cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

🏆🏆ፍኖት የደራሲያን ማኀበር🏆🏆

…… ፍኖት የጥበብ ቤት …… ሀሳብ አስተያየቶን በ @KING_SGL ላይ ያስቀምጡ

Show more
Advertising posts
620
Subscribers
+124 hours
+77 days
+2230 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

በትንሣኤ በዓል እርድ መከናወን ያለበት መቼ ነው? ༺ ༻ ✍ ብዙ ሰዎች የቀዳም ስዑር ምሽት በሬ፣ ዶሮ፣ በግ •• ወዘተ ያርዳሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይህ እንዴት ይታያል? በማለት ጥያቄዎች በውስጥ መስመር ስጠየቅ ነበር። ዘመኑ በአመጣው በሕዋ አውታር መልስ መስጠት ተገቢ በመሆኑ መልስ ለመስጠት ተገድጃለሁ !ቅዱስ ጳውሎስ " #መብል ግን ወደ እግዚአብሔር አያቀርበንም፤ ባንበላም ምንም አይጎድለንም ብንበላም ምንም #አይተርፈንም"ይላል(፩ቆሮ ፰÷፰) -በቀዳም ስዑር ምሽት ማረድ በልማድ ተያይዞ የመጣ እንጂ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያም ሆነ ትውፊቱ አይፈቅድም (አይደለም )። -✍አንዳንዶች በቀዳም ስዑር ለምን እንደሚያርዱ ሲጠየቁ "#ለበዓሉ ቅድመ ዝግጅት ለማድረግ ፣#ሌሊት ከቤተ ክርስቲያን አስቀድሰው ሲመለሱ ለመግደፍና ነዳያንን ለማስፈሰክ ነው" በማለት ይመልሳሉ።ወገኖቼ ምክንያት ከተጠያቂነት አያድንም ። ✍ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ግን ሲያትቱ የሚያስፈልጋቸው የሚባሉት በባሕርያቸው የሞቱ ለምንላቸው ምግቦች ነው። ማለትም እንጀራ ፣ዳቦ ወዘተ።ምክንያቱም እነዚህን ለማዘጋጀት ብዙ ጊዜ የሚፈልግ ነውና።እንሰሳት ግን ደመ ነፍስ ናቸው።እንሰሳትን ለማረድ ዝግጅት አይጠይቅም፣በፍጥነት የሚታረዱ ናቸው። ✍ ነዳያንን ለማስፈሰክ ለተባለውም ውኃ ለማያነሳ መልስ #ተንሥአ እሙታን ከሚባልበት ከመንፈቀ ሌሊት በኋላ ተሠርቶ የሚደርስ ነው። -✍ ስለዚህ "ወተንሥአ እሙታን፣ከሙታን ተለይቶ ተነሣ " ተብሎ ሳይታወጅ መታረድ የለበትም።በቀዳም ስዑር ማረድ ዐዋጅ ሳይታወጅ ከማረዳችንም በላይ የትንሣኤን በዓል አላከበርንም እንደማለት ነው። -✍ በቅዳሜ ምሽት" #በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ" ሳይባል ፣በመስቀል ሳይባረክ ማረድ ፣በዘመነ ኦሪት እንደ ታረደ (እንደ ተሠዋ) ነው የሚቆጠረው። ምክንያቱም "#ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ፣ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ " አልተባለምና። -✍እንደ ሊቃውንቱ አገላለጽ ለሌሊት ከቅዳሴ መልስ በየቤታችን ልንመገባው የሚገባ ከጥሉላት ምግቦች ርቀን ከመቆየታችን አንጻር ጤንነታችን የማይጎዳ፣ ተልባ፣ በወተት በእርጎ ተደርጎ መበላት አለበት ። እርድ መፈጸም ያለበት ጠዋት ወይም ደግሞ "ወተንሥአ እሙታን " ከተባለበት ከሌሊቱ ፮ ሰዓት በኋላ ነው ።ያኔ መስቀል ይዞራልና። ✍አንዳንድ ሰዎች ሲናገሩ ቀዳም ስዑር ጾም መሆኑን እምናለሁ ።ነገር ግን ከምሽቱ ፲፩ (ከዋዜማው ) ጀምሮ ወደ ሚቀጥለው ቀን (እሑድ ) ስለሚቆጠር ማረድ ይቻላል ሲሉ ይደመጣሉ።ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሲመልሱ ፍትሐ ነገሥት በአንቀጸ ጾም ላይ " ክብርት በምትሆን በ40 ጾም በመጀመሪያ ው ሱባኤ እስከ ፲፪ ሰዓት ፣በሰሙነ ሕማማት፣ እስከ ፲፫ ሰዓት ከሌሊቱ ፩ ሰዓት ጨምሮ ወይም እስከ #ፀአተ ኮከብ ( ኮከብ ከሰማይ መልቶ እስኪታይ፣ )ጹሙ" ይላል።ቅዱሳት መጻሕፍትም ለጾም ማድላት እንዳለብን ይመክሩናል። ✍ ከምሽቱ ፲፩ ጀምሮ ወደ ሚቀጥለው ቀን (ወደ ማግስት ) ነው የሚቆጠረው የሚባለው ለምስጋና ሲሆን ነው። ጾም ግን ወዲያውኑ በተግባር (በድርጊት ) የሚፈጸም ነው። ወደ ማግሥቱ ይቆጠራል አንልም።ምክንያቱም #ጾም ተግባር ነውና። ✍. በቀዳም ስዑር ማረድ #የጾም ክፍል በኾነው ሰዓት ከማረዳችን በተጨማሪ የትንሣኤን ምሥራችን አይሰብክም። ምክንያቱም ጌታችን እስኪነሣ ድረስ በኅዘን ነው ያለነው።እንደ ሥርዓቱ ከሆነ ሲታረድ ካህኑ ቢላዋውን ይባርክለታል አራጁ ያርዳል።በገጠሪቱ ኢትዮጵያ #በዐቢይ ጾም እንኳን ሰው #ቢላዋ ታጥቦ ይጾም ነበር። ቅዱስ ጳውሎስ "ነገር ግን ሁሉ በአገባብና በሥርዓት ይሁን"ብሏል(፩ኛ ቆሮ ፲፬፥፵) ሚዛን የጠበቀ ውይይት ማከናወን ይቻላል ። @ሐመር መጽሔት መጋቢት/ሚያዝያ 1996 ዓ.ም ★ ★ ★ “#ዘቦ ዕዝን ሰሚዐ ለይስማዕ (ማር.፬፥፱፣ማቴ፲፩፥፲፭፣) ★ ★ ★ ☜ መ/ር ተመስገን ዘገዬ ፈዋሴ ዱያን ጊዮርጊስ እምነ ከራድዮን ዖፍ ።ስምዐኒ ጸሎትየ ወስእለትየ ዘዘልፍ። #ኦ አምላከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕቀበኒ ወአድኅነኒ እመከራ ሥጋ ወነፍስ ሊተ ለወልደ ሥላሴ ! ━━━━━━━༺✞༻━━━━━
