cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

በጎ የአዲስ ኪዳን ማዕከላዊ ትምህርት

ይህ ቻናል አስቸኳይ የወንጌል ድምፅ ነው ዋና ርዕስ 2ኛ ጠሞ 4:5 መሠረት ያደርጋል

Show more
Advertising posts
189
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

👍👉ወደ ፊት ሕፃን አትሁን ግን ደግሞ ሕፃንነትህን አሳድገው።👈💝 እኛ ሰዎች ከፍ ስንል ወጣት፣ ጎልማሳ ፣ሽማግሌ ስንሆን ህፃንነት ለኛ ጥሩ ትዝታችን ነው። ህፃንነት ንፅህና ነው፣ የዋህነት፣ በአባት ላይ ያለን እምነት ነው፣ ቅንነት ነው፣ ጥልን መርሳት ነው፣ አብሮነት ነው፣ ሞኝነት ነው ከዘረዘርናቸው በላይ ብዙ ልንል እንችላለን ከዚህ ውስጥም የእኛን የህፃንነት ልብ አናጣውም። ይህ ህፃንነት ላይ መንፈሳዊነት ሲጨመርበት ያለው የሞኝነት ፀሎት እና ለእግዚአብሄር ያለን ክብር ታላቅ ነው። ኢየሱስ እንዲህ ብሎ አስተምሯል:- #ማቴዎስ 18 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³ እንዲህም አለ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም። ⁴ እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ፥ በመንግስተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው። 👉የሚገርመው እግዚአብሔር አሁንም አደግን ብለን ወጣት፣ ጎልማሳ እና ሽማግሌ ሆነን ይህን ልብ ከእኛ ይፈልገዋል። ማደግ ለእኛ ብልጥ መሆን፣ እኔ እችላለው ብሎ ከእግዚአብሔር ከአባት አለመጠበቅ፣ ልበ ክፉ መሆን፣ ነገርን አለመተው፣ ቅንነት ማጣት፣ በልዩነት ማመን፣ ስግብግብነት ሆኖብን ራሳችንን ስንገልጥ ትልልቆች ነን የምንል ምስኪኖች ነን። እንደዚህ ከምንሆን ሰዎች ይልቅ እግዚአብሔር ለህፃናት ኢየሱስን ሊገልጥላቸው ፈቃዱ ነው። #ማቴዎስ 11 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁵ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፦ አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤ ²⁶ አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና። 👉ወደ ፊት ህፃናት እንድንሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ ባይሆንም ልባችን ግን እንደህፃናት ንፁህ እንዲሆን ይፈልጋል። እግዚአብሔር በዚህ ይባርከን አሜን!! [ አንተ ጎበዝ ይልሃለሁ ተነሣ ] ( ሉቃ 7፡14)
Show all...
አዲስ ሰማይ አዲስ ምድር የብርሃን ሀገር የብርሃን ቅጥር ምርአፍ ተዘግቶ ምርአፍ ሲጀመር አየዋለው ያኔ በድል በክብር
Show all...
