en
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Open in Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Show more

📈 Analytical overview of Telegram channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Channel Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) in the Amharic language segment is an active participant. Currently, the community unites 15 327 subscribers, ranking 5 647 in the Religion & Spirituality category and 2 194 in the Ethiopia region.

📊 Audience metrics and dynamics

Since its creation on невідомо, the project has demonstrated rapid growth, gathering an audience of 15 327 subscribers.

According to the latest data from 17 June, 2026, the channel demonstrates stable activity. Although there has been a change in the number of participants by -87 over the last 30 days and by -13 over the last 24 hours, overall reach remains high.

  • Verification status: Not verified
  • Engagement rate (ER): The average audience engagement rate is 21.14%. Within the first 24 hours after publication, content typically collects 9.89% reactions from the total number of subscribers.
  • Post reach: On average, each post receives 3 240 views. Within the first day, a publication typically gains 1 515 views.
  • Reactions and interaction: The audience actively supports content: the average number of reactions per post is 23.

📝 Description and content policy

The author describes the resource as a platform for expressing subjective opinions:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Thanks to the high frequency of updates (latest data received on 18 June, 2026), the channel maintains relevance and a high level of publication reach. Analytics show that the audience actively interacts with content, making it an important point of influence in the Religion & Spirituality category.

15 327
Subscribers
-1324 hours
-147 days
-8730 days
Posts Archive
ዛሬ ጥር 22 ቀን፤ #የብርሃን_መልአክ_ከሣቴ_ምሥጢር_የሆነው_ቅዱስ_ዑር/ራ/ኤል_በዓለ_ሢመቱ ነው፤ እንኳን አደረሰን፡፡ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤ 1ኛ) በአዲስ አበባ የሚገኘው
+6
ዛሬ ጥር 22 ቀን፤ #የብርሃን_መልአክ_ከሣቴ_ምሥጢር_የሆነው_ቅዱስ_ዑር/ራ/ኤል_በዓለ_ሢመቱ ነው፤ እንኳን አደረሰን፡፡ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው አብያተ ክርስቲያናት፤ 1ኛ) በአዲስ አበባ የሚገኘውና ጥንታዊው ደብር #ደብረ_ጽጌ_ቅዱስ_ዑርኤል 2ኛ) #ግሸን_ቅዱስ_ዑርኤል 3ኛ) #ጎንደር_ደብረ_ኀይል_ቅዱስ_ዑርኤል_ወበዓታ፤ /ዛሬ ታቦተ ሕጉ ወደ ጠበል በመውረድ ይከብራል/ 4ኛ) አዲስ አበባ አዲስ ሰፈር አንፎ መንበረ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤልና መጥምቁ ዮሐንስና ቅድስት ልደታ ለማርያም ቤ.ክ. (ኮልፌ_ቀራንዮ_ክፍለ_ከተማ 5ኛ) ፉሪ ደብረ ገነት ቅዱስ ዑርኤል (የቤተ ክርስቲያኑ ፎቶ ካላችሁ ላኩልን) 6ኛ) ኤ(የ)ረር ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ዑርኤል (የቤተ ክርስቲያኑ ፎቶ ካላችሁ ላኩልን) /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

፨† መነኮሳት †፨ "ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል።" ማቴ ፲፱፥፳፱ ልመና ጸሎታቸው ትራዳን! /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

፠ ጥር 22 ቀን፤ #ርዕሰ_መነኰሳት_ቅዱስ_አባ_እንጦንስ_ልደቱና_ዕረፍቱ ነው፡፡ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት፤ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት የቅዱስ እንጦንስ ገዳማት፡፡ 1ኛ) #ጎንደር_ደብረ_እንጦንስ፤ በጻድቁ አፄ ዮሐንስ /ከ1659-1674/ የተመሠረተ፥ ከ44ቱ ታቦታተ ጎንደር አንዱና ዋነኛው፡፡ ጎንደር ከ300 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ መዲና ከተማ ሆና በቆየችባቸው ዘመናት የአቡን (የጳጳስ) ቤት (መንበረ ጵጵስና) ሆኖ ያገለገለ፡፡ 2ኛ) #እንጦንስ_ኢየሱስ፤ በጣና ላይ ከሚገኙ የደሴት ገዳማት አንዱ፡፡ 3ኛ) መንበረ ፓትርያርክ ቅዱስ እንጦንስ ገዳም፡፡ (አሁን ቅድስት ማርያምበመባል የሚጠራ) እንዲሁም 4ኛ) #ግብጽ_እንጦንስ_ገዳም ናቸው ‹‹ኀጢአታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል፤ ኃጢአታችንን እኛ ረስተን የምንጽናና ከሆነ ግን እግዚአብሔር ያስብብናል፡፡›› /ቅዱስ እንጦንስ/ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

#ጥር21_አስተርእዮ_ማርያም_ ( #በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_ለሶልያና ) #እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡ #ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ፤ #ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት፤ #ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት፡፡ ፠ ጌታችን ለእናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና  አባቷ  ወደተቀበሩበት  ወደ ጌቴ  ሴማኒ  ሲወስዷት  አይሁድ  አይተው፤  ልጇ ተነሳ፥ አረገ  እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው  አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ  በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ ….. ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ በነሐሴ 14 ነው /ሌላውን ታሪክ በፍልሰታ ጾም ላይ ያንብቡ፤ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››/ ጊዜ ዕረፍታ ለሶልያና(ለማርያም) ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡ #ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡ *የእመቤታችንን ዕረፍት ሊቁ ቅዱስ  ያሬድም  ‹‹ሞትሰ  ለመዊት ይደሉ፥  ሞታ  ለማርያም የአጽብ ለኵሉ፡፡ /ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁለን ያስደንቃል፡፡›› በማለት አደንቆ ጽፏል፡፡ *እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ የላይ ቤት (የግምጃ ቤት ማርያም) አብነትና የታች ቤት(የበዓታ) አብነትን ሁለቱንም አዘጋጅተንላችኋል፡፡ መልካም ክብረ በዓል፡፡ **ክብረ በዓሉ በሃገራችንና በዓለማችን ክፍሎች ባሉ የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት የሚከብሩ ቢሆንም ግን፤ በልዩ ሁኔታ እንደ ጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደ ጥምቀት በዓል፤ ከዋይዜማው ጀምሮ ወደ ጥምቀተ ተወርዶ በማደር ክብረ በዓሉ በልዩ ሁኔታ መከበሩን ልብ ይሏል፡፡ (የሎዛ ማርያምና የጥር 21 በዓል አከባበሯን ፎቶ ያላችሁ ላኩልን፡፡) ፠ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት የሚቆመውን ማኅሌ እነሆ ብለናል፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot1958

፨†  ሰማዕታት  †፨ "እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን::" ሥርዓተ ቅዳሴ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot2719

እንኳን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰባረ ዓፅሙ ፠ ዐላውያን ነገሥታት በደብረ ይድራስ ተራራ ላይ የሊቀ ሰማዕቱን ሥጋውንና አጥንቱ በመንኰራኵር ፈጭተው በነፋስ ለበተኑበት፤ ነገር ግን ለአምላካችን የታመነ ሰማዕት በመሆኑ ያረፈበት መሬትና ዕፅዋት ጊዮርጊስ ቅዱስ ለእግዚአብሔር እያሉ ያመሰገኑበት ነው፡፡ ፠ አማን በአማን፤ አማን በአማን፤ ኮከበ ልዳ ፀሐየ ፋርስ፡፡ ፠ እንደ ጎንደር አበራ ጊዮርጊስ ባሉት ክብረ በዓሉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርዶና አድሮ ነው በዓሉ የሚከበረው፡፡ ፠ በጥር 18 ከዋይዜማው ጀምሮ የቅዱስ ጊዮርጊስ አብያተ ክርስቲያናት ባሉበት በሙሉ የሚቆመውን ሥርዐተ ማኅሌት እነሆ ብለናል፡፡ /በፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሚድያና ሕዝብ ግንኙነት ዋና ማስተባበሪያ ክፍል የተዘጋጀ።/ • Facebook 👉 m.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool • Telegram 👉 t.me/finotehiwott • Tiktok 👉 tiktok.com/@finotehiwot  • YouTube 👉 m.youtube.com/@finotehiwot2719