en
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 366 subscribers, ranking 5 620 in the Religion & Spirituality category and 2 191 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 366 subscribers.

According to the latest data from 22 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -33 over the last 30 days and by -2 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 22.71%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 7.98% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 489 views. Within the first day, a publication typically gains 1 226 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 22.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 23 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

15 366
Subscribers
-224 hours
+317 days
-3330 days
Posts Archive
#_ግንቦት_26_ለዓለም ብርሃን የሆኑ #ኢትዮጵያዊው_ጻድቅ_አቡነ_ሀብተ_ማርያም_ልደታቸው_ነው፡፡ በመብረቅ፣ በቸነፈር፣ በረሃብ፣ በወረርሽኝ፣ በእሳት ቃጠሎ ላይ ቃል ኪዳን የተሰጣቸውን የእኒህን ጻድቅ #ታሪካቸውን_መልክአቸውና_በ ቃሌ ተራራ ደብረ መድኀኒት አቡነ ሀብተማርያም ገዳም( አዲስ አበባ ከዊንጌት ትምህርት ቤት አጠገብ) የሚቆመውን ሥርዓተ ማኀሌት እንሆ ብለናል፡፡ #share አቡነ ሀብተማርያም ፠፠በማዕጠንታቸው የታወቁ፤ ፠፠በጽድቅ ሥራቸው የተደነቁ፤ ፠፠5ት መቅሰፍቶችን የሚያርቁ ታለቅ አባታችን ናቸው፡፡፡፨ ፠በመራ ውዕይ (ሸዋ ፥ ቡልጋ) ከአባታቸው #ፍሬ ቡሩክና ከእናታቸው ቅድስት #ዮስቴና ነው የተወለዱት፡፡ ወላጆቹ በተለይም እናቱ ከማግባቷ በፊት መንና ነበር፡፡ ጻድቁን እንደምትወልድ በበቃ ባሕታዊ ተነግሯት ጻድቁን ወልዳ በጽድቅ ኑሮ ኑራ #7_አክሊላትን ተቀብላ በክብር አርፋለች፡፡ ፠አቡነ ሀብተማርያም በሕፃንነታቸው ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ ‹‹እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ›› ሲባል ይሰማሉ፤ በሕፃን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ ‹‹ማረን እባክህን›› እያሉ ይሰግዱ ነበር፡፡ ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ፡፡ ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል፤ ጓደኞቻቸው የሌላ ሰው እሸት እየነቀሉ ሲበሉ እርሳቸው ግን አይበሉም ነበር፡፡ የፈጣሪውን ስም ያቃለለውን አንድ እረኛም በአየር ላይ ሰቅለው አውለውታል፡፡ ፠ወደ ት/ቤት ገብተው ትምህርትን ከቀሰሙ በኋላ ለአካለ መጠን ሲደርሱ ቤተ ሰቦቻቸው ሚስት አጩለት፤ እርሱ ግን ወደ አፋር ከአባ ሳሙኤል ዘንድ ሂዶ ለ12 ዓመታት ረድዕ ሆኖ ተቀመጠ፡፡ ከአፋርም ወደ ምኔት ወደሚባል ቦታ መጥቶ በታላቁ አባት በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሰ፤ ከአፋር ወደ ይነውፋ፥ ከይነውፋ ወደ ጉሐርብ ወደሚባል ሃገር ሂዶ ምናኔን፣ ትሩፋትንና ተጋድሎን ሠራ፡፡ ለአብነትም፤ ባሕር ውስጥ ሰጥሞ 500 ጊዜ ይሰግዳል፤ በየቀኑ 4ቱን ወንጌልንና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያል፤ በ40 ቀናት ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባል፤ ምግቡ ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው፤ በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋል፤ ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላል፥ ክቡር ደሙን ይጠጣል፤ በልቡ ውስጥ በፍጹም ቂምን፣ መከፋትን አያሳድርም፡፡ የብረት ሰንሰለት በወገቡ ታጥቆ ይሰግዳል ይጸልያልም፡፡ "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሀብተ ማርያም" የተባለላቸው ታላቅ አባታችን ናቸው ፡፡ ፠ዲቁናን ከጳጳሱ አቡነ ይስሐቅ ዘንድ ተቀበሎ ወደ በዓቱ ተመለሰ፡፡ ፠ኋላ ቆይቶም እንደገና ከአቡነ ይስሐቅ ዘንድ ቅስናን ተቀበለ፡፡ ወደ ጓና ወደ ምትባል ሀገርም ሂዶ ተቀመጠ፡፡ ቀጥሎም ጐላጐት ወደ ምትባል አገር ሂዶ ተቀመጠ፡፡ *የአፄ ናዖድ የንስሐ አባት ነበረና ንጉሡን ያስተምረውና ይገስጸውም ነበር፡፡ ፠ጌታችንም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቶት በዚያ እየበረረ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ተለያዩ ቦታዎች ይሔድ ነበር፡፡ ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በኋላም የክብር ባለቤት መድኀኒታችን ክርስቶስ አእላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ እንዲህ አላቸው:: "*ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: *ስለ ምናኔሕ: *ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: *ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: *ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: *ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: *ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ::" "በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን: 500 የዕንቊ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ:: በስምህ የሚለምኑ: በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ በርእስየ' ብዬሃለሁ" አላቸው:: +ቅዱሳን መላእክትም "ሀብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው:: ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው:: ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች:: መላእክትም ዝማሬም ወሰዷት::  ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ሥልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነርሱም፤ ፩ኛ. #መብረቅ፣ ፪ኛ. #ቸነፈር፣ ፫ኛ. #ረሃብ፣ ፬ኛ. #ወረርሽኝ፣ ፭ኛ. #የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡ ፨በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ቦታውን ሲባርክ ሦስት አጋንንት በጸሎቱ ሥልጣን የታሠሩለት ታላቅ ጻድቅ ነው፡፡ በግንቦት 26 ተወልዶ፤ በ1490 ዓ.ም. በወርኀ ኅዳር 26 ባረፈ ጊዜም፤ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማኅሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በደብረ ሊባኖስ ቀበሩት፡፡ (ከወርቅ ንፁህ ከብርም የጠራ ከሁሉ የሚበልጥ የተመረጠ ሃብተማርያም መልአክ ዘበምድር ነው መልካሙ ዜናው እስከ አጽናፍ ተሰማ፡፡) ክብርት በሆነችው ጸሎቱና ምልጃው ይማርን ይጠብቀን፡፡ #ሰላም_ለጽንሰትከ_እማኅፀነ_ቅድስት_ዮስቴና፤ #በብሥራተ_ጻድቅ_ባሕታዊ_ሠናየ_ዜና፡፡ #ሀብተማርያም_ጴጥሮስ_ሐዋርያ_ወልደ_ዮና፤ #መሐረኒ_ምግባረ_ጽድቅ_ወጸግወኒ_ልቡና፤ #አፍቅሮ_ቢጽ_እኅሥሥ_ዘምስለ_ፍጽመት_ትሕትና፡፡ በዓሉ የሚከብርባቸው ገዳማት እና አድባራት 1 , ብሔረ ብፁዓን ደበረ ይሰበይ አቡነ ሀብተ ማርያም ገዳም ፤ ደብረ ሊባኖስ 2 ቃሌ ተራራ ደብረ መድኀኒት አቡነ ሀብተማርያም ገዳም ፤ አዲስ አበባ አስኮ —> ካውጄጄ መውጫ ፡፡ #share ꔰ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤ ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/ የተዘጋጀ :: ꔰ #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot .YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .

#መንፈሳዊ_መሰላል ልዩ ተከታታይ ትምህርት በዓርብ ጉባኤ ። በመንፈሳዊ ሕይወታችን እንዴት እንደምናድግ የምንማርበት ልዩ ጉባኤ ።
#መንፈሳዊ_መሰላል ልዩ ተከታታይ ትምህርት በዓርብ ጉባኤ ። በመንፈሳዊ ሕይወታችን እንዴት እንደምናድግ የምንማርበት ልዩ ጉባኤ ።

#እልፍ_መጻሕፍት ልዩ የመጻሕፍት ማሰባሰቢያ ወር ፡፡ ለአንድ ወር በሚቆየው የመጻሕፍት ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የአቅሞትን ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ቤተ-መጻሕፍት ድጋፎትን ያድርጉ ፡፡ #share #
#እልፍ_መጻሕፍት ልዩ የመጻሕፍት ማሰባሰቢያ ወር ፡፡ ለአንድ ወር በሚቆየው የመጻሕፍት ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር የአቅሞትን ለሰንበት ትምህርት ቤታችን ቤተ-መጻሕፍት ድጋፎትን ያድርጉ ፡፡ #share #share #share

#ግንቦት_21_ደብረ_ምጥማቅ_ማርያም ወሥርዐተ_ማኅሌት_ዘግንቦት_21፡፡ ደብረ_ምጥማቅ_ማርያም የምናከብርበት ምክንያት #ግብጻውያን ክርስቲያኖች ከግንቦት 21 እስከ 25 የእመቤታችንን በዓል (ምሰሶ አቁመው፥ አጎበር ጥለው፥ ድንኳን ተክለው፥ ድባብ ዘርግተው ያከብራሉ፤ እመቤታችንም ከቅዱሳን ጋር በመገኘት ትባርካቸዋለች፡፡) እነዚህ 5ት ቀናትም #ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት 5ቱን ከተ.