en
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 367 subscribers, ranking 5 600 in the Religion & Spirituality category and 2 189 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 367 subscribers.

According to the latest data from 26 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by 2 over the last 30 days and by 2 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 20.69%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 10.92% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 180 views. Within the first day, a publication typically gains 1 679 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 18.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 27 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

15 367
Subscribers
+224 hours
No data7 days
+230 days
Posts Archive
ጉዞ ወደ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ተክለሃይማኖት ገዳም። የፎቶ ማስታወሻ። ጥቅምት 6 ፤ 2015 ዓ.ም ።

#ጥቅምት_3_የቤተ_ክርስቲያን_ማኅቶት ፥ #አፈ_በረከት_ሊቁ_አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ፤#_ፅንሰቱ_ነው፡፡ ፠ይህ አባት ከ40 በላይ መጻሕፍትን የደረሰና ብዙ መጻሕፍትን እያጻፈ ለመላው ገዳማት ያዳረሰ፤ ጸሓፊ፥ ቅዱስና ጻድቅ፥ ፈላስፋና ደራሲ፥ መናኝና ባሕታዊ፥ ሊቅና ተመራማሪ፥ ገጣሚና በለቅኔ፥ የመጻሕፍት ተርጓሚና የዘመን አቈጣጠር (የአቡሻህር) ሊቅና ተንታኝ፥ አርክቴክትና መሐንዲስ ነው፤ በዚህም ምክንያት በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፤ ፠ዳግማዊ ቄርሎስ (ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ)፥ ፠ ዐምደ ሃይማኖት ፠ ዳግማይ ቅዱስ ያሬድ፤ ፠ የወርቃማ ዘመን ወርቃማ ደራሲ፤ ፠ የቤተ ክርስቲያን ማኅቶት፥ ፠ አፈ በረከት ፠ የከሃድያን ዘላፊ፥ የቅዱሳን ፀሐይ …….ተብሏል፡፡ እንዲሁም፤ + እንደ ቅዱስ ላሊበላ ቤተ መቅደሱን ራሱ ፈልፍሎ ያነፀ #የሕንፃ_ባለሙያ ነው። + ከጓደኛው ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር ሁኖ የወለቃ ወንዝ ድልድይን የሠራ መሐንዲስ፤ እስከ ዛሬም ድረስ ድልድዩን ሕዝቡ ይጠቀምበታል፡፡ + እንደ ቅዱስ አትናቴዎስ መናፍቃንን የረታ #ብርቱ_የቤተ_ክርስቲያን_ጠበቃ ነው። + እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በርካታ መጻሕፍትን የጻፈ (የደረሰ) #ደራሲ ነው፡፡ + እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ወንጌልን ዙሮ ያስተማረ #ሐዋርያ ነው፡፡ + እንደ ፍጹማን መነኰሳት በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስኖ በተጋድሎ ጸንቶ የኖረ #መናኝ_ጻድቅ ነው፡፡ + እንደ ቅዱስ ያሬድ በሰማያዊ ዜማ አምላኩን ያመሰገነ #የዜማ_ሊቅ #የዜማ_ደራሲ ነው። + እንደ ዕዝራ ሱቱኤል ሰማያዊ መጠጥ ጠጥቶ ምስጢራት የተገለጹለት #ድንቅ_ተመራማሪ #የጥበብ_አባት ነው:: (ለምሳሌ፤ በሰዓታት ድርሰቱ ውስጥ ዑደተ ማይን፣ በሌሎች ድርሰቶቹም ስለ አእባንና እጽዋት ቀድሞ ነግሮናል፣ እንዲሁም የውኃ ማቆር ቴክኖሎጂን በዘመኑ ተግባራዊ አድርጓል። + እንደ ሰማዕታት ከነገሥታቱ ስለ ሃይማኖት ብዙ ጸዋትወ መከራ የተቀበለ #ሰማዕት ነው፡፡ + አቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞን፤ አቡነ ኢየሱስ ሞ ሐይቅ እስጢፋኖስን፤ አቡነ ተከለ ሃይማኖት ደብረ ሊባኖስን፤ አቡነ ሳሙኤል ዋልድባን፤ አቡነ ዐምደ ሥላሴ ማኅበረ ሥላሴ ገዳምን እንደመሠረቱና የተመሠረተውንም እንዳስፋፉ፤ እርሱም ደብረ ባሕርይ ጋሥጫን የመሠረተ ቅዱስ ነው፡፡ + በሰዓታት ድርሰቱ ቤተክርስቲያን አምላኳን ፳፬ ሰዓት ያለማቋረጥ እንድታመሰግን ያስቻለ ምድራዊ #መልአክ ነው፡፡ + "አኀዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" እስከሚል ድረስ ጸጋ የበዛለት አባት ነውና ስንቱን እንናገረው? አይቻለንምና!!!፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com #Share #like

#እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡ ጥቅምት 5 በዓለ ዕረፋቱ ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጻድቁ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ስለዚህም ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር የመጋቢት 27 ስቅለት ደግሞ ጥቅምት 27 ቀን እንዲከበር ተደረገ፤ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ይህ ስርዓት ሆነ ይህንንም ስርዓት አባቶታችን ሰሩልን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤ * እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤ * እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤ * ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤ * ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤ * በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤ * 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤ * ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ #ላሊበላ፥ ለአቡነ #ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ #አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ) ፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤ *ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡ *ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤ ፠ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ ፣ #አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፡፡ ፠ እድሜያቸው ረዥም እንደመሆኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡ ፠#በግብፅ_300_ዓመታት_፥ #በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል) ፠ በድምሩ 562 ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥ ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡ ፠ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡ አምላከ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት፥ በረከትን ይክፈለን፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com