cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

በክርስቶስ/ In Christ

"፤ በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።" (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 1: 3) 💡የተለያዩ ሐሳቦች ካሉኣችሁ እና ትምህርቶችን፣መዝሙሮችን መላክ ምትፈልጉ @Cherill ላይ አግኙኝ።

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
201
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ለስምህ ክብር ይሁን ዘማሪ አብርሃም ሐላንቄ 🥁🥁🥁🥁🥁 🎷🎷🎷🎷🎷🎷🎷🎷🎷🎷 join and share to other @Cherinetjo71_Inchrist
Show all...
“…ጥንቃቄ ይጠብቅሃል፥ ማስተዋልም ይጋርድሃል…” ምሳሌ 2፥11 ይህን የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል አብዛኞቻችን ለብዙ አይነት ሁኔታዎች ስንጠቀም እንስተዋላለን። በአሁን ወቅትም በአለማችን ተከስቷል ስለሚባለው ቫይረስ(ኮቪድ-19) ሲነሳ ከብዙዎቻችን አፍ ቀድሞ የሚወጣው የመፅሐፍ ቅዱስ ክፍል ይህ ነው። ነገር ግን ማንኛውንም አይነት መፅሐፍ ቅዱሳዊ ቃል መጠቀማችን እኛን ትርፋማ የሚያደርገን የተፃፈበትን አላማ አውቀን ለዚያ አላማ መጠቀም ስንችል ነው። ያንን አላማ ለመረዳት ደግሞ ከክፍሉ ሙሉ ምዕራፉን ወይም ሙሉ መፅሐፉን ማንበብ ግድ ሊሆንብን ይችላል። ቃሉን ስናነብ ❓ለማን ተፃፈ? ❓ለምን ተፃፈ? የሚሉትን ጥያቄዎች አንስተን መረዳት አለብን። ❕መፅሐፍ ቅዱስ የሚተረጎም ያለበት ከገጠሙን ሁኔታዎች አንፃር ሳይሆን ከአላማው አንፃር ነው። 📖ወደ ክፍሉ ስንመለስ📖 በዚህ ስፍራ ላይ ያለውን ሃሳብ ሙሉ ምዕራፉን ከላይ ስናየው አንድ አባት ልጁን "ቃሌንና ትዕዛዜን ብትቀበል ብዙ በረከቶች ይከተሉሃል" የሚል ምክር እየመከረው እናገኛለን። በበረከቶቹ መሃልም ቁ.11 ላይ "ጥንቃቄ" እና "ማስተዋል" ይገኙበታል። 👉 ቦታው ላይ "ጥንቃቄህ ይጠብቅሃል" አይልም፤ "ጥንቃቄ ይጠብቅሃል" ነው የሚለው። እዚህ ጋር የተጠቀሰው ጥንቃቄ ተግባር ሳይሆን "ጥንቃቄ" የሚባል ሰውን መጠበቅ የሚችል ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚላክ ማንነት ነው። ማስተዋልም እንደዛው። ከእኛ ወይም ከሳይንቲስቶችና ከዶክተሮች ጥበብ ሳይሆን ከራሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ። 📖ሌላው ሃሳብ📖 ይህ ጥቅስ የሚገኘው በብሉይ ኪዳን መፅሐፍት ውስጥ ነው። ጥቅሱ በብሉይ ኪዳን ውስጥ መገኘቱ "ለማን ተፃፈ?" የሚለውን ጥያቄ እንድናነሳ ያደርገናል። ምክንያቱም በብሉይ ኪዳን ካሉት መልዕክቶች አብዛኞቹ የተፃፉት ለቤተ-ክርስቲያን ሳይሆን በስጋ ከአብርሃም ዘር ለተወለዱት ለእስራኤል ህዝቦች ብቻ ስለሆነ። እኛ ደግሞ በስጋ ከአብርሃም ዘር ያልተወለድን ከዘር፡ ከቋንቋ፡ ከነገድ ተዋጅተን በክርስቶስ በማመን ዳግመኛ የተወለድን ቤተ-ክርስቲያን