መብራቱን አብራው! አንድ ጊዜ በአንድ ከተማ አንድን ስልጠና ለመስጠት በነበርኩበት ጊዜ የተከሰተ የግል ልምምዴን ላካፍላችሁ፡፡ ያረፍኩበት ሆቴል ከፍ ያለ ኮረብታ ላይ ስለነበረና አካባቢው በዛፎች በመከበቡ ምክንያት የራሱ ውበት ስላለው በዚያ ማረፍን እመርጣለሁ፡፡ በዚያ ባደርኩበት አንድ ሌሊት ግን አንድ ነገር ተከሰተ፡፡ ሌሊት ነቅቼ ወደ መታጠቢያ ቤት መሄድ ስላስፈለገኝ ከአልጋዬ ለመውጣት ተንቀሳቀስኩኝ፡፡ ከውጪ በመስኮት በኩል በመጋረጃው ሾልኮ የሚገባው ደብዛዛ ብርሃን ለእንቅስቃሴዬ በቂ ስለነበር ልክ ከአልጋዬ ስወርድ ወደ መታጠቢያ ቤቱ በሚወስደው አቅጣጫ አንድ “እባብ” ተጋድሞ አየሁኝ፡፡ ከብርሃኑ ደካማነት የተነሳ ይህንን “እባብ” ቅርጹን እንጂ መልኩንና ሁኔታውን መለየት አልቻልኩም፡፡ በጣም ደነገጥኩ፣ በጣምም ፈራሁ፡፡ ወደኋላዬ በመሰብሰብ ሁለንተናዬን ትራሴ ላይ አገኘሁት፡፡ ብዙ አሰብኩኝ፡፡ ብዙ አወጣሁኝ፣ አወረድኩኝ፡፡ ትንሽ ጊዜ ካቃጠልኩኝ በኋላ፣ በመጨረሻ ያለኝ ብቸኛ አማራጭ እንደምንም የእባቡን ክልል አልፌ መብራቱን ማብራት ነው፡፡ ትንሽ ከወላወልኩኝ በኋላ የፈጣሪዬን ስም እየጠራሁ፣ ጨለማውን ለማሸነፍ አይኖቼን አፍጥጬ፣ ጥግ ጥጉን ተራምጄ መብራቱን ልክ ሳበራው ለካ ያየሁት “እባብ” ማታ በድካም ስሜት ወደ አልጋ ስቸኩል የጣልኩት ቀበቶዬ ነበር፡፡ በዚህ ገጠመኜ የገባኝ ነገር ይህ ቀበቶ እባብ መስሎኝ በነበረበት ሰዓት፣ ልክ እውነተኛ እባብን ብጋፈጥ የሚሰማኝን የፍርሃት ስሜት ነው የሰጠኝ፡፡ ከዚህ ስሜት የተነሳ ልጮህ እችል ነበር፣ እዚያው አልጋዬ ላይ ሆኜ እስከሚነጋ አፍጥጬ ልጠብቅ እችል ነበር፣ ሰዎች ጋር ስልክ በመደወል ልበጠብጥ እችል ነበር . . .፡፡ በፍርሃት ተወጥሮና ታስሮ የነበረውን ማንነቴን ነጻ ያወጣው እውነቱን ለማወቅ መብራቱን ማብራቴ ነው፡፡ ለካ እይታ የእውነታን ያህል ጉልበት አለው፡፡ በሕይወታችን አንድ ነገር ባይኖርም እንኳን፣ እንዳለ ከቆጠርነውና ከፈራን ማንነታችንን አስሮ ሊያስቀምጠን እንደሚችል በሚገባ የተገነዘብኩት ያን ጊዜ ነው፡፡ መድሃኒቱ መብራቱን ማብራት ነበር፡፡ አንዳንድ ሰዎች ገና ለገና ሆኖብኛል . . . ሳይሆንብኝ አይቀርም . . . አለብኝ . . . ሳይኖብኝ አይቀርም . . . ሊሆን ነው . . . መሆኑ አይቀርም ከሚሉት ምክንያት-የለሽ ፍርሃት የተነሳ ታስረው አመታት ያሳልፋሉ፡፡ ይህ ፍርሃት፣ እምቅ ብቃታቸውን አፍኖ፣ ነጻነታቸውን ነፍጎ፣ የሌለውን ችግር እንዳለ አድርጎ፣ ያለውን ችግር ደግሞ እጅግ አግዝፎ በማሳየት ከሰው በታች ያደርጋቸዋል፡፡ መፍትሄው መብራቱን ማብራት ነው!!! መብራቱን ማብራት ማለት እውነታውን ለመጋፈጥ አይንን መግለጥ፣ ስለሁኔታችን ከበሰለ ሰው ጋር መወያየት፣ ምንም ነገር ቢሆን በፍርሃት ታስሮ ከመኖር እውነታውን ተጋፍጦ በነጻነት መኖር እንደሚመረጥ መገንዘብ ማለት ነው፡፡ ይህንን አትርሳ፣ መፍራት እስከምታቆም ድረስ መኖር አትጀምርም! @begowongel
Show all...
