en
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 396 subscribers, ranking 5 565 in the Religion & Spirituality category and 2 183 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 396 subscribers.

According to the latest data from 28 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 15 over the last 30 days and by 5 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 21.32%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 10.24% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 282 views. Within the first day, a publication typically gains 1 576 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 17.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 29 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

15 396
Subscribers
+524 hours
+287 days
+1530 days
Posts Archive
‹‹#ያገለገለህን_ሰው_ሞት_ቸል_አትበል፡፡›› ሲራክ 38÷26 የደብራችን ታለቅ አገልጋይ መጋቤ ብሉይ አባ ወልደ ዮሐንስ አስቀድመው ከ8 ዕለታት በፊት እንደተናገሩት በበዓለ ቅዱስ ገብርኤል ዕለት (9.07.2014) ከዚህ ዓለም ድካም አረፈዋል ፡፡ ሥርዓተ ግብዓተ መሬታቸው ወደሚፈጸምበት ደብረሊባኖስ አቡነ ተክላሃይማኖት ገዳምም ማኀሌት ተቁሞላቸው በዕንባ ሽኝት ተደርጐላቸዋል፡፡ አባታቸን አባ ወልደ ዮሐንስ ያገለግሉበት ከነበረበት ገዳመ ደብረ ሊባኖስ ከመጡ ጀምሮ፥ በደብራችን ዕቃ ቤት እና ቤተ-መዘክር (ሙዚየም) በጽንዑ ታማኝነት አገልግለዋል ፡፡ መጋቤ ብሉይ አባ ወልደ ዮሐንስ በቀትር 6 ሰዓት ፤ ተሰዓት( 9) ሰዓት እንዲሁም በሠርክ 11 ሰዓት ደብራችንን በማጠን ፥ ጸሎት ሲያሳርጉ ፣ ምሕረት ሲለምኑ ሳናያቸው ቀርተን አናውቅም ነበር ፡፡ የቤተክርስቲያነችን ዕንቊ አባታችን ፥ የደብራችንን የዕጣን መዓዛ በመሥዋዕታቸው ትተውልን አልፈዋል ፡፡እንደእርሳቸው ያለ አገልጋይ መድኀኔዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ይተካልን ፡፡ የአባታችንን ነፍስ ከደጋጐቹ አባት ከአብርሃም ከይሰሐቅ ጋር ያኑርልን ፡፡ እኛንም በጸሎታቸው ይማረን ፤ በረከታቸው ይደርብን ፡፡ ወአቀቦሙ ከመ ብንተ ዓይን ለጻድቃን ፥ እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ .. /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#ደብረ_ዘይት : የዐቢይ ጾም 5ኛ ሳምንት ※※※ ከዳግም ምጽአት በፊት የሚከሰቱተ ድርጊቶች ※※※ #ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ተራራ ማለት ነው፡፡ ይህም ቦታ ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ ካለው ከቄድሮስ ሸለቆ ራቅ ብሎ የሚገኝ፣ ርዝመቱ ፪ ኪሎ ሜትር፥ ከፍታው ደግሞ ከኢየሩሳሌም ከተማ በላይ 62 ሜትር ያህል ከፍታ ያለው ነው፤ቢታንያና ቤተ ፋጌ ከደ/ዘይት ተራራ ሥር የሚገኙ ቦታዎች ናቸው፡፡ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ የተፈጸሙ ዋና ዋና ድጊቶች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፡- ⊚ በደብረ ዘይት ተራራ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ ጊዜ የሚያድርበት፣ የሚያስተምርበት፣ ውሎ የሚያርፍበት ሥፍራ ነበር። ሉቃ ፳፩፥ ፴፯፣ ሉቃ ፳፪፥ ፴፱፣ ዮሐ ፰፥፩፡፡ ⊚ ጌታችን በዳግም ምጽአት እንደሚመጣ አስተማሮበታል /ማቴ.24፥1-36/ ⊚ 33 ዓመት ከ3 ወር በዚህ ምድር ተመላልሶ ሞቶ ከተነሳ በኋላ ያረገበት ተራራ ነው፤ ‹‹ሁለት ሰዎች ነጫጭ ልብስ ለብሰው በአጠገባቸው ቆመው ታዩአቸው ‹እናንተ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እያያችሁት ለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ ያረገው ኢየሱስ፥ ከእናንተ ወደ ሰማይ ሲያርግ እንዳያችሁት እንዲሁ ዳግመኛ ይመጣል› አሏቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ደብረ ዘይት ከሚባለው ተራራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤›› ሐዋ.1፥11-12፣ ሉቃ.24፥51-52/፡፡ ⊚ ዳዊት ከልጁ ከአቤሴሎም በሸሸ ጊዜ ወደ ደብረ ዘይት አቀበት ወጥሮ ነበር /2ኛ ሳሙ.15፥30/፣ ⊚ ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ሆሳዕና ከደብረ ዘይት ወደ ኢየሩሳሌም ሒዷል /ማር.11፥1/ ⊚ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ግርጌ በምትገኘው ለምለም ስፍራ በጌቴ ሴማኒ በአይሁድ ጭፍሮች ተያዘ፡፡ ማር.26፥30-36፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተቀበረችበት ቦታም በጌቴሴማኒ ነበር፡፡ ⊚ በደብረ ዘይት ተራራ ወገብ ላይ በሰፊው ተንጣሎ የሚታይ የአይሁድ መቃብር አለ። ይህን ስፍራ ለመቃብርነት የመረጡበት ምክንያት ወደፊት መሢሑ መጥቶ እስራኤልን ነፃ አውጥቶ ወደ አባቱ ያርጋልና ኋላ ለፍርድ ሲመጣ በመጀመሪያ የሚፈርድበት ስፍራና ሙታንም የሚነሱበትና የሚሰበሰቡበት ስፍራ ይህ በመሆኑ እኛ መሢሐችንን ለማግኘትና ከሙታንም ለመነሳት የመጀመሪያዎቹ እንሆናለን ብለው በማመናቸው ነው። አይሁድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን መሢሕ እርሱ ነው ብለው አያምኑም። በመሆኑም እስራኤል ወደፊት አንድ ታላቅ መሢሕ እግዚአብሔር እንደሚልክላቸው ባላቸው ተስፋ መሠረት ገና አሁንም ድረስ መሢሐችንን እንጠብቃለን ይላሉ፤ ነገር ግን አይሁድ በዚህ በትልቁ ነገር ላይ ወደኋላ ቀርተው ተበድለዋል። ቀመረ አዝማናትን ቀንሰዋል፥ ቈነጻጸለዋል፤ የኦሪት መጽሐፋቸው ኦሪተ ብጡል ተብላለች፤ ይመጣል ያሉበትም ዘመን ሳይመጣ ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ 8ኛ ሺህ ላይ ደርሰናል፡፡ ይሁንና እግዚአብሔር እስራኤልን ብቻ ሳይሆን ዓለሙን ሁሉ እንዲያድን አንድ ልጁን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ልኮልን ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶልን በእርሱ ቁስል እኛ ተፈውሰናል፣ በእርሱ ሞት እኛ ሕይወትን አግኝተና/ኢሳ.