en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 792 subscribers, ranking 5 378 in the Religion & Spirituality category and 2 255 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 792 subscribers.

According to the latest data from 15 October, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 238 over the last 30 days and by 2 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 9.60%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 10.09% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 1 516 views. Within the first day, a publication typically gains 1 593 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 14.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 16 October, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

15 792
Subscribers
+224 hours
+1737 days
+23830 days
Posts Archive
እመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ወዳጇ አማኑኤል፣ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ በስደት ላይ ሳሉ ውሃ ቢጠማቸው ቸሩ መድኃኔዓለም ውሃ ያፈለቀላቸውና የጠጡበት ጉድጓድ: (ፎቶዎች በመ/ር ልዋ
+3
እመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ወዳጇ አማኑኤል፣ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ በስደት ላይ ሳሉ ውሃ ቢጠማቸው ቸሩ መድኃኔዓለም ውሃ ያፈለቀላቸውና የጠጡበት ጉድጓድ: (ፎቶዎች በመ/ር ልዋም ሃብቴ ከ አብርሃም ቆሎ ተማሪው ገጸ ላይ የተወሰደ)

#ፎቶዎቹ ፤ እመቤታችን ከልጇ ጋር ያረፈችበት ገዳመ ቊስቋም ማርያም ገጽታ የሚያሳዩ (ፎቶዎች በመ/ር ልዋም ሃብቴ ከ አብርሃም ቆሎ ተማሪው ገጸ ላይ የተወሰደ)
+9
#ፎቶዎቹ ፤ እመቤታችን ከልጇ ጋር ያረፈችበት ገዳመ ቊስቋም ማርያም ገጽታ የሚያሳዩ (ፎቶዎች በመ/ር ልዋም ሃብቴ ከ አብርሃም ቆሎ ተማሪው ገጸ ላይ የተወሰደ)

#ፎቶዎቹ ፤ እመቤታችን ከልጇ ጋር ያረፈችበት ገዳመ ቊስቋም ማርያም ገጽታ የሚያሳዩ (ፎቶዎች በመ/ር ልዋም ሃብቴ ከ አብርሃም ቆሎ ተማሪው ገጸ ላይ የተወሰደ) _______________________________ ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡ ይህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭) የክርስቶስ ስደቱ ቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹. . . እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፡፡ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይዋረዳሉ›› ተብሎ በተነገረው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ፈጣን ደመና ያለው ጌታችን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ግብፅ መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡ ፈጣን ደመና የተባለችውም እመቤታችን ነች፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩) በስደቱም ጣዖታተ ግብፅ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፡፡ ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቦና አውጥቶ አሳደደ፡፡ እመቤታችንም ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ያረፈችበትን ተራራ ደብረ ቁስቋምን ባረከችው ቀደሰችውም፤ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት፤ የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡›› ‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡ አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ፣ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡ እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እርሱን ዐይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው የለምና፡፡ እኛ ግን አየን፤ ከዚህ ማደሩንም ተረዳን፤ ዳግመኛም ንጽሕት በሆነች በማርያም ዘንድ አየነው፡፡ ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ በቤተልሔም ስለ እኛ በተዋሐደው ሥጋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ያለን እኛን ከቸርነቱና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ መጥቶ አዳነን፤ ከዓለም ሁሉ ይልቅ ጣዖትን በማምለክ ሲበድሉም ወደ ግብፅ ሀገር ወርዶ በእነርሱ ላይ የመለኮትነት ብርሃኑን በማብራት ታላቅ የሆነ ክብሩን ገለጠ››፡፡ (ድርሳነ ማርያም) ኅዳር ፮ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፤ አሜን፡ ፍቶዎች በመ/ር ልዋም ሃብቴ ከ አብርሃም ቆሎ ተማሪው ገጽ ላይ የተወሰዱ የቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት :: #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

ኅዳር 7 ( ፯ ) የሊቀ ስማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዳሴ ቤቱ ነው :: መክብበ ሰማዕት ፥ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ ኰከበ ልዳ፥ ፀሐየ ፋርስ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤ የኢትዮጵያ ገበዝ፤ ከአውሎ ነፋስ ይልቅ ፈጥኖ የሚደርስ ፈጥኖ ደራሽ ሰማዕት፤ እንደ እናቱ (እኅቱ) ቅድስት ማርያም ርኁሩህ የኾነ፡፡ ኅዳር 7 ቅዳሴ ቤቱ (ለመጀመሪያ ጊዜ የተሠራው ቤ.ክ የተመረቀበትና ቅዳሴ የተከናወነበት ክብረ በዓል) ነው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሚያዚያ 23 ቀን በሰማዕትነት ከሞተ በኃላ አጋልጋዮቹ እጅግ የከበሩ ልብሶችና ያማሩ ሽቶዎች አዘጋጁ በከበረ አገናነዝም ገነዙት በመርከብም ጭነው ወደ ትውልድ አገሩ ልዳ አመጡት ነገር ግን ቤተሰቦቹ በሙሉ ማለትም አባቱ ዘሮንቶስ እናቱ ቴዎብስታ እህቶቹ ማርታና እስያ እንዲሁም አጭተውለት የነበረች እጮኛው ሁሉም ሞተው አገኙዋቸው፤ እንድርያስ የሚባል አጎት ነበረው ስጋውን ተቀበላቸው አገሬው ተሰበሰበ የእየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳስ አባ ቴዎድሮስ ተጠርቶ መጣ ቤተክርስቲያኑን አነጹለት ስጋውንም በዚያ በክብር አኖሩት፤ በዚህች ቀን እጅግ ብዙ የሆነ ድንቅ ታአምራትና ታላላቅ ኃይላት ተደረጉ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስቲያን ይህንን ቀን ታከብረዋለች። ታላቁ ንጉሳችን እምዬ ምኒሊክ አራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን ሲሰሩ ከዚሁ ከልዳ የቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር ካለበት አፈሩን በመርከብ ከዚያም በበቅሎ አስጭነው አምጥተው ለቤተክርስቲያኑ መሰረት እንዳደረጉት እና ቅጥሩን ዙርያውንም እንደነሰነሱት መጻሕፍት ይናገራሉ ፡፡ ፠ ፠ በዓሉ በድምቀት በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ.ክ (በአራዳ ጊዮርጊስ) ይከበራል ———- ፨ ኅዳር ፯፤ (የአቡነ ገብረ እንድያስ በዓለ ዕረፍትና ነው)፨ ፠ ዕፁብ ድንቅ የኾነ ተዓምራትን የሚሠሩት እንጨቱ ጸበላቸው_=ውስጥ ሲገባ መቊጠሪያ የሚያደርጉት ፤ (በፎቶ የምታዩት)፤ ፠ በጠበላቸው ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተዓምራትን የሚያደርጉት ፠ ፻ ትውልድ የሚያስምሩት፤ ፠ በደንጊያ ሠረገላነት የሚጓጓዙት፤ ፠ ከ፯ቱ ቅዱሳን ዘጋሥጫ አንዱ የኾኑት፤ #አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_በዓለ_ዕረፍታቸው_ነው፨ ቦታቸውን ክርስቲያን የኾነ ኹሉ ሊያየው የሚገባ የተዓምራት ቦታ ነው፤ ✤✣✤ #ጻድቁ_አቡነ_ገብረ_እንድርያስ_ዘወለቃ_ወዘደብረ_ቆዘት_፤ ✤አባታቸው ተንሥአ ክርስቶስ፥ እናታቸው አርሴማ ሲባሉ፥ የትውልድ ሀገራቸው ወሎ፥ ቦረና፥ ጋሥጫ ሲኾን፤ የቀድሞ ስማቸው ንፍታሊም ይባል ነበር። ✤ ለትምህርት ሲሄዱ መምህራቸው ብዙኃኑን የምታድን ጻድቅ ትሆናለህ ብለው ትንቢት የተናገሩላቸው ሲኾን፤ የመጻሕፍትን ትርጓሜ በደንብ ካስተማሯቸው በኋላ ንፍታሊም ይባል የነበረውን የቀድሞ ስማቸውን ለውጠው ገብረ እንድርያስ አሏቸው። ✤ ጻድቁ በአቡነ ከማ ገዳም ለረጅም ጊዜ በታላቅ ተጋድሎ አገልግለዋል፤ ብዙ አባቶች ሱባኤ በሚይዙበት በስኮሩ ሥላሴ ቤተክርስትያን ጸሎት ሲያደርጉ ቅዱስ ዑር(ራ)ኤል በወርቅ ጽዋ ማየ ሕይወት አጠጥቷቸዋል። ✤ ጻድቁ አባታችን ሙታንን በማስነሳትና ድውያንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን ሲያደርጉ ኖረዋል። ✤ ጻድቁ ዐርብ ፥ ዐርብ የጌታችንን ቅዱስ ሥጋውን ና ክቡር ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም ይመላለሱ የነበረው በአየር ላይ ድንጋዩን እንደ ሰረገላ ፥ ዋርካውን እንደ ጥላ እየተጠቀሙበት ነበር። ይህ ሰረገላ የሆነው ድንጋይ በገዳማቸው ዛሬ ድረስ ይገኛል። (ፎቶውን ይመልከቱ) ✤ ጻድቁ አባታችን እግዚአብሔር ኀጥአንን እንዲምርላቸው ርቀት ወንዝ ከተሰኘው ቦታ በአንገታቸው ላይ በጣም ትልቅ ድንጋይ እየተሽከሙ ይጸልዩ ነበር። በዚህም ይጸልዩበት በነበረው ወንዝ ውስጥ በተአምራት መቊጠርያ የሚሰራ ጸበል ፈለቀላቸው፤ ጠበላቸው ውስጥም እንጨት ሲነከርበት እንጨቱ በተአምራት መቊጠርያ ሆኖ ይወጣል፤ ይኸውም መቊጠሪያ ለብዙ ሕመሞች መድኀኒት ነው፡፡ (ፎቶውን ይመልከቱ) ✤ ✤ ✤ አቡነ ገብረ እንድርያስና ሊቀ ሰማዕቱ ስለ ሃገራችን በተቀበሉት ቃል ኪዳን ሰላምና ጤና ያውርዱልን፤ ጠላታችንን ከሃገራችን ያባርሩልን፨ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

