en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 16 049 subscribers, ranking 5 274 in the Religion & Spirituality category and 2 238 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 16 049 subscribers.

According to the latest data from 30 October, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 511 over the last 30 days and by 3 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 23.32%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 10.33% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 742 views. Within the first day, a publication typically gains 1 658 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 29.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 31 October, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

16 049
Subscribers
+324 hours
+1077 days
+51130 days
Posts Archive
በኢትዮጵያ በዋነኛነትና በግንባር ቀደምትነት የስቅለት በዓል የሚከበርበት ታላቁ ገዳም #ዋልድባ (ዋሊ)፡፡ የሕማማትህንና የሞትህን ዜና ስለሰማች ዋልድባ ቅድስት ከዓመት እስከ ዓመት ታለቅሳለች፤ ፈጣሪዋ አምላኳ ስለሆንክ፥ በስደትህ ጊዜ የባረካትና የመሠረትሃት፥ ኋላም እንደ ተሰቀልክ ሆነህ የተገለጽክባትና የቀደስካት በመሆኗ ዓመት እስከ ዓመት በሱባዔ ታስብሃለች፡፡ ዛሬ መጋቢት 27 ግን እንባዋን በቅዳሴ ጭምር የምታብስበት የደስታዋ ቀን ነው፤ ሰብዐ ዓለም ወሰብአ ኢትዮጵያ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፤ ከሰሜን እስከ ደቡብ ተሰብስበው በኢትዮጵያ ደረጃ በዋነኛነትና በግንባር ቀደምትነት የስቅለት በዓልህን ያስባሉ፤ ማዕከላዊና ደቡባዊ የኢትዮጵያ ክፍሎች ከዋልድባ ገዳም በመራቃቸው ብዙሃን ሕዝብ ለክብረ በዓሉ ወደ ዋልድባ ባይሄድም፤ በሰሜናዊ ኢትዮጵያ በተለይም ከጎንደርና ከትግራይ የ7 ዓመት ሕፃናት ሳይቀር ያን በረሐ አቋርጠው ወደ ገዳሙ ይተማሉ ፤ መነኰሳቱም እንደ አሸን ለበዓሉ የሚመጣውን ምዕመን በቋርፍና በጭልቃ፣ በሰሊጥና በሻይ ይቀበሉታል፡፡ ቅዳሴው እንዳበቃም ነፋስ እንደበተነው አሸዋ ባንዴ ሕዝቡ ወደ መንደሩ ይተምማል፡፡ /ዛሬ ወደ ማምሻው ላይ በወር 1ዴ በገዳማትና አድባራት መርሐ ግብራችን ላይ ዋልድባን እንድምንዘግብ በገባነው ቃል መሠረት ገዳሙን እንዘግበዋለን፤ ይጠብቁን፡፡/

142 ዓመታትን ያስቈጠረው ጥንታዊው የጮቢ ደብረ መድኀኒት መድኀኔ ዓለም፡፡ በ1868ዓ.ም. የተመሠረተ፡፡ በምዕራብ ሸዋ ዞን በጀልዱ ወረዳ በጮቢ የሚገኝ፡፡

#ፍኖተ_ሕይወት_/#የሕይወት_ጕዞ/፤ #ሚያዝያ_06/2011ዓ.ም.፡፡ ወደ #ኵሉ_ወይን_ቅድስት_አርሴማ፡፡ **በብዙሃን ዘንድ ዜናው ያልተሰማው፤ 3ት ትላልቅና ሌሎችም ክፍሎች ያሉት፤ ብዙ ንዋያተ ቅድሳት የተገኙበትና በቁፋሮ የተገኘው ጥንታዊ ዋሻ ይጎበኛል፤ **ምክረ አበው በሊቃውንት መምህራን፣ ዝማሬ በዘማርያን ይቀርባል፡፡ **ከሰ/ትቤታችን ምሥረታ ጀምሮ የነበሩና አሁንም ያሉ አባላት በአንድነት የሚሳተፉበት ዐቢይ ጕዞ፡፡ **ለበለጠ መረጃ፤ 0977 30 17 18 (ፎቶው ላይ የምታዩት ተጓዦች፤ ከዚህ በፊት ወደ ኤረር ካደረግነው ጕዞ ላይ የተወሰደ ነው)፡፡

እንኳን ለአምላካችንና ለመድኀኒታችን፤ ለፈጣሪያችንና ለአዳኛችን መድኀኔ ዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፥ አደረሰን፡፡ *ከዋይዜማ እስከ ማኅሌት፤ *ከሰዐታት እስከ ኪዳን፤ *ከቅዳሴ እስከ ዑደተ ታቦተ ሕግ፤ *ከጠዋት የስብከት ጕባኤ እስከ ሠርክ ጕባኤ በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የመድኅነ ዓለም ቤተ ከርስቲያን ተገኝታችሁ እንድታከብሩ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚቆመውን ሥርዐተ ማኅሌት በግእዝና በአማርኛ ትርጕሙን ጭምር አቅርበንላችኋል፡፡ (በታላቁ ደብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ብቻ የሚቆሙትንም ቀለማት ዘቀጨኔ ደብረ ሰላም ብለን አካተን አስቀምጠናቸዋል፡፡

#ነግሥ_ነግሥ_ነግሥ እንኳን ለመድኀኔ ዓለም ጥንተ ስቅለት ክብረ በዓል አደረሳችሁ፡፡ የመድኀኔ ዓለምን ክብረ በዓል በማስመልከት፤ በማንኛውም ወርኀዊና ዓመታዊ ክብረ በዓላት ላይ ማኅሌት ሲቆም፤ መጀመሪያ የሚባለውን ነግሥንና የነግሥ መቅድምን ለመጀመሪያ ጊዜ አዘጋጅተንላችኋል፡፡ *ነግሥ ምን ማለት ነው *ዚቅ ምን ማለት ነው *የነግሥ መቅድምና ነግሥ ቀመረ መረግድ፤ (ማንኛውም ማኅሌት ሲቆም ባለ 5 መስመር ግጥም ሲሆን እያንዳንዱ መስመር 28ት ጊዜ በከበሮና በጸናጽል ይመረገዳል ፤ የአመረጋገዱን ቅደም ተከተል እንዲቀላችሁ በማሰብ በቀመር (በቊጥር አስቀምጠንላችኋል፡፡) ከጽሑፉ ያገኟቸዋል፡፡ ይህን ነግሥ በሁሉም ማኅሌት መጀመሪያ የሚባል እንደመሆኑ መጠን በቃላችሁ አጥኑት፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት/

#ፍኖተ_ሕይወት_/#የሕይወት_ጕዞ/፤ 11 ቀን ቀረው፤ #ሚያዝያ_06/2011ዓ.ም.፡፡ ወደ #ኵሉ_ወይን_ቅድስት_አርሴማ፡፡ **በብዙሃን ዘንድ ዜናው ያልተሰማው፤ 3ት ትላልቅና ሌሎችም ክፍሎች ያሉት፤ ብዙ ንዋያተ ቅድሳት የተገኙበትና በቁፋሮ የተገኘው ጥንታዊ ዋሻ ይጎበኛል፤ **ምክረ አበው በሊቃውንት መምህራን፣ ዝማሬ በዘማርያን ይቀርባል፡፡ **ከሰ/ትቤታችን ምሥረታ ጀምሮ የነበሩና አሁንም ያሉ አባላት በአንድነት የሚሳተፉበት ዐቢይ ጕዞ፡፡ **ለበለጠ መረጃ፤ 0977 30 17 18 (ፎቶው ላይ የምታዩት ተጓዦች፤ ከዚህ በፊት ወደ ኤረር ካደረግነው ጕዞ ላይ የተወሰደ ነው)፡፡

???? #አዚፋ_(በድፍን ምስር የሚሠራ ነው) ምን ማለት ነው!? በደብረ ዘይት ዕለትስ ለምን ይደረጋል?? ተሳተፋ፤ የሚመልሱትንም አበርቱ!

