cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ኤል -ሮሂ

" ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤" (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1:15) https://t.me/joinchat/AAAAAE2u_m2ZXQFlT2w-5w

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
234
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

አባታችን እግዚአብሔር ሆይ፦    ለኛ ለልጆችህ ስላደረክልን ፍቅርህ፣ ታማኝነትህና ገናናው ምህረትህ እናመሰግንሀለን። በእውነት በእዚህ ምድር ላይ ካጋጠሙን ክፋቶች ሁሉ የሚልቅ ፍጹም ፣ ቅዱስ ፣ እምነት የሚጣልበት አምላክ ነህና እናመሰግንሀለን፡፡ እየጠቀመን የከለከልከን፣ እንደሚጎዳን እያወክም የሰጠኸን አንዳች የለምና እናመሰግንሀለን። ኃጢአትን የሚጠየፍ፣ ክፋትን የሚሸሽ፣ ሐሰትን የሚጠላ ልብን ስጠን። ከፈተና አርቀን ወዳንተ አስጠጋን። የምንጠብቀው ተስፋችንን ኢየሱስ  ክርስቶስን ላክልን። በኢየሱስ ስም አሜን! ✍አዶኒ
Show all...
♨️ኢየሱስ ይመጣል! 💢ከዚህም በኋላ አየሁ፤ እነሆ፤ በዙፋኑና በበጉ ፊት ማንም ሊቈጥራቸው የማይችል ከሕዝብ፣ ከነገድ፣ ከወገን፣ ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሕዝብ ቆመው ነበር፤ እነርሱም ነጭ ልብስ ለብሰው፣ የዘንባባ ዝንጣፊ በእጃቸው ይዘው ነበር።በታላቅ ድምፅም እንዲህ ብለው ጮኹ፤ ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው፣ የአምላካችንና የበጉ ነው።”እንዲህም ይሉ ነበር፤ “አሜን፤ ውዳሴና ክብር፣ ጥበብ፣ ምስጋናና፣ ሞገስ፣ ኀይልና ብርታትም፣ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ለአምላካችን ይሁን፤ አሜን። 💢ብዙ ሰዎች ከበጉ ጋር ዘላለም እንደምንኖር ያምናሉ ግን፤ ዘላለም ሲባል ጊዜ ብቻ ያደርጉታል፡፡ዘላለም ከበጉ ጋር እንኖራለን ስንል ዝም ብለን መኖር መኖር አይደለም፡፡የምንኖረው የበጉን የሕይወት አይነት ነው፡፡ታውቃላችሁ እግዚአብሔር ዓለማትን ሳይፈጥር በፊት ብቻውን ነበር፤ አሁንም ለዘላለም ይኖራል! ታድያ እግዚአብሔር አንድም ቀን ተሰላችቶ አያውቅም፡፡ ምክንያቱም በጊዜ ብዛት ሳይሆን የሚኖረው ጊዜው በራሱ የሚኖረው በእርሱ መኖር ውስጥ ስለሆነ ነው፡፡ 💢እኛም ዘላለም ስንኖር በጊዜ ብዛት ሳይሆን የምንኖረው የሕይወት አይነት እንደ እግዚአብሔር ነው፡፡ምክንያቱም ኢየሱስ ሕይወትም መንገድም እኔ ነኝ! ስላለ ይሄ የሕይወት አይነት ከወደቀው አዳማዊ ሕይወት አልያም ምድራዊ ሕይወት ሳይሆን ሰማያዊ ከሰማይ የመጣ እግዚአብሔራዊ Life ነው፡፡የእኛ ሕይወት በሰማይ በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰውርዋልና፡፡ 💢በሚገለጠው ሰማያዊ የትንሳኤ አለም ላይ ገዢው መልአክ ሳይሆን የሰው ልጅ ነው፡፡ እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው (ዕብ 2:5)ስለዚህ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው አዲስ ፍጥረት የሆኑት ከእርሱ ጋር ነገስታት (ገዢዎች ) ይሆናሉ ያ የትንሳኤው ዓለም ላይ አዲስ ፍጥረት የሆንነው እኛ ገዢዎች ነን፡፡ምክንያቱም እኛ የተመረጥነው በኤፌሶን 1:3 ላይ በግልጥ እንደተጻፈው ዓለም ሳይፈጠር በፊት በክርስቶስ አስቀድሞ ስለመረጠን ከመረጠንም በኃላ በልጁ ስላፀደቀን፣ ካፀደቀን በኃላ ስላከበረን (ሮሜ 8: 29-30) በሚመጣው ዓለም ገዢ እንድንሆን በልጁ የነበረውን ስልጣን ለእኛም ሰጠን። @onlygrac @onlygrac @onlygrac
Show all...
