑት አማኞች ተጠርተው ሲሆን ያልዳኑት ግን ሳይጠሩ ቀርተው አለመሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል ፡፡ የንጉስን ጥሪ ችላ ያሉ አልፈልግም ብለው ከእዚህ ጥሪ ይልቅ የራሰቸው ድግስ ያስቀደሙ በስራቸው የተማመኑ ከእዚህ ጥሪ ይልቅ እንደ ገላቲያ ሰዎች ወደ ጎን የተመለከቱ እነዚህ ከጥሪው ድግስ ያልተቋደሱ ተላሎች ናቸው ፡፡ አብ ሲደግስ ልጁን ቤዛ ሲያደርግ ጳውሎስ እንዲህ ነበር የፃፈው ፡፡ ‹‹አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም #ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ #ራሱንም_ለሁሉ_ቤዛ_ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤›› 1ኛ ጢሞ 2፡5-6 ታዲያ ይህን የአብ ስጦታ ያልተቀበሉ ሊቀበሉ ካለቸው ቁጣ በላይ ምን የሚያስፈራ ቁጣ አለ? እውነተኛ ወንጌል እርሱ ግን መትረፊያ ነው ፡፡በወንጌል የተሰበከው መዳን ከእግዚአብሄር የሆነ ለሰዎች የመጨራሻ የዘላለም ህይወት መፍትሔ ነው ፡፡ ሁሉ ሐጢያት ስለሰሩ ለእነርሱ የሚሆን መፍትሔ በወንጌል ጥሪ ውስጥ ተቀምጧል ፡፡ የገላታያ ሰዎች ይህንን ጥሪ ሰምተው በክርስቶስ አምነው የሚኖሩ እውነተኛ አማኞች ነበሩ ፡፡ ይህም በፍሬያቸው ተገልጧል ፡፡ ጳውሎስም ይህንን በቀጣይ ምዕራፎች ላይ መስክሮላቸዋል፡፡ ምን ዋጋ አለው የስሕተት አስተማሪዎእ አይናቸውን ከዋና ጉዳያቸው ላይ አንስተው ወደ ልዩ ወንጌል እንዲያተኩሩ አደረጓቸው አንጂ ፡፡ ይህ ትልቅ ህመም ነው ፡፡ በተለይም እንደ ጳውሎስ አይነት ለሆነ እውነተኛ አገልጋል ፡፡ ለዛ ነው ጳውሎስ ምጥ ይዞኛል የሚለው ፡፡ ‹‹ልጆቼ ሆይ፥ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል።›› ገላ 4፡19 ከኢየሱስ ውጪ አማራጭ የለንም ብቸኛ ማረፊያ መደላደያ እርሱ ነው ፡፡ እርሱ ቢደገፉት ምቹ ነው ቢጠጉት ያማረ ነው፡፡ ቢሰማሩበት ለምለም ነው ፡፡ ቢኖሩበት እረፍት ነው ፡፡ በክርስቶስ ላይ ተደላድሎ መኖር ይሁንልን አሜን ይቀጥላል ..... ✍️ Girum Difek
Show all...
👍 3 1