Add channel
  • Support
Stay updated with our news!
Additional features

Use telemetr_io_bot to learn more about your audience

  • Telegram official statistics
  • Gender of subscribers
  • Channel audience core
  • Distribution by language
  • Detailed subscriber activity
  • Subscriptions / unsubscriptions by hour
  • *The function is available only to channel owners
Channel location and language
የሚያምኑት መረጃ!! እጅግ ፈጣንና ዘመናዊ በሆነ የመረጃ አሰጣጣችን ይረካሉ አሁኑኑ የቤተሰባችን አባል ይሁኑ   #ሸገር   የናንተ #ሸገር የኛ 
86 314-162
~8 887
~5
10.28%
Telegram general rating
Globally
9 782place
of 1 674 904
31place
of 939
In 
39place
of 826
Entertainment
|
39 of 826
Humor
|
34 of 725
Entertainment
|
2 of 17
Humor
|
1 of 19

Subscribers gender

Find out how many male and female subscibers you have on the channel.
?%
?%

Audience language

Find out the distribution of channel subscribers by language
Russian?%English?%Arabic?%
Channel growth
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

User lifetime on the channel

Find out how long subscribers stay on the channel.
Up to a week?%Old Timers?%Up to a month?%
Subscribers gain
ChartTable
D
W
M
Y
help

Data loading is in progress

የጤና ቀውስ የሚያስከትሉ መድኃኒቶች በህገ ወጥ መንገድ እየተሰራጩ ነው:: ከፍተኛ የጤና ቁውስ የሚያስከትሉ መድኃኒቶች በህገ ወጥ መንገድ እየተሰራጩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ ህብረተሰቡ በተሳሳተ ግንዛቤ ከውጭ የሚገቡትን መድኃኒቶች ጥራታቸው ሃገር ውስጥ ከሚመረቱት የተሻሉ ነው ብሎ እንደሚያምን ጠቅሰው እውነታው ግን ከዚህ ይለያል ነው ያሉት። በዓለም አቀፍ ደረጃ በአደገኝነት የተፈረጁ ምንም ፈዋሽ ንጥረ ነገር የሌላቸው ወይም የተሟላ ፈዋሽ ንጥረ ነገሮች የሌሏቸው መድኃኒቶች በህገ ወጥ መንገድ በአዲስ አበባ ከተማ ጭምር እየተሰራጩ መሆናቸውን አመልክተዋል። ችግሩን ለመቅረፍ በተደረገው ጠንካራ የቁጥጥር ሥራ ንጥረ ነገሮቻቸው ከደረጃ በታች የሆኑ መድኃኒቶች በሃገሪቱ ስምንት በመቶ መሆናቸውን ነው ያስረዱት፡፡ እነዚህ መድኃኒቶች በድንበርና በአየር መንገድ በኩል በህገ ወጥ መንገድ እንደሚገቡ አስረድተዋል፡፡ ነጋዴዎቹ ህገወጥ መድኃኒቶች በድብቅ በስልክና በማህበራዊ ትስስር ገጾች በሚስጥር እያሰራጩ በመሆናቸው ለመቆጣጠር ከባድና ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ጉዳይ ባለመሆኑ የሁሉም ህብረተሰብ ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ዳይሬክተሯ አሳስበዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
1 783
3
ኢትዮጵያ የስፖርት ውርርድ ከተስፋፋባቸው አምስት የአፍሪካ አገራት አንዷ ሆነች። የስፖርት የኦንላይን ውርርድ በአፍሪካ ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ እየተስፋፋ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ገቢ እያስገኘለት እንደሆነ ይህንን ስራ በበላይነት የሚያስተዳድረው ኤን ሶፍት አስታውቋል፡፡ በአፍሪካ ውስጥ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ገቢ እያገኘ ያለው ከደቡብ አፍሪካ እንደሆነ የገለፀው ድርጅቱ ሌሎች አገራት ውስጥ ይህ ቁማር በመስፋፋቱ ዘንድሮ ሌሎች አገራት ደቡብ አፍሪካን ሊበልጡ እንደሚችሉ አስረድቷል፡፡ ኔን ሶፍት ለዘንድሮ ማለትም የ2021 ገበያው አምስት አገራት ላይ እንዳነጣጠረም ገልጿል፡፡ እነዚህ አምስት አገራትም ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ዚምቡዋዌ፣ ሌሶቶና ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ የድርጅቱ የአፍሪካ ገበያ ሴልስ ማኔጀር ማርኮ ዶዚች በሰጡት መግለጫ ሲናገሩ ‹‹የገበያ ጥናት አድርገንና ያለውን አቅም ተረድተን በኢትዮጵያ ውስጥ ወኪሎችን ማሰራት የጀመርነው ከሴፕቴምበር 2019 አንስቶ ነበር፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ያለው የኢንተርኔት ግንኙነት ደካማ መሆኑን በመረዳታችን ለወኪሎቻችን በጣም አስገራሚ የድረ ገፅ ኮድ ሰጥተን እንዲሰሩ ለማድረግ ችለናል፡፡ ይህ ደግሞ ውጤታማ ያደረገን ከመሆኑም በላይ አሁን አዳዲስ ፕሮጀክቶችን ለማስተዋወቅ እየሞከርን እንገኛለን›› ብለዋል፡፡ Via Fidel Post @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
2 359
1
ለስድስተኛ ጊዜ ምርጫ ያሸነፉት የቻድ ፕሬዝደንት ኢድሪስ ዴቢ ተገደሉ! ፕሬዝደንቱ በአማጺያን ጥቃት መገደላቸውን የሀገሪቱ መከላከያ በብሔራዊ ቴሌቪዥን አስታውቋል፡፡ ፕሬዝደንቱ በውጊያው ከቆሰሉ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ነው ህይወታቸው ያለፈው፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
5 496
3