አጋጣሚ አይደለም መትረፌ መዳኔ የጌታ ተአምር ነው እረ ይገርማል የእኔ ሞት እንቅልፍ ሆነልኝ ጭንቀቴ ቀለለ የረዳኝ ጌታ ነው ውዴ እየተከተለ 🎤🕊🎤🕊🎤🕊🎤🕊🎤🕊🎤 ዝማሬ መላሕክት ያሰማልን 🥀🌷🥀🌷🥀🌷🥀🌷🥀 ስለዝማሬው የዝማሬው ባለቤት ልኡል እግዚአብሔር ይመስገኔ አሜን 🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
Show all...
እንድነጠራ ልጆቹ ተብለን አብ አንድ ልጁን ጨክኖ ሰጠን የሚጠብቀን መልካሙ እረኛ ከቃል በላይ ነው እግዚአብሔር ለእኛ ከእርሱ ተወልዷል ጽድቅን የሚያደርግ ስለተዋጀ በታረደው በግ ከጨለማው ነው ኅጢአት የሚሰራ ህብረት የሌለው ከደሙ ጋራ አለም ባያውቀው እንዳይገርመን በሰማያት ነው ሃገራችንን ዲያብሎስ ስራው ፈርሷል በአዎጅ ተገልጧልና የእግዚአብሔር ልጅ አባት ሆይ ብለን እንድንጣራ ወራሽ እንድንሆን ከበጉ ጋራ የልጅነትን መንፈስ ሰጥቶናል ከሕግ እርግማን ነፃ አውጥቶናል ከውሃውና ከመንፈሱ ነው በዳግም ልደት የተወለድነው በእኛ ዘንድ የለም የፍራት መንፈስ ድፍረት ስላለን ጽድቅን የሚያወርስ ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ልንጠራ አብ እንዴት ያለውን ፍቅር እንደ ሰጠን እዩ፥ እንዲሁም ነን። ”1ኛ ዮሐ 3፥1 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇🍇
Show all...
❤️ #የሕይወት_እንጀራ_እኔ_ነኝ❤️ =========================== 📌📌ዮሐንስ 6 (John) 35፤ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፡— የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ፤ ወደ እኔ የሚመጣ ከቶ አይራብም፡ በእኔ የሚያምንም ሁልጊዜ ከቶ አይጠማም። ✍️ ስለ መብል ስናነሳ የመጀመሪያው አዳም እናስታውሳለን አትብላ የተባለውን እንጨት ላይ የተንጠለጠለ ፍሬ በልቶ ሀጥያተኞችና ሙታን አድርጎን ነበር። ዘፍ 2:16-17, ኤፌ 2:1-3 📌 ኢየሱስ ግን አዳም ያልፈለገው በኤደን ገነት የነበረው የህይወት ዛፍ እርሱ ነበር። ሀጥያተኛና ሙት የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት እንዲያገኝ ከሰማይ የወረድኩ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ በማለት ለሀጥያተኞች መስቀል ላይ ራሱን አሳልፎ በመስጠት ብሉኝ ያለ የህይወት እንጀራችን ኢየሱስ ነው። 📌 ይህን የህይወት እንጀራ የሚበላ ከቶ አይራብም ከቶም አይጠማምና እኛም በእርሱ በማመናችን ለዘላለም እንዳንራብና እንዳንጠማ የህይወት ጥጋብና እርካታ የሆነልን ከአብ ዘንድ የተሰጠን የህይወት እንጀራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ✍️ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለሁላችንም ይሁን።
Show all...
