cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

BÅMY squad🤞

Tiktok videos Photos📸📸 Gangsta pics🖤 Dance videos🔥🔥 Cool pics🤞🔥 Best photo edition 🔥🔥 @swagy_junior 🔥🤞 Tg acc Tictok acc @makiba95 @swagy_junior @yoniboom @abulove On tiktok😋

Show more
Advertising posts
196
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

“የሳቃችን ምንጭ” ያልነው ተዋናይ ሕይወቱ የሀዘን ጅረት ነበረ፤ ዓይኑም ሰው እንደራበው አረፈ። ለተዋናዩ ፣ ለመልከ መልካሙ ፣ ለዝነኛው ተዋናይ ታሪኩ ብርሀኑ “አረፈ” የሚለው ቃል ይገልጸዋል። ታሪኩ ብርሀኑ በእርግጥም ከዚያ የመከራ ሕይወት አረፈ። ያ መልከ መልካም ፣ የሀገራችን ፊልም አበባ ፣ የሁላችንም ሳቅ ምንጭ ትክክለኛ ሕይወቱ በመራር ሀዘን የተሞላ ነበረ ። እኛን በስራው የሚያስፈነድቀን ትንግርተኛው ተዋናይ ወደራሱ ሕይወት ሲመለስ ግን መልኩ ሌላ የማናውቀው አይነት ነበረ ። ማናችንም ስለ ስራው እንጂ ስለ ሰውየው ግድ የለንም ። ኑሯችን እንዲህ ነው ። ማናችንም ስለማናችንም ሕይወት ደንታ የለንም ። ታሪኩ በተለይ ከትዳሩ መፍረስ በኋላ ያለው ሕይወቱ ሀዘን የሞላበት ነበረ ። ትዳሩ የፈረሰበት መንገድና ተያያዥ ጉዳዮች ፣ የፊልሙ ገበያ መቀዛቀዝና ያ ተፈላጊ ተዋናይ በስራ አለመጠመዱ ታሪኩን በስነልቦና ሰብረውታል ። ብቸኝነት ጎድቶታል ። በሕዝብ ዓይን በጉጉት የሚታየው ብርቱው ተዋናይ ዓይኑ ሰው ተርቧል ። ሰው ፈልጎ ሰው አጥቷል ። እንደ መጀመሪያው ሁሉ በመጨረሻም እናቱ ብቻ ከጎኑ ነበረች ። ታሪኩ ከህመሙ በላይ ህመም የሆነበት ሰው ማጣቱና ብቸኝነቱ ነበረ ። እንደዚያ ውድ የነበረው ተዋናይ በህመምና በስሜት ስብራት ታሞ እናቱ ደሳሳ ጎጆ ውስጥ በወደቀ ጊዜ ማንም ዞር ብሎ አላየውም ። " እግዜር ይውሰድህ " ሊለው እንኳ ቤቱ የሚሄድ ወዳጅ አልነበረውም ። በዚህ የተነሳ የታሪኩ የቀንና ሌሊት ሀሳብ ዳግም ከወደቀበት ተነስቶ ሰው መሆኑን ማሳየት ነበረ ። እንደገና ከአስገራሚ ትወናው ጋር ካሜራ ፊት መቆም ነበረ ። ግን አልሆነም ። ዛሬ የታሪኩ እናት ቤት በታዋቂ አርቲስቶች ተሞልቷል ። ዛሬ ለታሪኩ አልቃሹ ብዙ ነው ። ነገ ቀብሩ ይደምቃል ። የአስከሬን ሽኝት ፕሮግራም ወጥቶለታል ። የአበባ ጉንጉን ይጎርፍለታል ። ይህ ሁሉ ግን ለታሪኩ አንዳች የሚረባው የለም ። ዛሬ ለቅሶውን ካደመቁት አርቲስቶች ጥቂቶቹ እንኳ ከጎኑ ቆመው ቢሆን ምናልባት በትዳሩ መፍረስ ፣ በሚስቱ ፣ በስራ ባልደረቦቹ ፣ በሰው እጦት ከተፋጠነው ሞቱ ማገገም ፣ ምናልባትም መዳን በቻለ ነበር ። በሰው ተከቦ ኖሮ ብቻውን ተኝቶ አለፈ ። ታሪኩ ዛሬ ከብዙ ስቃይ ነው ያረፈው ። ታሪኩ ብርሀኑ ሰው እንደሌለው ሰው ተስፋ ቆርጦ ተመልሶ እናቱ ቤት በተኛ ወቅት ከእነዚያ ሁሉ ወዳጆቹና ፈላጊዎቹ ተክለ ሆስፒታል አስተኝታ የመድሀኒትና ሙሉ የህክምና ወጪውን የሸፈነችው ተዋናይት ረቂቅ ተሾመ ብቻ ነበረች ። እኔ ይቺን ልጅ የማመሰግንበት ቃላት የለኝም ። ካሁን ቀደምም ሰው የታጣበት ቦታ ላይ እንዲሁ ሰው ሆና ተገኝታ አመስግኛታለሁ ። አሁንም በድጋሚ አመሰግናታለሁ ። በተረፈ ጥቂት ወዳጆቹ ፊልም አሳይተው ገንዘቡን ሊሰጡት ቢጠይቁት ታሪኩ ፈቃደኛ አልሆነም ። ምናልባት ብዙ ምክንያት ይኖረዋል ። አንድ ተዋናይ የቀድሞ ወዳጁ ታሪኩ ወደተኛበት ተ/ሀይማኖት አካባቢ የእናቱ ቤት ሊጠይቀው ሲሄድ አልቅሶ ነበረ የተቀበለው ። ሰው ማጣቱ የዚያን ያህል ነው ። እናንተ ግብዞች አያችሁ ዝናና ተወዳጅነትን ( በተለይ ፊልሙ መንደር ) የታሪኩን ያህል እጁ ያስገባ አልነበረም ። አሁን የእሱን ቀብር ማሳመር ሰው አያደርጋችሁም ። " ታሪኩን ብታጫውቱት ፊልማችሁ ገበያ ያገኛል " የተባላችሁና ተለማምጣችሁ ያሰራችሁት ፕሮዲዩሰሮችና የሙያ አጋሮቹ አሁን የታሪኩን ለቅሶ ተዉት ። ዓይኑ እናንተን በተራበ ጊዜ አጠገቡ አልነበራችሁም ። መታከሚያ ባጣ ጊዜ አልከፈላችሁለትም ። ዛሬ ደረታችሁን ብትደቁ ምንም አትጠቅሙትም ። ይልቅ ህሊናችሁ ከወቀሳችሁ ልጃቸውን በማስታመምና በመጨረሻም ያን ሸበላ ልጃቸውን ያጡት እናቱን " አለንልዎት " በሏቸው ። ለታሪኩ ልታደርጉ የምትችሉት የመጨረሻው ነገር እናቱን መደገፍ ነው ። ቀብር ማሳመርን ለቀብር አስፈጻሚዎች ተዉላቸው ። ወንድምዓለም ነፍስህ በሰላም ትረፍ 🙏🙏 ፀሃፊው ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ  @albotv1212    @albotv1212
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram