en
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 335 subscribers, ranking 5 641 in the Religion & Spirituality category and 2 191 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 335 subscribers.

According to the latest data from 15 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -80 over the last 30 days and by -1 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 22.23%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 10.47% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 409 views. Within the first day, a publication typically gains 1 605 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 22.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 16 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

15 335
Subscribers
-124 hours
-117 days
-8030 days
Posts Archive
፪. ቦሌ አራብሳ ዘንዶ አስራ በዓታ ማርያም፤ መንግሥት (ግቢ ገብርኤል) ጋራ፤ ፫. ቂሊንጦ መካነ ፍስሐ ቅዱስ ሚካኤልና በዓታ ለማርያም ቤ.ክ.፤ ቂሊንጦ አደባባይ፤ ፬. ኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስትሥላሴ ቤ.ክ፤ ጠሮ፡፡ ታክሲ፤ ከአራዳ ጊዮርጊስ ሞቢሉ ጋር (4 ኪሎ) → ፈረንሳይ/ኢየሱስ/፤ ፮. ላፍቶ ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ፤ ላፍቶ፡፡ ፯. ፉሪ መካነ ቅዱሳን አቡነ ገብረመንፈስቅዱስ እና ቅዱስ ሚካኤል ለቡ(ፉሪ)፡፡ ፰. ቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ቤ.ክ.፤ ሰፈረ ገነት፡፡ ፱. ኮተቤ የካ ደብረ ምሕረት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት፤ (ብረታ ብረት)፡፡ ፲. ቱሉ ዲምቱ ደብረ ሰላም ቅዱስ ጊዮርጊስና ቅዱስ ሚካኤል ቤ.ክ.፤ አቃቂ ኬላ፡፡ ፲፩. ደብረ ሰሊሆም መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና መድኃኔ ዓለም ቤ.ክ.፤ ታክሲ፤ ከፒያሳ → ቃሊቲ → በርታ ሰፈረ ሰላም፡፡ #በመላው_ኢትዮጵያ ፲፫. ደብረ ኤረር በዓታ ወልደታ፤ (በ4ኛው ክፍለ ዘመን በአብርሃ ወአጽብሃ የተመሠረተ፤ የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ምድር፤ የምሥጢር ቦታ) (ዱከም) → ደብረ ኤረር፡፡ ፲፬. ባሕር ዳር ጽርሐ አርያም ደብረ ሲና በዓታ ለማርያም ቤ.ክ. (በ1313 ዓ.