መስቀል ላይ በኃጢአታችን ሳያፍርብን እርቃኑን የተጠረቀልን እዳችንን ከመንገዳችን ጠርቆ ለአሶገደልን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ትኩረት ይገባል! “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ #እርሱንም_በመስቀል_ጠርቆ_ከመንገድ_አስወግዶታል፤” — ቆላስይስ 2፥14
Show all...
ከእስትንፋሴ ይልቅ ታስፈልገኛለህ ከምስበው አየር ለኔ ትበልጣለህ እተነፍሳለው አየሬ ነህ እተነፍሳለው እተነፍሳለው ኢየሱሴን እተነፍሳለው ህይወት ማለት ካንተ ጋራ ያለኝ ህብረት ነው በቃ ምን ዋጋ አለው ሁሉ ሞልቶ በህይወቱ አንተን ካጣ አንተን ይዤ ተራ መሆን አልችልም ውስጤ ያለው ያንተ መንፈስ ቀልድ አይደለም እንደጥንቱ (ኢየሱስ)×2 ያሰኘኛል ፍለጋዬ ከትላንቱ እጅግ ብሷል ዘማሪ ሳሚ ንጉሴ የማርከን ዜማ የመዝሙር ግብዣ @Markengeta @markenzema_bot
Show all...
#ኢየሱስ_ጠበቃችን የኢየሱስ አገልግሎት በሁለት የሚከፈል ሲሆን የተፈጸመና ያልተፈጸመ በመባል ይታወቃል። የተፈጸመ የሚባለው በምድር ላይ ያገለገለው አገልግሎት ሲሆን ይህም ይህም ስለ ኃጢአታችን መሥዋዕት ማቅረቡን ያመለክታል<< እርሱ ግን ስለ ኃጢአት አንድን መሥዋዕት ለዘላለም አቅርቦ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ>> (ዕብ 10፥12)። ያልተፈጸመው አገልግሎቱ ደግሞ አሁን በሰማያዊት መቅደስ የሚያገለግለው አገልግሎት ነው ። ስለዚህ ነገር ቃሉ እንዲህ ይላል << ከተናገርነውም ዋና ነገሩ ይህ ነው በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፥እርሷም በሰው ሳይሆን በጌታ የተተከለች ናት >> (ዕብ 8፥1-2)። ኢየሱስ አሁን ከሚያገለግለው አገልግሎት አንዱ በጌታ ላሉ አማኞች ጥብቅና መቆም ነው። ቃሉ እንዲህ ይላል << ልጆቼ ሆይ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኀለሁ ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው >> (1ዮሐ 2፥1)። ጠበቃ የህግ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ከአንድ ሰው ጎን ተጠርቶ የቆመ ማለት ነው ። አንድ ሰው ተከስሶ ችሎት ፊት ሲቀርብ ከጎኑ ቆሞ ይሟገትለት ዘንድ ጠበቃ ይቀጥራል። ልክ እንዲሁ እኛ ሳንሆን እግዚአብሔር ያዘጋጀልን ጠበቃ ኢየሱስ አለን። ለምን ቢባል ቀንና ሌሊት የሚከሰን ከሳሽ ዲያብሎስ ስላለ (ሪዕ12፥10)። በት.