cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

መጽሐፈ ግጻዌ

ይህ ቻናል በየእለቱ በቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚባሉትን ምስባክና የሚነበቡትን የወንጌል ንባባት የሚያስተላልፍ ነው።

Show more
Advertising posts
3 342
Subscribers
+1224 hours
+447 days
+14230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 13:1-31፡ "ወበይእቲ ዕለት ወፂኦ ኢየሱስ" - "1፤በዚያን፡ቀን፡ኢየሱስ፡ከቤት፡ወጥቶ፡በባሕር፡አጠገብ፡ተቀመጠ፤ ርሱም፡በታንኳ፡ገብቶ፡እስኪቀመጥ፡ድረስ፡ብዙ፡ሰዎች፡ወደ፡ርሱ፡ተሰበሰቡ፥ሕዝቡም፡ዅሉ፡በወደቡ፡ቆመው፡ነበር። በምሳሌም፡ብዙ፡ነገራቸው፡እንዲህም፡አላቸው፦እንሆ፥ዘሪ፡ሊዘራ፡ወጣ። 4፤ርሱም፡ሲዘራ፡አንዳንዱ፡በመንገድ፡ዳር፡ወደቀ፥ወፎችም፡መጥተው፡በሉት። ሌላውም፡ብዙ፡መሬት፡በሌለበት፡በጭንጫ፡ላይ፡ወደቀ፤ ጥልቅ፡መሬትም፡ስላልነበረው፡ወዲያው፡በቀለ፥ ፀሓይ፡በወጣ፡ጊዜ፡ግን፡ጠወለገ፥ሥርም፡ስላልነበረው፡ደረቀ። ሌላውም፡በሾኽ፡መካከል፡ወደቀ፥ሾኽም፡ወጣና፡ዐነቀው። ሌላውም፡በመልካም፡መሬት፡ወደቀ፤አንዱም፡መቶ፥ አንዱም፡ስድሳ፥አንዱም፡ሠላሳ፡ፍሬ፡ሰጠ። የሚሰማ፡ዦሮ፡ያለው፡ይስማ። ደቀ፡መዛሙርቱም፡ቀርበው፦ስለ፡ምን፡በምሳሌ፡ትነግራቸዋለኽ፧አሉት። ርሱም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦ለእናንተ፡የመንግሥተ፡ሰማያትን፡ምስጢር፡ማወቅ፡ተሰጥቷችዃል፥ለእነርሱ፡ግን፡አልተሰጣቸውም። ላለው፡ይሰጠዋልና፥ ይበዛለትማል፤ከሌለው፡ግን፡ያው፡ያለው፡እንኳ፡ይወሰድበታል። ስለዚህ፥እያዩ፡ስለማያዩ፥ እየሰሙም፡ስለማይሰሙ፥ስለማያስተውሉም፡በምሳሌ፡እነግራቸዋለኹ። መስማት፡ትሰማላችኹና፡አታስተውሉም፥ማየትም፡ታያላችኹና፡አትመለከቱም። በዐይናቸው፡እንዳያዩ፥በዦሯቸውም፡እንዳይሰሙ፥ በልባቸውም፡እንዳያስተውሉ፥ተመልሰውም፡ እንዳልፈውሳቸው፥የዚህ፡ሕዝብ፡ልብ፡ደንድኗልና፥ዦሯቸውም፡ደንቍሯል፥ ዐይናቸውንም፡ጨፍነዋል፡የሚል፡ የኢሳይያስ፡ትንቢት፡በእነርሱ፡ይፈጸማል። የእናንተ፡ግን፡ዐይኖቻችኹ፡ስለሚያዩ፡ዦሮዎቻችኹም፡ስለሚሰሙ፡ብፁዓን፡ናቸው። እውነት፡እላችዃለኹ፥ብዙዎች፡ነቢያትና፡ጻድቃን፡የምታዩትን፡ሊያዩ፡ተመኝተው፡አላዩም፥ የምትሰሙትንም፡ሊሰሙ፡ተመኝተው፡አልሰሙም። እንግዲህ፡እናንተ፡የዘሪውን፡ምሳሌ፡ስሙ። የመንግሥትን፡ቃል፡ሰምቶ፡በማያስተውል፡ዅሉ፥ክፉው፡ይመጣል፥በልቡ፡የተዘራውንም፡ይነጥቃል፤በመንገድ፡ዳር፡የተዘራው፡ይህ፡ነው። በጭንጫ፡ላይ፡የተዘራውም፡ይህ፡ቃሉን፡ሰምቶ፡ወዲያው፡በደስታ፡የሚቀበለው፡ነው፤ ነገር፡ግን፥ለጊዜው፡ነው፡እንጂ፡በርሱ፡ሥር፡የለውም፥በቃሉ፡ምክንያትም፡መከራ፡ወይም፡ስደት፡ በኾነ፡ጊዜ፡ወዲያው፡ይሰናከላል። በሾኽ፡መካከል፡የተዘራውም፡ይህ፡ቃሉን፡የሚሰማ፡ነው፥የዚህም፡ዓለም፡ዐሳብና፡የባለጠግነት፡ መታለል፡ቃሉን፡ያንቃል፥የማያፈራም፡ይኾናል። በመልካም፡መሬት፡የተዘራውም፡ይህ፡ቃሉን፡ሰምቶ፡የሚያስተውል፡ነው፤ርሱም፡ፍሬ፡ያፈራል፡ አንዱም፡መቶ፡አንዱም፡ስድሳ፡አንዱም፡ሠላሳ፡ያደርጋል። ሌላ፡ምሳሌ፡አቀረበላቸው፡እንዲህም፡አለ፦መንግሥተ፡ሰማያት፡በዕርሻው፡መልካም፡ዘርን፡የዘራን፡ሰው፡ትመስላለች። ሰዎቹ፡ሲተኙ፡ግን፡ጠላቱ፡መጣና፡በስንዴው፡መካከል፡እንክርዳድን፡ዘርቶ፡ኼደ። ስንዴውም፡በበቀለና፡ባፈራ፡ጊዜ፥እንክርዳዱ፡ደግሞ፡ያን፡ጊዜ፡ታየ፡ የባለቤቱም፡ባሪያዎች፡ቀርበው፦ጌታ፡ሆይ፥ መልካምን፡ዘር፡በዕርሻኽ፡ዘርተኽ፡ አልነበርኽምን፧እንክርዳዱንስ፡ከወዴት፡አገኘ፧አሉት። ርሱም፦ጠላት፡ይህን፡አደረገ፡አላቸው።