በሶማሌ ክልል በቀጣይ አምስት አመታት የሚተገበረው አምስተኛው ዙር የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም (psnp 5) በዛሬው እለት በይፋ ተጀመራል ። መርሃግብሩን የሶማሌ ክልል የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ከፌደራል የግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በጅግጅጋ ከተማ አዘጋጅቷል፡፡ 5ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍኔት ፕሮግራም (psnp 5) ማስጀመሪያ ስነስርአት ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፤ የተለያዩ የክልሉ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ከክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮና የግብርና ሚኒስቴር ሀላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል። በስነስርአቱ ላይ ተገኝተው በክልሉ በቀጣይ አምስት አመታት የሚተገበረውን 5ኛውን ዙር የልማታዊ ሴፍኔት ፕሮግራምን በይፋ ያስጀመሩት የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ናቸው:: በክልሉ ባለፉት አምስት አመታት የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ህብረተሰቡን በማሳተፍ የአፈርና የውሀ ጥበቃ ስራዎች በማከናወን ፤ የመንገድ ጥገናና የተለያዩ አገልግሎት መሰጫ ማዕከላትን በመስራት መርሀግብሩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ተናግረዋል። ባለፉት አምስት አመታት ተግባራዊ ሲደረግ በቆየው 4ኛው ምዕራፍ የልማታዊ ሴፍኔት ፕሮግራም አፈፃፀም የታዩ ክፍተቶችን በማሻሻል በቀጣይ ፕሮግራሙን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ለቀጣይ አምስት አመታት ተግባራዊ የሚደረገው 5ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሁም ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላቶች በቁርጠኝነት እንዲንቀሳቀሱ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል። በስነስርአቱ ላይ የ4ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም አፈፃፀምና ቀጣዩ 5ኛው ዙር የፕሮግራሙ እቅድ ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
5 713
1
4 876
0
የትራፊክ ቅጣትን በሞባይል ስልክ መክፈል የሚያስችል መተግበሪያ ይፋ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክትር አቶ ጅሬኛ ሂርጳ የትራፊክ ቅጣት መተግበሪያው የደንበኞችን እንግልት የሚቀንስ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ይህም በከተማው ያለውን የትራፊክ እንቅሰቃሴ ፍሰት ሰላማዊ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል፡፡ የቅጣት መተግበሪያው በኢ-ብር አማካኝነት በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የሚከፈል መሆኑን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የአገልገሎት አሰጣጡ ላይ ግንዛቤ ፈጠራ ስራ ይሰራል ተብሏል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ በዓመት ከ700 ሺህ በላይ የትራፊክ ቅጣቶች እንደሚመዘገቡም ኤጀንሲው አስታወቋል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
4 866
3
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከአውሮፓ ህብረት የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኮሚሽነር ያኔዝ ናርሲክ ጋር መከሩ፡፡ በውይይታቸው በትግራይ ክልል እየተደረገ ስላለው ሰብዓዊ ዕርዳታ ጉዳይ ማንሳታቸው ተገልጿል፡፡ የአውሮፓ ህብረት የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ኮሚሽነር በክልሉ እየተሻሻለ ስለመጣው ሰብዓዊ አቅርቦት አበረታተዋል፡፡ እንዲሁም በክልሉ ተፈጽመዋል ስለተባሉ የሰብዓብዊ መብት ጥሰቶች ዙሪያ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጋራ ለመመርመር የወሰዱትን እርምጃ አድንቀዋል፡፡ በተጨማሪም የኤርትራ ወታደሮች ከክልሉ እንዲወጡ የተወሰደው ውሳኔም የሚበረታታ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ አቶ ደመቀ በበኩላቸው በክልሉ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጠቅሰው አሁንም ቢሆን ተግዳሮቶች መኖራቸውን አንስተዋል፡፡ Via fbc @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
4 920
2
4 587
0
በኩባ ብቸኛውና አድራጊ ፈጣሪው የኩባ ኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበር ፕሬዝዳንት ሚጉኤል ዲያዝ ካኔልን ዋና ፀሐፊው አድርጎ መረጣቸው፡፡ ዋና ፀሐፊነቱ በፖለቲካ ማህበሩ ከፍተኛው የመሪነት ደረጃ ነው፡፡ የኩባ አብዮት መሪ የፊደል ካስትሮ ታናሽ ወንድም ራውል ካስትሮ የፓርቲውን ዋና ፀሐፊነት ሀላፊነት እንደሚያስረክቡ የተናገሩት ባለፈው አርብ እንደነበር ሬውተርስ አስታውሷል፡፡ ከ60 ዓመታት በላይ በሆነ ጊዜ የኩባ ኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበሩ መሪነት ከካስትሮ ቤተሰብ እጅ ወጥቷል ተብሏል፡፡ ራውል ካስትሮ ከእንግዲህ በአረጋዊ መካሪነቴ እቀጥላለሁ ያሉት በ89ኛ ዓመታቸው ላይ በሚገኙበት ወቅት ነው፡፡ ፕሬዝዳንትነቱን ወደ ማጉኤል ዲያዝ ካኔል ካስተላለፉ 3 ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ የኩባ ኮሚኒስቶች የፖለቲካ ማህበር ዋና ፀሐፊ የሆኑት ካኔል በፖሊሲ ጉዳይ ራውል ካስትሮ እንዲያማክሩኝ አደርጋለሁ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