ም. በአቡነ ዘዮሐንስ የተመሠረተች)፤ ባሕር ዳር ፲፭. ጎንደር ደብረ ኀይል ወደብረ ጥበብ በዓታ ለማርያም /ወዑራኤል/፤ (የታች ቤት አቋቋም ዋና ምስስከር) (በጎንደር ዘመነ መንግሥት በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተመሠረተች) ጎንደር ፲፮. ጂንካ በዓታ ለማርያምና ቅድስት አርሴማ ቤ.ክ.፤ ጂንካ #የመልአኩ_የፋኑኤል_በዓል_ከሚከብርባቸው ፩. ካራ ቆሬ ቅዱስ ፋኑኤል፤ ካራ ቆሬ፡፡ ፪. መዝገበ ምሕረት ቅዱስ ፋኑኤል ቤ.ክ.፤ አያት አደባባይ፡፡ ፫. ቅዱስ ፋኑኤል #የአቡነ_ዜና_ማርቆስ በዓል ፩. ደብረ ብሥራት አቡነ ዜና ማርቆስ ጅሩ → ደብር፡፡ ፪. ምሁር አክሊል አቡነ ዜና ማርቆስ ወልቂጤ → ምሁር፡፡ ፫. ጣፎ አቡነ ዜና ማርቆስ → ጣፎ፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot • YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

እንኳን አደረሳቹህ | ታኅሣስ 3 #✤ በአታ ለማርያም፤ ✤ በዓለ ሢመቱ ለቅዱስ ፋኑኤል ሊቀ መላእክት፤ ዕረፍቱ ለአቡነ ዜና ማርቆስ እመቤታችን አባትና እናቷ ኢያቄምና ሐና በስዕለት(ለቤተ መቅደስ ሊሰጡ ብፅዓት ገብተው) ያገኟት ናት፡፡ በአባት በእናቷ ቤትም ፫ ዓመት ተቀመጠች፤ ከእንግዲህ ወዲያማ ስእለት መብለት ይሆንብን የለምን ወስደን እንስጥ ብለው ይዘዋት ወደ ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዘካርያስም ሕዝቡን ሰብስቦ ጉባኤ አድርጎ ቆያቸው። **ከዚያውም ደርሰው እነሆ ተቀበሉን አሏቸው እነርሱም እንቀበላለን ብለው ቢያዩዋት ከፀሐይ ፯ እጅ አብርታ፥ ከመብረቅ ፯ እጅ አስፈርታ፥ ዕንቈ ባሕርይ መስላ ታየቻቸው፤ እነርሱም እኛ ይህችን የመሰለች ፍጡር ምን እናደርጋታለን? ምን እናበላታለን? ምን እንጋርድላታለን? ብለው ሲጨነቁ በዚህም መካከል እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያም መንፈሳዊ ረኀብ ተነስቶባት ምርር ብላ አለቀሰች። ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል በመሶበ ወርቅ ኅብስት ሰማያዊ፤ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ታያቸው፡፡ ሕዝቡም ዘካርያስን አባታችን ይህ የወረደው ክብር ላንተ ነው የሚኾነውና ተነስተህ ታጥቀህ እጅ ነስተህ ሰግደህ ተቀበል አሉት፤ ዘካርያስም እሽ ብሎ እጅ ነስቶ ሰግዶ እቀበላለሁ ብሎ ሲጠጋ ወደ ሰማይ ራቀው፥ መጠቀው፡፡ ከሕዝቡም እያንዳንዱ እየተነሱ እንቀበላለን ብለው ቢያዩ ወደ ሰማይ ራቃቸው፥ መጠቃቸው፡፡ **ከዚህም በኋላ ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ ለናንተ ለእንግዶች የወረደ ክብር እንደሆነ ሕፃኒቱን ይዘሽ ወደዚያ ፈቅ ብለሽ ተቀመጪ አላት፡፡ እርሷም ሕፃኒቱን ይዛ ወደዚያ ፈቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ መልአኩም ከራሳቸው ላይ ረቦ አልወርድም