ደብረ ዘይት ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት ነው፡፡ ይህም ቦታ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ካለው ከቄድሮስ ሸለቆ ራቅ ብሎ የሚገኝ፣ ርዝመቱ ፪ ኪሎ ሜትር፥ ከፍታው ደግሞ ከኢየሩሳሌም ከተማ በላይ 62 ሜትር ያህል ከፍታ ያለው ነው፤ቢታንያና ቤተ ፋጌ ከደ/ዘይት ተራራ ሥር የሚገኙ ቦታዎች ናቸው፡፡ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ የተፈጸሙ ዋና ዋና ድጊቶች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፡- ⊚ በደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነበር። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥፩፡፡ ⊚ የጌታችን በዳግም ምጽአት እንደሚመጣ አስተማሮበታል /ማቴ.24፥1-36/ ⊚ 33 ዓመት ከ3 ወር በዚህ ምድር ተመላልሶ ሞቶ ከተነሳ በኋላ ያረገበት ተራራ ነው፤ ‹‹ሁለት ሰዎች ነጫጭ ልብስ ለብሰው በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው ‹እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እያያችሁት ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ፥ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል› አሏቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤›› ሐዋ.1፥11-12፣ ሉቃ.24፥51-52/፡፡ ⊚ ዳዊት ከልጁ ከአቤሴሎም በሸሸ ጊዜ ወደ ደብረ ዘይት አቀበት ወጥሮ ነበር /2ኛ ሳሙ.15፥30/፣ ⊚ ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ሆሳዕና ከደብረ ዘይት ወደ ኢየሩሳሌም ሒዷል /ማር.11፥1/ ⊚ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ግርጌ በምትገኘው ለምለም ስፍራ በጌቴ ሴማኒ በአይሁድ ጭፍሮች ተያዘ፡፡ ማር.26፥30-36፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተቀበረችበት ቦታም በጌቴሴማኒ ነበር፡፡ ⊚ በደብረ ዘይት ተራራ ወገብ ላይ በሰፊው ተንጣሎ የሚታይ የአይሁድ መቃብር አለ። ይህን ስፍራ ለመቃብርነት የመረጡበት ምክንያት ወደፊት መሢሑ መጥቶ እስራኤልን ነፃ አውጥቶ ወደ አባቱ ያርጋልና ኋላ ለፍርድ ሲመጣ በመጀመሪያ የሚፈርድበት ስፍራና ሙታንም የሚነሱበትና የሚሰበሰቡበት ስፍራ ይህ በመሆኑ እኛ መሢሐችንን ለማግኘትና ከሙታንም ለመነሳት የመጀመሪያዎቹ እንሆናለን ብለው በማመናቸው ነው። አይሁድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መሢሕ እርሱ ነው ብለው አያምኑም። በመሆኑም እስራኤል ወደፊት አንድ ታላቅ መሢሕ እግዚአብሔር እንደሚልክላቸው ባላቸው ተስፋ መሠረት ገና አሁንም ድረስ መሢሐችንን እንጠብቃለን ይላሉ፤ ነገር ግን አይሁድ በዚህ በትልቁ ነገር ላይ ወደኋላ ቀርተው ተበድለዋል። ቀመረ አዝማናትን ቀንሰዋል፥ ቈነጻጸለዋል፤ የኦሪት መጽሐፋቸው ኦሪተ ብጡል ተብላለች፤ ይመጣል ያሉበትም ዘመን ሳይመጣ ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ 8ኛ ሺህ ላይ ደርሰናል፡፡ ይሁንና እግዚአብሔር እስራኤልን ብቻ ሳይሆን ዓለሙን ሁሉ እንዲያድን አንድ ልጁን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልኮልን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶልን በእርሱ ቁስል እኛ ተፈውሰናል፣ በእርሱ ሞት እኛ ሕይወትን አግኝተና/ኢሳ.፶፫፥፬-፮/። ከዚህ በኋላ ሌላ መሢሕ ሌላ አዳኝ ፈጽሞ የለም፡፡ ※ ከዳግም ምጽአት በፊት የሚከሰቱተ ድርቶች /ማቴ. ፳፬፥ ፫-፴፮/ እንደተገለጸው፡- ⊚ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ ⊚ ጦርነትን የጦርነትንም ወሬ ትሰማላችሁ ⊚ ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣሉ ⊚ በየሀገሩም ረኃብ፣ ቸነፈርም፣ የምድር መናወጥም በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል ⊚ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችሁማል፤ ስለ ስሜም በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ⊚ በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በእርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፣ እርስ በእርሳቸውም ይጣላሉ ⊚ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ ⊚ ከዐመፅም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች ⊚ የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰችው ሥፍራ ቆሞ ታያላችሁ ⊚ በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል ካለ በኋላ እስከመጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል በማለት ገልጾላቸዋል። ※የዐቢይ ጾም 5ኛ ሳምንት ደብረ ዘይት በመባል የሚታወቀው የደብረ ዘይት ሰንበት ምጽአት የተነገረበት ከመሆኑም በስተጀርባ በዚህ ዕለት ምጽአት እንደሚሆን ይታመናል፡፡ ከዐቢይ ጾም በ5ኛ ሳምንት መከበሩ በ5,500 ዓመተ ዓለም የመጣው ጌታ ከዚህም በኋለ በዚሁ ዕለት የሚመጣ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ /የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት/