4 897
0
በአዲስአበባ የሚገኙ አንዳንድ የግል ሆስፒታሎች የኮሮና ሕክምና ለማግኘት ለአልጋ መያዣ ብቻ እስከ ኹለት መቶ ሺሕ ብር ድረስ እንደሚጠየቁ ታካሚዎች እና የታካሚ ቤተሰቦች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። የኮሮና ሕክምና ወደሚሰጥባቸው የግል የሕክምና መስጫ ተቋማት ሄደው የታከሙ እና ቤተሰቦቻቸውን ያሳከሙ አስተያየት ሰጭዎች ሲገልጹ፣ ወደ ሆስፒታሎቹ ለሕክምና ሲያመሩ አልጋ ይዞ ለመታከም 95 ሺሕ ብር ዝቅተኛ የማስያዣ ክፍያ ሲሆን 200 ሺሕ ብር ደግሞ ከፍተኛው አልጋ ይዞ ለመታከም የሚጠየቁት የማስያዣ ገንዘብ መሆኑን ነው። የተጠቀሰው ገንዘብ እጃቸው ላይ ከሌለ የቤት ካርታ ወይንም የመኪና ሊብሬ ጭምር ለማስያዣነት እንደሚጠየቁ ተናግረዋል። ታካሚዎቹ እና የታካሚ ቤተሰቦች ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት ካስያዙት የመታከሚያ ገንዘብ በተጨማሪ ለመድኃኒት መግዣ ማለትም አንድ ጊዜ ለሚወጋ መድኃኒት እስከ 35 ሺሕ ብር አውጥተው መግዛታቸውን ጭምር ተናግረዋል። ታካሚዎቹ ወደ ጽኑ ሕሙማን ክፍል (ICU) ገብተው ሕክምናቸውን የሚከታተሉ ከሆነ ደግሞ የሕክምና ክፍያው እንደሚጨምር ገልጸዋል። በዚህ የሕክምና ሂደት እሰከ አንድ ነጥብ ኹለት ሚሊየን ብር ያወጡ የኮቪድ ታካሚ እንዳሉም አዲስ ማለዳ ለማወቅ ችላለች። በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙና የጽኑ ህሙማን ሕክምናና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ የሰው ሰራሽ መተንፈሻ መሳሪያና የኦክስጂን እጥረት እያጋጠመ መሆኑን የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የጤና ሚኒስቴር ለሕብረተሰቡ በእጂ ስልክ የጽሁፍ መልዕክት በመላክ ጭምር እያስታወቁ እንደሚገኙ ይታወቃል። ኢንስቲቲዩቱ በተጨማሪም የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መሳሪያ (ቬንትሌተር) እና የኦክስጅን እጥረት ያለበት ሲሆን የባለሙያ ድጋፍና እንክብካቤ የሚሹ የኮቪድ ታማሚዎች ቁጥር የሕክምና ማዕከላት ማስተናገድ ከሚችሉት አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን ጨምሮ ገልጿል። ይህንን ተከትሎ በመንግሥት ሆስፒታሎች ሕክምና ለማግኘት ባለመቻላቸው ወደ ግል ሆስፒታሎች እየሄዱ የሚታከሙ የኮቪድ ታማሚዎች አልጋ ለመያዝ ብቻ በትንሹ ከመቶ እስከ መቶ ሀምሳ ሺሕ ብር ድረስ እንደሚጠየቁ ታካሚዎቹ ተናግረዋል። አዲስ ማለዳ ለሥራ በተዘዋወረችባቸው ቦታዎች ኅብረተሰቡ በኮሮና ላለመያዝ የሚያደርገው ጥንቃቄ የበሽታውን አስከፊነት እንዲሁም በበሸታው ከተያዙ በኋላ ሕክምና ለማግኘት ያለውን ውጣ ውረድ ያላገናዘበ መሆኑን ታዝባለች። የኮሮና ሕክምና መስጫ የሆኑ ተቋማት አካባቢ ያለው የሰው መጨናነቅ እና በሕክምና መስጫ ስፍራው ደግሞ በእርግጠኝነት የኮሮና ቫይረስ የተያዙ ታካሚዎች መኖራቸው እየታወቀ የሚደረገው ጥንቃቄ ቸልተኝነት የተሞላበት መሆኑንም አዲስ ማለዳ ታዝባለች። በኢትዮጵያ ይህ ዜና እስከተሰራበት ሐሙስ ሚያዝያ ሰባት ድረስ በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 236 ሺሕ 554 ሰዎች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ፣ 3 ሺሕ 285 ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። የኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በተለይም ሳንባን የሚያጠቃ ሲሆን በበሽታው ክፉኛ ለተጠቁ ጽኑ ህሙማን ሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ (ቬንትሌተር) እና ኦክስጂን ህይወታቸውን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት በእጅጉ አስፈላጊ ናቸው። በኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎችን ህይወት ለመታደግ በአሁኑ ወቅት በአገልግሎት ላይ የሚገኙት የሰው ሰራሽ የመተንፈሻ መርጃ ቬንትሌተሮች ቁጥር ከ500 የበለጠ እንዳልሆነ መረጃዎች ያመላክታሉ። በጤና ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ዮርዳኖስ አለባቸው የግል ሆስፒታሎች ኮቪድን ለማከም ስለሚያስከፍሉት ክፍያ ምንም መረጃ እንዳልነበራቸው ገልጸው፣ አገራችን ግን በነጻ ገበያ ኢኮኖሚ መመራቷን ከግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርብናል ብለዋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
6 180
12
5 670
0
የክልሉን ሰላም እና ደኅንነት ለማስጠበቅ በየአካባቢው ልዩ የጸጥታ ስምሪት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል የሰላምና ሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ገለጸ፡፡ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች በንጹሐን ላይ ሞት፣ በንብረት ላይ ውድመት እና በክልሉ ሰላም ላይ ስጋት አጥልቶ ሰንብቷል፡፡ ከጥቃት ያመለጡትም ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ወደ የተለያዩ አካባቢዎች ሸሽተዋል፡፡ ክልሉን ወደ ነበረበት ሰላም ለመመለስ በየአካባቢው የጸጥታ መዋቅር ተሰማርቷል ያሉን የክልሉ ሰላም እና የሕዝብ ደኅንነት ቢሮ ኀላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ በሰሜን ሽዋ ዞን አካባቢ የተፈጠረውን ችግር ለመቆጣጠር ከክልሉ እና ከፌደራሉ የጸጥታ ኀይል የተውጣጣ ኮማንድ ፖስት ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል፡፡ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ አካባቢ ተጨማሪ የክልሉ የጸጥታ ኀይል ወደ ቦታው አቅንቷል ያሉት አቶ ሲሳይ ትናንት ግጭቶች ቢኖሩም የጸጥታ ኀይሉ ችግሩን እየተቆጣጠረው ነው ብለዋል፡፡ የተዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ እና በከተማዋ አካባቢ የመሸጉ ሥርዓት አልበኞችን ከሕዝቡ ጋር እየለዩ መሆኑን አቶ ሲሳይ ዛሬ ለአሚኮ በሰጡት መረጃ ገልጸዋል፡፡ በክልሉ የገጠመው ወቅታዊ የጸጥታ ችግር በሽብር ቡድኖች ክልሉ ሰላማዊ ሆኖ እንዳይቀጥል ታስቦበት የሚሠራ በመሆኑ ሕዝቡ ይህንን በመረዳት ከጸጥታ ኀይሉ ጎን በመቆም የአካባቢውን ደኅንነት እንዲያስጠብቅ አቶ ሲሳይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ Viaአሚኮ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
7 519
4
የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር በወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጠ በዚህም በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት በንጹሃን ዜጎች ላይ የህይወት እና ንብረት አደጋ ባደረሱ የጥፋት ቡድኖች ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን መከላከያ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡ በመግለጫውም የኢፌዴሪ የመከላከያ ሰራዊት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ትግራይ ክልል ውጤታማ ህግ የማስከበር ተልእኮውን በጀግንነት በመፈጸም ላይ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የጸጥታ ችግሮች እየተስተዋሉ ይገኛል ብሏል፡፡ ይህ ሆን ተብሎ የሰራዊቱን ህገ መንግስታዊ ተልእኮ ለማስተጓጎል ታስቦ የተሰሩ የጥፋት ሴራዎች በሰላም ወዳዱ ህዝባችን እና በመከላከያ ሰራዊታችን የተቀናጀ ስራ ሊከሽፍ ችሏል ነው ያለው። 1ኛ በመተማ መስመር ለዘመናት አብረው በኖሩ የቅማንት እና የአማራ ተወላጆች መካከል የተፈጠሩ የጸጥታ ችግሮችን የፌደራል እና የክልል የጸጥታ ሃይሎች ከህብረተሰቡ እና ከአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች ጋር የተቀናጀ ስራ በመስራት የተከሰቱ የጸጥታ ችግሮን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ይገኛል ፡፡ በወለጋ ቡሬ መስመር በጊዳ አያና አንገር ጉቴ አዋሳኝ አካባቢዎች ለረዥም ጊዜ አብሮ በኖሩ የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎችን ሆን ብሎ ለማጋጨት ታስቦ የተደረገው ሙከራ በአካባቢው ህብረተሰብ ትብብር ወደ ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ ተችሏል ብሏል መግለጫው። እንደዚሁም የኢትዮጵያን የገቢ እና ወጪ የንግድ እንቅስቀቃሴን ለመገደብ በማሰብ በሱማሌ እና የአፋር ኢሳ ህዝቦችን ለማጋጨት የተሰራው ሴራ በሰላም ወዳዱ ህዝባችን የተቀናጀ ተሳትፎ በቁጥጥር ስር ለመዋል ተችሏልም ነው ያለው፡፡ ሌላው ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ እና በደቡብ ወሎ የኦሮሞ ልዩ ዞን ወረዳዎች በተለይም በዚህ ሁለት ሶስት ቀን በአጣዬ ከተማ እና በአካባቢው በታጠቁ ሃይሎች በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ በደረሰው ውድመት የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጸ በዚህ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች መጽናናትን ይመኛል ብሏል፡፡ በዚህ የጸጥታ ችግር ተሳታፊ የሆኑ ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር የማዋል እና መሳርያ ይዘው በጸጥታ አካላት ላይ ተኩስ የከፈቱ የሰራዊቱን እንቅስቃሴ የገደቡ ጸረ ሰላም ሃይሎች ላይ ሰራዊታችን እርምጃ መውሰድ መጀመሩን እየገለጽን÷ መንገድ መዝጋትን ጨምሮ የህብረሰተቡን ሰላም በማወክ ላይ የተሰማሩ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ሚኒስቴሩ በጥብቅ ለማሳሰብ ይወዳልም ብሏል መግለጫው፡፡ በዚህም መሰረት በሰሜን ሸዋ እና በደቡብ ወሎ የኦሮሞ ልዩ ዞን ወረዳዎች ከተከሰተው የጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ከክልል እና ከፌዴራል የጸጥታ ተቋማት ጨምሮ ሶስቱንም ዞኖች ያካተተ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን ሚኒስቴሩ አመላክቷል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ የአካባቢውን ጸጥታ በማደፍረስ ስራ ላይ በተሰማሩ የጥፋት ቡድኖች ላይ እርምጃ በመውሰድ የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራን ይሰራልም ነው ያለው፡፡ በዚህም መሰረት የአካባቢውን ሰላም ወደ ነበረበት ለመመለስ ሲባል የሚከተሉት ክልከላዎች የተደረጉ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ ይገልጻል፡፡ 1ኛ ከደብረ ሲና እስከ ኮምቦልቻ አዋሳኝ ወረዳዎች መንገድ ላይ ከመንገዱ ግራ እና ቀኝ እስከ 20 ኪ/ሜ ውስጥ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ 2ኛ መንገድ መዝጋትን ጨምሮ አብያተ ክርስቲያናትን እና የመንግስት ተቋማትን የግለሰብ መኖርያ ቤትን እና ንብረት ማውደም ወይም ለዚህ ተግባር በተናጥልም ይሁን በቡድን መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ ከላይ የተዘረዘሩትን እና ቀጣይ በኮማንድ ፖስቱ ለህብረተሰቡ የሚገለጹ ክልከላዎችን ተላልፎ የተገኘ የፖለቲካ ድርጅት የመንግስት መዋቅር እና በድኖች ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑን መታወቅ አለበት ብሏል፡፡ በመጨረሻም መላው ህብረተሰባችን እንደወትሮው ሁሉ ከጸጥታ ተቋማት ጎን በመሰለፍ ለገሀራችን ሰላም እና ደህንነት የበኩሉን ገንቢ ሚና እንዲጫወት ጥሪያችንን እናቀርባለን ፡፡ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስቴር @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