አለ፡፡ ***ሁለተኛም ዘካርያስ ሐናን ጠርቶ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ነገር የሚያውቅ የለም፤ ሕፃኒቱን ከዚያው ትተሽ አንቺ ወዲህ ነዪ አላት፤ እሽ ብላ ሕፃኒቱን እዚያው ትታ ወደነሱ ሄደች፡፡ ያን ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወርዶ ፩ ክንፉን ጋርዶ ፩ ክንፉን አጎናፅፎ ኅብስቱን አብልቷት፥ ወይኑን አጠጥቷት፤ እመቤቴ ሆይ መንገድ ባስመታሁሽ ማሪኝ ብሎ የብርሃን መሶብ፥ የብርሃን ጽዋ ይዞ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ **ሕዝቡም የምግቧማ ነገር ከተያዘ ከሰው ጋራ ምን ያጋፋታል፤ ቦታዋ ከቤተ መቅደስ ይሁን እንጂ ብለው ዙፋኑን ዘርግተው፥ ምንጣፏን አንጥፈው፥ መጋረጃውን ግራና ቀኝ ጋርደው ከቤተ መቅደስ አኖሯት፡፡ ***ይኸውም የተደረገው ታኅሣሥ ፫ ዕለት ነው፤ በአታ የሚለው ስያሜም የተሰጠው በዚሁ ነው፡፡ ‹‹አመ ፫ ለታኅሣሥ በኣታ›› እንዳለ መቅድመ ተአምር፡፡ በዚህም፤ #መቅደሲቱ_ወደ መቅደስ ገባች፤ #ቅድስቲቱ_ወደ ቅድስት ገባች፤ #ክብርቲቱ_ወደ ክብርት ቤቷ ገባች፤ #ልዩ_የሆነችው_ወደ ልዩ ሥፍራ ገባች፤ #ቅድስተ_ቅዱሳኗ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ገባች፤ #ንጽሕተ_ንጹሐኗ ወደ ንጽሕ አዳራሽ ገባች፤ #ቤተ_መቅደሷ ወደ ቤተ መቅደስ ገባች፡፡ ሊቃውንትም ‹‹መቅደስ ዘኢትትነሠት /የማትፈርሺ መቅደስ ነሽ››/ እያሉ አመሠገኗት፡፡ **እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ኅብስት ሰማያዊ እየተመገበች፤ ስቴ ሕይወት እየጠጣች ከመላእክት ጋራ እየተጫወተች 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ተቀመጠች፡፡ ‹‹ከመዝ ነበርኪ ውስተ ቤተ መቅደስ፤ ወመላእክት ያመጽኡ ወትረ ሲሳየኪ ከመዝ ነበርኪ ፲ተ ወ፪ተ ዓመተ እንዘ ትትናዘዚ እምኀበ መላእክት ወስቴኪኒ ስቴ ሕይወት ውእቱ። ወመብልዕኪኒ ኅብስት ሰማያዊ››። እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ***ምግቧ ከየት የተገኘ ነው ቢሉ በገበሬ እጅ ያልተዘራ በቤተ ሰብእ እጅ ያልተሠራ በእግዚአብሔር እጅ የተፈጠረ ያማረ የተመረጠ ነው እንጂ ፡፡ ‹‹ኦ ድንግል አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይኪ፤ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እም ሰማየ ሰማያት ዘበሰለ፡፡ ኦ ድንግል አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይኪ አላ ስቴ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘተቀድ›› (ድንንግል ሆይ ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን እንጂ፡፡ ድንግል ሆይ ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለሽም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጥን ነው እንጂ፡፡) /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/። ***ስታድግም በንጽሕናና በቅድስና ነው፡፡ ‹‹ድንግል ሆይ አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም በንጽሕና በቅድስና ኖርሽ እንጂ።