cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking ÂŤAccept allÂť, you agree to the use of cookies.

avatar

🌸Official Queen Azu👸

Join ma Chanel to get #new music #couple pics #tik tok challenge #Ďance #islamic pics #makeup💄 #video 👇👇👇 @queenazuu

Show more
The country is not specifiedThe language is not specifiedThe category is not specified
Advertising posts
671
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

ህይወቷን የቀየረ ዳዕዋ 💎 በየሳምንቱ ከጁሙዓ ሶላት በኃላ የአስራ አንድ ዓመት ልጁን ይዞ በሆላንድ ዋና ከተማ አምስተርዳምና በዙሪያዋ ባሉ ቦታዎች “ ጉዞ ወደ ጀነት ” የሚል ርዕስ የያዙ ኢስላማዊ መፅሃፍቶችን በነፃ የሚያድል አባት ነበር። ከሳምንቱ በአንደኛው ጁሙዓ አባት እና ልጅ ምሳቸውን እየተመገቡ ነው። በጎ ተግባራቸውን ሊያስተጓጉል የሚችል በረዶ የቀላቀለ ሃይለኛ ዝናብ መዝነብ ጀመረ። ልጁ የብርዱን ሀይል ለመቋቋም ልብሶቹን እየደረበ " አባቴ ! አሁን ዝግጁ ነኝ " አለ። አባት በልጁ ሁኔታ በመገረም " ለምኑ ነው ዝግጁ የሆንከው? " ሲል ጠየቀ። " መፅሃፎቹን የምናድልበት ሰዓት እኮ ደረሰ። እንንቀሳቀስ ብዬ ነው! " አለ ልጁ። አባት " አየሩ እኮ ከባድ ነው ፤ ብርድ ነው ። ለመንቀሳቀስ ያስቸግራል " አለ ። ልጁም ሲመልስ "አባቴ ሆይ! ወደ እሳት የሚጓዙ ሰዎች እያሉ ብርዱ ከተግባራችን ሊበግረን ከቶም መፍቀድ የለብንም" አባት በልጁ አንደበት የበለጠ ቢደመምም በዚያ ብርድ ወደ ውጭ መውጣት አልፈለገም። ልጁ ግን በአቅራቢያው ወዳሉ ቦታዎች እየዞረ መፅሃፍቶቹን እንዲያድል የአባቱን ፍቃድ ጠየቀ። 👉 ምንም እንኳ የልጁ እድሜ ትንሽ ቢሆንም በብርድ የተመቱትን የአምስተርዳም ጎዳናዎች እያሳበረ ተልዕኮውን ለመፈፀም አልገታውም ነበር። አልፎ አልፎ ላገኘው ሰው መፅሃፍቶቹን አድሎ ጨረሰ። በእጁ ላይ አንዲት መፅሃፍ ቀረች። ብቅ የሚል አንድም ሰው ጠፋ። ጎዳናው ላይ የሚታይ ምንም ነገር የለም። ካለበት ጎዳና በስተቀኝ በኩል ወዳለው መጀመሪያው ቤት በማምራት እጁ ላይ የቀረችውን መፅሃፍ ለመስጠት ከጀለ። 👉የቤቱን መጥሪያ ተጫነ። ማንም ብቅ ያለ የለም። በተደጋጋሚ መጥሪያውን ተጫነ። ምላሽ የለም። ለመጨረሻ ጊዜ መጥሪያውን ለተወሰኑ ሰከንዶች ተጭኖ ያዘ። በሩ ቀስ ብሎ ተከፈተ። ፊቷ በሀዘን የተቆራመደ ሴት ከልጁ ፊት ቆማለች ። በተርበተበተበአንደበት "ምን ልርዳህ ልጄ" !? አለችው። 