ኅዳር ፮፤ በግብፅ ሀገር ባለች ደብረ ቊስቋም ዋሻ ከ፫ ዓመት ከ፮ ወር ስደቷ ያረፈችበት፡፡ የቊስቋም ክብረ በዓል የሚከበርባቸው #ገዳማትና_አድባራት የተወሰኑት ፨ መንበረ ንግሥት ቊስቋም ማርያም_ቤ/ክ_፤ ዓመቱን ሙሉ ዝክር በማኅበረ_ሰላም መድኀኔዓለም የሚዘከርባት ቤ/ክ) 📍 ሽሮሜዳ (መነን) ቊስቋም፤ ፨ቃሊቲደብረ_ገነት_ቅዱስ_ሚካኤልና_ደብረ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤ (ቃሊቲ ቊስቋም) 📍 ቦሌ /በቀለበት መንገድ/ ፨ ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤ/ክ፤ 📍 /በቀለበት መንገድ.../ _____________ ፨ ኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ፤በድርብነት፤ 📍 አጣና ተራ ..ጠሮ ፨ ጉለሌ ሸጎሌ ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ፤በድርብነት፤ 📍 ሸጎሌ ፨ ማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ፤በድርብነት፤ 📍 (መርካቶ) → የሺ ደበሌ፡፡ ፨ ደብረ ኢያሪኮ መድኀኔ ዓለምና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፤በድርብነት፤ 📍 ላፍቶ፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

ኅዳር ፮፤ በግብፅ ሀገር ባለች ደብረ ቊስቋም ዋሻ ከ፫ ዓመት ከ፮ ወር ስደቷ ያረፈችበት፡፡ የቊስቋም ክብረ በዓል የሚከበርባቸው #ገዳማትና_አድባራት የተወሰኑት ፨ መንበረ ንግሥት ቊስቋም ማርያም_ቤ/ክ_፤ ዓመቱን ሙሉ ዝክር በማኅበረ_ሰላም መድኀኔዓለም የሚዘከርባት ቤ/ክ) 📍 ሽሮሜዳ (መነን) ቊስቋም፤ ፨ቃሊቲደብረ_ገነት_ቅዱስ_ሚካኤልና_ደብረ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤ (ቃሊቲ ቊስቋም) 📍 ቦሌ /በቀለበት መንገድ/ ፨ ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤ/ክ፤ 📍 /በቀለበት መንገድ.../ _________________ ፨ ኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ፤በድርብነት፤ 📍 አጣና ተራ ..ጠሮ ፨ ጉለሌ ሸጎሌ ኪዳነ ምሕረት ቤ/ክ፤በድርብነት፤ 📍 ሸጎሌ ፨ ማኅደረ መለኮት ወይብላ ቅድስት ማርያም ቤ/ክ፤በድርብነት፤ 📍 (መርካቶ) → የሺ ደበሌ፡፡ ፨ ደብረ ኢያሪኮ መድኀኔ ዓለምና መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቤ/ክ፤በድርብነት፤ 📍 ላፍቶ፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like