🎯🎯🎯🎯🎯🎯🎯 ውሎህን ቃኝ"! አንድ ቀን ዝንብና ንብ እያወሩ በወሪያቸው መሀል ዝንብ ንብን እንዲህ ስትል ጠየቀቻት " ንብ ሆይ ለምንድነው የሰው ልጆች እኔን የሚጠሉኝ? ለምንስ ነው የሚጸየፉኝ ? ቤታቸው ስገባ ያባርሩኛል ይገድሉኛል። የሚጠጡት ነገር ላይ ከተገኘሁ ይደፉታል የሚበሉት ነገር ላይ ካረፍኩ ያረፍኩበትን ቦታ ያለውን እህል ቆርሰው ይጥሉታል:: አንቺን ግን እንደ እኔ አይገፉሽም እንደውም ቤታቸው ስትገቢ ይንከባከቡሻል ደግሞም መልካም ነገርን ተስፋ በማድረግ ደስታቸው እጥፍ ነው ለምንድነው?" ስትል ዝንብ ንብን ጥያቄዋን አቀረበች በዚህ ጊዜ ንብ እንዲህ አለቻት ☞ "ውሎሽ የት ነው?" ◽️◼️◽️◼️◽️◼️◽️◼️◽️ ☞እንግዲህ እዚህ ጋር ቆም እንበል፣ ሰው ጠላን፣ ገፋን፣ ናቀን እያልን እንደ ዝንቧ ጥያቄን አዝለን ከምንጓዝ ውሏችንን በደንብ እንይ መቼም ማንም በጤፍ ማሳ ላይ ስንዴን አይጠበቅም። ስለዚህ ምንጊዜም:-ውድቀታችንን ለማረምም ይሁን ብርታታችንን ለማብዛት ውሏችንን እንቃኝ ምክንያቱም :-ሀሳባችን ስራችንን ስራችን ውጤታችንን ውጤታችን እኛነታችንን ይገልጽልናል ሼር በማድረግ ለወዳጅዎ ያካፍሉ እናመሰግናለን! ቻናላችንን ይቀላቀሉን ፣ ለወዳጅዎ ያጋሩ share 👇👇👇 @begowongel
Show all...
~ 👉👉ግጥም👈👈💝 👉 አንተስ የትኛው ነህ?👇 በጭንጫው አፈር ላይ ልክ እንደወደቀው ስሩ ስላልያዘ ወዲያው እንደደረቀው እንደዚኛው ዘር ነህ? ቃሉን እንደሰማ አምኖ የሚቀበል ምንም ሳየቅማማ መከራው ሲመጣ ፊቱን እንደሚያዞረው እምነቱ ሳይጠና ጠውልጎ እንደሞተው ወይስ ....... እንደዛኛው መንገድ ዳር እንዳለው ስርም ሳያወጣ ወፍ እንደለቀመው ምስራቹን ሰምቶ ከልቡ እንደልጣፈው የመስቀሉ እውነት አርቆ እንደሸሸው የህይወቱን መስመር ክፉው እንደነጠቀው ወይስ ....... እንደዚኛው በእሾህ እንዳለው የገንዘብም ፍቅር እድገቱን እንዲገታው ወንጌል እንዳይሰራ ፈርቶ እንደቀረው በሁለቱ ጌቶች መሀል ላይ እንዳለው ቃሉን እያወቀ ዓለም እንዳነቀው ወይስ ..........እነደዚኛው በመልካም እንዳለው ስሩን አሳድጎ መሬት እንደያዘው ቅጠሉን አስፍቶ ጥላ እነደሆነው ወደ ላይ አብቦ ፍሬ እንዳፈራው ቃሉን ተቀብሎ በልቡ እንደጣፈው በእምነት ስር ሰዶ መሠረት እንዳለው ምስራች ተናግሮ ብዙ እንዳበበው ከአምላኩ ዘንድም አክሊል ሚጠብቀው የመልካም ዘር ትርጉም ምሳሌ ይሄ ነው አንተስ የትኛዉ ነህ ከዚህ ዘር ምሳሌ ክፉ እንደነጠቀው መቶበት ኩነኔ ወይስ .......