cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

አዲስ ሕይወት በክርስቶስ

“እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።” — ሮሜ 6፥4 🌿 አዲስ ሕይወት የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት ነው። 🌿 በክርስቶስ ኢየሱስ ያለ ሰው አዲስ ፍጥረት ነው። 🌿 ክርስትና በትንሣኤው ኅይል የሕይወት ለውጥ ነው። Any comment and suggestion @Andyfa

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
176Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

➹ #ከሞት_ሰው_እንዴት_ሊያመልጥ_ይችላል!?? #ነፃ_አውጪ ያስፈልጋል?? ✅የመጀመርያ ወላጆቻችን በሰይጣን ተንኮለኛ ፈተናና አታላይነት የተከለከለውን ፍሬ በመብላት ኃጢአት ሠሩ። በዚህ ኃጢአት #ምክንያት የነበራቸው #መሠረታዊ_ጻድቅ ተገፈፈ ከእግዚአብሔር ጋር የነበራቸው #ዝምድና_ተቋረጠ በኃጢአት #ሞቱ በነፍሳቸው በሥጋቸው በሙሉ በኃጢአት የረከሱ ሆኑ። እኛም ሞተን ማለት ነዎ?? አዎ ሀላችንም ሞትን ( we all died) #ዘፍጥረት_ምዕራፍ 3 ውስጥ ግን ሰይጣን በእባብ ተመስሎ በመምጣት #መልካምና_ክፉን ማወቅ #የሚያስችለውንና የተከለከለውን ዛፍ ፍሬ እንድትበላ ሄዋንን ፈተናት። ሄዋንም ከበላች በሁዋላ ለአዳም ሰጠችው እርሱም በላ🙆‍♂️። ☑️ይህ ነበር የመጀመሪያው የሰው #ያለመታመን ወይም #አለመታዘዝ ድርጊት። አዳምና ሄዋን የሰይጣንን ምክር #አምነው የእግዚአብሔርን ስጦታና ትእዛዝ #ባለማመን* ድርጊቱን ፈጸሙ። ➾ የአዳምን ኀጢአት የወደቀው ሰብዓዊ ፍጡር ሁሉ #እዳ በማድረግ #ሁላችንን የመጀመሪያው መተላለፍ #ጥፋተኞች እንድንሆን አድርጓል። ይህ የሆነው #አዳም1የሰው_ዘር_ሁሉ_የቃል_ኪዳን እራስ ስለሆነ ነው። የወከለው ራሱን ብቻ ሳይሆን ሚስቱን እና በተፈጥሮዋዊ የመዋለድ መንገድ ከእነርሱ የሚወለደውን ሰብአዊ ፍጡር #ሁሉም ነው። በመሆኑም ከዚህ ጥፋት እና በዚህ ሳቢያ ከሚመጣው ዘላለማዊ ቅጣት #ነጻ የሚያደርገን #መታደግ እኛም ያስፈልገናል። “..... #ለርኵሳንና_ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ #ምንም_የለም፥ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሕሊናቸውም ረክሶአል።” — ቲቶ 1፥15 💢 GOD creats , WE imitate & SIN multilates ✅ የሰው ሁሉ ስርና መሠረት ስለሆኑ የኀጢአታቸው ፍርድ ከእነሱ በተፈጥሮ መንገድ ተወልደው በመጡት ሰዎች ሁሉ ላይ ተቆጠረ። “ስለዚህ ምክንያት #ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ በኃጢአትም #ሞት፥ እንደዚሁም ሁሉ ኃጢአትን ስላደረጉ ሞት #ለሰው_ሁሉ ደረሰ፤” (ኃጢአት~ሰው ሁሉ ላይ ሞት አስከተለ ከሞትም ማንም ሊያመልጥ አልቻለም ) — ሮሜ 5፥12 ➻ ይህም ፍርድ የኃጢአት ሞትና የባሕርይ በኃጢአት #የመበከል ነው። 🏃‍♂️🏃‍♀️ልናመልጠው ከማንችልበት ርኩስና ለመንፈሳዊ ነገር ሙት ከሆነው እንዲሁም #በጠቅላላ መጥፎ ሥራ ለመሥራት ካዘነበለውና የመልካም ነገር ሁሉ #ተቃራኒ በሆነው ባሕርያችን የኃጢአት ድርግቶች ሁሉ ምን ጊዜም ባለማቋረጥ #ይፈልቃሉ(ምንጭ መሆን)።😭😭 ➥ ክርስቶስ ሳይመጣ በፊት ሰዎች የዳኑባቸው የተለያይ መንገዶች ኖረው ይሆን? ➥ ሰው የሚያድነው ካልተገኘለት በምን ሊያመልጥ ነው? ➥ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ነው እንዴ ነገሩ በኃጢአት ተበክለን ተጨማልከን ሞትን አንፈራም ማለት ነው ደግሞ ሞቱ የሥጋው አይደለም ዘላለማዊ ቅጣት ከእግዚአብሔር መለየት ነው? 😭😭 ግን መልሱ ምንድን ነው?? 🙄🙄🙄 ይቀጥላል...... ውዶቼ share በማድረግ ተባበሩ!!! ይህ ቻናል አዲስ ሕይወት ነው። https://t.me/Addis_Hiwot
Show all...