ዘካ 3፥1-5 ያለው ክፍል ስለዚህ ነገር ያስረዳናል ። ታላቁ ካህን ኢያሱ እድፋም ልብስ ለብሶ በመቆሙ ሰይጣን ይከስሰው ዘንድ ቆመ (እድፋም ልብስ የኃጢአት ምሳሌ ነው)እግዚአብሔር ግን ሰይጣንን ገሰጸው የኢያሱን አበሳ አራቀለት እድፋሙን ልብስ አውልቀው ጥሩ ልብስ እንዲያለብሱት እንዲሁም ንጹህ በራሱ ላይ እንዲያደርጉለት በማዘዝ የሰይጣንን ክስ ውድቅ አደረገ። በጌታ ያሉ አማኞች ምንም እንኳ የዳኑ ቢሆኑም አዳማዊው አሮጌ ማንነት በወስጣቸው ስላለ ኃጢአትን ወደው ሳይሆን ተሸንፈው ሊሠሩ ይችላሉ። ቃሉ እንዲህ ይላል << ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን ፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም >> (1ዮሐ 1፥8 )። በጌታ ያሉ አማኞች በኃጢአት ሲወድቁ ሰይጣን ይህን አጋጣሚ በመጠቀም እንዲፈረድባቸው ለክስ ይቆማል። ዳሩ ግን ሰይጣን ለክስ ከመቆሙ በፊት ጠበቃችን ኢየሱስ እኛን ወክሎ ስለ እኛ ቆሞልናል << በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርሷ ወደ ሰማይ ገባ (9፥24)። ሰይጣን ኢየሱስን በማየቱ ብቻ ክሱ ውድቅ ይሆናል ። ምክንያቱም ስለ እኛ ኃጢአት ሆኖ የኃጢአት ደመወዝ የሆነውን ሞት በመሞት እዳችንን ስለከፈለ (ሮሜ6፥23፤2ቆሮ5፥21)። የኢየሱስ ጠበቃ መሆን ኃጢአትን እንድንሰራ የሚያበረታታን ሳይሆን ኃጢአታችንን በመናዘዝ በንስሀ ወደ እርሱ እንድንመለስ የሚያደርገን ነው። በሉቃ22፥31እና ቁጥር 60-62ያለው ቃል ይህን ያስረዳል ። ሰይጣን ደቀመዛሙርቱን እንደ ስንዴ ሊያበጥራቸው ሲለምን ኢሱስ ደግሞ የጴጥሮስ እምነት እንዳይጠፋ አማለደለት። ጊዜው ሲደርስ ጴጥሮስ እንደ ስንዴ በመበጠር ኢየሱስን ካደው ነገር ግን የኢየሱስ ምልጃ የጴጥሮስ እምነት እንዳይጠፋ አደረገ። ጴጥሮስን ኢየሱስ ዘወር ብሎ ተመለከተው ጴጥሮስም አለቀሰ። እዚህጋ ኢየሱስ መካከለኛ መሆኑን እንመለከታለን። ጴጥሮስን ወክሎ ስለ ጴጥሮስ መማለዱ እና እግዚአብሔርን ወክሎ ጴጥሮስን መመልከቱ መካከለኛነቱን ያስረዳናል። ምልጃው እምነቱ እንዳይጠፋ እንዳደረገ ሁሉ መመልከቱ ደግሞ ጴጥሮስን ለንስሀ አበቃው ። ብቼኛ መካከለኛ ይሉታል ይህ ነው እንግዲህ(1ጢሞ 2፥5)። ዛሬም ለእኛ የሚደረገው እንዲሁ ነው። ሰይጣን በኃጢአታችን ሲከሰን ኢየሱስ በጥብቅናው ያሳፍረውና ዘወር ብሎ በቃሉና በመንፈሱ አማካኝነት እኛን ይመለከተናል።በዚህን ጊዜ ተወቅሰን ኃጥአታችንን በመናዘዝ በንስሀ ወደ እርሱ እንመለሳለን(1ዮሐ1፥9)። በኃጢአት ምክንያት የተቋረጠው ህብረታችን ይታደስልናል።እንግዲህ እኛ ሳንሆን እግዚአብሔር ለእኛ ያቆመልንን ብቁ የሆነውን ጠበቃ ኢየሱስን እንጠጋው ምክንያቱም ከቅዱሳን መላእክት ጠበቃ እንፈልግ ብንል መላእክት ሰው ስላይደሉ ጠበቃ መሆን አይችሉም። ሰው ለሰው እንጂ መላእክት ጠበቃ መሆን አይችሉም። ኢየሱስ ግን አምላክ ብቻ ሳይሆን ሰውም ስለሆነ ጠበቃ መሆን ተቻለው።