Show all...
ትንሣኤከ ለእለ አመነ ትኖሣኤከ ለእለ አመነ፣ ፈኑ ዲቤነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ።
Show all...
ዮም ፍሥሐ ኮነ በሰንበተ ክርስቲያን፣ እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን አማን እስመ ተንሥአ።
Show all...
የትንሣኤ ወረብ ዮም ፍሥሐ ኮነ ሰንበተ ክርስቲያን እስመ ተንሥአ ክርስቶስ እሙታን ቀደሳ ወአክበራ ቀደሳ ወአክበራ ወአልዓላ እምኵሎን መዋዕል።
Show all...
ምስባክ ዘትንሣኤ (ዘማሕሌት) መዝ 77á65 ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃህ እምንዋም። ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን። ወቀተለ ፀሮ በድኅሬሁ።    ማጋራት መተሳሰብ ነው! ሟር!         ሟር!             ሟር! ቴሌግራም- ይ🀄 ላ 🀄ሉ 👇👇👇 🇪🇹 https://t.me/Loveerdey 🇪🇹 https://t.me/FENOT_ARTE 🌟🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌟 ፌስቡክ ገጽ - https://facebook.com/groups/1176146600045288/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v       💚 @FENOT_ARTE 💚 💛 @FENOT_ARTE 💛 ❤️ @FENOT_ARTE ❤️
Show all...
👉 ድርሳነ ማሕየዊ ዘቀዳሚት    ማጋራት መተሳሰብ ነው! ሟር!         ሟር!             ሟር! ቴሌግራም- ይ🀄 ላ 🀄ሉ 👇👇👇 🇪🇹 https://t.me/Loveerdey 🇪🇹 https://t.me/FENOT_ARTE 🌟🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌟 ፌስቡክ ገጽ - https://facebook.com/groups/1176146600045288/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v       💚 @FENOT_ARTE 💚 💛 @FENOT_ARTE 💛 ❤️ @FENOT_ARTE ❤️
Show all...
የማርያም ለቅሶ ልጄ ወዳጄ ሆይ ለእኔ ወዮታ አለብኝ ... በጦር ሲወጉህና ሲገድሉህ ዓይኖቼ ከምያዩ ይልቅ ልጄ ወዳጄ ሆይ ነፍሴን ከስጋዬ ትለያት ዘንድ እማልድሃለሁ። ልጄ ወዳጄ ሆይ ይህ በራስህ የተቀዳጀኸው የእሾህ አክሊል ምነው እኔ በተቀዳጀሁትና የመከራህ ተሳታፊ በሆንኩ። ልጄ ወዳጄ ሆይ አንተን በእሱ ላይ በሰቀሉበት መስቀልህ በሰላም እሰናበትሃለሁ። ልጄ ወዳጄ ሆይ አይሁድ መራቃቸውን በተፉበት ብርሃንንም በተሞላ ፊትህ እሰናበትሃለሁ: ንጉስ ሆይ በሁለት ወንበዴዎች መካከል እርቃኑን ለቆመው አካልህ እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ። ልጄ ወዳጄ ሆይ እጣ በተጣጣሉበት ክብር ልብስህ እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ። ልጄ ወዳጄ ሆይ አክሊለ ሶክክን ለተቀዳጀ እራስህ ሰላም እያልኩና እጅ እየነሳሁ እሰናበትሃለሁ። ምንጭ ግብረ ሕማማት    ማጋራት መተሳሰብ ነው! ሟር!         ሟር!             ሟር! ቴሌግራም- ይ🀄 ላ 🀄ሉ 👇👇👇 🇪🇹 https://t.me/Loveerdey 🇪🇹 https://t.me/FENOT_ARTE 🌟🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌟 ፌስቡክ ገጽ - https://facebook.com/groups/1176146600045288/?mibextid=rS40aB7S9Ucbxw6v       💚 @FENOT_ARTE 💚 💛 @FENOT_ARTE 💛 ❤️ @FENOT_ARTE ❤️
Show all...