ባሮቹም፦እንግዲህ፡ኼደን፡ብንለቅመው፡ትወዳለኽን፧አሉት። ርሱ፡ግን፦እንክርዳዱን፡ስትለቅሙ፡ስንዴውን፡ከርሱ፡ጋራ፡እንዳትነቅሉት፡አይኾንም። ተዉአቸው፤ እስከ፡መከር፡ጊዜ፡ዐብረው፡ይደጉ፤በመከር፡ጊዜም፡ዐጫጆችን፦እንክርዳዱን፡አስቀድማችኹ፡ልቀሙ፡በእሳትም፡ለማቃጠል፡በየነዶው፡እሰሩ፥ስንዴውን፡ግን፡በጐተራዬ፡ክተቱ፡እላለኹ፡አለ። ሌላ፡ምሳሌ፡አቀረበላቸው፡እንዲህም፡አለ፦መንግሥተ፡ሰማያት፡ሰው፡ወስዶ፡በዕርሻው፡የዘራትን፡የሰናፍጭ፡ቅንጣት፡ትመስላለች።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
Show all...
👍 1
1.05 KB
07/11/2016 ዓ.ም (፯/፲፩/፳፻፲፮ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 አርውዮ ለትለሚሃ። ወአሥምሮ ለማዕረራ። ወበነጠብጣብከ ትበቊል ተፈሢሓ። መዝ. 64፥10 🕯 ትርጉም ትልሟን ታረካለህ። ቦይዋንም ታስተካክላለህ። በነጠብጣብ ታለሰልሳታለህ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
Show all...
👍 3
1.82 KB
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ዮሐ. 1:1-6 "ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ" - "በመዠመሪያው፡ቃል፡ነበረ፥ቃልም፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነበረ፥ቃልም፡እግዚአብሔር፡ነበረ። ይህ፡በመዠመሪያው፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ነበረ። ዅሉ፡በርሱ፡ኾነ፥ከኾነውም፡አንዳች፡ስንኳ፡ያለርሱ፡አልኾነም። በርሱ፡ሕይወት፡ነበረች፥ሕይወትም፡የሰው፡ብርሃን፡ነበረች። ብርሃንም፡በጨለማ፡ይበራል፥ጨለማም፡አላሸነፈውም። ከእግዚአብሔር፡የተላከ፡ስሙ፡ዮሐንስ፡የሚባል፡አንድ፡ሰው፡ነበረ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
Show all...
7/11/2016 ዓ.ም (፯/፲፩/፳፻፲፮ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ሣህሉ ለእግዚአብሔር መልዐ ምድረ። ወበቃለ እግዚአብሔር ጸንዐ ሰማያት። ወእምእስትንፋሰ አፉሁ ኵሉ ኃይሎሙ፡፡ መዝ 32፡ 🕯 ትርጉም የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች። በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ። ሰራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
Show all...