አዲስ ሕይወት በክርስቶስ

“እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።” — ሮሜ 6፥4 🌿 አዲስ ሕይወት የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት ነው። 🌿 በክርስቶስ ኢየሱስ ያለ ሰው አዲስ ፍጥረት ነው። 🌿 ክርስትና በትንሣኤው ኅይል የሕይወት ለውጥ ነው። Any comment and suggestion @Andyfa

#የእግዚአብሔር_ልጅነት “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ #የእግዚአብሔር_ልጆች ይሆኑ ዘንድ #ሥልጣንን ሰጣቸው” — ዮሐንስ 1፥12 “#የእግዚአብሔር_ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ስለዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን ስላላወቀው እኛን አያውቀንም።” — 1ኛ ዮሐንስ 3፥1
Show all...
#መለኮታዊ_ልውውጥ🔃🔀🔁🔄🔓🔑 #The_Divine_Exchange ➦ Universal problems one All sufficient Solution =The cross “#አንድ_ጊዜ [one offering] በማቅረብ የሚቀደሱትን #የዘላለም_ፍጹማን[perfected Forever] አድርጎአቸዋልና።” — ዕብራውያን 10፥14 “አምላኬም #እንደ_ባለ ጠግነቱ_መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ #የሚያስፈልጋችሁን_ሁሉ ይሞላባችኋል።” — ፊልጵስዩስ 4፥19 ➥ #ለዘላለም_ፍጹማን: ዘላለም የሚለው ቃል ከጅማሬ እና ፍጻሜ ውጪ የነበረና ሁልጊዜ የሚኖር #የጊዜን_ልክ የሚያልፍ ነው። መሰዋዕቱ ለሁሉም ለሰው ዘር፣ለሁሉም ክፍለ ዘመን፣ ለሺህ ዓመታት፣ ላለፈው፣ላለው፣ለሚመጣው፣ ገና ለሚወለዱት ኃጢአት ሁሉ መስቀሉ የኃጢአትን ደመወዝ ከፍሏል። ➥ #የሚያስፈልጋችሁን_ሁሉ: የሰው ልጅ ፍላጎቶችን ሁሉ ያጠቃለለ ቃል ነው። ◆ ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው በእግዚአብሔር #አንድ_የሉዐላዊነት ድርጊት(ውሳኔ) የሚያስፈልገን እና ጥያቄዎቻችን #በአንድ_ከፍተኛ_መሰዋት ለሁሉ አድርጓል። ☑ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች #ለተለያዩ_ጥያቄዎች የተለያዩ መልሶችን አይሰጥም ነገር ግን #አንድ ሁሉን ያሟላ #መልስ ይሰጣል። ✅ የወንጌል አጠቃላይ መልዕክት በክርስቶስ መስቀል ላይ መስዕዋትነት፣ ስቅለትና ትንሣኤ ላይ ነው የምያጠነጥነው። መስቀሉ በኢየሱስ የተደረገ መሰዋዕትነት ነው። ☑ እግዚአብሔር አባት የዓለም ኃጢአት፣ጥፋት ውረደት እና ተቃውሞ ውጤት ሁሉ በኢየሱስ ትከሻ ላይ አደረገ። የመስቀሉ ጥቅም ለመቀበል ይህንን መገለጥ መረዳት ዋናው ቁልፍ ነገር ነው። መለኮታዊ ልውውጥ የታዘዘው በመሰቀል ላይ ነው። በእኛ ተቃውሞ የተፈጠረው እያንዳንዱ ክፉ ነገር ኢየሱስ ላይ ነበር የተቀመጠው። 👇 @Addis_Hiwot @Addis_Hiwot
Show all...