እንደዛኛው እንዳለው በእሾህ እውነቱን ትተሀል ከዓለም ፍቅር ይዞህ የገንዘብ እሾህሰ አጣብቆ ይዞሀል? ወይስ ደሞ ፈርተህ ቃሉን ሸሽገሀል ታዲያ የትኛው ነው ያንተ ዘር ምሳሌ ስቦ የሚያወጣህ ከዚ ዓለም ኩነኔ ልክ እንደመልካሙ ብዙ እንዳፈራ እውነት ተወተሀል የጌታን አደራ? ለችግር ለንግልት ምንም ሳትበገር ለሰው ተናግረሀል የኢየሱስን ፍቅር ? ጠይቅ ራስህን ፈትሸው ስራህን እኮ የትኛው ዘር ይገልጥሀል አንተን ????? [ አንተ ጎበዝ ይልሃለሁ ተነሣ ] ( ሉቃ 7፡14) 👉 @begowongel
Show all...
💝👉ዘገየ ለምን?🙏🙏 “Therefore say unto them, Thus saith the Lord GOD; There shall none of my words be prolonged any more, but the word which I have spoken shall be done, saith the Lord GOD.” — Ezekiel 12፥28 👉 ማለፍ ባለብህ ፈተና ውስጥ ሁሉ ታልፍለህ! ህይወት በብዙ ውጣ ውረድና በተለየያ እንቆቅልሽ የተሞላች ናት።ማንም ሰው ከፀሐይ በታች መልኩና መጠኑ በሚለያዩ ፈተናዎችና መከራዎች ውስጥ ያልፍል።በበሽታ፣በረሃብ፣በመከዳት፣በመገፋት፣በሀዘን፣በብቸኝነት ...ወ.ዘ.ተ በዚህ ሁሉ ግን አንድ ሀይል አለ በእሳት ውስጥ የሚያሳልፍ አንድ ክንድ አለ በወጅብ ውስጥ የሚያሻግር እርሱ የእግዚአብሔር አብሮት ይባላል።እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን እንጂ የማታልፍቸው የመከራና የተፈተና አይነቶች አይኖሩም።አብሮነቱ ሊያጠፍችሁ የተነሳውን እሳት ያጠፍል ሊያሰምጣችሁ የተነሳውን ወጀብ ፀጥ ያደርጋል።እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ነው። በ2015 ማለፍችሁ አይቅርም ነገር ግን በመከራ ውሃ ውስጥ ስታልፉ ውሃው አያሰምጣችሁም።በፈተና እሳት ውስጥ ባለፍችሁ ጊዜ እሳቱ አያቃጥላችሁም።ምክንያቱም እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነውና። “በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም።ኢሳይያስ 43፥2
Show all...