ነን። ስለዚህ ጥቅሱን ለቤተ ክርስቲያን ከተላኩት ከአዲስ ኪዳን መፅሐፍት አንፃር ማየት አለብን። ✍️ በሌላ አቅጣጫ ስናይ በብሉይ ዘመን የነበሩ እስራኤላዊያን ያስቆጥሩ የነበሩት የራሳቸውን የስራ ውጤት ነበር። መልካም ከሰሩ መልካም ያገኛቸው ነበር፤ ክፉ ከሰሩ ክፉ ያገኛቸው ነበር። ምክንያቱም እነርሱ የተቀበሉት ፀጋን ሳይሆን ሕግን ነው። ስለዚህ ከክፋት የሚጋርዳቸው መልካሙ ስራቸው ነው። ቤተ-ክርስቲያንን ግን የሚጠብቃትም የሚጋርዳትም መልካም ስራዋ ሳይሆን ያድነኛል ብላ የተማመነችበት ኢየሱስ ነው። ✍️ በመጨረሻም በሽታን እንደ መፅሐፍ ቅዱስ ካየን አንድ ማሰብ ያለብን ነገር የበሽታ ምንጭ አለመጠንቀቅ ሳይሆን ሐጢአት ነው። ያ ሀጢአት ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ደም ተወግዶልናል። “…በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።” (1ኛ ጴጥ 2፥24)(ኢሳ 33:24)(ማር 16:17-18) 👉 መጠንቀቅ ካለብን መጠንቀቅ ያለብን ባለመጠንቀቅ ከሚመጣ ነገር ነው። ከምን ከምን መንጠነቀቅ እንዳለብን መስማት ያለብን ከእግዚአብሔር ከራሱ ነው። 🤔"ተጠንቀቁ" የምትለውን ትዕዛዝ ከመፅሐፍ ቅዱስ ከተቀበልን የምንጠነቀቅበትንም መንገድ መቀበል ያለብን ከራሱ ከመፅሐፍ ቅዱስ ነው‼️ 💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠💠 ኢየሱስ በምድር ላይ ሲመላለስ ይፈውስ የነበረው ጥንቃቄን መሰረት አድርጎ ሳይሆን እምነትን መሠነት አድርጎ ነው።(ማር 5:36)(ማር 9:23) "እርሱ ይፈውሰናል" ብለው የሚያምኑትን ሁሉ ያለምንም ሌላ ምክንያት ይፈውሳቸው ነበር።(ማቴ 14:36) አሁን በሽታ ለክርስቲያን ያለመጠንቀቅ ውጤት ሳይሆን ያለማመን ውጤት ነው። Share share share share shared @Cherinetjo71_Inchrist @Cherinetjo71_Inchrist @Cherinetjo71_Inchrist
Show all...
❤የተከፈለው የደም ዋጋ ✍የእግዚአብሔር ቃል ሀጢአተኞች ናችሁ ብቻ አይለንም፤ ሙታን ናችሁ ጭምር እንጂ፣ በደለኞች ናችሁ ብቻ አይለንም፤ የእግዚአብሔር ጠላቶች ጭምር እንጂ። ✍️ወዳጆቼ ልባችን በምን ያህል ጥልቀት ክፉ እና የማይታዘዝ መሆኑን ካላወቅን እግዚአብሔር በህይወታችን ያለውን ቦታ መረዳት አንችልም። እግዚአብሔር ያለ እኛ ይኖራል እኛ ግን ያለ እርሱ ሙታን ነን፡፡ ጥልቅና ጠጣር የሆነው ክፉ ልባችንን ሊቀይርና ሕያው ሊያደርገን ወደሚችል ወደ እግዚአብሔር ምህረት እንሩጥ። ✍️ኢየሱስን ወደ ሕይወታችሁ ጋብዙት ብዬ አልጠይቃችሁም፤ ነገር ግን ባታምኑበት ለዘላለም እንደምትሞቱ በገሀነምም የሚረዳችሁ እንደሌለ ልነግራችሁ እወዳለሁ። መስቀሉ ድራማ አይደለም የብዙዎችን ሀጢአት ለማስተሰረይ የተከፈለ የደም ዋጋ የኢየሱስ የነብሱ ድካም እንጂ። #በመስቀሉ ጣር ወለደን፤ የእግዚአብሔርም ልጅ አደረገን!! ከእንግዲህ በውስጣችን የሞለው የጽድቅ ዘር ነው። አሜን! @Cherinetjo71_Inchrist @Cherinetjo71_Inchrist
Show all...