፶፫፥፬-፮/። ከዚህ በኋላ ሌላ መሢሕ ሌላ አዳኝ ፈጽሞ የለም፡፡ ※ #ከዳግም_ምጽአት በፊት የሚከሰቱተ ድርጊቶች /ማቴ. ፳፬፥ ፫-፴፮/ እንደተገለጸው፡- ⊚ ብዙዎች እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና ብዙዎችንም ያስታሉ ⊚ ጦርነትን የጦርነትንም ወሬ ትሰማላችሁ ⊚ ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣሉ ⊚ በየሀገሩም ረኃብ፣ ቸነፈርም፣ የምድር መናወጥም በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል ⊚ በዚያን ጊዜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችሁማል፤ ስለ ስሜም በሕዝብ ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ⊚ በዚያን ጊዜም ብዙዎች ይሰናከላሉ እርስ በእርሳቸውም አሳልፈው ይሰጣጣሉ፣ እርስ በእርሳቸውም ይጣላሉ ⊚ ብዙዎች ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ ⊚ ከዐመፅም ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች ⊚ የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰችው ሥፍራ ቆሞ ታያላችሁ ⊚ በዚያን ጊዜ ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ ይሆናል ካለ በኋላ እስከመጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል በማለት ገልጾላቸዋል። ※የዐቢይ ጾም 5ኛ ሳምንት ደብረ ዘይት በመባል የሚታወቀው የደብረ ዘይት ሰንበት ምጽአት የተነገረበት ከመሆኑም በስተጀርባ በዚህ ዕለት ምጽአት እንደሚሆን ይታመናል፡፡ ከዐቢይ ጾም በ5ኛ ሳምንት መከበሩ #በ5,500 ዓመተ ዓለም የመጣው ጌታ ከዚህም በኋለ በዚሁ ዕለት የሚመጣ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

#ቀን ፤ መጋቢት 15 / 07 / 2014 ዓ.ም ፤ #መርኀግብር ፤ የመጻሕፍ ዳሰሳ በፍኖተ ሕይወት ቤተ-መጻሕፍት #የተዳሰሰው መጽሐፍ ፤ ቃል ኪዳን በነገረ ድኅነት በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ #የዳሰሰው
+3
#ቀን ፤ መጋቢት 15 / 07 / 2014 ዓ.ም ፤ #መርኀግብር ፤ የመጻሕፍ ዳሰሳ በፍኖተ ሕይወት ቤተ-መጻሕፍት #የተዳሰሰው መጽሐፍ ፤ ቃል ኪዳን በነገረ ድኅነት በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ #የዳሰሰው ፤ ዲ/ን ዳንኤል #ቀጣይ መርኀ ግብር ፤ በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል ፡፡

#መፃጕዕ፤ አራተኛው ሳምንት አራተኛው ሳምንት መፃጕዕ ይባላል፡፡ በመፃጕዕ የተሰየመው የእርሱ ስህተት ለእኛ ትምህርት፥ ተግሳጽ እንዲሆነን እንጂ፤ በዚህ ሳምንት የሚታሰበው ጌታችን ሕሙማን መፈወሱን፣ ሙት ማስነሳቱንና ስለ ረቂቁ የነፍስ ደዌ ስለ ኀጢአትና ስለ ድኅነታችን የሚያዘክር ምስጋና ይቀርብበታል፡፡ ማቴ. 8፥1-37፣ ማር. 7፥13-37፣ ሉቃ. 17፥1-9፣ ዮሐ. 5፥1-18 በቤተክርስቲያን በሽተኞች በሦስት ስያሜ ይጠራሉ፡- ፨ #በሽተኛ፤ የዕለት ሕመም ወይም እስከ አንድ ዓመት የታመመ ሰው፡፡ ፨ #ድውይ፤ እስከ አምስት ዓመት ሕመሙ የቆየበት፡፡ ፨ #መፃጕዕ፤ ከአምስት ዓመት በላይ ሕመሙ የጸናበት፤ ሲሆን ድውይ፥ በሕመም የሚማቅቅ፥ የዐልጋ ቊራኛ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ #መፃጕዕ የተባለው ስለሕመሙ #38_ዓመታት_መጽናት_እንጂ ስሙ አይደለም፡፡ በዕብራይስጥ ቤተ ሳይዳ ትርጕሙ /የምሕረት ቦታ/፤ በግእዙ ቀላየ አባግዕ (የበጎች መዋኛ) በተባለች ምጥምቃት