#ይግባኝ_ለክርስቶስ፡፡ #ቅዱስ_ገብርኤል_ሆይ_ጠላቴ_ሰይጣን_የመቅሠፍት_እሳት_ወላፈኑን_በኔ_ላይ_በነዛ_ጊዜ_ፈጥነህ_በክንፎችህ_ጋርደኝ_። ጠላት ያደረባቸው በሰሜን ሸዋ ኤጄሬ የቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን ንዋያትን ዘርፈዋል፡፡ በሕደቡ አቦቴ ወረዳ ደግሞ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤልን አቃጥለዋል፡፡ እግዚኦ (አምላከ ቅዱስ ገብርኤል) በመዓትከ ኢትቅሰፈነ፥ ወበመቅሠፍትከ ኢትገሥጸነ፡፡ የቅዱስ ገብርኤል አምላክ መድኀኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ በቊጣ አትቅሠፈን፥ በመዓትህም አትገሥጸን፡፡ እንደ ልማድህ በትህትናህና በምሕረትህ፤ በቸርነትህና በርኅራኄህ፤ ይቅር በለን እንጂ፡፡ (መዝ. 33) ሰላም ለሕሊናከ ዘየአምር የብቦ፤ መሌሊተ ሥጋ ኵሉ በባሕርይከ ዘአልቦ፡፡ መልአከ አድኅኖ ገብርኤል አውጽአኒ እምተመንድቦ፤ አመ ነፍሐ በላዕሌየ እሳተ መቅሰፍት ላሕቦ፤ ኪያየ ጸልል በአክናፍ ዘገቦ፡፡ (ሰላም ለሕሊናከ፤ ገብርኤል ፡ ሆይ፤ ምስጋናን ፡ በዝማሬ ፡ ድምፅ ፡ ለሚያሰማ ፡ ለሚያመሰግን ፡ ኅሊናህ ፡ ሰላም ፡ እላለሁ። የሥጋዊ ፡ ባሕርይ ፡ ከፍለ ፡ አካል ፡ ግን ፡ በባሕርይህ ፡ የሌለ ፡ ነው። ገብርኤል ፡ ሆይ፤ የደኅንነት ፡ መልአክ ፡ ነህና ፡ እኔን ፡ አገልጋይህን ፡ ከችግር ፡ አውጣኝ ። ይልቁንም ፡ #ጠላቴ_ሰይጣን_የመቅሠፍት_እሳት_ወላፈኑን_በኔ_ላይ_በነዛ_ጊዜ_ፈጥነህ_በክንፎችህ_ጋርደኝ።) በቤተ ክርስቲያን ላይ እጃቸውን ባነሱት ላይ በዕለተ ቀንህ ተአምራትህን ግለጽ፤ አሕዛብ አምላካቸው ማን ነው ወዴትስ አለ እንዳይሉ ስለ አባቶቻችን ብለህ መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ ሆይ ተለመንን፤ አንተ ፍርዱን ስጥ፨

፨ ‹‹እስከ መቼ ድረስ በሁለት አሳብ ታነክሳላችሁ!?›› ፨ መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ፲፰፥፳፩