የእግዚአብሔር ስሞች በብሉይ ኪዳን የተጠቀሱ 📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 👉EL SHADDAI-The LORD GOD ALMIGHTY 👉ኤልሻዳይ-እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ 👉EL ELYON-THE MOST HIGH GOD 👉ኤል ኤልዮን-እጅግ የላቀ አምላክ 👉ADONAI-LORD,MASTER 👉አዶናይ-ጌታ፣አስተማሪ 👉YAHWEH-LORD,JEHOVAH 👉ያህዌ-ጌታ፣እግዚአብሔር 👉JEHOVA NISSI-THE LORD MY BANNER 👉ጂሆቫ ኒሲ-እግዚአብሔር አላማዬ 👉JEHOVA RAAH-THE LORD MY SHEPERD 👉ጂሆቫ ራህ-እግዚአብሔር እረኛዬ 👉JEHOVA RAPHA-THE LORD THAT HEALS 👉ጂሆቫ ራፋ-እግዚአብሔር ፈዋሼ 👉JEHOVA SHAMMAH-THE LORD IS THERE 👉ጂሆቫ ሻማህ-እግዚአብሔር በዚህ ነው 👉JEHOVA TSIDKENU-THE LORD OUR RIGHTEOUSNESS 👉ጂሆቫ ሲድኬኑ-እግዚአብሔር ጽድቃችን 👉JEHOVA MEKKODISHKEM-THE LORD WHO SANCTIFIES YOU 👉ጂሆቫ መኮዲሼኬም-የሚቀድስ ጌታ 👉ELOLAM-THE EVERLASTING GOD 👉ኤል ሆላም-ዘላለማዊ አምላክ 👉ELOHIM-GOD 👉ኤሎሂም-እግዚአብሔር 👉QANNA-JEALOUS 👉JEHOVA JIREH-THE LORD WILL PROVIDE 👉ጂሆቫ ጃይሬ-እግዚአብሔር አቅራቢዬ 👉JEHOVA SHALOM-THE LORD IS PEACE 👉ጂሆቫ ሻሎም-እግዚአብሔር ሰላሜ ነው 👉JEHOVAH SABAOTH-THE LORD OF HOSTS @Cherinetjo71_Inchrist @Cherinetjo71_Inchrist @Cherinetjo71_Inchrist
Show all...
#የፍርሃት_መንፈስ 📌ፍርሃት የእምነት ተቃራኒ ስሆን ባርያ አድርጎ ሊያስቀር የምችልና እስከ መግደል ድረስ ኃይል አለው። "፤ እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።" (2ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1: 7) ዛሬ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ይህንን ክፍል እንይ እስክ... አንድ ታርክ ልንገራችሁ አንብቤ ያገኘሁት ነዉና፦ በ1989 የታይም መጽሔት የጠጉር እንስሳትን ለማደን በተደረገው ጉዞ ላይ ተቀጥሮ ይሰራ የነበረው ጡረተኛ ቻርልስ ቦዴክ በጉዞው ህደት ቆዳዉ በትንኝ ተነድፎ ነበርና፤ በ1980ዎቹ መገባደጃ ላይ ትኩረት ያገኘው "ላይሜ" የምባለው በሽታ ይዞኛል ብሎ #ፍርሃት ይዞት እንደነበር አመለከተ። ቦዴክ ይህንን በሽታ ብቻውን ሳይሆን ምስቱም ላይ ያስተላለፈ መስሎት ነበርና፤ ብዙ ምርመራ ተደርጎለት በሽታው እንዳልያዘዉ ብረጋገጥለትም ፍርሃቱ በዝቶበት ራሱንና ምስቱን በጠመንጃ ገደለ። "፤ ፍርሃትና እንቅጥቅጥ መጡብኝ፥ ጨለማም ሸፈነኝ።" (መዝሙረ ዳዊት 55: 5) ፍርሃት ጨለማን ያመጣል፤ በመጨረሻም እስከመግደል ኃይል አለው። ለጢሞትዮስ በተላከው መልእክት ያሉትን 3 ነገሮችን ከፍርሃት ተቃራኒ የሆኑትን በትንሹ ከፋፍለን እንይ፤ #ኃይል፦ እግዚአብሔር የኃይልን መንፈስ ሰጥቶናል እንጅ የፍርሃትን መንፈስ አይደለም። ፍርሃት ድፍረትን እንደምያሳጣ በተቃራኒው ኀይል ድፍረትና ሙሉ እምነት እንዳለን ያረጋግጥልናል። "፤ ያለ ፍርሃት የተፈጠረ፥ እንደ እርሱ ያለ በምድር ላይ የለም።" (መጽሐፈ ኢዮብ 41: 25) ስለዚህ እንደ ዳዊት በእግዚአብሔር ኃይልን እናደርጋለን ማለት አሌብን። "፤ በእግዚአብሔር ኃይልን እናደርጋለን፤ እርሱ የሚያስጨንቁንን ያዋርዳቸዋልና።" (መዝሙረ ዳዊት 60: 12) #ፍቅር፦ እግዚአብሔር በመንፈሱ ፍቅርን በውስጣችን አፍስሶልናል ስለዝህም ፍቅር በእኛ ውስጥ አለ ማለት ነዉ ነገር ግን ፍጹም ፍቅር ፍርሃት የለውም። ፍርሃት የፍቅር ተቃራኒ ነው። ➲ፍርሃት ፍቅርን ገዳይ ነው ፤ "፤ ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።" (1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4: 18) #ራስን-መግዛት፦ ማለት ሀሳብን አንድ ማድረግ ማለት ስሆን በእግዚአብሔር ጥበብ ራሱን የምገዛ ማለት ነው። ፍርሃት ራስን የመግዛት ተቃራኒ ነው ፤ ፈሪ ራሱን መቆጣጠር አይችልም ሀሳቡም አድራጎቱ ሁሉ ከቁጥጥር ዉጭ የሆነለት ነው። 👉እኛ ግን ራሳችንን መግዛት እንችላለን፤ ራስን የመግዛት መንፈስ ተሰጥቶናልና። (ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕ. 8) 14፤ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና። 15፤ አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና #ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። ➲እግዚአብሔር ይመስገን። ወንድም እህቶች መልካም ነውና አንዳችን ለአንዳችን የእግዚአብሔርን ቃል እንገባበዝ። ሁላችንም በክርስቶስ ተባርከናል። @Cherinetyohannis71
Show all...
በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። (ወደ ኤፌሶን 1 ፡ 3) ሰው እዚህ በረከት ውስጥ የሚገባው በፆም ጸሎት አይደለም። በአንድ እግሩም በመቆም አይደለም። ማንም ሰው እዚህ በረከት ውስጥ የሚገባው በክርስቶስ በኩል ነው። @Cherinetjo71_Inchrist @Cherinetjo71_Inchrist
Show all...
መንፈስ ቅዱስ ሽልማት አይደለም ፤ ምክንያቱም ሽልማት የምገኘው በሩጫ ፍጻሜ ነውና። መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሔር የተሰጠን ኃይል ነው። ሩጫችንን እንድንጨርስ የተሰጠን የአቅማችን ምንጭ ነው እንጅ!! @Cherinetjo71_Inchrist
Show all...
ከማስታውሻዬ ፦ የሰውን ልጅ የሚጎዳው ያወቀው ነገር አይደለም፤ ካወቀዉ ነገር መካከል እውነት ያልሆነው ነው።
Show all...
#ሻሎም ከ እግዚአብሔር እና ከሰው መሀል በክርስቶስ የተደረገ የሰላም ስምምነት ነው። ማንም ይህን ሰላም ልወሰድብን አይችልም።
Show all...
#ስኬት ሁለተ ነው ምወለደው። 1.በሐሳብ 2.በተግባር ነው። ሰው ያሰበውን ከማድረግ ወደ ኋላ የማይል ፍጥረት ነው። 📌ክፉም ይሁን መልካም ያሰብከው ይደርስብሃል። @Cherinetjo71_Inchrist
Show all...