ቊ 25ኛ እስከ 29ኛ ያለውን ይይዛሉ፡፡ እነርሱም፤ ፠25ኛና 26ኛ፤ ግንቦት #21 ና 22 ቀን በግብጽ ሃገር ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቤተክርስቲያን ለተሰበሰቡት ምዕመናን በግልጽ የታየችበት ነው፡፡ ፠27ኛ፤ ግንቦት 23 ቀን ደብረ ምጥማቅ በተባለች ቦታ የታየችበት ነው፡፡ ፠28ኛ፤ ግንቦት 24 ተሰዳ ግብጽ የገባችበት ነው፤ /ኢሣ.1 9፥11፣ ማቴ.2፥13-15/ ፠29ኛ፤ ግንቦት 25 ልጇ መድኀኔዓለም ክርስቶስ የደረቁ በትሮችን ተክሎ ያለመለመበት በዓል ነው፡፡ እነዚህ ከላይ ያየናቸውን የደብረ ምጥማቅ በዓላት (ከግንቦት 21-25) በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን በግብፅ ተነሥቶ የነበረው ንጉሥ የግብጽ ክርስቲያኖች በዓሉን እንዳያከብሩ በመከልከሉ፤ ኢትዮጵያውያንም ይህንን በዓል ለማክበር ወደ ግብፅ ይሄዱ ነበርና ፤ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ለመጽናኛ እንዲሆን በሃገራችን የደብረ ምጥማቅ ጻድቃኔ ማርያምን መሠረተ፤ እመቤታችንም ብዙ ቃል ኪዳንን ሰጠችው፤ ይኸው ቃል ኪዳኗ ሳይታጠፍ በጻድቃኔ ማርያም ዛሬ ድረስ ስፍር ቊጥር የሌለው ብዙ ተዓምራትና የምሕረት ሥራ የሚፈጸምባት ቅዱስ ቦታ ኾና ትገኛለች፡፡ እስካሁን ባለን መረጃ በሃገራችን ግንቦት 21 የደብረ ምጥማቅ ክብረ በዓል በስሟ ተሰይሞ ! በዋነኛነት የሚከበርባቸው ቦታዎች የሚከተሉት ናቸው፤ *1ኛ) #ደብረ_ምጥማቅ_ጻድቃኔ_ማርያም_ገዳም /ሰሜን ሸዋ/ *2ኛ) ሐመረ ብርሃን ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን /ጎንደር ከተማ/ *3ኛ) ደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም /አዲስ አበባ/ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ #ግንቦት_24_በዓተ_ግብጽ_፤ እመቤታችን እመ አምላክ ድንግል ማርያም ከልጇና ከአረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ጋር ለ3 ዓመት ከ6 ወር ከተሰደዱ በኋላ ወደ ግብጽ ሃገር ገብታ በሰላም ያረፈችበት ቀን ነው፡፡ #ግንቦት_24_በዓተ_ግብጽ *በአዲስ አበባ ታቦተ ሕጉ የሚነግሥባቸው ቦታዎች፤ ፠እንጦጦ መንበረ ንግሥት ቅድስት ቊስቋም ማርያም፡፡ (365ት ቀናት ሙሉ ዝክር በማኅበረ መድኀኔ ዓለም አዳራሽ የሚዘከርባት ቤ/ክ) ፠ደብረ ናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን፡፡ (የቤ/ክርስቲያኑ ዐጸድ እጅጉን ልብን የሚገዛና የሚማርክ) ፠ ቃሊቲ ደብረ ቊስቋም ማርያም፡፡ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ꔰ Facebook https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem www.Finotehiwotsundayschool.com ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ

#ዕርገተ_እግዚእነ እንኳን ለጌታችን 1981ኛው  በዓለ ዕርገት፤ አደረሳችሁ፥ አደረሰን፤ ‹‹አልቦ ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘእንበለ ዘወረደ እምሰማይ ወልደ ዕጓለመሕያው፤ ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም፡፡›› እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው፡፡ ዮሐ.3፥13 * የሰውን ልጅ በመውደዱ ልዑል ባሕርዩን ዝቅ አድርጎ ከሰማይ ወረደ፥ ሥጋ ለበሰ፥ በምድር ላይ ተመላለሰ፥ ምድርን በኪደተ እግሩ ቀደሰ፥ ድውያንን ፈወሰ፡፡ * ፍጹም ሰው እንደ መሆኑ ተራበ፥ ተጠማ፤ ፍጹም አምላክ መሆኑንም ያስረዳ ዘንድ አምስት ገበያ ሕዝብ በአምስት እንጀራ በሁለት ዓሣ አጠገበ ማቴ.14፥19፡፡ * መምህረ ትሕትና ነውና ሠላሳ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር በዚህ ዓለም ኖረ ለሐዋርያት ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ወንጌልን አስተማረ፤ ትምህርት በሚገባ ከተረዳለት በኋላ ለድኅነተ ዓለም በማዕከለ ምድር በቀራንዮ ተሰቀለ፡፡#ወገብረ_መድኀኒተ_በማዕከለ_ምድር_በምድር_መካከል_መድኀኒትን_አደረገ_እንዲል _መዝ.73፥12 * ነቢያት እንደተናገሩ በሞቱ ዓለምን አድኖ ሦስት መዓልት ሦስት ሌሊት በከርሰ መቃብር አድሮ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ብርሃነ መለኮቱን ገልጾ ተነሣ፡፡ የተተነበየውን ትንቢት ፈጽሞ ተነሣ፡፡ * በሞቱ ሞታችንን ሻረልን፤ ‹‹በሞቱ ሞትን አጠፋው›› እንዲል መጽሐፈ ኪዳን፡፡ ሕንፃ መነኰሳት ‹እርሱ በሁሉ ምሉዕ ሲሆን በመቃብር ለመቀበር ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ገንዘውት ታየ፡፡ ከመሬት ውስጥ በመቀበሩም ሙስና መቃብርን አጠፋ፤ ከሥሩም ነቀለው ከተነሣ በኋላ ትንሣኤውን መጀመሪያ ለማርያም መግደላዊት ገለጸ ማር.16፥9፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ስለ ትንሣኤው ሲመሰክር ‹‹ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፤ ተቀበረም፤ መጽሐፍ እንደሚል፤ በሦስተኛው ቀን ተነሣ፡፡ ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ ከዚያም በኋላ ከአምስት መቶ ለሚበዙ ወንድሞች በአንድ ጊዜ ታየ፡፡ ከዚያም በኋላ ለያዕቆብ ኋላም ለሐዋርያት ሁሉ ታየ›› 1ቆሮ.15፥3-8 ብሎ ክርስቶስ ትንሣኤውን ለተከታዮቹ በሙሉ የገለጠ መሆኑን መስክሯል፡፡ *የሚያምኑ ፈሪሳውያንም ‹‹ትንሣኤው ምትሐት ነው›› እንዳይሉ እየታየ እያስተማረ እስከ 40 ቀን ድረስ መቆየቱን ይገልጽልና፡፡ በዚህም የአርባ ቀን ከትንሣኤ በኋላ ቆይታው ሦስት ቀን ጉባኤ አድርጎ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ ቅዱስ ወንጌል ይነግረናል፡፡ ኢየሱስ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ ሲገለጥላቸው ይህ ሦስተኛ ጊዜ ነበረ እንዲል ዮሐ.21፥14 ይህንም ሊቃውንት አባቶቻችን፡- 1ኛ) *የትንሣኤ 2ኛ) *የአግብኦተ ግብር /ዳግም ትንሣኤ/ 3ኛ) *የጥብርያዶስ፡፡ በዚህ 40 ቀን ቆይታ መጽሐፈ ኪዳንን ለደቀ መዛሙርቱ አስተምሯል፡፡ * ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስም ዕርገቱን ለመናገር ከሰማየ ሰማያት መውረዱን አስቀድሞ ከሰማይ ከወረደው ከሰው ልጅ በቀር ማንም ወደ ሰማይ የወጣ የለም እርሱም በሰማይ የሚኖረው ነው ብሎ ከዕርገቱ በኋላ በየማነ አብ፥ በዘባነ ኪሩብ ፥ ወደ ሰማይ የወጣ ከእርሱ በቀር ሌላ እንደሌለ አስረግጦ ነገረን፡፡ ሲጀምር ከሰማይ መውረዱን ማስቀደሙ ወረደ ብሎ ዐረገ ለማለት ይመቻል፡፡ ተጸነሰ ተወለደ ለማለት ጥንቱ ከሰማያት ወረደ ማለት እንደሆነ ሁሉ፤ ‹‹ተሰቀለ፤ ሞተ፤ ተቀበረ፤ ተነሣ›› ለማለት ‹‹ጥንቱ፤ ተጸነሰ፥ ተወለደ፥ አደገ፥ ተመላለሰ፥ ሠላሳ ዓመት ኖረ›› የሚለው ነው፡፡ ስለሆነም ቅዱስ ዮሐንስ ጠርዝና ጠርዙን ይዞ ተናገረ፡፡ * ‹‹ወረደ ዐረገ›› የሚሉት ሁለት ቃላት የዓለም ድኅነት መነሻና መድረሻ ናቸው፤ እነዚህን ሁለት ቃላት ስናይ በሁለቱ መካከል የተፈጸሙትን የአምላክ ሥራዎች ልብ ማለት ይገባል፡፡ ቤት በመሠረት ይጀመራል በጣሪያ ይፈጸማል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ይህን የቤዛነት ሥራ ሲያስረዳ በዮሐ.1፥14 ‹‹ቃል ሥጋ ኮነ፤�ቃል ሥጋ ሆነ›› ብሎ ጀምሯል፤ ይህንንም ቃል ‹‹ከሰማይ ከወረደው የሰው ልጅ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ የለም›› በማለት ሰው መሆኑን ብቻ ሳይሆን በአርያም የሚኖር መሆኑን አስተማረን፡፡ እንግዲህ ጌታችን ዕርገት እንዲሁ እንደ እንግዳ ደራሽ ፥ እንደ ውኃ ፈሳሽ አለመሆኑን ቀድሞ በነቢያት የተነገረ፤ ኋላም በሐዋርያት የተመሰከረ መሆኑን ማወቅ ያስፈለጋል፡፡ #የክርስቶስ_ዕርገት_በትንቢተ_ነቢያት ፠ ‹‹ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም ጨለማ /ዲያብሎስ/ ከእግሩ በታች ነበር በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ በነፍሳትም ክንፍ በረረ፡፡›› መዝ.17፥9 ፠ ‹‹አምላክ በእልልታ እግዚአብሔር በመለከት ድምጽ ዐረገ መዝ.46፥5 ወደላይ ዐረግህ፥ ምርኮን ማረክህ ፥ ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ›› መዝ.67፥18፡፡ ፠ ‹‹ዘምሩ ለእግዚአብሔር ዘዓርገ ውስተ ሰማይ ዘመንገለ ጽባሕ፤ በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ›› መዝ.67፥33፡፡ #የክርስቶስ_ዕርገት_በትምህርተ_ሐዋርያት ፠ ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተነጋገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ማር.16፥19 ፠ ‹‹እስከ ቢታንያ አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ፡፡››�ሉቃ.24፥50 ፠ ‹‹ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ ደመናም ከዐይናቸው ሰውራ ተቀበለችው፤ እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኩር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ እነሆ ነጫጭ ልብስ ለብሰው ሁለት ሰዎች /መላእክት/ በአጠገባቸው ቆሙ ደግሞም ‹‹የገሊላ ሰዎች ሆይ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት ዳግመኛ ይመጣል፡፡›› አሏቸው››� ሐዋ.1፥9-12 በማለት ሐዋርያት የክርስቶስን ዕርገት ከመላእክት ጋር ሆነው እንደተመለከቱ ደስታውን እንደተካፈሉ ቅዱስ ሉቃስ ጽፎልናል፡፡ በትንሣኤው ነጭ ልብስ ለብሰው የታዩ መላእክት የደስታ ዘመን ነው ሲሉ በዕርገቱም ነጭ ልብስ ለብሰው የዕርገቱን የምሥራች ለሐዋርያት አብስረዋል፡፡                                       ፠በዓለ ዕርገት መቼ ነው? ጥንተ ዕርገቱ ግንቦት ስምንት ሐሙስ ቀን በ34 ዓ.ም በዘመነ ማርቆስ ነው፡፡ ፠የዕረገት በዓል አከባበር እስከ አራተኛው መቶ ዓመት ድረስ እንደ ዛሬው ሐሙስን ሳይጠብቅ በጥንተ ዕርገቱ ግንቦት ስምንት ቀን ብቻ ይከበር ነበር፡፡ በአራተኛው ምዕተ ዓመት ወዲህ ግን ትንሣኤ በዋለ በአርባኛው ቀን ብቻ እንዲከበር ቅዱስ ዲሜጥሮስ በባሕረ ሐሳብ ቀመሩ ስሌት መሠረት ይከናወን ዘንድ በቀኖና ቤተክርስቲያን ተወስኖ በሥራ ላይ ውሎ ይገኛል፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤    ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/  የተዘጋጀ ::   #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram...  https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot  .YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w                    www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .

ግንቦት_16 ተዛካር ዮሐንስ  ፍቁረ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ  *በእንተ ስብከቱ ቅዳሴ ቤቱ ውስተ ሀገረ እስክንድርያ *ወሶበ ጽሕፈቱ *ወዕረገቱ ውስተ ሰማያት *ወርእዮቱ ለሠራዊተ ሰማያውያነ ፡፡ ✤ወደ ሰማይ ወጥቶ በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሰራዊትን ሥራዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ፡፡ ✤ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ነው ፡፡ ✤በእስክንድርያም ሀገር ቤተክርስቲያን የከበረችበት ዕለት ነው ፡፡ ሰላም ለቅደሴ ቤትከ በእለ እስክንድርያ ሀገር ፡፡ እለ ሐነፅዋ ኬነውት ወጠበብታ ምክር፡፡ ወእንዘ ትበውእ ዮሐንስ ውስተ መቃብር ፡፡ ተኀባዕከ ወተሠወርከ በሥልጣን ኀይል መንክር ፡፡ ባሕቱ ልብሰከ ዘተተፈ ለዝክር ፡፡ #በተለያዩ_ቅጽል_ስሞች_የሚጠራ፤ (100 አካባቢ ከሚጠጉ ስሞቹ ጥቂቶቹን /21ዱን ስሞች ከጽሑፍ በስተመጨረሻ ይመልከቱ) #ሰዓሊ_የኾነ፤ የጌታችንን ስነ ስቅለት የሳለ፡፡ #ከ81ዱ_የመጽሐፍ_ቅዱስ_ክፍሎች_5ቱንና_ሌሎች_መጻሕፍትንም_(ነገረ ማርያምን ..) የደረሰ፤ #ብዙ_ደቀ_መዛሙርትን_ያስተማረ፤ ወደ ሰማይ ወጥቶ በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሰራዊትን ሥራዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ፡፡ ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ነው ፡፡ በእስክንድርያም ሀገር ቤተክርስቲያን የከበረችበት ዕለት ነው ፡፡ #share እና #Like ማድረግ እንዳይረሱ ጌታ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን  ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው፡፡ ✤ዮሐንስ ንጹሕ በአምሳለ ትጉሃን፤ (#ዮሐንስ_እንደ_መላእክት_ንጹሕ_ነው፤) ✤ዮሐንስ ድንግል ምክሐ ቅዱሳን፤ (#ዮሐንስ_ድንግል_የቅዱሳን_መመኪያ_ነው፤) ✤ዮሐንስ ስርግው በቀጸላ ሥን በሜላተ ብርሃን፤ (#ዮሐንስ_በብርሃን_መጐናጸፊያና_ሻሽ_የተጌጠ_ነው፤) ✤ዮሐንስ አርጋኖነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ (#ዮሐንስ_የቤተ_ክርስቲያን_በገና_ነው፤) ✤ወበቃለ ቀርን ዘይኬልህ በኤፌሶን፥ ይስአል ለነ ስርየተ ለኀጥኣን፡፡ (#በኤፌሶን_ዐዋጅ_የሚናገር_ዮሐንስ_ኀጥኣን_ለምንሆን_ለኛ_ይቅርታን_ይለምንልን፡፡ /እመጽሐፈ ሰዐታት/ ፨ ‹‹ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ፤ ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ›› /መልክአ ኢየሱስ/ ፨ ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ ዘሰዓሞ፤ ዮሐንስ ርኄ ዮሐንስ ቀናንሞ፤ ለዝ ወልድኪ መሐሪ ኅሩመ በቀል ወተቀይሞ፤ ማርያም ሀብኒ በእዴኪ እንዘ ትጼውዒ ስሞ፤ ሥጋሁ ቅዱሰ ወክቡረ ደሞ፡፡ /መልክአ ሥዕል/ ፨#100_አካባቢ_ከሚጠጉ_ስሞቹ_ጥቂቶቹን_21ዱን_ስሞች_እነኾ፤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ፤ ዮሐንስ #ፍቁረ እግዚእ፥ (የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፣ ናያዕቆብ ) ዮሐንስ ቀዳሚዉ ነዉ፡፡ ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ፣ ምሥጢረ መንግስትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13፡ 23 ፡፡ ወልደ #ዘብድዮስ ፥ ዮሐንስ #ነባቤ መለኮት ፥ ዮሐንስ #ቦኦርኔጌስ ፥ ዮሐንስ #አብቀለምሲስ ፥  (ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ትጉሙም