❤️#ታላቁ_የመከራ_ዘመን❤️ (PERIOD OF TRIBULATION) ============================== 📌ማቴዎስ 24፡21 "በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናልና"። ✍️ ይህ የመከራ ዘመን እስከ ዛሬ በሰው ልጆች ላይ ከደረሱት መከራዎች ሁሉ ይበልጥ አስጨናቂ ጊዜ ሲሆን። የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት እንደሚናገረው፣ ይህ የሚሆነው የቤተ ክርስቲያንን ንጥቀት ተከትሎ በምድር ላይ ባልተነጠቁት በእስራኤልና በዙሪያዋ ባሉ ባልተነጠቁ አህዛብ የሚፈጸም ይሆናል፡፡ ማርቆስ 13:19፤ ዳንኤል 12:1፤ ማቴዎስ 24:21, 22 ✍️ይህም ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዲህ ተብሎ ተጠረቷል፡- 📌 ታላቁ የቁጣ ቀን( ራዕ 6:17) 📌 ታላቁ መከራ (ራዕ 7:14) 📌 የያዕቆብ መከራ ዘመን (ኤረ 30:7) በመባል ይታወቃል፡፡ ✍️ይህ የመከራ ዘመን ቤተክርስቲያንን(ቅዱሳንን) የሚመለከት አይደለም ምክንያቱም ክርስቶስ ዳግም የተወለዱትን አማኞች ሁሉ ከምድር ላይ ይወስዳል፣ መነጠቅ ይፈጸማል።(ተሰሎንቄ 4:13-18፤ 1 ቆሮንቶስ 15:51-54)። ቅዱሳንን የሚመለከተው በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት በምድር ላይ በነበሩበት ጊዜ ስለሰሩት ስለ መልካም ሥራቸውና ስለ ታመነ አገልግሎታቸው ሽልማትን ይቀበላሉ ወይም አይሸለሙም ይህ ሽልማት ግን የዘላለም ሕይወትን አይደለም ከአገልግሎት እና ከመታዘዝ ጋር የሚያያዝ ነው(1 ቆሮንቶስ 3:11-15፤ 2 ቆሮንቶስ 5:10)። ✍️የቤተክርስቲያን መነጠቅን ተከትሎ የመከራው ዘመን ይመጣል ይህ የመከራው ዘመን የዳንኤል የ70 ኛው ሱባኤ ፍጻሜ ማለት ነው። ይህን የዳንኤልን 70 ሱባኤ ለመረዳት ዳንኤል ስለ ሕዝቡ ስለእስራኤል ነጻነት በሚጸልይበት ጊዜ እግዚአብሔር ለዳንኤል 70 ሱባኤ እንደተቀጠረ ነገር ግን በ 69 ሱባኤ መሲሁ እንደሚገደል ይናገራል። 1ሱባኤ = ሰባት አመት እንደሆነ ቅዱሳን ሁሉ መረዳት አለብን። በዚህ መሠረት 70 ሱባኤ = 490 69 ሱባኤ = 483 ላይ መሲሁ ኢየሱስ ይገደላል 1 ሱባኤ = 7 አመት ሲቀር እስራኤል መሲህ የሆነውን ክርስቶስን ካለመቀበሏ የተነሳ መዳን ለአህዛብ ይሆናል። በ69ኛው መሲሁ በተገደለበት ሱባኤና በቀረችው 1 ሱባኤ (7 አመት) መካከልም የ2000 አመት የቤተክርስቲያን (የጸጋ) ዘመን ይገባል ይህን የጸጋ ዘመን ሐዋርያው ጳውሎስ የምስጢር ዘመን በማለት ያስረዳል። ኤፌ 3፡3-6 ይህ የቤተክርስቲያን ዘመን ፍጻሜ ሲያገኝ እና ጌታ ኢየሱስ ቤተክርስቲያኑን (ቅዱሳንን) በመነጠቅ ይዞ ሲሄድ። ወዲያው የቀረችው የዳንኤል 70ኛዋ ሰባኤ ማለት 1 ሱባኤ (7 ዓመቷ) ትቀጥላለች ይህን ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ የመከራ ዘመን ይለዋል። 📌የመጨረሻው ሱባኤ(የሰባት አመት ታላቁ የመከራ ዘመን) በራዕይ መፅሐፍ ከምዕራፍ 6-19 መሠረት ለሁሌት በመከፈል ይጠራል፡፡ 👉 የመከራዉ ምጥ ጣረ(Tribulation) 👉 ታላቁ የመከራ ዘመን(Great tribulation) ✍️ያን ጊዜ የክርስቶስ ተቃዋሚው (አውሬው) ወደ ሥልጣን ይመጣል፣ ከእስራኤል ጋርም ለሰባት ዓመት ቃል ኪዳን ይገባል (ዳንኤል 9፡27)። ይህ የሰባት ዓመት ጊዜ “ታላቁ መከራ” በሚል ይታወቃል። በታላቁ መከራ ጊዜ አስፈሪ የሆነ ጦርነት ይካሄዳል፣ ራብ፣ ቸነፈር፣ እና የተፈጥሮ ጥፋቶች። እግዚአብሔር በኃጢአት፣ በክፉ፣ እና በክፋተኝነት ላይ መዓቱን ያፈስሳል። መከራው፣ ራዕይ ላይ ያሉትን አራቱን ፈረሰኞች፣ እና ሰባቱን ማኅተም፣ መለከት፣ እና የፍርድ ማሳያ ትዕይንቱንም ያካትታል። በሰባቱ ዓመት ሂደት አጋማሽ ላይ፣ የክርስቶስ ተቃዋሚው ከእስራኤል ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ያፈርስና ጦርነት ያካሂዳል። የክርስቶስ ተቃዋሚው “የጥፋት ርኵሰትን” ይፈጽማል፣ የራሱምን ምስል አበጅቶ በኢየሩሳሌም ቤተ-መቅደስ እንዲሰገድ ያደርጋል (ዳንኤል 9፡27፤ 2 ተሰሎንቄ 2፡3-10)፣ እሱም ዳግመኛ የተገነባው። የመከራው ሁለተኛው አጋማሽ “ታላቁ መከራ” በመባል ይታወቃል (ራዕይ 7፡14) እና “የያዕቆብ የመከራ ጊዜ” (ኤርምያስ 30፡7)። ✍️ በዚያን ጊዜ እስራኤል በብዙ መከራና ስቃይ ውስጥ ትሆናለች፡፡ በምድር ላይም ታይቶ የማይታወቅ ከዚያም በዋላ የማይደገም ታላቅ መከራ ይሆናል፡፡ ✍️የዚህ መከራ አላማም እስራኤልን ለንስሃ በማደስ ራሷን ለመስሃዊ መንግስት ማዘጋጀት ነዉ፡፡ ኤር 30:1-10:: "(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕ. 30፡1-10) 📌📌📌ማሳሰቢያ፦ ==================== ✍️ይህ የመከራ ዘመን ቤተክርስቲያንን (ቅዱሳንን) የሚመለከት አይደለም፡፡ 1 ተሰሎንቄ 5 (1 Thessalonians) 1፤ ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ዘመናትና ስለ ወራት ምንም እንዲጻፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤ 2፤ የጌታ ቀን፥ ሌባ በሌሊት እንደሚመጣ፥ እንዲሁ ይመጣ ዘንድ ራሳችሁ አጥብቃችሁ አውቃችኋልና። 3፤ ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል ከቶም አያመልጡም። 4፤ እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ቀኑ እንደ ሌባ ይደርስባችሁ ዘንድ በጨለማ አይደላችሁም፥ 5፤ ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና። እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም፤...... 9፤ እግዚአብሔር ለቍጣ አልመረጠንምና፥ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ። ✍️2 ቆሮንቶስ 13 (2 Corinthians) 14፤ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። የወንጌል እውነት አገልግሎት ጅማ Gospel Truth Ministry Jimma https://scontent-sjc3-1.xx.fbcdn.net/v/t1.6435-9/247187388_4429615990487280_4694295063007040771_n.jpg?_nc_cat=106&ccb=1-5&_nc_sid=8bfeb9&_nc_ohc=wtPKHVeox9YAX8A-S9D&_nc_ht=scontent-sjc3-1.xx&oh=62492a179e0b3711c1f5a11c80595486&oe=6199443C
Show all...