8 122
14
7 391
1
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በተፈፀመ ጥቃት ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውን ተገለጸ:: የዞኑ የጸጥታ ኃላፊ አቶ አበራ መኮንን ለቢቢሲ እንደገለፁት ጥቃቱ የተፈፀመው በዞኑ በሚገኙ 5 ወረዳዎች ውስጥ ነው። ኃላፊው ጨምረውም "በጣም ከፍተኛ" ቁጥር ያለው የታጠቀ ኃይል "ወረራ" መፈፀሙን ተናግረዋል። የታጠቀው ኃይል " ቤቶችን ያቃጥላል፤ ሰዎችን ይገድላል" በማለትም ወደ አካባቢው የገባው የፌደራል የጸጥታ መዋቅርና የመከላከያ ሰራዊትም "ከአቅሙ በላይ" መሆኑን ለቢቢሲ አስረድተዋል። የአማራ ክልል መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ለክልሉ ሚዲያ በጥቃቱ የደረሰው ጉዳት የከፋ መሆኑን ገልፀዋል።ለጥቃቱም 'ኦነግ ሸኔ እና ሌላ 'ተከታይ' ያሉትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።በጥቃቱ የፀጥታ አካላት መዋቅርም ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አክለዋል። ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ማታ ጀምሮ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን እና ሰሜን ሸዋ መካከል በሚገኙ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር መኖሩን ገልፀው፤ ይህ ግን ጋብ ብሎ እንደነበር ኃላፊው አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ ትናንት ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ ከፍተኛ የታጠቀ ኃይል ወደ አካባቢው በመግባት ጥቃት በመግባት በአጣየ፣ አንጾኪያና ኤፍራታ ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን ተናግረዋል። ©BBC @Shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
9 618
13
የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ መሰረታዊ የምግብ ፍጆታዎች ያለውጭ ምንዛሬ ፈቃድ እንዲገቡ መፈቀዱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አስታወቁ፡፡ የንግድና ኢንዱስትሩ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ስኳር፣ምግብ ዘይት፣ስንዴ፣ሩዝ፣የዱቄት ወተት ከውጭ ሀገር እንዲገቡ መወሰኑን በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡ በዚህም 250 ሺህ ዶላር (የውጭ ሀገር ገንዘብ) ያላቸው ምንጩን በብሔራዊ ባንክ እያረጋገጡ ማስገባት ይችላሉ ነው ያሉት፡፡ Via fbc @shegernewsbot @shegernewsETH
11 590
11
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጅማ የሚያደርገውን በረራ ማቋረጡን ገልጿል። አየር መንገዱ በረራውን ያቋረጠው የጂማ አውሮፕላን ማረፊያ ለ ሁለት ቀናት [ሚያዝያ 11 እና 12 ቀን 2013 ዓ.ም] እድሳት ስለሚደረግለት ነው ብሏል። እድሳቱ ከተጠናቀቀ በኋላ መደበኛ በረራው ከሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ የሚቀጥል መሆኑን አሳውቋል። Via EthiopianAirlines @shegernewsbot @shegernewsETH
10 429
6
የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ማሺዲሶ ሬቤካ ሞቲን ጋር ተወያይተዋል። ውይይታቸው የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት፣ የጤናና የሰላም ጥብቅ ቁርኝት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። ሚኒስትሯ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ጤናን ጨምሮ እየተከናወነ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍና ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት ላይ ገለጻ አድርገዋል። አክለውም የዓለም ጤና ድርጅት፣ ሌሎች የተባበሩት መንግስታት ፕሮግራሞች እና በአጠቃላይ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ አዳጋች ሁኔታዎች በገጠማት ጊዜ ሁሉ ለሚያደርጉት እገዛ ከልብ አመስግነዋል። ዳይሬክተሯ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያን የመሰረታዊ ጤና አጠባበቅ አገልግሎት ሽፋን ለበርካታ አመታት ሲከታተሉት የቆየ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። በአጭር ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ የተሻሻለ ዘርፍ መሆኑ ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ እንደሆነም ተናግረዋል። በመጨረሻም በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች የኮቪድ-19 ክትባት እንዲደርስ በመደረጉ በተባበሩት መንግስታት እና በሰራተኞቹ ስም ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
Show more ...