የራዕይ አባት ማለት ነዉ፡፡) ዮሐንስ #ወንጌላዊ ፥ ዮሐንስ #ድንግል ዮሐንስ #ታዎሎጎስ  ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን  አስፍቶ በመጻፉ (ታዎሎጎስ) ተብሏል፡፡ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡ 1. #ዮሐንስ_ብፁዕ (ብፁዕ ዮሐንስ) 2. ዮሐንስ ድንግል 3. #ዮሐንስ_ፍንው 4. #ዮሐንስ_ካህን 5. #ዮሐንስ_ኅሩይ 6. ዮሐንስ ሥርግው 7. #ዮሐንስ_ምዑዝ 8. ዮሐንስ ቅኑይ 9. #ዮሐንስ_ማኅቶት 10. ዮሐንስ ቤዛ ሰማይ 11. #ዮሐንስ_ክቡር 12. ዮሐንስ ጻድቅ 13. #ዮሐንስ_ረድእ 14. ዮሐንስ ማኅቶት 15. #ዮሐንስ_ድንግል 16. ዮሐንስ ንጹሕ 17. #ዮሐንስ_ለባዊ 18. ዮሐንስ መረግድ 19. #ዮሐንስ_ዕንቈ 20. ዮሐንስ መልአክ 21. #ዮሐንስ_ኪሩብ 22. #ቁጽረ ገጽ ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል፡ በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን አሜን /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤    ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/  የተዘጋጀ ::   #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram...  https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot  .YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w                    www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .

ግንቦት_16 ተዛካር ዮሐንስ  ፍቁረ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ  *በእንተ ስብከቱ ቅዳሴ ቤቱ ውስተ ሀገረ እስክንድርያ *ወሶበ ጽሕፈቱ *ወዕረገቱ ውስተ ሰማያት *ወርእዮቱ ለሠራዊተ ሰማያውያነ ፡፡ ✤ወደ ሰማይ ወጥቶ በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሰራዊትን ሥራዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ፡፡ ✤ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ነው ፡፡ ✤በእስክንድርያም ሀገር ቤተክርስቲያን የከበረችበት ዕለት ነው ፡፡ ሰላም ለቅደሴ ቤትከ በእለ እስክንድርያ ሀገር ፡፡ እለ ሐነፅዋ ኬነውት ወጠበብታ ምክር፡፡ ወእንዘ ትበውእ ዮሐንስ ውስተ መቃብር ፡፡ ተኀባዕከ ወተሠወርከ በሥልጣን ኀይል መንክር ፡፡ ባሕቱ ልብሰከ ዘተተፈ ለዝክር ፡፡ #በተለያዩ_ቅጽል_ስሞች_የሚጠራ፤ (100 አካባቢ ከሚጠጉ ስሞቹ ጥቂቶቹን /21ዱን ስሞች ከጽሑፍ በስተመጨረሻ ይመልከቱ) #ሰዓሊ_የኾነ፤ የጌታችንን ስነ ስቅለት የሳለ፡፡ #ከ81ዱ_የመጽሐፍ_ቅዱስ_ክፍሎች_5ቱንና_ሌሎች_መጻሕፍትንም_(ነገረ ማርያምን ..) የደረሰ፤ #ብዙ_ደቀ_መዛሙርትን_ያስተማረ፤ ወደ ሰማይ ወጥቶ በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሰራዊትን ሥራዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ፡፡ ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ነው ፡፡ በእስክንድርያም ሀገር ቤተክርስቲያን የከበረችበት ዕለት ነው ፡፡ #share እና #Like ማድረግ እንዳይረሱ ጌታ እናቱንም እነሆ ልጅሽ ያላት እርሱን  ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ያለው ነው፡፡ ✤ዮሐንስ ንጹሕ በአምሳለ ትጉሃን፤ (#ዮሐንስ_እንደ_መላእክት_ንጹሕ_ነው፤) ✤ዮሐንስ ድንግል ምክሐ ቅዱሳን፤ (#ዮሐንስ_ድንግል_የቅዱሳን_መመኪያ_ነው፤) ✤ዮሐንስ ስርግው በቀጸላ ሥን በሜላተ ብርሃን፤ (#ዮሐንስ_በብርሃን_መጐናጸፊያና_ሻሽ_የተጌጠ_ነው፤) ✤ዮሐንስ አርጋኖነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ (#ዮሐንስ_የቤተ_ክርስቲያን_በገና_ነው፤) ✤ወበቃለ ቀርን ዘይኬልህ በኤፌሶን፥ ይስአል ለነ ስርየተ ለኀጥኣን፡፡ (#በኤፌሶን_ዐዋጅ_የሚናገር_ዮሐንስ_ኀጥኣን_ለምንሆን_ለኛ_ይቅርታን_ይለምንልን፡፡ /እመጽሐፈ ሰዐታት/ ፨ ‹‹ሰላም ለአፉከ ለዮሐንስ ዘሰዓሞ፤ ንጽሐ ኅሊናሁ ወልቡ ለዐይነ ፍትወትከ ሶበ አደሞ›› /መልክአ ኢየሱስ/ ፨ ሰላም ለሥዕልኪ ወለሥዕለ ወልድኪ ዘሰዓሞ፤ ዮሐንስ ርኄ ዮሐንስ ቀናንሞ፤ ለዝ ወልድኪ መሐሪ ኅሩመ በቀል ወተቀይሞ፤ ማርያም ሀብኒ በእዴኪ እንዘ ትጼውዒ ስሞ፤ ሥጋሁ ቅዱሰ ወክቡረ ደሞ፡፡ /መልክአ ሥዕል/ ፨#100_አካባቢ_ከሚጠጉ_ስሞቹ_ጥቂቶቹን_21ዱን_ስሞች_እነኾ፤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ዮሐንስ፤ ዮሐንስ #ፍቁረ እግዚእ፥ (የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ለጌታ በጣም ቀራቢ ከነበሩት ሦስት የምሥጢር ሐዋርያት (ጴጥሮስ ፣ ናያዕቆብ ) ዮሐንስ ቀዳሚዉ ነዉ፡፡ ጌታችን ምሥጢረ ተአምራትን በኢያኢሮስ ቤት ፣ ምሥጢረ መንግስትን (መለኮትን) በደብረ ታቦር፣ ምሥጢረ ምጽአትን በደብረ ዘይት ፣ ምሥጢረ ጸሎትን በጌቴ ሴማኒ ሲገልጽና ሲያሳይ አብሮ የተመለከተ በመሆኑና ለጌታ በጣም ቀራቢ በመሆኑና በወንጌልም ‹‹ጌታ ይወደዉ የነበረ ደቀ መዝሙር ››ተብሎ ስለ ተጠቀሰ የጌታ ወዳጅ ፍቁረ እግዚእ ይባላል፡፡ዮሐ 13፡ 23 ፡፡ ወልደ #ዘብድዮስ ፥ ዮሐንስ #ነባቤ መለኮት ፥ ዮሐንስ #ቦኦርኔጌስ ፥ ዮሐንስ #አብቀለምሲስ ፥  (ፍጥሞ በምትባል ደሴት ላይም ወደ ፊት የሚሆነዉን ነገር በራእይ ስለተገለጸለት በግሪክ ቋንቋ አቡቀለምሲስ ተብሏል፡፡ትጉሙም የራዕይ አባት ማለት ነዉ፡፡) ዮሐንስ #ወንጌላዊ ፥ ዮሐንስ #ድንግል ዮሐንስ #ታዎሎጎስ  ቅዱስ ዮሐንስ ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን  አስፍቶ በመጻፉ (ታዎሎጎስ) ተብሏል፡፡ትርጉሙም ነባቤ መለኮት (የመለኮትን ነገር የሚናገር)ማለት ነዉ፡፡ 1. #ዮሐንስ_ብፁዕ (ብፁዕ ዮሐንስ) 2. ዮሐንስ ድንግል 3. #ዮሐንስ_ፍንው 4. #ዮሐንስ_ካህን 5. #ዮሐንስ_ኅሩይ 6. ዮሐንስ ሥርግው 7. #ዮሐንስ_ምዑዝ 8. ዮሐንስ ቅኑይ 9. #ዮሐንስ_ማኅቶት 10. ዮሐንስ ቤዛ ሰማይ 11. #ዮሐንስ_ክቡር 12. ዮሐንስ ጻድቅ 13. #ዮሐንስ_ረድእ 14. ዮሐንስ ማኅቶት 15. #ዮሐንስ_ድንግል 16. ዮሐንስ ንጹሕ 17. #ዮሐንስ_ለባዊ 18. ዮሐንስ መረግድ 19. #ዮሐንስ_ዕንቈ 20. ዮሐንስ መልአክ 21. #ዮሐንስ_ኪሩብ 22. #ቁጽረ ገጽ ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል፡ በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን አሜን /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ፤    ትምሕርት ዋና ክፍል ፥ ንዑስ ክፍል /ሕትመት እና ሚዲያ/  የተዘጋጀ ::   #share Contact: https://t.me/finotehiwot1927 .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .Telegram...  https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot  .YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w                    www.finotehiwotsundayschool.com ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ት.ቤት .