👉 አንፀባራቂ በሆኑት አይኖቹ የደከመ ፊቷን እየቃኘ «በቅድሚያ ካስቸገርኩሽ እጅጉን ይቅርታ እንድታደርጊልኝ ስል እጠይቅሻለሁ። አላህ ይህን በእጄ ላይ የቀረውን መፅሃፍ አንቺ ዘንድ እንዲደርስ ፈቃዱ ቢሆን ነው ከበርሽ ያቆመኝ ። መፅሃፉ ስለ አላህ ማንነት ፣ የሰው ልጅ ወደዚህች ምድር የመጣበት ዓላማ እና ግብ እንዲሁም የአላህን ውዴታ ማግኘት የምንችልበትን መንገድ በጥልቀት ስለሚዳስስ ጥሩ ትምህርት ታገኝበታለሽ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ» በማለት መፀሃፉን ሰጣት። አመሰግናለሁ !" አለች። ልጁም ወደ ቤቱ ተመለሰ። 👉 ምዕመናኖች የጁሙዓን ሶላት ሰግደው እንደጨረሱ የሆነች ሴት ከመስጂዱ በር አቅራቢያ በመቆም እንዲህ አለች፡- "እዚህ ለሶላት ከመጡት ሰዎች መካከል እኔን ማንም የሚያውቀኝ የለም። ከዚህ በፊት በዚህ የመስጂድ ቅጥር ክልል ውስጥም ገብቼ አላውቅም። ከሳምንት በፊትም ሙስሊም አልነበርኩም። አንድም ቀን ሙስሊም እሆናለሁ ብዬ አስቤም አላውቅም። የማፈቅረው ውዱ ባለቤቴ ከጥቂት ወራት በፊት በሞት ተለየኝ። በዚህች ድቡልቡል መሬት ላይ ብቻዬን ጥሎኝ ሄደ። ያኖረልኝ ውርስ ሃዘን እና ጭንቀት ብቻ ሆነ። እንደኔ ፍላጎት ቢሆን ኖሮ ያለፈው ሳምንት አርብ ዕለት በገዛ እጄ ይህችን ዓለም የምሰናበትባት የፍፃሜዬ ቀን ነበረች። የተስፋ ጠብታ ከውስጤ ነጠፈ። የብቸኝነት እና የባዶነት ስሜት ከበበኝ ከፊቴ የሚታየኝ በጎ ነገር ስለሌለ ራሴን ለማጥፋት ወሰንኩ። ወንበር እና ገመድ አዘጋጀሁ። የቤቴ ጣራ ላይ ገመዱን አጥብቄ አሰርኩት። ፈራ ተባ እያልኩ ወንበሩ ላይ ወጣሁ። 👉ገመዱን አንገቴ ላይ እያጠለኩ ሳለ የቤቴ ደወል ጮኸ። ካለሁበት ቦታ ምንም መንቀሳቀስ አልፈለኩም ። ደወሉን የሚያቃጭለው ሰው ሲሰለቸው ይመለሳል ብዬ አሰብኩ። ነገር ግን ጥሪው እየበረታ ሄደ። ውስጤ በጥርጣሬ ታመሰ። < ማን ሊሆን ይችላል? > በማለት አሰብኩ። ነፍሴን ከስጋዬ ሊነጥላት ከተዘጋጀው ገመድ ውስጥ አንገቴን አወጣሁ። ገመዱን መልሼ አንገቴ ውስጥ በማጥለቅ እስትንፋሴ እንዲቋረጥ እንደማደርግለራሴ ቃል በመግባት በሩን ለመክፈት ሄድኩ። 👇👇👇👇👇👇👇 👉በሩን ስከፍት በዚያ ብርዳማ ወቅት በቀኝ እጁ አንድ መፅሃፍ የያዘ ልጅ ከበሬ ቆሟል። የፈገግታ ብርሃን ከሚረጭ ፊቱ አንዳች ነገር ሊለግሰኝ የመጣ ይመስላል። ከአንደበቱ የሚዘንቡት ቃላት ከልቤ ጓዳ ውስጥ በመክተም ተላወሱ። ሞትን ብቸኛ አማራጭ ያደረገው እኔነቴ ህይወትን በሚያለመልሙ ቃላት ፊት ተገትሯል። በእጁ የያዘውን መፅሃፍ እንዳነበው ሰጠኝ። ይህ አሁን በእጄ የያዝኩት “ጉዞወደ ጀነት” የሚሰኘውን መፅሃፍ በስጦታ መልክ አበረከተልኝ። መፅሃፉን ተቀብዬ በሬን ዘግቼ ወደ ውስጥ ገባሁ። አንገቴን ለተንጠለጠለው ገመድ ከመገበሬ በፊት ልጁ የሰጠኝን መፅሃፍ ለማንበብ ወሰንኩ። ውስጤ በአዲስ መንፈስ መራገብ ያዘ ። ተስፋ ከምንጩ እየተቀዳ እኔነቴ ውስጥ የሚጨመር ያክል ተሰማኝ። ማንበብ ያልጨረስኩትን መፅሃፍ ምልክት በማድረግ ገጠምኩት። ከጣሪያው ላይ የተንጠለጠለውን ገመድ ፈታሁ። ወንበሩን ከፊቴ ሰወርኩት። አሁን እንደ እኔ ደስተኛ የለም። ብቸኛውን እና ትክክለኛውን አምላኬን ተዋውቂያለሁ። ወደ እናንተ የመጣሁት ያ ልጅ ካበረከተልኝ መፅሃፍ የጀርባ ገፅ ላይ የዚህ ማዕከል አድራሻ ሰፍሯል። ፈጥኖ ደራሽ የሆነ ልጅ እጅግ አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ደረሰልኝ። ወደ ሞት ቀጠና ልታዘግም የነበረችው ነፍሴን ታደጋት። ከዘለዓለም ስቃይ አተረፈኝ። " በማለት በመስጂዱ ውስጥ ላሉት ታዳሚዎች ኢስላምን መቀበሏን አበሰረቻቸው። 👉መስጂዱ "አላሁ አክበር " በሚል የአማኞች ድምፅ ተንቀጠቀጠ። ሁሉም በደስታ ተዋጠ። ኢማሙ ልጁ ወደተቀመጠበት አቅጣጫ አመራ። ልጆቿን ከብርድ እንደምትከላከል ዶሮ ከእቅፉ ውስጥ አስገባው። ልጁን እንዳቀፈው ምዕመናኑ ፊት እንባውን ዘረገፈ። የሚደንቀው የመስጂዱ ኢማም የልጁ አባት ነበር። "አንብቦ ለሌላ ያካፈለ የአላህ እዝነትና በረከት በሱ ላይ ይሁን" እኛም በሰማነው የምንጠቀምበት አላህ ያድርገን አሚንንንንንንንንንንንንን አላሁመ አሚንንንንንንንንንንንንንንን ያረበል አለሚን ያረቢ ለሁላችንም 🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲 🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲🤲 @Razia_ni🦋 @heewan🦋
Show all...
✍የረመዳን ሌሊት! ~~ በጌታቸው የሚተማመኑ ሰዎች ስለሱ እንዴት እንደሚናገሩ ተመልከቱ! ➊ኛ ሷሊሕ እንዲህ ብለዋል:– ﴿إن ربي قريب مجيب﴾ "ጌታዬ በእርግጥ ቅርብ (ፀሎትን) ተቀባይ ነው!" [ሁድ: 61] ➋ኛ ሹዐይብ እንዲህ ብለዋል:– ﴿إن ربي رحيم ودود﴾ "ጌታዬ በእርግጥ አዛኝ ወዳድ ነው።" [ሁድ: 90] ➌ኛ ኑሕ እንዲህ ብለዋል:– ﴿إن ربي لغفور رحيم﴾ "ጌታ በእርግጥ መሃሪ አዛኝ ነው።" [ሁድ: 41] ➍ኛ ዩሱፍ እንዲህ ብለዋል:– ﴿إن ربي لطيف لما يشاء﴾ "ጌታዬ በእርግጥ ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው።" [ዩሱፍ: 100] ➎ኛ ኢብራሂም እንዲህ ብለዋል:– ﴿إن ربي لسميع الدعاء﴾ "ጌታዬ በእርግጥ ፀሎትን ሰሚ ነው፡፡" [ኢብራሂም: 39] ➏ኛ ሱለይማን እንዲህ ብለዋል:– ﴿فإن ربي غني كريم﴾ "ጌታዬ በርግጥም ሃብታም ቸር ነው።" [አንነምል: 40] ያ አላህ! ሁሌ ባንተ ከሚተማመኑት አድርገን። [ከዐብዱለጢፍ ኣሊ ሸይኽ የትዊተር ገፅ ተወስዶ የተተረጎመ] @muslimpp33 @muslimpp33 @muslimpp33
Show all...
💋Hani yee 🦋Cute habsha 🦋 🌸 Remla Remla 🌸 ☄CHANNEL☄ https://t.me/joinchat/AAAAAEZCX_wo9nCNJDBf9g
Show all...
🌸😍 yene zemen @ Join ma Chanel to ge💓In dis Channel u get 🛑✨Ŋāøľ€ pīç😎 🛑✨Quote❤ 🛑✨Music🎵 🛑✨Video🎬 🛑✨Entertianment 🛑✨Vine & prank🤣 🛑✨Books📖 🛑✨Dance & tiktok 🥳 🛑✨poem💬 🛑✨ All in one channel🛑✨ Comment&💁 https://t.me/joinchat/RkJf_Cj2cI0kMF_2
Show all...
😍 Remla Remla♥

🌸😍 yene zemen @ Join ma Chanel to ge💓In dis Channel u get 🛑✨Ŋāøľ€ pīç😎 🛑✨Quote❤ 🛑✨Music🎵 🛑✨Video🎬 🛑✨Entertianment 🛑✨Vine & prank🤣 🛑✨Books📖 🛑✨Dance & tiktok 🥳 🛑✨poem💬 🛑✨ All in one channel🛑✨ Comment&💁

ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ፦ 🔻"ዕውቀት የነብያቶች ውርስ ነው፤ ገንዘብ የንጉሶች ውርስ ነው: 🔻ዕውቀት ባለቤቱን ይጠብቃል፤ ገንዘብ በባለቤቱ ይጠበቃል: 🔻ዕውቀት ወጪ ሲደረግበት ይጨምራል፤ ገንዘብ ወጪ ሲደረግበት ይቀንሳል: 🔻ዕውቀት ያለው ሰው ሲሞት ዕውቀቱን ይከተለዋል፤ ገንዘብ ያለው ሲሞት ገንዘቡን ይተወዋል: 🔻ዕውቀት በገንዘብ ላይ ይፈርዳል፤ ገንዘብ በዕውቀት ላይ አይፈርድም: 🔻ገንዘብ ሙስሊምም ካፊርም፣ ሙዕሚንም ፋሲቅም ያገኘዋል፤ ጠቃሚ ዕውቀት ግን ሙዕሚን እንጂ አያገኘውም: 🔻ዕውቀት ያለው ሰው ንጉሶችም ተራ ሰዎችም ወደ እሱ ፈላጊ ናቸው፤ ገንዘብ ያለው ግን ድሆችና ችግረኞች እንጂ ወደ እሱ አይፈልጉም:: 📚مفتاح دار السعادة : (413/1) @muslimpp33 @muslimpp33 @muslimpp33
Show all...