ዘጵሩጳጥቄ በምትባል የጠበል መጠመቂያ ኩሬ ዳር የውኃውን መንቀሳቀስ እየጠበቁ በሽተኞች፥ እውሮች፥ አንካሶች፥ ልምሾች፥ ሰውነታቸው የሰለለ የደረቀና ያበጠ ብዙ ድውያን ሕዝብ ይተኙ ነበር፡፡ ከእግዚአብሔር የተሰጠውን የምሕረት ፈውስ ይዞ በሳምንት አንድ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ውኃውን ባርኮ ሲሄድ ቀድሞ የገባው በሽተኛ ይፈወስ ነበር፡፡ ተስፋ ሳይቈርጥ ለ38 ዓመታት ድኅነትን እየጠበቀ በሕመሙም እተሰቃየ በዚያ የተኛ አንድ ሰው ነበር፡፡ ጌታችን ይህን ሁሉ ዓመት እንደተሰቃየ አውቆ ድኅነት ሊሰጠው ወዶ መጣ፡፡ ‹‹ልትድን ትወዳለህን?›› ብሎ ጠየቀው፡፡ መጠየቁ ፍጹም የሰውን ሥጋ እንደተዋሐደ ሲያጠይቅ ነው፡፡ በተጨማሪም በዕለተ ዐርብ ‹‹ራሱ አዳነኝ እንጂ መቼ አድነኝ አልኩት!›› ብሎ ለመክሰስ ምክንያት እንዳያገኝ ጠየቀው፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ ውኃው በተናወጠ ጊዜ በመጠመቂያው ውስጥ የሚያኖረኝ ሰው የለኝም›› አለው፡፡ ‹‹እንዲህ ያለው የ30 ዓመት ጎልማሳ ነውና አንስቶ ይጨምረኛል›› ወይም አምስት ገበያ የሚያህል ሕዝብ ይከተለው ነበርና ‹‹ከእነርሱ መካከል አዞልኝ ወደ መጠመቂያው ይጨምረኛል›› ብሎ ነው እንጂ እንዲሁ ይፈውሰኛል ብሎ አልነበረም፡፡ ጌታ ግን ለመዳን መውደዱን ተመልክቶ ‹‹ተነሳና አልጋህን ተሸክመህ ሒድ›› አለው፡፡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚገኘው ፍጹም ድኅነት ነውና ወዲያው ሰውየው ዳነ፤ አልጋውንም ተሸክሞ ሔደ፡፡ ያን ሰውም ጌታችን በምኵራብ አገኘውና እነሆ ድነሃል፤ ግን ከዚህ የባሰ እንዳያገኝህ ዳግመኛ እንዳትበድል እወቅ አለው፡፡ አልጋውንም ተሸክመህ ሂድ ያለው 38 ዓመት የተሸከመችው ጠንካራና የብረት አልጋ ስለተሸከመ ፍጹም መዳኑ እንዲታወቅ ነው፡፡ መጻጕዕ የተፈወሰው በእለተ ቀዳሚት ስለነበረ ፤ በሰንበት ይህን ስላደረገ አይሁድ ኢየሱስን ያሳድዱት፣ ሊገድሉትም ይፈልጉ ነበር፡፡ በሽተኛው የተደረገለትን ተአምር ረስቶ በዕለተ ዐርብ ጌታን ከሰሰው፤ በጥፊም መታው ወዲያው እጁ ሰለለ፡፡ #ቅዱስ_ያሬድም ጌታችን ሰንበትን ለዕረፈት ስለፈጠራት፤ ሕሙማንን በመፈወስ (#የመቶ አለቃውን ልጅ በመፈወስ ማቴ. 8፥1-15፤ #የዕውራንን ዓይኖች በማብራት ማቴ. 20፥24-30፤ ዮሐ. 9፤ #ሽባ የነበረውን በመፈወስ) #በዕለተ_ሰንበት_ከበሽታቸው_እንዲያርፉ_አደረገ፡፡ በእኛ በሰው ልጆች ላይ በሽታ በተለያየ ምክንያት ይመጣል፡፡ † በኃጢአት ምክንያት የሚመጣ በሽታ፡፡ ዘኍ. 21፥4-9 † የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ይገለጥ ዘንድ የሚመጣ በሽታ አለ፡፡ ዮሐ. 9፥13 † ሰዎች ከእግዚአብሔር ዋጋ እንዲያገኙበት ከዲቢያሎስ የሚመጣ የፈተና በሽታ አለ እንደ ጻድቁ ኢዮብ፡፡ መጽ.ኢዮብ † ሰዎች በተሰጣቸው ጸጋ እንዳይታበዩ ማሳወቂያ የሚሆን በሽታ አለ፤ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ራስ ምታት፡፡ † የበደለውን የሚቀጣበት በሽታ አለ፤ እንደ ሳዖል አጋንንት አድሮበት ይሰቃይ ነበር፣ የመጻጕዕ እጁ የሰለለው በሁለተኛ በደሉ ነው፡፡ † ያልታመመው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግን፥ የታመመው ምሕረትን እንዲለምን የሚመጣ በሽታ አለ፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w, .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem