cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

°| ✍ከአፍቃሪያን ገጽ በፍቅር ቀለም |° •[ ከጠቢባን ምድር! ]• 🌴 دار الحكمآء

Show more
Advertising posts
4 488
Subscribers
-424 hours
-207 days
-7430 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

«የአይኔ ማረፊያ ፡ አንቱን ይዤ አላፍርም» ይላል ማዲሑ ከወደዚህ በኩል.... እዚህ ጋር ይመስለኛል የተገለጠልኝ... ማፈሬ/መውደቄ... ምክንያቱ ሲሉ አለመያዜ፣ አለመጠጋቴም።
Show all...
18👍 4
| ሀሳቦቻችሁን በውስጥ መስመር ላደረሳችሁኝ ፡ ወንድምና እህቶቼን ልባዊ ምስጋናዬን አደርሳለሁ። ሀሳቦቻችሁ የሞተ ሂማን የሚያድስ ፡ የሚያበረታም ፡ ነበር። ጀዛኩሙላሁ ኸይራ! ሀሳብ የሰሰታችሁም መስጠትን ይስጣችሁ እላለሁ።  :)   | እንደ አላህ ፍቃድ በሌሎች ስራዎች( ምናልባትም ለየት ባለ ይዘት ) እንገናኝ ይሆናል። ኢኽላስና ተቅዋን ይለግሰንና። እስከዛው ግን..ላልተወሰነ ጊዜ እዚህ መንደር ላይ ዝምታ ይነግሳል  ፡ ባላችሁበት አማን ቆዩልኝ! የልባችሁ ሰላም አይደፍርስ። በዱዓችሁም መሀል አስቡኝ😊🩵 አላሁመ ሰሊ ወሰሊም ወባሪክ አለይህ!💚 •ወሰላም•
Show all...
21👍 3🥰 1
Show all...
ስክነቴ..! [ Abdu Rumi ].m4a5.18 KB
00:21
Video unavailableShow in Telegram
አላህ🖤
Show all...
2.44 MB
👍 3 2
- - የሩሄ አበባ - - ° የተሰበሩ ክንፎች ፡ በፍቅሩ ሽረዋል ፡ ያልሰከኑ ነፍሶች ፡ የተሰበሩ ልቦች ፡ የዛጉ እስትንፋሶች በስሙ ታድሰዋል። ልንኖር የምንመኘውን የህይወት መንገድ ላይ ያስገኘን ፡ መሻታችን መሻቱን ይሁን። የወደደውንና እርሱን እሚወዱትን ያስወድደን ፡ ይውደደንም! ° ሰላም አለይኩም ወራህመቱላህ👋🏽 ውድ የ#ከጠቢባን_ምድር ቤተሰቦች🖤 :)     ከዚህ በፊት በነበሩ ፅሁፎች ላይ የምታደርሱኝ ፡ መልካም ሀሳብና አስተያየቶቻችሁ ሁሉ ፡ ላለፉ ፅሁፎች ጠቃሚ መሰረት ነበሩ። እነሆ. . . የሩሄ አበባ የተሰኘውን ሁለተኛው ልቦለድን ዛሬ እንደአላህ ፍቃድ አጠናቀነዋል። እንደ ሁሌው #ሀሳብና አስተያየቶቻችሁን፡ በመወያያ ግሩፑ በኩል አልያም @abudi058 ላይ እንድታደርሱኝ ሲል ይጠይቃችኋል። ወንድማችሁ - አል-ፈቂር •[ አብዱ ሩሚ ]•   |    ምናልባት መድረሻችን ፡ ለሌላ መነሻ እንደሚሆን ረዥም ተስፋ በማድረግ!😊  | • ወ ሰላም •
Show all...
19
| የሩሄ አበባ~ 20 |            • አብዱ ሩሚ •         • " ደረሰ እኮ ቀኑ! " ትላለች ፡  ለተጠጋት ሁሉ። አባቷ የህይወቱ እስትንፋስ እንዲህ እያያት ስትቃወስ ቁጭ ብሎ ሊመለከታት አልቻለም። ሀኪም ቤት ሊያስመረምራት ቢሞክርም ፡ ሀኪሞቹ ምንም የጤና ችግር እንደሌለባት ነግረውታል። ግራ እንደተጋባ ፡ እምባው ወደ ልቡ እየፈሰሰ ምታደርገውን ያያታል። ከሌላው ጊዜ በተለየ ዛሬ ፈገግታ በፈገግተ ሆናለች። ልክ ሙሽራዋን እንደምትጠብቅ ልጃ ገረድ በጉጉት ተሞልታለች። የተተራመሰ ቤቷን እያፀዳዳች ፡ " ደረሰ እኮ ቁኑ! " ትላለች።  ትልቅ እንግዳ ለመቀበል በሚመስል መልኩ ቤቱን አስውባዋለች። የቤቱን ውስጥና ደጁን ፡ ካሰማመረች ቡኋላ ወደ መስታወቷ አዘገመች። ያ ከብዙ አመታት በፊት ተፈቃሪዋን ልታገኝ ስትሄድ ከራሷ ጋር የምትፋጠጥበት መስታወት። ያኔ ያበበ ፊቷን የምታይበት መስታወት። የዘመን ገፅ ፊቷን እንዲህ በሀዘን ሳያወይበው በፊት ያ ውብ ፊቷን የለመደው መስታወት አሁን ላይ ፡ ሀዘን ያሳሳው ፊቷን ሲያይ ምን ብሎ ይሁን!?    " ደረሰ ቀኑ!. . መዓዛው አልደረሰህም ወይ? የኔ ሩህ እየመጣልኝ ነው? አይሸትም ባባ? አይሸትም? እህ ለኔ ብቻ እንዴት ሊሸተኝ ቻለ. . .! " በትካዜ ግቢ ላይ ቁጭ ብሎ ለሚመለከታት ሀዘንተኛ አባቷ ትናገራለች። መልስ አይሰጣትም። ልቧን ያዝ አደረገች። ደስታ አፍኗታል።      ፍቅር መዓዛ የለውም ወይ? ያዕቁብ የልጁ ዩሱፍን መዓዛ ከሰላሳ አመታት ቡኋላ ፡ ከርቀት እንዲያሸት ያደረገው ምን ሆነና! ዙርያው ያሉት " በቀድሞው ስህተትህ ላይ ነህ" እያሉ ሲሳለቁ ፡ ለነርሱ ያልደረሰው መዓዛ ለያዕቁብ ብቻ የደረሰው ፡ ፍ ቅ ር በሚባለው የሩህ ትስስሮች አማካኝነት ነው። ስጋዊ አካላቶቻችን ሊደርሱበት ማይችሉትን ነገራቶች በልብ ይዘለቃሉ። በፍቅር ይጠለቃሉ።    •   ጉዞ ስትጀምር ፡ መንገዱ ይገለጥልሀል • እንዳሉት ጀላሉዲን አል ሩሚይ። ወዴት የሚለውን ሳላውቅ መጓዝ ጀምርያለሁ። ሶስት ከባባድ ሌቶችን ተጋፍጬ ከአንድ ደማቅ መንደር ደረስኩኝ። ሸይኽ ቀመር ያሉኝ ከሀሳቤ ሊፋቅ አልቻለም። ችሮታውን እርግጠኛ ሆና ምትጠባበቅ ልቤ ፡ የዛለውን አካሌ እያዘዘች ወደ መንደሩ ዘለቅን። አካባቢው ከኔ ብዙ የራቀ አይደለም። ያልተናጋ ህይወቴን የገፋሁበት ቀዬ ነው። እንደ ሰው ተከብሬ የኖርኩበት ቀዬ ! ዩሚን የኔ ያደረግኩባት። እርሷን ስጠብቅ በናፍቆት ጀሂም የተቀጣሁበት ፡ ሽልማቴን ፡ የሩሄን አበባ ልቀበል እየተፍለቀለቅኩ ወደ ሀዘኔ ጎጆ የሄድኩበት ቀዬ። አካባቢያችን ልክ እንደ መፅሀፍ ነው። የእያንዳዳችንን ትዝታ ከትበን የምናኖርበት ንፁህ ወረቀት ነው። የእግሮቻችንን ፋና ከትዝታ መዝገቡ ላይ ያሰፍረዋል። ዛፎቹ በጥላቸው ስር ሆነን ስላሳለፍናቸው ጊዜያቶች ይመሰክራሉ። የኔ ትዝታ ውስጥ ዩሚ ከኔ በላይ ደምቃ ትታየኛለች።    እግሮቼ ያለኔ ፍቃድ ፡ በልቤ ተመርተው ወደ ቀድሞው ቤቴ ደጃፍ አደረሱኝ። በሸረሪት ድር የተወረረና የዛገን በር ነበር የጠበቅኩት። ግን አልሆነም። የግቢዬ ደጃፍ ታድሶዋል። በሚያማምሩ አበባዎች ታጥሮዋል። ቀለሞቹም ልብን ይስባሉ። ይዝጋል ያልኩት ብረት እንደ ወርቅ ያብረቀርቃል። የልቤ ምት ፍጥነቱን ሲጨምር ታወቀኝ። የሆነ ነገር አስፈርቶኛል። ማጣትን አልፈራም! እርሱን አግኝቻለሁኝና! "   . . .ምክንያቱም እውነተኛ ፍቅር ሁሌም ይፈተናል። ፈተና ደግሞ ልብን ሰባሪ ነው! ስብራቱ ውስጥ ካሉ ፈተናዎች ቡኋላ መድህን አለ! ችሮታ አለ! " በጆሮዬ የሸይኽ ቀመር ምክር ይመላለሳል። እግሮቼ ዝለዋሉ ፡ ወደ ቤቴ በር ያሉትን ሁለት እርምጃዎች ወኔዬን ሰብስቤ አለፍኳቸው። የቤቱን በር ፡ ለማንኳኳት አይበሉባዬን ወደ በሩ አስጠጋሁ። ገርበብ አለ። ትንሽ ገፋ አድርጌ አንገቴን ወደ ውስጥ አስገብቼ ፡ አጮለቅኩ። ከከርሞ ጊቢዬ ውስጥ ያየሁት ነገር ፡ አይኔን እንድጠራጠር አደረገኝ። ግርምት አፌን ሞልቶታል። አይምሮዬ ላይ የተሳለ ትዝታ እንጂ እውን አልመሰለኝም።  እምባዬ ከአይኖቼ ያለ ፍቃዴ ፈሰሱ። ከበሩ ደጃፍ ፈዝዞ ከመቆም ውጪ ምንም ማድረግ አልቻልኩም። ዝም ብዬ ፈዝዤ አያታለሁ። የሩህ አበባዬ አብባ ተውባ አየኋት! በምወድላት ጥቁር ሂጃብ ተከባ ፡ ወደኔ እየተንደረደረች መጣች። ዩምናዬ እንደህፃን አንገቴ ላይ ተጠመጠመችብኝ። እየሆነ ያለው ሁሉ ሊገባኝ አልቻለም። ደንዝዤ ቆምያለሁ። ልጇን እንዳገኘች እናት አገላብጣ ከሳመችኝ ቡኋላ ፡ እምባ በጨረሱ አይኖቿ በስስት አይን አይኔን ታየኛለች። " ህልም አይደለማ? " አንደበቴ ሊያወጣው የቻለው ብቸኛው ቃል ነው። ድጋሚ እቅፌ ውስጥ ተሸሸገች። ዝምታዋ አስፈርቶኛል። እቅፌ ውስጥ ቆየች። ነፍሴ እስክትሰክን እቅፌ ስር ቆየች። እጆቼ አጥብቀው ይዘዋታል። ሩኋችን ከአንድ የተሰፋ አይደል? ጀሰዳችንም በጠበቀው እቅፋችን እንደ አንድ ሰው ለመሆን ቀረብን። እቅፌ ውስጥ እንዳለች " ህልም አይደለም! አክረሜ . . ህልም አይደለም የኔ አክረም!  " . . .                       ግቢውና የቤት አጥሩን እንዳስዋበች ሁሉ ፡ ውስጠኛውንም ክፍል አስውባዋለች። ከምንም በላይ ግን እጅግ ደምቃ ምትታየውና የተዋበችው የኔዋ ዩምና ናት። በአፍቃሪ አይን ፡ ከተፈቃሪ ውጪ ያሉ ነገራቶች ሁሉ ደብዘዘው ይታዩም አይደል!?    ለሰዓታት አይኖቻችን ናፍቆታቸውን ከተወጡ ቡኋላ. .  "ዩሚ? ግን እንዴት  . . ሆኖ ..."  ቃላቶቼን ጨርሼ ሳልተነፍሳቸው አፌን በጣቶቿ ሸፈነችው። " መጅኑኔ እንዲህ ትሆንብኛለህ ብዬ እኮ ከዜናው ቡኋላ ደጋግሜ ስልክ ስደውልልህ ነበር ፡ ከመጣሁም ቡኋላ ያላፈላለግኩህ ቦታ አልነበረም። " ፈገግ አለች! እምባ ተከተላት። " . . . በዕለቱ ውቅያኖስ ውስጥ በሰጠመው ፕሌን ልሳፈር ሁሉን ነገር ጨራርሼ ነበር። እንደውም ትዝ ካለህ ስገባ እየመጣሁ እንደሆነ በቪድዮ ልኬልህ አልነበር? " ጭንቅላቴን በአውንታ ነቀነቅኩ። " መንገድ መሀል ላይ ፡ አምጭልኝ ያልከኝ መፅሀፍ ትዝ ብሎኝ ተመለስኩኝ። እሱን ፍለጋ ስዞር ፡ አርፍጄ ነበርና ፕሌኑ አመለጠኝ።. . . "   የሆነው ሁሉ ቀስ እያለ እየተገለጠልኝ መጣ። " ምን የሚል መፅሀፍ ነበር አምጪልኝ ያልኩሽ? "   ከተቀመጠችበት ተነስታ ከመደርደሪያው አናት ላይ ያለውን መፅሀፍ ሰጠችኝ። " የፍቅር እርከናት! " ይላል መፅሀፉ። ፀሀፊ ሸይኽ ሰልማን። ይላል ከመፅሀፉ ግርጌ! ሸይኽ ሰልማን የሸይኽ ቀመር ሸይኽ !! ላነበው የምመኘውን ህይወት ኖሬዋለሁ። በምናብ ልስለው ምሻውን የፍቅር እርከናት በእውኑ ተሸጋግሬዋለሁ። ከጠብታነት ወደ ውቅያኖስነት ተቀይርያለሁ። እርሱን በማፍቅር ውስጥ ያለውን የማይደፈርስ ሀሴትን አጣጥምያለሁ።   " አክሩ ቆይ ለባባ ልደውልለት! አላወቀም እኮ እንደመጣህ። "  ግንባሬን በቀስታ ስማ ከተቀመጠችበት ተነሳች።    የሆነውን ሁሉ እያሰብኩ ፡ ችሮታዬን ከሪሙ እንዴት እንደሸለመኝ እያሰብኩ ፈገግ አልኩኝ። "የፍቅር እርከናት" የተሰኘውን መፅሀፍ ስገልጠው ፡ ዩምናን ስናፍቅ ስለ እርሷ እፅፍበት የነበረበት ማስታወሻዬ ተቀምጦዋል። ገፁ ሰርክ እንደተነበበ ያስታውቃል። የወረቀቶቹ ገፅ ሳስቶዋል። በዩምና እምባዎች እየታጠበ ፡ በለቅሶ ድምፆ እየታጀበ ይሆናል የተነበበው ፡ ማን ያውቃል!?
Show all...
👍 10 2
የማስታወሽያዬ መጨረሻ ላይ አንዲት ገፅ ትቀራለች። አንዲት ባዶ ገፅ። ተፈቃሪዬን ካገኘሁ ቡኋላ ስላተሰማኝ ሀሴት በአጭሩ ልከትብባት የተውኳት አንዲት ገፅ. . .! አጠገቤ ምፅፍበትን እስክሪፕቶ ፈላልጌ በደማቁ እንዲህ ብዬ ፃፍኩበት. . . ۖ وَالَّذِينَ آمَنُوا أَشَدُّ حُبًّا لِّلَّهِ ۗ          >• እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ ይበልጥ የበረቱ ናቸው፡፡            >•       • • •  [   ተ  ፈ   ፀ   መ    ] • • • @ktebiban_meder
Show all...
11👏 4
| የሩሄ አበባ ~ 19  |              • አብዱ ሩሚ •      °     ፍቅር ሚታከመው ፡ በፍቅር ነው!      ° .. የነገሮችን ትክክለኛ መልክ አለማወቃችን ያባክነናል። የኛንም ይሁን በኛ ህይወት ውስጥ ስለሚፈጠሩ ነገራቶች። የነገሮችን ትክክለኛ መልክ መመልከት የቻለ ። የእውነትን እውነተኛ ገፅታን ካየ በኋላ ያንኑ ለመከተል ልቡን ለጉዞ ያሰናዳ. . ።የሀሰትንም ሀሰተኝነት ካስተዋለ በኋላ ከእርሱ ሽሽት ወዳንተ የተመራ ሰው  በርግጥ ድል አደረገ። የልቤን ቁስል ፡ ተሸክሜ ፡ እንግዳ በሆንኩበት ቀዬ እንደ እብድ መባከኔ ለእውነት ነበር። ለእውነተኛ ፍቅር። ያ እውነት ወደ ምንጨ እውነት፡ አደረሰኝ። የተሰበረ ክንፌ ፡ አልተጠገነም። ግን ያለ ክንፍ መብረር ጀምርያለሁ።        የሩሄ አበባ ከጠወለገች ይሀው አመት ከ አስር ወሩ! እኔም የእብድ ካባዬን ከአንድ አመት ቡኋላ ጥዬ ከሸይኽ ቀመር ስር ስር ምዘዋወር አገልጋያቸው ሆኛለሁኝ። ልቤን ወደ ልብን ጠጋኙ ፡ ሩህ በሚያዋስድ ቃላቸው ያስጠጉልኛል። የህመሜን መድህንነት ያሳዩኛል። ያጣሁት ምንን እንደነበር ይጠቁሙኛል።    የልቤ ቂብላ ወደ እርሱ ፍቅር ተቅጣጭቶዋል። ሰላም ልቤ ላይ ነግሶዋል። ስክነት እስትንፋሴ ሆኖዋል። ዝምታ የዘወትር ዜማዬ ከሆነ ሰነበተ። በዝምታዬም ውስጥ የልቤ እህታ ስለ እርሱ ያዜማል። ሞት አፋፍ ላይ ያገኘኋቸው ሰው ፡ ወደ ጥልቁ የህይወት ትርጉም መሩኝ። ያደፈውን ልብሴ ፡ ካለፈ ማንነቴ ጋር ጣልኩት። ታድሻለሁ. .!   " አክረም!  ልጄ! " እንዲህ ነው ፡ ሚጠሩኝ ፣ የሩህ ልጃቸውም አይደለሁ?  