አሞራው በሰማይ ላይ ነቢዩላህ ዳውድ በዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ሳለ አንዲት ሴት «ጌታህ ፍትሀዊ ነው ወይስ በዳይ?» የሚል ድንገተኛ ጥያቄን ሰነዘረች ለምን እንደዚህ እንዳለች ምክንያቷን ታብራራ ዘንድ ጠየቋት «አባታቸው የሞተባቸውን ሶስት የቲም ልጆችን አሳድጋለሁ ጉሮሯቸውን የምደፍነውም ጥጥ በመፍተልና በመሸጥ ከማገኘው ገንዘብ ነው። ዛሬ ግን ጥጤን ፈትዬ በጨርቅ ከረጢት ውስጥ አድርጌ ልሸጥ ወደ ሱቅ አመራሁ። በመንገዴ ላይ ሳለሁ አንድ አሞራ ከረጢቴን ይዞብኝ በረረ ለልጆቼ ዳቦ መግዣ አጣሁ በረሀብ እየተንገላቱ ነው ···· » ንግግሯን ሳትጨርስ በሩ ተንኳኳ። ፈቃድ ተሰጣቸውና ወደ ውስጥ ገቡ። አስር ነጋዴዎች ነበሩ። በእጃቸው 1000 ዲናር ይዘዋል ከመሐላቸው አንዱ መናገር ጀመረ «አንቱ የአላህ ነብይ ባህር ላይ እየተጓዝን ሳለ መርከባችን ተቀደደና መስመጥ ጀመረ። ሞታችንን በመጠባበቅ ላይ ሳለን አንድ አሞራ የተፈተለ ጥጥን የያዘ ቀይ የጨርቅ ከረጢት ከላይ ጣለልን። ቀዳዳውን በጨርቁ ደፈንን መርከባችንም ወደ ላይ ተንሳፈፈ። ከሞት ዳንን። አላህ ለዋለልን ውለታ ምስጋና ይሆን ዘንድ እያንዳንዳችን መቶ መቶ ዲናር ለመስጠት ቃል ገባን። ይሄው ገንዘባችን እርስዎ ዘንድ ላሉ ሚስኪኖች ሰደቃ ይስጡት » በማለት ብሩን እንዲቀበሏቸው እጃቸውን ዘረጉ። ነቢዩላህ ዳውድም ወደ ሴትዬዋ በመዞር 《ጌታሽ አንቺን ከድካም አሳርፎ በየብስና በባህር ይነግድልሻል አንቺ ግን በዳይ ትይዋለሽ በይ ገንዘቡን ተቀብለሽ ይዘሽ ሂጂ 》በማለት አዘዟት። ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያዳርሱ። ━─━────༺༻────━─━ @muslimpp33 @muslimpp33 ━─━────༺༻────━─━ Join👆👆👆
Show all...
ከአቢ-ሁረይረህ(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸው) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:– [ረመዷን በገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፋፈታሉ፤ የጀሀነም በሮች ይዘጋጋሉ፤ ሸይጧኖች(ዋና ዋናዎቹ) በሰንሰለት ይታሰራሉ።] 📚ቡኻሪ እና ሙስሊም @muslimpp33 @muslimpp33 @muslimpp33
Show all...
