cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ሸገር NEWS

የሚያምኑት መረጃ!! እጅግ ፈጣንና ዘመናዊ በሆነ የመረጃ አሰጣጣችን ይረካሉ አሁኑኑ የቤተሰባችን አባል ይሁኑ #ሸገር የናንተ #ሸገር የኛ

Show more
Advertising posts
24 317Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Posts Archive
የኢትዮጵያና የአማራ ህዝብ ጠላት የሆነው ትህነግ ወያኔ እንደአገር ባደረሰብን ህልቆ መሳፍርት የሌለው ግፍና በደል እንዲሁም ለፈጸመብን ሀገራዊና ህዝባዊ ክህደት የአገራችንን የግዛት አንድነት በመሸርሸር ሉአላዊነቷ የማይከበር፣ ራሷን ችላ መቆም የማትችልና በሁሉም መስክ ተንበርካኪ ሀገር ባለቤቶች እንድንሆን በርካታ ደባ ፈጽሞብናል፡፡ በአለም አደባባይ የምንኮራበት ሀገራዊና ህዝባዊ የጋራ ታሪክ ባህልና እሴት እንዳይኖረን አንድነታችንንና አብሮነታችንን በፈጠራ ታሪክ እየቦረቦረ እርቃናችንን እንድንቀር፣ አንዳችን ለሌላችን ጋሻና መከታ መሆን ሲገባን እርስ በእርስ በመጠራጠር አውሎ ነፋስ ወዲያና ወዲህ እንድንላጋና በጠላትነት እንድንፈራረጅ ከሰማይ በታች ያልፈጸመብን ግፍ የለም፡፡ ከሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ተባብረንና ተፈቃቅደን የጸረ ጭቆና ትግሉን አንድ ብለን ስንጀምር በጋራ ያነሳነው የፍትህና የእኩል ተጠቃሚነት ጥያቄ በትህነግ መንደር የቱን ያህል መራር የሆነ የመደፈር ስሜት እንደፈጠረ የቅርብ ጊዜ ክስተት ነው፡፡ አሸባሪው ትህነግ ከመንበረ ስልጣኑ ተምዘግዝጎ ሲወድቅና መቀሌ ሲከትም የነበረው ብቸኛ ምክንያት አይናችሁን ጨፍኑና ላሞኛችሁ የሚል ፖለቲካዊ ቁማር እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም፡፡ በውሁድ ፓርቲ ደረጃ የተፈጠረውን አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ አደረጃጀት የአህዳውያን ውጤት አድርጎ ያበሻቀጠው ፍላጎቱ በለመደው የአድራጊ ፈጣሪና የአዛዥነት ሚና ያልተሳተፈበትን መዋቅር ለማጣጣል ከማለም ባሻገር ለኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እኩል ተጠቃሚነት ባለው ከፍ ያለ ንቀትና ጥላቻ ምክንያት መሆኑ ለሁሉም ግልጽ ነው፡፡   ይህንን ተከትሎ በትግራይ ክልል የሰሜን ዕዝ እንዳይነቀሳቀስ በተደጋጋሚ ያደረገው ሙከራ የልብ ልብ ሰጥቶት ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም.የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ውድ ልጆችን በግፍ ያለርህራሄ አሰቃቂ ግድያ ከፈጸመባቸው በኋላ የዕዙን ጠቅላላ ንብረት በመውረስ በመላው ኢትዮጵያውያን ላይ ጦርነት ማወጁ ይታወቃል፡፡ የአማራ ክልልን ወሰን ጥሶ በማለፍ ጥቃት ለመፈጸም ያደረገው ጥረት ባይሳካለትም በማይካድራ ንጹሀን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የፈጸመው አረመኔያዊ የጅምላ ጭፍጨፋ የሚዘነጋ አይደለም፡፡ ይህንን ተከትሎም መንግስት በየደረጃው የህግ የበላይነት ለማስከበር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን አከናውኗል፡፡ በሂደቱም በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡ይሁን እንጂ ይህ አረመኔና አሸባሪ ቡድን አይኑን በጨው አጥቦ ጥቃት የተፈጸመበት በማስመሰል አለምአቀፉን ማህበረሰብ በተደጋጋሚ በማጭበርበር ላይ ይገኛል፡፡  የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐፕሊክ መንግስት በአንድ ወገን የወሰደውን የተኩስ አቁም ውሳኔ እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም በኢትዮጵያና በአማራ ክልል ህዝብ ላይ መሰረተ ሰፊ የሆነ ወረራና ጥቃት ማድረግ ጀምሯል፡፡ ይህ አሸባሪ ቡድን የጀመረብንን ግልጽ ወረራ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚያወግዘውና የምንጊዜም አጋራነቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ፍጹም ጥርጣሬ የለንም፡፡ በዚህ አጋጣሚ የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ በግልጽ እንደሚያውቀው የአማራ ክልልና ሕዝብ የዚህ አሸባሪ ቡድን ቀጥተኛና የቅርብ ተጠቂ መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም ትግላችን ለህዝባችን ህልውናና ለሀገር ሉአላዊነት መሆኑ ግንዛቤ ውስጥ ገብቶ የጋራ ጠላታችንን በጋራ እንድንፋለመው የአጋርነት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡  አሸባሪው የትህነግ ቡድን ከአማራ ክልል ጋር በሚያዋስኑት ሁሉም አቅጣጫዎች መጠነ ሰፊ ወረራና ጥቃት እየፈጸመ የሚገኝ አረመኔና ጨካኝ ቡድን መሆኑ እንዲታወቅና ሁሉም የአማራ ክልል ህዝብ ጉዳዩን ከህልውናው ጋር በማስተሳሰር እንዲመለከተውና ከዚህ ጨካኝና አረመኔ ቡድን ጋር ቀጣይ የምናደርገው ሁሉ አቀፍ ትግል የህልውና ትግል መሆኑን አውቆ በገንዘብ፣ በጉልበትና በህይወት መስዋዕትነት አስፈላጊውን አበርክቶ ለማድረግ ራሱን እንዲያዘጋጅና የመንግስትን ጥሪ እዲጠባበቅ የክልሉ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል፡፡  አሸባሪው ትህነግ የትግራይን ህዝብ ከህጻን እስከአዋቂ በማንቀሳቀስ አለም አቀፍ የጦርነት ህግጋትን በመቃረን ህጻናትንና ሴቶችን በጅምላ ጦርነት እየማገደና ያለ የሌለውን አቅሙን ተጠቅሞ ክልላችን ላይ ወረራ የፈጸመ ሲሆን በተለይም ለዘመናት የአማራ ህዝብ የማንነትና የወሰን ጥያቄ እያነሳ ሲታገልባቸው የቆዩ የራያ አላማጣና ኮረም አካባቢዎችን ዳግም በመውረር እንዲሁም ወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ በኃል ለመያዝ በተለይም ጠለምትና አካባቢውን ለመያዝ አሁናዊ ሙከራ የጀመረ መሆኑ በአካባቢው የሚኖሩ አማራዎችንና የአማራ ክልል ተወላጆችን ፈጽሞ የማጥፋት ህልሙን እውን ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ይህንን አረመኔያዊ ድርጊትና ዳግም ወረራ የክልሉ መንግስት በፍጹም የማይቀበለውና በጀመርነው የህልውና ትግል ተፈጥሯዊና ታሪካዊ መብታችንን የምናረጋግጥ መሆኑን አበክረን እንገልጻለን፡፡  ስለሆነም፡- 1ኛ. በየግንባሩ የምትገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት፣ የክልላችን ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት፣ ህዝባዊ ፖሊስና ሰላም አስከባሪ አባላት እንዲሁም አገርና ህዝብን ለማዳን የተግባር እንቅስቃሴ እያደረጋችሁ ያምትገኙ የየክልሉ የጸጥታ አካላት በዚህ ታሪካዊ መድረክ ከጠላት ጋር ፊት ለፊት በመግጠም ለአገራችሁ ሉአላዊነትና ለህዝባችሁ ህልውና የምትከፍሉትን ክቡር መስዋዕትነት ታሪክ ምንጊዜም ሲያስታውሰው ይኖራል፡፡ በቀጣይም የተሰጣችሁን ህዝባዊና አገራዊ ተልዕኮ በጽናትና በቁርጠኝነት እንደምትወጡ እምነታችን የጸና ነው፡፡ስለሆነም መላው የኢትዮጵያና የአማራ ህዝብ ከጎናችሁ መሆኑን አውቃችሁ በጀግንነት ታሪካዊ ጠላታችንን በመደምሰስ ለአገራችሁ ዳግም የኩራት ምንጭ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡   2ኛ. መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በትህነግ ወያኔ ላይ የተጀመረው ህግን የማስከበር ትግል ተጠነናክሮ እንዲቀጥል አስፈላጊውን እርብርብ ሁሉ ማድረግ አለበት ብለን እናምናለን፡፡ አሸባሪው ትህነግ አገር ከማፍረስ እኩይ ተልዕኮው ሊታቀብ የሚችለው የአገራችንን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት በጽናትና በአላማ ቁርጠኝነት  በጋራ መጠበቅ ስንችል ስለሆነ በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ በጋራ እንድንቆም የአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡    3ኛ. በየትኛውም ዘመን ሰልጥናችሁ፣ የአገርና የህዝብ ሉአላዊነት ለማስከበር በማንኛውም የመንግስት ጸጥታ መዋቅር ውስጥ ተሰልፋችሁ ስታገለግሉ የቆያችሁና በታሪክ አጋጣሚ የሙያ ዘርፍ የቀየራችሁ የክልላችን ነዋሪዎች ለህልውናችን የምናደርገውን የትግል ጥሪ ተቀብላችሁ በክልሉ ጸጥታ መዋቅር ውስጥ እንድትቀላቀሉ ጥሪያችንን እያቀረብን ከዛሬ ጀምሮ በየአካባያችሁ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት በአካል ተገኝታችሁ በፈቃደኝት እንድትመዘገቡ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡  4ኛ. መላው የክልላችን ወጣቶች ከፊት ለፊታችን የተደቀነብንን የህልውና አደጋ ያለበቂ ዝግጅትና ደረጃውን ከጠበቀ ስልጠና ውጭ የምንጋፈጠው አይደለም፡፡ ስለሆነም ከማንኛውም ግብታዊ እንቅስቃሴ ታቅባችሁ በየደረጃው ለሚኖረው ምልመላና ስልጠና በመሳተፍ በቂ ዝግጅት አድርጋችሁ የመንግስትን ጥሪ እንድትጠባበቁ እናሳስባለን፡፡  5ኛ. መላው የክልላችን ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክና የሙያ ማህበራት፣ ማህበራዊ አንቂዎችና የሚዲያ ባለሙያዎች የጀመርነው የህልውና ትግል የሁላችንንም አንድነት፣ ህብረትና ተቀራርቦ መስራት የሚጠይቅ ነው፡፡
Show all...
ኢትዮጵያና ሩሲያ በወታደራዊ ቴክኒክ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ሁኔታ ላይ በማተኮር ለሶስት ቀናት ሲያካሂዱት የቆዩት ውይይት የተለያዩ ስምምነቶች ላይ በመድረስ ተጠናቋል። ለ11ኛ ጊዜ የተካሄደው ይህ ውይይት በ10ኛው የጋራ ውይይት ላይ የተደረሱ ስምምነቶች አተገባበርን በጥልቀት ተመልክቷል። አሁን የተደረሰው ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት ይበልጥ የሚያጠናክርና ይበልጥ በማቀራረብ አብሮ መስራት የሚያስችል መሆኑን የመከላከያ ፋይናንስ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ማርታ ሊዊጅ ገልፀዋል። የሰራዊቱን አቅም በእወቀት ፣ በክህሎትና በቴክኖሎጂ ለማዘመን ለሚደረገው ጥረትም የሁለቱ ሃገራት ስምምነት ፋይዳው የጎላ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ በውይይቱ ከሩሲያ ፌዴሬሽን ወታደራዊ ሃይል የቴክኒክ ዘርፍ የተለያዩ ተቋማትና ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላት መሳተፋቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
አሸባሪው ህወሓት በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ ጭፍጨፋ እየፈጸመ መሆኑን ኤርትራ አስታወቀች አሸባሪው ህወሓት በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ የበቀል እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የኤርትራው የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል አስታወቁ። አቶ የማነ እንደገለጹት፤ ህወሓት በስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ ባሉ ንጹን ኤርትራዊያን ላይ ሳይቀር በበቀል ተነሳስቶ ጭፍጨፋ እየፈጸመ ይገኛል። ህወሓት እየፈጸመ ያለው የበቀል ግድያና ጭፍጨፋ ብሎም የድርጅቱ ህገ ወጥ ተግባራት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር ባሉ ኤጀንሲዎች እና የድርጅቱ አፍቃሪ መገናኛ ብዙሀን ቸል መባሉን ገልጸዋል። በጄኔቫ የኤርትራ ኤንባሲ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረትም ትግራይ ክልል ባሉ የስደተኛ ጣቢያዎች ውስጥ የሚገኙ ንጹሀን ኤርትራዊያን እየተገደሉ ይገኛሉ። በጄኔቫ ያሉት የኤርትራ አምባሳደር በዚህ ጉዳይ ላይ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ጋር መነጋገራቸውን ኤንባሲው አስታውቋል። ከዚህ መረጃ በፊትም አምንስቲ ኢንተርናሽናል ባወጣው መረጃ መሰረት በትግራይ ክልል ያሉ ንጹሀን ዜጎች የደህንነት ስጋት እንደተጋረጠባቸው ጠቅሶ ስጋቱን ማስተወቁ አይዘነጋም። በተመሳሳይመ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን የጤና ተቋማት መዘረፋቸውን ንጹሀን ዜጎች ለከፍተኛ እንግልት መጋለጣቸውን ማስታወቁ እንዲሁም ከሳምንት በፊት በክልሉ የተወሰኑ አካባቢዎች አገልግሎት መስጠት ማቆሙን መግለጹ ይታወሳል። Via (ኢ ፕ ድ) @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ካለፉት 5 ዓመታት ወዲህ መንግሥት በተለየዩ አካባቢዎች ከገነባቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች እስካሁን 12 ያህሉ ስራ ጀምረዋል፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አላማዎች አንዱ የእውቀት ሽግግርን ማምጣት ነው፡፡ ምን ያህል የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር እየመጣ ነው? ንጋቱ ረጋሳ #የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ባሳለፍነው ሳምንት (ከሰኔ 26 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 2 ቀን 2013) ድረስ ከ31 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተይዘዋል፡፡ የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከሀገር ሊወጡ እና ወደሀገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆን፣ የገቢ ኮንትሮባንድ 31 ሚሊየን 59ሺህ 580 ብር፤ ወጪ ደግሞ 550 ሺህ 931 ብር ግምት እንዳላቸው ከገቢዎች ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ አመልክቷል። ከተያዙት ከኮንትሮባንድ ቁሳቁስ መካከል የውጭ ሀገራት ገንዘቦች፣ ወርቅ፣ የተለያዩ አልባሳት፣ ጫማ፣ ምግብ ነክ፣ የጦር መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ኮስሞቲክስ፣ ሲጋራ፣ ልባሽ ጨርቅ፣ መለዋወጫ፣ የሰው መድኃኒትና ሌሎችም የሚገኙበት ሲሆን፤ ሶስት ተጠርጣሪዎች እና ታርጋ ቁጥር የሌላቸው አራት ሞተሮችን ጨምሮ 11 ተሽከርካሪዎች ኮንትሮባንድ ሲያዘዋውሩ ተይዘዋል፡፡ @shegernewsBot @shegernewsETH
Show all...