1.24 KB
3
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 24: 15-36 "ወይእተ ዓሚረ ይበጽሕ ሕልቀት " - "15፤እንግዲህ፡በነቢዩ፡በዳንኤል፡የተባለውን፡የጥፋትን፡ርኵሰት፡በተቀደሰችው፡ስፍራ፡ቆሞ፡ስታዩ፥አንባቢው፡ ያስተውል፥ 16፤በዚያን፡ጊዜ፡በይሁዳ፡ያሉት፡ወደ፡ተራራዎች፡ይሽሹ፥ 17፤በሰገነትም፡ያለ፡በቤቱ፡ያለውን፡ሊወስድ፡አይውረድ፥ 18፤በዕርሻም፡ያለ፡ልብሱን፡ይወስድ፡ዘንድ፡ወደ፡ዃላው፡አይመለስ። 19፤በዚያችም፡ወራት፡ለርጕዞችና፡ለሚያጠቡ፡ወዮላቸው። 20፤ነገር፡ግን፥ሽሽታችኹ፡በክረምት፡ወይም፡በሰንበት፡እንዳይኾን፡ጸልዩ፤ 21፤በዚያን፡ጊዜ፡ከዓለም፡መዠመሪያ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ያልኾነ፡እንግዲህም፡ከቶ፡የማይኾን፡ ታላቅ፡መከራ፡ይኾናልና። 22፤እነዚያ፡ቀኖችስ፡ባያጥሩ፡ሥጋ፡የለበሰ፡ዅሉ፡ባልዳነም፡ነበር፤ነገር፡ግን፥እነዚያ፡ቀኖች፡ ስለተመረጡት፡ሰዎች፡ያጥራሉ። 23፤በዚያን፡ጊዜ፡ማንም፦እንሆ፥ክርስቶስ፡ከዚህ፡አለ፡ወይም፦ከዚያ፡አለ፡ቢላችኹ፡አትመኑ፤ 24፤ሐሰተኛዎች፡ክርስቶሶችና፡ሐሰተኛዎች፡ነቢያት፡ይነሣሉና፥ቢቻላቸውስ፡የተመረጡትን፡እንኳ፡እስኪያስቱ፡ ድረስ፡ታላላቅ፡ምልክትና፡ድንቅ፡ያሳያሉ። 25፤እንሆ፥አስቀድሜ፡ነገርዃችኹ። 26፤እንግዲህ፦እንሆ፥በበረሓ፡ነው፡ቢሏችኹ፥አትውጡ፤እንሆ፥በዕልፍኝ፡ነው፡ቢሏችኹ፥አትመኑ፤ 27፤መብረቅ፡ከምሥራቅ፡ወጥቶ፡እስከ፡ምዕራብ፡እንደሚታይ፥የሰው፡ልጅ፡መምጣት፡እንዲሁ፡ይኾናልና፤ 28፤በድን፡ወዳለበት፡በዚያ፡አሞራዎች፡ይሰበሰባሉ። 29፤ከዚያች፡ወራትም፡መከራ፡በዃላ፡ወዲያው፡ፀሓይ፡ይጨልማል፥ጨረቃም፡ብርሃኗን፡ አትሰጥም፥ከዋክብትም፡ከሰማይ፡ይወድቃሉ፥ 30፤የሰማያትም፡ኀይላት፡ይናወጣሉ።በዚያን፡ጊዜም፡የሰው፡ልጅ፡ምልክት፡በሰማይ፡ይታያል፥በዚያን፡ ጊዜም፡የምድር፡ወገኖች፡ዅሉ፡ዋይ፡ዋይ፡ይላሉ፥የሰው፡ልጅንም፡በኀይልና፡በብዙ፡ክብር፡በሰማይ፡ደመና፡ ሲመጣ፡ያዩታል፤ 31፤መላእክቱንም፡ከታላቅ፡መለከት፡ድምፅ፡ጋራ፡ይልካቸዋል፥ከሰማያትም፡ዳርቻ፡እስከ፡ዳርቻው፡ከአራቱ፡ ነፋሳት፡ለርሱ፡የተመረጡትን፡ይሰበስባሉ። 32፤ምሳሌውንም፡ከበለስ፡ተማሩ፤ጫፏ፡ሲለሰልስ፡ቅጠሏም፡ሲያቈጠቍጥ፥ያን፡ጊዜ፡በጋ፡እንደ፡ቀረበ፡ ታውቃላችኹ፤ 33፤እንዲሁ፡እናንተ፡ደግሞ፡ይህን፡ዅሉ፡ስታዩ፡በደጅ፡እንደ፡ቀረበ፡ዕወቁ። 34፤እውነት፡እላችዃለኹ፥ይህ፡ዅሉ፡እስኪኾን፡ድረስ፡ይህ፡ትውልድ፡አያልፍም። 35፤ሰማይና፡ምድር፡ያልፋሉ፥ቃሌ፡ግን፡አያልፍም። 36፤ስለዚያች፡ቀንና፡ስለዚያች፡ሰዓት፡ግን፡ከአባት፡ብቻ፡በቀር፡የሰማይ፡መላእክትም፡ቢኾኑ፡ልጅም፡ ቢኾን፡የሚያውቅ፡የለም።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
Show all...
06/11/2016 ዓ.ም (፭/፲፩/፳፻፲፮ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 እስመ አድኀንካ ለነፍስየ እሞት። ወለአእይንትየኒ እምአንብዕ። ወለአገርየኒ እምዳህፅ። መዝ 55፥13 🕯 ትርጉም ነፍሴን ከሞት እግሮቼን ከመውደቅ አድነኻልና። በሕያዋን ብርሃን እግዚአብሔርን ደስ አሠኘው ዘንድ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
Show all...
👍 2👏 1
1.24 KB
Choose a Different Plan

Your current plan allows analytics for only 5 channels. To get more, please choose a different plan.