›› /እንዳለ ሊቁ አባ ሕርያቆስ/ ***እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በቤተ መቅደስ ሳለች አይሁድ ብዙ የክፋት ምክር ይመክሩ ነበር። ከዚህም ውስጥ አንዱ መጥቁል ወደሚባል ጠንቋይ ሄደው ‹‹ፍታሕ ማዕከሌነ ኢያቄም ወሐና›› ብለው እመቤታችንን እንዲያጠፋ እጅ መንሻን ሰጡት፤ መጥቁልም በመካከል አይሁድ በኋላ ሁነው ነጋሪት እየጎሰሙ፥ እምቢልታ እየነፉ እመቤታችንን እግዝእትነ ማርያምን ለመግደል ለቤተ መቅደስ ፪ ምንዳፈ ሐፅ ሲቀራቸው፤ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ እዚያ ድረስ ያልተደረገና ያልተነገረ መብረቅ ነጎድጓድ ወርዶ አጋንንትንም፥ መጥቁልንም፥ አይሁድንም ቀጥቅጦ አጠፋቸው። እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም በማግሥቱ ወጥታ አይታ መጥቁል ሆይ እኔን አጠፋ ብለህ መጥተህ አንተ እንዲህ ሆንህ ካንተ መከራ መዓት ያወጣኝ አምላክ ይክበር ይመስገን ብላ ፈጣሪዋን አመሰገነች፡፡ ከዚህ በኋላ በድኑ ለዝክረ ነገር የ፫ ቀን መንገድ እየሄደ ይሸት ጀመር። እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ‹‹ዮሰሜር፣ አድሜሽ፣ ድቸር፣ አዶናዊሮስ፣ ሰራሰቅሰሬል›› ብላ የአምላክ ኅቡዕ ስምን ብትደግም መሬት ተከፍቶ ዋጣቸው ከነሥጋቸውም ሲኦል ወረዱ፡፡ ከዚህ በኋላ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም እጅግ ታፈረች የሚናገራት ጠፋ ‹‹ኦ ግርምት ድንግል›› /እንዳለ ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም/። ✤#በዓለ_ሢመቱ_ለቅዱስ_ፋኑኤል_ሊቀ_መላእክት፤ #ሰዳዴ አጋንንት ነው፤ /ሄኖክ 10፥8፣ ድርሳን ዘፋኑኤል/ #መጋቤ ድንግል ነው፡፡/ተአምረ ማርያም/ #ማኅሌታዊ ነው፤ #በመንበረ መንግሥቱ ዙሪያ ከሚቆሙት ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው፡፡ /ሄኖክ 20፥39/ #በአራቱ የዓለም ማዕዘናት ሹም አንዱ ነው፡፡ #ለመልካም ነገሮች ከሚራዱ መላእክት አንዱ ነው /መዝ. 33፥7/ #ካህነ ንስሐ ነው /ሄኖክ 10፥5/ #ዐቃቤ ጻድቃን ነው፡፡ /2ኛ ነገ. 6፥14/ #ምስለ_አብያጺሁ_ከመ_አብ_እንዘ_ይሴስየኪ_መና፤ #ፋኑኤል_ጽጌ_ነድ_ዘይከይድ_ደመና፡፡ ✤#ኢትዮጵያዊው_አቡነ_ዜና_ማርቆስ_በዓለ_ዕረፍታቸው ነው፡፡ እኒህ ታላቅ አባት በምድረ ጉራጌ በሚገኘው በምሁር ኢየሱስ ገዳም 40 ዓመታትን ሱባኤ የገቡ፤ ምድረ ጉራጌን (ሙሉ ሸዋን ጨምሮ እስከ ደቡብ) እንዲሁም በሌሎችም የሃገራችን ክፍሎች ያስተማሩ፤ በርካታ ሊቃውንትን /አባ ጽጌ ድንልንና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታን ጨምሮ ሌሎችን ሊቃውንትም/ ያፈሩ ፈርጥ ሲኾኑ፤ በስተመጨረሻ በተአምራት የተሞላውን ታላቁን ገዳም #ደብረ_ብሥራትን (ጅሩ) መሥረተው በክብር አርፈዋል፡፡ #ክብረ_በዓሉ_ከሚከብርባቸው_አድባራትና_ገዳማት #በአዲስ_አበባ ፩. ዳግማዊ ምኒልክ መታሰቢያ ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም፤ (ግቢ ገብርኤል) ጋራ፤

*በጥንታዊው ደብረ ኃይል እንጦጦ ቅዱስ ራጕኤል ወኤልያስ፤ *በደብረ ኤልያስ ጎጃም፤ *በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን (በድርብነት አለ) *መካነ ሕያዋን ቅዱስ ኤልያስ ኋላ መካነ ሕያዋን ጎፋ ቅዱስ ገብርኤል የተባለ ፤ *በሻሸመኔ ልደታና በሌሎችም የቅዱስ ኤልያስ አድባራትና ገዳማት ይከበራል፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot • YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w

እንኳን ለቅዱስ ኤልያስ ዓመታዊ ክብረ በዓል (የልደት ቀን) በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ነቢያት ዝናም በማቆም ብቸኛ ነቢይ፡፡ ✤ የሰማርያው ነቢይ ኤልያስ ከቅዱሳን አበው ነቢያት አንዱ ሲኾን አባቱ ኢያሴዩ ይባላል፡፡ በነቢይነትም ሆነ በብቃት ኤልያስን የሚያክል፤ በሥራው የሚወክል ከእሱ በፊትም ኾነ በኋላ በተአምራት የተሞላ እሳት ለበስ ነቢይ እሱ ከመረጠው ከደቀ መዝሙሩ ከኤልሳዕ በቀር አልተነሳም፡፡ ነቢዩ ኤልያስ ከኢዮርብዓም እስከ እርሱ ድረስ ለአያሌ ዓመታት በሰይጣን ግፊት በሰው ሠራሽ ጣዖት የተመረዘ በኃጢአትም ረዘረዘ፣ የግፈኛው አክአብና የዘማዊቷ ኤልዛቤልን መንግሥት በሦስት ዓመት ከመንፈቅ በከባድ ድርቅ በመናጥ፣ እንዲሁም አፈር እንደበላው ብረት የዛገ አስተሳሰባቸውን በሰው ደምና በቅሚያ ገንዘብ የተሞላ ሰውነታቸውን በማን አለብኝነት ያበጠ ልባቸውን እንደሰም በማቅለጥ የሚይዙትንና የሚጨብጡትን ያሳጣ በፈጣሪው ለዚህ ሥራ የተመረጠ ሰመ ጥር ነቢይ ነው፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ነውና፡፡ ኤልያስ የከተማ ነቢይ ብቻ አይደለም ባሕታውያን ተብለው ከሚጠሩት ነቢያተ ጽድቅም አንዱ እንደነበር ሕልውናው ምስክር ነው፡፡ (( ኤልያስ ብዙ ነገር ስለሚያስተምር የቀና እምነቱን ውጤት ጥቂት መመልከት እኔ ማነኝ ለሚሉት እጅ ይዞ ይመራል፡፡ ✤ 1. ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ ሰማይ ዝናም ለዘር ጠል ለመከር ከመስጠት እንዲከለከል ምድርም የተከሉባትን እንዳታጸድቅ የዘሩባትን እንዳታበቅል ለባለንብረቱ አመለከተ ይህም ጥያቄው ከእግዚአብሔር መልስ አግኝቷል፡፡ ነገሥ 17፥1-2፡፡ ከዚህ ላይ የሊቀ ነቢያት ሙሴንና የኢሳይያስን ቃል ያስጠቅሳል ዘዳ 32፥1-4፣ ኢሳ 1፥2-5፡፡ በእነዚህ እስከፊ ዓመታት ውስጥ በመሪዎች አመፅ በኤልያስ ተግሣጽ የሚመለከተውም የማይመለከተውም የሚልሰውና ሚቀምሰው አጥቶ በዋለበት እንደ ቅጠል ረገፈ እንደሻሸተ ነጠፈ፡፡ የኀጥአን ፍዳ ጻድቅ ይደፋ ይሏል ይህ ነው፡፡ ዛሬም በአምስቱ ክፍለ ዓለም የብዙኃኑ እልቂት ሲፈጸም የሚታየው በጥቂት እግዚአብሔር የለሽ ሰይጣን ጁንታዎች ሽፍቶች መሆኑን ከአክአብና ኤልዛቤል ይማሯል፡፡ ይህን የኤልያስን ጠበቅ ያለ እገዳ ከስምንት መቶ አምሳው ነቢያተ ሐሰት ካህናተ ጣዖት አንዱም ወደ ሚመለከተው በጸሎቱም ሆነ በመሥዋዕቱ አመልክቶ ሊያስነሳ ወይም ለማስነሳት የቻለ የለም፡ ጠንቋዮችና አታላዮች በብሉይ ኪዳን ብዙ ጊዜ ከቤተ መንግሥት ተለይተው አይርቁም፡፡ 1ኛ ነገሥ 18፥22፣ዳን 2፥1-14፡፡ ✤ 2. አመጸኞች አክአብንና ኤልዛቤልን ምንነታቸውን ካሳወቀ በኋላ የዘጋውን ለመክፈት ወደ ፈጣሪው በመጸለይ ዝናም አዝንሟል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 18፥41-46፣ ያዕ 5 17-18 እግዚአብሔር ለወዳጆቹ የገባውን ቃል ኪዳን አያጥፍም አቁም ሲሉት ያቆማል ስጥ ሲሉት ይሰጣል እንጂ ምን አገባቸው ብሎ እንደፈለገው አያደርግም፡፡ የእግዚአብሔር ሐዋርያ ስለ ኤልያስ ማንነት ሲያደንቅ ኤልያስ እንደኛ ሰው ነበር ዝናም እንዳይዘንም ከለከለ እንደገናም እንዲዘንም አደረገ በማለት በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖች ከቀና ክርስትናቸው ምን እንደሚጠበቅባቸው ከእምነታቸው ምን ማግኘት እንዳለባቸው ይጠይቃል ያዕ.5፥13-20፡፡ ዛሬስ ምን ይመስሎታል፡፡ ኤልያስ በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ ካሉት ቅዱሳን ነቢያት ዝናም በማቆም ብቸኛ ነቢይ ነው፡፡ ነገር ግን በረዶ ያዘነመላቸው አንደኛ ሙሴ ዘፀ 9፥13-21 ሁለተኛ ኢያሱ 10፥9-12 ሦስተኛም ሳሙኤል 1ኛ ሳሙ 12፥1-19 ይመለከታል፡፡ ✤ 3. በተፈጥሮ የማይመስላቸው በቋንቋም የማይግባባቸው እንኳን ለሰው ሥጋ ሊያመጡ ከሰው ሥጋ የሚነጥቁ አሞራዎች ከየት እንደሚያመጡት የማይታወቅ እንጀራና ሥጋ ለምግብ እንዲያመላልሱለት አደረገ 1ኛ ነገሥ 17፥6-7፡፡ እነዚህ አሞራዎች ለሦስት ዓመት ከመንፈቅ በጋ ከክረምት የለምንም እረፍት ኤልያስን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ እምነት ካለ ተአምር መሥራት አይገድም ይህንም ከኤልያስ ይማራል፡፡ ✤ 4.ለአንዲት መበለት ዱቄትና ዘይት አበረከተ፡፤ ኤልያስ ቁራሽ እየለመነ ያደረገውን ተአምር ልብ ይሏል፡፡ 1ኛ ነገሥ. 17፥16-24፡፡ ✤ 5. ዱቄትና ዘይት ያበረከተላት ሴት ልጇ ቢሞት ከሞት አስነሳው 1ኛ ነገሥ. 17፥20-23 ይህች ሴት በእምነቷ አርአያነት ያላት ደገኛ ሴት ናት፡፡ ኤልያስን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ፣ ኀጢአቴንስ ታስብ ዘንድ ልጄንስ ትገድል ዘንድ ወደ እኔ መጥተሃልን ብላዋለች፡፡ ኤልያስም በእግዚአብሔር ኀይል ማንኛውንም ችግር ለመፍታት ሙሉ መብት ነበረውና ወዲያውኑ የሞተውን ብላቴና ጠጋ ብሎ ወደ ፈጣሪው በጸሎት በማመልከት አስነስቶ የብላቴናውን እናት አስደስቷል 1ኛ ነገሥ 17 17-24 ሐዋርያ እምነት ጀግኖችን በመዘገበበት አንቀጽ ይችን ሴት ልብ ይሏል፤ ዕብ 11፥35፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያሉ እናቶች ያስፈልቷል፡፡ ይህችን ሴት የሚመስሉ እናቶች 2ኛ ነገሥ. 4፥18-38 ፣ሉቃ 7፥11-17 ተመዝግበዋል፡፡ በሐዋርያት ሥራም ያሉት እናቶች ከእነዚህ ጋር ያነጻጽሯል የሐዋሥ 9 36-43፡፡ ✤ 6. ለብዙ ጊዜ በቤተ መንግሥት ተሰግስገው አክአብና ኤልዛቤልን በሐሰት ሲደልሉ ግብዝ ሕብረተሰቡን ሲያታልሉ ለፍቶ ያገኘው ገንዘቡን ሲሸልጉ በኀጢአት ሊያስወጉ የነበሩ ነቢያተ ሐሰትና ካህናተ ጣዖትን በሕብረተሰቡ ፊት እስከ መምህራቸው ሰይጣን በቅሌት አከናንቦ ሲያስቅባቸው ውሏል፤ 1ኛ ነገሥ 18 20 -29፡፡ ሰይጣን በሰማርያ በምድር እንደዚያ ቀን ሰው መዘባበቻ በመሆን የውርደት ቀን ገጥሞት አያውቅም፡፡ በገዛ አገሩና መንደሩ፡፡ 7. ወደ ፈጣሪው በጸሎት በማመልከት ያቀረበው ንጹሕ መሥዋዕቱን ከሰማይ እሳት ወርዶ በሰው ፊት በላለት 1ኛ ነገሥ 18 30-40፡፡ በዚህም ማንነቱን በሰይጣንና በሰይጣን አቀንቃኞች ፊት አስመስክሯል፡፡ ✤ 8. ምግብና መጠጥ መልአክ ከሰማይ አመጣለት ያንን ተመግቦ ለአርባ ቀን ያለምንም ምግብ መጠጥ ተጉዟል 1ኛ ነገሥ 19፥5-7 ✤ 9. እሳት ከሰማይ በማዝነም ሊጣሉት የመጡትን መምለኪያነ ጣኦት ምሉአነ ኀጢአት የሰይጣን ሠራዊት በሰው ደም የሰከሩ በዲያብሎስ የሚመሩ ጠላቶቹን አጋይቷል 2ኛ ነገሥ 1 9-13 ✤ 10. በመጎናጸፊያው የዮርዳኖስን ባሕር ከፍሎ ከነ ደቀመዝሙሩ በደረቅ ተሸግሯል 2ኛ ነገሥ. 2፥11 ✤ 11. ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ918 ዓመተ ዓለም ሳይሞት በሕይወቱ መራራው ሞት ዕያየው በብርሃን ሠረገላ ወደሰማይ አርጓል 2ኛ ነገሥ. 2 6-9 ✤ 12. እንደ እያስፈላጊነቱ ከፈጣሪው ጋር ለብዙ ጊዜ ተነጋግሯል ከአንድ እስከ አስራ አንድ ያደረጋቸውን ተአምራት የፈጸመለት ታማኝ ፈጣሪው ሰው በሆነበት ወራት በተራራ ከጓደኞቹ ጋር ብርሃነ መለኮቱን ገለጠለት ማቴ 17 ፥3 ፡፡ ከዚህ ዓለም ከተሰናበቱ በኋላ ወደዚህ ዓለም መጥተው የፈጣሪጣቸውን ሰው መሆን ያዩ ከነቢያተ ጽድቅ ሙሴና ኤልያስ ብቸኞች ናቸው ብፁዓን ከተባሉት ሐዋርያትም ተቆጥረዋል፤ በዚህም ቅዱሳን ከሞት በኋላ እንደሚያማልዱም መስክሯል፡፡ ማቴ 13፥16-17፡፡ ኤልያስ ሰው መባል ወይም ተብሎ በመጠራት እንደማንኛውም ሰው መሆኑ መልአክ አለመሆኑን ሐዋርያ ነግሮናል ያዕ 5፡17-20፡፡ ከኤልያስ ብዙ ነገር ወይም ተግባር ስለሚማሩ ከቅዱስ መጽሐፍ ከ 1ኛ ነገሥ 17፡1 ጀምረው እስከ 2ኛ ነገሥ 2፡11 ረጋ ብለው ይመርምሩ ክርስትናዎትንም ይፈትሹ፡፡ ታኅሣሥ 1 ፤ ክብረ በዓሉ የሚከበርባቸው፤