የሶማሊያ ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት መሐመድ ፋርማጆ ለብልጽግና ፓርቲ ሊቀመንበር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፉ "ከኢትዮጵያ ህዝብ በድጋሚ ይሁንታ በማግኘትዎ እንኳን ደስ አለዎት ለማለት እወዳለሁ" ብለዋል ፋርማጆ በትዊተር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፡፡ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በብልጽግና ከሚመራው መንግሥት ጋር በትብብር መስራቷን ትቀጥላለች ብለዋል፡፡ ሁለቱ አገራት ህዝቦቻቸውን ብቻ ሳይሆን ቀጠናውን ጭምር ለመጥቀም በትብብር ይሰራሉም ብለዋል፡፡ Via :- Al ain @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመሩት ብልፅግና ፓርቲ በከፍተኛ ድምፅ ማሸነፉን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በትናንትናው ዕለት አስታውቋል። ቦርዱ እንዳመለከተው ብልፅግና ፓርቲ ከ436 መቀመጫዎች ውስጥ 410 ያሸነፈ ሲሆን ለቀጣዩ አምስት አመታትም መንግሥት መመስረት የሚያስችለውን ወንበር አግኝቷል። የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ "በታሪክ ሁሉን ያካተተ ምርጫ" በማለት በትዊተር ገፃቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸው አስፍረዋል።ነገር ግን ከአገሪቱ የፀጥታና ሎጅስቲክ ችግሮች ጋር በተያያዘ በተወሰኑ አካባቢዎች ድምፅ መስጠት አልተቻለም። በሺዎች የሚቆጠሩ በረሃብ በተጋለጡባትና በጦርነት በተጎዳችው የትግራይ ክልል ምርጫ አልተካሄደም። ሰኔ 14፣ 2013 ዓ.ም ድምፅ መስጠት ባልተቻለባቸው አካባቢዎች በሌላኛው ዙር ጳጉሜ 1፣ 2013 ዓ.ም ምርጫው እንዲካሄድ ቢወሰንም በትግራይ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። የዘንድሮው ብሔራዊ ምርጫ ከተያዘለት ቀን በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት እንዲራዘም መደረጉ የሚታወስ ነው። አዲስ መንግሥት በጥቅምት ወር ይመሰረታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ሆኖም በምርጫው ትክክለኛነት ላይ አንዳንድ ጥያቄዎች መነሳታቸው አልቀረም። አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮቻቸው ለእስር በመዳረጋቸው ከምርጫው ራሳቸውን ያገለሉ እንዲሁም ለምርጫው ዝግጅት አስተጓጉሎናል ያሉ አሉ። በበርካታ ክልሎች ታዛቢዎቻችን በአካባቢው ባለስልጣናት እና ሚሊሺያዎች ታግደዋል በሚል ፓርቲያቸው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ከ200 በላይ ቅሬታዎች ማቅረባቸውን ብርሃኑ ነጋ (ዶ/ር) ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ በምልከታው "ከበድ ያለ ወይም የተስፋፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች አለመኖሩን" አስታውቋል። @shegernewsbot
Show all...
ሰበር ዜና አጠቃላይ የምርጫ ውጤት ይፋ ተደረገ (ለፓርላማ) 1. አዲስ አበባ ከተማ - ብልጽግና 22 መቀመጫዎችን አሸንፏል - አንዷን መቀመጫ አንድ የግል ዕጩ ተወዳዳሪ አሸንፈዋል 2. አፋር ክልል - 8 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት - ሰኔ 14 ምርጫ የተካሄደባቸው 6 መቀመጫዎችን በሙሉ ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል 3. አማራ ክልል - ምርጫ ከተካሄደባቸው 125 የፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ ብልጽግና በ114ቱ አሸንፏል - አብን 5 መቀመጫዎችን አሸንፏል 4. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ - 9 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት - በሶስት የፓርላማ መቀመጫዎች ሰኔ 14 ምርጫ ተከናውኗል - ሶስቱንም መቀመጫዎች ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል 5. ድሬዳዋ - 2 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት - ብልጽግና ፓርቲ አንዱን መቀመጫ አሸንፏል 6. ጋምቤላ ክልል - 3 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት - ሶስቱንም ምርጫ ክልሎች ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል 7. ኦሮሚያ ክልል - 178 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት - ምርጫ ከተካሄደባቸው 170 መቀመጫዎች ውስጥ ብልጽግና 167ቱን መቀመጫ አሸንፏል - ቀሪ 3 መቀመጫዎችን 3 የግል ዕጩዎች አሸንፈዋል 8. ሲዳማ ክልል - 19 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት - 19ኙንም መቀመጫዎች ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል 9. ደቡብ ክልል - 104 የፓርላማ መቀመጫዎች አሉት - ምርጫ ከተከናወነባቸው 85 የፓርላማ መቀመጫዎች ውስጥ በ75ቱ ብልጽግና ፓርቲ አሸንፏል - ኢዜማ 4 መቀመጫዎችን አሸንፏል - የጌድዮ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ 2 መቀመጫዎችን አሸንፏል @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የቱርኩ አናዱሉ በጋዛ መስሪያ ቦታቸዉ የወደሙባቸዉ የአልጃዚራና አሶሴትድ ፕሬስ ጋዜጠኞች እኔ ጋር መስራት ትችላላችሁ ሲል አስታወቀ! የቱርኩ መንግስታዊ የዜና ወኪል አናዱሉ በእስራኤል የአየር ላይ ጥቃት የመስሪያ ቦታቸዉ ለወደመባቸዉ የዜና ወኪሎች ለጊዜዉ እኔ ጋር መስራት ትችላላችሁ ሲል አስታዉቋል፡፡ አሶሴትድ ፕሬስና አልጃዚራን ጨምሮ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት ይጠቀሙበት የነበረዉ የጋዛ ህንጻ በእስራኤል ጥቃት ወደ ፍርስራሽነት መቀየሩ አይዘነጋም፡፡ የአናዱሉ ዋና የስራ ሀላፊ ሰርዳር ካራጎዝ ባስተላለፉት ጥሪ መሰረት ይህ ግጭት ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በዚሁ ዙሪያ የሚዘግቡ ጋዜጠኞችን ለማገድ የተፈጸመ ጥቃት ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ እስራኤል በዚህ ህንጻ ላይ ጥቃት ለመፈጸመ አንድ ሰዓት ሲቀራት ማስጠንቀቂያ በመስጠት ያወደመችዉ ሲሆን የአሸባሪዎች መሸሸጊያ ሆኗል ስትል መናገሯ አይዘነጋም፡፡ Via ዳጉ ጆርናል @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