ለበይኬን አስከትዬ አጠገባቸው እቀመጣለሁ። ፊታቸው ላይ ፈገግታ ይታያል። ሀዘንና ደስታን ያዘለ ፈገግታ። እንደ ሁሌው የልቤን ምግብ ያቀብሉኝ ጀመር " አክረሜ... በስቃይ ህመምህን ማከምህ አክትሞዋል። የኔ ልብ እንቁ ሊሰጥህ ይሻል። ኒያህ በፍቅር መንገድ መጓዝ እስከሆነ ድረስ ፡ በልብህ ላይ ባለው ፍቅር ትፈተናለህ። ሙዕሚን ሁሌም በፍቅር ይፈተናል። ምክንያቱም የአላህ ስም ሁሌም ከልቡ አፀድ ስር አለና። የልቡም ኤደን ስሙ ነው። ሰርክ የሚመላልሰው። እናም አላህ ከስሞቹ መሀል፡ " ዙል ጀላሊ ወል ኢክራም"  አንዱ ነው። አፍቃሪ ሰው ሰርክ የተፈቃሪውን ፊት መመልከትን ይሻል። ያ የምኞቱ ጣሪያ ነው። ነገር ግን ተፈቃሪው መጀመሪያ ልቅናውንና ታላቅነቱን ለአፍቃሪ ያሳየዋል። ከዛም ችሮታውን ይለግሰዋል። ' ዙል ጀላሊ ወል ኢክራም ' መጀመሪያ ላይ " ጀላል " ከዛም ' ኢክራም' ይቀጥላል። መጀመሪያ ስብራት ፣ ህመም ፣ ችግር ፣ ፈተና ፣ መከራ  . . ከዚያም እዝነት ፣ ብስራት ፣ ደስታ ፣ ሀሴት ፣ ችሮታ! ይከተላል። የዚህ ሰበብ ምን ይመስልሀል  አክረሜ? ለምን ይሁን መጀመሪያ ላይ " ጀላል" መጥቶ ከዝያም "ኢክራም/ችሮታው" ተከታይ የሆነው? " የአይኖቻቸው ዳርቻ በእምባ ተሞልታ በስስት እያዩኝ ጠየቁኝ። በዝምታዬ ውስጥ የ"አላውቅም" መልሴን ሲያገኙ ንግግራቸውን ቀጠሉ።     "  ምክንያቱም እውነተኛ ፍቅር ሁሌም ይፈተናል። ፈተና ደግሞ ልብን ሰባሪ ነው! ስብራቱ ውስጥ ካሉ ፈተናዎች ቡኋላ መድህን አለ! ኢክራም አለ! " ከተቀመጡበት በቀስታ ተነሱ። አብርያቸው ተነሳሁ። አጭር በትራቸውን ከግራ ወደ ቀኝ እጃቸው ቀበል ካደረጉ ቡኋላ እጃቸውን ለእቅፍ ዘረጉልኝ። እቅፋቸው የነፍስ እርካታ አለው። ሩህን ያስደሳል። ከእቅፋቸው ሳይነጥሉኝ የስንብት ቃላቶቻቸውን ከአንድበታቻው ረገፈ። የወራት አብሮነታችን በነዛ ቃላቶች ተሰበረ። •< በል ልብህ ወደመራህ ሂድ! ፍቅርን አግኝተሀል! ፍቅርን የፈጠረውን አፍቅረው። ልብህን ለባለቤቷ አሳድራት። አሁን "ጀላሉ"ን . . ስብራት ፣ መከራውን አልፈሀል። "ኢክራሙን" ችሮታና ብስራቱን ተጠባበቅ!  ማዕሸሩ ሜዳ ላይ ፡ ከአፍቃሪያን ዙምራ ይሰብስበን . .!>• . . [ የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል. . . ]
Show all...
15😢 4👍 1
إنِّي تركتُ الناسَ حِينَ وجدتُهُ ‏تَرْكَ التَّيمُّمِ في وجودِ الماءِ
Show all...