የረመዷንን ሌቦች ተጠንቀቁ አንደኛው ሌባ ፡- ቴሌቭዥን ፡ ለሥጋም ሆነ ለመንፈስ ከፍታ አጋዥ ካልሆኑ የረመዷን ሙሰልሰላቶችን እና አዘናጊ ድራማዎችን ተጠንቀቁ፤ የረመዷን ዉድ ጊዜያት ለዉድ ነገሮች መዋል አለባቸው፡፡ ሁለተኛው ሌባ ፡- ስልክ፡፡ ብዙ ማውራት ለብዙ ስህተት ያጋልጣል፣ ትርፍ ንግግር ወደ ሀሜትና ያልታሰቡ ወንጀሎች ይመራል፤ ለተሻለ ምንዳ በረመዷን በንግግር ጭምር ቁጥብ መሆን ያስፈልጋል፡፡ ሦስተኛ ሌባ ፡- ወጣ ገባ ማብዛት/መዞር፡፡ በረመዷን ከመስጊድ እና ከቤት የበለጠ ማረፊያ የለም፡፡ ወደ ከተማም ይሁን ወደ ገበያ ያለበቂ ምክንያት ወጣገባ ማብዛት ዐይንንም ሆነ ጆሮን ያልሆነ ነገር ይጥላል፡፡ ፆምን ይሰርቃል፤ ምንዳዉንም ያጓድላል፡፡  አራተኛ ሌባ ፡- ማምሸት፡ ያለምክንያት ማምሸት ኪሳራ እንጂ ትርፍ የለዉም፡፡ የረመዷን ምሽቶች ምርጥና ዉብ ናቸው፡፡ በቁርኣን፣ ዚክር እና በተለያዩ ዒባዳዎች መዋብ አለባቸው፡፡ አምስተኛ ፡- ኩሽና ፡፡ በተለይ ለሴቶች፡፡ ሙሉዉን ረመዷን ማዕድ ቤት የሚያሳልፉ ቁርኣንን፣ ሶላትና ዚክርን የረሱ ብዙ ናቸው፡፡ ረመዷን የፆም ወር ነው፡፡ ትልቁን ትኩረት ለሆድ መስጠት ዓላማዉን መሳት ነው የሚሆነው፡፡ ስድስተኛ ሌባ ፡- ስስት ፡፡ የረመዷን ዉስጥ ሶደቃ ምንዳው ትልቅ ነው፡፡ ስስት ግን ምንዳን ያስከለክላል ፤ አጅርን ያሳጣል፤ መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ ሰባተኛ ሌባ ፡- ሼል መፍታት፡፡ ሙእሚን ሁሌም ጠቃሚ በሆነ ሼል ላይ መገኘት አለበት፡፡ ያለ ምንም ምክንያት ጊዜን ማቃጠል ዕድሜን  áˆłá‹­áŒ á‰€áˆ™á‰ á‰ľ ማሳለፍ የኪሣራዎች ሁሉ ትልቁ ኪሣራ ነው፡፡ ስምንተኛ ሌባ ፡- ሶሻል ሚዲያ፡፡ ዛሬ ላይ የብዙዎቻችን ችግር ሆኗል፡፡ በቤትም ሆነ በመስጊድ ሳይቀር ትልቅ ትኩረት ሰጥተነው ጊዜያችንን እየጨረስንበት ነው፡፡ በዚህም ከዚክር፣ ከቁርኣን፣ ከዱዓ እንዳንጠቀም ሆነናል፡፡ እንጠንቀቅ፡፡     JOIN MA CHANNEL 👇👇 @muslimpp33 @muslimpp33 @muslimpp33
Show all...
✨"ከየት መጣህ ሳይሆን ወዴት ነው የምትሄደው የሚለው ነው ዋናው ጥያቄ"✨ 💛"የህይወት ፈተናን ተጋፈጠው፤ ካሸነፍክ ደስተኛ ትሆናለህ፤ ከተሸነፍክ ደግሞ ብልህ ትሆናለህ"💛 🔆"ብዙዎቻችን ህልሞቻችንን አላሳካንም ምክንያቱም ፍርሃታችንን ስለምንኖረው ነው"🔆 ✨"ብዙ ሽንፈቶችን እንቀምሳለን ነገር ግን መሸነፍ የለብንም"✨ ❤️ @Razia_ni @Razia_ni
Show all...
ለምርመራ የሚሰጥ ደም ፆም ያበላሻል? ~~~~~~~~~~~~~~~~~ ለህክምና ምርመራ ደም መስጠት ፆም አያበላሽም። የሸይኽ ኢብኑ ባዝንና የኢብኑ ዑሠይሚንን ፈትዋ ይመልከቱ። [መጅሙዑ ፈታዋ ኢብን ባነው: 15/274] [ፈታዋ አርካኒል ኢስላም፣ ኢብኑ ዑሠይሚን : 478] ┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓ 🦋🧕@heewan🧕🦋 🦋🧕@heewan🧕🦋 🦋🧕@heewan🧕🦋 ┗━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┛
Show all...