መርካቶ ዘመናዊ የከተማ አውቶቡስ ተርሚናል ዛሬ ይመረቃል አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)-በ200 ሚሊዮን ብር የተገነባው መርካቶ ዘመናዊ የከተማ አውቶቡስ ተርሚናል ዛሬ ይመረቃል ። ተርሚናሉ በአንዴ ለ20 አውቶቡሶች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሲሆን የራሳቸው መግቢያና መውጫ ያላቸው ሁለት ወለሎችም አሉት። 35 የሚደርሱ የአንበሳ የከተማ አውቶቡስ ድርጅት መስመሮች እና 17 የሚሆኑ ሸገር የብዙሃን ትራንስፖርት ድርጅት መስመሮች በድምሩ 52 መስመሮች ላይ አገልግሎት መስጠት ያስችላል። በሰዓት ከ6 ሺህ በላይ በቀን ደግሞ እስከ 80 ሺህ የብዙሃን ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች አገልግሎት ይሰጣል። መንጭ:- አዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ቴልአቪቭ የገባው የግብፅ ልዑክ ከምን ደረሰ ? ተኩስ አቁም ስምምነት ይደረግ ዘንድ ለማሸማገል እስራኤል ቴልአቪቭ የገባው የግብፅ ልዑክ ምንም አይነት አውንታዊ ውጤት እንዳላገኘ አንድ የግብፅ የደህንነት ምንጭ ለDPA ተናግረዋል። እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ለጊዜውም እንኳን ቢሆን ተኩስ ይቆም ዘንድ የቀረቡትን ሃሰቦች በሙሉ ውድቅ አድርጋለች። እስራኤል ወደ ተኩስ አቁም ድርድር ለመምጣት ፥ የሃማስ እና የሌሎች አንጃ ቡድኖችን ወታደራዊ አቅም ማጥፋት እና የምትፈልጋቸው በርካታ የሃማስ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኢላማ ማድረግ ትፈልጋለች ብለዋል የግብፁ የደህንነት ምንጭ። በጋዛ የሟቾች ቁጥር የጨመረ ሲሆን ከሰኞ ጀምሮ እስካሁን በትንሹ 119 ፍልስጥኤማውያን ተገድለዋል፤ 31ዱ ህፃናት ናቸው። 830 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ቤተሰቦች የእስራኤልን የአየር ጥቃት ሽሽት በሰሜን ጋዛ በUN ስር ባሉ ትምህርት ቤቶች ተጠልለዋል። ግጭቱ ከጀመረ አንስቶ በእስራኤል በኩል አንድ የህንድ ዜጋ ጨምሮ 6 እስራኤላውያን ተገድለዋል፤ አንድ ህፃን ልጅ ይገኝበታል። ግጭቱ ይቆም ዘንድ ዓለም አቀፍ ተማፅኖዎችና ጥሪዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ለመላው የ እስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1442ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም ፤ አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ ! መልካም በዓል @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከ700 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 42 የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች ግንባታቸው ተጠናቆ በተያዘው ዓመት አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምሩ የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎቹ ግንባታ የሚገኝበትን ደረጃ ለቅዱስ ጊዮርጊስና ለኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎችና በተለያዩ አደረጃጀቶች ለሚገኙ ወጣቶች አስጎብኝቷል። የአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽነር በላይ ደጀን፥ “በከተማዋ ከ700 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሆነባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በዚህ ዓመት ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት ይሆናሉ” ብለዋል። ወደ አገልግሎት ከሚገቡት የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች በግንባታ ላይ የነበሩና ገሚሶቹም በዚህ ዓመት የተጀመሩ እንደሚገኙበት ገልፀዋል። ማዘውተሪያ ስፍራዎቹ የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣ የቅርጫት ኳስና ሌሎች የስፖርት አይነቶችን ያካተቱ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
Show all...
‘ኢንተርኔት’ ማለት ማህበራዊ ሚዲያ ብቻ የሚመስልበት ግዜ ለምን ሆነ? ኢትዮጵያ ከፊቷ ምርጫ ይጠብቃታል፡፡ ለዚህ ደግሞ ኢንተርኔቱ መቃኘት እንዳለበት የሚቀበሉም የማይቀበሉም አሉ፡፡ አሁን ያለው የኢንተርኔት አጠቃቀም ግን ምን ይመስላል? ተህቦ ንጉሴ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
በህንድ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ዓለም አቀፍ ስጋት ነው:: ድርጅቱ ቢ.1.617 የተሰኘው የኮሮና ቫይረስ ዝርያ ከሌሎች የቫይረሱ ዝርያዎች በላይ በቀላሉ የሚተላለፍ መሆኑን ባደረገው ጥናት ያመላከተ ሲሆን፥ ሌሎች ጥናቶች እየተደረጉ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ቫይረሱ እስካሁን በ30 ሃገራት መሰራጨቱንም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡ ከእንግሊዝ ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ብራዚል የታዩት ሌሎች የቫይረሱ አዲስ ዝርያዎች ተመሳሳይ ስያሜ ተሰጥቷቸዋል ፡፡ በህንድ በአሁኑ ወቅት ለበርካታ ሰዎች ህልፈት እና በየቀኑ በቫይረሱ ለሚያዙት በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ምክንያት ይህ የቫይረሱ ዝርያ መሆን አለመሆኑ ጥናት እየተደረገበት እንደሚገኝም ነው የተነገረው፡፡ በህንድ እስካሁን ከ22 ሚሊየን 900 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ፥ ከ250 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡ © ቢቢሲ እና ዎርልድ ኦ ሜትር @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ሱዳን ተገን የጠየቁ የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን ወደ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ማስገባቷን የሀገሪቱ መንግስታዊ ቴሌቪዥን ዘገበ። የትግራይ ብሔር አባላት የሆኑ እና ቁጥራቸው 120 የሚሆኑ እነዚሁ የሰላም አስከባሪ አባላት የነበሩ ወታደሮች በቅርቡ ሱዳንን ጥገኝነት በጠየቁት መሰረት ወደ መጠለያ ጣቢያ መግባታቸውን የሰሜን ዳርፉር የስደተኞች ጉዳይ ኤጄንሲ ኃላፊ አል ፋተህ ኢብራሂም መሐመድ ተናግረዋል። ከወታደሮቹ 14ቱ ሴቶች ናቸው ተብሏል። በዚሁ መሰረት 31 ወታደሮች ምስራቅ ሱዳን ከሳላ አካባቢ ወደ ሚገኝ የስደተኞች ጣቢያ ዛሬ መጓጓዘቸው በዘገባው ተጠቅሷል። ወታደሮቹ በትግራይ ክልል ከተካሄደው ጦርነት በኋላ የፌዴራሉ መንግስት በቁጥጥር ስር ሊያውለን ይችላል ከሚል ስጋት የተነሳ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አለመፈለጋቸውን የአሶሽየትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል። በሱዳን ዳርፉር የተሰማራው የኢትዮጵያ የሰላም አስከባሪ ቡድን አባላት የሆኑ እና ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል «አለማቀፍ ጥበቃ እንዲደረግላቸው መጠየቃቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቃባይ ፈርሃን ሃግ ባለፈው ወር ተናግረው ነበር ።በምስራቃዊ ሱዳን በትግራይ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ሸሽተው የተጠለሉ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ። [DW/AP]
Show all...