#ዘመነ_አስተምህሮ በቤተ ክርስቲያናችን የወቅት አከፋፈል ሥርዓት #ከኅዳር_፮ እስከ #ታኅሣሥ_፯ ቀን የሚገኘው ወቅት ‹#ዘመነ_አስተምህሮ› ይባላል፡፡ ቀጣዩ ወቅት (ዘመነ ስብከት) ዕለተ ሰንበትን ጠብቆ የሚገባ በመኾኑ ይህ ወቅት አንዳድ ጊዜ እስከ ታኅሣሥ ፲፫ ቀን የሚዘገይበት ጊዜም አለ፡፡ ‹ዘመነ አስተምህሮ› የሚለው ሐረግ ትርጕሙም በሃሌታው ‹#ሀ› (‹#አስተምህሮ› ተብሎ) ሲጻፍ የቃለ እግዚአብሔር ማስተማሪያ ማለትም የትምህርተ ወንጌል ዘመን ማለት ነው፡፡ ሥርወ ቃሉም ‹‹መሀረ/አምሀረ – አስተማረ፤ ለመምህር ሰጠ፤  መራ፤ አሳየ፤ መከረ፤አለመደ››  ወይም ‹‹ተምህረ – ተማረ፤ ለመደ›› የሚለው የግእዝ ግስ ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፭፻፸፱)፡፡  ይኸውም የእግዚአብሔርን ቸርነት፣ ርኅራኄ፣ ትዕግሥትና የማዳን ሥራውን የሚመለከት ትምህርት በስፋት የሚቀርበበት ጊዜ ነው፡፡ ቃሉ በሐመሩ ‹‹#ሐ›› (‹#አስተምሕሮ› ተብሎ) ሲጻፍ ደግሞ የምሕረት፣ የይቅርታ ዘመን ማለት ነው፡፡ ሥርወ ቃሉም ‹‹መሐረ – ይቅር አለ፤ ዕዳ በደልን ተወ›› ወይም ‹‹አምሐረ – አስማረ፤ ይቅር አሰኘ፤ አራራ፤ አሳዘነ›› የሚለው የግእዝ ግስ ነው (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፣ ገጽ ፭፻፹፬)፡፡ ጠቅለል አድርገን ስንመለከተው ዘመነ አስተምሕሮ ስለ እግዚአብሔር ቸርነትና ርኅራኄ፤ እርሱ በደላችንን ዅሉ ይቅር እንደሚለን እኛ ምእመናንም እርስበርስ ይቅር መባባል እንደሚገባን ትምህርት የሚሰጥበት ጊዜ ነው፡፡ በቅዱስ ያሬድ የዜማ መጻሕፍት እንደ ተቀመጠው በዘመነ አስተምሕሮ ውስጥ የሚገኙ ሰንበታት (እሑዶች) 1ኛ. #አስተምሕሮ፣ (ከኅዳር ፮–፲፪) 2ኛ. #ቅድስት፣ (ከኅዳር ፲፫–፲፱) 3ኛ. #ምኵራብ፣ (ከኅዳር ፳–፳፮) 4ኛ. #መጻጉዕ፤ (ከኅዳር ፳፯ እስከ ታኅሣሥ ፫) እና 5ኛ. #ደብረ_ዘይት፤ (ከታኅሣሥ ፬ – ፮) ተብለው ይጠራሉ፡፡ ከመጀመሪያው ሳምንት (ከአስተምሕሮ) በቀር የአራቱ እሑዶቹ ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ጋር አንድ ዓይነት ነው፡፡ የሰንበታቱ ስያሜ ከዐቢይ ጾም ሰንበታት ጋር ተመሳሳይ ይኹን እንጂ በእነዚህ ሳምንታት ሌሊት የሚዘመሩ መዝሙራት፣ በቅዳሴ ጊዜ የሚነበቡ #ምንባባትና_የሚቀርቡ_ትምህርቶች ግን #በምሥጢር_ይለያያሉ፡፡ ትምህርቶቹ ይለያያሉ ስንልም በዚህ ወቅት የሚነገረው ምሥጢርና ይዘት በወቅቱ ላይ የሚያተኵር መኾኑን ለመግለጽ ነው እንጂ በየትኛውም ጊዜ በቤተ ክርስቲያናችን የሚቀርበው ትምህርት አንዱ የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው። ሳምንታቱን በዚህ መልክ የከፋፈለውም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡ ይህንንም ከመጽሐፈ ድጓው መመልከት ይቻላል (ድጓ ዘአስተምህሮ)፡፡ የአራተኛ ሳምንት መጻጉዕን መዝሙር እና ምንባባት እነሆ ብለናል... • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w