ከሰዎችም ጠበቃ ብንፈልግ በብሉይም ሆነ በአዲስ ኪዳን<<ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ ተብሎ ስለተጻፈ>>(መዝ13፥2-3 ፤ሮሜ 3፥11)።ሁሉም ኃጢአተኞች ስለሆኑ(3፥23) በኃጢአታቸው ተከሰዋል<<አይሁድም የግሪክ ሰዎችም ሁሉ ከኃጢአት በታች እንደሆኑ አስቀድመን ከሰናቸዋልና>> (ሮሜ 3፥9)።እንግዲህ ተከሳሽ ከክስ ነጻ የሆነ አካል በጠበቃነት ያቆማል እንጂ እንደርሱ ተከሳሽን በጥብቅና ቢያቆመው ሁለቱም ተያይዘው ወደ ወኅኒ ይወርዳሉ።መላእክትም ሰውም ጠበቃ መሆን አይችሉም ። ጠበቃ ኢየሱስ ብቻ ነው። ከዚህ ባለፈ <<እከሌ እከሊት ዋስ ጠበቃ ናቸው የሚለው በጌታ ቃል ሲመዘን አንድም ስንዴ የሌለበት እንክርዳድ ብቻ መሆኑ ስለተረጋገጠ እንኳን ደስ አላችሁ። እንግዲህ ንጹህ ስንዴ ትክክለኛ ጠበቃ ወደ ሆነው ኢየሱስ ዘወር በሉ። ኢየሱስን ጠበቃችን አድርገህ ስላቆምክልን አብ አባት ሆይ በልጅህ ተባረክ። https://t.me/joinchat/AAAAAE2u_m2ZXQFlT2w-5w
Show all...
ኤል -ሮሂ

" ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም ዋና እኔ ነኝ፤" (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1:15)

https://t.me/joinchat/AAAAAE2u_m2ZXQFlT2w-5w

በቂ ነው! ለመዳን ከወደድን የፈሰሰው የኢየሱስ ደም በቂ ነው።ስለዚህ ሌላ አዳኝ አንፈልግ።እግዚአብሔር የልጁን መስዋዕት ሰውን ለማማለድ በቂ ነው ካለ እኛም ከእርሱ ጋር ሆነን በቂ ነው እንበል እንጂ ሌላ አማላጅ አንሻ። የፈሰሰው ደም እኛን ወደ እግዚአብሔር አስገብቷል።ስለዚህ ከፍጡር ወገን ወደ እግዚአብሔር የሚያስገባን በመፈለግ አንዛል።ደሙ ሐጢአትን ማስተስረይ ችሏል።ስለዚህ ሐጢአቴን አስተስርዪልኝ ብለን ማንንም አንጠይቅ።ደሙ እርግማናችንን ሰብሯል።እርግማን ሰባሪ ፍጡር በመፈለግ አንድከም። "የኮርማዎችና የፍየሎች ደም በረከሱትም ላይ የተረጨ የጊደር አመድ ሥጋን ለማንጻት የሚቀድሱ ከሆኑ፥ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?"ዕብ 9:13 የደሙን ጉልበት መረዳት ይሁንልን። ዲያቆን ኤርሚያስ ኪሮስ
Show all...
ልቤ እርፍ ይላል እደሰታለሁ አባቴ ስለው ኢየሱስ*4 የፍቅር የሰላም ንጉስ ኢየሱስ የሚታየኝ ፍቅሩ የሚታየኝ መውደዱ ሌላውን ሸፍኖ የጋረደብኝ ትኩረቴን የሳበ ይዞ ያስቀረኝ ፍቅሩ ነው ፍቅሩ መውደዱ ነው መውደዱ ምህረቱ ነው መውደዱ የጥበብ ቁንጮ መጀመሪያው የእውቀት ልኩ መጨረሻው የጀግንነት ልክ ወሰን የለው ውበት ሞገሱ እንከን የለው ፈጣሪ ባልሽ እንደተባለ ውድዬ ብልህ ብልህ ፍቅርዬ ወድጄህ ነው በፍቅርህ ወድቄ ማምለክ ማልጠገብ አደናንቄ ተማርኬ ነው ተሸነፌ ነው በቀንና ሌት እንዲህ ምሆነው __ . ፍቅሩ ዘማሪ መዝሙረ ዳዊት
Show all...