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሰጠ መግለጫ:: ኢትዮጵያ ሀገራችን በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከምትታወቅባቸዉና ከምትከበርባቸዉ ሀገራዊ ልዩ እሴቶቿ ዉስጥ አንዱ የዘርፈ ብዙ ልዩነቶች የመቻቻል ምድር መሆኗ ሲሆን ህዝቦቿ በፈረሃ አምላክ የሚመሩ ናቸዉ፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ሀገራችን የሀይማኖት ብዝሃነትን በመቻቻል፣ በአብሮነትና በመከባበር የሚያስተናግድ ማህበረሰብ ያላት ታሪካዊ ተምሳሌት መሆኗ ነዉ፡፡ የተከበራችሁ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች፣ የእስልምና ኃይማኖትና ሀገራችሁ ኢትዮጵያ ከከተማችሁ አዲስ አበባ ጋር ያላቸዉ ታሪካዊ ትስስር በማይናወጥ መሠረት ላይ የተጣለዉ ገና ከጅምሩ በመሆኑ ከእምነት ጋር ተያይዞ ለዘመናት ሲያጋጥሙን ለኖሩት የዉስጥና የዉጪ ተግዳሮቶች ሳንበገር አንድነታችንን፣ አብሮነታችንን፣ ሉዓላዊነታችንንና ተቻችሎ በፍቅር የመኖር እሴቶቻችንን በጥበብና በጀግንነት አስጠብቀን ኖረናል፡፡ የዚህ ማንነታችን ቀጣይ የሆነዉን ዛሬያችንን በፍቅርና በክብር አብረን በማሳለፍ ላይ እንገኛለን፡፡ ዘንድሮ የታላቁን የረመዳን ጾም ወቅት በታሪካችን ከእናትና ከአባቶቻችን የወረስነዉን እሴት በማስጠበቅ በተለያየ መልኩ በየቦታዉ አብረን አሳልፈናል፡፡ ለአብነትም በቅርቡ የሰጠነው የማምለኪያ ቦታዎች ይህንን ይመሰክራሉ። በስካይ ላይት ሆቴል ሁሉም ሃይማኖቶች በተገኙበት ከሙስሊም ወንድቻችን ጋር አብረን አፍጥረናል፡፡ ከሶሪያዊያን ተፈናቃይ ወንድምና አህቶቻችን ጋር እንዲሁ፡፡ በቤተ-መንግስት፣ በሆቴሎችና በየክፍለ ከተሞቻችን ማዕዶችን ተጋርተናል፡፡ በፍቅርና በመከባበርም አብረን አሳልፈናል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ የዘንድሮዉን የረመዳን ጾም ልዩ በሚያደርግ ሁኔታ በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች ሰፋፊ የጎዳና ላይ የአፍጥር ፕሮግራሞች እጅግ በሚያስደስትና ጠላቶቻችንን በሚያስቀና ሁኔታ በመንግስት አካላት እና በሁሉም ነዋሪዎች ትብብርና አብሮነት ሲካሄዱ ቆይቷል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በከተማችን አዲስ አበባ ብዙ ቁጥር ያለዉ የሙስሊሙን ማህበረሰብና ሌሎችን ያሳተፈ የጎዳና ላይ አፍጥር ለማካሄድ የተዘጋጀዉ እቅድ ባዘጋጁ አካላትና ግለሰቦች እንዲናዉቀዉ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ ፕሮግራሙ በተሳካና የዓለም ሪከርድ በሚሰብር ሁኔታ እንዲፈጸም ከፍተኛ ጥረት ሲናደርግ ቆይተናል፡፡ ከአዘጋጆቹ ጋር በተደጋጋሚ እየተገናኘን ለፕሮግራሙ ዉጤታማነት በሙሉ ልባችን ስንሰራ ቆይተናል፡፡ ለስኬቱም እስከመጨረሻዋ ድረስ በሙሉ አቅማችን ሰርተናል፡፡ ይህን ትልቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ለአብሮነትና ለሀገር አንድነት ለማዋል የተሰራዉ ሥራ የሀሳቡን አመንጪዎችና አዘጋጆቹን የሚያስመሰግን ታላቅ ተግባር መሆኑን እናምናለን፡፡ በእርጥም ዛሬም በከተማዋ የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ የአፍጥር ፕሮግራሞች ተካሂደዋል ። የተከበራችሁ የከተማችን የእስልምና እምነት፣ ተከታዮች፣አብሮ አንድ ማዕድ በጋራ የተቋደሰ አደባባይ የኔ ያንቴ ብሎ አይጣላም፡፡ ነገር ግን በአንድ የአደባባዩ የመጨረሻ የግንባታ ሥራዎች አለመጠናቀቃቸዉ፣ ከሥነ-ሥርዓቱ መከናወን ጋር ተያይዞ ተገቢ ያልሆነ የደብዳቤ ልዉዉጦች ካደረጉት አካላት ጋር በመወያየት በጋራ ግንዛቤና በመተሳሰብ ላይ የተመሰረተና ያለንበትን አጠቃላይ ሀገራዊ ሁኔታ ከግምት ባስገባ መልኩ ፕሮግራሙ በታቀደዉ መሠረት የእፍጣር ቦታዉ ስፋቱና ርዝመቱ እንዲያሳትፈዉ ከታሰበዉ የታዳሚ ብዘት አንጻር እንቅፋት እንዳይፈጠር እዛዉ በዉስን አካባቢ እንዲካሔድ እንደመፍትሔ ተወስዶ ነበር፡፡ እንደፍላጎታችን ቢሆን ኖሮ ዛሬ በመድረኩ ላይ ተገናኝተን በባህላችናና በታሪካችን መሠረት ፕሮግራሙን በአብሮነትና በፍቅር ባከበርን ነበር፡ ሆኖም አዘጋጆቹ የእፍጣር ቦታዉ ስፋቱና ርዝመቱ ውስንነት ላይ ስላልተሰሙ የመሰረዝ አማራጭን ወስደዋል፡፡ በሌላ በኩል ይህን ለሌላ አላማቸው ለማዋል በማህበራዊ ሚዲያ ተገቢ ባልሆነ መንገድ እንዲራገብ ያደረጉ አካላት እንዳሉ አስተውለናል። ይህም የተወሰነ ቅሬታን መፍጠሩን እንገነዘባለን፡፡ ዉድ ሙስሊም ወገኖቻችን በተለያዩ ድምር ምክንያቶች በተፈጠረዉ የፕሮግራሙ መስተጓጎል ቅሬታ ሊፈጥር የሚችል መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ቅሬታችንን የምንገልጽበት መንገድም በሰላማዊና በሰከነ አግባብ መሆን ይኖርታል፡፡ ከሌሎች እምነት ተከታይ ወንደሞቻችን ጋር ሆነን ለዘመናት ነብሳችንን ገብረን ያቆየናትን ሀገራችንን ለጥቃት ማገላጥ አይገባንም፡፡ ዉሻ በቀደደዉ ጅብ ይገባል ነዉና ተረቱም፡፡ ስለሆነም ሌሎች ተመሳሳይ ፕሮግራሞችን ለሺ ዓመታት የምናከብርባትን ታላቋን ዲሞክራሲያዊትና የበለጸገች ሀገር ለመገንባት እየተደረገ ያለዉን ርብርብ ለማደናቀፍ እየሰሩ ላሉ አካላት ዕድል እንዳንሰጥ እንደ እምነቱ አስተምህሮት ታጋሽነታችሁን ታጸኑ ዘንድ አደራ እንላለን፡፡ የተፈጠረዉን ከፍተት በመጠቀም የግል ጥቅማችሁንና ፍላጎታችሁን ለማሳካት ሲባል ጨዋዉን ህብረተሰብ ለማሳሳትና በማይገባ ተግባር ላይ ለማሳተፍ የምትጥሩ ግልሰቦችና አካላትም ከድርጊታችሁ ትቆጠቡ ዘንድ እናሳስባለን፡፡ ወቅቱ በእልህና ለጠላቶቻችን ክፍተት በሚፈጥር መልኩ መሆን የለበትም በማለት ይሄንኑ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ጉዳዩ በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ ህዝበ ሙስሊሞች በሙሉ የከተማ አስተዳደሩ ምስጋናቸውን ያቀርባል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
“ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል” የተባለው የቻይናው ሮኬት በህንድ ውቅኖስ ላይ አረፈ “ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል” የተባለው የቻይናው ሮኬት በህንድ ውቅኖስ ላይ ማረፉ መረጋገጡን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት አስታወቀ። የኢንስትቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አብዲሳ ይልማ ለኢቲቪ እንደገለፁት የቻይና ሎንግ ማርች 5ቢ ሮኬት ተወሰነ ክፍሉ መሬት ላይ ሳይደርስ የተቃጠለ ሲሆን የቀረው ስብርባሪም በህንድ ውያኖስ ማልዲስ ደሴት አቅራቢያውቅያኖስ ውስጥ አርፏል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የ2013 ዓ.ም ለሁለተኛ ዙር የመሰረታዊ ውትድርና ሰልጣኞች የስልጠና ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተከናወነ፡፡ በስነ-ስርዐቱ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ቤቱ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አዲሱ ተርፋሳ ባስተላለፉት መልዕክት ፣ የውትድርና ሙያ ለሀገራችን ያለንን ፍቅር እስከ ህይወት መስዋትነት ለመክፈል በፍላጎት እና በሙሉ ፍቃደኝነት ወደ ሰራዊት የምንቀላቀልበት ሙያ ነው ብለዋል፡፡ ሽብርተኛው ህወሀት በሰሜን ዕዝ ሰራዊታችን ላይ የፈፀመው አፀያፊ የክህደት ተግባር በህግ ማስከበር ዘመቻው የጁንታውን ሀይል በመደምሰስ ሀገር የማዳኑን ስራ በጀግንነት በፈፀምንበት ማግስት የታሪኩ ተቋዳሽ በመሆናችሁ ልትኮሩ ይገባል ብለዋል ፡፡ ሀገራችን ከጥንት ጀምሮ አባቶቻችን በጀግንነታቸው የህይወት መስዋትነት በመክፈል ሉአላዊነቷን አስጠብቀው ትልቅ ታሪክን እንደፃፉ ሁሉ ፣ ይህንንም የጀግንነት ተግባር የማስቀጠል ሀላፊነት እንዳለባችሁ አውቃችሁ መሰልጠን ይኖርባችኋል ብለዋል፡፡ ሰልጣኞቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተከበረውን 80ኛው የአርበኞች ቀን በአልን በደማቅ ስነ-ስርዐት ያከበሩ ሲሆን ፣ ቀጣይ በሚኖራቸው የስለጠና ቆይታም ብቁ ወታደር ለመሆን የሚያስችላቸውን ሁሉ በእውቀት እና በክህሎት የሚያገኙ ይሆናል፡፡ Via ፋህሚ አህመዲን @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የመራጮች ምዝገባ በድጋሚ ተራዘመ የምርጫ ቦርድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የመራጮች ምዝገባ እስከ ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን አሳውቋል። በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር፣ በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ በአማራ ክልል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል፣ በጋምቤላ ክልል፣ በሃረሪ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በሲዳማ ክልል የመራጮች ምዝገባ እስከ አርብ ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ለተጨማሪ 07 ቀናት እንዲከናወን ተወስኗል ሲል ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። የመራጮች ምዝገባ በተራዘመበት ወቅት ተደራራቢ የበአላት ቀናት መኖራቸው እና የመራጮች ምዝገባ ሊከናወን አለመቻሉ የምዝገባ ግዜ መራዘም ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷል።በተጨማሪም ከፍተኛ የመራጮች መጨናነቅ ምርጫ ጣቢያዎች ላይ በመፈጠሩን ነው ተብሏል። የመራጮች ምዝገባ ከተያዘለት የጊዜ ገደብ በተጨማሪ ለ15 ቀን ተጨምሮ ከአፋር እና ከሶማሌ ክልሎች ውጪ የማጠናቀቂያ ጊዜው በዛሬ ሚያዝያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሆን ማሳወቁ ይታወሳል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም የስድስተኛው አጠቃላይ ምርጫ የድምጽ መስጫ ዕለት ሲሆን የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተሞች መስተዳድሮች የድምጽ መስጫ ደግሞ ሰኔ 5 ቀን 2013 ዓ.ም ነው:: የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎች በምርጫው ነፃነት፣ ፍትሐዊነት እና አሳታፊነት ላይ ጥያቄ እያነሱ የየራሳቸውን አማራጭ ሐሳብ እየሰነዘሩ ይገኛሉ። የአገሪቱ የጸጥታ እና የፖለቲካ ነባራዊ ሁኔታ በምርጫው ላይ በተለያዩ መንገዶች ተጽዕኖ አሳድሯል። ከተጽዕኖዎቹ መካከል የመራጮች ምዝገባ በወቅቱ አለመጠናቀቅ አንዱ ነው። በኦሮሚያ ክልል በሚገኙት ምዕራብ ወለጋ፣ ምሥራቅ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ዞኖች ከተወሰኑ የምርጫ ክልሎች በቀር የመራጮች ምዝገባ እስከ ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም መራዘሙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በከማሽ ዞን ከሚገኙት አምስት የምርጫ ክልሎች በአራቱ እንዲሁም በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔር ልዪ ዞን በሚገኙት ዳዋ ጨፌ፣ ጨፋ ሮቢት እና ባቲ ምርጫ ክልሎች ምዝገባው በተመሳሳይ ተራዝሟል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ማረፊያዉ የት እንደሆነ ያልታወቀዉ ሮኬት አለምን አስጨንቋል። ቻይና ወደ ጠፈር ያመጠቀችዉ ሮኬት ከቁጥጥሯ ዉጪ መሆኑ ከተሰማ ቀናቶችን አስቆጥሯል። ሮኬቱ ወደ መሬት 18000mph እየተምዘገዘገ የተለያዩ ሀገሮችን ሲያቋርጥ ዉሏል። ዘጋርዲያን እንደዘገበዉ ግብፅ አካባቢ በተደጋጋሚ ሲመላለስ ታይቷል። ወይኔ ግብፅዬ፤ አልአህራም የተባለዉ የግብፆች ሚዲያ ይህንንኑ አምኖ ሰፊ ዘገባ ይዞ ቀጥቷል። የአሜሪካዉ ስፔስ ስቴሽንና ፔንታጎን የሮኬቱን ስብርባሪ ከሚምዘገዘግበት የአየር ክልል መለየት መቻላቸዉን ነገር ግን የመጨረሻዉ መዉደቂያ የት እንደሆነ አላማወቃቸዉ ቢዝነስ ኢንሳይደር ዘግቧል። ሮኬቱ ቅዳሜ ሜይ። 8 መሬት ይደርሳል። የትኛዉ ሐገር እንደሆነ መልስ አልተገኘለትም። ወደ ምስራቅ አፍሪካ አሊያም ሩቅ ምስራቅ ማረፊያዉ ሊሆን ይችላል ሲሉ አስትሮናቶች ግምት ሰጥተዋልም ተብሏል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ዋዜማ ራዲዮ- በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አጠቃላይ የማሻሻያ ስራ ላይ እየተከናወኑ ያሉ የጥናት ስራዎችን እያከናወነ የሚገኘው የሰላም ሚኒስቴር ባስጠናው ጥናት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ‘’የፌደራል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መመሪያ’’ የሚል ስያሜ እንዲኖረው ሀሳብ ቀርቧል። በክልል ደረጃ የሚደራጁ የፖሊስ ኮሚሽኖች ደግሞ አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው በየክልሉ ስያሜ በጠቅላይ መመሪያ ደረጃ እንዲደራጁ ታስቧል። በዚህ መሰረትም የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ወደ ኦሮሚያ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ወደ አማራ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ስያሜያቸው እንዲቀየር ሌሎችም የክልል ፖሊስ ኮሚሽን አደረጃጀት በዚህ መልኩ እንዲደራጅ የሚያደርግ ጥናት መቅረቡን ነው ዋዜማ የተረዳችው። አጠቃላይ የፌደራልና የክልል ፖሊስ አደረጃጀትን የሚገልፀውን ዘገባ እዚህ ያንብቡ። የልዩ ፖሊስ ሀይል ጉዳይስ? በጥናቱ እንደተመላከተው በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና በክልሎች የፖሊስ ኮሚሽኖች መካከል ያለው የተጠሪነት የተዋረድ ስልጣን ሃላፊነት በሀገሪቱ እየተስተዋሉ ላሉ የፀጥታ መደፍረስ እና ህግን የማስከበር እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱ በጥናቱ እንደ መሰረታዊ ችግር ቀርቧል። በሰላም ሚኒስቴር በኩል ተዘጋጅቶ ለውይይት ሊቀርብ በተሰናዳው የኢትዮጵያ ፖሊስ ዶክትሪን ላይ በግልፅ እንደሰፈረው ‘’ የፖሊስ ተልዕኮ በዋነኛነት ከዜጎች ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ጋር እጅግ የተቆራኘ በመሆኑ ከሁሉ በፊት ውስጣዊና ውጫዊ የአደረጃጀት ስርአቱ በግልፅ አሰራርና ፍልስፍና መገንባት አለበት፡” ይላል። አስከትሎም በገፅ 23 “ የፖሊስ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት በግልፅ የአደረጃጀት ስርዓት ካልተደራጁ የስራ ወይም የኃላፊነት ግጭት እና የፍላጎት ወይም የጥቅሞች ግጭት በመፍጠር የተሰጣቸውን ተልዕኮ እና የተቋቋሙበትን አላማ በመሳት ላልተፈለገ ግጭትና መስዋዕትነት ይዳረጋሉ’’ ሲል ደምድሟል። የፌደራል እና የክልል ፖሊስ ኮሚሽን አደረጃጀት እስከዛሬ በኮሚሽን የአደረጃጀት መጠሪያ በተመሳሳይ ቅርፅ መደራጀታቸው መመሪያዎችን እና ተልእኮዎችን በመቀበል ደረጃ ችግር ሆኖ መቆየቱንም ነው ይህ የውይይት ሰነድ የሚያወሳው። ለዚህም ይመስላል በአዲሱ አወቃቀር የክልል ፖሊስ ኮሚሽን ወይም በአዲሱ መጠሪያ የክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የስልጣን ወሰንን ሰፍሮ ለመስጠት የታሰበው። የክልልና የፌደራል ፖሊስ ስልጣን ወሰን የፖሊስ አደረጃጀት ፍልስፍና የፌዴራል ስርዓቱን ቅርፅ እንደሚከተል ይገልፅና ‘’በፌዴራል ደረጃ የሚኖር የፖሊስ አደረጃጀት የሚኖረው ስልጣን በዋነኛነት ለፌዴራል ፍ/ቤቶች የተሰጡ የስልጣን ወሰኖችን መሰረት የሚደርግ ሲሆን የክልል ፖሊስ ስልጣንም ምንጩ ለክልል ፍ/ቤቶች በተሰጡ ስልጣን ወሰኖች ውስጥ ሆኖ ከየስራ ክፍሎቹ ለየት ያለ ባህርይና ተልዕኮ ጋር የተገናኘ ነው’’ ሲልም ይዘረዝራል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የክልል ፖሊስ ኮሚሽኖች ከአስተዳደር ክልል ወሰን የተሻገረ የጋራ ወንጀልን የመቆጣጠር የተዋረድ የጋራ ስራ ብዙ መሳናክሎች የነበረበት በመሆኑም ይህንን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ግልፅ አሰራር ማስቀመጥ መፍትሄ መሆኑንም ይጠቁማል። ‘’በህገ መንግስቱ ለፌዴራልና ለክልል መስተዳድሮች ተለይተው የተሰጡ ተግባራት እንደተጠበቁ ሆነው ፖሊሳዊ ተልዕኮ በባህሪው ድንበር አልባ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት የጋራ መግባቢያ ሰነድ በማዘጋጀት እና የህግ ድጋፍ እንዲኖረው በማድረግ በትብብርና በአጋርነት መፈፀም አለበት፡፡’’ ሲልም አፅንኦት ይሰጣል የዚህ የተጠሪነት ወይም የስልጣን ተዋረድ አስፈላጊነት ክልሎች ባላቸው የፖሊስ ኮሚሽን አደረጃጀት ምክንያት ከማአከል ጋር ያለው አልያም ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር የነበራቸው ግንኙነት እንደ ሀገር የጋራ ራእይ ሰንቆ ለጋራ የደህንነት መረጋገጥ ከመንቀሳቀስ ይልቅ በክልሎች የመታጠር ውሱንነት በመስተዋሉ መሆኑን የሚያብራራው ጥናቱ ይህንን ችግር ለመፍታት ያለመ የአደረጃጀት ክለሳ ስለመሆኑም ይጠቁማል። የፖሊስ የአደረጃጀት መዋቅሩን “ኮሚሽን” ከሚለው ስያሜ ወደ “ጠቅላይ መምሪያ” ስያሜ ለመቀየር አስፈላጊ ከሆኑ መነሻዎች መካከል ለፌደራልና ለክልል በህግ በተሰጡ ህገ መንግስታዊ ተልእኮዎች መነሻነት መሆኑን የሚያብራራው ይህ ሰነድ ሌላው ዓቢይ ምከንያት ደግሞ ‘’የፖሊስ አደረጃጀት አጠቃላይ ዓላማና ግብ ኢትዮጵያዊ የሆነ የፖሊስ ተቋምን በመገንባት ላይ ያተኮረ ሆኖ የአደረጃጀቱ ቅርፅና ይዘቱ የፌዴራል አወቃቀሩን የተከተለ ይሆናል’’ ሲል ተቋሙንም ከሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አዋህዶ ይበልጥ መልክ ማስያዝም እንደሚያስፈልግ ይገልጻል። ከተቋሙ መጠሪያ ስም ለውጥ ባሻገር ከዚህ ቀደም በፖሊስ አገልግሎት ውስጥ ይሰጡ የነበሩ የማዕረግ መጠሪያዎች ጭምር ሀገራዊ ለማድረግም የሚያስችል ጥናት መቅረቡን ነው ዋዜማ ከምንጮቿ የሰማችው። Via ዋዜማ ራዲዮ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
በደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ማኅበር የተዘጋጀው ልዩ ”የአብረን እናፍጥር” የኢፍጣር መርኃግብር በደሴ ከተማ የተለያዩ ጎዳናዎች ላይ ተካሂዷል። መርኃግብሩ ፍቅርንና አንድነትን ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ መሆኑን የደሴ ከተማ ሙስሊም ወጣቶች ማኅበር ሊቀመንበር ይማም አህመድ ተናግሯል። በኢፍጣር ዝግጅት ላይ የደሴ ከተማ ሙስሊም ማኅበረሰብ፣ የክርስትና እምነት ተከታዮች እና አቅመ ደካሞች መታደማቸውን አሚኮ ዘግቧል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
አቶ አበረ አዳሙ ህይወታቸው አለፈ:: የቀድሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙ መሞታቸውን ከETHIO251 የሚዲያ ተቋም ያገኘነው መረጃ ይገልጻል። የቀድሞ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽነር መሞታቸው ቢረጋገጥም ፤ የሞታቸው ምክንያት ግን እስካሁን በግልፅ አልታወቀም። አቶ አበረ አዳሙ ከጥቂት ቀናት በፊት ነበር ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ኃላፊነት የተነሱት። @ShegernewsBot @ShegernewsETH
Show all...