9 098
3
የኢትዮጵያ የወቅቱ አቋም በግድቡ ውሃ ሙሌት እና በሙሌቱ አስተዳደር ላይ ብቻ መነጋገር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ቃል አቀባዩ ባሳለፍነው ሳምንት የግድቡ ተደራዳሪ ሶስቱ ሃገራት ወደ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በማቅናት ያደረጉት ድርድር በፍላጎት መለያየት ሳቢያ ያለስምምነት መጠናቀቁን አስታውሰዋል፡፡ ኢትዮጵያ ለድርድሩ ወደ ኪንሻሳ የሄደችው እንደተለመደው “የአፍሪካውያን ችግር በአፍሪካውያን ብቻ ይቀረፋል” በሚለው የዲፕሎማሲ መንገድ ማመኗን ለማረጋገጥ ነውም ብለዋል፡፡ ይህ ደግሞ “ወንዙም የአፍሪካውያን ነው” ከሚል የጋራ እሳቤ የሚመነጭ ነው ያሉት ቃል-አቀባዩ፥ ጉዳዩን ከአፍሪካ ህብረት ማዕቀፍ ለማራቅ የሚደረገውን ጫና ኢትዮጵያ ፈፅሞ እንደማትቀበል ገልፀዋል፡፡ ሆኖም ግብፅ ራሷ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ከነበረችበት ወቅት ጀምሮ አሁን ህብረቱ በኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሊቀመንበርነት እስከሚመራበት ጊዜ ድርድሩን ወደራሷ ወደጅ ሃገራት ለማሸሽ እና የግል ጥቅሟን ለማስከበር ወደሚያግዟት ተቋማት ለመሳብ ያልሞከረችው መንገድ አልነበረምም ነው ያሉት አምባሳደር ዲና፡፡ ኢትዮጵያም ይህን አመለካከት ብቻ ሳይሆን “ሌሎች ወገኖችም የአፍሪካን ያህል በግድቡ ድርድር ላይ ሚና ይኑራቸው” የሚለውን ፍላጎት እንኳን እንደማትቀበል አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ ከሱዳን ጋር በተያያዘም በተለይም የሱዳን ወታደራዊ ክንፍ የውክልና ተልዕኮ ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሯ አብደላ ሃምዶክ በኩል የቀረበውን “በዝግ የእንነጋገር” ጥያቄ ኢትዮጵያ በአንክሮ እንደምትመለከተውም ጠቅሰዋል፡: ሱዳን ከድንበር ግጭት ጋር በተገናኘ በኢትዮጵያ ላይ የፈፀመችውን የመሬት ወረራ እና የንብረት ጉዳት በተመለከተ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ወዳጅ ሃገሮቿ ተፅዕኖ በመፍጠር ወደ ቀደመው የግንኙነት መንገዷ እንድትመለስ እንዲያደርጉ ኢትዮጵያ ጥሪ እያስተላለፈች መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ በትግራይ ክልል ካለው ሰብዓዊ ድጋፍ ጋር በተያያዘም ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቅሰው፥ “መንገድ ክፈቱልን” ሲሉ የነበሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መንገድ ሲከፈት ከአሜሪና ከተወሰኑ ሃገራት ውጪ ባዶ እጃቸውን መሆናቸውን መመልከት እንደተቻለ አስረድተዋል፡፡ በሶዶ ለማ @shegernewsbt @shegernewsETH
Show more ...