#ሰበር_ዜና የሀገሬ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መምህር ብርሃኑ አድማስ ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓም በፀጥታ ኀይሎች ከቢሯቸው ተወስደዋል። መምህር ብ
#ሰበር_ዜና የሀገሬ ቴሌቪዥን ሥራ አስኪያጅና  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መምህር ብርሃኑ አድማስ ዛሬ ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓም በፀጥታ ኀይሎች ከቢሯቸው ተወስደዋል። መምህር ብርሃኑ ለጥያቄ እንፈልግሃለን ተብለው በፌደራል የወንጀል ምርመራ ቢሮ ውስጥ እንደሚገኙ ማ.ቅ አረጋግጧል።

፨፨፨የዓለም ኹሉ መምህር የኾነው #ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ባረፈ በ35 ዓመቱ (በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን) በዛሬዋ ዕለት ያረፈበት ነው፤ የቅዱሱ ሥጋውም ፍልስት ኅዳር 17 በቊስጥንጢንያ ሆኗል ሥጋውም በዚያን ሰዓት ሕዝቡን ቀና ብሎ  ባርኳል፡፡ #share ፨፨፨በአንበሳ ላይ የምትጫነው ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዕረፍቷ ነው፡፡ ---በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው የሊቁ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቤተ ክርስቲያን በደቡዊት ኢትዮጵያ ሌሾ ማዞሪያ ፤ ታኅሣሥ 12  ቀን 2012 ዓ.ም. የመሠረት ደንጊያ ተቀምጧል፡፡ሌሾ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቦታው፤ ከአ.አ. ወደ ወላይታ መንገድ፤ ወደ ዱራሜ መታጠፊያ፤ ከአደሮ ከተማ  አጠገብ ሌሾ ማዞሪያ ጋር የሚገኝ፤ ሌሾ ማዞሪያ የሚገኘው፤ በደቡብ ክልል በከምባታ ጠንባሮና ሃላባ ሀገረ ስብከት፤ ከአ.አ  287 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ የሚገኝ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፨በ347 ዓ.ም. በሶርያ ዋና ከተማ በአንጾኪያ ሲኾን የተወለደው፤ አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ አትናስያ ይባላሉ፡፡ ፨ገና የ15 ዓመት ሕፃን ሳለ በሕፃንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) በሙሉ ተምሮ ተመልሷል፤ በዚህም በመንፈሳዊውም ኾነ በዘመናዊው ይፍልስፍና ይህ ቀረህ የማይባል ሊቅ ኾነ፡፡ ፨ቅዱሱ በ16 ዓመቱ ኃብትና ንብረቱን ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ፤ በበርሃ ሳለም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጥተው፤ ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሰጡት፡፡ የመጻሕፍት ድርሰት ተገለጹለት፤ በዚህም ቅዱስ በትጋትና በንቃት እጆቹ ታመው በክር አስሮ እስኪጽፍ ድረስ ዐሥር ሺህ  የሚደርሱ ድርሳናትን መልዕክታትንና ትርጓሜያትን ጻፈ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ፤ በቅድስናው ወደውታልና የቊስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት፡፡ በሚያስተምርበት ጊዜም ከጣዕመ ትምህርቱ የተነሣ ሕዝቡ ተመስጠውና ተደመው ይሰሙት ነበር፤ ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር፡፡ በሠርጓ ቀን በሞት ሊወስዳት የመጣውን መልከአከ ሞት ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ ገዝቶ 10 ዓመት አቁሞታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ.ም. አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: ገና የ15 ዓመት ሕፃን ሳለ በሕፃንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) በሙሉ ተምሮ ተመልሷል፤ በዚህም በመንፈሳዊውም ኾነ በዘመናዊው ይፍልስፍና ይህ ቀረህ የማይባል ሊቅ ኾነ፡፡ *ቅዱሱ በ16 ዓመቱ ኃብትና ንብረቱን ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ፤ በበርሃ ሳለም ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጥተው፤ ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሰጡት፡፡ የመጻሕፍት ድርሰት ተገለጹለት፤ በዚህም ቅዱስ በትጋትና በንቃት እጆቹ ታመው በክር አስሮ እስኪጽፍ ድረስ ዐሥር ሺህ  የሚደርሱ ድርሳናትን መልዕክታትንና ትርጓሜያትን ጻፈ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ፤ በቅድስናው ወደውታልና የቊስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት፡፡ በሚያስተምርበት ጊዜም ከጣዕመ ትምህርቱ የተነሣ ሕዝቡ ተመስጠውና ተደመው ይሰሙት ነበር፤ ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር፡፡ በሠርጓ ቀን በሞት ሊወስዳት የመጣውን መልከአከ ሞት ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ ገዝቶ 10 ዓመት አቁሞታል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ.ም. አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ:: ✣✣✣ስለ ቀዳማዊው ሊቅ ቅዱስ  ዮሐንስ አፈወርቅ ዳግማዊው ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ (አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ) እንዲህ ብሎ ገልጾታል፡፡፣አፈ ዕንቊ ፣አፈ ጳዝዮን ፤(/ስለ እመቤታችን ፍቅር/ የወር አበባ ያላትን ሴት አንቀጸ ሥጋ ለመሳም ያላፈረ)፣አፈ ባሕርይ (በድርስቶቹ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስጌጣት)፣አፈ መዐር ፣አፈ ሦከር (በቃሉ ጣፋጭነት ምእመናንን የሚያለመልማቸው)፣አፈ አፈው /ሽቱ/ (በትምህርቱ መዐዛ የምሥጢር በጎችን ደስ የሚያሰኛቸው) ፣አፈ ርኄ፣አፈ ሰይፍ (በውግዘቱ ሥልጣን ከሀዲዎችን የሚቆርጥ) ፣አፈ መጥባሕት፣የማይነዋወጥ ዐምድ፣የማይፈርስ መሠረት፣ከሞገዶች መነሣት የተነሣ የማይሰበር መርከብ፣በሃይማኖት ባሕር ውስጥ የሚዋኝ ዋናተኛ፣የማይፈርስ ግንብ፣በጠላት ፊት የሚፀና አዳራሽ /መጽሐፈ ምሥጢር፣ /