2 ፊሊያ (philia) ፍቅር ፊሊያ የተሰኘው ፍቅርን ገላጭ ቃል የጓደኝነትን ፍቅር ለመግለጽ የሚጠቀሙበት ቃል ነው። ታላቁ ፈላስፋ አሪስቶትል አንድ ሰው በሌላው ሰው ላይ ይህንን አይነት ፍቅር ሊገልጽ የሚችለው በሶስት ምክንያት ነው ይለናል 1. ሰውየው ለእኛ ጠቃሚ ሲሆን 2. ሰውየው ደስ የሚለን ሲሆንና 3. ሰውየው መልካም ሰው ሲሆንልን። ይህ የወንድማማችነትና የጓደኝነት ፍቅር ገጽታ አብሮነትን፤ አንዱ በሌላው ላይ የመደገፍንና የመተማመንን ሁኔታ ያቀፈ ነው ይቀጥላል 👩‍❤️‍👨 @relationship4christ 👩‍❤️‍👨 👩‍❤️‍👨 @relationship4christ 👩‍❤️‍👨
Show all...
ሐሳብን ከዘራሽ ፣ ተግባርን ታጭጂያለሽ፤ ተግባርን ከዘራሽ፣ ልማድን ታጭጂያለሽ፤ ልማድን ከዘራሽ ፣ ባሕርይን ታጭጂያለሽ፤ ባህርይን ከዘራሽ፣ ዕድል ፈንታን ታጭጂያለሽ። ....ሳሙኤል ስማይልስ 👩‍❤️‍👨 @relationship4christ 👩‍❤️‍👨 👩‍❤️‍👨 @relationship4christ 👩‍❤️‍👨
Show all...
💑"#በቅድስና ለምትይዘው ወደፊት ለሚኖርህ ወይም አሁን ላለህበት #የእጮኝነት ህይወት #እግዚአብዘሔር ካንተ ይልቅ ይደሰትበታል።" 🔥Pastor Billy Graham & Ruth Graham💯 @relationship4Christ @relationship4christ
Show all...
መዝሙር 92 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ² #በማለዳ_ምሕረትን፥ በሌሊትም እውነትህን ማውራት ³ አሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ። ⁴ አቤቱ፥ #በሥራህ_ደስ_አሰኝተኸኛልና፤ በእጅህም ሥራ ደስ ይለኛልና። ⁵ አቤቱ፥ #ሥራህ_እጅግ_ትልቅ ነው፥ አሳብህም እጅግ ጥልቅ ነው። ⁶ ሰነፍ ሰው አያውቅም፥ ልብ የሌለውም ይህን አያስተውለውም። … ⁸ አቤቱ፥ አንተ ግን ለዘላለም ልዑል ነህ፤
Show all...
💢 የማለዳ ቅምሻ💢 #21/12/2013 ሁሌ ከጓዳዬ ከእንቅልፈ ስነቃ አስታውሳለሁ የአንተን ጥበቃ ሌሊቱን በሙሉ በክንፍ ከልለህ በሰላም አደርያለሁ #ኢየሱስ ስላለህ
Show all...
፦ እንዴት relationship ን ከእግዚአብሔር ቃል አንጻር እናስኪድ💏💏 ተከታታይ ጾታዊ ትምህርቶች በቅድስና እንዴት እንኑር for any comment @edbornagain https://t.me/relationship4christ
Show all...
ፍቅርን በመጽሐፍ ቅዱስ

፦ እንዴት relationship ን ከእግዚአብሔር ቃል አንጻር እናስኪድ💏💏 ተከታታይ ጾታዊ ትምህርቶች በቅድስና እንዴት እንኑር for any comment @edbornagain