8 406
5
7 540
0
12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያመለጣቸው በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምሀርት ቤት ተማሪዎች መፈተናቸውን ሸገር ሰምቷል፡፡ በኮሮና ቫይረስ መከሰት ምክንያት ተራዝሞ የነበረው የ2012 የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወር በፊት መስጠቱ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ በሪያድ የሚገኘውና በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የሚያስተምረው የኢትየጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎችም አብረው መፈተን ነበረባቸው፡፡ ነገር ግን ፈተናው በወቅቱ ስላልተላከላቸው እንዳመለጣቸው እና ይህም ወላጆችንና ተማሪዎችን ለኢኮኖሚያዊ ስነ ልቦናዊ ጫና ዳጓቸው እንደነበር በቀደመ የወሬ ጊዜያችን ነግረናችኋል፡፡ የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ድርጅትም ከ2013 ተፈታኞች ጋር እንዲፈተኑ አደርጋለሁ ብሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይሁንና ድርጅቱ በቅርቡ ለተማሪዎቹ አዲስ ፈተና አዘጋጅቶ በመላክ ካለፈው ሚያዚያ 3 ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ እንደ ፈተናቸው የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር አቶ አበበ ጫላ ለሸገር ተናግረዋል፡፡ ኤጀንሲው የፈተና ጣቢያ ሀላፊ መድቦ ተማሪዎቹ ፈተናቸውን በሰላም ማጠናቀቃቸው ሰምተናል፡፡ ከወር በፊት በኢትዮጵያ ሃገር አቀፍ ፈተናውን የወሰዱት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥባቸውን ማወቃቸው ይታወሳል፡፡ ትናንት ፈተናቸውን ያጠናቀቁት የሪያድ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎችም ፈተናቸው ታርሞ የማለፊያ ነጥብ የሚያገኙት ከወር በፊት ከተፈተኑት ጋር ዩኒቨርስቲ ይገባሉ ተብሎ ይታመናል ብለውናል አቶ አበበ፡፡ ትዕግስት ዘሪሁን @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
7 875
0
7 884
4
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በ18 ከተሞች ውስጥ የከተማ መሬት ፋይል የማደራጀት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ ሚኒስቴሩ የከተሞችን ፋይል የማደራጀት ስራ ለመስራት በዓለም አቀፍ ጨረታ ኤ.ኤች.ሲ ከሚባል የዩጋንዳ አማካሪ ድርጅት ጋር ውል በመያዝ ወደ ትግበራ የተገባ ነው፡፡ ስራው በዋናነት ማዕከል የሚያደርገው የተሟላና በኮምፒዩተር የታገዘ የከተሞች የመሬት ይዞታ እና መሰረታዊ የማዘጋጃ ቤት ገቢ የፋይል አያያዝ ስርዓትን የማጎልበት ስራ ነው፡፡ በዚህ ማዕቀፍ በሌሎች የፋይል መልሶ ማደራጀትና የቅድም-ይዞታ ማረጋገጥ ስራዎችን የማገዝ፣ የንብረት መብት ምዝገባ ሂደትን ለማቀላጠፍ እና ለማፋጠን ከመሬት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስራዎችን በሚፈለገው ጥራትና በወቅቱ ለማከናወን የሚረዳ ስርዓትን የመፍጠር እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት ገቢ አስተዳደር ተቋማትን ለመደገፍ እንደ ግብዓት ሆኖ የሚያገለግል ስርዓት ለመፍጠር ይሰራሉ፡፡ አማካሪ ድርጅቱም በሀረሪ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በደቡብ እና በሲዳማ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ከተሞች እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በ18 ከተሞች ውስጥ 630 ሺህ የሚሆኑ የመሬት ፋይሎችን በብሎክ የማደራጀት ስራን ይሰራል፡፡ አማካሪ ድርጅቱም ለካዳስተር ስራም ዝግጁ እንዲሆኑ የማድረግ ስራን ጨምሮ፤ ፋይሎችን ስካን በማድረግ መረጃውን በኮምፒዩተር በማደራጀት ዳታ ቤዝ ውስጥ በማስገባት ዘመናዊና የተቀላጠፈ አሰራር እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ይህም ከዚህ በፊት በመሬት ሃብት አያያዝ ዙሪያ ይስተዋል የነበረውን አግባብ ያልሆነ የመረጃ አያያዝ ለማስቀረት ቁልፍ መሳሪያ እንደሆነ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መስፍን አሰፋ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
9 478
2
8 129
0
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በ18 ከተሞች ውስጥ የከተማ መሬት ፋይል የማደራጀት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡ ሚኒስቴሩ የከተሞችን ፋይል የማደራጀት ስራ ለመስራት በዓለም አቀፍ ጨረታ ኤ.ኤች.ሲ ከሚባል የዩጋንዳ አማካሪ ድርጅት ጋር ውል በመያዝ ወደ ትግበራ የተገባ ነው፡፡ ስራው በዋናነት ማዕከል የሚያደርገው የተሟላና በኮምፒዩተር የታገዘ የከተሞች የመሬት ይዞታ እና መሰረታዊ የማዘጋጃ ቤት ገቢ የፋይል አያያዝ ስርዓትን የማጎልበት ስራ ነው፡፡ በዚህ ማዕቀፍ በሌሎች የፋይል መልሶ ማደራጀትና የቅድም-ይዞታ ማረጋገጥ ስራዎችን የማገዝ፣ የንብረት መብት ምዝገባ ሂደትን ለማቀላጠፍ እና ለማፋጠን ከመሬት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ስራዎችን በሚፈለገው ጥራትና በወቅቱ ለማከናወን የሚረዳ ስርዓትን የመፍጠር እንዲሁም የማዘጋጃ ቤት ገቢ አስተዳደር ተቋማትን ለመደገፍ እንደ ግብዓት ሆኖ የሚያገለግል ስርዓት ለመፍጠር ይሰራሉ፡፡ አማካሪ ድርጅቱም በሀረሪ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በትግራይ፣ በደቡብ እና በሲዳማ ክልሎች ውስጥ በሚገኙ ከተሞች እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ በ18 ከተሞች ውስጥ 630 ሺህ የሚሆኑ የመሬት ፋይሎችን በብሎክ የማደራጀት ስራን ይሰራል፡፡ አማካሪ ድርጅቱም ለካዳስተር ስራም ዝግጁ እንዲሆኑ የማድረግ ስራን ጨምሮ፤ ፋይሎችን ስካን በማድረግ መረጃውን በኮምፒዩተር በማደራጀት ዳታ ቤዝ ውስጥ በማስገባት ዘመናዊና የተቀላጠፈ አሰራር እንዲኖር ያደርጋል፡፡ ይህም ከዚህ በፊት በመሬት ሃብት አያያዝ ዙሪያ ይስተዋል የነበረውን አግባብ ያልሆነ የመረጃ አያያዝ ለማስቀረት ቁልፍ መሳሪያ እንደሆነ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር መስፍን አሰፋ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
Show more ...