🌼🌼አንተም አዲስ ነህ!🌼🌼           🌼🌼🌻🌻🌼🌼 አዲስ ነገር ቦታውን ይይዝ ዘንድ አሮጌውና የቀድሞው ነገር ቦታ መልቀቅ ይኖርበታል። አሮጌው ጊዜ ስፍራውን ሲለቅ በአዲስ ይተካል፤ የቀድሞው ማንነትም ሲሻርና ሲተው ብቻ የተሻለው ማንነት ይከሰታል። ያልታሰበ ስኬትና ከፍታ ኬትም ሊመጣ አይችልም። ከዚህ ቀደም ብዙ ሃሳቦች በውስጥህ ተመላልሰው ይሆናል፣ መሆን የምትፈልገውን ሰው እንዳትሆን ፍረሃት አስሮህ ስጋትም ጋርዶህ ይሆናል፣ ላይ ታች በማለትም ብዙ ለፍተህ ይሆናል። አዲስና ልዩ ባልከው ጊዜም ሃሳብህን፣ ምኞትህን፣ ህልምህን መኖር ትጀምራለህ። አዎ! በትልቁ ለማሰብ፣ የተሻለውን ለመምረጥ፣ የተሻለ ቦታም ለመገኘት ግዴታ የተፈጥሮን የጊዜ ኡደትና ለውጥ መጠበቅ አይኖርብንም። ስላለን የጊዜን ሽግግር፣ የአመታትን ልውውጥ እናያለን። ከእይታችን ባሻገር ግን የለውጡ ተሳታፊ፣ የሽግግሩም ተካፋይ መሆን ይኖርብናል። ከንግርቱና ከትረካው በላይ በአዲስ ዘመን ተነሳሽነት ሙሉውን አመት በደስታና በፍቅር ማሳለፍ፣ ነገ በሚያረጀው የዛሬ አዲስ አመት የማያረጅ ዘላቂ የህይወት መሰረት ማስቀመጥ፣ የህይወት ስንቅም መሰነቅ የተሻለው አስደሳች ምርጫ ነው። አዎ! ጀግናዬ..! አንተም አዲስ ነህ፤ በዘመን ከፍታ ከፍ የምትል፣ በአዲስ ተፈጥሮአዊ መስተጋብር የምትደምቅ፣ የለውጥ ወዳጅ፣ እድገትን ፈላጊ ልዩነትን የምትፈጥር ብርቱ ሰው ነህ። ሃሳብህ አዲስ ነው፤ ምልከታህ፣ እይታህ አዲስ ነው። በጊዜያት መታደስ ውስጥ እራስህን አድስ፤ በዘመን ልውውጥ እራስህን ለውጥ፣ በዘመን ሽግግር ችግሮችህን፣ ፈተናዎችህን ጥለህ ተሻገር። ዘመን ብቻውን አይታደስምና በታደሰና በተሻለ ስብዕና ተቀበለው። ደስታን ተሞላበት፣ ሃሴትን አድርግበት፣ በፍካት በድምቀት ጎልተህ ታይበት።                🌼🌼🌻🌼🌼 መልካምነትን ከስኬት፣ ከፍታን ከደስታ የሚያስተሳስር የድንቅ አድራጊነታችን ማሳያ የሚሆን፣ የተረጋጋና ሰላማዊ አዲስ አመት ይሁንልን!                 🌼🌼🌻🌼🌼 ምክረ-አዕምሮ ለተሻለ ነገ! 🦋
Show all...
ዘጸአት 14 (Exodus) 16፤ አንተም በትርህን አንሣ፥ እጅህንም በባሕሩ ላይ ዘርጋ፥ ክፈለውም፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ። 21፤ ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የምሥራቅ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፥ ባሕሩንም አደረቀው፥ ውኃውም ተከፈለ። 22፤ የእስራኤልም ልጆች በባሕሩ መካከል በየብስ ገቡ፤ ውኃውም በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ሆነላቸው።   ወዳጆቼ ሆይ 👇👇 ሳያደርሳችሁ እና ላያስወርሳችሁ እግዚአብሔር አያሻገርም ። እስራኤላውያን እግዚአብሔር ቀይ ባሕሩን ከፍሎ ያሻገሬ ላያስወርስ አይደለም። በምድረ በዳ እንድሞቱ ብፈልግ ኖሮ አያሻግርም ነበር። በቃ እመኑ ያሻገራችሁ እርሱ ያደርሳችኃል    ያስጀመራችሁ ጌታ እርሱ ያጨርሳችኃል    ያሳያችሁ እግዚአብሔር ያስወርሳችኃል   በቃ 2015 ዓ.ም የመውጣት፤ የመሄድ፤ የመድረስ፤ የመውረስ ነው።
Show all...