🔥 2
| የሩሄ አበባ~18  |     •    አብዱ ሩሚ     • °        " - ምግብ እንኳን ትብላ እንጂ! ሰውነቷ አለቀ እኮ? "  ግራ የገባቸው ሁሉ የአካሏን መገርጣት እያዩ ለብቸኛ ቤተሰቧ ምክራቸውን እየለገሱ ይሰናበታሉ። የሰፈሩ ነዋሪ በሁኔታው ልባቸው ተሰብሮዋል። " እውነተኛ ፍቅር! እውነተኛ አፍቃሪ. . " እያሉ በድብቅ ያደንቃሉ። ወደ ጆሮዎቿ የሚንቆረቆር ድምፅ ሁሉ ህመም ሆኖባታል። የእርሱ ድምፅ ካልሆነ። ፀግሯን ሌላ ሰው ሲደባብስላት ይነዝራታል ፡ ያ ብዕር መጨበጥ የሚያበዛው እጁ ናፍቋታል። ምታየው ነገር ሁሉ ትርጉም የለሽ ሆኖባታል ፡ እርሱን. . ህይወቷን እስካላየች መርግያ የላትም። የአይኖቿ ዳርቻ በእምባ ብዛት ወፋፍረው እነዛ ሰፋፊ አይኖቿ እጅግ ጠብበዋል። የቀራት ምንም እምባ የለም። ከልቧ እህህታና ከልቧ እምባ በስተቀር ፡ እርሱን የሚያብሰው ደግሞ የእርሱ ልባዊ መዳፍ ነው!   >                                 °          የኢሉ መንደር ድምቀት ፡ ብቸኛው የሸይኽ ቀመር ቅሪት ላይመለስ አሸለበ። ከሚወዳት ዱላ ጋር እንደተቃቀፈ የዚህ አለም አይኖቹ ተከድነው የአኼራው ብሌን ተገለጠ። "ሻሚል ሞተ. .!" "እብዱ ሻሚል? " ሰው ግራ እየተጋባ እርስ በእርስ ያንሾካሽካል። የኢሉ መንደር ነዋሪ በነቂስ ወጥቶ ጀነዛውን ሸኘ። ከአፈሩ ስር አደላድለውት እምባ ሳያዋጡለት በዝምታ ወደየመጡበት አዘገሙ። " ማን ያውቃል ቀመርም አንድ ቦታ እያጣጣረ ይሆናል . . ሰው የእጁን እያጣ! "  እርስ በእርስ ይንሾካሾካሉ። " በሲህርም ሊሆን ይችላል የሞተው. .! " ወደ ገበታቸው ተመለሱ ፡ በመሰለኞቻቸው ላይ ተመስርተው የእውነትን ብርሀን በሸረሪት ድር ሊሸፍኑ።                          °          °    ስለ ሱምኑን ታውቃለህ የኔ ልጅ? " እግሬ የእግራቸውን ኮቴ እየተከተለ ከተራራው ጀርባ የነበረውን መንደር አቋርጠናል። በመሀል በመሀል ማላውቀውን እየጠየቁኝ አሉታዊ መልሴን ተከትለው ስለ መልሱ እያወጉኝ ይሀው መንገድ ላይ ነን። " አላውቅም. .ማን ይሁን? "   " አሄ! በነጁነይድ ዘመን የነበረ አፍቃሪ ነው እሱማ። የሱ ነፀብራቆች ግን አሁናችን ላይም አላችሁ። " ሱምኑን አፍቃሪው! " እያሉ ይጠሩታል በዙሪያው ያሉት ሁሉ። እርሱ ግን ራሱን " ሱምኑን ውሸታሙ! " ሲል ይደመጥ ነበር። እንዲህ ናቸው ቀደምቶች ምንም ያህል የደግነት ማማ ላይ ቢደላደሉ ፡ ራሳቸውን ከምንም ነበር የሚቆጥሩት። እርሱ ከዋለላቸው ውለታ አንፃር የነርሱ የበዛ አምልኮና ፍቅር ነጃ እንደማያወጣቸው ያውቁ ነበር። ባርነታቸውን ፡ ተናናሽና ተዋዳቂ ተስፈኛ መሆንን የመረጡትም ለዚሁ ነው። ታድያ ይህ አፍቃሪ የበራ ፋኖስን ስለ ፍቅር ላውራሽ ሲላት ወደ ስብርባሪነት ከመቀየር ውጪ አማራጭ አልነበራትም። ምን አይነት ፍቅርን ነበር የተሸከሙት አንተዬ? እንዴትስ ልባቸው ቻለው?   " ግርምት እንደ ደመና አጥሎኛል። ምን ብዬ መቀጠል እንዳለብኝ አላወቅኩም። " ምን አይነት ፍቅር ነው? " ሲል ለራሴም ባዕድ በሆነ መልኩ ከራሴ አንደበት ድምፅ ተሰማ። እስካሁን ድረስ ያላየሁትን ፈገግታቸውን ለገሱኝ። የሩህ ምግብ የሆነ ፈገግታ.. ንግግራቸውን ቀጠሉ " ያ ፍቅርማ ያንተው ልብ ውስጥ እንዳለው ነው። ሚለየው ግን የፍቅሩን ምንጭ የተፈቃሪውን አስገኚና የልቡን ጌታ ማፍቀሩ ነው። እንዴት ነው ያቺን የልብ አበባ የሰጠህን ጌታ ፡ በዚች ንፁህ ልብህ አፍቅረህበታል? አይኖችህ ስለርሱ ፍቅር አነቡ? ተፈቃሪህን ለሰጠህ ምንጨ ፍቅር ፡ ፍቅርህን ሳትለግስ የምታገኘው ፍቅር ላይ ስቃይ አለ። እርሱን አለማፍቀርህም ቅጣት ሆኖ ሳለ። ከማንም በላይ እርሱን ፡ ስታፈቅር. . የህመምህ ሁሉ ማብቅያ ወደ ድልም መግብያ በሩ ገርበብ ይልልሀል።  ለመሆኑ ግን ማንን ነው ያጣሀው?  " እኚህም ሰው እንደባለፈው ምናብ እንዳይሆኑ ሰጋሁ። አካላቸውን ዳሰስኩት። ምንም ሚያጠራጥር ነገር አጣሁ። ስለኔ ይሄን ያህል ማወቃቸው ገረመኝ። የጠየቁኝን መመለስ ትቼ ሌላ ጥያቄ አስከተልኩ። " ስለኔ ይሄን ሁሉ ፡ እንዴት ልታውቁ ቻላቹ? " ፊታቸው ላይ የሚይጠፋው ፈገግታ አሁንም አለ።    " የአፍቃሪያን አይን ፡ ላይ የአይን ባለቤቶች የሚያዩት እሳት አለ። ፍም እሳት. . .የ ና ፍ ቆ ት እሳት!  ጥያቄዬን ግን አልመለስክም? " ይሄስ አይኔ ላይ አልተፃፈም? ልል ፈልጌ ነበር " ዩምናን. . የነፍሴን ግሞሽ...ልቤን ነው ያጣሁት. . እኔን ነው ያጣሁት! " እንደለቅሶ ሀዘንተኛ ዝም ብለው ከሰነበቱ ቡኋላ " ያጣሀውን ምታገኝበት መንገድ አለ። አንተን ማጣትህ ሁሉን ያስገኝልሀል። ግን ልብ ያለ ሩህ ቁራጭ ስጋ ብቻነው። ሩህ ከአላህ ዘንድ ምትቸር ናት። ያጣሀው ልብህን ሳይሆን የልብህን ፣ የሩህህን ባለቤት ነበር። እርሱን በዛች ልብህ አለማኖርህ ፡ በዚህ ሁሉ ነገራቶች ውስጥ እንድታልፍ ሆነ። የሆነው ሁሉ በእጣ ፈንታህ ላይ የተከተበ "በጎ" ነገር ነው። እርሱን ስታገኝ ፡ ያጣሀውን አንተነትህንና ልብህንም ታስመልሳለህ። እርሱን ስታጣ ፡ ያለህም ምንም ይሆናል። . . " "   አብሽር. . የአይኖችህ ብርሀን ፡ የልብህን ደስታ ማጣትህ ; ትልቅ ስቃይ ውስጥ ቢጨምርህም መውጫ መንገድ አለ። ዘላለማዊው መለያየት የለም። ልብህን ወደ ዘላለማዊ ቁርኝት ቀይረው።  " . . . . ይቀጥላል @ktebiban_meder
Show all...
6👍 4🥰 2🤔 1
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.