7 893
0
የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታ ድርጅት (ኢጋድ) ሊቀመንበር ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር በመውረር የአፍሪካ ቀንድን ሰላምና ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ተግባር ላይ መሰማራቷ የሚያሳዝን ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሱዳን ምንም እንኳን የኢጋድ ሊቀመንበር ብትሆንም የኢትዮጵያን መሬት ወራ፣ ሰላማዊ ዜጎችን አፈናቅላ አሁንም ተጨማሪ መሬቶችን ለመውረር የጦርነት ነጋሪት እየጎሰመች ነው ብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሱዳን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል ህግን የማስከበር እርምጃ ሲሰማራ ከወረረችው የኢትዮጵያ መሬት ሰራዊቷን እንድታስወጣ እና ወደ ራሷ እንድትመለስ ጫና እንዲፈጥር በትዊትር ገጹ ላይ በማሰፈረው ፅኁፍ ጥሪ አቅርቧል ። ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 1972 የማስታወሻ ልውውጥ መሰረት የድንበር ልዩነቱን በግጭት መፍቻ መንገዶች መፍትሄ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል። @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
7 513
0
መነሻውን ባሕር ዳር በማድረግ ወደ አዲስአበባ ሲጓጓዝ የነበረ 180 ሽጉጥ እና ከ2 ሺህ 800 በላይ ተተኳሸ ጥይት በማንኩሳ ከተማ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ መነሻውን ባሕር ዳር በማድረግ ህገወጥ የጦር መሳሪያዎችን በመያዝ ወደ አዲስ አበባ ለመውሰድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ተጠርጣሪ ግለሰቦች በምዕራብ ጎጃም ዞን ጃቢጠህናን ወረዳ ማንኩሳ ከተማ ሲደርሱ ከነጦር መሳሪያቸው በቁጥጥር ስር እንደዋሉ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡ የምዕራብ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮምዩኒኬሽን ባለሙያ ዋና ሳጅን መንገሻ ይማም እንደገለጹት በተካሄደ ፍተሻ ከ2 ሺህ 800 በላይ ተተኳሸ ጥይቶች እና 180 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ በቁጥጥር ስር በዋሉት ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ዋና ሳጅን መንገሻ አመላክተዋል፡፡ Via AMMA @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
7 659
6
የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መሪዎች በዝግ እንዲወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጥሪ አቀረቡ! በታላቁ የህዳሴ ግድብ ጉዳይ ለአመታት ተደራድረው ከአንዳች ስምምነት መድረስ የተሳናቸው የኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ መሪዎች በሚቀጥሉት 10 ቀናት ተገናኝተው በዝግ እንዲወያዩ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጥሪ አቀረቡ። ካሁን ቀደም የተደረጉ ድርድሮች ወደ ስምምነት አለማድረሳቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመጋቢት 14 ቀን 2007 ዓ.ም. የሶስቱ አገሮች መሪዎች ለትብብር እና ልዩነቶቻቸውን በሰላም ለመፍታት በፈረሙት ውል መሠረት ጥያቄውን ማቅረባቸውን ጽህፈት ቤታቸው ትናንት ማክሰኞ ዕኩለ ለሊት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከግብጽ እና ሱዳን መሪዎች የተፈራረሙት “የመርሆዎች ስምምነት” (Declaration of Principles) የተባለ ውል አስረኛ አንቀጽ፤ “ሶስቱ አገራት አለመግባባቶችን በምክክር ወይም በድርድር መፍታት ከተሳናቸው ዕርቅ ወይም ሽምግልና ሊጠይቁ ወይም ጉዳዩን ወደ መሪዎቻቸው ሊመሩ ይችላሉ” ይላል። ሱዳን የውይይት ጥሪውን ያቀረበችው ይህንን አንቀጽ በመጥቀስ ነው። Via ኢትዮጵያ ኢንሳይደር @shegernewsbot @shegernewsETH
Show more ...
8 004
1
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ 232,512 ሺህ አለፉ። ባለፉት 24 ሰዓታ ከተደረገው 7,601 የላብራቶሪ ምርመራ 1,568 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ወረርሽኙ ወደ ሀገራችን ከገባ ጊዜ አንስቶ ቫይረሱ የተገኘባቸው አጠቃላይ ሰዎች 232,512 ደርሰዋል። በ24 ሰዓት ውስጥ የ 22 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 3,230 ደርሷል። የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር በእጅጉ እየጨመረ ሲሆን የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየው 967 ሰዎች በፀና ተመውብናል። @shegernewsbot @shegernewsETH
8 795
5
በምዕራብ ሸዋ ዞን ሊበን ጃዊ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ በአደጋው ሕይወታቸው ካለፉት በተጨማሪ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፡፡ የሊበን ጃዊ የትራፊክ አስተባባሪ ሳጅን ግዛቸው ዳማ እንደገለፁት አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ነቀምት ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከነቀምት ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበረ ሎንግ ቤዝ መኪና ጋር በመጋጨቱ የደረሰ ነው፡፡ በደረሰው አዳጋም ከአንድ ቤተሰብ እናትና ልጅን ጨምሮየሰባት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ከምራብ ሸዋ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ @shegernewsbot @shegernewsETH
8 689
3
Quick access by date
    Privacy Policy