ሱዳን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ይገባኛል ማለቷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኮነነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። በሳምንታዊ መግለጫቸውም የታላቁ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ በሱዳን በኩል የተጣረሱ መረጃዎች እየወጡ ነው ብለዋል። በሱዳን በኩል ከዚህ በፊት ወደ ኢትዮጵያ ድንበር መግፋቷ ሳያንስ አሁን ደግሞ የታላቁ የህዳሴ ግድብ እየተገነባ ያለበትን የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል ይገባኛል ማለቷ ያልተገባ ተግባር ነው ብለውታል ቃል አቀባዩ። የሶስቱን ሃገራት ድርድር በተመለከተ ኢትዮጵያ ባላት አቋም እንደጸናች መሆኗንም ገልጸዋል። በሌላ በኩል ባሳለፍነው ሳምንት ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ ለእስያ አምባሳደሮች በኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ፣ በታላቁ ህዳሴ ግድብ እና በትግራይ ክልል እየተከናወነ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍ ማብራሪያ ተሰጥቷል። በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ረገድም የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል ነው የተባለው። ስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫን በተመለከተ የሃገሪቱን የምርጫ ህግ ተከትሎ ነጻ ገለልተኛ ምርጫ እንዲሆን እየተሰራ ነው ብለዋል አምባሳደር ዲና። የመራጮች ምዝገባም በጅማሬው ወቅት ካሳየው መቀዛቀዝ መውጣቱንም ጠቅሰዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በአፍሪካ ምርጡ 10ኛ ዩኒቨርሲቲ ተባለ! ዩኤስ ኒውስ ግሎባል ዘንድሮ ባወጣው ደረጃ መሰረት ዩኒቨርሲቲው ከአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች 10ኛ ደረጃ ሲይዝ በምስራቅ አፍሪካ ደግሞ ቀዳሚ ሆኗል። በዓለም ላይ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች አንጻር ደግሞ 553ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ባለፈው አመት ኒውስ ግሎባል ባወጣው ደረጃ ከምስራቅ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች 2ኛ እንዲሁም ከዓለም 616ኛ ደረጃ ላይ የነበረው ዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ ደረጃውን አሻሽሏል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
ጠ/ሚ ዐቢይ  የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ  ታያቸው የትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማዕድ አጋሩ ። በአንድነት ፓርክ በተካሄደው የማዕድ ማጋራት ላይ አረጋውያን ፣ አርበኞች ፣ አካል ጉዳተኞችና ችግረኛ  ታዳጊዎች ታድመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩና ቤተሰባቸው በዓሉን በታላቁ  ቤተ መንግሥት  አንድነት ፓርክ  ውስጥ ከ210 ዜጎች ጋር  አሳልፈዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
በአራዳ ክፍለ ከተማ የመጀመሪያው የምገባ ማዕከል ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቆ ሥራ ጀመረ፡ “የተስፋ ብርሃን ምገባ ማዕከል” በሚል ስያሜ ወደ ስራ የገባው ማዕከል ከ800 በላይ የሚሆኑ አቅም የሌላቸው ነዋሪዎችን በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የሚያስችል ነው ተብሏል። በከተማዋ ወደ መሰል ስራ ለመግባት በሂደት ላይ ካሉ 5 ማዕከላት መካከል አንዱ የሆነው ይህ ማዕከል የመመገቢያና እና የማብሰያ ቦታዎችን አካቶ የተገነባ ነው። አንድ መቶ ሺህ የሚደርሱ ዜጎች በቀን አንድ ጊዜ እንኳ መመገብ የማይችሉ መሆናቸው በጥናት በመረጋገጡ በሂደት ሁሉንም ወደ ምገባው ለማምጥትና በቀን አንድ ጊዜ የነበረውን ወደ ሁለት ለማሳደግ እንደታቀደ ተገልጿል። በማዕከሉ የሚካሄደውን የምገባ መርሃ ግብር ፈቃደኛ ባለሃብቶችና ሆቴሎች እ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የሚኒስትሮች ምክር ቤት “ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)” እና “ሸኔ” በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሃሳብ አሳልፏል:: የምክር ቤቱ መግለጫ እንደሚያስረዳው በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ሲፈጸሙ የቆዩት ጥቃቶች የተለያዩ ፈጻሚ አካላት ነበሯቸው። ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)እና “ሸኔ” ሲፈጸሙና ሲያስፈጽሙ የቆዩዋቸው የጥፋት ተግባራት የሽብር ወንጀል ተግባራት መሆናቸው ገልጿል። እነዚህ ተግባራት የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ሥር ስለሽብር የወንጀል ድርጊት የተሰጠውን ትርጓሜ ሙሉ ለሙሉ የሚያሟሉ ተግባራት እንደሆኑ በቀላሉ ለመገንዘብ ይቻላል ብሏል። ስለዚህ የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 18 እና 19 መሠረት “ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት)” እና “ሸኔ” የሽብር ወንጀልን ዓላማቸው አድርገው የሚንቀሳቀሱ በመሆኑና የድርጅቶቹ የሥራ አመራር ወይም ውሳኔ ሰጭ አካላት ወንጀሉን አምነው የተቀበሉት ወይም አፈጻጸሙን እየመሩት በመሆኑ፤ የሽብር ተግባር መፈጸምም የድርጅቶቹ ጠቅላላ መገለጫ በመሆኑ፤ ድርጅቶቹ በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ቀርቧል ነው ያለው። እንዲሁም የሽብር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በወጣው ዐዋጅ ቁጥር 1176/2012 አንቀጽ 23 መሠረት በተመሳሳይ ተግባር በተሰማሩ እና በዚህ ውሳኔ ሐሳብ መሠረት ከተሰየሙት የሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ትብብር፤ ትሥሥር ወይም የሐሳብ እና የተግባር ዝምድና ያላቸው ድርጅቶችና ግለሰቦች ላይም ይህ ውሳኔ ሐሳብ ተፈጻሚ ይሆናል ብሏል ምክር ቤቱ በመግለጫው። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
የስቅለት በዓል በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው የስቅለት በዓል በክርስትና ዕምነት ተከታዮች ዘንድ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ ነው፡፡ በዓሉ በክርስትና እምነቶች በስግድት እና በፀሎት ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በስግደትና በየጾም የስቅለት በዓል የሚታወስ ሲሆን በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት በተለያዩ ስነ-ስርዓቶች ተከብሮ ይውላል፡፡ በዓሉ በተለያዩ ቤተክርስቲያኖች በሚካሄዱ መንፈሳዊ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅን ለማዳን ሲል የተቀባላቸውን መከራዎች ለማስታወስ መንፈሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በዓሉ በሌላው አለም በሚገኙ የክርስቲያን ማህበረሰብ ዘንድ በመከበር ላይ ይገኛል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...
አዲስ የዩኒቨርስቲ ገቢ ተማሪዎች ምደባ ተለቀቀ። የ2013 ትምህርት ዘመን የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ላመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከዛሬ ሚያዝያ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይፋ ሆኗል። በመሆኑም ተማሪዎች ከታች በተገለጸዉ የበየነ መረብ ጠቋሚ በመግባት የተመደቡበትን ተቋም ማወቅ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ ዩኒቨርሲቲዎች እስከ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት አድርገው የመጀመሪያ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎች አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትቆዩ እናሳስባለን፡፡ • ዉጤት ለማየት መግቢያ ዌብሳይት፡- http://result.neaea.gov.et/Home/Placement • ቅሬታ ለማቅረብ መግቢያ ዌብሳይት (በአካል መምጣት አያስፈልግም)፡- http://moshe.gov.et/ ወይም https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7 @shegernewsbot @shegernewsETH
Show all...